የመጨረሻው ምእራፍ (ታፈረ በደጁ)

ታፈረ በደጁ

Ethiopian Border Affairs Committee

የያዝነው የፈረንጆች ኣመት በሀገራችን በርከት ያሉ ክስተቶችን እያስተዋልን ያለንበት ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ የወያኔ ዘረኛ ሰርአት ጉዞ የመጨረሻ ምእራፍ ላይ መገኘታችንን በተለያየ መልኩ የሚጠቁሙ ሆነው ይታያሉ።

ሰሞኑን በመቀሌ የኢትዮጵያድንበር ለሽያጭ ቀርቦ ድርድሩ ደርቶአል። ወያኔም በረሃ ሳለች ከሱዳን የበላችውን ቀብድ  ሙሉ የሽያጭ ዋጋ ለመቀበል ከስርአተ ቀብሯ በፊት  ቀን ተሌት ትሰራለች።  ወያኔ ከመለስ የሙት መንፈስ እቅድ ፈቀቅ አላለችም የልቁንም የሙት መነፈሱን እቅድ ሳይበራባት እዳር ለማድረስ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ  ደርሰናል እያለች ነው። የወያኔ ጉምቱ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ባሁኑ ጊዜ በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ስር መቀጠል አለያም ለመበታተን ዝግጅት  እንድታደርግ ካወጁ ሰንበትበት አሉ።

ወያኔ ባወጣችው እቅድ መሰረት ለመስረቅ ያቀደችውን ብድርና እርዳታ ከልክለዋት ትቅበዘበዛለች። እዚህ ላይ ወያኔ ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ላይ መውደቇን በብዙ ማሳያዎች መመልከት ይቻላል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያዎች መነሳቱ ፈገግ ማሰኘቱ የግድ ቢሆንም ምን ያህል እንደሚያዋጣ  ባይገባኝም ጸጉራችንንም ጭምር በመሸጥ ምንዛሪ እስከማግኘት ታቅዳለች። የአስቸኵዋይ ጊዜ አዋጁን ማንሳትም ሆነ ማራዘሙ በሁለቱም ወገን የሚያስከትለውን ውጤት ለመተንበይ የተቸገረችው ወያኔ በብዙ ውጥረት ትዋትታለች። የአዲስ አበባን መሬት የመሸጥ ፕሮጀክቴን ሳልጨርስ የአስቸኻይ ጊዜ አዋጄን አላነሳም ማለትዋን ልብ ይበሉ። ይህ የአዲስ አበባና አካባቢዋ መሬት ሽያጭ ብዙ ያነታረከና የኦሮሞ ወጣቶችን ለትግል ያነሳሳ ክስትት መሆኑን ልብ ይሉዋል። በአዲስ አበባም ብዙ የከተማ ነዋሪዎችን ቤት አልባ ያደረገ ደምም ያፋሰሰ ክስተት መሆኑ አይዘነጋም። ከዚህ ባለፈም የወያኔ ዲያስፖራ ዝምድናን ውል ያቇረጠውን አዲሱን የባንክና ኢንሹራንስ ህግ መመልከቱ ምን ያህል የምንዛሪ እጥረት መኖሩን ያሳየናል።

የተቃዋሚው ጎራ ደግሞ በዘውግ ጡዘት በናወዘ የዲያስፖራ  አባዜ በዚም በዚያም ወገን በመቆም  በከረረ የጎጥ ቅዥት ውስጥ ሲዋትት እንመለከታለን ። እነህዝቅኤል ገቢሳ ለምን ኢትዮጵያ ብላችሁ ተነፈሳችሁ ይሉናል። ሰሞኑን ደግሞ እነሄኖክ የሺጥላ በአማራ ስም ግለሰባዊ ይዘት ያለው መርዘኛ የጥላቻ ቅስቃሳ ስናስትውል ቆየን።

በዘር መደራጀት የወቅቱ ፋሽን በመሆኑ ሁሉም የየዘሩ ጠበቃ ፓርቲ ሲኖረው አማራውስ ለምን ያሉ ደግሞ ሰሞነኛ ሆነው ከረሙ። ተነሳንበት ያሉትን በአማራ ህዝብ ላይ  የተነጣጠረ  ጥቃት መረዳት ብዙም የሚያነጋግር ባይሆንም የመረጡት የትግል ስልት ግን ጥይታቸውን ወያኔ ላይ ያነጣጠሩትን የአንድነት ሃይሎች ላይ ማድረጋቸው በሚምሉበት በኢትዮጵያዊነት አንታማም ጉዞ ላይ ከፍተኛ ብዥታን የፈጠረ ሆኖ ይታያል። በሰከነ የብስለት ጉዞ ስልዩነትን አቻችሎ ሲሆን የጋራ አገራዊ ጥቅምን በማስቅደምና ሃይል ሳይከፋፈል ወያኔን በፈረጠመ ጉልበት የመምታትን አቅም በሚያጎለብት መንገድ ቢሰሩ አለዚያም ሌሎች ለወያኔ ያሉትን ጉልበት በማዳከም የወያኔን እድሜ ባያስረዝሙ የተሻለ ነው።

የሆነ ሆኖ የነገሬን ዋና ጭብጥ ግልጥ ባለ መንገድ ለማስቀመጥ የዚችን መከረኛ አገር መከፋፈል ላልተመኘና በኢትዮጵያ ለሚያምን ሁሉ በምንም ይደራጅ መምንም ኣይኑን ከወያኔ ለማንሳት ለኣፍታ እንኳን ለማሰብ ጊዜው ባለቀበትና የመጨረሻው ደወል ወደተቃረበበት ጉዞ ስናመራ ብዙ ትኩረትን የሚሹ ነገሮችን መመልከት የግድ ይላል።

ወያኔ የቆሰለች አውሬ ናት ቢቻላት ከዳር እስከ ዳር ደም አቃብታን ስንጫረስ  ጥግ ለመያዝ መስራትዋን አንርሳ። መላ ሀገሪቱን ከዳር እስከዳር ያናወጠው የተቃውሞ ማዕበል ያስገኘውን ውጤት ካለበት ደረጃ ወደታለመለት ወደመጨረሻው የወያኔ ማክተሚያ ምዕራፍ በማድረስ ለዚህ ትግል ውድ ህይወትና ሌላም ክቡር መስዋዕትነት የከፈሉትን ኢትዮጵያውያን ውጥን ከግብ እናድርስ። ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ከጥንት አስከዛሬ ከባንዲራዋ ስር የወደቁትንና በመውደቅም ላይ ያሉትን ጀግኖቻችንን በመመልከት የጋራ ጥቅማችንን ለጠላት አሳልፈን አንስጥ።

እግዚአብሄር ሀገራችንንኢትዮጵያን ከክፉዎች ጥፋት ይጠብቅልን

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17462/#sthash.1bZZsMon.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s