የኮማንድ ፖስቱ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

BBN News  | የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በበላይነት አስፈጽማለሁ የሚለው አካል እርምጃውን አጠናክሮ እደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ራሱን የአዋጁ አስፈጻሚ አድርጎ የሾመው የህወሓት የደህንነት ቡድን ወይም ኮማንድ ፖስቱ፣ አዋጁ ከወጣ ወዲህ ሀገሪቱ እየተረጋጋች እንደመጣች የገለጸ ሲሆን፣ ሀኖም ሀገሪቱ ተረጋግታለች ቢልም አዋጁን ለማንሳት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡


የመከላከያ ሚኒስትር እና የኮማንድ ፖስቱ ዋና ጸሐፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ‹‹አዋጁ ውጤታማ ስራ አከናውኗል፡፡›› ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጭምር ውግዘት እየወረደበት የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ጥፋት እያስከተለ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡


ለጋዜጠኞች፣ ለተቃውሞ ፖለቲካ አራማጆች፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ለሌሎችም የሀገሪቱ ዜጎች እስር እና ግድያ ምክንያት እየሆነ የሚገኘው አዋጁ፣ በቀጣይነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው በመንግስት በኩል እየተገለጸ ያለው፡፡ ‹‹ከአዋጁ በኋላ ለውጦች ቢኖሩም አሁንም አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የተቀናጀ ስራ መስራት ይገባል፡፡›› ሲሉ አቶ ሲራጅ በቀጣይነትም እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይነት እነማንን ማሰር እንዳለበት እየመከረ እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s