የታላቁ የጨጎዴ ቅኔ ት/ቤት መቃጠልን በተመለከት ከጎዓት የተሰጠ መግለጫ

ከአንድ ሳምንት በፊት በታላቁ የጨጎዴ የቅኔ ት/ቤት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ በተመለከተ የጎዓት ጊዚያዊ ኮሚቴ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል። የጨጎዴ ሐና ቅኔ ጉባኤ ቤት በምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት በቋሪት ወረዳ ልዩ ስሙ ፈንገጣ በሚባል ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን በሀገራችን ውስጥ አሉ ከሚባሉ ጥቂት የሊቃውንት መፍለቂያ ት/ቤቶች አንዱ ነው። እንደ ጨጎዴ ያሉ ትውልድ የሚኮራባቸው ታሪካዊ የሀገር ሀብቶች በተለያዬ ምክንያት ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው መሆኑ ጎዓትን እጅግ ያሳስበዋል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እየተጣራ ያለ ጉዳይ መሆኑ ቢዘገብም ጉዳዩ በአፋጣኝ ተጣርቶ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ጎዓት ለሚመለከተው አካል ሁሉ ጥሪ ያቀርባል። የሀገርና የትውልድ ታሪካዊ ሀብት የሆነውንና ለእምነት፣ ለባህልና ለታሪክ ሽግግር ትልቅ አስተዋጽኦ ያለውን ይህን የሊቃውንት መፍለቂያ የቅኔ ት/ቤት በእሳት ተቃጥሎ እንዲወድም ያደረገው የተቀነባበረ ሴራና ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑ ከተረጋገጠ ለወንጀሉ ትክክለኛ ፍርድ የማግኘት ጉዳይ የጎጃም ሕዝብና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ምዕመናን ብቻ ሳይሆን የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ መሆኑን ጎዓት አጥብቆ ያምናል። በመሆኑም በመልሶ ግንባታው ላይም ሁሉም አካል ተረባርቦ በመማሪያና መጠለያ ዕጦት አደጋ ላይ የወደቁትን ከ600 በላይ የጉባኤ ቤቱ ተማሪዎች መርዳትና ጉባኤ ቤቱን ወደ ቀደመ ሕልውናው ለመመለስ እንዲቻል ጥሪ እናቀርባለን።

መልሶ ግንባታው በተሳካ ሁኔታ ይካሄድ ዘንድ ጎዓት አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ የወሰነ ሲሆን ስለ ደረሰው ጉዳትና ስለ መልሶ ግንባታው ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት ጉዳዩ ከመመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ ይገኛል። በመላው ዓለም ያላችሁ የጎዓት አባላትና ደጋፊዎች አሁን የጀመራችሁትን እርዳታ የማድረግ ስራ እንድትቀጥሉ እያሳሰብን ሌሎች ስለሚደረጉ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝርዝር ሁኔታዎች የጎዓት ጊዚያው ኮሚቴ ወደ ፊት ለአባላትና ደጋፊዎቹ የሚያሳውቅ ይሆናል።

የጎጃም ዓለም አቀፍ ትብብር

ዋሽንግተን ዲሲ

ይድረስ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው: ለሆድ ብሎ ገሎ ሊያልፍ ለሚያደባ ጠላት ከመንበርክክ አብሮ ከሚኖረው ህሊና ጥያቄ መንፃትና አኩሪ ህዝብን ይዞ ስምን ተክሎ ማለፍ

ለሆድ ብሎ ገሎ ሊያልፍ ለሚያደባ ጠላት ከመንበርክክ አብሮ ከሚኖረው ህሊና ጥያቄ መንፃትና አኩሪ ህዝብን ይዞ ስምን ተክሎ ማለፍ

ይድረስ ለውድ ወንድማችን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው (አንዱ ባለአደራ የአማራ ልጅ)

ወያኔና ግበረ በላዎቹ መገነዣ ልጣቸው ተርሶ መቀበሪያ ጉድጓዳቸው ተምሶ የግብዓተ መሬቱን ስዓት እየጠበቁ እንዳሉ ከእኛ በጓሮ በር ከምንሰልለውና ከምንሰማው ይልቅ አንት በቀጥታ ድንገት አንዳትሰማው ቢፈለግ እንኳ በመላው ጎንደር ምናልባትም አማራ ህዝብ ያለህን ተቀባይነትና የወያኔ መወደቅ አይቀሬ መሆኑን በሚያወቁ አብረውህ በበሉ ሚስጠሩ እንደሚደርስህ እርግጠኞች ነን። አቶ ገዱ አስኪ ቆም ብለህ አስብ? ከአንተ ጀምሮ ዞን ወረዳ መስተዳድሮችህ ስማቸውን አስተካክለው በማይፀፉ የትግሬ አፋኝ ወታደር አዛዞች እዝ ስር ሆነው በቁም አስረኝነት የ10 ሳንቲም ግምት ያለው ትዕዛዝ የማትስጡ አስተዳደራችሁ ፈርሶ ግዑዛን ሰለመሆናችሁና አጣብቂኝ ውስጥ ሰለመሆናችሁ ነጋሪ አትፈልጉም ብለን እንገምታለን።

አንዱ ኢትዮጵያዊ ጅግና ባንድ ወቅት ሁሉም ያመኑዋቸው የማይጠረጥሩዋቸው ሁሉ ከዱዋቸው ከክሃዲዎቹ በእጃቸው የገቡትን ከሳር ጎጆ በማስገባት ሲቃጠሉ ለማየት ከተቀመጡበት ከፍ ካለ ቦታ ሆነው ከሃዲዎቹን ወደ ሳር ጎጆ እንዲያስገባ የመደቡትን ኃላፊ (አሁን አንት በቆምክበት ቦታ የቆመውን ማለት ነው) ሞላ? ብለው ይጠይቁታል እረ አንድ ይቀረዋል በሎ ይመልስላቸዋል ከአንተስ ምን እጠብቃለሁ በል አንተም ግባ ብለው አብሮ ተቃጠለ ይባላል። የአንተም ዕጣ ፈንታ ይህ እንደሆነ ጠንቅቀህ ታውቃለህ “አይጋ ፎረምን ያዩአል”…. ልዩነቱ ይህ ትልቅ ሰው በሀገር ፍቅር ነደው አሁንም ከሰው ያልተሳካላቸውን ድንገት በእሳቱ ተፈትኖ ከአመዱ ሰው ባገኝ አያሉ እያለቀሱ ማድረጋቸው። የአንተዎቹ አለቆች ደግም ለግል ሆዳቸው እንዝረፍ እንደፈለግን እንሁን ሀገር ወገን ገደል ይግባ የሚሉ የሀገርም የወገን ለአገልጋዮቻቸው ለእናንተም ፍቅር የሌላቸው ሆዳሞች መሆናቸው ነው።

አቶ ገዱ ይህ ከእኛ ወገኖችህ የመጀመሪያም የመጨረሻም ምክራችን ነው። እባክህ 37 ሚሊዮን ህዝብ ይዘህ ለ6 ሚሊንም ቢሆን ግጥሚያው አትፍራ? ብትሞት የምትሞተው አንድ ሞት ነው ሞትህ ግን ለልጆችህ አስከ ትውልዳችው ስምህን ከምደር በላይ ዘላዓለማዊ ክብርና ሞገስ ትተህላቸው ከማለፍ ውጭ የምታጣው ነገር የለም። ምክንያቱም እንደ ወያኔ ውሳኔ በእኛ ደጀንነት እንጅ የመኖር ፈቃድህ የእርድ ቀንህን አየጠበቅ እንደሆነ እርገጠኛ ነህ። ይህንም በፍፁም መሰሪነታቸው አንት ልትጠቀምባቸው ትችላለህ ተብለው የሚሰጉ የልዩ ኃይል የማረሚያ ቤቱንና ሌሎች ጀግኖችህን አያሰሩ ቀነዘሉ ተቆርጦ እንደሚደርቅ ዛፍ አጅ አግርህን ክተክተው እየጣሉሀ እንደሁ እንዴት አትረዳም?
በትንሽ መንደሮች በቁጠር አርበኞች ከመላው ኢትዮጵያ የመጣውን ጦር እንዴት እያስተናገድን አየመለስነው እንደሆነ ከምታየው ሰርቶ ማሳያ ብትረዳና እኛ የምንልህን በመቀበል አቋም ይዘህ አምቢ ለአማራ… እምቢ ለኢትዮጰያ… አሻፈረኝ ህዝቤን አትንኩ ተከተለኝ ወገን በማለት ለመሪነት ብትዘጋጅ የምትሳሳላቸውን ቤተሰቦችህን ጨምሮ በአንት ላይ አይደልም ሞት ዝንብ እንደማናሳርፍ መላ ኢትዮጵንም በስዓታት በመድረስ ነፃ እንደምናወጣት ቅንጣት ባትጠራጠርና ስም ብናስር። አትፍራ…. መቸም ሟች ነህ ልዩነቱ በክብር ከመኖር ተስፋ ጋር የክብር ሞት ለመሞት ወይም የተወሰነልህን የማይቀር የወያኔን የውርደት ሞት ለመሞት መዘጋጀት ናቸው።

አንት ባታደርገውም ወያኔ በሚያገኛት ትንሽ ቀን ምናልባት ወራት ወደ እኛ ጎንደሬ አርበኞች የማይነካ አሳት አንድም ትግሬ ሳይጨምሩ አየላኩ እንደማገዶ እንጨት የሚያልቁት ኢትዮጵያዊ ልጆቻችን ሞት አንጅ ወያኔንማ አያክርምን አናከርመውም…።

አሳዛኙ ግን ለእኛ አንት በአድሜህ በትምህርት በባህልም ከእነሱ የተሻለክ ነህ ብለን ስለምንገምት እነዚህ እንጀራ ጠግበው ያልበሉ ሊተኩሱት ቀርቶ ሊሽከሙት የማይችሉትን ጠመንጃ አሸክሞ በርሃብ ለጥይት የሚማግዳቸው ተተኪ ንፁሃን ኢትዮጵያዊ ተባበሪ መሆንህና ወንጀሉን ዝም ብለህ ማየትህ አጅግ እጅግ ያሳዝናል አንተስ ሽክሙን እንዴት ቻልከው?

ስለዚህ ምከረው ምከረው አምቢ ካላ መካራ ይምከረው በሚባለው የአባቶች አባባል ባለብን የደም የስጋ የማንነት ትስስር እራስህን እንደትፈትሽ የከበረ ምክራችን እንለግሳለን መንገዱንም እንዲያሳይህ እንፀልይልሃለን።

ድል ለኢትዮጵያዊያን
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላዓለም ትኑር
መላው ጎንደር አማራ ኢትዮጵያዊያን ንቅናቄ
እባካችሁ ይህ መልዕክት የሚደርሳችሁ ሁሉ በተቻለ መጠን መልዕክቱ ለአቶ ገዱ አንዲደርስ አድርጉልን አናመስግናለን።

 1  148  149

የህወሃት ድራማ ተዋናኞች ሆይ!  እጃችሁን ከወልቃይት ላይ አንሱ !

የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ በፋሽስቱና በተስፋፊው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድን የተፈጸመበትን የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት እኩይ ወንጀል ለመመከትና ለመቀልበስ እንዲሁም በመጥፋት ላይ የሚገኘውን ዘሩን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ሲያደርግ የኖረውን ህዝባዊ ተጋድሎ በወልቃይት ህዝብ አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አማካኝነት የካቲት 24, 2008 ዓ.ም ጎንደር ከተማ “ላንድ ማርክ” አዳራሽ ውስጥ በተጠራ ታሪካዊና ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ለጎንደር ህዝብ የሃገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች ትግሉን በይፋ ማስረከቡ ይታወቃል።

ይልቁንም ይህን ታሪካዊ የትግል ቅብብሎሽ ከሃምሌ 5, 2008 ዓ.ም ጀምሮ እዛው ጎንደር ከተማ ላይ በተከፈለው ታላቅ ህዝባዊ መስዋዕትነት የጎንደር ህዝብ ስለወልቃይት የገባውን ቃልኪዳን በደሙ አፅንቶና አትሞት ያለፈ ሲሆን። ይህ ጎንደር ላይ በንፁሃን ወገኖቻችን ደም የታሰረው ታሪካዊ ውል፤ በቆራጥ የአማራ ህዝብ ልጆች ውድ የህይዎት መስዋዕትነት የፀና፣ መላውን ኢትዮጵያዊ በደም ካሳ ያስተሳሰረና፣ ወጣቱን ትውልድ ከወልቃይት ህዝብ ትግል ጋር በማይጠፋ ቃልኪዳን ያቆራኘ የህዝባችን ለዘመናት ያደረገው ትግል ታላቁ ድልና ስኬት ሆኖ አግኝተነዋል።

የወልቃይት ህዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ማለት የጎንደር ህዝብ “ድንበራችን ተከዜ ነው!” እያለ ደሙን እንደ ጅረት ያፈሰሰለት፣ የጎጃም ወጣት “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!” እያለ ምድሪቱን በደሙ ያጨቀየለት ፣ የኦሮሞ ኤጆሌ “ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ይፈታ!” በማለት ከነህይወቱ በቢሾፍቱ ገደል በግፍ የተወረወረለት፣ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በአንድነት “የንጹሃን ወገኖቻችን ደም በግፍ ማፍሰስ ይቁም!” “ወልቃይት አማራ ነው!” እያሉ በዓለም ታላላቅ አደባባዮች ቀን ከሌሊት፣ ክረምት ከበጋ የተሰለፉለትና የጮሁለት፣ በአጠቃላይ ህዝባችን በአንድነትና በህብረት ሆኖ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የታገለለትና መስዋዕትነት የከፈለለት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ተቀዳሚ አጀንዳ፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ግንባር ቀደም ጥያቄ ነው!

ይህን ህዝባዊ ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ህዝብ በአደባባይ በጠየቀው መሰረት መመልስ የነገውን ህዝባዊ ቁጣና ቅጣት አሻግሮ መመልከትና ከታሪክ መማር የሚችል የማንኛውም አካል ተቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበት ልሳነ ግፉዓን ድርጅት በፅኑ ያምናል። ነገር ግን ከጅምሩ የኢትዮጵያና የህዝቧ ጠላት ሆኖ የተነሳው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድን ይህን ሃገርንና ትውልድን ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ያሰለፈና ያስቆጣ ህዝባዊ ጥያቄ በሰላማዊና አግባብነት ባለው ህጋዊ መንገድ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በተቃራኒውና በተለመደው ፋሽስታዊ የሃይልና የጭካኔ መንገድ የህዝብ መሪዎችንና ተወካዮችን በጀምላ በማሰር፣ በተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎች በማሰቃየትና፣ በማሳደድ ለማንበርከክ መሞከርና በአላማቸው እስከ መጨረሻው የፀኑትንና በመራር ስቃይ ውስጥ ሆነው እንኳ ያልተንበረከኩትን ትንታግ የህዝብ ልጆች በግፍ በመግደልና  አስከሬናቸውን በገበያ መካከል በመጎተት ህዝብን ለማሸበር መጣርና እስከ የማይቀረው ውድቀት ድረስ አጥፍቶ በመጥፋት ለመግዛት መሞከርን ነው።

ከላይ በአጭሩ እንደተገለፀው የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ ከህዝብ የተቀበለውን ታላቅ ተልዕኮና የትውልድ አደራ ለጎንደር፣ ለአማራና፣ ብሎም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እጅግ በተሳካ፣ ታሪካዊ ደረጃውንና፣ ሂድቱን በጠበቀ ሁኔታ ህዝባዊ ትግሉን አስረክቧልና ምንም አይነት ኢፍትሃዊ የጭካኔና የአፈና መንገድ በህዝባችን ላይ ቢተገበር ትግሉን ሊያጎለብተው እንጂ ሊቀለብሰውም ሆነ ሊያዳፍነው እንደማይችል የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ታሪክ ህያው ምስክር ነው።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያስተላልፈውን የቁጣ መልዕክት ዛሬም ድረስ በሃይል እጨፈልቃለሁ የሚለው ፋሽስቱና አጥፍቶ ጠፊው የህወሃት እኩይ ቡድን እንደለመደው ሁሉ ዛሬም ህዝብን ወደ ባሰ ቁጣና ተቃውሞ የሚያስገባ ሌላ ተልካሻ ሴራ ውስጥ ተወሽቆ ሲንቦጫረቅ እንደሚውል በተጨባጭ መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል። ይኸውም ፦

1ኛ. ሃሰተኛ የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ ማቋቋም

ህወሃት እንደ ለመደው በአንድ በኩል እውነተኛ የህዝብ ወኪሎችንና መሪዎችን በግፍ በማሰር እያሰቃየና በሽብር ወንጀል በመክሰስ በህግ ሽፋን ሞትና እድሜ ልክ እስራት ለማስፈረድ የተበላበትን የ“አኬልዳማ ክፍል …” ድራማ ላይ እየተወነ፤  በሌላ በኩል ለጊዚያዊ ጥቅም ባደሩና በተለያዩ ህወሃታዊ የማንበርከኪያ ወጥመዶች ተጠልፈው ለህወሃት ርካሽ የጥፋት አላማ በተንበረከኩ ደካሞችና ሆድ አደሮች ተጠቅሞ ሃሰተኛ የኮሚቴ አባላትና መሪዎች እየጠፈጠፈ መክረሙንና ህዝብን እንደ ህፃን ልጅ አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ እያለ ሲጃጃል እነሆ 25 ዓመታት እንደዋዛ አለፉ።

ትላንት በሌሎች እንዳየነው ሁሉ ዛሬ ደግሞ ተረኛ ሁኖ የተገኘው “የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ” አቅራቢ ኮሚቴ ነው። ምንም እንኳ የወልቃይት ህዝብ እንደ አንድ ልብ መካሪ፤ እንደ አንድ አንደበት ተናጋሪ በመሆን ከ 50 ሺ በላይ የህዝብ ፊርማ በማሰባሰብ “ትግሬ ሁን የተባልኩትና ወደ ትግራይ ክልል የተካለልኩት ያለአግባብ በሃይል ነው” “የአማራዊ ብሔርተኝነት ማንነቴ ይከበርልኝ!” “ድንበሬ ተከዜ ነው!” በማለት ጥያቄውንና ውክልናውን ለመረጣቸው ወኪሎቹ ከነ ሙሉ ፊርማው በመስጠት በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ምላሹ ግድያና እስራት ስለሆነ ዛሬም እምነቱንና ቃሉን ጠብቆ በፅናት ከወኪሎቹ ጋር በመቆም መራራውንና አስከፊውን ትግል እያደረገ ይገኛል።

ይህ ህዝባዊ ፅናትና ቁርጠኝነት ያርበተበተው ፋሽስቱ ህወሃት ዛሬም እንደ ትላንቱ ታማኝ ተላላኪዎቹንና አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ ተንበርካኪዎችን በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በማፈላለግ ለማሰባሰብና ሃሰተኛ የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ኮሚቴ ለማቋቋም እየዳከረ እንደሚገኝ በተጨባጭ ደርሰንበታል።

ለዚህም ርካሽ ተግባር ተባባሪ ሆነው የተገኙት የሃሰተኛው የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ኮሚቴ አባላት ሁለት አበይት ተልዕኮ የተዘጋጀላቸው ሲሆን እርሱም ፦

  1. በወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ መነሻነት በሃገሪቱ ለተከሰተው አለመረጋጋትና ለደረሰው ሃገራዊ ኪሳራና ለጠፋው የሰው ህይወት ሁሉ በወልቃይት ህዝብ ስም መንግስትን ይቅርታ መጠየቅና፣

 

  1. በወልቃይት ህዝብ ስም “የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄን” እንደ አዲስ ለትግራይ ክልል መንግስት አስተዳደር ማቅረብና የትግራይ ክልል በሚሰጠው “የራስ ገዝ” አስተዳደር ተስማምቶ ዳግም ወልቃይትን በህጋዊነት ሽፋን ከነዋሪው 90% ለሚሆነው የትግሬ ሰፋሪ ወልቃይትን በሃስተኛው ኮሚቴ ፊርማ ማስረከብን መዳረሻው ያደረገ እኩይ እቅድ ነው።

2ኛ. በእስር ላይ በሚገኘው የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አባላት ላይ የሃሰት ምስክር አቅርቦ ማስመስከርና ማስፈረድ።

የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ ሰላማዊና ህጋዊ አባላትንና የህዝብ መሪዎችን በግፍ አስሮ ማሰቃየትና በሃሰተኛው የካንጋሮ ፍርድ ቤት ውስጥ በሚሰራ የተለመደ ተራ ድራማ በሞትና በእድሜ ልክ እስራት ለመቅጣት መሞከር ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ “ጥፋተኛ ነኝ በጥልቅ እታደሳለሁና ጊዜ ስጡኝ” ያስለመነ፣ 100% ተመርጫለሁ ባለ በአመቱ 100% ካቢኔውን በአዲስ ለመተካትና፣ ሃገራችን በታሪኳ አይታው በማታውቀው ሁኔታ ከ6 ወር በላይ ለሆነና መቋጫው በማይታወቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንድትወድቅ ያስገደደን ህዝባዊ ጥያቄና ቁጣ ላይ በመንግስት ደረጃ መሳለቅና በቀጣይ ከሚመጣው ህዝባዊ ቁጣ መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖር አድርጎ በእራስ ላይና ቆሜለታለሁ በሚሉት ህዝብ ላይ አርማጌዶን እንደማወጅ ይቆጠራል።

በአንፃሩ ደግሞ በ200 ሺ ብር የገንዘብ ክፍያና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ተደልለው በወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት ላይ ለመመስከር በህወሃት የተዘጋጁት

1ኛ. አቶ መኮንን ጋረድ

2ኛ. አቶ ሰጠኝ ለማ ገሪማ

3ኛ. አቶ ተገን መርሻ

4ኛ. አቶ ፀጋይ ሙሉ

መሆናቸውን በተጨባጭ መረጃ አረጋግጠናል። ሌሎች በድርድር ላይ ያሉትንም እንደ ሚወስዱት አቋም ተከታትለን በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን።

ይልቁንስ ቀልዱን ለጊዜው እዚህ ላይ አቁሙትና በህግ ሽፋን በግፍ ታፍነውና በየማሰቃያ ቤቱ እየተሰቃዩ የሚገኙ የህዝብ ልጆችን ማለትም፦

ሀ) አዲስ አበባ ላይ የታፈኑ                                    ለ) ጎንደር ላይ የታፈኑ

1ኛ. አቶ ነጋ ባንቲሁን                                       1ኛ. አቶ አታላይ ዛፌ

2ኛ. አቶ አዲሱ ሰረበ                                       2ኛ. አቶ አለነ ሻማ

3ኛ. አቶ ጌታቸው አደመ

4ኛ. አቶ መብራቱ ጌታሁን

5ኛ. ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ

6ኛ. ወጣት ንግስት ይርጋ

7ኛ. አቶ ክንድሺ ሃጎስ …..ወዘተ………

ሐ) በወልቃይትና አካባቢው ታፍነው ሁመራ በእስር ላይ የሚገኙ

1ኛ. አቶ አሊጋዝ አየለ            7ኛ. አቶ ሰጠኝ ድረስ

2ኛ. አቶ ሞላ ሃይሉ      8ኛ. አቶ ባየው ካሰኝ

3ኛ. አቶ ሰለሞን ግዛቴ            9ኛ. አቶ ሰጠኝ አረሩ

4ኛ. አቶ አሻግረው ገዛሃኝ      10ኛ. አቶ መሐመድ ያሲን

5ኛ. አቶ ግዛቸው ድረስ            11ኛ. አቶ መኮነን ደስታ

6ኛ. አቶ ጎይቶም አማረ            12ኛ. አቶ ሊላይ ብርሃኔ….ወዘተ……

እንዲሁም በዚህ ዝርዝር ውስጥ ልናካትታቸው ያልቻልናቸውን የወልቃይት ተወላጆች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና ወደ ቤተሰቦቻቸውና ህዝባቸው እንዲቀላቀሉ እናሳስባለን።

በመጨረሻም ልሳነ ግፉዓን ድርጅት በአንክሮ ማሳሰብና ማስገንዘብ የሚፈልገው ነገር ቢኖር የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት በወልቃይት ህዝብ ላይ የፈፀመው ግፍና ያደረሰው መከራ የንጹሃንን መገፋት በሚያየውና በእውነተኛው ዳኛና ፈራጅ በሆነው በሃያሉ በእግዚአብሄር ፊት ፅዋው ሞልቶ ነበርና ህዝባችን ለዘመናት ዘሩን ከጥፋት ለማዳን ያደረገው ፍትሃዊ ትግል በሃምሌ 5, 2008 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ላይ በተደረገው ታላቅ መስዋዕትነት ምክንያት በተቀጣጠለው የአማራ አናብስት ቁጣና ተጋድሎ የሚገባውን ታሪካዊ ክብሩንና ቦታውን ሊይዝ ችሏል። ስለሆነም ከዚያች ታሪካዊ እለት ጀምሮ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ከወልቃይት ህዝብ እጅ ሊወጣ ችሏል። የወልቃይት ጥያቄ ከኮሚቴዎችና ከፍትህ ተቋማት እጅ ላይመልስ አፍትልኳል። ይልቁንም የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ የአደባባይ ጥያቄና የቀጣዩ ትውልድ የትግል አጀንዳ ወደ መሆን ተሸጋግሯል። እዚህ ላይ ከአዲስ አበባ የማስፋፋት ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የኦሮሞ ወጣቶች ያነሱትን የአደባባይ ጥያቄና ተቃውሞ እንዲሁም ህወሃት መራሹ መንግስት ለጥያቄው በአደባባይ የሰጠውን ምላሽ ልብ ይሏል።

ስለዚህ ለህዝባችን ጥያቄ መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው ብሎ ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ብፅኑ ያምናል። ይኋውም የተለመደውን ተራ ቀልድና ድራማ በአስቸኳይ አቁሞ ህዝብ ከኮሚቴ ጥያቄ ወደ አደባባይ ትግል ያሸጋገረውን የአደባባይ ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአደባባይ ፍትህ መመለስ ብቻ ነው።

ጀግናውና ብርቱው ህዝባችን ሆይ! ለዘመናት ልጆችህን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ገብረህ የተጓዝክበት ትግል ዛሬ የጠላትህን የጣረሞት ጩሃት ለመስማት አብቅቶሃልና ደስ ሊልህ ይገባል። ነገር ግን ይህ ወደ ማይቀርለት ታሪካዊ ሞቱ በውርደት እየተሸኘ ያለው ፍሽስት ቡድን አጫፋሪና ፍርፋሪ ለቃሚ የነበሩት ጥቂት ግለሰቦች ሞቱ የተረጋገጠውን ህወሃት ለማዳን የመጨረሻ እድላቸውን ለመሞከር በሚል እላይ ታች መንቀዥቀዣቸውን ተያይዘውታል። ህወሃት ግን ከቶ ላይመለስ ሞቷልና የባንዳዎችን ልፈፋና ድለላ ሰምተህ ከድሉ ማዕድ ፊትህን እንዳትመልስ አደራ እንላለን! ይልቁንም አንድነትህን አጠናክረህና ሃያሉ ክንድህን አስተባብረህ የጠላትህ ግብአተ ፍፃሜ ላይ ተረባረብ!

ለህዝባችን ሃይል ፅናት የሆነውን ሃያሉን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን!

ድል የህዝብ ነው!

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

ጥር 17, 2009 ዓ.ም

 

ሌላዋ የሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ ጀግና የአስቴር ስዩም የፍርድ ቤት ውሎ፥

በሽብርተኝነት ተከሳ ቃሊቲ የምትገኘው ወጣት አስቴር ስዩም ጥር 9 ቀን ልደታ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የመከላከያ ቃሏን በማቅረብ ዳኞቹን በአስደናቂ ሁኔታ እንደሞገተቻቸውና የችሎት ታዳሚው በከፍተኛ አድናቆት ሲመለከት እንደዋለ ተሰምቷል።

ተከሳሽ አስቴር ስዩም ባቀረበችው ሙግት የተበሳጩ ዳኞችም የተለመደውን ማስፈራሪያ ቃላቸውን ሰንዝረው፥ ውጤቱን ዓርብ በጥር 19 ይዘው ሊቀርቡ በቀጠሮ ችሎቱ ተበትኗል፥
ወጣቷ የፖለቲካ እስረኛ አስቴር ስዩም የአንድ ሕጻን ልጅ እናት ስትሆን በጎንደር የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር የነበረች፥ ከጎንደር ዩንቨርስቲ በኬምስትሪ ማስትሬት ዲግሪዋን እንደያዘች ስራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ እንደሄደች በወያኔ ወታደሮች ታፍና በሽብርተኝነት ክስ ቃሊቲ ተጥላ በስቃይ የምትገኝ የወያኔ/ኢሕአዴግ ዘረኛ አገዛዝ ሰለባ ነች።

አስቴር ስዩም በእስራት ላይ ሆና፥ እናቷ ልጄን እንዳሉ በቅርብ ቀን የሞቱባት፥ ጡት ጠብቶ ሳይጠግብ ድንገት እናቱን በወያኔ የተነጠቀው ህጻኑ ልጇ የትም ተጥሎ የሚሰቃይባት 3 እናትና ልጅ እንደተነፋፈቁ እስር ቤት ሆና ዓመታት በማስቆጠር ላይ የምትገኝ በሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ ተወላጅ ጀግና ወጣት ናት።

አሮጊት እናት የእስረኛ ሕጻን አሳዳጊ ሆነው፥ ልጄን እንዳሉ ህይወታቸው ዓለፈ፥ የወለደች እናት ከእስር ቤት ስቃይ ጋር፥ ወየው እናቴን፥ ወይኔ ልጄን እንዳለች ቃሊቲ ማሰቃያ ቤት በመከራ ትማቅቃለች፥ ከሁለት ዓንድ ያጣው ሕጻን የትም ተጣለ።

ግፈኛው የወያኔ ኢሕአዴግ ስርዓት በተለይም በጎንደር እናቶች፥ ወጣቶችና ሕጻናት ላይ የሚያደርሰው በደል እጅግ የከፋ መሆኑን በአስቴር ስዩም ቤተሰብ ላይ እያደረሰ ያለው ሶስቱን ትውልድ በታትኖ የማጥፋት ሴራ ቀላል ማስረጃ ነው።

ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

የወያኔ ብሄራዊ መረጃ ተደማጭንት አላቸው የሚባሉ ግለስቦች እንዲታፈኑ በሚስጥር ማሳሰቡ ተሰማ

በብሄር ብሄረሰብ አስተዳደር ክልል ውስጥ የተዋቅሩ የብሄራዊ መረጃ ቅርንጫፍ አስተዳደር ባለስልጣን አካሎች እነርስም ተጠሪነታቸው ለክልል የደህንነት ብሄራዊ መርጃ ክንፍ የሆኑ የየወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዋች በአካባቢያቸው የሚኖሩ የተቃራኒ ፓርቲ አባላቶችንና አመራሮችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ በማጥናት እንዲያቀርቡ ከብሄራዊ መረጃ የህዝብ ግንኙንት እና መምሪያ አምራር ባልስልጣናት ቀጭን ትእዛዝ ወርዶላቸዋል::

ብሄርዊ መረጃው ያወረደው ትእዝዝ በተለየ መልኩ ሕዝብን በማሳመን ተደማጭንት አላቸው የሚባሉ ግለስቦች እንዲታፈኑ የሚያዝ ከመሆኑ ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ፖርቲዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ 2000 ሺ ይሚጠጉ ግልስቦችን ስም ዝርዝር አዳብሎ ከጥብቅ አጽንኦት ጋር ያስተላለፈ ሲሆን ድንገትኝና አደገኛ ሐገርዊ ጥቃት በእነዚግለስቦች እንደተቀናበረ. አውስቷል::


የህወሀቱ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት ከተራ የአካባቢና የወረዳ ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ጋር በብርቱ ያወራረደው ትእዛዝ አርበኞች ግንቦት 7 ለ 460 አባልት ህቡሕ አደራጆች ከፍተኛ የጥቅም በጀት ያፈሰሰ ነው ከማለቱ ባሻገር 900 የታጠቁና የተበተኑ ግዳጅ ተወጪዎች መሰማራታቸውን ፍንጭ ሰጥቷል::


ከህወሀት የወታደራዊ ደህንነት ኮማንድ ፖስት እውቅና ውጭ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ብሄራዊ መረጃ ስውር ደህንነቶች በብዛት እየተገደሉበት ከፍተኛ ችግር ላይ የወደቀው የመረጃው ክንፍ እጅግ በወረደ ሁናቴ ከአካባቢ የጸጥታ ዘርፍ ሐላፊዋች ጋር ለመስራት እንደተገደደ ምንጮቻችን አጣምረው ገልፀዋል::ጉድሽ ወያኔ
ethiopia-curfew

 

በነገራችን ላይ ‘ውይይቱ’ የት ደረሰ? – ክንፉ አሰፋ

 

የሙስናውን የመረጃ እጦት ኩምክና ሰምተን ስቀን ሳንጨርስ ሰሞኑን ደግሞ የውይይት ፉገራ አመጡ። ልክ እንደቀበሌ ስብሰባ ተቃዋሚዎችን በአዳራሽ ውስጥ አጉረው ሲያበቁ እነሱ ከመድረክ ሆነው ይቀልዱባቸዋል።  የNBC ውን፤ የዴቭድ ሌተርማን ‘ሌት ናይት ሾው” (late night show) የሚመስል ነገር በቴሌቭዥን ለቀውብን ነበር።  ሁለቱ ባለስልጣኖች፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ መድረክ ላይ ጉብ በለዋል። በአነስተኛና በጥቃቅን የተደራጁ 21 የፓርቲ መሪዎች ደግሞ እንደ ቲያትር ተመልካች አዳራሹ ውስጥ ተሰይመዋል።  እነዚያ ከላይ፣ እነዚህ ከታች ተቀምጠዋል።  እነዚያ ይናገራሉ፣ እነዚህ ደግሞ ይሰማሉ።…ሌላ ምን አማራጭ ሊኖራቸው?

ውይይት ብለውታል። ሌላው አይደለም። አቀማመጣቸው ብቻ የውይይቱን አቅም እና ያይል ያሳብቃል።  በሙስናው የመረጃ እጦትት ኩምክና ስቀን ሳናበቃ  ነው ይህንን ፉገራ የለቀቁት።   ሲት ኮም ክፍል ሁለት።

አይጋ ፎረም ላይ ስለሁኔታው የጸፉት “ባለሙያ” የሃገራችንችግሮች በውይይት ብቻ እንደሚፈቱ አስምረውበታል። “ይህንን ማን አጣው?” ብሎ ሚጠይቃቸው አልተገኘም እንጂ። በድርድር ሰላምን ለማምጣት መልካም ፈቃዱ ካለ፤ መጀመሪያ በእስር ላይ ያሉትን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በመፍታት ነበር የሚጀመረው። ከቶውንም የህሊና እስረኞች ለመደራደርያ መቅረብ አልነበረባቸውም። አሁን ግን የምናየው የተገላቢጦሹን ነው። ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ እንዳስቀመጡት “መጀመርያ የፖለቲካ እስረኞችን ፍቱ!” የምትለው ቅድመ ሁኔታ ለገዥው ፓርቲ የሰጥቶ-መቀበል መደራደርያ ሆና ቀርባለች። ይህ የተቃዋሚዎች የመደራደር አቅም ምን ያህል እንደሆነ የሚለካው አንዱ መስፈርያ ነው።

ድርድር የምትለዋ ርዕስ እነሱ በችግር በተወጠሩ ቁጥር የሚመዟት አንደኛዋ ካርድ ለመሆንዋ ያለፉ ተመክሮዎች ምስክሮች ናቸው። አለም አቀፍ ጫና ሲበዛና የህዝብ ልብ ሲሸፍት ይመዙዋትና አዘናግተው ሲጨርሱ መልሰው እኪሳቸው ይመልሷታል።  እንግሊዞቹ “talks the talk but doesn’t walk the walk.” እንደሚሉት ነው። ወሬውን ያወሩታል –  ስራውን አይሰሩትም። በዚህ መንገድ ከሰባት ግዜ በላይ በህዝብ እና በተቃዋሚዎች ላይ ቀልደዋል።

ድርድር ወይንም ውይይት አንድ ነገር ነው። በድርድሩ ቢቻል የበላይነትን አልያም እኩል ስፍራ መያዝ ሌላ ነገር።  በክብ ጠረጴዛ የመቀመጥ እድል ሳይኖራቸው መወያየት ከመሞከር ይልቅ አለማድረጉ ይመረጣል። ጉልበተኛው የጫወታውን ህግ በሚወስንበት ጫወታ መሳተፍ ከማጅራት መች እጅ ጥምዘዛ የተለየ አይሆንም።

አንዳንዶች ተገቢ የሆነ ጥያቄ ያነሳሉ። “የተቃዋሚዎች ጡንቻ ከገዥው ፓርቲ የጠነከረ ባለመሆኑ የሚሰጣቸውን መቀበል ግድ ይላቸዋል።” ይላሉ። ይህ እይታ ትክክል ሊሆን ይችላል።  በዚህ መንገድ መሄዱ ግን ፍጹም ስህተትና ሕዝብን መካድ ነው የሚሆነው።

የገዥው ፓርቲ ጸብ ከህዝብ ጋር ነው። ሕዝብ በጅምላ ይገደላል፣ ሕዝብ በፈረቃ ይታሰራል፣ የሕዝብ ሃብት ይዘረፋል። በዚህ ሁኔታ – ከሕዝብ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ ለረጅም መዝለቅ ደግሞ አይቻልም። የውይይቱ አጀንዳ የህዝብ ጥይቄ ላይ የሚነሳ ሲሆን ለተቃዋሚዎች የሞራል ብቻ ሳይሆን የሃይልም የበላይነት ይሰጣቸዋል። እዚህ ላይ ተቃዋሚ ስል  የተገዙትን ወይንም የተቃውሞ አራራ ያላቸውን እንዳልሆነ ግልጽ ይሁን። እርግጥ ነው።  ደፋር እና ትክክለኛ የምንላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በእስር ቤት አልያም በስደት ላይ ናቸው።

የቴሌቭዥን ጋዜጠኛው ታዲያ አፉን ሞልቶ “የፓርቲዎች ውይይት” እየተካሄደ እንደሆነ በዜና አወጀ። ይህን ውይይት ልማቱ ካመጣቸው አዳዲስ ፍላጎቶች ጋር በማያያዝ ለመተንተን ግን አልደፈረም።

በአቶ ይልቃል ጌትነት የሚመራው የሰማያዊ ፓርቲ በዚህ ኢሕአዴግ በጠራው የፓርቲዎች “ውይይት” እንዲቀመጥ የተፈቀደለት እስከ ሻይ እረፍት ድረስ ብቻ ነበር። የሰማያዊ ፓርቲ ባህርይ እስከ ሻይ እረፍት ድረስ ተገምግሞ ሲያበቃ፣ ፓርቲው ጽንፈኛ እና ጸረ-ሰላም በመሆኑ ከምድቡ ተሰርዟል። ሌሎች “ነግ በኔ” ብለው መባነን የነበረባቸው በዚህ ግዜ ነበር። እነ አስመላሽ ወልደሥላሴ የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው በውይይት ብቻ ነው ብለው ሳይጨርሱ ተሳታፊውን ማባረር ሲጀምሩ ጉዳዩ እዚያው ያቆማል።

በፖለቲካ ኩምክና የሚታወቀው የእንግሊዙ ሳሻ ቦራት የተወነበት “The Dictator” የሚለው ፊልም ታወሰኝ። የዋዲያ ሪፐብሊክ መሪ የሆነው አድሚራል ጀነራል አላዲን የሩጫ ውድድር አዘጋጅቶ ሲያበቃ ተሳታፊዎችንም ራሱ መረጠ።  ዳኛው ራሱ ጀነራል አላዲን ነው። ጀነራል አላዲን ተወዳዳሪም ነው።  ሩጫውን የማስጀመርያ ሽጉጡን አንስቶ ወደሰማይ ተኮሰ። ሩጫ ተጀመረ።  ከዚያም ተወዳዳሪዎቹን  በሙሉ እግር-እግራቸውን እያለ ጥሎ በውድድሩ አንደኝነቱን አበሰረ።

በ”ስልጣን ወይም ሞት!” መፈክር የሚሄደው ይህ ድርጅት ያዘጋጀው መድረክ ከጅምሩ የሚሸት ነገር አለው። በቅንነት እና በሙሉ ልብ የሚደረጉ ውይይቶች ከአነሳሳቸው ይታወቃል። “ከአያያዝ ይቀደዳል፣ከአነጋገር ይፈረዳል” እንዲሉ፣ ይህ በግማሽ ልብ የተጀመረ መድረክ ለሃገር ሰላም ታስቦ እንዳልነበር ግልጽ ነው። ለውይይቱ የተጠሩት “ሰላማዊ መንገድ የመረጡ” ተቃዋሚዎች ብቻ ናቸው ተብሏል። ጉድለቱ የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው።

አንዱን ትክክለኛ ልጅ፣ ሌላውን ደግሞ የእንጀራ ልጅ ብሎ የሚመድበው ማን ነው?  አንዱን ጠርቶ እንነጋገር እያለ፣ ሌላውን ደግሞ አንተ “ጽንፈኛ” መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ ከሚል አካል ሰላም ይመጣል ብሎ ማሰብ ሞኝመት ይሆናል። ህወሃት ለውይይት ሲጠራ የራሱ መለኪያ አውጥቶ ለመሆኑ ከአጠራሩ ሂደት እና ከተጋበዙት እድምተኞች ለመረዳት አያዳግትም።  በውይይቱ የበላይነትን ይዘው ለመደራደር መስፈርቱን የሚያሟሉትን ከጠራ በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደፈረደ ይቆጠራል።

እሳት ከሌለ ጭስ አይታይምና ይህ ሾው ያለ ነገር፣ ያለ ግዜውም አልመጣም። የሰሜኑ ችግር እጅግ እየባሰ መጥቷል። ከወደ ምዕራብም ችግር አለ። የአልባሽር ፍቅር ከደቡብ ሱዳን እያላተማቸው ነው። ደቡብ ሱዳን አሁን ያመረረች ይመስላል።  ይህ ደግሞ ለአማጽያን ከኤርትራ የተሻለ አማራጭ ሊሆንላቸው ነው።  ሰሞኑን ግጭቱ ተካርሮ ዲፕሎማት እስከማባረር ተደረሷል። የካይሮ እጅ ኖርበትም አልኖረበት፣ የጁባው ዲፕሎማሲ የስርዓቱን ግባዓተ-ቀብር ማፋጠኑ በግልጽ የሚታይ ነገር ነው።

ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ የከተተበት ምክንያት ገዥው ፓርቲ የሚታመን ስርዓት ባለመሆኑ ብቻ ነው። ለበርካታ ግዜ ህዝብን እና ተቃዋሚዎችን በሃሰት አዘናግቷል።  ከመተማመን በፊት ውይይት ሊኖር አይችልም። ይህ ደግሞ የሚሆነው የሰማዕታት ቤተሰቦች ሲካሱ  እስረኞች ሲፈቱ እና ሁሉም ፓርቲዎች ሲጋበዙ ነው። ያለበለዝያ ጠቀሜታው ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ ይሆናል።

ታጋባዥ ተቃዋሚዎቹ ለጥቂት ሰዓታት ከገዥው ፓርቲ ጋር ከተመካከሩ እና በባለስልጣናቱ ከተመከሩ በኋላ እረፍት እንዲወስዱ ተደርገዋል የሚል ዜና ተለቅቋል። ፓርቲዎቹ ከ15 ቀናት እረፍት በኋላ  እንደሚመለሱ አይጋ ፎረም ላይ አነበብኩ። ሳባቲካን እረፍት መሆኑ ነው። ለሰዓታት ውሎ የ15 ቀን እረፍት ከተሰጣቸው፣ ለቀናት ቢወያዩ ደግሞ የአመት እረፍት የማግኘት እድል ይኖራቸዋል። የዚህ አይነት ውይይት ያልተለመደና እንግዳ ነገር ቢሆንም በገዥው ፓርቲ በኩል ለሚሰሩ ሸፍጦች ግዜ መግዣነት የታሰበም ይመስላል።

 

የድርድሩ ቀልድ ግን የተበላበት ካርታ ስለሆነ የሚደረደረው ምክንያት ሁሉ ውሃ አያነሳም።

የአወዛጋቢው ት.እ.ም.ት (EFFORT) ምሥጢሮች በከፊል | ሊነበብ የሚገባው ጥብቅ መረጃ

 

በኦማን ኡሊያህ፣ ለአዲስስታንዳርድ የተጻፈ (ትርጉም)

ሁሉም አምባገነኖች የኢኮኖሚ ምዝበራ እና የበላይነታቸውን የሚያረጋግጡበት የቢዝነስ ዓይነት ወይ በግለሰቦች ሥም አሊያም በድርጅት ጭምብል ይኖራቸዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ፣ ምንም እንኳ ምዕራባዊ ወዳጆቿን ድህነትን በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እየተዋጋች እንደሆነና ዴሞክራሲዋን እያሻሻለች እንደሆነ ማሳመን ብትችልም፣ በጣም ድሃ እና ዝግ ሆነው ሀብትና ሥልጣን በጥቂት ሰዎች እጅ ከተወሰነባቸው አገሮች አንዷ መሆኗ አልቀረም፡፡ ከሁሉም በላይ የሆነው የገዢው ፓርቲ ልኂቃን ቡድን አንድ ሕዝብን መርጦ (ትግራይን) እወክላለሁ ማለቱ ደግሞ ከሌሎች አምባገነኖች ይለየዋል፡፡ በምላሹም ከሌሎች ክልሎች በተለየ ቡድኑ በትግራይ የበለጠ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ 

ይኸው የልኂቃን ስብስብ ብዙ ቢሊዮን ዶላሮችን የሚያንቀሳቅስ የቢዝነስ ድርጅቶች ሰንሰለት አለው፡፡ ት.እ.ም.ት ይባላል፡፡ ት.እ.ም.ት (ትካል እግሪ ምትካል ትግራይ ወይም በእንግሊዝኛ ሥሙ ኤፈርት) በጦርነቱ ወቅት የተጎዳችውን ትግራይ መልሶ ለማቋቋም የተመሠረተ ኢንዶውመንት ነው፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ሕወሓት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለተወዳዳሪ ሲነግሥ፣ ትእምት ደግሞ ትግራይን መልሶ በማቋቋም ሥም ትልቅ የቢዝነስ ተቋም ለመሆን በቅቷል፡፡ 

ትእምት ምንድን ነው? 

ላይ ላዩን ሲታይ ትእምት በኢንዱስትሪ፣ ባንኪንግ እና ኢንሹራንስ፣ ኢምፖርት ኤክስፖርት፣ ሚዲያ፣ ኮንስትራክሽን፣ ግብርና እና ማዕድን ማውጣት የመሰሰሉትን ሥራ የሚሠሩ ቢዝነሶችን ያቀፈ ተራ ዣንጥላ ነው፡፡

በ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መነሻ ካፒታል ሥራውን የጀመረው ትእምት፣ አሁን ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ሲያካብት ለ47,000 ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

የትእምት ኩባንያዎች መጀመሪያ የተመዘገቡት በሕወሓት ኃላፊዎች ሥም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እየተባሉ ነበር፡፡ በኋላ ግን የኩባንያዎቹ ባለቤቶች ድርሻቸውን ለግሰዋል ተብሎ በ1954ቱ የፍትሐብሔር ሕግ መሠረት ‹ኢንዶውመንት› ተብለው ድጋሚ ተመዘገቡ፡፡ ሆኖም፣ አሁንም የሕወሓት ሰዎች ዋና ሥራ አስኪያጆች ሆነው እያስተዳደሩት ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹን ለማበረታታትም በሚል ትንንሽ ድርሻ እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

‘የመጀመሪያው ኩነኔ’: ሕወሓት ሀብቱን አንዴት አጠራቀመው? 

የትእምት ኦፊሴላዊ መግለጫ፣ የትእምት ቢዝነሶች የተመሠረቱት ሕወሓት በትግል ወቅት ያከማቸውን ሀብት ተጠቀሞ እንደሆነ ይናገራል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2008፣ የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ አረጋዊ በርኸ፣ አምስተርዳም ለሚገኘው ቨርጀ ዩንቨርስቲ በሠራው የዶክተራል ዲግሪ ጥናቱ፣ የሕወሓት የፖለቲካ ታሪክን ሲተርክ፣ የመጀመሪያው የሕወሓት ስኬታማ ዘመቻ ‹ዘመቻ አክሱም› እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ከተማዋ የነበራት አንድ ፖሊስ ጣቢያ እና አንድ ባንክ ሲሆን፣ ሕወሓቶች ከፖሊስ ጣቢያው እስረኞችን ካስፈቱ እና መሣሪያ ከዘረፉ በኋላ፣ ወደአክሱም ባንክ ሔደው የገንዘብ ዘረፋ አድርገዋል፡፡ እንደ አረጋዊ፣ በዝርፊያው 175,000 ብር (በወቅቱ ግምት 84,000 ዶላር) ዘርፈዋል፡፡

ባንኮችን በመዝረፍ የተጀመረው የሕወሓት ሀብት የማካበት ጉዞ ቀጥሎ እጅግ አወዛጋቢ የነበረውን የእርዳታ ገንዘብ ለድርጅት ጥቅም ማዋል ላይ እንደደረሰ አረጋዊ በርኸ ይነግረናል፡፡ ሕወሓት፣ ትግል ላይ እያለ ማኅበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት) የተባለውን የእርዳታ ድርጅት እንደ ክንፍ አቋቁሞ ነበር፡፡ አረጋዊ እንደጻፈው፣ “በጁን 1985፣ ማረት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት በሚል አገኘ፡፡ ነገር ግን መለስ ዜናዊ ገንዘቡን እንደሚከተለው መደበው፤ 50% ለማሌሊት ምሥረታ፣ 45% ለሕወሓት ሥራ ማስኬጃ፣ እና ቀሪው 5% ደግሞ ለድርቅ ተጎጂዎች፡፡” እርግጥ ነው፣ እንደምንገምተው፣ የሕወሓት ኃላፊዎች ይህንን ክደዋል፡፡

አሁን አረናን ያቋቋመው የቀድሞው የሕወሓት ኃላፊ ገብሩ አሥራት ለምሳሌ፣ ‹ሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ› ባለው መጽሐፉ ላይ፣ ‹ትግል ላይ እያለን ብዙ ገንዘብ በእርዳታ እናገኝ ስለነበር፣ ገንዘቡን ለተለያዩ ተግባራት ማከፋፈል የሕወሓት ውሳኔ ነበር› በማለት የእርዳታ ገንዘብ ለፓርቲ ሥራ ውሏል ብሎ ለማለት ፈፅሞ አይቻልም ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ በሕግ የሚያጠያይቁ ሀብት የማካበቻ መንገዶች፣ ፓርቲው የመንግሥት ሥልጣን ከያዘ በኋላም መቀጠሉን የሚናገሩ አሉ፡፡ የቀድሞው የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ፣ አዲስ ባሳተመው ሁለተኛ መጽሐፉ ‹የመለስ ልቃቂት› ላይ በትእምት አመሠራረት እና አቋቋም ላይ ብዙ አወዛጋቢ ነጥቦችን አንስቷል፡፡

በኤርምያስ 565 ገጽ መጽሐፍ ውስጥ ምዕራፍ ስድስት፣ ትእምት የገንዘብ ምንጩ ምን እንደሆነ እና እንዴት የአገሪቷን ገንዘብ ወደካዝናው እንዳዛወረ ይነግረናል፡፡ ኤርምያስ በ1986 በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ የተፈረመ ደብዳቤ ቅጂ አያይዟል፡፡ ደብዳቤው ሕወሓት በትግል ወቅት መድኃኒት ለሕዝቡ ያከፋፈልኩበት ወጪዬ ነው በሚል ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዓመት በጀት ላይ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ (የወቅቱ ጠቅላላ በጀት 67 በመቶ) ለሕወሓት ገቢ እንዲሆን ይጠይቃል፡፡ በዚህ መንገድ ወደሕወሓት ካዝና ገቢ የተደረገው ገንዘብ 17 ሚሊዮን ብር ይደርሳል፡፡ ኤርምያስ መድኃኒቱ ቀድሞውኑም ከፋርማሲ ተዘርፎ ለሕመምተኞች የተከፋፈለ መሆኑን አብሮ ያስታውሳል፡፡

ቀጣይ ኩነኔዎች እና አወዛጋቢ ሥራዎች 

የትእምት ኩባንያዎች ከግል ኩባንያነት ወደኢንዶውመንትነት መተላለፋቸውን ከላይ አንስተናል፡፡ ኢንዶውመንት ሆነው ድጋሚ ሲመዘገቡ ባለቤቶቻቸው ሀብታቸውን ለግሰዋል ተብሎ ነው የሚታሰበው፡፡ ይህም የሕዝብ ገንዘብ አልተጠቀሙም የሚለውን ሽፋን ለመስጠት የተደረገ ይመስላል፡፡ አሁን፣ ኢንዶውመንቱ ትርፉ ለግለሰቦች አይከፋፈልም በሚለው ሕግ ቢተዳደርም ለጥቂት ግለሰቦች የመክበሪያ ዕድል ሆኖላቸዋል፡፡

በ1996 በቀድሞው የሕወሓት ታጋይ የተመሠረተው የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ ትእምት ከሕዝብ ባንክ የተበደረውን እና የተሰረዘለትን ገንዘብ አወዛጋቢ ጉዳይ እየተከታተለ ይፋ አድርጓል፡፡ (የእነዚህ እትሞች ቅጂ በአዲሱ የኤርምያስ ለገሠ መጽሐፍ መዝጊያ ላይ በአባሪነት ተያይዘዋል፡፡)

እነዚህ ተከታታይ እትሞች እንዳስነበቡን፣ ትእምት 1.7 ቢሊዮን ብር ከመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይበደራል፡፡ ብድሩ ከነወለዱ 1.8 ቢሊዮን ብር ይደርሳል፡፡ መጀመሪያ የንግድ ባንክ ኃላፊዎች ለትእምት ያበደርነው ገንዘብ የለም ብለው ካዱ፡፡ ነገር ግን ብድሩን ወደ ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማዘዋወራቸው ተደረሰበት፡፡ በመጨረሻም፣ ልማት ባንክ ብድሩን መሰብሰብ አልቻልኩም በሚል የዕዳ ስረዛ አደረገ፡፡ ኤርምያስ የትእምት ድርጅቶች መጀመሪያውንም ገንዘቡን የተበደሩት ያለምንም ማስያዥያ ነው ብሎ ያምናል፡፡ በቀጣዩ ዓመት፣ ልማት ባንክ ራሱ የ3.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ሪፖርት ተደርጓል፡፡ ያልተመለሰው የትእምት ብድር ብቸኛው ምክንያት ባይሆንም ለኪሳራው አንዱ ምክንያት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

ሌላው አወዛጋቢ ጉዳይ ትእምት የቢዝነስ ሥራውን የሚያካሔድበት መንገድ ነው፡፡ ኃላፊዎቹ እንደሚሉት ለሕግ ያላቸው ታዛዥነት እና ጉቦ ለመክፈል ፈቃደኛ አለመሆናቸው ከሌሎች ጋር ዕኩል መወዳደር እስኪያቅታቸው ድረስ ለሥራቸው እንቅፋት ሆኗል፡፡ እነርሱ ይህን ይበሉ እንጂ፣ የትእምት ኩባንያዎች በጥቅሉ በመንግሥት ሠራተኞች ልዩ እንክብካቤ ነው የሚደረግላቸው፡፡ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን፣ እምብዛም ባልተለመደ ሁኔታ ታኅሣሥ 3 ቀን 2005 በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዋለው ችሎት የተላለፈ ብይን ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ከትእምት አንዱ የሆነው እና በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራው ሜጋ የመዝናኛ ማዕከል ለቀደሙት 8 ዓመታት ሥራውን በማጭበርበር መንገድ እያካሔደ እንደነበር እና ገቢውን በማሳነስ እና ወጪውን አብዝቶ ሪፖርት በማድረግ ለመንግሥት የሚገባውን ግብር ሳይከፍል ቀርቷል ሲል በይኗል፡፡

ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ምሥጢሮች ግን አደባባይ የሚበቁት በባለድርሻዎች መካከል ግጭት ከተነሳ ብቻ ነው፡፡ በሜጋ ጉዳይ የአመራሩ አካል የነበሩት የአዜብ መስፍን እና የእቑባይ በርኸ ፀብ ምሥጢሩ እንዲወጣ ረድቷል፡፡

አሁንም ግን፣ ትእምት ምንድን ነው?

በዊኪሊክስ ሰነዶች ይፋ ከወጡ በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ደብዳቤዎች መካከል፣ ከቀድሞው የሕወሓት ታጋይ አቶ ስዬ አብርሃ ጋር ያደረጉት ንግግር ይገኝበታል፡፡ አቶ ስዬ ትእምት የተቋቋመበትን ምክንያት ሲያስረዳ “የአካባቢውን ሀብት ተጠቅመው ትርፍ ሊያመጡ የሚችሉ ኩባንያዎችን አጥንቶ በማቋቋም ለትግራይ የሥራ ዕድል መፍጠር ነው፡፡” ብሎ ነበር፡፡ በዚህ ረገድ፣ ትእምት፣ ምንም እንኳን ጥሬ እቃውን እና ገበያውን ከትግራይ ውጪ ባሉ የኢትዮጵያ ክልሎችም የሚያገኝ ቢሆንም፣ በአብዛኛው (ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም) የሚቀጥረው ግን የትግራይ ተወላጆችን ነው፡፡

በመርሕ ደረጃ፣ ትርፉም ትግራይን መልሶ ማቋቋም አለበት፡፡ ነገር ግን ብዙ የትግራይ ተወላጆች ‹ኢንዶውመንቱ› ጥቂት የሕወሓት ልኂቃንን ለማበልፀግ ውሏል ይላሉ፡፡ የቀድሞ የትግራይ ክልል የዐሥር ዓመት ፕሬዚደንት እና የሕወሓት ታጋይ የነበሩት አቶ ገብሩ አሥራት ከላይ በጠቀስነው መጽሐፋቸው ላይ እንደተናገሩት፣ ትእምት በሕወሓት ኃላፊዎች እየተበዘበዘ ነው፡፡ አቶ ገብሩ እንዲያውም የትእምት ሀብት ተሰፍሮ በአክሲዮንም ቢሆን ለእያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ የሚከፋፈልበት መንገድ እንዲኖር እስከመጠቆም ደርሷል፡፡

‹ሌሎቹስ› ምን አላቸው?

አንድ የማያጠራጥር ነገር አለ፡፡ እስከ 1983 በተደረገው የ17 ዓመቱ ጦርነት ወቅት ሌሎቹም ክልሎች ጉልህ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በወቅቱ የአገሪቱ በጀት ዋና ወጪ ለወታደራዊ አለግለግሎት ነበር የሚውለው፤ ስለሆነም ሌሎቹም ክልሎች ‹ኢንዶውመንቶች› ያስፈልጓቸው ነበር፡፡

ይህንኑ በመረዳት ይመስላል፣ ሕወሓት፣ ለሌሎች እንዶውመንቶች መነሻ ካፒታል ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት፣ በኦሮሚያ ዲንሾ የነበረውና አሁን ቱምሳ የተባለው በኦሕዴድ አመራሮች እንዲመራ ሆኖ ተቋቁሟል፤ በአማራ ጥረት የተባለው በብአዴን እንዲመራ ሆኖ ተቋቁሟል፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ደግሞ ዎንዶ በደኢሕዴን አመራሮች እንዲመራ ሆኖ ተቋቁሟል፡፡

ስዬ አብርሃ “ሕወሓት የሀብቱን ጥቂት ክፍል ለነዚህ ለሦስቱ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ሰጥቷል” ሲል ተናግሯል፡፡ ይሁን እንጂ፣ እነዚህ ሦስቱ አንድላይ የሚያስተዳድሯቸው ኩባንያዎች ብዛት ከ20 በታች ነው፤ ትእምት ብቻውን የሚያስተዳድራቸው ኩባንያዎች በኦፊሴላዊ መንገድ የሚታወቁት 24 ቢሆኑም እስከ 380 እንደሚደርሱ ሌሎች ምንጮች ያሳያሉ፡፡ የኩባንያዎቹ ማንነት እና ብዛት ምሥጢራዊነት በራሱ ክፍተቱን ለመጠቀም ያለመ ይመስላል፡፡

በተቃራኒው ደሞ ሦስቱ – ኦሕዴድ፣ ብአዴን እና ደኢሕዴን ለ80 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥራ ዕድል የመፍጠር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህ እንግዲህ የሚነጻፀረው ሕወሓት እወክለዋለሁ ከሚለው ከ6 በመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ነው፡፡

‘Rethinking Business and Politics in Ethiopia’ በሚል ርዕስ በሳራ ቮጋን እና መስፍን ገብረሚካኤል እ.አ.አ. በ2011 የተሠራ ጥናት እንደሚያመለክተው “[የጥረት] ኩባንያዎች 2,800 ሰዎችን መቅጠር ችለዋል፡፡ ትእምት በአንፃሩ 14,000 ቋሚ እና 34,00 ጊዜያዊ ሠራተኞችን ቀጥሮ ያሠራል፡፡” የሚገርመው፣ በኢትዮጵያ በባሰ ድህነታቸው የሚታወቁት ክልሎች፣ ማለትም ሶማሊ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የሚያቋቁማቸው ኢንዶውመንት የላቸውም፡፡ ነገር ግን የሚመሩት በኢሕአዴግ እህት የፖለቲካ ፓርቲዎች ነው፡፡

የትእምት ድርጅቶች የሆኑት እና ያልሆኑት

የትእምት ቢዝነሶችን በቀላሉ ለመረዳት የማያስችሉ ነገሮች አሉ፡፡ ሠላም ባስ አክስዮን ማኅበር ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1996 የተመሠረተው ሠላም ባስ 99.6 በመቶ የሚሆነው ባለቤትነቱ የትግራይ ልማት ማኅበር (ትልማ) ሲሆን ቀሪው በሌሎች ግለሰቦች ተይዟል፡፡ ሠላም ባስም እንደትእምት ኩባንያዎች የቦርድ አባላቱ የሕወሓት ሰዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ፣ ብዙ ሰዎች የትእምት ኩባንያዎችን ዘርዝሩ ሲባሉ መጀመሪያ የሚመጣላቸው የሠላም ባስ ሥም ነው፡፡ ይህ የተምታታ የባለቤትነት ጉዳይ ነው ምናልባትም ሠላም ባስን በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በተነሱ ተቃውሞዎች ላይ ተጠቂ እንዲሆኑ ያደረጋቸው፡፡

ደጀና ኢንዶውመንት ደግሞ ሌላ ምሳሌ ነው፡፡ ‹በትግራይ ልማት ለማሳለጥ› የተቋቋመው ደጀና ኢንዶውመንት የማረት ንብረት ነው፡፡ በደጀና ድረገጽ ሥር 11 ኩባንያዎች ተዘርዝረዋል፡፡  እ.ኤ.አ. በ2009 የወ/ሮ አዜብ መስፍን የትእምት ኃላፊ ሆኖ መምጣትን ተከትሎ ደጀና ኢንዶውመንት ከትምእት ጋር ተዋሃዶ ነበር፡፡ የትእምት ኩባንያዎች እርስበርስ ሼር እየተገዛዙ አንዱ ሲወድቅ ሌላኛው እንዲያነሳው ማድረግ የተለመደ አካሔዳቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ ዛሬም ድረስ ስለደጀና እና ትእምት ውህደት ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በዚያ ላይ፣ የሁለቱም ድረገጾች እንዳሉ መቆየት ለተመልካች ሁለቱ ኢንዶውመንቶች የተለያዩ እንዲመስሉ ያደርጋል፡፡ የትእምት ኩባንያዎች እንደሆኑ የሚታወቁ አንዳንድ ኩባንያዎች የደጀና ናቸው ተብለው ተዘርዝረዋል፡፡

የሸገር እና የመቐለ ትንቅንቆች 

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቢዝነስ እና ፖለቲካ መሐከል ያለውን ግንኙነት የታዘበ ተመልካች አገሪቱ በሁለት ዐብይ ትርክቶች እንደተከፈለች መረዳት አይከብደውም፡፡ እነዚህን ትርክቶች ‹የሸገር ትርክት› – በተለይ በአዲስ አበባ የሚውጠነጠነው እና፣ ‹የመቐለ ትርክት› – በተለይ በመቐለ የሚውጠነጠነው ትርክት ብዬ ከፍያቸዋለሁ፡፡

ይሁን እንጂ፣ ሁለቱም ትርክቶች እየተቦኩ ከሚጋገሩበት ማዕከል ውጪም እንደየግለሰቡ የፖለቲካ አመለካከት ከማዕከላቱ ውጪም ይገኛሉ፡፡ ‹የሸገር ትርክት› (ብዙ ተቀባይነት ያለው ትርክት) ሕወሓትን ቅቡልነት የሌለው ነገር ግን በኃይል ሥልጣን የያዘ መንግሥት አድርጎ ያየዋል፡፡ ‹የመቐለ ትርክት› ደግሞ በጥቅሉ ሕወሓትን ቅቡልነት ያለው ነገር ግን መሥመሩን በአባላቱ ሙሰኝነት በጥቂቱ የሳተ መንግሥት አድርጎ ይረዳዋል፡፡

ይህ አተረጓጎም፣ ብዙዎቹ የትግራይ ተወላጆች (በ‹መቐለ ትርክት› በመመራት) እንዲሁም ‹ሌሎች› (በ‹ሸገር ትርክት› በመመራት) እንዴት እና ለምን በሕወሓት እና ትእምት መካከል ያለውን ልዩነት እንደሚመለከቱት እንድንረዳ ያግዘናል፡፡

የትግራይ አክቲቪስቶች ትእምት ላይ ያላቸው ትችት የሚታየው በ1993 የሕወሓት መሰንጠቅ ወቅት በተባረሩት የቀድሞዎቹ የሕወሓት ኃላፊዎች ገብሩ አሥራት እና ስዬ አብርሃ አስተያየቶች ውስጥ ነው፡፡ ስዬን በዊኪሊክስ እና ገብሩን በመጽሐፉ እንዳነበብናቸው፣ ሁለቱም የሚቆጫቸው ትእምት የተቋቋመለትን ትግራይን መልሶ የማቋቋም ሕልም መርሑን ስቶ ማሳካት አለመቻሉ ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ትእምት የትግራይ ሕዝብ ሀብት በመሆኑ ላይ ይስማማሉ፡፡

በተቃራኒው፣ ከትግራይ ውጪ ያሉት አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች በኢሕአዴግ ኃላፊዎች የሚሾሩትን ትእምት እና ሌሎች ኢንዶውመንቶች የኛ አይደሉም ባይ ናቸው፡፡ የቀድሞው የኢዴፓ ሊቀመንበር፣ አቶ ልደቱ አያሌው እና በሽብርተኝነት የተፈረጀው ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ሁለቱም ትእምት የአገሪቱን ኢኮኖሚ በብቸኝነት እየበዘበዘ ያለ የፓርቲ ቢዝነስ ነው፤ ወደግል ይዞታ መዛወር አለባቸው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ፣ ብዙ አክቲቪስቶች ዜጎች የትእምት ምርት እና አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ እስከመወትወት የሚደርሱበት ጊዜ አለ፡፡

በተመሳሳይ፣ የትግራይ አክቲቪስቶች ሌሎች እንደ ማረት እና ትልማ ያሉ የክልሉ ሰብኣዊ ድርጅቶች ሳይቀሩ ሕዝባችንን ለመቆጣጠር እታች ድረስ የሚወርዱ የትግራይ ተወላጆችን ለሕወሓት ታማኝ ለማድረግ የሚውል የጭቆና መዋቅሮች ናቸው በማለት ቅሬታ ያሰማሉ፡፡ ከትግራይ ውጪ ያሉ አክትቪስቶች ደግሞ፣ እነዚህ ድርጅቶችም ልክ እንደ ትእምት ሁሉ በሌሎች ወጪ ለትግራይ ተወላጆች ያልተመጣጠነ ተጠቃሚነት ለማምጣት የተቋቋሙ ድርጅቶች ናቸው ባይ ናቸው፡፡

ከዚህ ልዩነት መደምደም የምንችለው ‹የመቐለ ትርክት› ትእምትን የትግራይ ሕዝብ ሀብት አድርጎ የሚቆጥረው ቢሆንም ለሕወሓት አመራሮች የግል ጥቅም ሲባል እየተመዘበረ ነው የሚል ቅሬታ አለው፡፡ የ‹ሸገር ትርክት› ግን ትእምት አንድ ቡድን የኢኮኖሚ የበላይነት በመፍጠር የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት የሚበዘብዝበት መሣሪያ እንደሆነ ነው የሚረዳው፡፡

ቀዩ መሥመር 

ለሕወሓት እውነቱን መንገር ብዙ ግዜ አደገኛ ሆኖ ከርሟል፡፡ ስለትእምት መናገር ደግሞ የባሰውኑ አደገኛ ነገር ነው፡፡፡ አሁን በእስር ላይ የሚገኝ አንድ የአዳማ ኬላ ተቆጣጣሪ ለዚህ ጸሐፊ እንደነገረው፣ ‹የትእምት ኩባንያዎች ወደጅቡቲ ጭነው ሲሔዱ እና ሲመለሱ አይነኬ ናቸው›፡፡ በተመሳሳይ፣ ስለ ትእምት ኩባንያዎች ጥናት ማድረግ ለጋዜጠኞች እጅግ አደገኛ ነው፡፡፡ ይህም የኩባንያዎቹን ምሥጢራዊነት አጠናክሮ ያቆየዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ይህ ጽሑፍ ስለ ትእምት ሙሉ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ስለ ትእምት እና በጥቅሉ በመንግሥት አመራሮች ስለሚደረጉ የኢኮኖሚ የበላይነት እንቅስቃሴዎች ብዙ ሊጻፍ ይችላል፡፡

ወያኔን እየታገልን ዴሞክራሲያዊ ባህልንም እናዳብር!

ያሬድ በላይነህ ከብራሰልስ ቤልጀም

ወያኔን መርገምና ማሳጣትን ብቻ የፖለቲካ ግባቸው አድርገው የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ቆም ብለው ማሰብ ይገባቸዋል።ለተግባቦት እና አብሮ ለመስራት አስቸጋሪ የሆነውን ነባር የፖለቲካ ባህላችንን ፈትሸው ህዝቡን በጋራ እንዲቆም የሚያስችል ስልት መቀየስ ይገባቸዋል።ለውጡን ከላይ ብቻ ሳይሆን ከስር የህዝቡንም ስነ ልቦና ጠጋ ብሎ በመፈተሽ ከሚመጣ ሁለንተናዊ ለውጥ ጋር ካልተጣጣመ በቀር የወያኔ መወገድ በራሱ ኢትዮጵያን በአንዴ የዴሞክራሲያዊት ሃገር አያረጋትም።

ዴሞክራሲ ባህል ነው። ባህል ደግሞ ከህዝብ ማንነትና ስነልቡና ጋር ተቆራኝቶ የሚያድግ ነገር ነው።በነጻነት ማሰብን፣ በልዩነቶች ላይ ተነጋግሮ መግባባትን ወይም ባለመግባባትም ቢሆን አብሮ ለመስራት መፍቀድን፣ የኔ ብቻ ሃሳብ፣ እቅድ፣ ፖሊሲ ብቻ ትክክል ነው ከሚል ጽንፍ የረገጠ አስተሳሰብ ወጥቶ የተለያየ ሃሳብ ካላቸው ጋር ተነጋግሮ ለመስራት መፍቀድንም ይፈልጋል ዴሞክራሲ።ለዚህም ይመስለኛል በሃገራችን ውስጥ አንባገነን ስርአት አቆጥቁጦ ለመብቀል ለም የሆነ አፈር ውሃና አየር የሚያገኘው።ዛሬ ህዝባችንን የመከራ ፍዳ እያበሉ ያሉት ገዥዎች ከኛው መሃል የወጡ እንጂ ከሰማይ የወረዱ ስላይደሉ ለውጥን ስናስብ ከስርአት ለውጥ ጋር ህዝቡንም ልናመጣ ለምንሻው ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዴሞክራሲያዊ ስርአት ያለውን ሁለንተናዊ ዝግጅት ማጤን ይገባናል።

ዛሬ ላይ ህዝቡ ጋር ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲኖር የመፈለግና ለዛም ለውጥ በቁርጠኝነት እስከመስዋእትነት የመቆም ፍላጎት ቢኖርም ህዝቡን ወክለው የፖለቲካ ትግሉን እንመራለን የሚሉት የፖለቲካ ልሂቃኑ ግን ውሥጣቸውን ሊፈትሹ ይገባል።ዛሬ በየማህበራዊ ሚዲያው እንደምንሰማው የጨረባ ተስካር የሚሉትን አይነት ፖለቲካን አንግሰው እንዲተራመሱ ህዝቡ ፈቃድ አልሰጣቸውም።በኢትዮጵያ መበታተን ላይ የኛን አዲስ ሃገር እንመሰርታለን እስከሚል ጥግ እንዲሄዱ ወክለነዋል ያሉት ህዝብ ፈቃድ አልሰጣቸውም ጩኸታቸውም ሆነ ቅዠታቸው የራሳቸው ነው።ይህ አይነቱ የፖለቲካ ስካር ደግሞ ስልጣን ማግኘትን ብቻ አላማ አድርጎ የሚንደረደር የጥቂት ግለሰቦች እብደት ነው።አንዳንዶች ግን ይህን መሰሉን ግለሰባዊ የፖለቲካ ስካር ድርጅታዊ ካባ አልብሰውት መታገያ አርማ ሊያረጉት ሲሯሯጡም ታዝበናል ይሁን እንጂ ህዝቡ ለዚህም ፈቃዱን አልሰጠም።ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ እጣ በልተው በማይጠግቡ ዘራፊዎችና ነፍሰገዳዮች እጅ ላይ ወድቋል።

ህዝቡ ማንኛውም የተገፋና የተማረረ  ህዝብ እንደሚያደርገው ከፍተኛ የነጻነት ፍላጎት አለው።ድህነቱ፣ኢፍትሃዊነቱ፣ተስፋቢስነቱ ለነጻነት የሚከፈለውን ውድ ዋጋ ህይወትን መስዋእት አድርጎ እስከማቅረብ አድርሶታል ግን ይህ ድፍረቱ ብቻ ግን የሚፈልገውን ለውጥ ሊያመጣለት እንደማይችል ካለፉት የትግል ተመክሮዎቹ ያየን ይመስለኛል።ደርግ አንባገነን ነበር የተኩት በሱ መቃብር ላይ ነጻነትን እናመጣልሃለን ብለው መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ከጎናቸው አሰልፈው ከሚኒሊክ ቤተመንግስት ሰተት ብለው ገቡ።ጠባብ የብሄር ፖለቲካን ቢያቀነቅኑም ለአንድ ብሄር ነጻነት ነው የምንታገለው ቢሉም ህዝቡ በመማረሩ ብቻ ደግፏቸው ለድል በቁ። የቋመጡለትን የስልጣን መንበር ሲያገኙ የህዝብን ውለታ ረስተው ይገሉት ፣ያስርቡት ከዛም አልፎ በኑሮ ተማሮ ልጆቹ ለስደት ቀሪውም ተስፋቢስ ለሆነ ህይወት ዳርገውት አረፉ።እነሱን ከደደቢት በረሃ ጀምሮ እስከሚኒሊክ ቤተመንግስት ደጃፍ ድረስ ተሸክሞ ለስልጣን ያበቃቸው ህዝብ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ በጠላትነት ቆሞባቸዋል። ለውጥ ይፈልጋል ለውጡ ደግሞ ያለፈውን የሚደግም መሆን የለበትም።አንዱን ጨቋኝ በሌላው የሚተካ ለውጥ ሌላ ማቆሚያ የሌለው የመከራ ድግስ ለትውልድ ከማቆየት ውጭ ጥቅም የለውም። ስለዚህ አንባገነኖችን ከማስወገዱ ጎን ለጎን በህዝቦች መሃል የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት በልዩነቶች ላይ ተባብሮ በጋራ የመስራት ስልጡን የፖለቲካ ባህልን አብሮ ማስፈንም ያስፈልጋል።

ነባሩን ባለመተማመንና በመጠፋፋት ላይ የቆመውን ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህላችን ላይ የለውጥ ሰይፋችንን ልናሳርፍበት ይገባል።ፖለቲከኞቻችንም ትግላቸው የመንግስት ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ለሁለንተናዊ የዴሞክራሲያዊ ለውጥ ከሆነ ራሳቸውን መፈተሽና ለውጡን ከራሳቸው ሊጀምሩት ይገባል።የጎንዮሽ ትግሉን ትተው በጋራ ለመቆም ዛሬ ህዝቡ ውስጥ ያለው የለውጥ ፍላጎት የግድ ሊላቸው ይገባል።እንደ ሃይማኖት ቀኖና ከሚያዩትና ከሚያመልኩት ከራሳቸው የፖለቲካ ፓርቲ፣ ድርጅት ወይም ተቋም ፕሮግራምና አላማ በላይ የሃገር ህልውና እና የህዝብ ዘላቂ ተስፋ ሊያሳስባቸው ይገባል።በየጊዜው እየተቀጣጠሉ የሚጠፉ የለውጥ እሳቶች የተከፈለላቸውን ዋጋ የሚመጥንና የሚታይ ለውጥን ለህዝቡ ካላመጡ በትግሉ መማረንንና ተስፋ መቁረጥን ይጋብዛሉ።ያ ደግሞ የነጻነቱን ጊዜ ማርዘምን ብቻ ሳይሆን ጭራሽም ስለነጻነት ማሰብን ትቶ በምናገባኝ የሚኖርን ተስፋ ቢስ ዜጋን ያበራክታል።

የህዝቡን ትግል የመምራት ሃላፊነት ትከሻቸው ላይ የወደቀው ሃገር በብዙ ድካም ያስተማረቻቸው የፖለቲካ ልሂቃንም ከራሳቸው ትክለ ስብእና እና የፓለቲካ ግብ በላይ ሳይማር ያስተማራቸው ህዝብ መከራ ለእውነተኛ ለውጥ እንዲቆሙ ሊያተጋቸው ይገባል።በምናገባኝና በተለያየ ምክንያት ራሳቸውን ከፖለቲካው አግለው የተቀመጡም ምሁራንም በተመሳሳዩ የዛች ሃገርን ጎስቋላ ህዝብ መከራ እንዳላዩ ሆነው መቀመጣቸው ከህሊናና ከታሪክ ተጠያቂነት አያድናቸውም። የውጭውን አለም የዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት በረከት ተቋድሰው የነጻነትን ምንነት በመኖር ያዩ በውጭ የሚኖሩ በኢትዬጵያውያንም ይሄ በጨካኞች ተረግጦ ያለ ህዝባቸውን ከመከራ ለማውጣት ለሚደረገው ትግል የተሻለ አስተዋጽኦ ማበርከት ሲችሉ በምናገባኝ ጀርባ መስጠታቸው አስተዛዛቢ ነው።

ነጻነት ብዙ ዋጋ ቢያስከፍልም እውነትና ፍትህ ጉልበት ሆነውት የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣቱ አይቀርም። ዛሬ ህወሃት ህዝቡን በጎሳ ከረጢት ውስጥ ከቶ ከፋፍየዋለው ብሎ ቢያስብም የነጻነት ፍላጎቱ ግን አንድ ያደርገዋል።ወያኔ መሰረትኩት የሚለው የብሄር ፌደራሊዝም የግለሰቦች ነጻነትን እውቅና ነስቶ የቡድን ነጻነት አስከብራለሁ በሚል ባዶ ትርክት ላይ የቆመ ጸረ ዴሞክራሲ ስለሆነ እንኳን ሌሎች ብሄሮችን ሊጠቅም ቆሜለታለሁ የሚለውንም ብሄር ተጠቃሚ አላረገም። ስለዚህ የህዝቡ የነጻነት ፍላጎት ያልተገደበ እና ከዳር ዳር ያለ በመሆኑ ይህ የነጻነት ጥማት በተገቢው ለውጥ እንዲታጀብ የስርአት ለውጥ ለማድረግ ከሚደረገው ትግል ጎን ለጎን ህዝቡንም እንዲመጣ ለሚታገልለት የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሚሆን ትክለ ሰውነት ማላበስ ያስፈልጋል።በችግሮች ላይ በግልጽ ተወያይቶ መግባባትን አሊያም ባለመግባባትም በጋራ ግቦች ላይ አብሮ የመስራትን ባህል ከወዲሁ መገንባት ይገባል።ከፓርቲዎች ቁመና በላይ ጎልቶ የሚታይን በህዝቦች ሁለንተናዊ ስብእና ላይ የሚመሰረት የዴሞክራሲ ስርአት ባህልን ለመትከልም ነገ ሳይሆን ዛሬ ላይ ሊታሰብ ይገባል።የምእራባውያኑ ዴሞክራሲ መሰረቱ ለሰብአዊ መብት ክብር ያለው ህብረተሰብ ነው። በህግና በስርአት የሚመሩ የፍትህ ተቋማትም የስርአቱን ቀጣይነት ደግፈው ያቆሙ ዋልታዎች ናቸው።እነዚህ በሌሉበት አንባገነኖችን በማስወገድ ብቻ የሚፈለገው ለውጥ አይመጣም።

ለነጻነቱ ክብር የሚሰጥ፣ባርነትን አምርሮ የሚጠላ፣ለሰብአዊ መብት ክብር በጋራ የሚቆም ህብረተሰብ መፍጠር ባልተቻለበት ሁኔታ ብቻውን በትግል የሚመጣ ለውጥ ህዝብን ከነጻነት ክብሩ ጋር አያገናኘውም።ካለፉት ለውጦች የተማርነው እውነት ይህንኑ ነው። የንጉሱ የፊውዳል ስርአት በህዝቡ ትግል መውደቅ ተፈላጊውን ለውጥ አላመጣም ይልቁንም በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ አንባገነንን ነው የተከለው ያም ለአንድ ትውልድ እልቂትና ዛሬም ሃገራችን ለገባችበት የጥፋት ማጥ ምክንያት ሆኗል።ደርግን ታግሎ በመጣልም ሌላ የባሰ ከፋፋይና ሃገር ለማፍረስ ሌት ተቀን የሚሰራ አውዳሚ ስርአት ተፈጠረ እንጂ ትግሉ በራሱ ህዝብ የሚናፍቀውን የዴሞክራሲ ስርአት አላመጣም።ለዚህም ነው ይህንንኑ ችግር ላለመድገም ዛሬ ላይ ለውጡ የማያዳግም አገር አድን እንዲሆን ጨቋኙን ስርአት ታግሎ ከመጣል ባለፈ ዴሞክራሲያዊ ባህል እንዲዳብር የህዝባችንን አስተሳሰብ እና ስነልቡና በመፈተሽ ጎጂ እርስ በእርስ የመጠላለፍና የመጠፋፋት ባህላችንንም እያከምን እንሂድ የምንለው።ትግሉን እየመሩ ያሉ የፖለቲካ ልሂቃንም ከኔ በላይ ላሳር ማለታቸውን ትተው ወደውጭ ብቻ ሳይሆን ወደውስጣቸውም እንዲታገሉ ጨቋኙን ብቻ ሳይሆን ተጨቋኙንም በሞራል ልእልና ከፍ አርጎ የሚያቆም ሁለንተናዊ ሰብአዊ ልእልና ሊያጎናጽፍ የሚችል የዴሞክራሲ ባህል ባለቤት ለማድረግ እንዲታገሉ የምንሻው።

ይህ ሲሆን ብቻ የህዝብ መስዋእትነት ተገቢውን ዋጋ ያገኛል።አንባገነንነት የሚበቅልበት ለም መሬት ያጣል።ወያኔንም ተሸክሞት የሚቆም የጭቆና ቀንበርን የሚሸከም ትከሻ ይጠፋል። ከፋፍሎና ለያይቶ ሊያቆመን የሚችልበት የህልውናው መሰረት የሆነውንም ጭቆናን የሚሸከም የወረደ ስብእናና  አድርባይ ማንነት ስለሚያጣ ወደማይቀርለት የጥፋት መቃብሩ ይወርዳል።

የኮማንድ ፖስቱ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

BBN News  | የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በበላይነት አስፈጽማለሁ የሚለው አካል እርምጃውን አጠናክሮ እደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ራሱን የአዋጁ አስፈጻሚ አድርጎ የሾመው የህወሓት የደህንነት ቡድን ወይም ኮማንድ ፖስቱ፣ አዋጁ ከወጣ ወዲህ ሀገሪቱ እየተረጋጋች እንደመጣች የገለጸ ሲሆን፣ ሀኖም ሀገሪቱ ተረጋግታለች ቢልም አዋጁን ለማንሳት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡


የመከላከያ ሚኒስትር እና የኮማንድ ፖስቱ ዋና ጸሐፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ‹‹አዋጁ ውጤታማ ስራ አከናውኗል፡፡›› ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጭምር ውግዘት እየወረደበት የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ጥፋት እያስከተለ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡


ለጋዜጠኞች፣ ለተቃውሞ ፖለቲካ አራማጆች፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ለሌሎችም የሀገሪቱ ዜጎች እስር እና ግድያ ምክንያት እየሆነ የሚገኘው አዋጁ፣ በቀጣይነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው በመንግስት በኩል እየተገለጸ ያለው፡፡ ‹‹ከአዋጁ በኋላ ለውጦች ቢኖሩም አሁንም አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የተቀናጀ ስራ መስራት ይገባል፡፡›› ሲሉ አቶ ሲራጅ በቀጣይነትም እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይነት እነማንን ማሰር እንዳለበት እየመከረ እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ድርድር ዬደራጎን ግርግር – ዬሴራ ግግር። – ከሥርጉተ ሥላሴ

ከሥርጉተ ሥላሴ 25.01.2017 (ዙሪክ ሲዊዘርላንድ።)

 „ዬምትሞቱባትን፡ ቀን፡ አስቡ፡ ነፍሳችሁ፡ ከሥጋችሁ፡ በተለየች፡ ጊዜ፡ ገንዘባችሁንም፡ ለሌላ፡ በተዋችሁ፡ ጊዜ፡ ወደማታውቁት፡ ጎዳናም፡ በሄዳችሁ፡ ጊዜ፡ የምትመጣባችሁን፡ መከራ፡ አስቧት።“

(መጽሐፈ መቃብያንም ሣልስ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፩)

ዬዛሬ በር።

እጅግ ዬማከብረዎት አቶ ፈቃደ ሽዋ ቀና እንዴት ሰነበቱልን። ደህና ነዎት ወይ? ባለፈው ጊዜ ኢሳት ላይ በነበረዎት ቆይታ ዬእርሰዎ ትህትና ጉዞ አደከመኝ ብዬ በኢሜለዎት መልዕክት ልኬለዎት ነበር። ዬዛሬውም እንዲሁ። እርእሱ እራሱ ዬሚገርም ነው። „አትነጋገሩ ብሎ መምከር ጥሩ ፖለቲካ አይደለም  – ፍቃደ ሸዋቀና“ ይላል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/71512#comments

ለመሆኑ አትናገሩ ብሎ ከልካዩ ማነው? ዬነፃነት ትግሉ እንብርት ሴሉ ዬመናገር፣ ዬመጻፍ፤ ሃሳብን በነፃነት ዬመግለጽ፣ ዬመደራጀት፣ ድርጅት ሲባል ሰዎች ዓላማቸውን ለማስፈጸም ዬሃሳብ ምክክር ዬሚያደርጉበት ዬዓላማ ማህበር ማለት ነው። ፍላጎታችን ይህ መሰለኝ ….

ይህን ያሰረው ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው፤ ወይንስ ተፎካካሪ ዬፖለቲካ ድርጅቶች ወይንስ ዬኢትዮዽያ ህዝብ? ውጪ ያለነውንም ይጨምራል። ኢትዮዽያ ሀገራችን ኢትዮዽያዊነት ደግሞ ዜግነታችን ነውና። ዬኢትዮዽያ ህዝብ ካቴናው እኮ ጉሮሮ ውስጥ ነው ያለው።ካቴናው ያለው ህሊና ውስጥ ነው። „አትናገሩ አታስቡ“ ማለት ይሄ ነው። በእዝነ ህሊናዎት እንደ          Gastroskopie ጀርመኖች ዬጨጓራ መስታውት ነው ዬሚሉት (die Magenspiegelung) ይሰቡት፤ ጉሮሮ ውስጡ ላይና ከነቃው ህሊና ውስጥ ዬብረት ካቴና ሲገጠም። Gastroskopie ከዕይታው ግብረ ምላሽ (feedback) በኋላ ይወጣል። ካቴናው ግን ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶና ዬግራ ፖለቲካ መንፈስ ግራቀኙ ካላከተሙ አይፈታም።

አትናገሩም ብሎ ካቴናውን ህሊና ውስጥና ጉሮሮ ውስጥ በህግ ገጥሞ ተናገሩ ማለት አይችልም – ወያኔ። ሳይናገሩ መናገር አይቻልም። በዚህ ዘመን፤ ዘመኑን ዬማጥናት አቅሙ ቢኖረን አሁን እኮ „ደሞ ለዓይኔ ያሻኝን ባይ ማን አለኝ ከልካይ“፤ እራሱ ዬቁም እስር ላይ ነው። ወያኔ ቢችል እኮ ጸሐይን ማከፋፈል፤ ዝናብና በክልል ማደራጀት፤ ወቅታትን ከተፈጥሯቸው ባገደ ነበር። ዬሆነ ሆኖ አትዩ ፤ አታዳምጡ፤ አታንብቡ፤ ተብሎ ተጨማሪ ዬዓይን ካቴና፤ ተጨማሪ ዬጆሮ ካቴና በአፓርታይዱ ወያኔ ተመርቷል። ዬእርስዎ ቅናዊ መንገድ ዬተከተሉ ከወያኔ ጋር ዬተቀመጡ ኃይሎች ለእኔ ዬግድ ግዳ ፎቶ ወይንም ዬመንገድ ፖስተር ናቸው! ጉድጓድ ውሃ ውስጥ ዬገባ ሰው ይሰምጣል። መተንፈሻ ስለሚያጥረውም – ይሞታል። በሞት መንፈስ ላይ ይወያዩ እያሉ ነው እዬመከሩ ያሉት።

ለነገሩ „አፈርሳታ“ ዬማህበራዊ ሚዲያ አክታቢስቶች ጋር አዘጋጅቶት በነበረው ውይይትም ስለአማራ ዬዘር ጥፋት „ምን መረጃ ዕውነተኝነት አላችሁ“ ዬሚል ዕድምታ ያለው ጥያቄ አቅርበዋል። ግነት እንዳይኖር፣ ዬመረጃ ተቀባይነት እንዳይሳሳ ነው – ስጋቱ።

https://www.youtube.com/watch?v=7a4of2PdGQc

እንደ ታላቅ ዬሀገር ሃብትነተዎትና ዬትውልደ ዬሊቃውንት ዬቀለም ዋርካነተወት ቢያንስ በወያኔ መራሹ ዬስታስቲክ ጽ/ቤት ዬታመነውን 2.4 ሚሊዮን ህዝብ ህሊናዎት ላይ መቀመጥ አልቻለም። „አማራ“ መሆን ማለትና „አማራነትን“ በውስጥ ማስቀመጥ ማለት በፍጹም ሁኔታ ዬተለያዬ ነው። ጉር ያላለ ለስታ ቅቤ እንደማለት ነው  – ለእኔ። ጉር ያላለን ለስታ ቅቤ ተፈጥሯዊ ባህሪን ዱቅዱቃነቱን ዬጎንደር ሴት ታውቀዋለች።ዬሆነ ሆኖ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ዬማሌሊት ማኒፌስቶ ዓላማና ግብ ጭንቅላቱ እራሱ ይህንን ጥያቄ ይመልሰዋል።  „በአማራ መቃብር ላይ ዬታላቋን ትግራይ ሪፓብሊክ እንመሰርታለን“ ይላል። ለዚህስ ዬስታስቲክ ቢሮ ይከፈትለትን?! ዬጥናትና ዬምርምር ወይንም ዬትርጉም ሥራ ከቶ ይደራጅለት ይሁን?  አማራነትን ዬእኔ ለማለት በጋብቻ፣ በአበልጅነት፣ በጉርብትና ያሉ ግንኙነቶችን ለማንነት መደለያነት አለማዋልን በአጽህኖት ይጠይቃል። ቅጂ ያለው ዬሰው ልጅ ዬለምና። አማራነት የደም ውርስ እንጂ ዬንግግር ማሟያ አይደለም! ደሙ ሲነካ መነሸጥ አለበት! ዬጥቃት ጋሻ ጃግሬ ልጅን ዬአማራ ወላጆች አይወልዱም እና። ሌላውን ለዛሬ ልተወዎው። ሲያስፈልገኝ ደግሞ እንሸራሸርበታለሁ። ዬራሴ ጌታ እኔው እራሴ ነኝና። በሽታውን ሳናውቅ ነው ዓመታት እዬተሳለቁብን ዬነጎዱት። ድፍረትም ያንሰናል ስለዕውነት።

ጉዳዩን ካነሳሁት ዘንድ „አፈርሳታ“ ቃሉ ሆነ ትርጉሙ፣ ተግባሩም ትውፊታችን ነው። ወደ ውስጣችን ለማዬት አቅም እያሸተ ስለሆነ ያስመሰግናል። እንኳንም ለዚህ አበቃን!  „አፈርሳታ“ ማለት ባህላዊ ዬወታደር ቤት ማለት ነው። ባህላዊ ዬወንጀል ምርመራ ቢሮእንደማለት።  ዝንባሌው ዬወንጀል ጥፋቶችን በባህላዊ መንገድ ፤ ባልተፃፈው ህጋችን ማውጣጣት ነው፤ አውጫጭኝ ነው። ስለሆነም ዬነፃነት ፍለጋ ጉዟችን ከወንጀልና፤ ከወንጀላዊ ቀጠናዎች ጋር ምንም ንክኪ ስሌለው መድረኩና ዓላማው በፍጹም ሁኔታ ዬማይገናኝ ነው። ፕሮግራሙ ነፍሱ ካለች ስሙን ከተግባሩ ጋር ሰያሚዎቹ ቢያገናኙት መልካም ነው እንላለን እኔና ብዕሬ።

እፍታ።

ወይ ልግጫ! ዓመት ድገሙ እያለን ነው ደግሞ ባላንባራስ እርግጫ። ዬልግጫ ዑደት ዬዕንባ ዳንሰኞች አጃቢነት ነው – ለእኔ። ለዬትኛውም ዬህይወት ዘርፍ መወያዬት ሆነ አንዱ ከሌላው ጋር መነጋገር ዬንጹህ አዬር ያህል ተፈላጊ ነው። ከግል ህይወት እስከ ሀገራዊ፣ ዓለምዓቀፋዊ ኩነቶች ድረስ መሪው ምክክር፣ ውይይት ነው። ሃይማኖታዊ ጉዳዮችም ሆነ ለኪነጥበብ ዬብልጽግና መሰረት ነው  – መወያዬት። ለፖለቲካ ተልዕኮማ ሩሁ ነው።

መወያዬት፣ መመካከር ዬመኖር ሳይንስ ናቸው። ዬአብሮነት ሲሳይ ናቸው። በቅኖች ከተቀረጹ። በግልጽነትና በቀጥተኝነት ከታወዱ። በማስተዋል ከተመሩ። በሙሉ ሀገራዊ ተቆርቋሪነት ስሜት ከተነሳሱ ስክነታቸው ህዝበ – ጠቀም ይሆናል። በስተቀር ግን እያደባ ለሚነሳ አውሬ ዬበቀል ልኳንዳ ቤት መክፈት ነው። እንደ ሰው እስከ አስር ጊዜ ስህተት በተመሳሳይ ጉዳይ ዙሪያ መስራትን ይሁን ተብሎ ቢቀበሉት እንኳን፤ በ25 ዓመት ውስጥ ተመሳሳይ ሺህ ሥህተት ውስጥ እዬዳከሩ ዬደሃውን ህዝብ አሳር ማበራከት ለእኔ ዬፖለቲካ ወንጀል ነው። ባለፈው ጊዜ ተው እዬተባሉ፤ ምርጫ ገቡ። ያው ውድ ህይወታቸውን ሌሎች ገበሩ – ምስኪኖች። እስር ቤት ዬታጎሩትም ጠያቂ ዬላቸውም።

ያን ጊዜ ከሙሁራን ዬተደመጠው ወያኔ በምርጫው ተሸንፎ ቢያጭበረብር – በዓለም ማህበረሰብ ይጋለጣል ዬሚል ነበር። ተጋልጦ ምን ዬፖለቲካ ትርፍ ተገኜ? አሁንም ይህ እዬተደመጠ ነው።

(„ትልቁ ነገር በድርድሩ መድረክ ላይ የሚቀርበው ጉዳይ ነው። ማወቅና ማረጋገጥ ያለብን በድርድር ጊዜ ተደራዳሪ ወገን ከድርድሩተጠቃሚ ለመሆን ጥረት የማድረግን ጉዳይ ነው። ተቃዋሚዎች መሰረታዊ የሚሉዋቸውን የሚታገሉላቸውንና እንዲለወጡየሚፈልጉዋቸው ጉዳዮች ላይ ማተኮርና ቢያንስ በከፊል ወይም በሙሉ መልስ የማያገኙ ከሆነ ድርድሩን ተገቢ መግለጫ አውጥተውማቋረጥ ከቻሉ የፖለቲካው ትርፍ የነሱ የሆናል። የፖለቲካ አሸናፊነቱን ተቀዳጁ ማለት ነው።“  ከአቶ ፈቃደ ሽዋ ቀና)

ለአዳዲስ ሴራዎች ዬሰው ልጅ ዬሞት ሙከራ ይካሄድ እያሉን ነው – እነ አቶ ፈቃደ ሽዋቀና – ሙሁሮቻችን። ትህትናቸውንና ዬሃሳብ ልዩነታቸውን ባከብረውም ነገረ ሥራቸው ድክም ያደርገኛል። እሳቸው ባነሷቸው ህፃጽ ሃሳቦች ትራስነትም ደግሞ አዲስ ጉግስ ተጀምሮ ከሁለት – ከሦስት መተርተር እንደተጠበቀ ሆኖ። ምን አለ ሁሌም ይድላቸው ነው ነገርዬው። አይዋ ወያኔ አራት ኪሎው ተራራ ላይ ሆኖ ዬለመደውን ዬቀጥቅጦ ግዛት ሂደቱን እረፍቱን እዬወሰደ ይቀጥላል። ፍቅር ጥሩ ቢሆንም ህዝብ ለዬዘመኑ ዬሴራ ካቴና ዬሞት መሞከሪያ ሟሟሻ ይሁን ማለት ሥም የለሽ አዟሪት ወይንም ዬሆነ ድግምት ነገረ  ነው ለእኔ – ለሥርጉተ ሥላሴ።

ዬአጓጉል ጉጉል።

ወያኔ ፍንክች አይልም። ፋሽስት ፋሽስት ነው። ፈርዖንም ፈርዖን። ደራጎንም ደራጎን። ወራሪም ወራሪ።ለአማራው ተጋድሎ ዬሰጠው መልስ ፍንጭ  „የወልቃይትን ‹‹ታሪካዊና ባሕላዊ ትግሬነት ለማረጋገጥ›› ጥናት ለሚሠሩ ተማሪዎች የተለየ በጀት መመደቡ ተሰማ፤“  ዬኔታ * ሙሉቀን ተስፋው በ23.01.2017 አስነብቦናል። ሌብነትን ህጋዊ ዕውቅና በውንብድና በማሰጠት ዬጥናትና ዬምርምር ሥራ ለማሰራት መወጠን – ለእኔ ይሄ ማለት „ለትምህርተ – ሌብነት¡“ ካሪክለም ተነድፎለታል ማለት ነው። ለዚህ ደግሞ አረና ለተፈጻሚነቱ ቀኝ እጅ ለወያኔ እንደሚሆን ሳይታለም ዬተፈታ ነው።

ለአማራ ዬህልውና ተጋድሎ ምላሽ በማስገኘት ደረጃ በቁመትም በወርድም አቅሙ ዬሚመጥን ዬፖለቲካ ድርጅት ከስብስቡ ዬለም። ለለበጣ ወያኔ ሌላ ተለጣፊ ካልፈጠረ በስተቀር። ጥያቄዋን እራሱ ዬሚደፍራት አንድም ህብረ ብሄር ፓርቲ አልተፈጠረም። ስለዚህ በዚህ ዘርፍ እራሱ ዳሽ ነው።

ውይይት መፍትሄም ስኬትም ነው። ውይይት መርህም ነው ለዴሞክራሲ ጉዞ። ነገር ግን በተዘጋ በር ዬሚገኝ መፍትሄም ስኬትም አይኖረውም። ዬሰው ልጅ መጀመሪያ መተንፈስ አለበት። ኦክስጅን በሌለበት ህይወት አይቀጥልም። ንፁህ አዬር በሌለበት ሁኔታ በዬትኛው ትንፋሽ ነው አንደበት ዬሚከፈተው? ዬሰው ልጅ ቁሟ መሄዱ ብቻውን መኖሩን ሊተረጉም አይችልም። ከሁሉም በላይ ዬሥነ – ልቦና ዬበላይነት በሌለበት፤ ዬራስ መተማመን ተፈጥሮ በተሰደደበት ዬቀውስ ጊዜ፤ በምን ሁኔታ ነው ውይይት ዬሚካሄደው? ከችግር ፈጣሪው፤ ከሞት ዬማምረቻ ድርጅቱ ከወያኔ ጋር? ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሳይተያዩ በደበሳ መናበብ ይኖራልን? ወይንስ እህል ውሃ አልባ ህይወት ይቀጥላልን? ጥያቄው እኮ ዬህልውና ነው። ማስቲካ እያላመጡ ዬማይዘነጥበት።

በአሁኑ ወቅት ዬመፍትሄ ቁልፋ ከውይይት በፊት እራሱ ወያኔ ቀድሞ ሊከውናቸው ዬሚገባ መሰረታዊ አመክንዮች አሉ። ወያኔምያውቃቸዋል ዬደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ“  ካልሆነ በስተቀር። መቅደም ያለባቸውን እርምጃዎች መውሰድ ያለበት ወያኔ ብቻ ነው።ዬተፎካካሪ ኃይሎች ፋይዳ በአዳራሽ ላይ መከተም አይመስለኝም መፍትሄ – አመንጩ። በተለሰነ ዬደራጎን ህሊና ግርግር መፍትሄ ለማግኘት ተስፈኛ መሆን ባይከለከልም፤ በወታደራዊ ሥር በወደቀ መንፈስ ውስጥ ሆኖ ራዕይን ለማሳካት ማሰቡ ጸሐይ ጨረቃን ተክታዬቀን ብርኃን ትሆናለች እንደ ማለት ነው።

ምክንያቱም ምግብ ለመሥራት ለምግብ መስራት ዬሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች – ያስፈልጋሉ። ይህ ካልኖረ ምግብን ለማብሰል፤ አብስሎም ለመብላት ማሰብ ማለት ነው። ማሰብ ብቻውን ደግሞ ዬራህብ ማስታገሻ ሊሆን አይችልም። ማሰብ ብቻውን ራህቡን ቢጨምር እንጂ ምግብ ሊሆን በፍጹም አይችልም። ገበሬ ለመሆን መሬትና ዬእርሻ መሳሪያ ያስፈልጋል። መምህር ክፍል ውስጥ ለማስተማር ዬትምህርት ድጋፍ መስጫ መጸሐፍት፤ ብላክቦርድ፤ ቾክ ቢኖሩ እንኳን ተማሪ ከሌለ ማስተማር ህልም ነው ዬሚሆነው። ምኞት ብቻውን ዬድል እርካብ አይሆንም። ህዝብ ሙሉ ለሙሉ አመኔታውን ለነፈገው አውሬ ዬመተንፈሻ ቧንቧ ሊሰራለት ይገባል ማለት – በሳሉን ወቅትን ካለማድመጥ ዬተቀነጨበ ጭንጋፍ ዕሳቢም ይመስለኛል። ልፍስፍስነትም ነው። ከዚያ ይልቅ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ዕድሜ ያርዝምልን ብሎ ሁለት ሰባት ሱባኤ መያዙ ሳይሻል አይቀርም¡ ጠበቅ አድርጎ መስገዱንም – ቢአስነኩት¡

ህዝብ መከፋቱን ዬሚገልጽበት መንገዱ ታስሯል። ያ …  ከሥር መለቀቅ አለበት። ይህን ለመፍታት ደግሞ በህግ ዬታሰሩ መብቶችሙሉ – ለሙሉ ነፃ መውጣት ይኖርባቸዋል። በህግ ዬታሰሩ ህሊናዎች፤ ኑሮዎች፤ ዓላማዎች፤ ግቦች፤ መንፈሶች፤ ዬህልውና ንጥረ ነገሮች፤ ዬትውልድ ተስፋዎች፤ ብራናዎች፤ ብዕሮች ሙሉ – ለሙሉ ነፃ መውጣት ይኖርባቸዋል። ዬዚህ ባለ ሙሉ ሥልጣን ዬወያኔ ሃርነት ትግሬ ድርጅት ብቻ ነው። ስለዚህ ለማሟያ ካልሆነ በስተቀር፤ አዳራሽ ውስጥ ዬተቃዋሚ ኃይሎች ለመምክር መሰብሰባቸው ዬድርድር በረዷዊ ግግር ለመፍጠር ካልሆነ፤ ሊያስገኝ ዬሚችለው ዕሴት ለዛዛ እንጨት ነው። ለዘዛ እንጨት ደግሞ ወይ አነድም ወይ አነድም። ዬወያኔ ሃርነት ትግሬ ሴራ ወቅቱን ግግር በረዶ እንዲሆን ማድረግ ነው። ይህ ዬኖረበት … ተንደላቆ ዬሚዘንጥበት ዓውራ መንገዱ ነው።

ዬአሁኑ ከወትሮው ዬተለዩ – ቁምጥ ዬሚያደርጉ አጓጒ መላሾዎችን ዬጎንዮሽ መስመር መዘርጋትን አክሎ፤ በአቀራረቡ ረቀቅ ያሉ ሲናሪዎች ሊኖሩት ይችላሉ። ረቂቅ ሂደቶችን ጤናማ መሆናቸውን አገላብጦ መመርመር፣ ተገቢውን ዬክህሎት አቅም ሰጥቶ በአሸናፊነት ለመውጣት መቻልን በሚመለከት አሁን ሀገር ቤት ያለው ዬተቃዋሚ ሃይል መደገፊያ ምርኩዝ ዬሚያስፈልገው ሆኖ ነው ዬሚታዬው። ሚዲያ ላይ ወጥቶ ሃሳብን መግለጽና አሸናፊ ሃሳቦችን ቀርፆ ተፎካካሪ ፖርቲን ማሸነፍ መንገዱ ዬክረምትና ዬበጋ ያህል ልዩነት አለው፤ ወይንም ዬብስን እና ውቅያኖስን ማወዳደር ነው አሁንም ለእኔ –  ለሥርጉተ ሥላሴ።

ዬኢትዮዽያ ተቃዋሚ ኃይል ይሁን ሂደቱ እንዲቀጥል ቅንነታቸውን ዬሚለግሱ ሙሁራን ከ25 ዓመት በኋላ እንኳን ዬወያኔ ሃርነት ትግራይን አብሶ ዬአቶ በረከት ስምኦን -ን እንጦርጦስ ገጸ ባህሪ በአግባቡ ዬመተርጎም አቅም አዝጋሚ መሆኑ ለነፃነት ፍለጋ ጉዞ ዬቁርጥማት ህመም ሆኖል። አድሮ ጥጃ።“  ለዚህ እኮ ነው ህዝቡ አይቶ … አይቶ ዬጥያቄው መሪ እራሱ የሆነው። ሞቱንም፤ እስራቱንም፤ እንግልቱንም፤ ጥማቱንም ችሎ ትግሉን በትጋትና በቁርጠኝነት ዬቀጠለው። ዬህዝቡ ዬማህበራዊ ንቃተ ህሊና ከፍታ አብሶ ዬአማራ ተጋድሎ – ዬተቃዋሚ ዬፖለቲካ ድርጅቶችን በሙሉ ተመልካች አድርጓቸዋል። ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚያስችል ደረጃ ከጨዋታ ውጪ ነው ያደረጋቸው። ስለምን? ዬብሶትን ውስጥ ዬመተርጎም አቅማቸው የምች ሰለባ በመሆኑ።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መድረክ ላይ ጎልተው ዬሚታዩት ደቡብ ህዝቦችና አረና ናቸው። ሁለቱ እንወክላቸውአለን በሚሉት ቦታ አብሶ አረና በረድ ዬፈሰሰበት ዬፖለቲካ አቋም ላይ ነው ዬሚገኘው። ሁለቱም ዬኦሮሞን ፕሮቴስት እና ዬአማራን ተጋድሎ መስዋእትነት ለቀረመት ያጠመዱት ይመስላል። ሌላው ነገረ ሰማያዊን በሚመለከት  እራስ ሳይጠና ጉተና ነው“ – ለእኔ። ገና ራሱን ለመግራት ጊዜ ያስፈልገዋል። ዬወጣት ዬተስፋ ማህደር ነበር፤ ነገር ግን ዬማይገኙ ወጣቶቹን ገብሮ፤ እያረገረገ መሆኑ እዬተደመጠ ነው። ሌሎች ያው ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ዬጆሮዎቹ ዓይኖች ናቸው። ከቁጥርም ዬማይገቡ። ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ልቡን ዬገጠመላቸው።

አጋጣሚው ጭስ መሆኑ መድረክም ይሁን ያሰባሰባቸው – አንድ ዬሚ/ር ማእረግ ካገኙ ሸብረክ ማለታቸው አይቀሬ ነው። ለሰላማዊ ትግል ጽናታቸው አዎንታዊ አስተምህሮ ቢኖረውም፤ ለስላሳና ወጣ ገብ ዬፖለቲካ አቋም ያላቸው ሊቃናት እንዳሉ ይታወቃል። አብዛኛውን ጊዜም ዬአቅም ዬመተርተሬያ ፋስነትም መሆንም አለ። ይህን ደግሞ በስማ በለው ሳይሆን በቀደሙ ሀገራዊ ዬመሰባሰብ ዬአብሮነት ጉዞ ሳንኮችን ሳያቸው ነበር።

እርገት ይሁን …

ዬግራ ፖለቲካ ዬጭቃ እሾህ ፖለቲካ ነው። መግቢያ እንጂ መውጫ ዬሌለው። በዚህ ላይ በአናሳነት ላይ ዬተገነባ ዬጎሳ ስልጣን፥ ይህም ብቻ አይደለም፥ በፍቅረ ንዋይ ልዕልና ዬመሸገ ፖለቲካ፣ እንዲሁም በአማተር ወታደራዊ ሥር ዬወደቀ ፖለቲካ ችግሮቹም ሆነ፤ ዬችግር አመንጪ መፍትሄዎቹ በንፋስ ኃይል በሚመራ ፖለቲካዊ ስሜት አሸንፎ ለመውጣት ኔቱን ዬገመዳቸው፣ ያያዛቸው ሥሮች በጥናት ላይ ዬተመሰረቱ – በተከታታይና በትጋት ዬተከወነ ዬህሊና ብቃትን ይጠይቅ ይመስለኛል። ዬፖለቲካዊ ብቃት ብልጽግናዊ መንፈስ ብልህነትን መሰነቅ – ይኖርበታል። ምራቁን ዬዋጠ – ብቃት።

በተጨማሪም ወቅትን ብቻ ሳይሆን ሊመጡ ለሚችሉ መጠራቅቆች ዬመሰናዶ ትንበያ በእጅጉ ያስፈልጋል። በደራሽ ነገሮች ላይ ሙሉ አቅም ከፈሰሰ፤ ለቀጣዩ ፈተና ዬህሊና ስንቅና ትጥቅ እጥረት ይገጥማል። አቅምም ይበተናል፣ ዬነፃነት ፍለጋ ጉዞው ተረጋግቶ መራመድም ይሳነዋል። ተሰፋ ቆራጭነት ከመጣ ፍርሰት ይገጥማል። ፍርሰቱ ደግሞ እጅ ወደ ላይን አመቻችቶ ይሸልማል።

ዛሬ ዬሚታዬው ዬፖለቲካ ትንታግ ዬአልገዛምባይነት ሙቀት ከመሪዎች ህዝቡ በእጅጉ እዬቀደመ ነው። እዬታዬ ያለውም ይሄው ነው። ዬባለቤትነት ስሜቱ ሽሚያ ላይ ዬመሆኑ ችግርም ይሄው ነው። ዬእኔ ነው ለማለት ከህዝቡ ዬበቃኝ እርምጃ በፊት ዛሬ ዬህዝቡ ዬበቃኝ ማኒፌስቶ ውስጠት ተኮር ላይ ዬቀደሙ ዬዓላማና ዬግብ ውሎች አልነበሩም። እሱ እራሱ በመከራው በቀረጸው ማኒፌስቶ ነው ዬፖለቲካ ድርጅቶች እሰጣ ገባ ላይ ዬሚገኙት። ዬዘራ ዬፍሬው ባለቤትቱን ማንም አይከለክለውም። ግን አልሆነም። ቀድሞ ነገር ይመጣል፤ ሊሆን ይችላል ተብሎ ዬሚተነበይ አመክንዮ አለመኖር፤ ዬተገኙ ትርፎችን በአቅም ግንባታ ተቀማጭ ሃብት አድርጎ ዬማስቀጠል ሆነ፤ ዬአቅም ጥሪቱን ተከታታይነት በአስተማማኝና በጥራት ሁነኛ ዬተስፋ እልፍኝ ዬማድረጉ ነገርም እንዲሁ እንዲያና እንዲህ ነው። ስለሆነም ወያኔን ያህል ጉድጓድ ድርጅት ለመቋቋም ትጥቃችነን ዬምናውቀው እኛው ነን። ለዚህም ነው ዬሴራ መተከዣ፣ ዬሴራ መረማመጃ፣ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስን ቀለብ ያደረግነው። ዬአሁኑ ጅማሮ ከእርቦ ጌጥነት በታች ያነሰ ነው። ይብቃኝ  ….

  • ዬኔታ —- ዬአማራ ወጣት አክቲቢስቶች ለእኔ መምህሮቼ ስለሆኑ ነው – ዬእኔታ ዬምላቸው። ዬዘብሄረን አማራነትን ነገር ገና ፊደል ቆጣሪ ነኝ። ሁሉ ችግር በአንድ ማዕቀፍ ይፈታል ዬሚል ሙሉ ዕምነት ነበረኝ። እውነቱ ግን አንጀዳ ያልሁኑ፤ ባለቤት ዬሌላቸውጉዳዮች እንዳሉ ተገንዝቤያለሁ። ይህ ዬውስጥነት ዬምርመራ ሂደት መጀመሩ በራሱ በእኔ ህይወት፤ አዲስ ምዕራፍ ነው። ዬረዳኝም ዬእነሱ በህይወቱ ውስጥ መኖር ጭብጡ ቀልብን ለመሸለም አቅም ያለው መሆኑ ነው።

ዬማስተዋላችን ጌታ ያድርገን ፈጣሪ። አሜን!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።