ወያኔ የመጨረሻውን እርሾ እየጋገረ ነው (መስቀሉ አየለ — ክፍል ፪)

መስቀሉ አየለ

መንግስትታ ሲባሉ ከውጭ በሚደረግብቸው የጦርነት ግፊት ብቻ እንደማይወድቁ የቀደሙትን ሁለት መንግስታት ተሞክሮ እንደ መነሻ እናያለን። እነርሱም ከውጭ ከነበረባቸው ተጽእኖ ይልቅ የውስጣዊውን ቅራኔ አስታርቆ መሄድ ተስኖዋቸው ከውስጥ በኩል በስብሰው እንደ ወደቁ ግልጽ ነበር።Snake on Tigrayan People's Liberation Front (TPLF) logo

እንደ መነሻ

የንጉሱ አስተዳደር በጣም ባህላዊ በሆነ አስተምህሮ ውስጥ የነበረው እና ባመዛኙ በጣሊያን ወረራ ዘመን በተጋድሎ ባለፈው አብዛሃኛው ማህበረሰባችን እንዲሁም ዘመናዊ ትምህርት ቀመስ ሆነው አለምን እንደ ሰደድ እሳት እያጥለቀለቀ በመጣው የኮሚኒዝም ጽንሰ ሃሳብ የሰከሩ አዲሱ ትውልድ መካከል ያለውን ተቃርኖ አስታርቆ ወደ ፊት ለመሄድ ተሳነው። ምክኛቱም የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ላይ የተሞከረው የ1953 መፈንቅለ መንግስት ንጉሱ ላይ ጥሎት ያለፈው ጠባሳና ያን ተከትሎ በዙሪያቸው ላይ ያሉትን ካቢኔቶች አምኖ መጓዝ በተሳናቸው ሰዓት አገሪቱን የተሰራችበትን የህብረተሰብ ድርና ማግ እንዲሁም የአለማቀፍ ፖለቲካውን የሃይል አሰላለፍ ምን መልክ እንደነበረው እንኩዋን በቅጡ ያልተረዱ እራሳቸውን “ደርግ” ብለው በመጡ አንድ መቶ ሃያ ያህል አስር አለቆች እጅ የንጉሱ ተሰልቅጠው ሽንት ቤት መቀበር የሶስት ሽህ አመት የእድሜ ባለጸጋ የሆነው ሞናርኪ ፍጻሜ ሆነ እንጅ ብዙ የተወራለት የተማሪዎች ንቅናቄ ለነጉሱ ውድቀት ይኽ ነው የሚባል አስተዋጾ አሳድሮ ነበር ማለት አይቻልም። በወቅቱ የተጻፉትን ኩታ ገጠም የታሪክ ድርሳናት ብናያቸው በጣም ጽንፈኛ ከሚባለው የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች ህብረት እንኩዋን ውስጥ ይወጡ የነበሩት መግለጫወች ብናያቸው በግብር ይቀነስ፣በመሬት ላራሹና በመሳሰሉት ነገሮች ላይ የአካሄድ ለውጥ እንዲደረግ እንጅ አንድም ግዜ ንጉሱ ይውረዱ የሚል ጥያቄ አንስተው እንዳልነበር ያስረዳሉ።

ደርግም ቢሆን ምንም አንኩዋን አንድ ብሎ ስልጣን ላይ ከዎጣበት ቀን ጀምሮ ከሱማሌ፣ ኢህአፓ ኢዲዩ ሻቢያ ወያኔ ሱዳን (አሜሪካ በሚሰራው የፕሮክሲ ጦርነት) ሁሉ ተጠምዶ የነበረ ቢሆንም ለርሱ መውደቅ ግን ትልቁን አስተዋጾ ያደረገው ከውጭው ይልቅ የውስጡን ቅራኔ አቻችሎ መሄድ የተሳነው ቀን ነው። በተለይም በተለይም የግንቦት ስምንቱ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ የአገሪቱ ስመ ጥር ወታደራዊ መኮንኖች ላይ ያ ሁሉ ፍጅት የፈጸመ ቀን ደርግ የገዛ እጁን በጎራዴ እንደ ቆረጠው ግልጽ ነበረ። በወቅቱ የአገሪቱ መከላከያ ጦር ከአምስት መቶ በላይ እዝ የነበረው ሲሆን ይሕንን ሁሉ ቦታ ለመሸፈን ምንም አይነት የወታደረዊ እውቀት ልምድ የሌላቸውን የፖሊስ ሻለቆች ሳይቀር በነበራቸው ታማኝነት ብቻ እየመዘነ በወታደሩ ላይ ጀነራል አደርጎ እንዲሾም መገደዱ እንዲሁም ያለ አንዳች ጦርነት ትግራይን በሙሉ ለወያኔ ለቆ ሲወጣ ኤርትራ ውስጥ የነበረውን ከሶስት መቶ ሽህ ያላነሰ የአገሪቱ የጀርባ አጥንት ነው የሚባለውን ሜካናይዝድ ጦርና ድፍን የኤርትራን ህዝብ ለማስተዳደር ማንኛውንም አይነት ስንቅ እና ትጥቅ ከመሃል አገር የሚወስድበትን ብቸኛ መንገድ መዝጋት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አደጋውን ማየት ያልቻለ እውር አመራር፣ ይልቁንም ኢትዮጵያን በምታህል ከድህነት ወለል በታች የሆነች አገር የነበሩዋትን ጥቂት ቦይንግ አውሮፕላኖች ወንበራቸው እየታጠፈ ስኩዋር፣ ዘትይ፣ ዱቄት፣ መሳሪያ፣ ወዘተ ሁሉ ከባህርዳ አየር ጣቢያ ወደ አስመራ በማመላለስ ክፍተቱን ለመሙላት የተሞከረበትን እብደት ጤናማ ዜጋ ሆኖ ማሰብ አይቻልም።በእርግጥም ደርግ ከዚህ ቀን ቦሃላ በየትኛውም ግንባር ላይ የማጥቃት ሙከራ ሳያደርግ ይልቁንም ራሱን በራሱ ግዝግዞ በመብላት ላይ ተጠመደ እንጅ ወያኔ እንደሚለው ነገሩ ተራራውን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሆኖ ስለመጣበት አልነበረም። ለዚህም ማስረጃው ለአስራ ስድስት አመት ያህል ሲዋጋ ያላስደፈራቸውን ከምጽዋ እስከ መሃል አዲስ አበባ ያሉ መሬቶች ሁሉ በመጨረሻው አንድ አመት ውስጥ ብቻ እንደ ውሃ ሙላት በፈጠነ ኩነት ያስረከበበት የውድቀት ቁልቁለት ነበር።

በዚህ ላይ የቀዝቃዛውን ጦርነት ማክተም ተከትሎ አለም ላይ እየተቀየረ የመጣው የሃይል ሚዛን ማጋደልና የጎርብቾቭ አስተዳደር በመንግስቱ ኃይለማርያም ላይ ጀርባውን መስጠት ሲጨመርበት ደርግ የወደቀው በጦርነት ሳይሆን እንደ መሬት ስበት ወደ ውስጥ ሰንጎ በሚይዝ የራሱ ተቃርኖ አርጅቶ በወደቀ ግዜ ከወያኔ ውጭ የተደራጀ አካል አልነበረምና ትግራይን ሊገነጥል ደደቢት የገባው ቫይረስ አንዲት ትልቅ አገር ከነሙሉ ታሪኩዋና ሙሉ በረከቷ ድንገት እጁ ላይ ወደቀችለት።

ወያኔ

በየትኛውም መመዘኛ ስናየው ወያኔ ደግሞ ከቀደሙት መንግስታት ጋር ፈጽሞ ሊወዳደር በማይችል ከፍተኛ የሆነ ተቃርኖ ብቻ ሳይሆን በጣም የመረረ ቀውስ ውስጥ የተዘፈቀ፣ መኖሪያ ፈቃዱን በየ ሃያ አራት ሰዓቱ የሚያድስ ቡድን ሆኖ መውጣቱ አሌ አይባልም። በግድያ፣ በአገር ክህደት፣ በዘረፋና በኑፋቄ ከድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የማይታረቅ ልዩነት ውስጥ የወደቀው ይህ ጎጥን መሰረት ያደረገ የአናሳዎች ስብስብ በቡድን አባት ተከፋፍሎ እድሜውን ለማራዘም እየሞከረ ነው። ለዚህም ሁለት የሃይል አሰላልፍ ነጥሮ እንደ ወጣ ባለፈው ሰሞን ለማሳየት የሞከርኩ ሲሆን ይኸውም አኩርፈው ከወጡት ሰየ አብራሃና ኩባንያው በተጨማሪ የምእራብ መንግስታትን ከኋላው ያሰለፈው በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የህወሃት የፖለቲካ ክንፍ በአንድ በኩል በሳሞራ የኑስ የሚመራው መከላከያ ሃይልና የትግራይን ክልል ከነ ሚኒሻው ጠቅልሎ የሚዘውረው የአባይ ወልዱ ቡድን በሌላ በኩን መቧደናቸውን ገልጨ ነበር።

በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ቡድኖች የሃይል ቀጠናቸውን በማስፋት ሁለቱም ቡድኖች ክልሎችን በየስራቸው ለማሰለፍ በሩጫ ውስጥ የሰነበቱ ሲሆን የሳሞራ የኑስ በኮማንድ ፖስቱ ሽፋን የኦሮሚያን ክልል ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥሩ ስር ሲያደረገ የሶማሊያን ክልል በተመለከተ ግን ወትሮም የሳሞራ የግል አሽከር የሆኑ ጀነራሎች የቢዝነስ ሃብ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

በሌላ በኩል የአማራ ክልል ደግሞ በጌታቸው አሰፋ በሚመራው ቡድን ውስጥ የወደቀ ሲሆን ለዚሁም ዋነኛው ምክኛት እነ ገዱ አንዳርጋቸው ከነ አባይ ወልዱ ጋር የነበራቸው ስር የሰደደ ቅራኔ ለነጌታቸው ቡድን የመግቢያ ቀዳዳ እንደፈጠረላቸው ይታወቃል።

ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የቀረው የዚህ ቅራኔ የመጨረሻ የትንቅንቅ ቀጠና አዲስ አበባን መቆጣጠር ሲሆን ኮማንድ ፖስቱም ሆነ የጌታቸው አሰፋ ክንፍ በየወረዳው የየራሳቸውን ምህዋር በማስፋት ላይ በመጠመድ አዲስ አበባን ከመቆጣጠር ባሻገር አንዳቸው አንዳቸው ውስጥ ሰርገው በመግባትና ደጋፊዎቻቸውን በማስከዳት ጭምር ውስጥ ተዘፍቀዋል።

ለማጠቃለል ያህል የዚህ ፍጥጫ ሁለተኛው ምዕራፍ አዲስ አበባን በመቆጣጠር ላይ በሚያደርጉት የፍጻሜው ጦርነት የሚወሰን በመሆኑ ለሁለቱም ቀላል እንደማይሆን እያየነው ነው።ይቀጥላል።

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17448/#sthash.cp3HL8ll.dpuf

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s