የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

ሸንቁጥ አየለ
—————-
-ዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያን 179 አመታት በጨለማ ዘመን ዉስጥ አስሮ አኖራት::በርካታ ሀገራት በተለይም ምዕራባዉያን ወደ ቀጣይ እድገት የተሸጋገሩበትን የግንዛቤ ለዉጥ የጨበጡት እና መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለዉጥ ያመጡበት ወቅት ይሄዉ ኢትዮጵያ በዘመነ መሳፍንት ጨለማ ዉስጥ ስትዳክርበት የነበረዉ ዘመን ነዉ::


-ኢትዮጵያ በታላቁ አጼ ቴዎድሮስ ራዕይ እና ተጋድሎ በዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ የማግባባት ጥበብ እንደ ሀገረ ከተሰባሰበች ብኋላ ከማህጸኗ የሚፈልቀዉ አስተሳሰብ አሁንም ወደ ጨለማ ዘመን የሚጎትታት ሆኗል::ህዝቡን እንደ ዘመነ መሳፍንት በብዙ ንጉሶች እና ገዥዎች ለመቀጥቀጥ እና ሀገሪቱን ለመበተን የሚጮህ ከፉ መንፈስ ጉልበት ያገኘ ይመስላል::


-የኢትዮጵያን ህዝብ እግዚአብሄር ኢትዮጵያ ብሎ የጠራዉ አንድ ህዝብ ነዉ::መልኩ እና መልከዓምድሩን ባህሪዉን እና ማንነቱን ሁሉ መጽሀፍ ቅዱስ ዘርዝሮ የዘገበለት ህዝብ ነዉ:: ሆኖም የኢትዮጵያ ምሁር እና ፖለቲከኛ ተብዬዉ ኢትዮጵያዊነትን እንኳን በተባለዉ ደረጃ ሊያከብረዉ ቀርቶ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ነጋ ጠባ እንደተጨቃጨቀ ይሄዉ አመታታ አለፉ:: አንዱ ጎሳ ከሌላዉ ጎሳ የተለዬ እንደሆነ የሚሰብኩ እና ጥላቻን የሚዘሩ ፖለቲከኞች ምድሪቱን ቀስፈዉ ከያዟት ይሄዉ 50 አመታት አለፋቸዉ:: ወደ ፊት በማዬት የነገን የጋራ በረከት ብሎም በመላዉ አለም እየፈለቀ ያለዉን የቴክኖሎጂ ጸጋ ህዝባቸዉ እንዲጠቀምበት ከማድረግ ይልቅ ኢትዮጵያዉያን ለታላቅ የመጠፋፋት መንፈስ እንዲነሳሱ ልዩነት እና ጥላቻን ሰባኪ በዝቷል::


-ቢልጌት እና ታላላቅ የምድራችን ተጽእኖ ፈጣሪዎች እንደሚተነብዩት የሰዉ ልጅ በ2025 ዓም አጠቃላይ የህይወት እንቅስቃሴዉ በቴክኖሎጂአዊ ቀመር በእጅጉ ይለወጣል:: ይሄ የሚሆነዉ ታዲያ አሁን በቴክኖሎጂዉ ላይ በጥልቀት ሳያሰልሱ እየሰሩ ባሉ ህዝቦች እና ሀገራት ዘንድ ነዉ::


-ኢትዮጵያስ? የኢትዮጵያ ጉዳይ እማ አሁንም ወደኋላ መጎተት ሆኗል::ቴክኖሎጂ ላይ መስራት እና ከቴክኖሎጂ ጋር ህዝቡ መተዋወቁ ቀርቶበት የሚግባባበት የጋራ ሀገር; የጋራ መንፈስ እና ቃላት እንኳን አጥቷል::አሁን ያለዉ ትዉልድ እርስ በርሱ ሊግባባ ቀርቶ ቀድመዉ ከነበሩ የታሪክ ተዋንያን ጋርም ተጣልቷል:: የተሰራለትን ሀገር በምስጋና ተረክቦ የተሻለ ዲሞክራሲያዊ ሀገር አድርጎ ለመስራት በመግባባት ከመስራት ይልቅ ሀገሩን በመከራ ዉስጥ አልፈዉ የገነቡ አባቶችን ምላሱን እያወጣ መሳደቡን ቀጥሏል::የሰፈነዉ ሀገራዊ መንፈስ እጅግ አስጨናቂ እና አስፈሪ ነዉ::


-ይሄን ያስተዋለ እና ጭቅጭቅ የሰለቸዉ አንዳንድ ሰዉ ታዲያ አብረን መኖር ካልሆነልን ለምን አንለያይም ሲል ሀሳብ ያቀርባል:: ግን ጥያቄዉ የኢትዮጵያ ሰዉ ቢለያይስ አሁን በሀገር ደረጃ ያለዉ የመለያዬት እና የጥላቻ መንፈስ ወደ እዬ ነገዱ አይወርድም ወይ? ደግሞስ እዉነት ለመለያዬት ኢትዮጵያኖች ቢወስኑ እርስ በርስ የሚያጫርሳቸዉ ብዙ ነገር የለም ወይ? አንዳንዱ እንደሚያስበዉ እያንዳንዱ ቁራጭ መሬት እያንጠለጠለ መሮጥ ይቻላል ወይ? ይሄኛዉ መሬት የዚያኛዉ ጎሳ/ነገድ ብሎ እርኩስ መንፈስ የሰፈረበት ወያኔ እንደከለለዉ ሀገሩ ሲፈርስ ህዝቡ ተስማምቶ ይሄ የኔ ያኛዉ ያንተ ብሎ ምድሪቱን መከፋፈል ይችላል ወይ?መለያዬትስ አብሮ ከመኖር ቀላል ነወይ? ከቶስ ኢትዮጵያ ብትፈራርስ አትራፊ ወገን አለ ወይ? አሁን ነገር እና ጥላቻ የሚጎነጉነዉን ፖለቲከኛ እና ምሁር አብሮ መኖር ያላስማማዉ መለያዬት ሊያስማማዉ ይችላል ብሎ ማሰብ ይቻላል ወይ?


ዋናዉ ጥያቄ ግን እንዲህ የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እንኳን ለታላቁ የአድዋ ድል ፻፳፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል አደረሳቹህ!

በእርግጠኝነት የክብርን፣ የኩራትን፣ የማንነትን፣ የሉዓላዊነትን፣ የፍትሕን፣ የሰብአዊ መብትን ወዘተረፈ. ዋጋና ምንነት የሚያውቅ የየትኛውም ሀገር ዜጋና ኢትዮጵያዊ ልብ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉም ስለ አድዋ ድል ሲሰማና ሲያወራ ልቡ በኩራት ይሞላል፣ መንፈሱ ይነቃቃል፣ ለአድዋ ድል ታላቅ ክብር ይሰጣል፡፡
ይሄ ድል እከሌ ከእከሌ ሳይባል በወቅቱ የነበረው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሰልፎ ያስመዘገበው አንጸባራቂ ድል ነው፡፡ ይሄንን ታላቅ ዓለማቀፋዊ ድል ለመቀዳጀት ፈተና የነበሩት ነገሮች ምን ምን ናቸው? ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ተገኘ? የዚህ ታላቅ ድል ትሩፋቶችስ ምን ምን ናቸው? የዚህ ድል ጠላቶችስ እነማን ናቸው? ይህ ድል እንዴት ይጠበቃል? ብዙ ቢባልለት ከማይበቃው ከአድዋ ድል እነዚህን ነጥቦች ብቻ ነጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡

ፋሽስት ጣሊያን በዘመነ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ተቆጣጥሮት ከነበረው የባሕረ ምድር (በኋላ ላይ ፋሽስት ጣሊያን ኤርትራ ሲል ከሠየማት) አልፎ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከእሳቸው ቀጥለው እንዲነግሡ በማሰብ ሊሞቱ በሚያቃትቱበት ወቅት “ወራሸ እሱ ነው ለእኔ ያደረጋችሁትን ሁሉ ለእሱም አድርጉ!” በማለት ተናዘውላቸው የነበሩትን የትግሬውን ገዥ ራስ መንገሻን ድል አድርጎ ሠራዊታቸውን ከበተነ በኋላ አልፎ መላዋን ሀገራችንን ቅኝ ለመግዛት ወደ መሸገባቸው ቦታዎች ወደ አንባ አላጌ፣ መቀሌ እንዳኢየሱስና አድዋ ዐፄ ምኒልክ “ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት!” ብለው አውጀው በመዝመት እነዚያን አኩሪ ድሎች ከማስመዝገባቸውና ታሪክ ከመሥራታቸው በፊት በዋዜማው እነኝህን ድሎች በፍጹም እንዳንቀዳጃቸው የሚያደርጉ እጅግ ከባባድ ፈተናዎች ደርሰውብን ነበር፡፡ የአድዋን ድል በሌሎች ሀገራት ከተገኙት ድሎች ልዩ የሚያደርገውም ይሔው ነው፡፡ እነዚህ ፈጽሞ ሊታለፉ የማይቻሉ መሰናክሎችን ታልፎ የተገኘ እጅግ አስደናቂ ድል በመሆኑ፡፡

የአድዋን ድል ለመቀዳጀት አያስችሉ የነበሩት ፈተናዎች ምን ምን ናቸው፡-
የከብት እልቂት፡- ፋሺስት ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ቅኝ ለመያዝ ሲያስቡ ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካና እስያ በቀላል ግጭት ቅኝ ሀገር መያዝ እንደቻሉ ሁሉ በኢትዮጵያ ይህ መልካም ዕድል እንደማያጋጥማቸው ጠንቅቀው ዐውቀውት ነበር፡፡ በመሆኑም ጦርነት መግጠማቸው የማይቀር ከሆነ የኢትዮጵያንና የመንግሥቷን አቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ነደፈ፡፡ ከስልቶቹ አንዱም የሀገሪቱ አቅምና ሀብት መሠረት የሆነውን ግብርናዋን ማሽመድመድ መጉዳት ነበር፡፡ ይህንን ሲያስቡ ግብርናዋን ለመጉዳት ማድረግ የሚኖርባቸው ነገር ሆኖ ያገኙት የከብት ሀብቷን መጨረስ ነበር፡፡ ይህንን ለመፈጸም ሲባል ከህንድ ሀገር ሶስት የታመሙ ከብቶችን በምጽዋ በኩል አስገብተው ከደማቸው እየወጉ የኞቹን ደኅናዎቹን ከብቶች በመውጋት አደገኛውን የከብት በሽታ አጋቡባቸው፡፡ በሽታውም በአጭር ጊዜ ተዛምቶ ከኢትዮጵያም አልፎ እስከ ታንዛኒያና አጠቃላይ የቀጠናውን ከብት ፈጀው፡፡ ውጤቱም ፋሽስቶቹ ከጠበቁት እጅግ የበዛ ሆኖ በሀገራችን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ‹‹ክፉ ቀን›› በመባል የሚታወቀውን ረሀብና ችጋር አመጣ፡፡ የሚበላ ነገር ጠፍቶ የዋልካ አፈርና ሳር ቅጠሉ ሁሉ የተበላበት ዘመን ነበር፡፡ ሕዝቡ አለቀ ሀገሪቱ ተሽመደመደች፡፡

የስንቅና ትጥቅ (logistics) ዝግጅት እጅግ ውስንነት፡- ፋሽስት ጣሊያን በወቅቱ ኃያላን ከሚባሉ የአውሮፓ ሀገራት አንዱ ነበረ፡፡ እንደ ኃያልነቱም ከ20 ሺ በላይ ለሆነው ላሰለፈው ጦሩ ዘመናዊ መሣሪያ በነፍስ ወከፍ ከማስታጠቁም ባሻገር ሠራዊቱ በወጉ የተደራጀ ዘመናዊ የውትድርና ሥልጠና የወሰደ ባጠቃላይ ከበቂ በላይ የስንቅና ትጥቅ ዝግጅት የነበረው ነበር፡፡ በእኛ በኩል የነበረው ደግሞ ባጋጠመው የረሀብና አስከፊ ችጋር የደከመ የባላገር ሠራዊት ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ የሆነ የስንቅና ትጥቅ አቅርቦች ችግርም ነበረበት፡፡ በወቅቱም ሠራዊቱ ነፍሱን ለማቆየት በቀን እጅግ መጥኖ ከሚቀምሳት በየ አገልግሉ ቋጥሮ ከያዛት ጥቂት ዳቦቆሎ፣ የደረቀና የሻገተ ቂጣ፣ ቆሎና በሶ የመድኃኒት ያህል ጥቂት ጥቂት የሚቀምስ ሠራዊት ነበረ እንጅ የስንቅ አቅርቦቱን አስቦ በየ ዕለቱ አብስሎ የሚቀርብለት ሁኔታ አልነበረም፡፡ ሰራዊትም ሲባል ሐበሻ እንዲያው በተፈጥሮው ተዋጊ በመሆኑ እንጅ ሊገጥመው እንደተዘጋጀው ጠላቱ ሠራዊት በወጉ የወሰደው ዘመናዊ የውትድርና ትምህርት ጨርሶ አልነበረም፡፡ የታጠቀው መሣሪያም ቆመህ ጠብቀኝ በመባል የሚታወቁ ኋላ ቀር መሣሪያ ሆኖ ይሄንንም ቢሆን የያዙት ከሠራዊቱ እጅግ ጥቂቶቹ ነበሩ የተቀረው ግን የያዘው ጦርና ጋሻ ጎራዴ ነበር፡፡ ይሔም አይጠቅምም ማለት ሳይሆን በጦር በጎራዴና በጋሻ ውጊያ የሚደረግበት ዘመን አልፎ ከሩቁ ጠላትን መልቀም ማስቀረት የሚቻልባቸው ከመድፍ እስከ መትረየስ ያሉ ዘመናዊ መሣሪያዎች የነበሩበት ዘመን በመሆኑ ለሚደረገው ጦርነት የጦር የጎራዴ እና የጋሻ ጥቅምና አገልግሎት እጅግ በጣም ውስን ሆኖ ነበር፡፡ ጦርነት በጦር በጎራዴ ይደረግ የነበረበት ዘመን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እጅግ የቀና የበጀና የተመቸም ነበር፡፡

የባንዶች ሚናና የጠላት የመከፋፈል ስልት፡- ፋሽስት ጣሊያን የኢትዮጵያን ሠራዊት ለማዳከም ከተጠቀመበት ስልት ሌላኛው ባላባቶችንና መሳፍንቱን እስከ ራሶች ድረስ እንዲከዱ በማድረግ የትግሬ መሳፍንትንና ባላባቶችን ከጎኑ ማሰለፍ መቻሉ ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ የከዱና ከነሠራዊታቸው ለጠላት በባንድነት የተሰለፉ መኳንንት ከጣሊያን በኩል የጠበቁትንና የፈለጉትን አቀባበልና መስተንግዶ እንዳላገኙና እንደማያገኙም ሲገባቸው የዐፄ ምኒልክ ይቅር ባይነት ዋስትና ሆኗቸው ብዙዎቹ ተመልሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ እነኝህ ከድተው የነበሩ ሹማምንት መመለሳቸው የእውነት ከልብ ነው ወይስ ለተልዕኮ? የሚለው ጉዳይ ለወገን ሠራዊት በወቅቱ እጅግ አንገብጋቢ ጥያቄና እውነቱን ለመረዳት ከመቸውም አጋጣሚ በበለጠ አምላክነትን የሚያስመኝ፤ ሥጋት ጥርጣሬውም እረፍትና እንቅልፍ የሚነሳ አምኖ ከጎን ለማሰለፍም ለመተውም እጅግ ያስቸገረበት ጉዳይ ሆኖ ነበር፡፡
የፋሽስት ጣሊያን ጦር መሽጎ የሚጠብቅ መሆኑ፡- ጦርነት በሚደረግበት ወቅት ጦርነት ከሚያደርጉት ባላንጣ አካላት አንደኛው ምሽግ ይዞ የሚጠብቅ ከሆነ ጦርነቱ ለአጥቂው ወይም ምሽግ ላልያዘው ክፍል እጅግ ከባድና አስቸጋሪ የሚያስከፍለው ዋጋም ከመሽገው አካል ጋር ሲነጻጸር በጣም የሚበዛ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ እኛንም ያጋጠመን ይሄው ነበር በሦስቱም ቦታዎች የጠላት ጦር ምሽጉን በሚገባ ገንብቶ ከምሽግ ማዶም በባዶ እግሩ የሚጓዘውን አርበኛ ሠራዊት እግር እንዲቆራርጥ በጠርሙስ ስብርባሪና በጦር ችካሎች ከዚያም በደማሚት ፈንጅ የታጠረ ምሽግ ውስጥ ሆኖ አድፍጦና መሽጎ ይጠብቅ የነበረ ጦር ከመሆኑ የተነሣ የጠላትን ጦር ከዚህ ምሽጉ ለማስወጣት ምን ያህል መሥዋዕትነት ሊጠይቅና ሊያስከፍል እንደሚችል መገመት ቀላል ነው፡፡ እንኳንና ተመጣጣኝ ትጥቅ ሳይያዝ ቢያዝም እንኳ ሁኔታው እጅግ ከባድ ነው፡፡ በዚህ ላይ የእኛ ጦር ዘመናዊ የውጊያ ስልት ካለመማሩ ጋር ተያይዞ ተኝቶ መሬት ላይ በመሳብ መተኮስን እንደ ነውርና ፈሪነት አድርጎ የሚቆጥር በመሆኑ ደረቱን ሰጥቶ በከፍተኛ ድፍረትና ወኔ እደፎከረና እያቅራራ ይዋጋ የነበረ ጦር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መሥዋዕትነቱን እጅግ የከበደ አድርጎት ነበር፡፡ በጣም አስገራሚው ነገር ግን ተአምር ሊባል በሚችል ሁኔታ ከነዚህ ነባራዊ ሁኔታዎች አኳያ ከጦርነቱ በኋላ የደረሰብን የሟችና ቁስለኛ መጠን በጠላት ሠራዊት ከደረሰው እምብዛም የሚበልጥ አልነበረም፡፡

የህክምና አገልግሎት ችግር፡- እንዲህ ዓይነት የሕዝብ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወረርሽኝ ይከሰታል፡፡ ወረርሽኝ ሲከሰትም ለዚህ ጉዳይ ቀድሞ የተዘጋጀ የህክምና አገልግሎት ከሌለ ከባድ ጥፋት አስከትሎ ያልፋል፡፡ የወገን ጦር ይሔንን አደጋ መከላከል የሚችልበት አቅምና ዝግጅት አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ቁስለኛን እንኳን ማከም የምንችልበት መድኃኒትና የሠለጠነ ባለሙያ አልነበረንም ሁሉም ለየራሱ ሐኪም ነበረ፡፡ አስተናግር ቅጠሉን ጨምቆ አዘጋጅቶ በቅል ይዞት የመጣውን ቁስሉ ላይ እያፈሰሰ እርስ በራሱ ለመተካከም ይሞክራል እንጅ ይሔንን ጉዳይ የሚከውን የህክምና ባለሙያዎች ቡድን አልነበረም፡፡

እንግዲህ እነዚህና ሌሎች ሊታለፉ የማይችሉ እንደተራራ የገዛዘፉ ከባባድ ደንቀራዎችን ፈተናዎችን በረድኤተ እግዚአብሔር፣ በሐበሻነት ጽናት እናት አባቶቻችን አልፈው ነው የአንባላጌውን፣ የመቀሌውንና በመጨረሻም የአድዋውን ድል ለመቀዳጀት የተቻለው፡፡ የአድዋ ድል በሌሎች ሀገራት ዜጎች ዘንድም ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረውና የሚከበረውም ከዚህ ከዚህ የተነሣ ነው፡፡

ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ሊገኝ ቻለ?፡- ለድሉ መገኘት ትልቁ ድርሻ የእግዚአብሔር ረድኤት ቢሆንም እግዚአብሔር ሲሠራ በምክንያት ወይም መሣሪያ የሚያደርገው ነገር መኖሩ አይቀርምና ለእናት አባቶቻችን ቁርጠኝነትን፣ ጽናትን፣ መጨከንን ሰጥቶ ከቶውንም የማይታለፉትን ፈተናና መከራን አስተናግዶ ተሽመድምዶም ደክሞ ደቆ የነበረ ሕዝብ እንደምንም የሞትሞቱን ተነሥቶ እንዲህ ዓይነት አስደናቂ ድል ለማስመዝገብ በቃ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ድል ለማስመዝገብ ሐበሻ ሆኖ መገኘትን የግድ ይጠይቅ ነበር አደረገውም፡፡ በመሆኑም “ነፃነት ወይም ሞት!” “ባሪያ ሆኖ ከመኖር ነፃ ሆኖ መሞት!” የሚለው የጨከነ መርሑ ከፊቱ የተደቀኑ ገዛዙፍ ፈተናዎችን መሰናክሎችን ከነ አካቴው ከግምት ውስጥ እንዳያስገባ አድርጎት በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ጽናት በመዋጋቱ ድሉን ሊያገኝ ቻለ፡፡

የዚህ ታላቅና አንጸባራቂ ድል ትሩፋቶች ምን ምን ናቸው? ይህ ታላቅ ድል ከእኛም አልፎ ለመላው ዓለም ጭቁኖች በርካታ ትሩፋቶችን አበርክቷል ከእነዚህ በርካታ ትሩፋቶቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡-

\1. የቀለም ልዩነትን መሠረት ያደረገው የብቃት ደረጃ ልዩነት የተሳሳተ አስተሳሰብ ፉርሽ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል፡፡ ከዚህ ድል አስቀድሞ ጥቁር ሲባል ሰብአዊ እሴት አልባ፣ ለባርነት የተፈጠረ፣ ሥልጣኔ የማይገባው አድርገው ያስቡት ነበር፡፡ ከዚህም አልፈው “ተናጋሪ እንስሳ!” እያሉ ይገልጹትም ነበር፡፡ ጥቁሮቹ እናት አባቶቻችን ግን ፈጽሞ ሊታለፉ የማይቻሉ ፈተናዎችን አልፈው ለክብራቸው ለነፃነታቸው፣ ለሉዓላዊነታቸው የማይችሉት ነገርም እንኳን ቢሆን “አንችለውምና ምን እናድርግ?” ብለው ክብራቸውን፣ ነፃነታቸውን፣ ሉዓላዊነታቸውን ለድርድር ሳያቀርቡ ለሰብአዊ ክብራቸውና ለማንነታቸው ታይቶ በማይታወቅ ቀናኢነት በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ ማንኛውም ዓይነት የሰው ዘር “አደርገዋለሁ!” ብሎ ሊሞክረው ቀርቶ ሊያስበው በማይችለው እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በግሩም ችሎታና የአጨራረስ ብቃት ከውኖ በማሳየቱ “ጥቁር… ነው!” እየተባለ ዝቅ ተደርጎ ይቆጠርና ይታይ የነበረው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑን የግዳቸውን እንዲያምኑ አድርጓል፡፡

2. የነፃነት ትግልን አነቃቅቷል ቀስቅሷል፡- ጥቁር አፍሪካውያን ለአምስት ምእተ ዓመታት ያህል በግፈኛ ነጮች ሲሰበክላቸው የኖረውን የጥቁርን ተገዥነት ወይም ለአገልጋይነት መፈጠር አምኖ ተቀብሎ፣ ሰጥ ለበጥ ብሎ የመገዛትን አስተሳሰብ አዳብሮ ወደ አውሮፓና አሜሪካ እየተጋዘ እየተሸጠ እየተለወጠ ይገዛ ያገለግል ነበር፡፡ ሐበሾቹ ጥቁሮች አድዋ ላይ ያበሩላቸው ፀሐይ ግን ይሄንን የጨለመ አስተሳሰብ ጠራርጎ በማጥፋቱ የነጻነት ትግልንና የነፃነት ታጋዮችን በየስፍራው በየአቅጣጫው እንዲቀጣጠል አድርጎ እነሆ ዛሬ ላይ ያን ሁሉ ግፍ በጥቁርነቱ ብቻ ይጋት የነበረው የሰው ዘር ነጻነቱን አረጋግጦ ቢያንስ በገዛ ሀገሩ እንኳን እንደ ሰው መኖር የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር እንዲችል አብቅቷል፡፡

3. የተረሳውን ታሪካችንን አስታውሷል፡- ሐበሻ (የአቢስ ሕዝብ) እንደሕዝብና እንደ ሀገር ከማንም የቀደመ የሥልጣኔና የመንግሥት ታሪክ ያለውና የነበረው ሕዝብ ነው፡፡ ይህ ግን በወቅቱ በነበረው አስገዳጅ ችግር ሳቢያ ከዐፄ ፋሲል ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ በነበረው ዝግ መመሪያ (closed policy) ምክንያት ዓለም እኛን እኛም ዓለምን ረስተን ተረሳስተን ስለነበረ ዓለም በየጊዜው መረጃውን እያደሰ እንዳወቀን እዲቀጥል ማድረግ ሳንችል ቀርተን ነበር፡፡ የአድዋ ድል ግን ዓለም ስለኛ ያለውን መረጃ ካጎረበት እያወጣ እንዲያወራ “…. እኮናቸው! እንዲህእኮ ነበሩ!” እያለ እንዲያወራ አድርጎታል፡፡ ያወሩልን ይጽፉልን ከነበረው ታሪኮቻችን የሚበዛው እኛም እንኳን እራሳችን የማናውቃቸው ናቸው፡፡
4. የሕዝባችንን አንድነት አጽንቷል፡- የጠላት ወረራ ለመኳንንቶቻችንና ለመሳፍንቶቻችን ትልቅ ትምህርትን ሰጥቷል፡፡ በአንድነት የመቆምን አስፈላጊነት የአንድነትን ጥቅም በሚገባ አስገንዝቧቸዋል፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ከዘመነ መሳፍንት ጀምሮ በመሳፍንቱና በባላባቶች ዘንድ የየራሳቸውን ጎጥ እንደ ሀገር በመቁጠር የየራሳቸውን ‹‹ሀገር›› የመመሥረት የማይጠቅምና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ያስቡ ነበር፡፡ ይህን የትም የማያደርስ ኋላቀርና የደነቆረ አስተሳሰብ ለማጥፋት ዐፄ ቴዎድሮስን እጅግ አድክሟል፡፡ በዐፄ ቴዎድሮስ እጅ ያደጉት ዐፄ ምኒልክ 2ኛም የዐፄ ቴዎድሮስ 2ኛ ሕልም ገብቷቸው ስለነበር ጥረታቸውና ሁኔታዎች ፈቅደውላቸው ቀሪውን የዐፄ ቴዎድሮስን ሕልም ለማሳካት ችለዋል፡፡ የአድዋ ድልም ለመሳፍንቱ የማይረሳ ትምህርትን ስለጣለላቸው ከዚያ በኋላ አስቀድሞ የነበረው ዓይነት የመሳፍንት አስተሳሰብ እንዳይኖር አድርጓል፡፡
5. ለቀጣይ ትውልድ ታሪክ እንዴት እንደሚሠራና እንደሚጠበቅ ምሳሌነቱን ትቶ አልፏል፡- ሀገራችን ከ4500ዓመታት በላይ የመንግሥት ታሪክ አላት፡፡ እንደ ሀገር ከቆመችበት ጊዜ ጀምሮ ነጻነቷን ለመንጠቅ ተደጋጋሚና አደገኛ ፈተናዎችን አሳልፋለች፡፡ እነዚሁ ጣሊያኖች በቀደመው ስማቸው ሮማዊያን ከቄሳሮች ዘመን ከሁለት ሽህ ዓመታት በፊት ጀምረው ሲፈታተኑን ኖረዋል፡፡ የአድዋ ድል እናት አባቶቻችን የዚህችን ሀገር ነጻነት እንደምን ባለ መሥዋዕትነት አስጠብቀው እንደቆዩና ይህ ረጅም ታሪኳ እንዴት እንደተሠራ የቅርብ ጊዜ ምሳሌነት የተወ ድል ነው፡፡ በደካማ ጎን መግባት የሚችሉበት ጠላቶቻችን ግን የትግል ስልታቸውን በቀጥታ ከሚተኮሰው አፈሙዝ ወደ ተለየ ዓይነት የማጥቃት ስልት በመለወጥና ባንዶችን በማሠማራት የአድዋ ድል ከተወልን ምሳሌነት ልንማርና እኛም የድርሻችንን ታሪክ ልንሠራ የምንችልበትን ዕድል አጥበውት ሀገርን፣ አንድነትን፣ ታሪክን፣ ነጻነትን፣ ሉዓላዊነትን፣ ክብርን መሠረቱ ያላደረገ የየግል ዓላማና አስተሳሰብ አራጋቢዎች አድርገውን አንድነታችንን አደጋ ላይ ጥለውታል፡፡ በዚህ ረገድ እየተሳካላቸው ይገኛል፡፡ ፈጣሪ ይቅደምልን እንጂ የዚህ ውጤት ደስ የሚያሰኝ አይሆንም፡፡

6. የታሪክ ሀብትን ትቶልናል፡- አንዲት ሀገር ዜጎቿ ጠንካሮች ከሆኑ ሁለቱም ሀብቶች ይኖሯታል ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብቶች፡፡ ታሪክ መንፈሳዊ ሀብት ነው፡፡ ታሪክ ወኔን፣ መነቃቃትን የሚፈጥር ታላቅ አቅም ያለው ኃይል ነው፡፡ ታሪክን በአግባቡ ማሰብ መዘከርና ማስተላለፍ ከተቻለ ሁሌም የሚመጣውን ትውልድ ለሀገሩ ሊከፍለው የሚገባውን መሥዋዕትነት ዓይኑን ሳያሽ እንዲከፍል “እኔስ ለሀገሬ ምን ሠራሁ?” ብሎ እራሱን እንዲጠይቅና የድርሻውን አበርክቶ ለማለፍ እንዲተጋ እንዲጣጣር በማድረግ ኃይልን እልህን ቁርጠኝነትን በመሙላት ጉልበት በመስጠት የማይተካ ሚናን ይጫወታል፡፡ ይሄንንም ስላወቁ ነው ባንዶቹ ጠባብና ደንቆሮ የሆነ ምክንያት ፈጥረው ለታሪክ የሚገባውን ክብርና ትኩረት በመንፈግ፣ ከትምህርት ሥርዓቱ ውጪ በማድረግም ጭምር ትውልዱ ታሪኩን ማንነቱን እንዳያውቀውና እንዲጠፋ ስለተደረገ ነው ለሀገሩ፣ ለማንነቱ፣ ለክብሩ፣ ለሉዓላዊነቱ፣ ለእሴቶቹ ሁሉ ክብርና ዋጋ የማይሰጥ፣ ለግል ጥቅሙ ወይም ለሆዱ ሲል ሀገሩንና የሀገሩን ጥቅሞች ሁሉ ለመሸጥ ዓይኑን የማያሽ፣ የሀገር ፍቅር የሚባል ነገር የማያውቅና የማይገባው ጉደኛ ትውልድ ሊፈራ ሊወጣ የቻለው፡፡

ታሪክ ላወቀበት ቁሳዊ ሀብትንም ለመፍጠር የማይተካ ሚና አለው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለቱም ሀብቶች ነበሯት፡፡ ነበሯት ማለቱ ግድ ሆኗል፡፡ አሁን ላይ ቁሳዊው እንደሌለ ግልጽ ቢሆንም ከላይ እንደጠቀስኩት መንፈሳዊው ሀብታችንም ራሱ ድራሹ እንዲጠፋ በከፍተኛ ትጋት እየተሠራበት ነውና ነበረን ማለቱ ይቀላል፡፡ ሊገባኝ ያልቻለው ነገር ግን ከዚህ ማን? ምን ዓይነት ትርፍ? አንዴት ሆኖ? እንደሚያገኝ፤ ጥቅሙም ምን እንደሆነ ነው፡፡ ማንም ሊገምተው እንደሚችለው ከዚህ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው ጠላት ብቻ ነው፡፡ ለሕዝቡ ልጠይቅ የምሻው አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ የእናት አባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ በዓለም ውስጥ ከነበሩት አራት ኃያላን መንግሥታት አንደኛዋ ነበረች፡፡ ይህች ሀገር ዛሬ የዓለም ጭራ ደሀዋ ሀገር ሆናለች ለምን? ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? እነሱ ጋር የነበረው ጠንካራ ጎን ይህችን ደሀና ደካማዋን ኢትዮጵያ ከፈጠርነው ከእኛ ጋር ግን የሌለውና ደካማ ጎናችን ምንድን ነው? ይሄንን ጥያቄ በትክክል መመለስ የቻልን እንደሆነ ብቻ ነው እንደጥንቱ የኃያልነትን ሥፍራ ልንቆጣጠርና ህልውናችል ሊቀጥል የሚችለው፡፡

7. ዕውቅናና መከበርን አትርፎልናል፡- ይህ ድል የማያውቁን አንዲያውቁንና ሀገር ለሀገር ለሚደረግ ግንኙነት ተመራጭ እንድንሆን አድርጓል፡፡ የሚያውቁንም ይበልጥ እንዲያከብሩን አድርጓል፡፡ ባጠቃላይ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጠላትም እንዲሁ በተመሳሳይ ሳይወድ በግድ ዕውቅናንና ክብርን እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡ የዛሬን አያርገውና ከዚያ በኋላ ለመጣችው ኢትዮጵያም ሞገስን አጎናጽፎ በዲፕሎማሲው (በአቅንዖተ ግንኙነቱ) ተደማጭ ተከባሪ እንድንሆን አድርጓል፡፡

8. ለመሪነት ሚና ተመራጭ እንድንሆን አድርጓል፡- ይህ ድል በሰጠን ዕውቅና ሳቢያ በተለያየ አቅጣጫ የፈጠራቸው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ሀገራት የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት ይህንን እንቅስቃሴያቸውንና ትግላቸውን እንድንደግፍ እንድናስተባብር ለመጠየቅ አስገድዷቸዋል፡፡ ሀገራችንም ይህንን ትግል የመምራቱን ታሪካዊ ኃላፊነት ሙሉ ለሙሉ በማመን ሀገራቱ ነጻ እስኪወጡ ድረስ የራሷን የጦር መሪዎችንና ተዋጊዎችን በማሰለፍ ጭምር የነጻነት ትግሉን ስታግዝ፣ ስታስተባብር ቆይታ የተጣለባትንም አደራ በሚገባ ተወጥታለች፡፡ ለቀድሞው የአ.አ.ድ ለአሁኑ አ.ኅ እና ለሌሎች አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ድርጅቶች መቀመጫነት እንድትመረጥ ያበቃትም የዚሁ ድል ትሩፋት ነው፡፡

9. ሰንደቅ ዓላማችንን እንድንወስን አብቅቷል፡- በእርግጥ ከአድዋ ድል አስቀድሞም የሀገራችን ነገሥታት ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ወይም አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ይጠቀሙ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በአዋጅና በይፍ ዕውቅና ተሰጥቶት ሀገራችንንና ሕዝባችንን እንድትወክል የተደረገው ዐፄ ሚኒልክ አድዋ ላይ ይህንን አንጸባራቂ ድል ከገኙ በኋላ እዚያው አድዋ ላይ አዋጅ አስነግረው “ከእንግዲህ ወዲህ ይህ ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ሰንደቅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይሁን! ከክብር በላይ ክብርን፣ ከፍቅር በላይ ፍቅርን፣ ከአለኝታነት በላይ አለኝታነትን ስጧት!” ብለው በማስነገራቸው ይፋዊ ሰንደቃችን ሆና ለመቀጠል ቻለች፡፡

እንግዲህ በአጭር እንቋጨው እንጅ የአድዋን ትሩፋት እንዲህ በቀላሉ ዘርዝሮ የሚጨረስ ጉዳይ አይደለም፡፡ በመቀጠል የአድዋ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? የሚለውንና ይህንን ቅርስ እንዴት ልንጠብቀው እንችላለን? የሚለውን በአጭር በአጭሩ ዐይተን እንቋጭ ፡፡

የአድዋ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው?

የእድለቢስነት ጉዳይ ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለጠላት የታደለች ሀገር ነች፡፡ በዚህች ሀገር በየትኛውም ሀገር ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለቁጥር የሚያታክቱ ጦርነቶች ከውጭና ከውስጥ በሚፈጠር ቀውስ ሰበብ አስተናግዳለች፡፡ ይህች ሀገር ካስተናገደችው የጦርነቶች ብዛት አንጻር በታሪኳ በአማካኝ ከ10 ዓመታት ያለፈ የሰላምና የእፎይታ ቆይታ ዓይታ አታውቅም፡፡ ተአምር የሚሆንብኝ ነገር ቢኖር ይህንን ያህል የአውዳሚ ጦርነት ዓይነት ያስተናገደች ሀገር ደብዛዋ አለመጥፋቱ፣ የሥልጣኔና የታሪክ አሻራዎቿም ጥቂቱንም ያህል ቢሆን መቆየት መቻላቸው ነው፡፡ አሁን ላይ አስቀድሞ የነበሩን ጠላቶቻችንም ሆኑ ሌሎች አዳዲስ ቢኖሩ ጥቃታቸውን እየፈጸሙብን ያለው እንደቀድሞው በወረራ ሳይሆን በመሀከላችን ልዩነቶች እንዲፈጠሩ በማድረግና እርስ በእርስ በማናቆር በማፋጀት ሆኗል፡፡ ይሄም ይዞላቸዋል፡፡ አርቀውና አስፍተው ማሰብ የማይችሉ አንዳንድ ወገኖቻችን የሀገራችን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ምንም እንኳን እንከን የለሽ ነበር ማለት ባይቻልም በየትኛውም የዓለም ክፍል ከነበረው ተመሳሳይ የመንግሥት ሥርዓት ተሞክሮ ግን እጅግ የተሻለው እንጅ ተመሳሳይ እንኳን እንዳልነበረ፣ በበቂ ምክንያትና አማራጭም በመታጣቱ ለሀገር አንድነትና ህልውና ሲባል የዚህችን ጥንታዊት ሀገርና የሕዝቧን ህልውናና ደኅንነት አደጋ ላይ በጣሉ ወገኖች ላይ አንዳንድ የማያስደስቱን ነገሮች መደረጋቸውን መገንዘብ ማስተዋል የተሳናቸው ወገኖች ለእነኝህ ጠላቶቻችን መሣሪያ በመሆን የሀገራችንንና የሕዝባችንን ህልውና ገደል አፋፍ ላይ አድርሰውታል፡፡ ዛሬ ላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ያሉ የባርነትና ጭቆና ቀማሽ የነጻነት ደጋፊና አቀንቃኞች የሚኮሩበትን የሚያከብሩትን የሚያደንቁትን የአድዋን ድልና ያንን ድል ያስገኙልንን አርበኞች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው በጥላቻ የሚመለከቱ፣ የሚያወግዙ፣ መጥፋት መረሳቱን የሚሹ፣ ለዚህም በርትተው የሚሠሩ ዜጐች ለማየትና ለመስማት በቅተናል፡፡ መፍትሔው ምንድን ነው ትላላቹ?

ይሄንን ቅርስ እንዴት ልንጠብቀው እንችላለን?

ይሄንንና ሌሎች ቅርሶቻችንን ሀብቶቻችንን ታሪኮቻችንን ልንጠብቃቸው የምንችለው ለነዚህ ሀብቶቻችን አንድ ዓይነት መግባባት ሲኖረንና የማይተካ ዘርፈ ብዙ ጥቅማቸው ሲገባን ሀብቶቹ በሚገባ የመጠበቅ ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ በሳል ከሆንን፣ አእምሮ ካለን፣ አርቀንና አስፍተን ማሰብ ከቻልን እዚህ አንድ ዓይነት መግባባት ላይ ላንደርስ የምንችልበት እንዳችም ምክንያት አይኖርም፡፡ ወደራሳችን ወደ ውስጣችን እንመልከት! ለጠላቶቻችን አሳሳች የጥፋት ምክር ጆሯችንን እንድፈን፣ እያደረግነው ያለውን ነገር ከመፈጸሙ በፊት የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ እንመዝን፡፡ እንዲህ እንድናደርግ እንድንናቆር እንድንባላ የሚመክሩን የሚገፋፉን የሚደግፍን ሀገራት በታሪካቸው ከእኛ የከፋ የእርስ በእርስ ሰብአዊ መብት ገፈፋ ዝጋብ (record) ያለባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ነገሥታቶቻቸው ሲያርፉ ጠባቂ እያሉ ሰዎችን ከነነፍሳቸው ግራና ቀኝ ይቀብሩ የነበሩ ናቸው፡፡ የሰው ልጆችን ከአራዊት ጋራ እያታገሉና እያስበሉ ለመዝናኛነት ይጠቀሙ የነበሩ ሀገራት ናቸው፡፡ ይህ ተሞክሮ በሀራችን ፈጽሞ ኖሮ አያውቅም፡፡ ነገሥታቶቻችን ሃይማኖተኞች መሆናቸው ከእንዲህ ዓይነቱ ኢሰብአዊ ግፍ እንዲጠበቁ አድርጓቸዋል፡፡ ዛሬ ላይ እነዚያ ሀገራት እንኳ አንድ ዓይነት መግባባት ደርሰው በአንድነት ቆመው ለሀገራችው ጥቅሞች በአንድ የተሰለፉ ሆነዋል፡፡ እነሱ ለዚህ የበቁ እንደነዚህ ያሉ ዘግናኝና ኢሰብአዊ ድርጊቶችንና አስተሳሰቦችን ዓይተን የማናውቀው እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዴት አንድ ዓይነት መግባባት ላይ ለመድረስ ያቅተናል? ለሀገርና ለሕዝብ እስካሰብን ጊዜ ድረስ ፈጽሞ አያቅተንም፡፡ ሀገርንና ሕዝብን ጠልተንና ንቀን ባንዳነትን ከመረጥን ግን መቸም ጊዜ ቢሆን ልንግባባና የሰላም አየር ልንተነፍስ አንችልም፡፡ በንዶች እንዲህ እንዲጫወቱብን ከፈቀድን የእሳት ልጅ አመድ መሆናችንን እንወቅ!!!
ይህ ጽሑፍ ከዓመታት በፊት ለንባብ የበቃ መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ!
ዘለዓለማዊ ክብር ለአርበኞቻችን!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

የመጨረሻው ምእራፍ 

 

ከታፈረ በድጁ

የያዝነው የፈረንጆች ኣመት በሀገራችን በርከት ያሉ ክስተቶችን እያስተዋልን ያለንበት ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ የወያኔ ዘረኛ ሰርአት ጉዞ የመጨረሻ ምእራፍ ላይ መገኘታችንን በተለያየ መልኩ የሚጠቁሙ ሆነው ይታያሉ።

ሰሞኑን በመቀሌ የኢትዮጵያድንበር ለሽያጭ ቀርቦ ድርድሩ ደርቶአል። ወያኔም በረሃ ሳለች ከሱዳን የበላችውን ቀብድ  ሙሉ የሽያጭ ዋጋ ለመቀበል ከስርአተ ቀብሯ በፊት  ቀን ተሌት ትሰራለች።  ወያኔ ከመለስ የሙት መንፈስ እቅድ ፈቀቅ አላለችም የልቁንም የሙት መነፈሱን እቅድ ሳይበራባት እዳር ለማድረስ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ  ደርሰናል እያለች ነው። የወያኔ ጉምቱ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ባሁኑ ጊዜ በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ስር መቀጠል አለያም ለመበታተን ዝግጅት  እንድታደርግ ካወጁ ሰንበትበት አሉ።

ወያኔ ባወጣችው እቅድ መሰረት ለመስረቅ ያቀደችውን ብድርና እርዳታ ከልክለዋት ትቅበዘበዛለች። እዚህ ላይ ወያኔ ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ላይ መውደቇን በብዙ ማሳያዎች መመልከት ይቻላል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያዎች መነሳቱ ፈገግ ማሰኘቱ የግድ ቢሆንም ምን ያህል እንደሚያዋጣ  ባይገባኝም ጸጉራችንንም ጭምር በመሸጥ ምንዛሪ እስከማግኘት ታቅዳለች። የአስቸኵዋይ ጊዜ አዋጁን ማንሳትም ሆነ ማራዘሙ በሁለቱም ወገን የሚያስከትለውን ውጤት ለመተንበይ የተቸገረችው ወያኔ በብዙ ውጥረት ትዋትታለች። የአዲስ አበባን መሬት የመሸጥ ፕሮጀክቴን ሳልጨርስ የአስቸኻይ ጊዜ አዋጄን አላነሳም ማለትዋን ልብ ይበሉ። ይህ የአዲስ አበባና አካባቢዋ መሬት ሽያጭ ብዙ ያነታረከና የኦሮሞ ወጣቶችን ለትግል ያነሳሳ ክስትት መሆኑን ልብ ይሉዋል። በአዲስ አበባም ብዙ የከተማ ነዋሪዎችን ቤት አልባ ያደረገ ደምም ያፋሰሰ ክስተት መሆኑ አይዘነጋም። ከዚህ ባለፈም የወያኔ ዲያስፖራ ዝምድናን ውል ያቇረጠውን አዲሱን የባንክና ኢንሹራንስ ህግ መመልከቱ ምን ያህል የምንዛሪ እጥረት መኖሩን ያሳየናል።

የተቃዋሚው ጎራ ደግሞ በዘውግ ጡዘት በናወዘ የዲያስፖራ  አባዜ በዚም በዚያም ወገን በመቆም  በከረረ የጎጥ ቅዥት ውስጥ ሲዋትት እንመለከታለን ። እነህዝቅኤል ገቢሳ ለምን ኢትዮጵያ ብላችሁ ተነፈሳችሁ ይሉናል። ሰሞኑን ደግሞ እነሄኖክ የሺጥላ በአማራ ስም ግለሰባዊ ይዘት ያለው መርዘኛ የጥላቻ ቅስቃሳ ስናስትውል ቆየን።

በዘር መደራጀት የወቅቱ ፋሽን በመሆኑ ሁሉም የየዘሩ ጠበቃ ፓርቲ ሲኖረው አማራውስ ለምን ያሉ ደግሞ ሰሞነኛ ሆነው ከረሙ። ተነሳንበት ያሉትን በአማራ ህዝብ ላይ  የተነጣጠረ  ጥቃት መረዳት ብዙም የሚያነጋግር ባይሆንም የመረጡት የትግል ስልት ግን ጥይታቸውን ወያኔ ላይ ያነጣጠሩትን የአንድነት ሃይሎች ላይ ማድረጋቸው በሚምሉበት በኢትዮጵያዊነት አንታማም ጉዞ ላይ ከፍተኛ ብዥታን የፈጠረ ሆኖ ይታያል። በሰከነ የብስለት ጉዞ ስልዩነትን አቻችሎ ሲሆን የጋራ አገራዊ ጥቅምን በማስቅደምና ሃይል ሳይከፋፈል ወያኔን በፈረጠመ ጉልበት የመምታትን አቅም በሚያጎለብት መንገድ ቢሰሩ አለዚያም ሌሎች ለወያኔ ያሉትን ጉልበት በማዳከም የወያኔን እድሜ ባያስረዝሙ የተሻለ ነው።

የሆነ ሆኖ የነገሬን ዋና ጭብጥ ግልጥ ባለ መንገድ ለማስቀመጥ የዚችን መከረኛ አገር መከፋፈል ላልተመኘና በኢትዮጵያ ለሚያምን ሁሉ በምንም ይደራጅ መምንም ኣይኑን ከወያኔ ለማንሳት ለኣፍታ እንኳን ለማሰብ ጊዜው ባለቀበትና የመጨረሻው ደወል ወደተቃረበበት ጉዞ ስናመራ ብዙ ትኩረትን የሚሹ ነገሮችን መመልከት የግድ ይላል።

ወያኔ የቆሰለች አውሬ ናት ቢቻላት ከዳር እስከ ዳር ደም አቃብታን ስንጫረስ  ጥግ ለመያዝ መስራትዋን አንርሳ። መላ ሀገሪቱን ከዳር እስከዳር ያናወጠው የተቃውሞ ማዕበል ያስገኘውን ውጤት ካለበት ደረጃ ወደታለመለት ወደመጨረሻው የወያኔ ማክተሚያ ምዕራፍ በማድረስ ለዚህ ትግል ውድ ህይወትና ሌላም ክቡር መስዋዕትነት የከፈሉትን ኢትዮጵያውያን ውጥን ከግብ እናድርስ። ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ከጥንት አስከዛሬ ከባንዲራዋ ስር የወደቁትንና በመውደቅም ላይ ያሉትን ጀግኖቻችንን በመመልከት የጋራ ጥቅማችንን ለጠላት አሳልፈን አንስጥ።

እግዚአብሄር ሀገራችንንኢትዮጵያን ከክፉዎች ጥፋት ይጠብቅልን

Politically Motivated Charges Against Ethiopian Opposition Leader

Arrest Came After Hearing in European Parliament

Three months after Ethiopian security forces arrested opposition leader Dr. Merera Gudina upon his return to Ethiopia, following his participation in a hearing at the European parliament about the crisis in his home country, prosecutors on Thursday charged the prominent 60-year-old politician with rendering support to terrorism and attempting to “disrupt constitutional order.” Ethiopian marathon runner Feyisa Lelisa and the head of the banned opposition group Ginbot 7, Dr. Berhanu Nega, had also participated in the hearing that had been hosted by Member of the European Parliament Ana Gomes, and which was to inform delegates about the protests that have swept through Ethiopia since November 2015. Hundreds of people have been killed and tens of thousands detained since these protests began. Merera is now at Maekelawi, a prison where mistreatment and torture are commonplace.

Dr. Merera Gudina briefing the European parliament about the crisis in Ethiopia on November 9, 2016.

Dr. Merera Gudina briefing the European parliament about the crisis in Ethiopia on November 9, 2016.

Merera is the chair of the Oromo Federalist Congress (OFC), a legally registered political opposition party. He joins many other senior OFC leaders facing terrorism charges over the last 18 months. Among those presently standing trial is OFC deputy chairman Bekele Gerba. Prosecutors included as evidence of his crimes a video of Bekele at an August 2016 conference in Washington, DC, where he spoke of the importance of nonviolence and commitment to the electoral process. Like Merera, he has been a moderate voice of dissent in a highly polarized political landscape.

Merera and Bekele join a long list of opposition politicians, journalists, and protesters charged under the 2009 anti-terrorism law, regularly used to stifle critical views of governance in Ethiopia. Acquittals are rare, credible evidence is often not presented, and trials are marred by numerous due process concerns.

During the state of emergency – called by the government in October 2016 in response to the crisis and to crush the growing protests – the Ethiopian government publicly committed to undertake “deep reform” and engage in dialogue with opposition parties to address grievances. Instead of taking actions that would demonstrate genuine resolve to address long-term grievances, the government again used politically motivated charges to further crack down on opposition parties, reinforcing a message that it will not tolerate peaceful dissent. This raises serious questions regarding the government’s commitment to “deep reform” and dialogue with the opposition. Instead of responding to criticism with yet more repression, the Ethiopian government should release opposition politicians jailed for exercising their basic rights, including Bekele and Merera. Only then can a meaningful and constructive dialogue with opposition parties take place that can begin to address long-term grievances.

 

ሰማያዊ ፓርቲ መሰንጠቅ አልገጠመኝም አለ

ዋዜማ ራዲዮ- በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ያገኘው አዲሱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር በፓርቲ ውስጥ መስንጠቅ አለመከሰቱን ይልቁንም ፓርቲው በዲስፕሊንና በምዝበራ ጥፋተኛ ያላቸው የአመራር አባላት ላይ እርምጃ የወሰደበት እንደነበረ አስታወቀ።
ለፓርቲውና ለቀድሞ አመራሮች ክብር ሲባል ጉዳዩን በዝምታ ይዞት መቆየቱን የገለፀው አዲሲ የፓርቲው አመራር ችግሩን በፓርቲው ውስጥ ለመፍታት የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ጉዳዩ ወደ አደባባይ መውጣቱንና በአሁኑ ወቅት ፓርቲው በአብላጫው የቀድሞ አመራር አባላትን ይዞ ስራ መቀጠሉን ገልጿል። ዝርዝር ዘገባው የሚከተለው ነው።

የካቲት 8/2009 በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተቸረው የሰማያዊ ፓርቲ አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ በዛሬው ዕለት (የካቲት 19/2009) በጽ/ቤቱ በሰጠው የፓርቲው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ፣ የፓርቲው የቀድሞ የፓርቲ መሥራችና የሥራ አስፈፃሚ አባላት የነበሩ፣ እንዲሁም አሁን የብሔራዊ ምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ጌታነህ ባልቻ “ተከስቶ የነበረው ችግር መከፋፈል ሊባል አይችልም” በማለት አስተባብለዋል። “ጥቂት ሰዎች በዲሲፕሊን እና በንብረት ምዝበራ ቢሰናበቱም፣ አሁንም 37 ቋሚ እና 13 ጊዜያዊ አባላት ያሉት ብሔራዊ ምክር ቤት አለ። ሥራ አስፈፃሚውም የጠቅላላውን ጉባዔ እና የምርጫ ቦርድን ዕውቅና አግኝቷል” ብለዋል።

በአዲሱ የፓርቲው ሊቀ መንበር አጭር የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው የማብራሪያ መድረክ፣ የተለያዩ ሰነዶችን በማቅረብ በቀድሞው ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል እና ደጋፊዎቻቸው፣ እንዲሁም በአቶ የሺዋስ አሰፋ የሚመራው አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ መካከል የነበረው ችግር በቀድሞው ሥራ አስፈፃሚ ድክመት የተፈጠረ እና አሁን ግን እልባት ያገኘ መሆኑን ለማስረዳት ሞክሯል።

 

አቶ የሺዋስ በመክፈቻ ንግግራቸው “እስካሁን ዝም ያልነው፣ አንደኛ የሰውን ክብር ላለመንካት እና ሁለተኛ የመታረቅ ትንሽ ዕድል ካለ ብለን ነበር።” ብለዋል። አቶ ጌታነህም የቀድሞው ሊቀመንበር እና ሌሎች የተባረሩ አባላቱ ለሠላማዊ ትግሉ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ግምት ውስጥ በማስገባት ፓርቲው ጉዳዩን ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን ገልጸዋል።

 

አቶ ጌታነህ ባልቻ “የችግሩ መነሻ የፓርቲው የቀድሞ ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት እና ሌሎቹም የድርጅቱን ንብረት መመዝበራቸው ነው” ብለዋል። “የንብረት መመዝበሩ ጥያቄ እንደተፈጠረ የሥነ ስርዓት አጣሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ ጉዳዩን በመመርመር ያረጋገጠ ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ ነባሩን ሊቀመንበር በማውረድ አዲስ ምርጫ በማካሔድ አቶ የሺዋስ የሊቀ መንበርነቱን ቦታ በውስጠ ደንቡ መሠረት ወስደዋል” ብለዋል። አቶ የሺዋስም በመግቢያ ንግግራቸው ከሊቀ መንበር በስተቀር ቀሪው የሥራ አስፈፃሚው ኃላፊዎች ባሉበት መቀጠላቸውን አስረድተዋል።

 

ከፓርቲው አስራ አምስት መስራች አባላት መካከል አንዱ ብቻ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የቀድሞውን ሊቀመንበር ጨምሮ ሁለት ተጨማሪ መሥራች አባላት በሥነ ስርዓት ጉድለት በመታገዳቸው መሥራች ዐሥራ አንድ አባላት የፓርቲውን ሥራዎች ለማከናወን በሚጥሩበት ሰዓት ፓርቲው እንደተሰነጠቀ መነገሩ ትክክል አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል።

የድርጅቱን ንብረት መዝብረዋል የተባሉት 5 ሰዎች በድርጅቱ ደንብ መሠረት ክስ የቀረበባቸው እና በደንቡ መሠረት የተከራከሩ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ጥፋተኛ መሆናቸው ሲበየን፣ አቶ ይልቃልን ጨምሮ በይቅርታና በቅጣት ለመታለፍ ያልፈቀዱት አራቱ ከአባልነት ሲሰናበቱ አቶ ጌታነህ ባልቻ ግን በቅጣት ታልፈው የአዲሱ የሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ቀጥለዋል።

የአጣሪው ኮሚቴ ገለልተኝነት፣ የተመዘበረው ንብረት ግምት፣ የጠቅላላ ጉባዔው ምልዓትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባላት ሲመልሱ የሥነ ስርዓት አጣሪ ኮሚቴው ሦስት አባላት በምክር ቤቱ የፀደቁ በመሆናቸው ገለልተኛ ናቸው ብለዋል። ተመዘበረ የተባለውን ገንዘብ ትክክለኛ መጠን ለመግለጽ በተደጋጋሚ ያመነቱት አቶ ጌታነህ፣ በመጨረሻ “ከመጀመሪያ ጀምሮ ከተደረጉት 3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ በሰነድ ሳይወራረድ የቀረ ነው” ብለዋል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር አስቸጋሪ ገጽታ ምክንያት ለቅስቀሳ የሚታተሙ በራሪዎች እና ተመሳሳይ ወጪዎች የሦስተኛ ወገንን ደኅንነት ከመጠበቅ አንፃር ያለ ደረሰኝ ሊሠሩ እንደሚችሉ እና ችግሩ በዚህ ሳቢያ ተፈጥሮ እንደሆነ እና የአሠራር ክፍተት ካለ የተጠየቁት አቶ ጌታነህ፣ “እንደዚህ ዓይነት ወጪዎች በልዩ ቃለ ጉባኤ የሚፈፀምበት አሠራር አለን” በማለት የአሠራር ክፍተት ለምዝበራ እንዳላጋለጣቸው አስረድተዋል።

የጠቅላላ ጉባዔውን ምልዓት በተመለከተ በመተዳደሪያ ደንቡ የተወሰነ ቁጥር ባይኖርም ሰማያዊ ፓርቲ መዋቅሮቹን በዘጋባቸው ወረዳዎች ቁጥር ልክ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት እንደሚኖረውና በ2007 አቶ ይልቃል ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ በፀደቀው እና ከዚያ ጀምሮ ለ3 ዓመታት በሚያገለግለው 226 አባላት ያሉት ጠቅላላ ጉባዔ ዳግም ጥሪ ተደርጎ፣ 129 አባላት ተገኝተው ኮረም በመሙላቱ በተደረገው ምርጫ አቶ ይልቃል ወርደው አቶ የሺዋስ በምትካቸው ተመርጠዋል።

 

በአቶ ይልቃል እና ደጋፊዎቻቸው ከተነሱ ቅሬታዎች መካከል፣ የፓርቲው አባላት ያልሆኑ ሰዎች መገኘታቸው አግባብ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ አቶ የሺዋስ “ታዛቢ እንዲኖር በማለት ከቀድሞው አንድነት ፓርቲ፣ ከመኢአድ እንዲሁም ከምርጫ ቦርድ ታዛቢ ጋብዘናል። እነዚህ ግን በደምፅ ቆጠራው አልተሳተፉም። የአቶ ይልቃል ደጋፊ የነበሩ 13 ሰዎች ከ129ኙ በተጨማሪ ቢገኙም ጉባዔውን ለማስተጓጎል እንጂ ለመሳተፍ ፊርማቸውን ለማኖር ስላልፈቀዱ በጠቅላላው ጉባዔ ውሳኔ እንዲወጡ ተደርገዋል” በማለት ተሳታፊዎቹ የፈረሙበትን ሰነድ አሳይተዋል።

 

ጠቅላላ ጉባዔው የተካሔደው ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ነው በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የተራገበውን ዜና ሲያስተባብሉም፣ አቶ ጌታነህ ሁለት ደብዳቤዎችን አቅርበዋል። የመጀመሪያው ከፓርቲው ለሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ሰጪ ጉባዔውን ለማካሔድ የተጠየቀበት ደብዳቤ ሲሆን፣ ሁለተኛው የሰሜን አሜሪካው ድጋፍ ሰጪ ድጋፍ ማድረጉን የገለጸበት እና ለአቶ ይልቃል ጌትነትም ግልባጭ የተወበት የኢሜይል መልዕክት ነው።

 

ከቀድሞው ሊቀ መንበር እና ደጋፊዎቻቸው ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት፣ በወቅቱ ከሁለት ዓመት እስር በኋላ በነጻ የተፈቱት አቶ የሺዋስ አሰፋ በግንቦት ወር 2008 ልዩነቱን በእርቅ ለመፍታት ንግግር ላይ የነበሩ መሆናቸውን አስታውሰው፣ በዚህ ውይይት መሐል ሊቀ መንበሩ አቶ ይልቃል ወደካናዳ መሔዳቸውን የውይይቱ አካላት እንደማንኛውም ሰው ከሚዲያ መስማታቸውን ተናግረዋል። የቀድሞውም፣ የአሁኑም ሥራ አስፈፃሚ ውስጥ በውጭ ጉዳይ ኃላፊነት የሚያገለግሉት አቶ አበበ አካሉም “እኔ እንኳን አቶ ይልቃል በፓርቲው ሥም ሊሔዱ ስለመሆናቸው ምንም መረጃ አልነበረኝም። ፓርቲው የግለሰብ ንብረት የሆነ ያክል ነበር። እኔ የማገለግለው የኢትዮጵያ ሕዝብን እንጂ የፓርቲውን ሊቀመንበር አይደለም” በማለት በምሬት ተናግረዋል።

የገንዘብ ምዝበራው አሁንም እንደቀጠለ የተናገሩት አቶ ጌታነህ፣ “በቅርቡ ከሰሜን አሜሪካ ደጋፊዎቻችን የተላከልን 7,600 ዶላር ድጋፍ አቶ ይልቃል እጅ ከገባ በኋላ ወደ ፓርቲው ገቢ አልተደረገም። ደጋፊዎቹም እውነቱን ሲያውቁ ለማስመለስ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም” ብለዋል። “ከዚህም ውጪ ሌሎች ምዝበራዎች አሉ” ያሉት አቶ ጌታነህ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዱት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

የቀድሞ የፓርቲ መሪ ይልቃል ጌትነት ግን የአዲሲ አመራር እርምጃ ፓርቲውን ለማፍረስ የተቀነባበረና ባልታወቁ ሀይሎች የተቀነባበረ ሴራ ነው ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ላይ 12 የቀድሞ የፓርቲ አባላትን የያዘ ሁለት ኮሚቴ መመሥረቱ ተነግሯል። የአቶ ይልቃል ደጋፊዎች የምርጫ ቦርዱን ውሳኔ በፍርድ ቤት ሊሞግቱት ይችላሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የኮሚቴው አባል እና ከሦስት ወራት የማዕከላዊ እስር  በኋላ በቅርቡ የተፈቱት፣ የሕግ ባለሙያው አቶ አዲሱ ጌታነህ በትላንትናው ዕለት አመሻሹ ላይ ባልታወቁ ሰዎች በጩቤ ተወግተው ሆስፒታል መግባታቸው ተነግሯል።

የደከመን መርገጥ ሳይሆን የደከመን ማገዝ ነው ትክክል – (ምላሽ ለአቶ ይገረም አለሙ)- ግርማ ካሳ

 

ይገረም አለሙ የተባሉ ጸሃፊ “ድርድሩ” በሚል ያቀረቡትን ጽሁፍ  ዘሃበሻ ላይ አነበብኩ። እኝህ ሰው ከሚጦምሩትና ከሚጽፉት ዉጭ ማን እንደሆኑ፣ አገር ቤት ይኑሩ፣ ዉጭ አገር፣ በእዉነተኛ ስማቸው ይጻፉ፣ በብእር ስም ብዙ የማውቀው ነገር የለም። ሆኖም ባቀረቡት ሐሳብ ዙሪያ እኔም የተሰማኝን አንዳንድ ምላሾሽ፣ በአክብሮት መስጠት ፈለኩ።

“ድርድር በእነማን መካከል፣ ድርድር እንዴትና በምን ሁኔታ? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ የሚችል አስተያየት መጻፉ፣ ልምድ ማካፈሉ ነበር የሚበጀው፡፡ እኔ ይህን ለማድረግ የሚበቃ እውቀትም ልምድም የለኝም፡፡ ፍረጃና ውንጀላ ላይ በመሮጥም ሆነ ጭፍን ድጋፍ በመስጠት  ደግሞ አላምንም፣ በዚህ መካከል ሆኜ ስለ ድርድሩ የተሰማኝን  ልበል፡” ሲሉ ነው የጀመሩት ጽሁፋቸው። ሆኖም ግን እንዳለ ጽሁፋቸው፣ እንኳን ለድርዱሩ የሚጠቅሙ ሐሳቦችን ሊያቀርቡ ቀርቶ፣ ጭራሽ ፍረጃና ወገዛ የሞላበት፣  “ድርድሩ መደረግ የለበትም” የሚል አቋም ያንጸባረቀ ጽሁፍ ነው።

አቶ ይገረም “ወያኔ የድርድር ጥሪ ያቀረበው በመላ ሀገሪቱ በተለይ ደግሞ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች በተቀጣጠለው የህዝብ ቁጣና እንቢተኝነት በደረሰበት ድንጋጤ መሆኑን ወያኔዎችም ቢሆን የሚክዱት አይመስለኝም፡” ሲሉ የጻፉት ትክክለኛ አባባል ነው። በኦሮሚያና በአማራው ክልል የተከሰተው ተቃዉሞ ድንጋጤ ዉስጥ ከመክተትም ባለፈ፣ በዉስጣቸው ከፍተኛ የሆነ መከፋፈልን ነው የፈጠረው። በተለይም በብአዴን እና በሕወሃት መካከል ብዙዎች ያልተረዱት ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ነው ያለው። የብአዴን መካከለኛና ታችኛው አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል የሕወሃት የበላይነት መቆም አለበት ብለው የቆረጡና የተነሱ ናቸው።

አቶ ይገረም ድርድሩ የሕዝብ ትግል ዉጤት መሆኑን ከገለጹበት አባባል በስተቀር ግን፣ ሌሎች ያሰፈሯቸው ነጥቦች በድርዱሩ ላይ ከወዲሁ ዜጎች ጨለምተኛ አመለካካት እንዲኖራቸው የሚገፋፉ፣  ተስፋ አስቆራጭ የሆኑ ፣ በመፍትሄ ላይ ሳይሆን ብሶት በማሰማት ላይ ያተኮሩ ደካም ነጥቦች እንደሆኑ ነው ለማየት የቻልኩት።

እኝህ ሰው በተለይም ተቃዋሚዎችን የገለጹበት አገላለጽ ከማስገረም አልፎ አስቆኛል። “ይቅርታ ይደረግልኝና የድርድሩ ተካፋይ የተባሉትን ፓርቲ ብሎ ለመጥራት አንደበቴ፣ ለመጻፍ ጣቶቼ እሽ አይሉኝም፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ለድርጅቶቹ ወይንም ለመሪዎቹ ጥላቻ ኖሮኝ ሳይሆን ፓርቲ ለመባል የማይበቁ በመሆናቸው ነው” ይሉናል አቶ ይገረም። እርግጥ ነው ተቃዋሚዎች ጠንካራ ናቸው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው። እርግጥ ነው በተቃዋሚዎች ዉስጥ በየትኛውም ድርጅት ችግሮች እንዳሉ ችግሮች አሉ።  ሆኖም ግን ድርጅቶቹ የሚጠናከሩበትን መንገድ ከመፈለግና በዚያም ረገድ ሐሳቦችን ከመስጠት በዚህ መልኩ ፣ በትንሹም ቢሆን ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ወገኖችን እንቅስቃሴ ማሳነስና ዜሮ ማስገባት፣ በግሌ ሃላፊነት የጎደለው አድርጌ ነው የምወስደው።

በነገራችን ላይ አቶ አቶ ይገረም ተቃዋሚዎች ሲሉ ሁሉንም ጨፍልቀው ማየትቸው ራሱ አንዱ ትልቁ ድክመታቸው ነው። ሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ፣ መድረክና ኢዴፓ አሉ። እነዚህ አራት ድርጅቶች ሕዝብን እንወክላለን ያሉበት ሁኔታ የለም። ሊሉም አይችሉም። ሆኖም ግን የሕዝብን ጥያቄ ግን እንደ ድርጅት ማቅረብ ይችላሉ። ያንንም ነው እያደረጉ ያሉት። የእስረኞች መፈታት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መቆም፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ እንዲሆኑ፣ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ….የመሳስለኡት የሕዝብ ጥያቄ አይደሉም እንዴ ?

በአገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች በከባድ ሁኔታ ውስጥም ሆነው ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ መሆናቸውን አቶ ይገረም፣ አዉቀው ላለማመን ካልፈለጉ በስተቀር፣  ያጡታል ብዬ አላስብም። ለምሳሌ ሁለት ምሳሌዎች ልጥቀስ፡

በአማራው ክልል ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከመደረጉ፣ ከአንድም ሁለት አመታት በፊት በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደሴ በመሳሰሉ ቦታዎች ሕዝቡን ለማደራጀትና  ለማንቀሳቀስ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ ሥራ ሲሰራ እንደነበረ አገር ሁሉ የሚያወቀው ነው። የአንድነት ፓርቲ በምርጫ 2007 ወቅት ከ547  የፓርላም ወረዳዎች በ508 ተወዳዳሪዎች አሰልፎ ፣ በሰላሳ አራት ዞኖች ጽ/ቤት ከፍቶ በምርጫው ጠንካራ ፓርቲ ሆኖ ለመውጣት ዝግጁ የነበረ ፓርቲ ነበር። (ከአንድነት ቀጥሎ የብዙ ድርጅቶች ስብሰብ የሆነው መድረክ 270 ብቻ ነበር ያሰለፈው)   በድርጅቱ ዉስጥ ችግር የነበረ ቢሆንም፣ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ችግሩን ፈቶ፣ አዲስ አመራር መርጦ የተንቀሳቀሰ ፣ ከፓርቲው ምስረታ ጀመሮ አራት ሊቀመናብርትን ያስተናገደ የአንድ ሰው መፈንጫ ያልሆነ ዘመናዊ ፓርቲ ነበር። ብርሃንን ሰላምን ጨመሮ የግል ማተሚያ ቤቶች የአንድነት ልሳኖችን፣ ጋዜጦችን ፣ በደህንነቶች ትእዛዝ አናወጣም ቢሉም ፣ ፓርቲው የራሱ ማተሚያ ማሽን እና የራሱ ጀኔሬተር በመግዛት በሳምንት ሁለት ጋዜጦችን (ፍኖተ ነጻነት እና የሚሊዮኒች ድምጽ ) እያተመ ለሕዝብ ያቀርብ ነበር። በተለያዩ የአገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ አማራጭ ሐሳቦችን ያዘለ ዳንዲ የሚባል መጽሔት፣  በኦሮሚያ ላለው ማህበረሰብ በአፋን ኦርሞ ቶኩማ በቢሊሱማ በሚል ጋዜጣ መረጃዎች እንዲደርሰው ለማድረግ ዝግጁትን ጨርሶ ነበር።

አንድነት ጠንካራ ሆኖ በመውጣቱ ነው ሕወሃት የፖለቲካ ዉሳኔ፣ ጉልበቱና ጠመንጃው ስላላለው የወሰነው።  በድርጅቱ መድረክ ለሊቀመንበርነት ተወዳድሮ አንድ ድምጽ ብቻ (የራሱን ድምጽ) ያገኘውንና ለኑሮ ደሞዝ የሚፈልዉን ደካማ ግለሰብ በመጠቀም፣ ምርጫ ቦርድ አንድነት ሕጋዊ ሰርተፊኬቱን እንዲያጣ አደረገ። እዉነታው ይሄ ሆኖ እያለ፣  አቶ ይገረም ግን በጭራሽ የማይገናኝ ነጥቦች በማገናኘት፣ የተሳሳተና በእዉነት ላይ ያልተመሰረተ፣ ግን እርሳቸው ትክክል ነው ያሉትን ለመሸጥ ሲሉ ፓርቲዎችን ሲያሳንሱ ነው የሚታዩት። “ፓርቲዎች የሚፈርሱት በራሳቸው አባላት ነው” ብለው በጻፉት ጽሁፍ ላይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት፡

ንድነት ህመሙ የጀመረው ሊቀመንበሩ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ስትታሰር ነው፡፡ መድሀኒት የሚፈልግለት አይደለም በሽታውን የሚያውቅለት ጠፍቶ ለአምስት አመታት ከተሰቃየ በኋላ በሀገር ቤትም በውጪም የሚኖሩ  ከአመራር እስከ አባል የነበሩ  የግዛቸው ነኝ፣ የበላይ ነኝ በማለት በፈጠሩት የሥልጣን ሽኩቻ በሽታው ተባብሶ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ በመቃብሩ ላይ የቆመው ትእግስቱ አዎሉም በየግዜው በሹመት ላይ ሹመት ሲሰጡት የነበረ ሰው ነው፡፡ ታዲያ ለአንድነት ሞት ቀዳሚው ተጠያቂ ወያኔ ወይንስ የሥልጣን ጥም ያናወዛቸው የአንድነት አመራሮችና የዲያስፖራ ብር ያናወዛቸው አጃቢዎቻቸው” ሲሉ እኝህ ሰው፣ የአንድነት ፓርቲ ከምርጫ 2007 የነበረዉን ጉልህ ተሳትፎ በመናቅ፣ በሚሊዮሞች ድምጽ የተሰሩ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ወደ ጎን በማድረግ ፣ አንድነት ከጨዋታ ዉጭ እንዲሆን 90% ድርሻው የወያኔ እንደሆነ እያወቁ በዚህ መልኩ ለተቃዋሚዎች መዳከም ወያኔ የለበትም ማለታቸው በራሱ አጠያያቂ ነው። በነገራችን ላይ የአንድነት ፓርቲ ሕጋዊ ሰርተፊኬቱን ቢነጠቅ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ግን አሁን በትግል ዉስጥ ናቸው። የተወሰኑይ እንደ መኢአድ እና ሰማያዊ ተቀላልቀለውም እየታገሉ ናቸው። ወያኔ ሰርተፊኬቱን ቢነጥቅም፣ አባላቱን ደጋፊዎች፣ የአንድነት የለዉጥ ሃይል አሁንም አለ።

አቶ ይገረም፣ ትንሽ የነበረዉን ሁኔታ ይረዱ ዘንድ ከጥቂት አመታት በፊት፣ ከብዙ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል፣  በአማራው ክልል በባህር ዳር የተደረገን አንድ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲመለከቱ ልጋብዛቸው እፈልጋለሁ። የእምቢተኝነት መንፈስ፣ ለመብት የመቆም ስሜት፣ ድፍረት፣አገራዊ ወኔ እንዲኖር የአንድነት ፓርቲና የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቀ የነበረዉን አስተዋጾ ለማየት ይረዳቸዋል።

ሌላው የሰማያዊ ፓርቲን በተመለከተ ነው።ሰማያዊ ፓርት ከተመሰረተ ጀምሮ ለትግሉ ብዙ አስተዋጾ ያደረገ ፓርቲ ነው። በፓርቲው ውስጥ እንደ ማንም ድርጅት ልዩነቶች ይኖራሉ። ሆኖም ፓርቲው ከግለሰቦች ይልቅ በድርጅቱ ያሉ ተቋማት ጠንካራ እንደሆኑ ያስመሰከረ ድርጅት ሆኗል። አገዛዙ ልክ እንደ አንድነት ፓርቲ፣  ጠንካራ የሰማያዊ አመራሮች በሽብርተኝነት ክስ አስሮ አሰቃይቷል። እያሰቃየም ነው። የድርጅቱ የአሁኑ ሊቀመነበር ወደ 2 አመት ገደማ በወህኒ የተሰቃዩ ናቸው። እንደ ዮናታን ተስፋዬ ያሉ አንጋፋ ታጋዮችም በአሁኑ ወቅት በወህኒ ነው የሚገኙት። ሰማያዊ በከባድ ሁኔታ ዉስጥ ሆኖም ግን በከፍተኛ ተነሳሽነት ለትግል የተዘጋጀ ድርጅት ነው።

ይሀን ስል በፓርቲዎች ዉስጥ “ችግር አልነበረም፣ ድካም አልነበረም” ማለቴ አይደለም። ሆኖም ግን አቶ ይገረም ለማቅረብ እንደሞከሩት፣ አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ምንም እንዳልሰሩ፣ “ስማቸውን መጥቀስ እስከማፈር ድረስ” የማይረቡ እንደሆኑ አድርጎ ማቅረብ ግን ፣ ያውም የሚረባ የሚሉትን ሳያሳዩን እና ሳያመላከቱን የደከመ፣ የሽንፈት፣ ጨለምተኛ ፖለቲካ ነው።

 

አቶ ይገረም በድርድሩ ዙሪያ ሲጽፉ  አሁንም በተስፋ መቆረጥ ውስጥ ተሞልተው ነው። ወያኔዎች የሚደራደሩት ጊዜ ለመግዛትና የአለም አቀፍ ድጋፍ እንዳይቀርባቸው ነው ከሚል ነው በሚል፣ ከድርድሩ ምንም ነገር እንደማይገኝ ነው የገለጹልን። ተቃዋሚዎችም ፓርላማ ለመግባትና ጥቅም ለማግኘት ብለው እንደሚደራደሩም አይናቸውን በጨው አጥበው ነው የጻፉት። አንደኛ የተቃዋሚ መሪዎች ጥቅም ቢፈልጉ ኖሮ አገዛዙን ተቀላቅለው ፣ ወያኔ ሆነው፣ ይሄን ጊዜ ሃብት በሃብት ይሆኑ ነበር። ሁለተኛ የምእራባዊያን መንግስታት ሁኔታም የመረዳት ችግር ያለባቸው መሰለኝ። ያን ቢረዱ ኖሮ ምእራባዉያን  ለሰብአዊ መብትና ለዲሞክራሲ ሳይሆን ለጥቅማቸው ብቻ የቆሙ እንደሆኑ ያወቁ ነበር።  ወያኔ ድርድር አደረገ አላደረገ ፣ ጥቅማቸውን እስካስጠበቀላቸው ድረስ የውጭ ድጋፍ እንደማይለየው  ይረዱ ነበር። “የዲፕሎማሲ ድጋፍ ቆመ” ያሉትን አቶ ይገረም፣ ስህተት ነው። አልቆመም። “ቆመ” ካሉ መረጃዎች ያቅረቡና ይከራከሩ።

ወያኔ ለድርድሩ የቀረበው እርሳቸው እንዳሉት በሕዝብ ተገዶ ነው። በሕዝብ ብቻ ሳይሆን በድርጅቱ ውስጥ ባሉ መካከለኛና አነስተኛ አመራሮች ግፊት ነው። አሁን ያለው አገዛዙ ከ5 ወይም 10 አመታት በፊት የነበረው አይደለም።በመሆኑም ይህ ድርድር በአንጻራዊነት የፖለቲክ ምህዳሩን እንዲሰፋ ሊረዳ ይችላል። ያም ባይሆን እንኳን  ያ እንዲሆን ሙከራ ማድረጉና መታገሉ አስፈላጊ ነው። አቶ ይገረም፣ አሁንም እላለሁ፣  ሌላ አማራጭ ሳያሳዩን ፣ ትንሽ ቢሆን የተሻለ ነገር እንዲመጣ ወደ ድርድር የመገባቱን ሂደት ማሳነሳቸው፣ ማጣጣላቸው ተገቢ አይደለም።

በግሌ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አቤል ዋቤላ እንዳለው “አገር የሚገነባው በድርድር ነው” የሚል እምነት አለኝ። ከአሁን ለአሁን ትላንት አልተሳካምና ዛሬ መሞከር የለበትም የሚለው አነጋገር ፣  የትም አያስኬድም። ይልቅ ይሄ ድርድር ትንሽም ቢሆን ፍሬ እንዲያፈራ የድርሻችንን መወጣት ነው የሚጠበቅብን።

አሁንም ደግሜ የምለው አገር  ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች እንደ ማንም ድርጅት በውስጣቸው ችግሮች ይኖራሉ። ሆኖም ግን በዋናነት በገዢው ፓርቲ በኩል የደረሰባቸዉን የሚደርስባቸው ግፍና መከራ በጣም የከፋው። እዉነቱ ያ ሆኖ እያለ፣ እነርሱ ከማገዝና ከመደገፍ፣ እነርሱ ከድካማቸው እንዲወጡ የድርሻችንን ከማድረግ ፣ ወያኔ በነርሱ ላይ የሚያደርሰው ጫና ሳያንሳ እኛ ደግሞ “ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው” እንደሚባለው፣ እነዚህ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ላይ ጠጠር መወርወር ዘመናዊ ፖለቲካ አይደለም። ተቃዋሚዎች መተቸት ፣ መወቀስ አለባቸው። መሪዎቻቸው ተጠያቂ መሆን አለባቸው። ሆኖም ትችታችንን ወቀሳችን ፈረንጆች constructive  criticism ( ገንቢ ትችት) መሆን አለበት እንጂ  destructive criticism  (አፍራሽ ትችት) መሆን የለበትም። የአቶ ይገረም ጽሁፍ በኔ እይታ destructive የሆነ ትችት ነው።

“እኔም ጥያቄ አለኝ እነርሱ የሚሉትንና የሚያደርጉትን ነው መከተል ያለብን ወይንስ ትክክል የምንለውን? “ ነው ሲሉ በመጠየቅ ጽሁፋቸው ያጠቃላሉ አቶ ይገረም። ትክክል የሆነውን ነው መከተል ያለብን የሚል መልስ ነው ያለኝ። ሆኖም እርሳቸው የሚቃወሙት፣ ችግርን በዉይይት መፍታት ትክክል ብቻ ሳይሆን የሰለጠነ ፖለቲካ ነው። ከላይ ጠቅሼዋለሁ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ እንዳለው አገር የሚገነባው በድርድር ነው። ትክክል ሳይሆን ትክክል የተበላን ትክክል እንዲሆን መስራትና መድከም ያ ትክክል ነው። አቶ ይገረም እንደሚያደረጉት፣ ዜጎች ተስፋ ማስቆረጥ፣ የደከመዉን ደካማ ነው ብሎ መረጋገጥ ትክክል አይደለም። የደከመውን ማንሳትን ማበረታታት፣ የተሳሳተዉን እንዲታረም መምከርና መዉቀስ  ያ   ትክክል ነው።  የአቶ ይገረም ችግር ትክክል ያልሆነውን ያለመከተል ሳይሆን ትክክል የሆነውን ነገር አለመከተላቸው ነው።

(ይሄ ጽሁፍ የተጻፈው ምሉ በሙሉ አቶ ይገረም ባቀረቧቸው ሐሳቦች ዙሪያ ነው። በርሳቸው ላይ ምን እንደሆኑ ባላወቅም ችግር የለኝም። እርሳቸው ወደ ግለሰብ እንካ ሰላምቲያ ሳይገቡ በቀርቡ ሐሳቦች ዙሪያ ምላሽ የሚሰጡ ከሆነ እጠብቃለሁ)

“አንቱ አጤ ሚኒሊክ ምን ያሉት ሰው ነዎት ?… ” – አሌክስ አብርሃም

 

የዛሬ አመት በዚህ ወቅት ነው …..አዳራሹ ካፍ እስከገደፉ ግጥም ብሎ በተሰብሳቢወች ተሞልቷል ! የኢሃዴግ ወጣቶች ሊግ ..የሴቶች ሊግ …ጥቃቅንና አነስተኛ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ የቀረ የለም ! ለዩኒቨርስቲ ተማሪወች ከሚሰጠው ስልጠና ጎን ለጎን የአገሪቱን ‹‹ነባራዊ ሁኔታ›› ለነዋሪውም ለማስገንዘብ የተዘጋጀ የሶስት ቀን የመወያያ መድረክ ነው … አዳራሹ ዙሪያውን የአክሱም የላሊበላ ምስሎች ተስለውበታል በቀኝ በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ፎቶ በትልቁ ይታያል በስተግራ የአፄወቹ ምስል ተደርድሯል የአፄ ቴውድሮስ የአፀጼ ሚኒሊክና የአፄ ይኋንስ . . .

ስብሰባው ሶስተኛ ቀኑ ነበር ….ሰብሳቢው እንዳለፉት ሁለት ቀናት ሁሉ ዛሬም እንዲህ ሲል ቀጠለ ‹‹ እና ባለፉት ሁለት ቀናት በስፋት ታሪካችንን እንደዳሰስነው አሁን ላለው የብሄረሰቦች እርስ በእርስ መቃቃር መነሻው አፄ ሚኒሊክ ነበሩ …. አሁን ከኤርትራ ጋር ላለው አንዳንድ ተገቢ ያልሆነ የድንበርና ሌላም ውዝግብም ያው መነሻው የአጼው ስርአት ነበር … ›› እያለ ለድፍን ሶስት ቀናት የአፄ ሚኒሊክን ድክመት ደካማ አስተዳደር እና ፀረ ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ ያወገዘበትን ትንታኔ አገባደደ …… ከዛም ህዝቡ ጥያቄ ካለው እንዲያቀርብ እድል ሰጠ!

በስብሰባው ላይ የጥንቱ ሲወገዝ እና ሲገዘት የአሁኑ አገዛዝ የፅድቅ ዘይት ሲቀባና ሲሞካሽ ግራ ከገባቸው ታዳሚወች መካከል አንዲት እናት ከወንበራቸው ተነስተው በቀጥታ ወደሚኒሊክ ፎቶ ሄዱና አዳራሹን በሚያናውጥ ድምፅ ሚኒሊክን በጥያቄ አፋጠጧቸው

‹‹አንቱ አጤ ሚኒሊክ …. አሉ የሚኒሊክ ፎቶ ላይ አፍጥጠው …..እንግዲህ የዚች አገር ችግር ሁሉ መነሻ እርሰዎ ከሆኑ …ጥያቄ አለኝ ለእርሰዎ ! ምን ያሉት ሰው ነዎት ግን ?
ለምንድን ነው ላባችንን ጠብ አድርገን ግብር በምንከፍልበት አገር መብራት በየቀኑ የሚያጠፉብን ?
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምንድነው የስልክ ኔትወርኩን የማያስተካክሉልን ‹‹ያለዎት ቀሪ ሂሳብ ›› የምትለው እቴጌ ጣይቱ ናት ?›› ለምን አይመክሩልንም …?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. የውሃ ማማ በምትባል አገራችን ውሃ እንዲህ የሚያጠፉብን ለምንድን ነው ?
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….ለምንድነው ልጆቻችን ስራ አጥ እንዲሆኑ ያደረጉብን? ያሰሩብን ”””’

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ””’እርሰዎና ጋሻጃግሬዎቾ በአውቶሞቢል እየፈሰሱ ስለምን ህዝብዎት በትራንስፖርት እጦት ፍዳውን እንዲበላ ፈረዱ ?ማንስ ነው ተጠያቂው?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….ለምንድነው የትምርት ጥራቱ ከእጅ አይሻል ዶማ የሆነው ለምን ልጆቻችንን በነቀዘ ቲወሪ ያነቅዙብናል? ››

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …..ለምን ምርጫ በደረሰ ቁጥር አገር ምድሩን ያዋክቡታል ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …. ለምን ሃሳባቸውን በነፃነት የሚገልፁትን ሁሉ አሸባሪ እያሉ እስር ቤት ይወረውራሉ? ያስደበድባሉ ያስገድላሉ ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምን የህዝቡን የሰቆቃ ኑሮ በመስተዋት ህንፃወች በቀለበት መንገዶች ግርጌ ሊደብቁ ይፍገመገማሉ ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምን መርፌ ያነሱ ሙሰኞችን እያሰሩና ከበሮ እያስደቁ በሬ የሚጎትቱትን በዝምታ ያልፋሉ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …..ለምን በብሔራዊ ቴሌፊዥናችን ብሔራዊ ውሸት ያልኖርነውን ዝባዝንኬ እየተረቱ ያደነቁሩናል ?ለምን ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭ የውሸት ታሪክ ይፈጥራሉ ህዝቦችን የሚያቃቅር ሀውልት ያቆማሉ ….ንፁህ ውሃ ያጣ ህዝብ ከጥላቻ ሃውልት ንፁህ ውሃ ይቅዳ ብለው ነው ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምን ፍትሃዊ ምርጫ አይኖርም … እስከመቸ ከዚህ ሁሉ ችግሮዎት ጋር ዙፋንዎት ላይ ይቆያሉ ?
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ……እስከመቸ የከበረ ታሪክን በመንደር ቱሪናፋ ሲያራክሱና ዝቅ ሲያደርጉ ይኖራሉ ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …..እርሰዎ የጀመሩትን እናስቀጥላለን ! በቃ ለመጭዋም ምርጫ እንመርጠዎታለን አሁን ሰብስበው አይነዝንዙን ….ሲሉ እንደእብድ ጮሁ

ሰብሳቢው
‹‹ሴትዮ ….. አካሄድ አካሄድ ……ከአጀንዳ ወጥተዋል›› ሲል ጮኸ
‹‹ አሃ አጀንዳው የሚኒሊክ መስሎኝ …አካሄድ የምትለኝ ታዲያ ወዴት ሂደን እንጩህ .›› ብለው ቀጠሉ ,,,,
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ,,,,,,,,,,