አቶ ዓባይ ወልዱ የወልቃይት ዐማሮችን ነገ በሰላማዊ ሰልፍ ተቀበሉኝ አለ፤ 6 መኪና ሙሉ የታጠቀ ኃይል ዛሬ አዲረመጥ ገብቷል

 


ሙሉቀን ተስፋው

ነገ የካቲት 17 ቀን 2009 ዓም ወደ አዲረመጥ የሚሔደው አቶ ዓባይ ወልዱ በሰላማዊ ሰልፍ ድጋፍ ሕዝቡ እንዲቀበለው ቅስቀሳ እያሠራ ነው። በርካታ ካድሬዎች ተመድበው በእልልታና በሆታ ጌታቸው እንዲቀበሉ ከማስፈራሪያ ጋር ተነግሯቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ 6 መኪና ሙሉ የትግሬ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ከነሙሉ ትጥቃቸው ዛሬ ገብተዋል። ከወታደራዊ ጥበቃም በተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፍም ያደርጋሉ ተብሏል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ሰላማዊ የነጻነት ታጋይ ወጣት ዘመኔ ጌጤ በደኅንነት ታፍኖ የደረሰበት እንደማይታወቅ ተገለጸ::
ሰላማዊው የነጻነት ታጋይ ወጣት ዘመነ ጌጤ ከጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ቤቱ እንዳልተመለሰ ቤተሰቦቹ ተናገሩ፡፡ ዘመነ ጌጤ በሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በአይሲስን ለመቃወም በተጠራው ስብሰባ ሽብር ለመፍጠር አሲረሃል ተብሎ ለአንድ ዓመት ያክል በማዕከላዊ ታስሮ የተፈታ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የመኢአድ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ በመሆን አግልግሏል፡፡

የአቶ ዘመኔ ጌጤ ቤተሰቦች እንደሚሉት ጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጎንደር ደርሼ እመለሳለሁ በማለት ትንሽ የጉዞ ቦርሳ በመያዝ ከቤቱ እንደወጣ እንዳልተመለሰ ነው የተናገሩት፡፡ ከጎንደር አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ከጓደኛው ወጣት ክንዱ ጋር በደኅንነት ጥር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ ውስጥ መታፈናቸውን ነው፡፡

እነዘመነ ጌጤና ክንዱ በደኅንነት ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የደረሱበት እንደማይታወቅ ነው የተነገረው፡፡ የዘመነ ጌጤ ቤተሰቦች ወንድማቸውን የት ብለን እንደምንፈልግም አላወቅንም ሲሉ በሀዘን አስታውቀዋል፡፡ ወጣት ዘመነና ወጣት ክንዱ ወደ ማዕከላዊ ወይም ወደ ትግራይ ሊወሰዱ እንደሚችሉ ጥርጣሪያቸውን መረጃውን የሰጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s