አማራውን ፍለጋ

 

(መስቀሉ አየለ)


የአማራው ህብረተሰብ በታሪክ አጋጣሚ እንደ ሎተሪ እጣ ከወጣላቸውና ከበታችነት ስሜት (የኢንፌሪየሪቲ ኮምፕሌክስ) ፣ ኤክዞኖፎቢያ፣ ወዘተ መገለጫ የሆነው የዘረኝነት ወይንም ስሙን ሲያጣፍጡት ብሄርተኝነት የሚሉትን የስነልቦና ቀውስ አምልጦ የወጣ፣ አማራዊነትን በኢትይጵያዊነት ተክቶ ማሳደግ (ማኒፌስት ማድረግ) የቻለ ህዝብ ነው። ይሕ
መታደል ነው። ከማንነት ወደ ሰውነት ማደግ ነው። ከመንደርተኝነት ወጥቶ ዩኒቨርሳል የሆነ መገለጫን ገንዘብ ማድረግ ነው። ይህንን ነገር ከታደሉት በአለም ውስጥ ካሉት በጣት የሚቆጠሩት ህዝቦች

፩) የሰርብ ህዝብ፤
፪) የራሽያ ህዝብ፤ይኽ ህዝብ ከናፖሊዮን እስከ ናዚ… ከናዚ እስከ የዘመኑ የአሜሪካ ኒዮ ኮንሰርቫቲቨ በየዘመኑ የተነሱትን አምባገነኖን ልክ ያስገባን በምን አይነት ከሰማይ ባለ መከራ ተፈትኖ ያልተሰበረ ህዝብ ነው።
፫ የእንግሊዝ ህዝብ፤ የመጫረሻው ኢምፓየር ሆኖ መውጣቱ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ከተፈጠረበት ዘመን ጋር መግጠሙ አመች ሁኔታ ፈጥሮለት አሁን አለማችን የምትመራበትን Time & Space መለኪያዎች ወጥነት ባለው መልኩ ቅርጽ
መስጠታቸው ;የአለም አገሮችን ካርታ መወሰናቸው; ፣ቋንቋቸውን አለም አቀፍ ማድረጋቸው፤ እንዲሁም አለማቀፋዊ ተቁዋማትን በመልካቸው ቀርጾው በማለፋቸው የራሳቸውን አሻራ በመጣል የተሳካላቸው በመሆኑ ይኽ ነገር ዛሬ ድረስ ለማንም በሚታይ መልኩ የፈተረላቸው ሳይኮሎጅካል አድቫንቴጅ የማይካድ ነው።
፬) የአማራ ህዝብ፤ እንደ ህብረተሰብ ከወጣበት ግዜ ጀምሮ ከቱርኩ፣ከሱዳኑም ከግብጹም ከጣሊያኑም ከሱማሌውም ወዘተ ሲተናነቅና እርስቱንና ማተቡን ሲጠብቅ የቆየው የአማራ ህዝብ ሌላኛው በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ የተመዘገበ፣ ሰብእና ለመገንባት የቻለ ህዝብ ነው። እስካሁን ባደረኩት ዳሰሳ በዚህ ቁመና የሚሰፈርና በሁለት እግሩ ለመቆም የማንም ድጋፍ የማያስፈልገው የተሙዋላ ስነ ልቦና ያለው ሌላ ህዝብ በየትኛውም የዓለም ጥግ አላገኘሁም። በምእራብ አገሮች ታላላቅ ከተሞች ተዎልዶ ካደገውና እራሱን አፍሪካዊ አሜሪካው ወይንም አፍሪካዊ አውሮፓዊ ብሎ ከሚጠራው ጥቁር ይልቅ ለምን ትናንት የሄደው አበሻ በተሻለ የነጻነት ስሜትና በሙሉ ስነልቦና ሳይሸማቀቅ እንደሚራመድ
ለአንድ ሰከንድ ቆም ብሎ የሚያስብ ማንም ቢኖር መልሱን ያገኛዋል።
በአዲሱ የግሎባላይዜሽን ዘመን “የኒው ወርልድ ኦርደር እንቅፋት እንዳይሆኑ በግድም ሆነ በውድ በውስጣቸው ያለው የስነልቦና የበላይነት መሰበር አለበት” ተብለው ጥርስ ውስጥ የገቡት ሶስት አገሮች ኢኒሁ ራሽያ፤ሰርቢያና ኢትዮጵያ መሆናቸው ብዙ የተጻፈለት ብቻ ሳይሆን የሚሸረበውን ሴራና የሚደረገውን ከበባ ባይናችን የምናየው እውነት ነው።በአድዋ ጦርነት ወቅት ወሳኙን ሚና የተጫወተው በአመዛኙ የአማራውን ህዝብና ኦርቶዶክስን ማእከል ያደረገው ኢትዮጵያዊነት በተቀዳጀው ድል የተነሳ ሌሎች በባርነት ስር ለሚማቅቁ አገሮች ፋና ወጊ ምልክት መሆን ብቻ ሳይሆን እንግሊዞቹ የአፍሪካን ህዝብ እንደ አውስትራሊያ ጥቁሮች ሙሉ ለሙሉ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የነበራቸው ታላቁ ሴራ
(ግራንድ ስትራቴጅ) የተሰረዘው በአድዋ ድል ብስራት የተነሳ መሆኑ ነበር። በካረቢያን ያሉትን ጥቁሮች ጨምሮ በምድር ላይ እንደ ጨው ለተበተኑት ጥቁሮች ሁሉ የነጻነት ምልክት የሆነች አገር፣ እራሷን ችላ ለመቆም የሚያስችል የራሷ ሙሉ ታሪክና ማንነት ያላት፣ በፓን አፍሪካን ሙቭመንት ጉልህ ድርሻ የተጫወተች፣ ለዝምባቡየ፣ ቦትስዋና ፣
ናምቢያ ደቡብ አፍሪካ ወዘተ ለመሳሰሉት አገሮች የነጻነት ትግል ይበረከተች አገር መሆኗ; ኢትዮጵያዊነት በ1960-ዎቹ የተጀመረውን ፓን አፍሪካኒዝም ዳር ለማድረስ እንደ አንድ የጥቁሮች አይዲዮሎጅ የማገልገል ሃይሉ ከፍተኛ ነው የሚለው ሁሉ ተደማመረና አንድ የኒው ወርልድ ኦርደር እንቅፋት ተደርጋ እራሽያን ከመሰሉ አገሮች ጎን እንድትፈረጅ አደረጋት።
በሌላ በኩል ደግሞ እንደ አሜሪካ ያሉ እድሜያቸው ገና በሰው ስንዝር የሚለካባቸው አገሮችን ትተን እረጅም እድሜና ከፍተኛ የስልጣኔ እርከን ላይ የደረሰ እንደ ጀርመን ያለውን አገር ብንወስድ ሲጀመር አለምን ለመቀራመት ባነሳው የይገባኛል ጥያቄ የተነሳ ለሁለቱም ታላላቅ የአለም ጦርነቶች መነሻ በመሆኑ ምክንያት አከርካሪው የተሰበረ፣ የጦርነቱን ፍጻሜ ተከትሎ ቦሃላም ምእራባና ምስራቅ ጀርመን ተብሎ ለሁለት በመከፈሉ የተነሳ የፈጠረበት ውርደት ከፍተኛ የሆነ የጀርመን ብሄርተኝነትን ስሜት እንዲያጎለብት አድርጎታል። ዛሬ ጀርመን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ማፈሰስ የአውሮፓን አገሮች ሁሉ የበጀት ቀዳዳቸውን በመሙላት ጫማውን እንዲስሙለት እስከማስደረግ የሄደበት ኩነት
ትናትንት አለምን በጉልበቴ አስገብራለሁ ብሎ አከርካሪውን ሲስበር የደረሰበትን የሞራል ስብራት ለመጠገን የሚያደርገው አንዱ አካል ነው። ዛሬ የጀርመን ብሄርተኝነት ወርዶ ወርዶ በእግር ኩዋስ ጨዋታ ላይ ሳይቀርየሚያሳዩት ፺ ደቂቃ ሙሉ ያለ ማቁዋረጥ የሚንቀለቀል እልህ ላስተዋለ ሰው ይኽ ስሜት ያልገባበት የጀርመናዊ ማንነት እንደሌለ ይረዳዋል።
እንግዲህ የብሄርተኝነት ጥያቄ በኢትዮጵያ በዋናነት ጉልህ ሆኖ እንደ አንድ ንቅናቄ መውጣት ከጀመረበት ባለፈው አምሳ አመታት ገደማ እንኩዋን ያለውን ለይተን ብናየው ይኽ ነገር በነፍጥ ወደ ታገዘ ነውጥ የተለወጠው በዋናነትበኦሮሞ እና የትግሬ ብሄርተኝነት በኩል ነው።
ሁለቱም ዘውጎች ይኽንን የብሄርተኝነት ጥያቄ ለመፍጠር ብሎም የህዝባቸው የመታገያ አይዲዮሎጅ አድርገው እንወክለዋለን የሚሉትን የዘውግ ክፍል ለማጥመቅ መነሻ ያደረጉበት ቅኝቱ ሙሉ ለሙሉ አማራ ብለው በመደቡት የህብረተሰብ ጥላቻ ላይ መነሻ ያደረገ ነው።የዚህ ጽሁፍ ማእከላዊ ነጥብ ይኼው ነው። ምክንያቱም ኢትይጵያዊ ብሎ
ወጥነት ያለው ዘር እስከሌለ ድረስ ኢትዮጵያን እንደ አገር ተቀብሎ ዘርን መሰረት ያደረገ የብሄርተኝነት ጥያቄ ማንሳቱ የሚያዋጣቸው አለመሆኑን በጠዋቱ ስለተረዱት የደደቢት ማኔፈስቶም እንደሚገልጠው ቀላሉ መንገድ “አማራ የሚባል በዘሩ ተደራጅቶ የሌላውን ማንነት የሚጨፈልቅ ህዝብ አለ” ብሎ እርሱኑ ጠላት አድርጎ በማራገብ የሚሰማቸውን የበታችነት ስሜት በዘር ጥላቻ ለውጠው በማራገብ ንቅናቄውን ማሳደግ ነበር የፈለጉት። ያደረጉትም ይኽንኑ ነው።ጥያቄው አገሪቱ የብዙ ብሄረሰቦች አገር ሆና ሳለ ከሌላው በተለየ መልኩ እንዲህ አይነቱ አጀንዳ እንዴት በኦሮሞውና በትግሬው ላይ ለምን ተለይቶ ወጣ ለሚለው ጥያቄ ግን ሁለት ጭብጦችን ማስቀመጥ ይቻላል።
፩ የኦሮሞን የብሄርተኝነት ጥያቄ አሁን በሚታየው መልኩ የተጠነሰሰው ሜጫና ቱለማ በሚባለው የኦሮሞ መረዳጃ ማህበር ውስጥ ሲሆን መስራቾቹም የወለጋ ጴንጤ ቆስጤዎች ነበሩ። እኒህ ስብስቦች ኦርቶዶክሳዊ ማንነት በተላበሰው የአገሪቱ ገጽታ ላይ ጥላቻ የነበራቸውና ኦርቶዶስ ቤተክርስቲያን ላይ ያላቸውን ጤነኛ ያልሆነ ስሜት ወደ ዘር
አውርደው አማራው ሁሉ ኦርቶዶክስ ኦሮሞው ሁሉ ጴንጤ ነው የሚል ስያሜ በመስጠት; ኢትዮጵያውያንን አቢሲኒያዊ የሆኑና ያልሆኑ በማለት በሁለት በመክፈልና ብሎም ከረጅሙ የታሪክ ዳራ ራሳቸውን በመለየት ማንነታቸውን የዘር ቀፎ ውስጥ ጨመሩት። ይሕ ነገር ዛሬ በአዲሱ የነጃዋር እስላማዊ ትውልድ እስከተተካበት ግዜ ድረስ በኦሮሞ ብሄርተኝነት
ስር ፕሮቴስታንታዊ መንፈስ የነበረው ንቅናቄ ሆኖ ቆይቶዋል።
፪ የትግሬ ብሄርተኛ ፈጣሪ ቀዳማዊ ወያኔዎች ግን ይህን የበታችነት ስሜትና ጸረ አማራነትን መነሻ ያደረገየዘረኝነት ልክፍት ውስጥ የገቡት የአማራው ማእከላዊ መንግስት ከዳማት ወደ ሳባ ከሳባ ወደ አክሱም ዘመእያተሸጋገረ በመጣው መንግስታዊ አስተዳደር ውስጥ ዛሬ አክሱም በሚባለው አካባቢ ሰፍረው ለነበረው የአማራ ነገስታት ከአምስተኛው ክፍለዘመን ገደማ ጀምሮ ከደቡብ አረቢያ ሰርገው የገቡት ትግሬዎች በዋናነት የ አሽከርነት
ስራ ይሰሩ ስለነበር በሂደት ማእከላዊ መንግስቱ ወደ መሃል አገር ሲዛወር ትግሬዎቹ በዚያው በአክሱም አካባቢ ተወስነው መቅረታቸው እንዲሁም ይኽ ሰሜናዊ አካባቢ ለረጅም ዘመን ሰው የሰፈረበትና የተራቆተ በመሆኑ የተነሳ
ለእርሻ ስራም ሆነ ለኑሮ አመች ባለመሆኑ ትግሬዎች እዛው ተቆርጠው ቀርተው በተፈራረቀባቸው የረሃብ፣ የችጋር እና
የሰቀቀን ኑሮ መግፋታቸው ዛሬ ድረስ እንደ ነቀርሳ ደዌ አልሽር ያለ የውስጥ ቁስላቸው ሆኖ መቅረቱ ብቻ ሳይሆን
አኡን ድረስ ለገቡበት ምንም አይነት የይሉኝታ ጫፍ የሌለው ዘረፋ ፣በቀል፣ ጭካኔና አልጠግብ ባይነት ሁሉ መደበኛ
ማንነታቸው እስከ መሆን ደረሰ፨
ትግሬዎቹ ሲጀመር ወደ አመጽ ደረጃ ያደገ የብሄርተኝነት ስሜት ባያዳብሩም ኢትዮጵያን ሊወር ከመጣ ባእድ ሁሉ ጋር
እራሳቸውን የተሻለ ባንዳ አድረጎ በማቅረብና ከጠላት ጋር በመተባበር የመሃል አገሩን ህዝብ ሲያደሙ ኖረዋል።
ነገር ግን እንደ ብሄር ተደራጅተው በራሳቸው ንቅናቄ የፈጠሩት በቀዳማዊ ወያኔ መሆኑ ግልጥ ነው። ይኽ ነቅናቄ
ደግሞ ከላይ እንደተጠቀሰው ጸረ አማራዊ እንጅ ጸረ ኢትዮጵያዊነት ነው የሚል አልነበረም። የቀዝቃዛውን ጦርተንት
ማለቅ ተከትሎ የመጣው የአለም ጆፖለቲካዊ ለውጥ ምክኛት ሆኖ የትግራይ ብሄርተኞች ትልቂቱን አገር ለመግዛት ወደ
ስልጣን በመጡ ማግስት ጀምሮ ዛሬ ድረስ እንደ መዥገር የተጣበቁንበት የማይጠረቃ ስግብግብነታቸውን ላስተዋለ ማንም
ሰው አንድ ብለው ወደ በረሃ የገቡበትን ትክክለኛ ምክንያት እነርሱ እንደሚሉት ለሰላምና ለዲሞክራሲ እንዳልሆነ
የሃያ አምስት አመት አኗኗራቸው ምስክር ነው። ዛሬ ወያኔ በዘረፋ ሱስ ተጠምዶ የሚውለውን ያህል የነ ገላሳ ዴልቦ
ኦነግም ወደ ስልጣን ቢመጣ ኖሮ ያልነበረ ካርታ ፈጥሮ እንደ አገር ለመቆም ከመጣር ባሻገር የጼንጤኮስጤ ቸርች
በመገንባት ይጠመድ የነበረ ሲሆን የነጃዋር ቡድን ደግሞ በለስ ቢቀናው ዘመኑን ሙሉ መስኪድ በመገንባት
እንደሚጠመድ ከውስጥ ስሜታቸው ከሚነዝራቸው ማንነት ማወቅ ይቻላል።
ፕሮፌሰር መስፍን አማራ የለም ሲሉ ምን ማለታቸው ነበር?
በአማራ ጥላቻ ሰክረው አዲስ አበባ የገቡት ወያኔና ኦነግ እድሉን ሲያገኙ በውስጣቸው ይዘው የመጡት የኤክሶኖፎቢያ
ቫይረስ በጸረ አማራና ጸረ ኦርቶዶክስ እርሾ ተቦክቶ የተጋገረ ስለነበረ አማራ ብለው መደብ ያበጁለትን ህዝብ
ለይተው የጥቃት ኢላማ በማድረግ በማንነቱ እንዲሸማቀቅ በፖሊሲ ደረጃ የተደገፈ የማያቋርጥ ፕሮፓጋንዳ ከማካሄድ
ጀምሮ ፣ የታሪክ ወንጀለኛ አድርጎ በመፈረጅ ከማንኛውም አገራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መዋቅር እንዲገለል
ማድረግን ስራየ ብለው ከመያዝም ባሻገር አልፈው ሄደው ከኢትዮጵያዊ ሰውነት አውርደው በአማራዊ ማንነት ብቻ
እውቅና እንዲወስድና እነሱ በሰሩለት የዘር ቅርጫት ውስጥ ገብቶ እንዲቆጠር ከሰማይ በታች የሚችሉትን ሁሉ
አድርገዋል።ይኽ ነገር ወንጀሎቹ ነገ በታሪክ ፊት የሚቀርቡና ምናልባትም ብዙ ዋጋ የሚያስከፍላቸው መሆኑ አሌ
አይባልም፣፥ሆኖም ግን ግን በወቅቱ በኦነግና በወያኔ በየቦታው ይፈጸምበት የነበረውን የተቀናጀ የጅምላ ግድያ፣
ዘረፋና ስደት ተከትሎ ጥብቅና ሊቆሙለት የሞከሩት ፕሮፌሰር አስራትና ጉዋደኞቻቸው ሲሆኑ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን
በማድረግ ነገር ግን የ አደጋውን ስረ መሰረት፣የወያኔና ኦነግ ያመረቀዘ ቁስል መነሻ አካሄዱና ዘላቂውን መፍትሄ
በማመላከት እረገድ ወሳኙ ነጥብ በደንብ የገባቸው ከሃኪሙ ፕሮፌሰር አስራት ይልቅ የማህበረሰብ ሳይንስ ሊቀ
ሊቃውንት የሆኑት የንታ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ነበሩ።ባጭሩ አማራ የለም ነበር ያሉት። ይኽንን ነገር
ለመጀመሪያ ግዜ ሲናገሩ ዛሬ አማራ ሆነን አድገናል ከሚለው የቤተ አማራ አዲሱ ትውልድ በላይ በወቅቱ በጣም
የተቃጠሉት ወይንም የደነገጡት የወይኔና የኦሮሞ ብሄርተኞች ሲሆኑ ምክንያቱ ለምን እንደነበር በደንብ ልብ ማለትና
ለምን በዛ ደረጃ ነርቫቸው እንደተበጠሰ ሆደ ሰፊ ሆኖ ላስተዋለ ሰው የወያኔ የዘር ፖለቲካ የቆመበት ዋልታና
ማገር የቱ ላይ እንዳለ በደንብ ከመረዳት አልፎ የክትባቱን መድሃኒት… ከበሽታው ለመስራት ግማሽ መንገድ መሆኑን
ለመረዳት አንዳች ብዥታ ሊኖረን አይገባም::
ጨዋታው እንዲህ ነው። ከላይ ባጭሩ ለማሳየት እንደተሞከረው የትግራይ ባንዳ እርዝራዦችና እራሳቸውን የኦሮሞ
ተዋካይ አድርገው ያቀረቡ ጆሮ ጠገብ የኦነግ አቀንቃኞች መነሻቸው ወይንም የቆሙበት ዋነኛ መሰረታቸው ጸረ
አማራነት ላይ በመሆኑና የፕሮፌሰር መስፍን አማራ የሚባል ዘር የለም ማለታቸው ደግሞ ይዘው የመጡትን አዲሱን
የዘረኝነት ፖለቲካ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስለሚደረምሰው እነ መለስ በዛ ደረጃ ቢያብዱ የሚደንቅ
አይሆንም።ወያኔዎች ከጽንሰታቸው ጀምሮ ይሞትልናል ይደግፈናል የሚሉትን ህዝባቸውን ያጠመቁበት፣ ኢትዮጵያ የምትባል
አገር የማያይ፣ ዘረኛና ጠባብ ትውልድ በመፍጠር አላማቸውን ለማሳካት ለሞት ኢንዶክትሪኔት ያደረጉበት ዋነኛው
ግብአት ይኼው ጸረ አማራ የዘር ፖለቲካ ነው።ይኽም ሂትለር በጸረ አይሁዳዊ ፕሮፓጋንዳ ድፍን ጀርመንን አስክሮ
ድፍን አውሮፓን በሞት ሰረጋላ ካጋዘበት አሳፋሪ ታሪክ ቅንጣት ታክል ምንም ልዩነት የሌለው ነው፥፥ በርግጥ የነ
መለስ ቁስል ማከኪያው ሰበዙ ጸረ አማራነት ላይ እንደቆመ ሌላው ምልክቱ ከትግራይ ተነስቶ ሰሜን ሸዋ የደረሰው
የትግሬ ጀሌዎች በባዶ እግሩ የሚሄድ ደሃ አማራ አይተው መደንገጣቸውን፣” አማራ ብላችሁ ስታዋጉን የኖራችሁት
እንደዚህ ካለ ደሃ ህዝብ ጋር ነውን፧” ብለው በመጠየቃቸው የተደናገጠው ህወሃት የለም የአማራ ገዥ መደብ የሚባል
ሌላ አይነት መደብ አለ ብሎ ለማምለጥ መሞከሩና በመልሱም ያልረኩት የተወሰኑ የወያኔ ጀሌዎች መሳሪያቸውን
አስረክበው ወዳገራቸው መመለሳቸውን ያነበብነው እውነታ ነው።
አማራው ማነው?
ምንም ይሁን ምን ይኽ ህዝብ እራሱን ችሎ የተፈጠረ ህዝብ ይሁንም አይሁን ነገር ግን አገሪቱን ለብዙ ዘመናት
በበላይነት በማስተዳደሩ የተነሳ የአገሪቱን መልክና ደገኛ ታሪኩዋን በመልኩ ሊቀርጽ ችሏል። ይህንንም ተከትሎ
ቋንቌውን አገር አቀፍ ለማድረግ በመቻሉ የተነሳ የራሱ ማንነት የአገሪቱ ማንነት ወይንም የአማራ ብሄርተኝነት
ከኢትዮጵያ ብሄርተኝነት አንድ ወጥ ሆኖ መውጣት በመቻሉ እራሱ አማራ የተባለው ህብረተሰብ ከማንነት በላይ ከፍ
ብሎ ወደ ሰውነት ደረጃ ለማደግ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጠረ። በዚህ ምንነት የተቃኘ ማህበረሰብ “ጎጤ”
“አካባቢየ” ሳይል ኢትይጵያን ፈልጎ የመጣን ወራሪ ሁሉ እንደ ኢትይጵያዊ ዋጋ ሲያስከፍል ኖረ። በዚህ የተነሳ
በድል ላይ ድል በወኔ ላይ ወኔ በጀግንነት ላይ ሌላ ጀግንነት እየደራረበ በቀላሉ ማንም አሳንሶ ሊያየው
የማይቻለውን በጋለ ማረሻ የተተኮሰ የአቸናፊነት ስነ ልቦናን ተቀዳጀ። ከላይ እንዳነሳነው ራሽያና ሰርቢያ ፤ላይ
የምናየውን የአትንኩኝ ባይነትን ገንዘብ አደረገ። በጣም ጤናማ ነገር ግን በጣም ውስብስብ በሆነ የታሪክ ሂደት
ውስጥ አልፎ ወደ ሰውነት ደረጃ ያደገው ይኽው የህብረተሰብ ክፍል እራሱን በዘሩ ከመጥራት ይልቅ ጎንደሬ ሸዋ
ወሎዬ ጎጃሜ ብሎ ማየቱ፣ የዘፈኑ የቅኔ መወድሱና የፉከራ አይነት ሁሉ ያለው ወጥነት ያለው ሲሆን ይህንን ለሺዎች
አመታት የዳበረ ሂደት (ፕሮሰስ) በወቅታዊ የፖለቲክ ግርግር አስታኮ አንድ ፋሲል ደመዎዝ የሚባል ዘፋኝ አማራ
የሚል ዘፈን በማዘፈን ብቻ እንደ ሌሎቹ የጎሰነኝት ልክፍተኞች ሰዎች “በማንነቴ ምን አሉኝ ይሆን?” የሚል
ኢንሰኪዩሪቲ የሚሰማው ዘር እፈጥራለሁ ማለት ሞኝነት ነው።
እውነታው ይኽ ከሆነ ለዚህ አይነት የብሄርተኝነት ስሜት ማቆጥቆጥ ሌላው መነሻ ምንድን ነው ብለን ብናስብ ያው
የወያኔ የዚህን የመደብ ክፍል ለይቶ ማጥቃት “እትይዮጵያን ድርና ማግ ሆኖ ያስተሳሰረልኝን ገመድ በቀላሉ
ለመበጣጠስ ያስችለኛል” ብሎ ማመኑ ሲሆን እንደ አጠቃላይ የትግል ተሞክሮ ይኽ የህብረተሰብ ክፍል “ከትግራይ
ጀሌዎች እና በምእራባውያን የኒው ወርልድ ኦርደር አራማጆች ከውስጥና ከውጭ በተቀናጀ ደረጃ የተጋረጥበኝ አደጋ
አለ “ብሎ ከማሰብ የዘለለ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ለምን ቢባል አማራ ከየትም ይሁን አሁን /ወቅታዊውን አደጋ
መነሻና መድረሻ ምክኛት በማድረግ ብቻ ለሽህዎች ዓመታት ያዳበረውን አገራዊ ብሄርተኝነት እንደ ካቦርት አውጥቶ
ጥሎ አንድ ግዜ ከደረሰበት ከፍ ያለ ልዕልና ወርዶ ወደ ዘር ማንነት ደረጃ መኮስመን ይችላል ብሎ ማሰብ የማይሆን
ቤተ ሙከራ ነው።
ማንነት ድሮና ዘንድሮ
ለዘመናት እንደሚታወቀው ሰው ማንነቱ የሚሰፈርባቸው መስፈርቶቹ በጣም ውሱኖች ነበሩ። ዘር፣ ሃይማኖት፣ የቆዳ
ቀለም፣ እና ጾታ ይመስሉኛል። አንድ ተጽእኖው የሚገዛኝ ሰው በአንድ አለማቀፍ ኮንፈረንስ ላይ አምስት አይነት
ማንነት ያላት ሴት ቀርባ ነበር ብሎ አጫውቶኛል።ይኸውም;
አረብ ናት፤ ማንነት ነው።
ኦቢሲቲ (የውፍረት በሽታ) አለባት፤///ማንነት ነው።
ፌሚኒስት ናት፤ማንነት ነው።
ሶዶሚ ናት፤ማንነት ነው።
ቬጋን ናት፤ማንነት ነው።
እንግዲህ በመሰልጠንም በሉት በመስይጠን ሰው እንዲህ ወርዶ ወርዶ እንደ ጥጥ መፈርቀጥ ከጀመረና አስር ሺህ
አይነት ማንነት በፈጠረ፣ ለማንነቴ እውቅና ስጡኝ ባለ ቁጥር ወደ የት ልናመራ እንደምንችል ግልጥ ነው። በዚህ
ሁሉ ስሌት ስናየው ግን አማራ የተባለ የህብረተሰብ ክፍል ከማንነት ወጥቶ ወደ ሰውነት ደረጃ ያደገበትን የመንፈስ
ከፍታ እንደ ሰጋቱራ ጠቅጥቀን ወደ ዘር እናወደዋለን ማለት እንደ ሰው ማደግ የከበዳቸው የደደቢት ጭንጋፎች “እኛ
ታመናልና አንተም መታመም አለብህ” ለሚልው ቅዠታቸው መሳሪያ መሆን ነዉ። አማራነት ዘር ነው ብለው ከሚያምኑት
በላይ አማራነት እንደ ትግሬ ወይንም ሃዲያ ወይንም ኦሮሞ ዘር አይደለም ብለው በጣም በርካታ የታሪክ ሰነድ
የሚያቀርቡ ስመጥር ልሂቃን አሉ። ለዚህም ከሚጠቅሱዋቸው በርካታ የታሪክ ፈሰቶች የሚያጠነጥኑት የአክሱም የሰፈራና
የወታደራዊ ልዩነቶች እየጠበቡ ሄደው በያቅጣጫው ሰራዊቱን ሲያሰማራ ለም የሆነውን የአባይና ገባር ወንዞችን
ከሱዳንና ከግብጽ ቆላማ ቦታዎች ከሚፈልሱ አህዛቦች ለመቆጣጠር የማያቁዋርጥ ዘመቻ ተደርጓል። በዚያ ላይ የአክሱም
አካባቢ መሬቱ እየተራቆተ መምጣ፣ የቤጃና የዮዲት በአክሱም አስተዳደር ላይ የፈጠሩት መናጋትና ማእከላዊ መንግስቱ
በደረሰበት መፍረክረክ ወድ ሸዋ መሸሹ ይህን ለስርጭቱ አስረጅ ነው። ሆኖም ግን የተለያዩ የታሪክ ክንዋኔዎችን
እንደ አስረጅ ሁኔአታዎች በማገጣጠም የተደረሰበት የታሪክ ጭብጥ የአክሱም ሰራዊት አገነባብ ዘመቻ አፈጻጸምና
ከተሸናፊ ህዝቦች ጋር የነበረው ግንኙነት የሚያሳየው ነገር አለ ባዮች ናቸው። ይልቁንም ሰራዊቱ በአብዛሃኛው
አገዎች እንደሚበዙበትና ከሰፈረበት አካባቢ ካሉ ሰዎችም ጋር በነበረው ግንኙነት ጦሩ የራሱ የሆነ የሚስጥር
መግባቢያ ቁዋንቁዋ እንዳስፈለገውና መጀመሪያ ላይ ግእዝ ተናጋሪ የሆነው ዝቅተኛ የወታደሩ ክፍል ሴማዊ ከሆነው
የአገው ቁዋንቁዋ ጋር እየተዳቀለ ሄዶ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ላይ ሳይቀር እየሰረጸሰና ወጥ የሆነ አመርኛ
የሚባል ቁዋንቁዋ ሊፈጠር ችሎዋል ይላሉ። ይሕ በወታደሩና በቤተመንግስቱ ዘንድ የሚስጥር መነጋገሪያ ሆኖ የቆየው
ቁዋንቁዋ በሂደት ከአገውኛና ከግእዝ በላይ እራሱን ችሎ የ አገሪቱ መግባቢያ ቁዋንቁዋ ሆነ ይላሉ። ዝርዝሩ በጣም
ሰፊ ነው።
እንግዲህ አሁን ጥያቄው መሆን ያለበት አማራ የሚባል እራሱን ይቻለ ዘር አለ የለም የሚለው ሳይሆን አማራ ኖረም
አልኖረም ይሕ የህብረተብ ክፍል በታሪክ አጋጣሚ በተጫወተው ሚና፣ በነበረው የስንለቦና እና የስልጣን የበላይነት
የተነሳ ከነበረበት ማንነት ወደ ሰውነት ደረጃ ያደገ ፣ በማንነቱ የማይሰማው፣ ጎጠኝነት እርቆ የሄደ፣ ሲዳማ
ከምባታ፣ ኦሮሞ ትግሬ ቀርቶ ነጭ ጥቁር ብሎ ሰውን የማይለይ ብቻ ሳይሆን በማንነቱ በምንነቱ የማይሰማው፣ ሌሎች
በዘራችን ተናቅን ብለው ስር በሰደደ የስነ ልቦና ጠባሳ እንደሚሰቃዩት የሚሰቃይ ስነልቦና የለለው ማለት ነው።
“ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” ኢትዮጵያዊነት እና ብሄርተኝነት
አንድነት ሃይል ነው የሚለው መፈክር የደርግ ስሪት ኢስኪመስል የተለመደ ነበር። ያው ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
እንደሚሉት መሆኑ ነው። ይኽ እንደ መነሻ እውነትነት ያለው ነገር ቢመስልም አንድነት የሚፈጠረው ከምን አይነት
ሃይል ጋር ነው የሚለው ነገር ላይ ነው ወሳኝ ነጥቡ። The collapse of quantum wave
function የፊዚክስ ህግ አለ። በአካሄድ አንተ የምትከተለውን መስመር የማይከተልና የራሱ ቅኝት ያለው ሃይል
ጋር ግንባር ብትፈጥር ጉልበት በመሆን ፋንታ ይዞህ ሊጠፋ ይችላል እንደ ማለት ነው።
ባለፈው ሁለት አስርተ አመታት ውስጥ የተቃዋሚው አካል ወይ ጠባብ ብሄርተኝነትን ወይንም አገራዊ አጀንዳን መሰረት
ያደረገ አሰላለፍ የተከተሉ ሲሆን በውስጥ ያላቸውን ልዩነት ምን ያህል አብሮ ያስኬዳቸዋል የሚለውን ሳያዩ ነገር
ግን ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ በሚል የህዝብ ግፊት ሲናጡ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ ስንዝር ሳይራመዱ
መንገድ ላይ ባክነው ቀርተዋል። መሰረታዊ ምክንያቱ ግን ሁለቱም በጣም ከተራራቁ እና አስታርቆ ለመሄድ
ከሚያስቸግሩ መሰረታዊ ችግሮች ይመነጫሉ።
፩ የብሔርተኝነትን አላማ የሚያራምዱት ድርጅቶች ወይንም ድርጅቶቹን የሚያንቀሳቅሱት ሰዎች አንድ የሚሰማቸውና ወደ
ፎቢያ ደረጃ ያደገ የሚመስል ሰዎች ትግሬ ስለሆንኩ ብቻ እንዲህ ይሉኛል፣ ከንባታ ስለሆንኩ እንዲህ ይሉኛል ወዘተ
የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው አንዱ ችግር ነው።
፪ ለምሳሌ እራሱን የአዲሱ ኦሮሞ ትውልድ ምልክት አድርጎ የሚያየው ጃዋርና የአንድነት ሃይሉ ምልክት የሆነው
ዲባቶ ብርሃኑ ነጋን ወደ አንድ ቦታ ላይ ለማምጣት ይነጋገሩ ቢባል ጃዋር አንድ ብሎ የሚነሳው እኔ ኦሮሞ ነኝ፣
እኔ እስላም ነኝ ከሚል ማንነት ሲሆን ዲባቶ ብርሃኑ ደግሞ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚለው ይሆናል።ይኽ የሚያሳየው
የ አንድነት ከኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ወርዶ እራሱን የዘር ቅርጫት ውስጥ ፈልጎ ለማግኘት የማይችል መሆኑ ላይ
ነው።ኩነቱ አንድ የ አሜሪካን ዜግነት ያለውን አበሻ ፓስፖርት ስላለው ብቻ ነጩ አሜሪካዊ የሚሰማውን ስሜት
እንዲሰማው የመጠበቅ ያህል ሞኝነት የመሆኑ ነገር ላይ ነው። የአሜሪካን ፓስፖርት ያለው ማለት እና አሜሪካዊ
በሚለው መካከል ያለው የስነልቦና ግንኙነት ነው። በሁለቱ መሃል ያለው እርቀት የ አትላንቲክ ውቅያኖስን በዋና
የማቁዋረጥ ያህል አታካች በመሆኑ ይኽን ትግል ወደፊት በመግፋቱ በኩል በሁለቱ መሃል አማካኝ ቦታ ለመፈለግ
ከሰማይ ቢታች የሚደረግ ምንም አይነት ድርድር የትም አይደረስም:: እስከዛሬ ድረስ የሆነውም ይኼው ነው።
አዲሱ በወያኔ የዘር ፖለቲካ የተቃኘው የአማራ ትውልድ ልብ ያላለው ነገር
፩ በአሁኑ ሰዓት አማራ ተብሎ በተፈረደው ህዝብ ላይ የተቃጣውን አደጋ በመከላከል እና ብሄርተኝነትን በመፍጠር
መካከል ያለውን ግንኙነት ግዜ ወስዶ አለመመርመሩ አንዱ ችግር ነው።
፪ ድፍን ሃያ አመስት አመት ሙሉ በወያኔ ሲቀነቀን የኖረውን አማራን ህዝብ የማጉደፍና የማዋረድ ዘመቻ እየተጋተ
በማደጉ የተነሳ አማራ ለዘመናት የከፈለውን መስዋእትነትና የደረሰበትን ከፍ ያለ የመንፈስ ልእልና አሳንሶ
እንዲያይ መገደዱ ሌላው ችግር ነው::
፫ በዚህ ሁሉ ተዛማጅ ግንኙነት “አማራውን ወደ ዘር ማንነት አውርጀ በማደራጀት ያለውን ችግር እቀለብሳለሁ” ብቻ
ሳይሆን “ሌላ መንገድም የለውም ብሎ ማመኑ” ሌላው ችግር ነው።
፬ ይሕ የአማራው ብሄርተኝነት የመፍጠር ጉዞ ቢሳካ ትልቁ አስተዋጾ የሚያደርገው እራሱ አማራውን ከመጥቀም ይልቅ
ብሔርተኝነታቸውን በጸረ አማራነት ላይ መነሸ አድርገው ለተፈጠሩት የዘመኑ ተውሳኮችና እነርሱን ለሚንከባከቡት
የምእራብ መንግስታት መሆኑን ልብ አለማለቱን ነው።
፭ ይኽን ሂደት ማለት በሌላ አነጋገር
ምንፍቅና የተሞላባቸው የሃይማኖት አስተምህሮዎች ሰዎች በተጋድሎ ጸንተው እንዴት ወደ መንፈስ ከፍታ እንደሚወጡና
እራሳቸውን ቤተመቅደስ ማድረግ እንደሚችሉ ማስተማር ሲገባቸው ጭራሽ ሰዎቹ እራሱን ሃይማኖቱን እነርሱ ወዳሉበት
የዘቀጠ አስተሳሰብ በማውረድ እራሳቸውንም ሌላውንም ለመሸንገል የሚወርዱበትን የተሃድሶ አስተሳሰብ አለ ።ተሃድሶ
ወይንም ረፎርማአሽን ይባላል። በኢትዮጵያ ብሄርተኝነት የሚገለጠውንና እንደሰው ያደገውን አማራነት ወደ ዘርህ
ወርደህ አስብ ማለትም ከዚህ የወጣ አይደለም።
እንደማጠቃለያ
ሰዎች አማራ ማነው በሚለው ትንታኔ እንደ መረጃ ምንጫቸው እና እንደ ግንዛቤያቸው ከተለያየ ማእዘን ተነስተው
የየራሳቸው ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።
፩ ሁሉም ብሄረሰቦች በየዘራቸው እና በየቁዋንቁዋቸው ሲሸጎጡ ከዛ የተረፈውና የህብረተሰብ አማራ ሆነ የሚሉ አሉ
፪ ከላይ በተወሰነ ደረጃ በአመዛኙ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲውን ቦላያን ላይብረሪ መነሻ አድርጎ የተጻፈው የዶር
አሰፋ መጽሃፍ አማርኛን ከአገውና ከግዝ ሽራፊዎች እየተውጣጣ የተፈጠረ የሚስጥር ቁዋንቁዋ ሆኖ በሂደት ወደ
ህብረተሰቡ መስረጹንእና ያም ህዝብ አማራ መባሉን ይገልጣል
፫ ከዳማት ወደ ሳባ ከሳባ ወደ አክሱማዊነት ከአክሱማዊው ግእዝ ወደ ዘመናዊዊ አማራኛ የሚናገረው ቋንቋ
እየተቀያየረበት የመጣ አንድ ዘር አንድ ህዝብ ነው ብሎ የሚያምን አለ
፬ ክህነትን ከመልከ ጸዴቅ የተቀበለ ከኦሪት ታቦቱን ከሓዲስ መስቀሉን ገንዘብ ያደረገ እንደ አይሁዳዊነት
አማርነት ዘር ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትም ጭምር የሆነ ነው ብሎ በዚሁ የሚኖርም አለ። ይሕ በአመዛኙ ከሰው ጋር
ሳይቀር ሲጣላ ከዛሬ ጀምሮ እኔና አንተ እስላምና አማራ ነን ብሎ የሚምለው እና የሚገዘተው ፍልስፍናው ወደ ቤተ
አማራ የሚቀርበው አካል ነው።
የዚህ ጸሃፊ እይታ የትኛው ነው ትክክለኛው የሚለው ነጥብ ላይ መስመር ማስመር ሳይሆን እንደ ህብረተሰብም
እንዳገርም የሚሰራው ለአገሪቱም ከገባችበት ቅርቃር ወጥታ ወደ ተሻለ መንገድ እንድትሄድ አሁን ባለው ተጨባጭ
ሁኔታ የሚያዋጣው የቱ ይሆን የሚለው ላይ ነው።
ይኽም ማለት አንድ ድሮ የሚያውቀኝና ያኔ የተለየኝ የልጅነት ጉዋደኛየ የልጅነት ፎቶ ግራፍፌን ይዞ እኔን ፍለጋ
ጥንት ትቸው ወደ ወጣሁት መንደሬ የመሄድ ያህል ከንቱ ሙክራ ነው። ያ የጥንት ማንነቱ አድጎና ተለውጦ በተለየ
ቁመና በሌላ ስፍራ ያለን ሰው ፈልጋ መሄድ ሞኝነት የመሆኑን ያህል አማራው በታሪክ አጋጣሚ በብዙ ታሪካዊ
ተጋድሎና ውጣ ውርድ ወደ መንፈስ ከፍታ የወጣ፣ ከዘር ማንነት አምልጦ ወደ ሰውነት ደረጃ ያደገና እንደ ኮካኮላ
ከጠርሙስ ገንፍሎ ኢንላይትንድ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል ነው። በየትኛውም መልኩ በዚህ ደረጃ ያደገን አካል
ዘረኝነት አስክሮዋቸውና ማንነታቸው ቁስል ሆኖባቸው ደደቢት እንደገቡት የትግሬ ወለፈንዲዎች ተመለሰህ የቁልቁሊት
ውረድና ጥበብ ማለት የገነፈለውን ኮካኮላ መልሶ ወደ ጠርሙሱ ለማስገባት የመሞከር ያህል የሞኝነት ጉዞ
ነው።የአማራውን ብሄርተኛ ፍለጋ መንገድ የገቡትን ሳስባቸው ሕያውን ክርስቶስ ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ
የተባሉትን የእየሩሳሌም ሴቶችን ከንቱ ድካም ያስታውሰኛል።አምናለሁ፤ ይኽ ህዝብ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ለዘመናት
ባዳበረው የስነልቦና የበላይነት ተጠቅሞ የራሱንም ሆነ የአገሪቱን ክብር ያስመልሳል ብዬ ከልብ አምናለሁ።
“ዘ-ጸሃፍኩ ጸሃፍኩ”
የጻፍኩትን ጽፌያለሁ! …እንዲል ወንጌሉ:

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s