ህወኃት/ ኢህአዲግ አገዛዝ የጠራውን የእርቅና ሰላም ውይይት አስመልክቶ  – ከቱሳ የኢትዬጵያ ትንሳኤ ድሞክራሲያዊ ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

ቱሳ የኢትዬጵያ ትንሳኤ ድሞክራሲያዊ ድርጅት
Tussa Ethiopian Salvation Democratic Orgaization

February 4,2017

ቱሳ የኢትዬጵያ ትንሣኤ ድርጅት በኢትዬጵያ አንድነት ፅኑ እምነት ያለው ብሔራዊ ድርጅት ነው! ቱሳ ማለት በወላይትኛ ምሰሶ ወይም ዋልታ ማለት ሲሆን ህዝቡ ለኢትዬጵያ አንድነት ቀንዓይ እንደመሆኑ ዛሬ አገራችን በምትገኝበት አሳሳቢ ሁኔታ ከሌሎች መሰል የድሞክራሲ ኃይላት ጋር ለኢትዬጵያ ትንሤኤ የሚታገል አጋር ድርጅት መሆኑን ለማመልከት ነው፤

ቱሳ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ January 13 እና 14 በተካሄደውና በርካታ ድርጅቶች በተገኙበትና በአሳሳቢው የአገራችን ወቅታዊ ጉዳዬች ዙሪያ በተካሄደው የሁለት የቀናት የምክክር ጉባኤም ባለድርሻ አካል ሲሆን በዚህም የኢትዬጵያ አገር አድን የቀውጢ ጊዜ ግብረ ኃይል ከመሰረቱ ዘጠኝ የአንድነትት ድርጅቶች አንዱ ነው።

እናት አገራችን ኢትዬጵያ በ1960ዎች የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግሥት ሕዝባችን የፊውዳሉ ሥርዓት አንገሽግሾት ለውጥ በመፈለጉ መሬት ለአራሹ የሚል መፈክር  አንግቦ ከዳር እስከ ዳር በመንቀሳቀሱ አፄው የሚኒስትሮች ሹም ሽር በማድረግ የሕዝብን ትግል ለማብረድ በርካታ ማማለያ ሙከራዎች ቢያደረጉም የኢትዬጵያ ህዝብ ከዳር እስከዳር እንቢኝ በማለት ጭራሽ ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ  አያጣፍጡ በማለት በተጋጋለ ስሜት በመንቀሳቀስ የአፄውን መንግስት እንዲያከትም አድርጓል።ሆኖም ከህዝባዊ ዕምቢተኝነቱ ባሻገር በወቅቱ ሁነኛ የተደራጀ ሃይል ባለመኖሩ ወታደራዊ አገዛዝ ስልጣን በመያዝ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በህዝባችን ጫንቃ ላይ በመሆን በጉልበት ስገዛ ኖሮ በስተመጨረሻ በዉስጥም በዉጭም የሕዝብ ብሶት በመበራከቱ ሳይወድ በግድ ስልጣኑን ለቋል ።

በቀጣይም እንደባለፈው “ብሶት የወለደው “በሚል ጠመንጃ አንግቦ የመጣው ወያኔ ትግራይን ለመገንጠል በነበረው ህልም በጂኦ ፓለቲካው ሁኔታና በባዕዳን ድጋፍ በለስ ቀንቶት የመላውን ኢትዬጵያ መንበረ ስልጣን ስይዝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 26 ዓመታት ያተረፈዉ ግድያ ፣ እስር ፣ እንግልትና ዘረኝነት ነው ። እንዲየያዉም መሬት ላራሹ መፈክር አንግቦ ለሕዝብ ክብር የሕይወት መስዋዕት ከፍሎ ያስገኘውን ድል በመንጠቅና ወደ ጎን በማድረግ መሬት የመንግስት ነው በማለት ከረጅም ጊዜ ጉልተኝነት የተላቀቀውን ገበሬ ከመሬቱ እያፈናቀለ በሚልዪኖች የሚከራዩ ሕንፃዎችን ለራሳቸውና ለካድሪዎቻቸዉ በመሓል ከተማ እየገነቡ ያከራያሉ ፣ ይንደላቀቃሉ ፤ ይኽው ምዝበራና ዘረኝነት አንሶ ወገኖቻችንን ለጅምላ እስር  ፤ እንግልት ፤ ለሞትና ለስደት እየዳረገ ያለዉን የህወኃት ኢህአዴግ ሰቆቃና ግፍ ያንገሸገሸው ሕዝባችን እንቢኝ በማለት በኦሮሚያ ፣ በደቡብ ኮንሶናቁጫ የመረረ ህዝባዊ እምቢተኛነት ትግል ሲያደርግ ምሬቱ የበዛበት ፣ ጨቅላ ልጆቹን ያጣውና ማንነቱን የተነጠቀው  አማራው ወገናችን ብረት በማንሳት የሞት ሽረት ትግል በማካሄድ ስልጣን የሰፊው ህዝብ መሆኑን በማስረገጥ ወደኃላ ላለመመለስ ቆርቶ እየታገለ ነው ፤ አገዛዙም ይህን ን በየቦታው የተዛመተውንና ህዝባዊ እምቢተኝነትለሥልጣኑም አስጊ እየሆነ በመምጣቱ የአስቸኳይ ጊዜ በማወጅ ይህንንም ሽፋን በማድረግ ፀጥታን በማረጋጋት ሰበብ ህዝባችን ላይ የጅምላ እስርና እርምጃ በመውሰድ እምቢተኝነቱን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም ላይ ይገኛል ።

ከዚህም አልፎ ይህንን ጊዜ ለመግዛት መልካም አስተዳደርና ሙስና መንስኤው አድርጎ በመሳል ስር ነቀል ጥያቄውን በተኃድሶ ስም ለማርገብ ብዙ ሙከራዎች አድርጓል ፣ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥም አሁንም በርካታዎችን በቁጥጥር ስር ከማዋሉም ባሻገር ዛሬም አንጋፋ መሪዎችን ጭምር በሽብርተኝነት ስም በየማጎሪያ ቦታዎች በማስገባት ላይ ይገኛሉ።

አሁንም በአንድ በኩል ህዝቡን በማፈንና በማሸማቀቅ በሌላ ጉኑ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሰላማዊ የድርድር እፈልጋለው በማለት ሰበብ በአምሳያው እንደአሸን የፈበረካቸውን የፖለቲካ ፓርቲወችን ጭምር በመጋበዝ ውይይት መጀመሩን ድርጅታችን በአፅዕኖት በመከታተል ላይ ይገኛል ፤ ማንም ወገን እርቅና ስላምን ሊቃወም አይችልም! ነገርግን በርካታ ወገኖቻችን በጠራራ ፀሐይ በጥይት ተቆልተዋል ይህ ከምርጫ 97 እነ ሺብሬን ጨምሮ ብዙዎች ለስር ነቀል ለውጥ ህይወታቸውን ከፍለውበታል እየከፈሉም ይገኛሉ፤ “ባለ ራዕይው መሪ” የነበሩት ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ለሥርዓት ለውጥ ቋፍ ላይ የደረሰውን የአዲስ አበባን ህዝብ ህዝባዊ ማዕበል ከሰማይ በታች በምንም ጉዳይ ልንስማማ ፈቃዳችን ነው በማለት ይህንን ሁሉ የህዝብ አልገዛም ባይነትን ትግል ጊዜ በመግዛት የቅንጅት መሪዎችን ለጅምላ እስር በመዳረግ ህዝባዊ ማዕበሉን በማፈን እነሆ ይህንን ትግል በህወኃት መሪነት ለአስራ ስድስት ዓመት እድሜ ሰጥተነዋል ፤

ዛሬም ደግሞ ከዚያን ጊዜ በላይ በብዙ ሺዎች በጅምላ ታፍሰው ታስረዋል በሺዎች ለጋ ወጣቶች የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል እየከፈሉም ነው ስለሆነም ይህ የተጀመረው ውይይት ከጥገናዊ ለውጥ ተላቆ ዘላቂ ሰላም ፣ ዕድገትና መረጋጋት የሰፈነባት እናት አገር ትኖረን ዘንድ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያሳትፍ የሽግግር መንግሥት ወይም አንድ የባላደራ መንግሥት መመስረትና በቀጣይም የዲሞክራሲያዊ ተቋማትን ከአንድ ገዥ መዳፍና ቁጥጥር ስር በማላቀቅ በነፃነት በአዲስ በመገንባት በነፃና ዴሞክራሲያው የምርጫ ሂደት ዲሞክራሲያዊት ኢትዬጵያን መገንባት ብቸኛው መንገድ ሊሆን ይገባል ፤

ይህ ባልሆነበት ካለፈው ታሪካችን ሳንማር ዛሬም ጥገናዊ ለውጥ እናት ሃገራችንን ከተመሳሳይ የህዝብ እልቂትና አፈና የማያከትም ይልቁንም የህዝባችንን ትግል እንዲነጠቅ የሚያደርግ በመሆኑ በአገር ቤት የሚገኙ የህዝብ ወገን የሆኑ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅድመ ምክክር በማድረግ በተወከሉ የጋራ ተወካዬች አማካይነት ለዘላቂ ለውጥ እንዲደራደሩ ጥሪ እናደርጋለን ።

ድል ለኢትዬጵያ ህዝብ!

ቱሳ የኢትዬጵያ ትንሣኤ ድሞክራሲያዊ ድርጅት

Phone USA 1+2022814459

Tussa Ethiopian Salvation Democratic Organization/ Email  tassaethiopia@gmailil.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s