አዲሱ የወያኔ ኢንተሃሞይ ሓረካት (መስቀሉ አየለ)

የሩሲያው ዲዮቶዝቭስኪ እንዲህ ብሎ ነበር። “If there is no God, Nothing is forbidden” ፤ሰው ክቡር ሆኖ ተፈጥሮ መለኮታዊነት ገንዘብ ያደረገ ፍጡር የሆነውን ያህል በተሰጠው ብሩህ አይምሮ የፈለገውን ያህል ወደ አውሬነት የተጠጋ ፍጥረት ለመሆንም አቅምም ነጻ ፈቃድም እንዳለው ለማሳየት ነበር። በዚህም አለምን በፍቅር፣ በቅድስና እንዲሁም በእውቀት ያከበሩ ድንቅ ሰዎች ኖረው የማለፋቸውን ያህል የሰውን ልጅ እንደ ከብት ወደ ስጋ መፍጫ ውስጥ ወስደው የፈጩ አላውያን ነገስታትንም አይተናል።ዲዮቶዝቭስኪ እንዳለው የሰው ልጅ ወደ ዚህ እኩይ ምግባር እንዳይወርድ መጠበቂያው ውሃ ልኩ (የሞራል ባውንደሪው) ፈሪሃ እግዚአብሔር መሆኑን ሲያጠይቅ ነበር።

ከዲቶቭስኪ ቦሃላ ጥቂት አስርተ ዓመታት ቆይቶ ብቅ ያለው የመጨረሻው ፈላስፋ ፍረደሪክ ኒቸ ይህንኑ ሃሳብ “ዘ ጎድስ ዴድ ቲዎሎጅ” በተባለው ስራው ላይ እንዳሰፈረው እግዚ አብሔርን “ገደልነው”አለ; (በኛ ልብ ውስጥ ስፍራ የለውም ክደነዋል፤ ህይወትም አልሆነንም ለማለት ነው)፣ ደሙም በጃችን ላይ ነው፤ ይሕንንም ደም የሚያነጻ በቂ ውሃ ስለመኖሩን አላውቅም ሲል ይዘረዝረዋል። በዘመኑ የተከሰተውን አዲስ የኢንላትመንት አስተሳሰብ ተከትሎ ኢአማኒ መሆን ፋሽን የነበረበት ግዜ ላይ መድረሳችንን ለማጠየቅ ነበር።

ሁለቱ የ19ኛው ምእተ አመት ታላላቅ ሰዎች ይህን በተናገሩ ሃያ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ኮሙኒዝም በራሽያ ቦታ መያዝ ጀመረና የምስራቁንም ክፍል መዋጥ ጀመረ። ይህን የአስተሳሰብ ለውጥ ተከትሎ ከቱርክ የአርሜንያ ጀኖሳይድ- ሁለቱ የአለም ጦርነቶች- የስታሊን ቀይሽብር-ሳውዝ ኢስት ኤስዥያ- ቻይናና የኮምቦዲያን አብዮት ብናሰላው ወደ ሁለት መቶ አምሳ ሚሊዮን በላይ ሰው ነበር ያለቀው። የክህደት እና የ አይዲዮሎጅ ደመዎዙ መሆኑ ነው።

ደደቢት ላይ የተፈለፈለው እንቁላል ከሁለት ነገር የተጸነሰ ነው። አንዱ ክህደት ሲሆን ሁለተኛው ዘርን መሰረት ያደረገ ጥላቻ ነው። ዛሬም ድረስ ከአርባ አመት ቦሃላ በዚህ ነገር ላይ ቅንጣት ታህል የአስተሳሰብ ለውጥ አላደረገም። ይኽን እኩይ ተፈጥሮውን ምርጫ ዘጠና ሰባት ደርሶ በድንገት የተገለጠበት ኩነት ግርታ የፈጠረ አዲስ ክስተት እንደነበር ዛሬም ድረስ አንስተውም። ኢንተርሃሞይ ነበር ያለው። ያን ተከትሎ ተከታዮቹን በይፋ መውጋት የጀመረው የዘረኝነት የጥላቻና የክህደት መርፌ በሚያስደነግጥ ፍጥነት እያደገ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ አቅሙን እያጠናከረ መሄዱን ሁላችን ባይናችን የታዘብነው ነገር ነው። አንድ የጽጌ ረዳ አበባ ባልተቀነጠሰበት ነገር ግን ሶስት ሚሊዮን ሰው የወጣበት የመስቀል አደባባን ታሪክ ባየንበት አይናችን ይሕ የእፉኝቶች ስብስብ የተረዳበት ማእዘን ግን ሌላ ነበር።
አሁን ደግሞ ከመቸውም ግዜ በላይ ወደ ፍጻሜው መጀመሪያ መድረሱን ደመ ነፍሱ እንደነገረችው ከሚወጡት ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል። ፍጹም ሰላማዊ በነበረው የምርጫ ዘጠና ሰባት የብርቱካን አብዮት ስለ ኢንተርሃሞይ የዘመረ ቡድን ዛሬ አገሪቱ ውስጥ ዙሪያውን ሰፎ የሚታየውና እንደ ኢርታሌ እሳተ ጋሞራ የሚንተከተከው ትኩሳት ፈንድቶ ሊወጣ አንድ ሃሙስ የቀረ በሚመስልበት በዚህ ሰአት እንዲህ አይነቱን ቀስቃሽና መርዘኛ ድራማ ሰርቶ አይለቅም ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አንድ የስርዓቱ ሰለባ እና ይኽ ስርዓት በምንም አይነት መስዋዕትነት መሄድ አለበት ብሎ ከልቡ የሚያምን ታጋይ እንዲህ አይነት ነገር ሰርቶ በአደባባይ ቢለቅ ለትግራዩ ገዥ ጉጅሌ የእድሜ ማራዘሚያ መርፌ እንደሚሰጠው ያውቃልና። ኢትዮጵያውያን በእንዲህ አይነቱ እኩይ ምግባር ሳይደናገጡና አይናቸውንም ከተከሉበት ሳይነቅሉ ወደ ነጻነት አደባባይ የሚያደርጉትን ጉዞ አጠናክረው መቀጠል የምርጫቸው ጉዳይ አይሆንም ።

https://www.facebook.com/plugins/video.php?href=https%3A%2F%2Fwww.facebook.com%2FEthiopian.DJ%2Fvideos%2F1266298863477890%2F&show_text=0&width=600

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s