የማለዳ ወግ…ታላቋን ንግስት እቴጌ ጣይቱን እናዘከር ! – ነቢዩ ሲራክ

* ” ሴት ነኝ ፣ ጦርነት አልወድም ! ነገር ግን ሃገሬ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸለም ጦርነትን እመርጣለሁ! ”

እትጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ይባላሉ ፣ የኢትዮጵያ ብርሃን … ሁሌም እቴጌ ጣይቱ ብጡልን ሳስታውስ በአድዋ ጦርነት ዋዜማ በውጫሌው ውል ክህደት ተቆጥተው ለጣሊያን ፋሽሽት የሰጡት ምላሽ አይዘነጋንም ፣ ይህ በወኔ የተሽቆጠቆጠ ቆራጥነት ምላሽ ንግግራቸው ፣ በኩራት የሚታወስና ከአዕምሮየ የማይጠፋ ሆኖ አብሮኝ የሚኖረው በእኔ ብቻ ሳይሆን በሚሊዮኖች ልብ ነው …!

“ … የዛሬ ሳምንት አድርገው፡፡ እኔ ሴት ነኝ፡፡ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ! እግሩን ለጠጠር፤ ደረቱን ለጦር አስጥቶ፤ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ፤ ለአፈሩ ክብር ለብሶ፤ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጵያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን፡፡ ያንተን ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን ጊዜ እናየዋለን ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ፡፡”

እትጌ ጣይቱ ብጡል በ1851 ዓም ተወልደው በ1918 ዓም የተለዩን ጀግና እናት ናቸው ! ስመ ጋናናዋ ንግስት እትጌ ጣይቱ የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ባለቤት ሲሆኑ የጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነው የአድዋ ድል ሲወሳ ስም ዝናቸው ከአጽናፍ አጽናፍ አልፋና ኦሜጋ ሲነሳ የሚኖሩ እናት ናቸው! እምዬ ምኒሊክ ስልጣኔን ለሃገራቸው ሲያስተዋውቁ እትጌ ጣይቱ ቀዳሚ ምሳሌ ነበሩ ። በሐገሪቱ እንደ ነውር ይቆጠር የነበረውን ቀሚስ ለብሰው እና ሽቶ ተቀብተው ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ ወጥተውም ያውቃሉ ። አዎ እቴጌ በባህል ተቀፍድዶ የነበረውን ሃገሬ በልበ ሙሉ ያስተማሩ ልበ ሙሉ ወይዘሮ ነበሩ !

መልከ መልካሟ እትጌ ጣይቱ ብጡል ለኢትዮጵያ ሴቶች እህቶቻችን አሁን ድረሰ በታላቅ አርአያነት ይጠቀሳሉ ፣ እትጌ በወቅቱ ብቸኛ የእውቀት ምንጭ በነበረው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን የሐይማኖት ትምህርት በአድባራቱ የቀሰሙ ፣ የግእዝ ቁዋንቁዋ አቀላጥፈው የሚናገሩ ፣ አስተዳደር አዋቂ ፣ አስተዋይና በሙዚቃውም አለም በገና መደርደር የሚያውቁ ባለ ብሩህ አዕምሮ እመቤት እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ!

ጣይቱ የአባ ዳኘው መንግሰት እንዲረጋ ፣ በብልሃት ሕዝቡንና ባለሟሎችን በመያዝ የአስተዳደሩን ያረጋጉ በመኳንንቱና በጦሩ ዘንድ ተወዳጅ ንግስት ፣ ብልህ ሴት ነበሩ ። አፄ ምኒሊክ ስልጣን በጨበጡ ማግስት “ብርሃን ዘኢትዮጵያ ” የሚል ስራቸውን ገላጭ የንግስና ክብር ስም የተሰጣቸው ንግስት እትጌ ጣይቱ ብጡል ከባላቸው ፣ ከጦር አለቆችና ከሰራዊቱ ጋር እጅ ለጅ ሆነው ተጣጥመው ሐገር መርተዋል ። በእምዬ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ለተከናወኑት ስራዎች ሁሉ ትልቅ አሻራቸውን የጣሉት ንግስት ጣይቱ ብጡል ከሐገር ስልጣኔ እስከ መስፋፋትና ዋና ዋና ተጠቃሽ የምኒሊክ ክንውኖች ቀዳሚ ተጠቃሽ ናቸው ።

እትጌ ፈጣሪ ነገር ሆኑ በአብራካቸው ልጅ ለማፍራት ባይታደሉም የተቸገሩትንና ያጡትን በመደገፍ ይታወቃሉ ። እትጌ በአድዋው ዘመቻ ጦሩን በማነቃቃት ከፍተኛውን ሚና መጫወታቸው በታሪክ ተደጋግሞ ተጠቅሷል ። ከድል በኋላ ሐገር ረግቶ እምየ ምኒሊክ ታመው ሲደካክሙ አስተዳደሩን በመምራት ባላቸውን በማማከር ሀገሯን በእጅ አዙር ያስተዳድሩ የነበሩ እመቤት ናቸው ! የመጨረሻ አመታት የአባ ዳኘው እምየ ምኒሊክ መዳካከም እና መታመም ሲጀመወሩ የባለቤታቸው የአፄ ምንሊክ ብቸኛ አማካሪ ሆነው አገሪቱን በእጅ አዙር አስተዳድረዋል፣ ለሃገራቸው ታምነው እምየ ምኒሌክን በክብር የሸኙ ጠንካራ ንግስት ነበሩ ፣ ጣይቱ ብጡል !

እምዬ ምኒሊክ ባረፉ ማግስት ግን በዙሪያው ያሉ መኳንንትና ሹማምንት በእትጌ ላይ አሴሩ ፣ ብዙ የክፋት ሙከራ በጦሩ ድጋፍ ባይሳካም ብርቱዋ ንግስት እትጌ ጣይቱ በንግስና ይኖሩበት ከነበረው ቤተ መንግስቱን በአሻጥር እንዲለቁ ተደረገ ። ብዙም ሳይቆይ በግዳጅ ወደ በፊቱ የእንጦጦ ቤተ መንግስታቸው ተወስደው ከማንኛውም የመንግሰት ውሳኔ ተከልክለው እስከ ህልፈታቸው እዚያው ኖሩ ነ !
በግዞት ባሉበት በእንጦጦው ቤተ መንግሰታቸው እአአ በ1918 ዓም በ67 አመታቸው በውስጠ ደዌ በሽታ ከዚህ ከንቱ አለም ተለዩ ! በቀጣይም ትውልድ ውለታቸውን እያወሳ በክብር እያዘከረ ያወድሳቸዋል !

ክብር ከሚገባው ክብር እሰጣለሁ !

ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 18 ቀን 2009 ዓም

ድርድሩ – ይገረም አለሙ

መንደርደሪያ ፤ ብዙ ግዜ አዲስ ያልሆኑ ግን እኛ አዲስ የተፈጠሩ ያህል የምንጮህባቸው ነገሮች ሲከሰቱ ብዙዎች የሚያሳዩት ነገር “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” ይሉ አይነት ነው፡፡ ወያኔ ሥልጣኔን ያሰነብትልኛል ብሎ እስካመነ የማይቆፍረው ጉድጓድ እንደሌለ እየታወቀ  ድርድር ጠራ ተብሎ  ተቀዋሚ ተብየዎችም ጥሪውን ተቀብሉ  ተብሎ አዲስ ተአምር የተፈጠረ ይመስል ድጋፍና ተቃውሞ በተለመደው መንገድ እየተሰማ ነው ነው፡፡ ነገር ግን ከተለመደውና መረጃም ማስረጃም ፍለጋ ከማያደክመው የፍረጃና ውንጀላ ጉዞ ወጣ ብሎ ድርድር ለምን፣  ድርድር በእነማን መካከል፣ ድርድር እንዴትና በምን ሁኔታ? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ የሚችል አስተያየት መጻፉ፣ ልምድ ማካፈሉ ነበር የሚበጀው፡፡ እኔ ይህን ለማድረግ የሚበቃ እውቀትም ልምድም የለኝም፡፡ ፍረጃና ውንጀላ ላይ በመሮጥም ሆነ ጭፍን ድጋፍ በመስጠት  ደግሞ አላምንም፣ በዚህ መካከል ሆኜ ስለ ድርድሩ የተሰማኝን  ልበል፡፡

ድረድር፣  ለድርደር ምክንያት የሆነው ጉዳይ ምንነት፣  የተደራዳሪዎቹ ማንነት፣ የድርድሩ ሂደት አንዴትነት ወዘተ ቢለያይም  ዙሪያ ጥምጥም ገለጻ ውስጥ ሳይገባ ድርድር ሰጥቶ መቀበል ነው፡፡ ትንሽ የያዘው ወይንም ምንም የሌለው የሚፈልግበት፣ ብዙ የያዘው የሚሰጥበት፡፡ በመሆኑም ያየዘውን ወዶና ፈቅዱ የሚሰጥ “ቅዱስ ፖለቲከኛ” የለምና   ያለ አስገዳጅ ሁኔታ በውዴታና በፈቃደኝነት ወደ ድርደር መድረስ አይቻልም፡፡ አሁን የሚወራለት ድርድር ይካሄዳል የሚባለው ሁሉንም ጠቅሎ በያዘውና የሚሰጠውም የማይሰጠውም በብዛት ባለው ወያኔና በየግልም በጋራም ምንም ባልያዙና ምንም የሚሰጡት ነገር በሌላቸው ተቀዋሚዎች መካከል ነው፡፡ (ይቅርታ ይደረግልኝና የድርድሩ ተካፋይ የተባሉትን ፓርቲ ብሎ ለመጥራት አንደበቴ፣ ለመጻፍ ጣቶቼ እሽ አይሉኝም፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ለድርጅቶቹ ወይንም ለመሪዎቹ ጥላቻ ኖሮኝ ሳይሆን ፓርቲ ለመባል የማይበቁ በመሆናቸው ነው፡፡) ስለ መስጠት መቀበሉ ከማየታችን ቀደም ግን እዚህ ደረጃ እንዴትና በምን ምክንያት ተደረሰ የሚለውን ማየቱ ይበጃል፡፡

የድርድሩ ምክንያት የህዝብ እንቢተኝነት፡፡  ወያኔ የድርድር ጥሪ ያቀረበው በመላ ሀገሪቱ በተለይ ደግሞ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች በተቀጣጠለው የህዝብ ቁጣና እንቢተኝነት በደረሰበት ድንጋጤ መሆኑን ወያኔዎችም ቢሆን የሚክዱት አይመስለኝም፡፡ በማሰር፣ በመግደል፣ በማስፈራራት አመጹን መግታት አልቻሉም፤ የሀያ አመስት አመት ብሶት ነውና ፡፡ የሚመጻደቁበትን ህገ መንግሥት ጣጥለው በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስም ወታደራዊ አገዛዝ አሰፈኑ፤ ለወያኔ ከሥልጣን የሚብስ ነገር የለምና፡፡ ይህን ሁሉ ቢያደርጉም የህዝቡን ተቃውሞ አጥፍተው ሥልጣናቸው ሲረጋጋ አልታይ አላቸውና “ጅብን ሲወጉ በአህያ ተከልሎ ነው” እንዲሉ ተቀዋሚ ተብየዎችን ተጠቅመው የህዝቡን ተቃውሞ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እናጠፋለን ብለው ተነሱ፡፡ ይህን ሀሰት የሚል ይኖር ይሆን? ካለ በጽሞና እንነጋገር፡፡

ወያኔን ለድርደር ያንበረከከው የህዝብ ትግል በህይወትም በአካልም አያሌ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል፡፡ የድርድሩ አብይ ፈተና የሚመጣው እዚህ ጋር ነው፡፡ ምክንያትም ወያኔ ህዝብ መስዋዕትነት የከፈለበትን ጥያቄ መመለስ አይችልም፣ተቀዋሚ ተብየዎቹ ደግሞ ( ስም አጣሁላቸውና ተቸገርኩ) ለህዝቡ ጥያቄ መልስ የማስገኘት ፖለቲካዊ አቅም አይደለም ጥያቄውን ይዞ ለመደራደር የሞራል ብቃት የላቸውም፡፡ አረ እኔ አለሁ የሚል ካለ በጩኸትና በዘለፋ ሳይሆን በሚታይ በሚዳሰስ ማስረጃ ያሳየን፡፡

ወያኔ ለምን ይደራደራል፡ ወያኔ ተገዶም ቢሆን ለምን ወደ ድርድር መምጣት እንደፈለገ ለሁሉም ሰው ግልጽ ነውና ብዙ የሚያነጋግር አይመስለኝም፡፡ አንደኛውና የመጀመሪያው ምክንያት ከአዋጅ በፊትም ሆነ በአዋጅ መግደል ማሳሩ የህዝቡን ተቃውሞ ሊያዳፍነው ካልሆነ በስተቀር ጨርሶ ሊያጠፋው እንዳልቻለ ማየቱ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የግዜ ጉዳይ ነው አንጂ ተቃውሞው በተመሳሳይ ሁኔታ መነሳቱ አይቀሬ ነው፡፡  ታዲያ በየግዜው የህዝብ ቁጣ እየተነሳበት በለመደው መንገድ እየገደለ በአንድ በኩል ውግዘትና ወቀሳ እያስተናገደ ከመኖር፣በሌላ በኩል ደግሞ ከሥልጣን ሲወርድ የሚጠየቅበትን የወንጀል ክምችት እየበዛ  ከሚቀጥል የህዝብን ተቀዋሞ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማጥፋት ነው፡፡ ይሄ ይችላል? አሁን ከመተንበይ ግዜው አጭር ስለሆነ ጠብቆ ማየቱ ይሻላል፡፡ ሌላው በኃያላኑ መንግሥታት የገንዘብ እርዳታና ብድር እንዲሁም የዲፕሎማሲ ድጋፍ የቆመ በመሆኑ ሰላም ፈላጊ ችግርን፣ በዴሞክራሲያዊ አግባብ በሰላም የሚፈታ፣ ከተቀዋሚዎቹ ጋር የሚነጋገር መስሎ በመታየት ድጋፉን ማስቀጠል መቻል ነው፡፡ ድርድሩ ከቀጠለ ይህ እንደሚሳካለት የሚያጠራጥር አይመስለኝም፡፡ ሌላው ተቀዋሚዎችን አፍ ማስያዝ፣ ቁርጥ ያለ ዓላማ፣ እምነትና አቋም የሌላቸውን ተቀዋሚ ነን ባዮች ደግሞ (በውጪም በውስጥም ያሉ) ሲሆን በአባልነት፣ ካልሆነም በደጋፊነት ማሰልፍ መቻል የድርድሩ አንዱ ዓላማ ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡

ተቀዋሚዎች ለምን ይደራደራሉ፤ የሚሰጡት የሌላቸው፣ ወያኔን ወደ ድርድር ባመጣው የህዝብ ትግል ውስጥ ጠብታ አስተዋጽኦ ያልነበራቸው፤ በተናጠል ፓርቲ ለመባል የማይበቁ፣ በጋራ፣ የጋራ የመደራደሪያ አጀንዳ ቀርጾ ለመቅረብ የሚያስችል የትግል አንድነትም ሆነ የአንድ ሀገር ልጅነት ፍቅር የሌላቸው ምን ለማትረፍ ነው ወደ ድርድሩ መድረክ ያመሩት ብሎ መጠየቁ ተገቢ ቢሆንም እንደ ስማቸው ፍላጎታቸው የበዛ እንደ ብዛታቸው መልካቸው የተዥጎረጎረ ነውና አንድ ወጥ የሆነ ምላሽ ማግኘት የዳግታል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ምላሽ መፈለግ ግድ ነውና ለመልሱ መንደርደሪያ ወይንም በር ከፋች ጥያቄ ይቅደም፡፡

የሚደራደሩት ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ለማስገኘት ወይንስ የየግል ፍላጎታቸውን ለማርካት? የመጀመሪያው ከባድ የሚባል ብቻ ሳይሆን የማይሞክሩት ነው፡፡ ምክንያቱም የህዝቡ ጥያቄ የሥርዓት ለውጥ ነውና፡፡ ሁለተኛው ግን በጣም ቀላል ነው፡፡ መለስ ፍለጋውን ከቀላሉ እንጀምር፡፡

ወያኔ በፓርላማው ስራ መጀመሪያ ቀን በፕሬዝዳንቱ አንደበት ያስነገረውን “የፓርላማ ወንበር በችሮታ አንሰጣለን” የሚል መልእክት ያለው ንግግር የሚረሳ ያለ አይመስለኝም፡፡ በተነገረው መሰረት የምርጫ ህጉን በማሻሻል ( ይህን ህግ ለማሻሻል ህገ መንግሥቱን ማሻሻል ቢያስፈልግም ወያኔ ለዚህ ግድ የለውም) ፓርላማ በመገኘት ባለመገኘታቸው በወያኔ ላይ ምንም የማያመጡትን ሰዎች ወደ ፓርላማ መግቢያ በር በድርድሩ ካሳያቸው፣ በጣም ቸር ልሁን ካለ ደግሞ የተወሰኑቱ የምኒስትርነትም ባይሆን የምክትልነት ሹመት በዚህ ድርድር ማትረፍ አንደሚችሉ ካሳያቸው በወያኔ ድርጎ የሚተዳደሩ ወትሮም ከህዝብ ጋር ጉዳይ የላቸውምና “ምኞቴ ተሳካ ያሰብኩት ደረሰ” የሚለውን የጥላሁን ገሰሰን ዜፈን እያዜሙ ድርድሩ በስኬት ተጠናቀቀ፣ ኢህዴግ ለሀገርና ለህዝብ አሳቢነቱን ”

ለድረድር ከቀረቡት መካከል  ሌላው ቢቀር ቤት ኪራይ የሚከፍልልንን ደጋፊ እንዳናጣ ብለው የሚሰጉና በእምቢተኝነት የፖለቲካ ትርፍም እናገኛለን ብለው የሚያስቡ ቢገኙና በዚህ መንገድ አንደራደርም፣ ይሄን ይሄን አንቀበልም ፣በዚህ መልክ ችግሩ በዘለቄታ  አይፈታም ወዘተ ለማለት ከቻሉ ብዙም አይሆኑምና በጸረ ሰላምነት ተወግዘው፣ በድርድር አደናቃፊነት ተከሰው፣ ከዛም አልፎ የሌሎችን ተልእኮ አንግበው የመጡ የሚል ሰም ተሰጥቶአቸው አፋቸውን ለጉመው፣ እግር ከወርች ታስረው በሚኖሩበት ቢሮአቸው መመሸግ ነው፡፡

አሁን ወደ ከባዱ ጥያቄ እንመለስ፡ ህዝቡ የጠየቀው የሥርዓት ለውጥ በመጀመሪያ በአጀንዳነት ሊመዘገብ አይችልም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል፡ ከወያኔ ባህርይ አንጻር፡፡ ምክንያት ወያኔ ሰማይ መሬቱን የሚቧጥጠው ሥልጣኑን ለማጥበቅ እንጂ ለመልቀቅ ምን አደከመው፡፡ ተደራዳሪ ተብየዎቹስ ይህ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ  መጀመሪያ ፍላጎቱ፣ ቀጥሎ ዝግጅቱ፣ ከዛስ  አጀንዳ አንዲሆን የማስገደድ የተናጠል ብቃቱ የጋራ  ህብረቱ አላቸው? ከየት መጥቶ! እናም ጉዳይ እዚሁ ላይ ያበቃል፡፡የተደራዳሪዎችም ፍላጎትና ማንነት እዚሁ ጋር ይታወቃል፡፡ “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል ይሉ አይነቱ ጭፍን ድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ፍረጃና ውንጀላው አሁን ተገቢ የማይሆነው ለዚህ ነው፡፡

የድርድሩ የመጨረሻ ውጤት ዜሮ ነው፡  ድርደሩ ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ለወያኔ  ርዳታና ብድሩ አንዳይነጥፍ፣ የዲፕሎማሲ ድጋፉ እንዳይቆም ሊያደርግለት ይችል ይሆናል፣ ችግሮችን በውይይት የሚፈታ፣ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ህገ መንግሥትን እስከ መሻሻል  ድረስ የሚሄድ፤ ለተቀዋሚዎቹ ወንበር ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ የመሳሰሉ ቅታያዎችና ማደመቂያዎች ተጨምረውበት  ገጽታ ግንባታ ለሚባለው  የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ፍጆታ ሊጠቅመው  ይችል ይሆናል፤ የትግላቸው መነሻም ሆነ መድረሻ የራስ ጥቅም ለሆኑ በተቀዋሚ ካባ ለሚንቀሳቀሱትም ትንሽ ትንሽ የሥልጣንም የገንዘብም ፍርፋሪ ሊያስገኝላቸው ይችል ይሆናል፡፡ (አሁን ከሚሰጣቸው ዳረጎት በተጨማሪ)

እንዲሁም የእነርሱ ፓርላማ መግባት የኢትዮጵያዉያን ችግር መፍትሄ ማግኘት ለሚመስላቸው ወይንም አድርገው ለሚያስቡ (ይህ ከዚህ ቀደም በተግባር ያየነው ነው)  በመጪው ምርጫ ተወዳድረው አሸንፈው ሳይሆን በችሮታ ፓርላማ የሚገቡበትን መንገድ ሊያመቻችላቸው ይችል ይሆናል፡፡ሌላም ሌላም ፤

ወያኔና ተደራዳሪዎች እንዲህ በየመጠናቸው ከድርድሩ ሊያተርፉ ይችላሉ ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ ትርፍ እናገኛለን ሳይባል ሳታሰብና ሳይታቀድ አይደከምምና፡፡ የድርድሩ ምክንያት የሆነው በህይወትና በአካል መስዋዕትነት ወያኔን ወደ ድርድር ያመጣው ህዝብ ግን ጥያቄውን የሚመልስለት አይደለም ለጉዳቱ ካሳ የሚሆነው አንዳችም ነገር አያገኝም፡፡ ይሄ ነው አንግዲህ የድርድሩን ውጤት ዜሮ የሚያደርገው፡፡  እንደ እስራት ግድያውና የአስቸኳይ አዋጁ ድርድሩም  የህዝቡን ጥያቄ መመለስም ተቃውሞን ከነአካቴው ማጥፋትም አያስችልምና፡፡

በመጨረሻ፤ ለመሆኑ ድርድር ከተባለ መደረግ ያለበት ከመንግሥት ጋር ነው ወይንስ ከኢህአዴግ ጋር፡፡ ወያኔ የመንግሥትና የድርጅት ኮፍውን ሲሻው የሚቀላቅለው ሲፈልግ የሚለያየው ለእኩይ ተግባሩ መጠቀሚያ ሲል ነው፡፡ እንደውም አቶ መለስ በተካኑበት የማደናገሪያ ስልት ተከታዮቻችውንም እኛንም ሊያደናግሩ የድርጅታቸው አንዱ ችግር የድርጅትና የፓርቲ ኮፍያ ማደባለቅ አንደሆነ ነግረውን ነበር፡፡ “ፖለቲከኞቻችንስ” ኢህዴግ ማለት መንግሥት፣ መንግሥት ማለት ኢህአዴግ ነው ብለው አምነው ተቀብለው ነው ፡፡

ትክክል የሚባል ነገር ከጠፋ አመታ ተቆጠሩ እንጂ ትክክለኛው ነገር ወያኔም እንበለው ኢህአዴግ ፓርቲ ነው፤ እውነተኛ (አቅም፣ ብቃት፣ የዓላማ ጽናትና ግልጽነት ያለው ) ተቀዋሚ ቢኖር ፓርቲ ከፓርቲ ጋር መፎካከር መወዳደር እንጂ መደራደር የለም፡፡መደራደር ከመንግሥት ጋር ነው፡፡ እዚህ ጋር ኢህዴግንና መንግሥትን ምን ለያቸው የምትለው የተለመደች  ነገር አንደምትነሳ እገምታለሁ ፡፡እኔም ጥያቄ አለኝ እነርሱ የሚሉትንና የሚያደርጉትን ነው መከተል ያለብን ወይንስ ትክክል የምንለውን?

ቸር አንሰንበት

በሰንበትና በክረምት የተሰደደ ህዝብ (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ

Ethiopian Patriots

እንደ ሳውዝ አፍሪካ እንስሶች በማያጌጡበት ህንጻ ከመታበይ ከነሙሉ ኩራታችንና በደሃ ጎጇችን መኖራችን የሚያኮራን ለምን እንደሆነ ሰሞኑን የነጻነትን እረሃብ አጋዚ ከቆፈረው የሞት ሸለቆ ያልተማሩት የሚሊኒሊክን ወጭት ሰባሪ ድኩማኖች ባይናቸው ብሌን እያዩት ነው ብለን ተስፋ እናደርጋለን። አፍሪካውያን በባሪያ ፍንገላ ውስጥ ኖረዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የነርሱ ዝርያዎች ዛሬ ባህር ተሻግረው በነጭ ምድር አንገታቸውን ደፍተው “እኔ እከሌ ነኝ” ሳይሉ ይኖራሉ። ሌላው ቢቀር መልካቸው በጣም ጠቆረ በሚል ምክንያት ከእስፔና ከፈረንሳይ አገር ከተጋዙ ነጭ እስረኞች ጋር በግዴታ እንዲዳቀሉ በመደረጋቸው ዛሬ በላቲን አሜሪካን ያሉት ወልጣቀኝ መልክ ያላቸው ህዝቦች የተፈጠሩበት ኩነት በጥቁሮች ላይ ሳይሆን በጥቁርነት ላይ የተፈጸመ ጀንፕሳይድ መሆኑ መራሩ እውነታ ነው። አንድ ጥቁር አሜሪካዊ እኔ አፍሪካን አሜሪካን ነኝ የሚለው አንድም ቋንጃውን ተቆርጦ ባህር ማዶ የተጔዘው ምንጅላቱ ከየትኛው የአፍሪካ አገር እንደተወሰደ ቆጥሮ ሊደርስበት ስለማይችል ነው።ደረትን ነፍቶ ኢትዮጵን አሜሪካን ብሎ ለመናገር ማንነት ካለው አገር በክብር መሄድ ይጠይቃል።

አባቶቻችን ምስጋና ይግባቸውና ዛሬ እነ ጃዋርን ጨምሮ የባንዳዎቹ ልጆች ሳይቀሩ ማነህ ቢባሉ ማን መሆናቸውን፣ አያት ቅድማያት እንዳላቸው፤ ኮራ ብለው በአውሮፕላን ቀበቷቸውን አስረው የመጡ መሆናቸውን ማሰብ የሚችል ተፈጥሮ ካላቸው ይኽ ማንነት በምን ላይ የቆመ መሆኑን ቢያስቡት አይከስሩበትም። ዛሬ አጠገባቸው ያሉት ጥቁሮች እረፍት ቢያምራቸው ተሳፍረው የሚዱበት አገር፤ “ወገኔ; አመት በአሌ” ብለው የሚናፍቁት ማንነት የሌላቸው ናቸው::

አፍሪካውያን እንደ ማህበረሰብ ከቆሙበት ግዜ ጀምሮ መጀመሪያ በባሪያ ፍንገላ ዋጋ ከፍሉ። ባሪያ ፍንገላው በአዋጅ ተሻረ ሲባል መልኩን ቀይሮ በበርሊን ኮንፈረንስ አህጉሪቱን ኮሎኒያሊዝም ብለው እንደ ቅርጫ ስጋ ለመቃረጥ ተስማሙ። ድርጊቱም የሆነው በአስራ ስምንት ሰማንያ አራት ሲሆን ይኽ በሆነ በአስራ ስምንት አመታት ውስጥ ነጻ ሆና የቀረችው አንዲት አገር ኢትዮጵያ ነበረች። አፍሪካውያንን ሊግ ኦፍ ኔሽንን በመሳሰሉ አለማቀፍ መድረክ ለዘመናት ስንወከል የኖርን እኛ ነን። ከፓን አፍሪካኒዝም የተወለደው የአፍሪካ የነጻነት ጥያቄም እርሾው የአድዋ ድልና ከምስራቅ አፍሪካ የተነሳው የነጻነት ችቦ ነው። ስለዚህ እነርሱ የባርነት ጭራቃዊ ገጽታ አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ የገባባቸው ቁስለኞች ናቸውና ባንዲራችን ባንዲራቸው የነጻነታቸው ምልክት አደረጔት እንጅ እንደ ዛሬዎቹ የኛ አገር ለምጻሞች አላፈሩበትም ወይንም በሶ አልቋጠሩባትም።ዛሬ በእኛ አገር እንደ ኬንያ ኳኩዩ ኪሮስ የሚለው ማንነቱ ክርስቶፈር፣ ቶሎሳ መባሉ ቀርቶ ስቴፈንሰን የተባለ ሰው የለም ስንል እንዲሁ በነጻ ያለዋጋ ተጠብቆ የቆየ ነገር አይደለም:: ከኮሎኖያሊዝም ወደ አፓርታይድ ከአፓርታይድ ደግሞ የነጻነት ትግሉን ግማደ መስቀል መሸከም ወደተሳናቸው መጹጉዎች እጅ ወድቆ ከማንነቱም በታች ሰብአዊነቱ የተወሰደበት የሳውዝ አፍሪካ ህዝብ ቆንጨራውን ይዞ አደባባይ ቢወጣ፤ የአንድ ምስኪን አንገት ለመቁረጥ አጃቢ የሙዚቃ መሳሪያ ሲያስፈልገው ብናይ ምን ይደንቃል?! ወትሮም ነጮቹ ሲገዙዋቸው ከሰውነት በታች አውርደውና ሰብአዊነታቸውን ገፈው በራቁት ህሊና የለቀቋቸው ሆነዋልና የሚገርመን አይሆንም። ማንም አባቶቻችን የከፈሉትን ዋጋ መልኩን ለማየት የሚፈልግ ቢኖር በዚህ ሰአት በጆሃንስበርግ; በፕሪቶሪያና በደርባን ከተሞች ዘወር ዘወር ይበል።

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17456/#sthash.zx8EOi6W.dpuf

የወልቃይት ጠገዴ ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነው — (ዶ/ ር አክሎግ ቢራራ)

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ ር)

“የውርደት በትር” ገጽታ

“በመጨረሻ እኛ የምናስታውሰው የጠላቶቻችን ቃላቶች ሳይሆን ድምጻቸውን ያጠፉትን የወዳጆቻችን ቸልተኛነት ነው” ዶር ማርቲን ሉዘር ኪንግ

መግቢያ

ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ሕዝቧን ለእርስ በርስ እልቂት የአመቻቸው የህወሓት፤ ኢህአዴግ አምባገነናዊ ስርአት የፈጠረውን መሰረታዊ ችግር አሁንም ገዢው ፓርቲ አግባብ ባለው ሁኔታ አላየውም፤ ቢያየውም ችግሩን ንቆ ትቶታል። ይህ የጥፋት ክስተት እንዳለ ሆኖ “ተቃዋሚ ነን” የምንለው ግለሰቦችና ስብስቦች በአበይት ብሄራዊ ችግሮች ላይ ምን አይነት አቋም እንወስዳለን? ጥፋቶችን እያየን ለምን ዝም እንላለን? የሚሉት ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጥባቸው እጠይቃለሁ።

የእኔ መከራከሪያ ነጥብ እንዲህ የሚል ነው። አማራው፤ ኦሮሞው፤ ጉራጌው፤ አፋሩ፤ አኟኩ፤ ሲዳማው፤ ትግራዩና ሌላው በደሙ መስዋእት ከፍሎ፤ በብሄር፤ በገቢ፤ በጾታ፤ በኃይማኖት ሳይታገድ የኢትዮጵያን ነጻነት፤ ዘላቂ ጥቅምና ሉዐላዊነት ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለእኛና ለተከታታይ ትውልድ ያሸጋገረልንን አገር፤ የኢትዮጵያ ሰፊ ሕዝብ ራሱን አሁንም የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ህወሓት) ብሎ የሚጠራው ጠባብ ብሄርተኛና ፍጹም ጎጠኛ ቡድን ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያችን እንድትበታተንና ሕዝቧ በእርስ በርስ ጦርነት እልቂት እንዲካሄድበት የሚፈቅድ አይመስለኝም የሚል ነው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Author, Dr. Aklog Birara

አቶ ዓባይ ወልዱ የወልቃይት ዐማሮችን ነገ በሰላማዊ ሰልፍ ተቀበሉኝ አለ፤ 6 መኪና ሙሉ የታጠቀ ኃይል ዛሬ አዲረመጥ ገብቷል

 


ሙሉቀን ተስፋው

ነገ የካቲት 17 ቀን 2009 ዓም ወደ አዲረመጥ የሚሔደው አቶ ዓባይ ወልዱ በሰላማዊ ሰልፍ ድጋፍ ሕዝቡ እንዲቀበለው ቅስቀሳ እያሠራ ነው። በርካታ ካድሬዎች ተመድበው በእልልታና በሆታ ጌታቸው እንዲቀበሉ ከማስፈራሪያ ጋር ተነግሯቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ 6 መኪና ሙሉ የትግሬ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ከነሙሉ ትጥቃቸው ዛሬ ገብተዋል። ከወታደራዊ ጥበቃም በተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፍም ያደርጋሉ ተብሏል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ሰላማዊ የነጻነት ታጋይ ወጣት ዘመኔ ጌጤ በደኅንነት ታፍኖ የደረሰበት እንደማይታወቅ ተገለጸ::
ሰላማዊው የነጻነት ታጋይ ወጣት ዘመነ ጌጤ ከጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ቤቱ እንዳልተመለሰ ቤተሰቦቹ ተናገሩ፡፡ ዘመነ ጌጤ በሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በአይሲስን ለመቃወም በተጠራው ስብሰባ ሽብር ለመፍጠር አሲረሃል ተብሎ ለአንድ ዓመት ያክል በማዕከላዊ ታስሮ የተፈታ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የመኢአድ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ በመሆን አግልግሏል፡፡

የአቶ ዘመኔ ጌጤ ቤተሰቦች እንደሚሉት ጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጎንደር ደርሼ እመለሳለሁ በማለት ትንሽ የጉዞ ቦርሳ በመያዝ ከቤቱ እንደወጣ እንዳልተመለሰ ነው የተናገሩት፡፡ ከጎንደር አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ከጓደኛው ወጣት ክንዱ ጋር በደኅንነት ጥር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ ውስጥ መታፈናቸውን ነው፡፡

እነዘመነ ጌጤና ክንዱ በደኅንነት ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የደረሱበት እንደማይታወቅ ነው የተነገረው፡፡ የዘመነ ጌጤ ቤተሰቦች ወንድማቸውን የት ብለን እንደምንፈልግም አላወቅንም ሲሉ በሀዘን አስታውቀዋል፡፡ ወጣት ዘመነና ወጣት ክንዱ ወደ ማዕከላዊ ወይም ወደ ትግራይ ሊወሰዱ እንደሚችሉ ጥርጣሪያቸውን መረጃውን የሰጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተመሰረተባቸው | ባለ 24 ገጹን የክስ ቻርጅ ይዘናል | ጀዋር መሐመድ እና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋም አብረው ተከሰሱ

 

(የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ዘገባ) አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ንግግር ለማድረግ ተጋብዘው ሲመለሱ የግንቦት ሰባት አመራር እና ሊቀመንበር ከሆኑት ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ታይተዋል በሚል ለእስር የተዳረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከሶስት ወር የማእከላዊ ምርመር ቆይታ በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ የክስ ፋይሉ በዶ/ር መረራ ስም የተከፈተ ሲሆን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሁለተኛ ተከሳሽ ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ሶስተኛ ተከሳሽ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ ሶስቱም ተከሳሾች የተከሰሱት በወንጀለኛ መቅጫ ህጉን የተለያዩ አንቀጾች በመተላለፍ ሲሆን አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሽ የሆኑት የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቪዥን ( ኢሳት) እና ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ( ኢኤም ኤን) ተቋማቱ በሽብር ህጉን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር መረራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የመተላፍ ተጨማሪ ክስ ተመስቶባቸዋል፡፡ የሚቀጥለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የካቲት 24 2009 አም ነው ፡፡
የክስ ዝርዝሩ ተከሳሾች በዋና አድራጊነት ሽብር ተግባር መፈጸማቸውን እና ለኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመጾች ተጠያቂ መሆናቸውን እና በሚሊኖች የሚቆጠር ንብረት መጥፋት የነሱ አመጽ ማነሳሳት መሆኑን ክሱ ያትታል፡፡

 

ሙሉ ክሱን ከስር በሚገኘው ሊንክ ላይ ዳውን ሎድ ማድረግ ይቻላል፡፡ – PDF 

ኪዳኔ ዓለማየሁ ስለየካቲቱ የግራዚያኒ ጭፍጨፋና የአድዋ ድል በዓል – ሊደመጥ የሚገባው ታሪካዊ ቃለምልልስ “ይህ ትውልድ ጣልያን የፈጸመችብንን ረስቷል”

 


ኪዳኔ ዓለማየሁ ስለየካቲቱ የግራዚያኒ ጭፍጨፋና የአድዋ ድል በዓል – ሊደመጥ የሚገባው ታሪካዊ ቃለምልልስ “ይህ ትውልድ ጣልያን የፈጸመችብንን የረሳ ይመስለኛል”

ኢትዮዽያዊነት ማለት ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ማለት ነው። አፍሪካዊነት ማለትም ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ/ ገመድህን ማለት ነው

ከሥርጉተ ሥላሴ 22.02.2017 (ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ)

„ጥበብ፡ ፈጽማ፡ የጎላች፡ ናት፡ ሥርዓቷም፡ አይልፍም፡ የሚወዷትም፡ ሰዎች፡ ፈጥነው፡ ያዋታል፡ የሚፈልጓትም፡ ሰዎች፡ ያገኙአታል። ለሚወዷት፡ ሰዎች፡ ትደርስላቸዋለች፡ አስቀድማም፡ ትገለጥላቸዋለች። በደጃፉ፡ ስትጠብቀው፡ ሁልጊዜ፡ እርሱ፡ ያገኛታል፡ ወደርስዋ፡ የሚገሠግሥ፡ ሰው፡ አይደክምም።  እርስዋን፡ ማሰብ፡ የውቀት፡ ፍፃሜ፡ ነውና። ፈጥኖ፡ ስለርሷ፡ የሚተጋ፡ ሰው፡ ያለ፡ ሃዘን፡ ይኖራል።“ (መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ 6 ቁጥር 12 እስከ 16)

ይድረስ ለቅኔው ልዑል ለብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን  – ሰማይ ቤት።

አዬ … ቀን ይሄዳል – ይጓዛል። እኛን አስቀምጦ እሱ ማንአለበት ይነጉዳል፥ ይተማል፥ መጪ ይላል። ጋሼ ጸጋዬን በሥጋ ያጣንበት ወርኃ ዬካቲት። ወርኃ የካቲት የሰማዕታት መታሰቢያ … ዛሬ እስኪ ትንሽ ስለ ቅኔው ልዑል ስለብላቴ መንፈሴ ያሰኘውን ባሻው መንገድ ይል ዘንድ ወደድኩ። እንዲህና እንዲያ …

ማን እንደአንተ ጋሼ ጸጋዬ በንጽህና እና ቅድስና ኢትዮዽያን ከውስጧ ሆኖይቃኝላት። በመሆን የከበርክ – ስለእሷ እሷን ሆነህ፤ እሷን ጠጥተህ ተመገብኽ የኖርክ ሩቅ አሳቢ፤ የተበተነን መንፈስ ሰብሳቢ፤ የአፍሪካዊነት ልዑቅ – ሊቅ፤ የሰው ዘር አፍቅሮተ ትንግርትህ  – ቀንዲልነቱ የምዕተ ዓመታት ህትምት ነው ቤተመዘክር። ደጉ የቅኔው ግሥ ፤ ሩህሩሁ ሰዋሰው፤ ጌታ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ / መድህን፤ እንደ ስምህ በምግባርህ የከበርክ የእናት ኢትዮጵያ  የውብ ቀን መርህ

መሆንን በመሆን እንዝርት ፈትለህ ለሰንደቅህ ልዕልና ነበርክ ነገረፈጅ። ባለችሎት ቢኖር፤ የመንፈሱ አቅም ያልተንኮላሼ ቢገኝ፤ ያ … ንዑድ መንፈስህ ምንኛ የኢትዮዽያዊነት የፊደል ገበታ በሆነ ነበር? አልፈህ ተርፈህ ስለ እማማ አፍሪካ የተጨነክ – የተጠበብክ የድርጊት አንበልነበርክ። ስለእያንዳንዷ ቅንጣት አመክንዮ በጉዳዬነት የያዝክ ዝልቅ ሰው ነበርክ። ትናትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ ያዋደድክ ዬጥበብ ንጡር ናሙና። አንተ፤ አንተማ ለእኔ ህዝብ ነበርክ። መቼ ቀንጣ እንደእኔ ነበርክና። በሕዝብ ውስጥ ሆነህ ስለህዝብ የኖርክ፤ የህዝብ የፍቅር አውደ ምህረት።ሞት ክፋ ሳያራራ ነጠቀን እንጂ። አንተ ራስህ እኮ ሀገር ነህ። የኢትዮዽያዊነት እንደራሴ! የአፍሪካዊነት ጭንቅላት።

የጥቁርነት ዕንቁነት በፀዳለ ትውፊት በሙሉዑ ሥነ ባህሪ ያበራህ፤ ኢትዮዽያን ያደመቅህ፤ ያስዋብክ፤ ያፈካህ የዘለዓለም ብርሃን። ውስጥህን ሳትሳሳ፤ ለእናትህ ያለተቀናቃኝ ንጹህ ልብህን የሸለምክ፤ ብሩካዊ መንፈስህን ያለ የግለኝነት ጣውንትነት ለልዕልት ኢትዮዽያ ፍቅር ያስገዛህ – ቀንዲል። እናት ሐገራችን ኢትዮዽያ ከፍ ብላ ስትታይ፤ ሞገሷ ሲጎመራ፤ ብቃቷ በአለም አደባባ ሲናኝ፤ ልጆቿ ሲወጡላት ነበር የሐሴትምንጭ። ለዚህም በምድር በኖርክባቸው ዘመንህ ሁሉ ሁለመናዋ ነበርክ። ክብሯ፤ ሞገሷ፤ ማማዋ፤ ጸዳሏ፤ ዘመኗ! ዋስ ጠበቃዋ፤ ዋቢዋ።

ትውልድ አልፎ ትውልድ መተካቱ ተፈጥሯዊ ዶግማ ቢሆንም፤ አንተን፤ ስለእናት ሀገርህ ያለህ መወድሳዊ  ያን ረቂቅ ቅዱስ መንፈስህን ግን የሚተካ አልተገኘም። ኢትዮዽዊነት እንደ ቁጥር ትምህርት በመደመርና በመቀነስ፤ ወይንም በመዳበል፤ ወይንም እንደ ተገጣጣሚ ዕቃ ተወልቆ እንደሚገጣጠም የጋራጅ ብረታ ብረት፤ ወይንም እንደ ጭቃ ተጠፍጥፎ ወይንም ተንቦልቡሎ እንደሚሰራ ጉሽጉሻ ሆነ ዕሳቤው ሁሉ።

ይህን ስልህ ግን ቅርጹ ተሸራርፎም ቢሆንም አለ – የተሰወረብን ይዘቱ ነው። የተሰወረው ዬፍጥረተ ነገሩ ንጥረ – ቅመም የግንዛቤው ጥልቀት ግልፍተኛ መሆኑን ነው። ኢትዮዽያዊነት ማሰሪያው በዛ። ምሳሩም አዬለ።በቅድመ ሁኔታ ገመድ ተተበተበ። ይለፋ አንተ ከምታውቀው ከጸዳ የዕውነት ዕሴት መነሳት ተሳነው።

ይሄውልህ የእኛ ግርማ እንዲህ የሆነበት ነገረ ምክንያቱ አሰዋወሩ ዬፍጥረተ ነገሩ ንጥረ ቅመም – የግንዛቤው ጥልቀት – ቀመሩ ሰነፍ በመሆኑ ነው። የኢትዮዽያዊነት ዕውቅናው ዜግነት መሆኑ ቀርቶ በቅድመ ሁኔታ ተገነዘ — በገጠርና በከተማ፤ በተማረና ባልተማረ፤ በሠለጠነና ባልሰለጠነ፤ ከአማርኛ ቋንቋ ተጨማሪ ቋንቋ በማወቅና ባለማወቅ፤ በተዕባትና በአንስት፤ በክት የዘውገ አባልነትና በዘወትረ፤ በአለ ዘውገኝነትና በየምነት፤ በማኒፌስቶ ማህበርተኝነትና በአልቦሾቹ … ምኑን እነግርሃለሁ በቃ ዜግነት በዚህና በዚያ ፍዳና አሳሩን ይከፍልልኃል። ቁስለቱ  – ያመግላል፤ መስፈሪያው – ያበግናል። ለዕውነት ሱባዬ ያስይዛል። የማይሰማ፤ የማይታይ የፈተና ዓይነት የለም። የኢትዮዽያዊነት አሳሩ፤ በቦንዳ፤ በደርዘን ነው። መራር ዘመን ላይ ይገኛል፤ ዓውራው ማንነት ኢትዮዽያዊነት። ስለሆነም እማም ጎዳና ላይ ስለተጣሉት ልጆቿ አምርራ – ታለቅሳለች። አብሶ ባለቤት አልቦሾቹ ይበልጡን እጅግ የበዙ ናቸው። ሰው በመጠጥና በውኃ ብቻ አይኖር ነገር …

አንተ ተፈጥሮህ አመክንዮ፤ ጉዞህ ወደ አመክንዮ። መዳረሻህም አመክንዮ። ስለምን? ሚስጢርነትህን  የመንፈስህ ብቸኛ ሚሥጢረኛ ለማድረግ ስለፈቀድክ። በአንድ ነገር ግን መጽናናት ይቻላል። ኢትዮዽያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና። ወደፊትም ልብ ሞልቶ ሊያናግር የሚችለው የአመክንዮ አናት ኢትዮዽያዊነት አሸናፊ ማንነት ሆኖ ቀጣይ መሆኑ ነው። የሚያቆበቁቡ ማናቸውም ሳንኮች ሁሉ ከእግሩ ሥር ይነጠፋሉ። ኢትዮዽያዊነትን ተረግጦ የህዝብን ፍቅር ያፈሰ ማንም – ምንም ኃይል የለም። ወደፊትም አይኖርም። እዚህ ላይ በትልቁ የምጋራው የሊቀ – ሊቃውንቱ የታሪክ ሙሁር የፕሮፌሰር ኃይሌ ላሪቦን „ኢትዮዽያዊነት ረቂቅ መንፈስ ነው“ ይህ አገላለጽ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ እንደ ዶግማ ነው የምቀበለው። የቅኔው ንጉሥ ዬብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገመድህን መንፈስም ቅመሙ ይሄው ነውና።

ስለምን? በውስጤ ያለውን ረቂቅ ሙቀቱን አሳምሬ ስለማውቀው። እሱን ሳስብ ብቻ ነው አጃዬ የሚሞላው። ከእሱ ጋር ለመኖር ስፈቅድ ብቻ ነው ድንጉጥ የማልሆነው። በየትኛውም ሁኔታና ቦታ ስለእሱ ስመሰክር ብቻ ነው መንፈሴ ከዕውነተኛው ሐሴት ጋር የሚገናኘው። ስለእሱ ስናገር ብቻ ነው በሰው ሀገር ብኖርም ባለሀገር መሆኔ ድፍረት የሚኖረው። በሌላ በኩል በዚህ የስደት የዝንቅ ህይወት ውስጥ ከሌላ ሀገር ዜጎች ጋር በሚኖረኝ ማናቸውም ግንኙነቶች ሁሉ ንጽጽሩ በእርጋታ ሳስተውለው ረቂቁ ማንነቴ ኢትዮዽያዊነት የሰጠኝን ዝቀሽ ዕሴት ማገናዘብ ችየበታለሁና። የመሰደዴ ዋናው ተቋሜም እራሴን የምለካበት ወቄት ማግኘቴ ነው። እማላማርረውም ለዚህ ነው እንጂ፤ ለእኔ ተፈጥሮ ውጭ ሀገር መካን አመክንዮ ነው።

ኢትዮዽያዊነት ሊገልጹት የማይችሉት የመንፈስ እጨጌ ነው። አውልቆ ለመኖር ቢታሰብ እንኳን – የሚስብ  አንዳች ብቁ ኃይል ነገር magnet አለው። እህል ውሃው የማይለቅ ጥልቅ ማንነት ነው ኢትዮዽያዊነት። ወለሉ ዲካ ዬለሽ ነው። በመገፋፋት ውስጥ መቻቻልየነገሰበት። በመሸጋሸግ ውስጥ መዋህድ የተፋቀረበት።

ኢትዮዽያዊነት ፈተናው የዘመናት ነው፤ ግን ትብትቡን ጣጥሶ አሸናፊ ይሆናል። እሱም እንደ እናቱ አላዛር ነው። ሌላው ቀርቶ ሌት ተቀን ተቀናቃኙ እያዬለ ስለእሱ በባለቤትነት የሚከወን የታቀደ ተከታታይ ተግባር ሳይኖርግን ጎልቶ፥ ፈክቶ እጅግም ጎልብቶ ብቅ ይላልታምረኛው – ኢትዮዽያዊነት። ለዚህም ነው ሊቀ ሊቃውንቱ ፕ/ ኃይሌ ላሬቦ ቃል ቢያጡለት፤ መፍቻ ትርጉም ቢያጡለት ረቂቅ መንፈስ“ያሉት። ረቂቅ መንፈሱን መቀበልም በቅድመ ሁኔታ ከወገብ በላይና በታች መሆን አይኖርበትም፥  ከመንገድ በላይና በታችም። „ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ“ ይላሉ ጎንደሬዎች ሲተርቱ። ከጋብቻ በኋላ በተጋቢ ቤተሰቦች ያለውን ትርምስ በቅኔ – ሲቃኙት። ጋብቻው ሁሉ በኢትዮዽያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ ከሆነ የሸሪፎ ቤተኝነትን ተከልቶ መሆን ይኖርበታል።

ስለሆነም ኢትዮዽያዊነት ሞገሴ ለሚል ተቋም፤ የፖለቲካ ድርጅት፤ ወይንም ግለሰብ ማዕቀፋ ዥንጉርጉሩንም አጽድቆ ከልብ ስለልብ ሁነኝልሁንህ ማለትን ይጠይቃል። ድፍረት! ከምላስ ርጥበት ያለፈ ሁነኛ ዬማመሳከሪያ ውስጣዊ ሰነድ። ወጀብ የማይንጠው። ዬግላዊነት ቁንጥጫ የማያሸማቅቀው።

ለዛ የኢትዮዽያዊነትን መንፈስ ጥልቅነቱን ለገለጸ አንደበትም፤ ዘመን አሻጋሪ ዶግማም፤ በትረ የትውልድ ሥህንም ክብሩን ቁልቁል ማውረድ ዘመንም ታሪክም ይቅር የማይለው፤ የህሊና ዕዳ ነው። በተለይ „ኢትዮዽያ  ለዘለዓለም በክብር  ትኑር!“ አቡነ ዘበሰማያቱ ወይንም „አላህ አክብር“ ላደረገ ተቋም፤ ድርጅት ወይንም የእኔ ቢጤ ባተሌ። የእግዚአብሄር ቃል ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ „ ይላል። ለተዋህዶ አማንያን ይህን ቃለምህዳን መጋፋታም የእርግማ ጥሪት ማጠራቀም ይመስለኛል። የጻድቃን አባቶቻችን የልፋትና የድካም ዋጋ እሾህ ሆኖ ይወጋናል።

ልዕልት ሐገራችን ኢትዮዽያ በጅምላና በችርቻሮ በንግድ የገብያ ሥርዓት የተቸረቸረች ወይንም ሱቅ ተሂዶ የተሸመተች ሀገር አይደለችም።ከፈጣሪ በታች ከእሷ ልቅና እና ልዕልና በላይ ማንም፥ ምንም ዬለም። ስለሆነም በእሷ የሚመጣ ጉዳይ ሁሉ፤ ከክብሯ አገላለጽ ውጪ ያሉ ጉዳዮች ሁሉ፤ እንደ አግባብነታቸው በመንፈሷ ሥር ሊተዳደሩና በቅጡ በብልጥነት ሳይሆን በብልህነትና በጥበብ ሊመሩ ይገባል። ንጉሥ ዳዊት „ዬቤትህ  ቅናት በላይ“ ያለው ይፈጸም ዘንድ – ዶግማውን መፍቀድ ይኖርብናል። ዬቤቷ ቅናት ሊያርመጠምጠን ይገባል። ጊዜ ያልፋል፤ ዘመን ያልፋል፤ ትውልድም ያልፋል። ኢትዮዽያ ግን ፈጽሞ አታልፍም። ለዘለዓለም ትኖራለች! አልፋና ኦሜጋ ናት። ትምክኽቷ አምላኳ ነውና።

ኢቲዮዽያዊነት መሸፈኛ፤ መጠቅለያ፤ ማሸጊያ ወረቀት መሆን አይኖርበትም። የልብ ክፍል፤ የኩላሊት ክፍል፤ ቤተ – ትልቅና ትንሽ አንጀት – ዓፄው ጭንቅላት ወዘተ … ሁሉም በአንድ ላይ በተፈጥሮ ሥርአታቸው ተግባራቸውን ሲወጡ ብቻ ነው ሰውም እንደሰው፤ ትውልድም እንደትውልድ የሚቀጥለው። ስለሆነም በኢትዮዽያዊነት ውስጥም የላይ ቤት፥ የታች ቤት ሠርቶ ስብከት ለእኔ የእንቧይ ቤት ነው። በመሆንየከበረ ኢትዮዽያዊነት ነው ነፍስን ሊገዛና ሊነዳ የሚችለው። እንደ ጌታ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን – መሆን መቻል።

ጌታ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ከሊቅ እስከ ደቂቅ መንፈሱ ክብር ያልሰጠበት፤ ከውስጡ ያልተመሰጠበት ከቶ አንዳችም ብሄራዊ ጉዳይ ሆነ ማህበረሰብ የለም። ለዛውም ሰውንና ዕውነትን ማዕከል በማድረግ። ዛሬ በዘመናችን በኢትዮዽያዊነት አመክንዮ ውስጥ ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ናሙና የምለው የስሜን አሜሪካ ዬስፖርት ፌስቲባል መሰናዶና ዕሴቱን ብቻ ነው። ወጣ ገባ አይደለም። ቀጥ ባለ ግልጽና ቀጥተኛ አቋም በየዓመቱ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማችን ከፍ እንዲል ያደርጋል። ይህ የሰንደቅ ተጋድሎ ገድል ነው ለእኔ። ተቋሙ በብሄራዊ ዓርማችን ላይ ያለው ምራቁን የዋጠ አቋም በውስጣችን ያለውን አክብሮትና ልቅና ገላጭ – የታሪካችን ቁንጮ ነው ማለት ያስችለኛል። ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ የስሜን አሜሪካው ዓመታዊ የስፖርት ዝግጅት አድዮ አበባ ነው። ለእኔ የኢትዮዽያዊነት አዝመራ ነው። ለእኔ ባለቅኔው ጸጋዬ ገመድህን ነው። ለእኔ ጀግና አብዲሳ አጋ ነው። በአጋጣሚው ያለኝን የውስጥ ፍቅር ስገልጽ ለአዘጋጆች በሐሴት ነው።

እርገት።

በል የእኔ አባታዊ ዬሥነ ጥበብ ጌታ ጋሼ ጸጋዬ ልሰናበትህ ስለእናታችን እንወዛወዝልህአለን የንፋስ ፍጥነት መለኪያው Anemometer እንዲህና እንዲያ …

ማጠናከሪያ ጹሁፍ  …

http://www.zehabesha.com/amharic/?p=39302

የውስጥ እንደራሴ – እንደ ህዝብ … – ሥርጉተ ሥላሴ

 

ኢትዮዽያዊነት ይከበር!

መሸቢያ ጊዜ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።