ሌላዋ የሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ ጀግና የአስቴር ስዩም የፍርድ ቤት ውሎ፥

በሽብርተኝነት ተከሳ ቃሊቲ የምትገኘው ወጣት አስቴር ስዩም ጥር 9 ቀን ልደታ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የመከላከያ ቃሏን በማቅረብ ዳኞቹን በአስደናቂ ሁኔታ እንደሞገተቻቸውና የችሎት ታዳሚው በከፍተኛ አድናቆት ሲመለከት እንደዋለ ተሰምቷል።

ተከሳሽ አስቴር ስዩም ባቀረበችው ሙግት የተበሳጩ ዳኞችም የተለመደውን ማስፈራሪያ ቃላቸውን ሰንዝረው፥ ውጤቱን ዓርብ በጥር 19 ይዘው ሊቀርቡ በቀጠሮ ችሎቱ ተበትኗል፥
ወጣቷ የፖለቲካ እስረኛ አስቴር ስዩም የአንድ ሕጻን ልጅ እናት ስትሆን በጎንደር የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር የነበረች፥ ከጎንደር ዩንቨርስቲ በኬምስትሪ ማስትሬት ዲግሪዋን እንደያዘች ስራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ እንደሄደች በወያኔ ወታደሮች ታፍና በሽብርተኝነት ክስ ቃሊቲ ተጥላ በስቃይ የምትገኝ የወያኔ/ኢሕአዴግ ዘረኛ አገዛዝ ሰለባ ነች።

አስቴር ስዩም በእስራት ላይ ሆና፥ እናቷ ልጄን እንዳሉ በቅርብ ቀን የሞቱባት፥ ጡት ጠብቶ ሳይጠግብ ድንገት እናቱን በወያኔ የተነጠቀው ህጻኑ ልጇ የትም ተጥሎ የሚሰቃይባት 3 እናትና ልጅ እንደተነፋፈቁ እስር ቤት ሆና ዓመታት በማስቆጠር ላይ የምትገኝ በሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ ተወላጅ ጀግና ወጣት ናት።

አሮጊት እናት የእስረኛ ሕጻን አሳዳጊ ሆነው፥ ልጄን እንዳሉ ህይወታቸው ዓለፈ፥ የወለደች እናት ከእስር ቤት ስቃይ ጋር፥ ወየው እናቴን፥ ወይኔ ልጄን እንዳለች ቃሊቲ ማሰቃያ ቤት በመከራ ትማቅቃለች፥ ከሁለት ዓንድ ያጣው ሕጻን የትም ተጣለ።

ግፈኛው የወያኔ ኢሕአዴግ ስርዓት በተለይም በጎንደር እናቶች፥ ወጣቶችና ሕጻናት ላይ የሚያደርሰው በደል እጅግ የከፋ መሆኑን በአስቴር ስዩም ቤተሰብ ላይ እያደረሰ ያለው ሶስቱን ትውልድ በታትኖ የማጥፋት ሴራ ቀላል ማስረጃ ነው።

ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s