አርበኛ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ – ቀሪን ገረመው

ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ በስማቸው እና በፆታቸው ሴት ናቸው ። በቆራጥነታቸው እና በጀግንነታቸው ግን የወንድነት ስም የተሰጣቸው ዝነኛ አርበኛ ነበሩ ። በሴትነታቸውም ቢሆን በዘመናቸው ከነበሩት ወይዛዝርት የበለጡ እንጂ ያነሰ ውይዝርና አልነበራቸውም ። በአርበኝነት ደግሞ እንኳን ለሴቶች ለወንዶች አርአያ የሚሆኑ ሙያ በማሳየታቸው በታሪክ ዓምድ የሚልቋቸው ወንዶች ጥቂቶች ናቸው ። ከፈጸሟቸው የጀብዱ ሙያዎች አንደንዶቹን ብናስታውሳቸው ለትውልድ ደስታ እና ኩራትን ያጎናጽፋሉ ።

አንድ ቀን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የኢጣልያ ሲሰቀል አልቅሰሻል ተብለው ተከሰው ከፋሽስት ከፍተኛ የጦር ሹማምንት ፊት ቀርበው ተጠይቀው ነበር ። ጀግናዋ ወ/ሮ ግን በዚያን ግዜ የፍርሃትና የሴትነት መንፈስ ሳያሳዩ ያላንዳች መርበትበት ቁርጥ ያለ አነጋገር ምንም ክሳቸውንም አላስተባበሉም ፣ << አዎ አልቅሻለሁ ፤ የእናንተ አገር ሴቶች በሰው አገር ቀንተው የጣታቸውን ቀለበት እያወለቁ ኢትዮጵያን ለመውረር ለመጡት ሽፍቶች ሲያበረክቱ እኔ አገሬ በባዕድ ሕዝብ ሲወረው መንግሥት ጠፍቶ የአገሩ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ ሌላ ሲሰቀል ለሰንደቅ ዓላማዬ ማልቀስ ይነስብኝ ወይ ? >> ሲሉ መልሰዋል ። ከዚህም በቀር ለአርበኞች ስንቅ ታቀብያለሽ ፣ ቀይ መስቀልን ትረጃለሽ በሚል ተወንጅለው ለጥያቄ ቀርበው ነበር ። ወይዘሮዋ ግን አሁንም በክሱ ሕሊናቸው ሳይሸበር << ሰለ ነፃነት ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው የሌሊት ቁርና የቀን ሐሩር ከሚገርፋቸው የአገሬ አርበኞች ጎን ተሰልፌ ጠላቴን መውጋቴ ቀርቶ የረኃብና የጥም መድኃኒት እያዘጋጀሁ መላኩ ቁም ነገር ሆኖ ነው የተጠየቅሁበት ? እኔ ይህን ባለማድረጌ ለሀገርም ባልቆረቆር እንኳን እንኳን እነሱ እናንተም እንደምትታዘቡኝ ይሰማኛል ። >> ሲሉ ለቀረበባቸው ክስ እጅግ አስደናቂ የሆነ ያገር ፍቅር የተሞላበት መልስ ቆራጥነት በተቀላቀለበት አነጋገር መልስ ሰጡ ።

በጠላት አደባባይ ቆሞ ይህን የመሰለ ኃይለ ቃል በመናገር ጠላትን ካስደነቁ ጀግኖች ወ/ሮ ሸዋረገድ የመጀመርያዋ ናቸው ። ወ/ሮ ሸዋረገድ ይህን መልስ በሰጡበት ሰዓት አንድ የፋሽስት ባለስልጣን << አርበኞችን ከረዳሽ እንግዲያ እኛን አትወጅማ ፤ >> ሲል ኃይለኛ ጥያቄ ቢያቀርብላቸው ታላቋ አርበኛ ወ/ሮ ሸዋረገድ ያላንዳች ፍርሃት << አዎ አልወዳችሁም ፤ ማን ነው የአገሩን ደመኛ የሚወድ ? >> ሲሉ እንደገና ጥያቄውን በጥያቄ መልሰውለታል ።

ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ልጅ ባለመውዳድቸው እናዝናለን ፤ ግን ሰው ሰሙን ሊያስነሳውና ሊያስረሳው የሚችለው በመውለድና ባለመውለድ አይደለም ። የተወለደው የተባረከና ቁም ነገረኛ ካልሆነ ቢወለድም እንዳልተወለደ ነው የሚቆጠረው ። እንዲያውም አንድ አንድ ልጆች በጀግንነትም በቁም ነገረኛነትም ሙያቢስ እየሆኑ ዘር ከሚያሰድቡ ክርስቶስ ይሁዳን ሰው ባይወልድ ይሻለው ነበር ሲል እንደተናገረው እነሱም ያልሆነ ልጅ ወልደው አሳድገው ስማቸውን በከንቱ ከሚያስነሱት መካን ሆነው በቀሩ በተሻላቸው ነበር ። እንግዲያስ የሰው ስም ሕያው ሆኖ ሊኖር የሚችለው ከመውለድ ይልቅ በጥሩ ሥራው ነው ። ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድም የልጅ መካን ቢሆኑም የታሪክ እናት በመሆናቸው ስማቸው በጀግንነት ታሪክ ውስጥ ለሰለዓለሙ ሕያው ሆኖ ይኖራል ።

ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ለአባታቸው ሴት ልጅ ናቸው ። ግን ሴትነታቸው ወንድነት ሙያ ከመፈፀም ሊያግዳቸው ባለመቻሉ የአባታቸውን ሰም ለማስጠራት ወንዶች አልቀደሟቸውም ።

ቀሪን ገረመው
የአርበኞች ታሪክ የተወሰደ !

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s