በፍ/ቤቱ የዐቃቢ ህግ ቁጥር እጥረት ምክንያት የአቶ ዮናታን ተስፋዬ ምስክር ሳይሰማ ቀረ፣ የመከላከያ ምስክርነት ተጠሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬም አልቀረቡም


የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የፓለቲካ መብቶች አክቲቪስት አቶ ዮናታን ተስፋዬን የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ጥር 29 ቀን 2009 ዓ.ም የፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ምስክር ዐቃቢ ህግ ባለመገኘቱ ለየካቲት 13 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋዬ አሉኝ ካላቸው ምስክሮች መካከል ማረሚያ ቤት የሚገኙት አቶ እስክንድር ነጋ (ጋዜጠኛ) እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ምስክርነትን ለመስማት በዋለው በዚህ ችሎት አቶ እስክንድር ነጋ የቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የዐቃቢ ህግ ቁጥር እጥረት ያለበት በመሆኑ የቀረቡትን የመከላከያ ምስክር መስማት እንደማይቻል የመሃል ዳኛው አስታውቀዋል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና ፍ/ቤት ተገኝተው የመከላከያ ምስክርነታቸን እንዲሰጡ ለማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ ቢፃፍም ፖስታ ቤት በትክክል ያላደረሰበትን ምክንያት ደብዳቤውን ያደረሱት የፖስታ ቤት ሰራተኛ በዕለቱ ከሠዐት በኃላ በዳኞች ፅ/ቤት ተገኝተው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡
አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለራሱ ምስክርነት ከመስጠቱ በተጨማሪ ወላጅ አባቱ ቀሲስ ተስፋዬ ረጋሳ፣ እህቱ ወ/ት ገዳምነሽ ተስፋዬ፣አቶ በፍቃዱ ሃይሉ፣በቀለ ገርባ፣ሙላቱ ገመቹ፣ዶ/ር ያዕቆብ ኃይሉ እና ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የመከላከያ ምስክር ሆነው መቅረባቸው የሚታወቅ ነው፡፡

ምንጭ: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s