የታላቁ የጨጎዴ ቅኔ ት/ቤት መቃጠልን በተመለከት ከጎዓት የተሰጠ መግለጫ

ከአንድ ሳምንት በፊት በታላቁ የጨጎዴ የቅኔ ት/ቤት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ በተመለከተ የጎዓት ጊዚያዊ ኮሚቴ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል። የጨጎዴ ሐና ቅኔ ጉባኤ ቤት በምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት በቋሪት ወረዳ ልዩ ስሙ ፈንገጣ በሚባል ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን በሀገራችን ውስጥ አሉ ከሚባሉ ጥቂት የሊቃውንት መፍለቂያ ት/ቤቶች አንዱ ነው። እንደ ጨጎዴ ያሉ ትውልድ የሚኮራባቸው ታሪካዊ የሀገር ሀብቶች በተለያዬ ምክንያት ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው መሆኑ ጎዓትን እጅግ ያሳስበዋል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እየተጣራ ያለ ጉዳይ መሆኑ ቢዘገብም ጉዳዩ በአፋጣኝ ተጣርቶ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ጎዓት ለሚመለከተው አካል ሁሉ ጥሪ ያቀርባል። የሀገርና የትውልድ ታሪካዊ ሀብት የሆነውንና ለእምነት፣ ለባህልና ለታሪክ ሽግግር ትልቅ አስተዋጽኦ ያለውን ይህን የሊቃውንት መፍለቂያ የቅኔ ት/ቤት በእሳት ተቃጥሎ እንዲወድም ያደረገው የተቀነባበረ ሴራና ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑ ከተረጋገጠ ለወንጀሉ ትክክለኛ ፍርድ የማግኘት ጉዳይ የጎጃም ሕዝብና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ምዕመናን ብቻ ሳይሆን የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ መሆኑን ጎዓት አጥብቆ ያምናል። በመሆኑም በመልሶ ግንባታው ላይም ሁሉም አካል ተረባርቦ በመማሪያና መጠለያ ዕጦት አደጋ ላይ የወደቁትን ከ600 በላይ የጉባኤ ቤቱ ተማሪዎች መርዳትና ጉባኤ ቤቱን ወደ ቀደመ ሕልውናው ለመመለስ እንዲቻል ጥሪ እናቀርባለን።

መልሶ ግንባታው በተሳካ ሁኔታ ይካሄድ ዘንድ ጎዓት አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ የወሰነ ሲሆን ስለ ደረሰው ጉዳትና ስለ መልሶ ግንባታው ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት ጉዳዩ ከመመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ ይገኛል። በመላው ዓለም ያላችሁ የጎዓት አባላትና ደጋፊዎች አሁን የጀመራችሁትን እርዳታ የማድረግ ስራ እንድትቀጥሉ እያሳሰብን ሌሎች ስለሚደረጉ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝርዝር ሁኔታዎች የጎዓት ጊዚያው ኮሚቴ ወደ ፊት ለአባላትና ደጋፊዎቹ የሚያሳውቅ ይሆናል።

የጎጃም ዓለም አቀፍ ትብብር

ዋሽንግተን ዲሲ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s