የ‹ፍቱን›ንን ጎጆ በህወሓት ‹መድፎች›! – ጋዜጠኛ ፍቃዱ በርታ

 

ኢህአዴግ  የግል ሚድያውን በመዝጋት እና ስጋት ላይ ጥለውት  የነበሩትን አንድነት ፓርቲን  በማፍረስ(መኢአድን  በማሽመድመድ) የ2007ቱን ምርጫ ማጅራቱን ብሎ ሊደፋው እንደሚችል እርግጠኛ ነበር፡፡ይህን አቅዱን ለማሳካት በተለይ የግል ሚዲያውን የመዝጋት ዘመቻውን የጀመረው ገና ‹ምርጫው› ከመድረሱ አመት ከመንፈቅ ቀደም ብሎ በቁጥጥሩ ስር ባሉት በኢቲቪ፣በሬዲዮ ፋና፣በአዲስ ዘመን እና በብሮድካስት ባለስልጣን አማካኝነት  ነበር፡፡

ህወሓት በሰላሙ ጊዜ የዘወትር ስራቸውን የሚከውኑ ፤በችግር ጊዜ በ‹ጠላቶቹ› ላይ እንዲዘምቱ፤ መልምሎና አሰልጥኖ  ያስቀመጣቸው -ከተሜው በተለምዶ ‹‹የህወሓት መድፎች›› የሚላቸው፡ ሬዲዮ ፋና፣ኢቲቪ፣ምርጫ ቦርድ፣ ብሮድካስት ባለሥልጣን፣ገቢዎችና ጉምሩክ ወዘተ የተሰኙት አጠቂ  ምድብተኞች አሉት፡፡ከላይ እንደተገለጠው የዚህ  ሰራዊት ግዳጅ እንደ ተጠባባቂ ጦር በሰላሙ ጊዜ አምራች  ህወሓት  ምጥ ውስጥ ሲገባ  ደግሞ እየተወነጨፉ  ‹ ጠላቶቹን›  ልክ ማስገባት ነው፡፡ ለህወሓት ‹ጠላት› የመተንፈሻ አካሉ ስለሆነ ‹የጠላት› ትንሽ የለውም ፡፡ ታንክና መድፍ አሰልፎም የሚዋጋው  ኃይልም ይሁን፣  ነውሩን የሚጋልጥበት ጋዜጠኛ ፣ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ  ሰላማዊ  ታጋይም ይሁን ተቃዋሚ ፓርቲ  በህወሓት ዘንድ ለውጡ እምብዛም ነው፡፡  ስጋት ውስጥ እስከ ጣሉት ድረስ መድፎቹን  አሰልፎ ‹‹ውረድ እንውረድ›› ማለት የሚኩራራበት ተግባሩ ነው፡፡

የግሉ  ፕሬስ  (ፋክት፤አዲስ ጉዳይ፣ሎሚ፣ ጃኖ ፣ ዕንቁ እና አፍሮ ታይምስ)  ጋዜጠኞች ላይ ህወሓት የወሰደው ኃላ ቀር  እርምጃ  ተሳታፊ የነበሩት ደህንነት፣ገቢዎችና ጉምሩክ፣ የብሮድካስት ባለሥልጣን፣ ሬዲዮ ፋና ኢቲቪ እንዲሁም ፍትህ ሚኒስቴር ነበሩ፡፡በጋዜጠኞቹ  ላይ በተካሄደባቸው  ያልተቋረጠ ክትትል ፣የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ  እና  በከፈተው ‹‹አመጽ የማነሳሳት›› ክስ ምክንያት ለህይወትና ደህንነታቸውን ዋስትና አሳጥቶ አገር  አልባ ሲያደርጋቸው ፤ ለወሬ ነጋሪት የተረፈው ፍቱን መጽሔት ሆነ፡፡

መጽሔታችን በንዴት በደፈረሱት  የህወሓት ዓይኖች  መታየት የጀመረው ስያሜውን ከላይፍ ወደ ፍቱን ቀይሮ ህትመት በጀመረ በጥቂት ወራት ልዩነት ነበር፡፡ በተለይም  ስድስቱ የህትመት ውጤቶች ከስራ ውጪ ሆነው  ፍቱን አንባቢ እጅ  የሚገባ  ብቸኛ  ሚዲያ መሆን  ሲጀምር    የሁሉም ቡጢ  የሚያርፍብን  የቦክስ መለማመጃ  ከረጢት መሆን  ግዴታችን  ሆነ፡፡ በተለይ ነጭ ለባሾች ቢሮአችን አካባቢ  ማዘውተር  የየዕለት ስራቸው ሆነ፡‹‹ ድጋፍ የሚያደርግላችሁ የውጪ  ኃይል  እንዳለ እናውቃለን፣ በሰላም አገር ማንም ባልታሰረበት  ፍቱን የሚባል መጽሔት እያሳተማችሁ የምታሰራጩት ህዝቡን ለአመጽ ለማነሳሳት እንደሆነ ደርሰንበታል ፤ ይህን አመጽ ቀስቃሽ መጽሔታችሁን የማትዘጉ ከሆነ በሽብር ክስ ቃሊት እንደምትከርሙ አትጠራጠሩ፤›› የሚሉ  ዛቻና  ማስጠንቀቂያች መዘውተር ጀመሩ፡፡

ህወሓት ወደ ፍቱን ጎጆ የተኮሰው  ተከታዩ መድፍ  የብሮድካስት ባለሥልጣን ነበር፡፡  በግዳጁ  መሰረት ባለስልጣኑ ‹‹አፍራሽ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ የግል ህትመቶችን  ልከስ ነው›› በሚል ማደናገሪያ ፤ በመጽሔታችን ላይ ብቻ ያነጣጠረውን  ክሱን አጠናቅሮ መጨረሱን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት  ቀርቦ አረጋገጠ፡፡http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=15222፤ ብሮድካስት ለፓርላማው ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት የግል ህትመቶችን-‹‹ገንቢ ፣ አፍራሽና  ገንቢም አፍራሽም  ያልሆኑ ዘገባዎቸን የሚያሰራጩ ›› በማለት በሶስት ምድብ ከፍያቸዋለሁ ያለ ሲሆን – ‹‹አፍራሽ  ዘገባ ያሰራጫል ›› ተብሎ የተወነጀለው ፍቱን መጽሔት እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ለማረጋገዘጥ ችለናል፡፡

 በወቅቱ በገበያ ላይ የነበሩት የግል የህትመት ውጤቶች፡ ሪፖርተር፣ አዲስ አድማስ፣ሰንደቅ፣ ፎርቹን ፣ ካፒታል  እና ፍቱን  መሆናቸው ለሚያውቅ ማንኛውም ሰው  በብሮድካስት አማካኝነት ‹‹አፍራሽ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ የግል ህትመቶች ልከስ ነው›› በሚል ሽፋን  ለፓርለማ የቀረበው  ሪፖርት ቀጥታ ያነጣጠረው ፍቱን መጽሔት ላይ እንደነበር በቀላሉ መረዳት አይከብደውም፡፡

ወደ ፍቱን ጎጆ የተተኮሰው ሌላኛው መድፍ አገር ውስጥ ገቢ ነበር፡፡ በደህንነትቶች  የታጀቡት የሀገር ውስጥ ገቢ ሰዎች በድንገት ቢሮአችንን ወረው  ያገኙትን  መጽሔቶች እና ሌሎች ዶክሜንቶችን  በመውሰድ፤አጋጣሚ ሆኖ የድርጅቱ  የሂሳብ መዝገብ ሰነድ ለድጋሚ ኦዲት  ኦዲተሮች ወስደውት ስለነበር  ቢሮ ውስጥ ሊያገኙት ስላልቻሉ ከ5 ቀናት ውስጥ አጠናቀን እንደምናስረክባቸው ተስማምተን ቢሮውን ቀውልን ሔዱ፡፡

 የሂሳብ መዝገብ ሰነዱ  ድጋሚ ኦዲት ከተደረገ  በኋላ በተባልነው ቀን መገናኛ ከሚገኘው  ዋናው መስሪያ ቤታቸው ወስደን አስረከብን፡፡የሂሳብ መዝገብ ፋይላችን ሳሪስ ከሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ወደ መገናኛ ሲዘዋወር  በአምስት አመት  ጊዜ ውስጥ  የመጀመሪያ  ቢሆንም በአጋጣሚ ግን  አይደለም፡፡ ወደ መገናኛ የሚወሰዱ አብዛኞቹ ሰነዶች  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የህወሓት የቅጣት ሰለባ እንዲሆኑ የሚፈረድባቸው ድርጅቶች ናቸው፡፡በክፉ ዓይን ታይቶ እዚያ  ቤት የሚገባ  የድርጅት የሂሳብ ሰነድ እንኳን በሰው በመላዕክታትም ቢሰሩ የጅብ ራት ከመሆን  አይድኑም፡፡

‹‹ሕገ ወጡ›› ደረሰኝ!

የድርጅታችንን የሂሳብ ሰነድ ካስረከብንናቸው በኋላ ‹‹ማመሳከር እንፈልጋለን ›› የሚሉንን ሰነድ ለሁለተኛ ጊዜ  ወስደን አስረክበናቸዋል፤የከሳምንት  በኋላ ሌላ ማመሳከር እንፈለጋለን ያሉንን ደረሰኝ እንድናቀብላቸው በስልክ ነግረውን  ቢሮአቸው ስደርስ  የተቀበለኝ አቶ ቴዎድሮስ አብቹ የሚባል ‹‹የኢንስፔክሽንና ኦዲት ቡድን አስተባባሪ ››ነው፡፡

‹‹ ሕገ ወጥ ደረሰኝ ተጠቅማችኋል!›› አለኝ፣ገና ከመቀመጤ ፤

‹‹ ስለየትኛው  ህገ -ወጥ ደረሰኝ ነው የምታወራው? ›› ብስጭትና ግራ መጋባት ውስጥ ሆኜ ጠየቅኩት፤

ታትመው  ለረጅም ጊዜ  ጥቅም ላይ ያልዋሉ 2 ጥራዝ ደረሰኞችን  እያሰየኝ፤ ‹‹ስለእነዚህ ነው የማወራው፤››

‹‹ይሄ እኮ ከ 5  ዓመት በፊት  በ2002 ዓ.ም፣መገልገል የነበረብን በእናንተ እውቅና የሚታተም ደረሰኝ እንደነበር ሳታሳውቁን በፊት ስንጠቀምበት የነበረ ነጭ ደረሰኝ ነው፡፡ያም የሆነው  የእናንተ ቸልተኛነት ምክንያት ተፈጠረ ስለመሆኑ ሁለታችንም መግባባት ላይ ደርሰን  ቅጣት ከነወለዱ ከፍለን ያበቃ ጉዳይ ነበር እኮ ፡፡ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በ2002ዓ/ም የሂሳብ መዝገብ ውስጥ ተያይዟል እኮ፤ አላየኸውም እንዴ? ››፤

‹‹ባየውም  ለውጥ አያመጣም !››

‹‹ይኸውልህ አቶ ቴዎድሮስ ፤  የዛሬ አምስት ዓመት በ2002 PLC ተደርገን  ለምዝገባ ወደ መስሪያ ቤታችሁ ስንመጣ  ምን አይነት ደረሰኝ መጠቀም እንደነበረብ የ10 ደቂቃ ጊዜ ወስዳችሁ ሳትነግሩን ነበር የሸኛችሁን ፡፡ እኛ ደግሞ እንደ እናንተ ቸልተኞች መሆን ስላልፈለግን እናንተ ጋ ከመመዝገባችን በፊት እናደርግ እንደነበረው  ነጭ የሽያጭ  ደረሰኝ  አሳትመን መጠቀም ጀመርን፡፡ በመጨረሻም  18 ደረሰኞችን ከተጠቀምን በኋላ በ2003 ዓ/ም  አመታዊ ግብር ለመክፈል መስሪያ ቤታቹሁ ስንሄድ፤ ሽያጭ ያካሄድነው turnover tax(tot) ሳንጠቀም በመሆኑ በዚያው መሰረት ሂሳቡን  አስተካክለን  እንድንመለስ ተነገረን፡፡ እንደተባልነው የሽያጭ ሂሳቡን ከ2% ቲኦቲ ጋር  አስተካክለን አስረከብን፤የሂሳብ ሰራተኞቻቹም  ለ18 ወራት  ያካሄድነው  18 የሽያጭ  ደረሰኝ  ሂሳብ የኮምፕዩተር ሲስተም ውስጥ ሊያሰገቡ የሚችሉት  ከቅጣትና ወለድ ጋር ስለሆነ  ያንን ክፍያ መፈጸም እንዳለብን ነገሩን፤  እናንተ ለፈጠራቹሁት ችግር  እኛን መቅጣት ተገቢ ስላልሆ  መክፈል እንደማይገባን ለማስረዳት ሞከርን፡፡ ሰራተኞቹም  የምንጠቀምበትን  ደረሰኝ የማሳወቅ  ሓላፊነት የመስሪያ ቤቱ ስለነበር ቅሬታችን ተገቢ መሆኑን አምነው ነገር ግን የኮምፕዩተር ሲስተሙ ያለፉትን ወራት የሽያጭ ሂሳብ ሲያስገቡ ያለ ወለድና ቅጣት ስለማይቀበል የተባለውን ቅጣትና ወለድ ከመክፈል ውጭ አማራጭ እንደሌለን ነገሩን፡፡ እኛም የተጣለብን ቅጣት ከፍለን ከእዳ  ነጻ መሆናችን የሚያረጋግጥ ክሊራንስ  ወስደን  እስከ ዛሬ በሰላም ስንሰራ ነበር ፤›› በማለት ለማስረዳት ሞከሩ፡፡

‹‹ቢሆንም ለውጥ የለውም፤››

‹‹ ምን ማለት ነው ለውጥ የለውም ማለት? በ2002  ዓ/ም  የእናንተ ቸልተኛነት ውጤት መሆኑን ያመናችሁትን ጉዳይ ፤ ዛሬ  በድንገት   ከ5 ዓመት በ ኋላ እንዴት የእኛ ጥፋት ሊሆን  ቻለ?››

‹‹ ስለዚያ የማውቀው ጉዳይ የለም፤››

‹‹አቶ ቴዎድሮስ የሂሳብ ባለሙያም አይደለህ? ፍላጎትህ እውነቱን ለማወቅ  ቢሆን መዝገቡን በማየት ብቻ ትደርስበት አልነበር!››

ሰዉዬው  የጠራኝ  ግራ የተጋባበት ጉዳይ ኖሮት አልበረም፤ የጠራኝ መጽሔታችን የመስዋዕት በግ መሆንዋን ሊያረዳኝ ነው፡፡ የሚሞግተኝ  እውነታው ጠፍቶት ሳይሆን በመጽሔቱ ላይ ያገኘውን የሽፍትነት ድል ሊያረጋግጥልኝ ነው፤  ለነገሩ ስንት ጉድ በሚሰራበት አገር ይህ ሰው ለምን ብሎ  ለዕሊናው ይቆማል?፤

‹‹ አቶ ቴዎድሮስ መጽሔታችንን  ለመዝጋት የማትፈጽሙት ነገር እንደሌለ ይገባኛል፤ ነገር ግን ይህን ተልካሻ ምክንያት ትጠቀማላችሁ ብለን ግን  አልጠበቅንም፤››

‹‹እኛ  የተለየ ፍላጎት ኖሮን ሳይሆን ወንጀል ስለተሰራ ነው››

‹‹እሺ አለቃህን ማነጋገር እፈልጋለሁ?››

‹‹ስራውን እንድጨርስ የተመደብኩት እኔ ስለሆንኩ  የምታነጋግረው አለቃ የለኝም፤ ለማንኛወም ሁኔታው ተደውሎ ይነገርሃል፤››

በቀጣዩቹ ቀን በአንዱ፤ አንዱ የስራ ባልደረባዬ፡ ‹‹ፍቃዱ ደህንነቶች ሰፈር  ደረስ መጥተው ‹ከእንግዲህ እዚያ መጽሔት ላይ ብትሰራ  አጎቶችህ መስዋዕት ሆነው ያስኙትን ስርዓት  እንደከዳህ ነው የምንቆጥረው › ብለውኛል፤ ከዛሬ  በኋላ ስራው  ቢቀርብኝ  ምን ይመስልሃል? ››

በዚያው ሰሞን፤ እየጠራ ያለውን ስልኬን አንስቼ ‹አቤት› አልኩ፤ ከማተሚያ ቤት ነበር የተደወለልኝ፡ ‹‹ ፍቃዱ ከዚህ ሕትመት በኋላ መጽሔታችሁን ላለማተም ወስነናል፤ መቼም ጉዳዩን እንደምትረዳን ተስፋ እናደርጋለን ››፤

የህወሓት በደህንነቱ አማካኝነት  ከአገር የማልወጣ ከሆነ በጸረ ሽብር ህግ  ልከሰሰ ዝግጅት መጠናቀቁን  ካረዳኝ  ሳምንት ሆኖታል፡፡ሌላኛው  መድፈኛ በ‹‹ሕገወጥ ደረሰኝ መገልገል ›› ሊከሰኝና መጽሔታችንንም ሊዘጋ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አርድቶኛል፡፡የህወሓትን ‹‹መድፎች ›› በባዶ እጅ እየተጋፈጥኩ እንዳለሁ ተሰማኝ፡፡በገዛ አገሬ በሆነ ወራሪ ኃይል እንደተከበብኩ ተሰምቶኝ የተስፋ መቁረጥ ጽልመት ውስጥ ሰጠምኩ፡፡

የቅምጦቹ፡ ብሮ ወሸባዬ›!

በሳምንቱ ፤ለህወሐት የደረጃ ቅምጥነት ፉክክር ውስጥ የሚገኙት ሬዲዮ ፋና እና ኢቲቪ መጽሔቱን እና እኔን ግዳይ ጥለው ‹ብሮ ወሸባዬ› ጭፈራ ላይ  ነበሩ፡፡ፋና ምሽቱን ጨምሮ  ቀኑን ሙሉ ፡‹‹ ሁለት ተመሳሳይ ደረሰኞችን በማሳተም ያልተገባ ጥቅም ሲሰበስብ በመገኘቱ ነው እገዳ የተጣለበት››፤በማለት አትቶ፡ ያለሁበትን‹‹ በመጠቆም ህዝብ ትብብር እንዲያደርግ›› ጥሪ  አስላለፈ፡፡ ኢቲቪ በበኩሉ የምፈለገው ‹‹ በሕገ -ወጥ ደረሰኝ እንጂ በፖለቲካ ጉዳይ›› እንዳልሆ ምስሌን አስደግፎ የድል ዜና› ሰራ፡፡ ከአገር እንድወጣ የሰጠኝን የአንድ ሳምንት ጊዜ ተግባራዊ  ካለማድረጌ ጋር ተያይዞ  ጉዳዩን  በመጽሔታችን ላይ ለህዝብ ይፋ እንዳላደርግ ስጋት የገባው ህወሓት፤በቅምጦቹ አማካኝነት፡ ‹‹መጽሄቱም ቢሆን በድብቅ እንዲታተም ቢመጣ እንኳን የህትመት ተቋማት ይህን ተረድተው ከማተም እንዲታቀቡ››አዋጅ በማስነገሩ፤ ጣጣውን የፈራው ማተሚያ ቤት ለደህንነቶች  በማሳወቅ ፣ለአንባቢ ሊሰራጭ የነበረ  ወደ 50 ሺህ ብር ወጪ የተደረገበት መጽሔት በማገት ለአንባብያን ዓይኖች እንዳይበቃ ማድረግ ችኋል፡፡

ብእር ብቻ የጨበጥን አስር  የማንሞላ የፍቱን ጋዜጠኞች፡ የህወሓትን አምስት ኋላቀር (አንዳንዶቹም ዘረኛ) ‹መድፎች› ተቋቁመናል፡፡ አለቆቻችን ለነበሩት አንባብያንና የኢትዮጵያ ህዝብ ቃል የገባነውን በታማኝነት የማገልገል ግዴታችንን ጠብቀናል፡፡ በማባበያም ፣ በማማለያም ሳንደለል የህዝቡ ታማኝ አገልጋይ ሆነን ከህሊና ወቀሳ የጸዳ ስራ ሰርተን በማቆማችን፤ ዛሬን ቀና ብለን እንድንሔድ ምክንያት ሆኖናል፡፡

በጃናሞራ የዐማራ ገበሬዎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞ እንዳነሱ ተሰማ | ኃይለማርያም የወልቃይት የዐማራ ብሔርተኝነት ጥያቄን ካዱ

 

 

 የካቲት 15 ቀን 2009 

ከሙሉቀን ተስፋው

 የዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛዎች በዳኛ ቢኒያም ዮሐንስ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ተቃወሙ፤
 በጃናሞራ የዐማራ ገበሬዎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞ እንዳነሱ ተሰማ፤
 በወገራ የገበሬዎች ቤት የወያኔ ወታደሮች ካምፕ እንደሆነ ተገለጸ
 ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የተነሳ የማንነት ጥያቄ የለም ሲሉ የወልቃይት የዐማራ ብሔርተኝነት ጥያቄን ክደዋል
 በነማስረሻ ሰጤ መዝገብ የተከሰሱ የዐማራ ወጣቶች በሐሰት ውንጀላ ጥፋተኛ ተባሉ፤

ዝርዝር፤
፩ ትናንት የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት አቶ ቢኒያም ዮሐንስ ችሎት ላይ እንዳሉ የወያኔ ደኅንነቶች አፍነው መውሰዳቸውን ተከትሎ የዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ዛሬ ተቃውሟቸውን መግለጻቸው ተሰምቷል፡፡ ዳኞቹ የፍርድ ቤትን አሠራርንና ሕገ መንግሥትን በጠራራ ፀሐይ ሙልጭ አድርጎ የጣሰ የማፍያ ሥራ መሆኑን ለፍትኅ ቢሮ አስታውቀዋል ተብሏል፡፡ ወያኔ ምንም እንኳ በዳኞች ውሳኔ ላይ ጣልቃ በመግባት ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም እንዲህ ያለው ዐይን ያወጣ የማፍያ ሥራ ግን በታሪክ ታይቶ አይታወቅም ሲሉ ተችተዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ዳኞች መደበኛ ሥራቸውን እንዳላከናወኑ ተገልጧል፡፡
አቶ ቢኒያም ዮሐንስን እንዲታሰር ያደረገው አዲሱ የጎንደር ማረሚያ ቤት ሹም የትግራይ ተወላጁ ጀማል ሰኢድ ሲሆን በዳባት ማረሚያ ቤት በነበረ ጊዜ ለበርካታ ወጣቶች እንግልትና ሞት ተጠያቂ እንደሆነም መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
፪ በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ዐማራ ገበሬወች ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2009 ዓ.ም ተጋድሎ መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡ ገበሬዎቹ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው እና በዐማራ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ግድያ እና እስራት ካልቆመ ተጋድሏቸውን እንደማያቆሙ ተነግሯል፡፡ በአካባቢው የስልክ አገልግሎት አስቸጋሪ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ማግኘት አልቻልንም፡፡
፫ በተያያዘ ዜና ደግሞ በወገራ ወረዳ የእንቃሽ አካባቢ ገበሬዎች መኖሪያ ቤቶች ወደ ወታደር ካምፕነት መቀየራቸውን የጎብዝ አለቆች ገልጸውልናል፡፡ ‹‹ቤታችን አቃጥለውት እንደገና ለመሥራት እየሞከርን ነበር፤ ሆኖም ባለፈው ሳምንት መጥተው እንደገና ጦርነት ከፈቱብን፡፡ ተታኩሰን ወደ ጫካ ወጣን፡፡ ካልያዝን ወይም ካልገደልን አንመለስም ብለው ቤታችንን እንደካምፕ እየተጠቀሙ እዚያው እየኖሩ ነው›› ሲሉ አንድ የጎበዝ አለቃ ማምሻውን ገልጾልናል፡፡ እንደ ጎበዝ አለቃዎቹ ገለጻ አሁን ላይ ዝናብ እየዘነበ ሲሆን እርሻም ማረስ የሚጠበቅ ቢሆንም በግፍ ከቤታችን ተፈናቅለን በጫካ ለመኖር ተገደናል ብለዋል፡፡
፬ የወያኔዎቹ አሽከር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ትናንት ባአከር ኹመራ ላይ ከትግሬ ሰፋሪዎች ጋር ባደረገው ንግግር የተነሳ የማንነት ጥያቄ የለም ሲል እንዲናገር የታዘዘውን አስተጋብቷል፡፡ ይህም በመቶ የሚቆጠሩ የዐማራ ወጣቶች ሕይወት የጠፋበትን የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ነው የደመሰሰው፡፡ በሌላ በኩል የብአዴኑ ደመቀ መኮነን በሳምንቱ መጀመሪያ ከጎንደር ከተማ ሕዝብ ጋር ባደረገው ስብሰባ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ዋናው የመወያያ አጀንዳ እንደነበር እንዲሁም እርሱም በአፋጣኝ ሊፈታ እንደሚችል ተናግሮ ወጥቷል፡፡ የፋና ብሮድካስቲንግ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ አፈታት በተመለከተ ዜና ሰርቶ በወያኔዎች ትእዛዝ ወዲያውኑ አንስቶታል፡፡ ስለሆነም ከትግሬ ጠባብ ብሔርተኞች ጋር የሚደረገው የሞት የሽረት ተጋድሎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአካባቢው ተወላጆች ተናግረዋል፡፡
፭ በነማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በተከሰሱ 6 የዐማራ ወጣቶች ላይ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 4ኛ ምድብ ችሎት የእስር ውሳኔ መስጠቱ ተገልጧል፡፡ በስድስቱ የዐማራ ወጣቶች ላይ የቀረበው ክስ ከግንቦት 7 ጋር የተያያዘ እንደሆነና ከ6 እስከ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት መሆኑን መረጃውን የላኩልን ሰዎች ተናግረዋል፡፡

የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል/

በኢትዮጵያ እና በሕዝቧ ፍቅር መላው ቤተሰባቸው የተለከፈው የታሪክ ተመራማሪው እና የመብት ተሟጋቹ የአንጋፋው ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት ገድል እና ዝክር

 

በኢትዮጵያ እና በሕዝቧ ፍቅር መላው ቤተሰባቸው የተለከፈው የታሪክ ተመራማሪው እና የመብት ተሟጋቹ የአንጋፋው ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት ገድል እና ዝክር (ልዩ ዘገባ) በታምሩ ገዳ

ትንሽ ስለብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ – ከኮ/ል አለበል አማረ

 

በብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ ግለ ታሪክ ብዙ የሚነገርለት ብርቱና ጀግና የጦር ባለሙያ ነው። ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞን በቅርብ የማውቀውን ያክል ስለሱ ማውሳት ደጋግሜ ባስብም ተፈላጊ መረጃወችን ለማግኘት ባለመቻሌ ዘገየሁ፣ አሁን ግን ገላጭ መረጃወችን በቅርብ ለማግኘት እድሉ ያላቸውን ሰወች በማግኘቴ ስለ ጀግናችን ማንነትና በጀ/ል ሳሞራ የኑስንና ህወሃት የሚመራው ሰራዊት ንቅዘትና ብልግናን ለማሳየት የአንድን የትግሬ የጦር አዛዝ ጀኔራልን ድርጊት በማሳያነት በመውሰድ እንደሚከተለው አቅርቤዋለው።

አንባቢወቻችንን ላለማሰላቸት ጹሁፉን በሁለት ተከታታይ ክፍል አቅርበነዋል። መልካም ንባብ።

ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ማነው?

ተፈራ ማሞ የተወለደው በላስታ እውራጃ ቡግና ወረዳ ነው። ተፈራ የድሮውን ኢህዴን ያሁኑን ብአዴን የተቀላቀለው 1976 ዓ.ም ነበር። ትግሉን ሲቀላቀል እድሜው በግምት በአስራዎቹ መጨረሻ ነበር። በወቅቱ ለምልምል ታጋዬች የሚሰጠውን መሰረታዊ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና የወሰደው ምእራብ ትግራይና ሰሜን ጎንደር ( ወልቃይት) በሚዋሰኑበት ተከዜ ወንዝ ነበር። የሰለጠነበት ጊዜ ከሃምሌ 1976 እስከ ህዳር 1977 ባሉት ወራት ነበር።

ተፈራ የአርሶ አደር ልጅ ቢሆንም በስልጠናው ሂደት የነበረው ተሳትፎ እጅግ ንቁ ነበር። ፊደል ቆጥረናል ብለው ሙህራዊ ትምክህት ያስቸግራቸው የነበሩትን በብዙ መንገድ የሚያስከነዳ ነበር። ያን ግዜ ጊዜ 6ኛ ክፍል ያጠናቀቀም ሙህራዊ ትምክህት አለብኝ እያለ ግለሂስ ያደርግ ነበር።
ዘመኑ የደርግ ኢሰፓአኮ የገነነበት ስለነበር በእለቱ የስልጠና መግቢያና ማጠቃለያ ላይ ” ኢሰፓአኮ ቀዳዳ ባኮ፣ ትግላችን ረጅምና መራራ ነው ድል ማድረጋችን የማይቀር ነው”የሚሉ መፈክሮችን በማስተጋባት የሚቀድመው ማንም አልነበረም።

ስልጠናው እንደጠናቀቀ የተመደበው ወደ ተዋጊ ሰራዊቱ ስለነበር ከወልቃይት ተነስቶ ወደ ወሎ ግንባር (ዋግ) ተነቃነቀ። በ1977 በነበረው ድርቅና ርሃብ፣ በደርግ ሰራዊት ተደጋጋሚ ወረራ ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ትግሉን እየጣሉ ሲሄዱ አዲስ ታጋይነቱ ሳይበግረው በአላማው ጸንቶ ያን ክፉ ጊዜ አለፈ።
ትዝ ይለኛል ህዳር 1977 የተለያየን ታህሳስ 1980 ዓ.ም በለሳና ዋግን እያዋሰነ በሚያልፈው ተከዜ ወንዝ ላይ ዳግም ተገናኘን። በወቅቱ እሱ ተመድቦ ይሰራ የነበረው ኢህዴን ውስጥ በሁሉም መመዘኛ ምርጥ የሆኑ ታጋዮች መገኛ በነበረችው ኮማንዶ ሻምበል ውስጥ ነበር። በወቅቱ ሰራዊቱ ከየነበረበት የስምሪት ግንባሮች ተከዜና አሪ ወንዞች ወደ ሚገናኙበት ቦታ የተሰባሰበው ለወራት የተሰጠውን የፖለቲካ ስልጠና ለመውሰድ ነበር።

ስልጠናው እንደተጠናቀቀም ኮረምና ማይጨው የነበረውን የደርግ ሰራዊት ለማጥቃት ተንቀሳቅሰን ከህወሃት ሰራዊት ጋር በመሆን ሁለቱንም ከተሞች ከግማሽ ቀን ባነሰ ውጊያ ተቆጣጠርን። ጊዜው ግንቦት 1980 ነበር። ማይጨው መሽጎ የነበረውን የደርግ ሰራዊት ለመደምሰስ በተደረገው ዉጊያ ግን አንድ ቁልፍ ወታደራዊ መሬት ላይ መሽጎ የነበረውን የደርግ ሰራዊት አጥቅቶ ቦታውን መቆጣጠር ከባድ ፈተና ሆነ።

ይህን ቁልፍ ቦታ የመቆጣጠር ግዳጅ የተሰጠው ለህወሃት ሰራዊት ነበር። ነገር ግን የህወሃት ሰራዊት ቦታውን መቆጣጠር አልተቻለውም። አጁሃ በሎ እየተባለ ለስአታት ቢሞከርም ከመንደፋደፍ በቀር ምንም ዉጤት አልተገኘም። በዚህ ጊዜ ነበር እነ ተፈራ ማሞ ያሉባት የኢህዴን ኮማንዶ ሻምበል ግዳጁን ተቀብላ እንድታጠቃ የታዘዘችው።

ድሮም ጀምሮ በኢህዴንና በህወሃት ሰራዊቶች መካከል ሃይለኛ ፉክክር ነበርና ግዳጁን በደስታ ተቀብላ ማጥቃቱን ጀመረች። ለማመን በሚያስቸግር ጀግንነትና ፍጥነት በቦታው የነበረውን የደርግ ወታደር ጠራርጋ ቁልፍ ወታደራዊ ቦታውን ተቆጣጠረች። የህወሃት ሰራዊት በብዛት እንጅ በጀግንነት አይበልጠንም በሚል ውስጥ ውስጡን ይብላላ የነበረው ስሜት በተግባር ታየ ተብሎም ተነገረበት።
ተፈራ ማሞ ከተራ ተዋጊነት ጀምሮ ቲም አዛዥ፣ የመቶ አዛዥ፣ የሻምበል አዛዥ፣ የሬጅሜንት ምክትልና አዛዥ፣ የክፍለጦር ምክትል እያለ ቀጥሎ ደርግ ከመውደቁ በፊት የክፍለ ጦር አዛዥ መሆን ቻለ። በሁሉም የሃላፊነት ደረጃዎች የተሰጠውን ሃላፊነት በብቃትና በጀግንነት እየተወጣ የደርግ መንግስት ወደቀ።

በሽግግር መንግስቱ ዘመንም መጀመሪያ የቴዎድሮስ ክ/ጦር ቀጥሎም ኢህአፓን ለማጥፋት ከኢህዴንና ህወሃት ተዉጣጥቶ የተደራጀው ፓራ ኮማንዶ ክ/ጦር አዛዥ ሆኖ ይሰራ ነበር። ሃገር አቀፍ የመከላከያ ሰራዊት ታህሳስ 1987 ሲደራጅም የ21ኛ ክ/ጦር አዛዥ በመሆን ለአጭር ጊዜ ሰርቱዋል።

በወቅቱ መከላከያ በከፈተው አዳሪ ት/ቤት እየተማረ 9ኛ ደርሶ እያለ ነበር የኤርትራ ወረራ መርዶ የተሰማው። ሁሉም ነገር ወደ ሰሜን ግንባር ሲባል በንፋስ ፍጥነት ወደ ባድመ ግንባር ዘመተ። በወቅቱ ወገን የነበረው የክ/ጦር ብዛት ሰባት ብቻ ስለነበር አራት ተጨማሪ ክ/ጦሮች እንዲደራጁ ሲወሰን እሱም 33ኛ (አባይ) የተባለ ክ/ጦርን እንዲያደራጅ ግዳጅ ተሰጠው።
ጊዜው እናት አገር ልትወረን ቀርቶ ልታስበን በማተገባ ታሪክ የለሽ ኤርትራ የተደፈረችበት ነበርና ሌት ተቀን ለፍቶ በብቃት መዋጋት የሚችል ክ/ጦር በወራት ውስጥ አደረሰ። የማይተዋወቁ የበታች አመራሮችን፣ ተዋጊ ወታደሮችንና የስታፍ አካላትን አሰጣጥሞ አንደ አንድ ሰው ማሰብና መንቀሳቀስ እንዲችሉ ለማድረግ የሚታለፈው ፈተና እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም።
ምንም ይክበድ አገር ነውና አደራጅቶ፣ አግባብቶ፣ አዋህዶ፣ አሰልጥኖ፣ ገንብቶ፣ ሙሉ የውጊያ ቁመና ፈጥሮ በባድመ ግንባር በተደረገው የጽሃይ ግባት ዘመቻና በተከታታይ በተካሄዱ ወሳኝ ዉጊያዎች በሙሉ ክ/ጦሩን እያዋጋ የአዛዥነት ሃላፊነቱን በብቃት ተወጥቱዋል። የሚገርመው ነገር በዚህ ውጥረት ውስጥ ሆኖ ማንም ባላደረገው ሁኔታ ትምህርቱን በርቀት ይከታተል የነበረ መሆኑ ነው።
ከ1994 ጀምሮ ደግሞ የ108ኛ ኮር ምክትል ኣዛዥ፣ ከታህሳስ 1997 ጀምሮ የሰሜን ዕዝ ኦፕሬሽናል ምክትል አዛዥ፣ ከግንቦት 2000 ጀምሮም በመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ የእቅድ ዝግጅት መምሪያ ሃላፊ ሆኖ እስከታሰረበት እለት ድረስ ይሰራ ነበር።

በጥቅሉ ተፈራ ከታገለበት እለት ጀምሮ ለእስር እስኪዳረግ ድረስ ህይወቱ ከተዋጊነትና አዋጊነት ጋር የተያያዘ ነበር።
ወደ መከላከያ ስታፍ የተዛወረው የቅንጅት ፖለቲካ በፈጠረው ቀውስ የተነሳ በሰራዊቱ የማጥራት ግምግማ ሲካሄድ ቅንጅት ነህ ተብሎ ክፉኛ ተገምግሞ ስለነበር ለክትትል እንዲያመች ተብሎ ነው ወደ መከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ የተመደበው።

ተፈራ ከአቻዎቹም ሆነ ከአለቆቹ የሚለይበት አንዱ ነጥብ ትምህርት ወዳድ መሆኑ ነበር። ሁሌም አጀንዳው መማር መማር የሚል ነበር። ማንም ባላደረገው ሁኔታ በዚያ አስቸጋሪ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ምሽግ ውስጥ ሆኖ በርቀት ትምህርቱን ይከታተል የነበረውም ይህንን ጥማቱን ለመወጣት ነበር።

ጦርነት የሰውን ሞራል የሚፈትን፣ ነገን ሳይሆን ዛሬን ልኑርበት በሚል አስተሳሰብ የምትወረርበት፣ ለብዙ ጉዳቶችና በሽታዎች ዴንታ ቢስ የምትሆንበት በመሆኑ አቻዎቹና አለቆቹ በተገኘች ትርፍ ጊዜ ወደ ሽራሮና ሽሬ እየከነፉ ከወታደሩ ጋር እየተጋፉ ሲጫረቱ እሱ ግን መሃይምነትን ይዋጋ ነበር።

ሌላው ተፈራ በሁሉም ዘንድ የሚታወቅበት ስብእና ደግሞ ብሄርን መሰረት ያደረገ አድሎ ይቁም፣ የህወሃት የበላይነት መላ ይበጅለት፣ በመንግስት ስልጣኑም ሆነ በልማቱ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የለም ወዘተ እያለ የሚጠይቅና የሚከራከር የነበረ መሆኑ ነው። በዚህ እምነቱ የተነሳ ማንም እየተነሳ “ትምክህተኛ፣ የትምክህት ለም መሬት፣ ነፍጠኛ፣ ዘረኛ፣ ጸረ ትግሬ” ይለው ነበር።
እኔም በተሳተፍኩበት ሁለት ስብሰባዎች (በ1994 እና 1999) ትምክህተኛ፣ ዘረኛ፣ ሁሌም ራሱን የአማራ ወኪል አድርጎ የሚቆጥር ወገኛ፣ ጸረ ትግሬ፣ የትምክህት ለም መሬት፣ ትምክህት ያለበት ቦታ ሁሉ የማይታጣ፣ የቅንጅት ተስፈኛ ወዘተ ተብሎ የተገመገመበትን ሁኔታ በሚገባ አስታውሳለሁ።

እንዲያው በጥቅሉ ኦህዴድን ሲፍቁት ኦነግ ይሆናል ይባል እንደነበረው ሁሉ ተፈራን ሲነኩትም የአማራ ትምክህተኝነት ፈጦ ይወጣበታል ይባል ነበር።
በተለይ በቅንጅት ዘመን “ቅንጅት እንዴት የዕዝ አመራር መሆን ቻለ?” እያሉ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ይናገራሉ ተብሎ በከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ሲነቀፍ ስብሰባ ላይ ቁጭ ብየ የሰማሁበት ሁኔታ በመጪው ሰላማዊ ህይወቱ ላይ አደጋ እያንዣበበበት እንዳለ እኔ ብቻ ሳልሆን የተፈራ ወዳጆች ሁሉ ጥርጥሬ ነበር።

እውነቱን ለመናገር እንዲህ አይነት አመለካከት እያለውም ቢሆን ጀነራል ሳሞራ የኑስና የትግራይ ጀኔራሎች ተፈራ የመሰለውን ፊት ለፊት ስለሚነግረን እሱ ይሻለናል በዚበሂደት ስህተቱን ያርማል በማለት በተለይም በታችኞቹ የትግራይ ከፍተኛ መኮንኖች የሚነሳበትን ግፊት ሊከላከሉለት ይሞክሩ ነበር።

በእርግጥ የአርሶ አደር ልጅ ነው እያለ መደጋገሙ የትም አይደርስም ከሚል ስሌት ይሆን እንዴ እያልን እናወራ ነበር። ለዚያም ይመስላል ተጽእኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ የነበሩትን በተግባርም ያስቸግሩት የነበሩትን ሜ/ጀነራል ሃይሌ ጥላሁንና ብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌን በቅንጅትነት ወንጅሎ በጠረባ ሲዘርራቸው ተፈራ የገበሬ ልጅ ስለሆነ ሊያሻሽላል ይችላል ትንሽ እንየው በማለት ለጊዜው አቆዩት።
ከመታሰሩ ከወራት ቀደም ሲልም ለሜ/ጀነራልነት ማእረግ እንዲሾም ሃሳብ ቀርቦ የነበረ ሲሆን የመከላከያ አዛዦች ካውንስል አባላት የነበሩት ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰና ሜ/ጀነራል አለሙ አየለ የከረረ ተቃውሞ በማቅረባቸው ሳይሾም መቅረቱ ከታማኝ ምንጭ ተረጋግጦ ነበር። የሁለቱ ጀነራሎች የተቃውሞ ነጥብ የተለመደው ትምክህተኛ ነው የሚለውና በቅንጅትነትም የተገመገመ ነው በሚል ነበር።
እነዚህ ጀነራሎች የኢህዴን ታጋዮች የነበሩ ሲሆን የራሳቸው ሰው ላይ እየቆመሩ በአቀባባይ ከበርቴነት በማገልገል የስንቱን ህይወት አጨልመው እንጀራቸውን ይወጠወጡ እንደነበር ሁሉም ያውቃቸዋል። ለሁሉም ጊዜ አለውና እነዚህ ሁለት ጀኔራሎች በሃብት ተምነሽንሸው በመባረር ባይሆንም መስራት እየቻሉ ይብቃችሁ ተብለው ወደ ነጋዴነት ተሸጋግረዋል።

በጥቅሉ ብ/ጀነራል ተፈራ ከራስ በላይ ነፋስ የሚል አመለካከት ስላልነበረው እንጅ በግሉ የደረሰበት በደል አልነበረም። የተነሳበት አላማ ትክክል ይሁን አይሁን፣ የተከተለው የትግል ስልት አዋጭ ይሁን አይሁን ሌላ ጉዳይ ሆኖ ለግል ጥቅም ሳይሸነፍ ለመታገል መወሰኑ በራሱ ትልቅ ጀግንነት ነው ።

ብ/ጀነራል ተፈራ ሲበዛ ቅን፣ ሰው አክባሪ፣ ሁሉም በእኩል አይን እንዲታይ ትልቅ ምኞት የነበረው፣ በትልልቅ ዉጊያዎች አልፎ የተገነባ ጀግንነት፣ ስብእናና ታማኝነት ባለቤት ነበር። ተፈራ በሰራዊቱም የጦሩ ገበሬ እየተባለ ነበር የሚጠራው።

የታገልነው ለእኩልነት ስለሆነ እኩል እንታይ፣ የታገልነው ስርአታዊ አድሎን ለማስወገድ ስለሆነ አድሎ ይቁም፣ የታገልነው ሁሉም ዜጋ በህግ ፊት እኩል እንዲሆን ስለሆነ የህግ የበላይነት ይስፈን፣ የታገልነው ሁሉም ህዝብ እኩል እንዲለማ ስለሆነ ፍትሃዊ የመልማት እድል ለሁሉም እኩል ይረጋገጥ፣ በመንግስትም ሆነ በመከላከያ የሚታየው የአንድ ብሄር የበላይነት ይወገድ ስላልን ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ዘረኛ፣ ጸረ ትግሬ ማለት ልክ አይደለም ወዘተ ከማለት በቀር እንደተባለው ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ዘረኛና ጸረ ትግሬ አልነበረም።
ይቀጥላል።

ወያኔ እንዲህ እያሰበ መሆኑ ጭምጭምታ ተሰማ፤ ዕውነት ከሆነ ጥቅምና ጉዳቱ ምን ይሆን? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት!

ዛሬ ላለንበት ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ከመኖር ወደ አለመኖር ያደረሳቸውን ምክንያት መገንዘብ፣ ለምንፈልገው መፍትሔ ጥርጊያ መንገድ ይከፍትልናል። ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (የትግሬ-ወያኔ) የትግል ጉዞ እንደምንረዳው፣ ችግር በገጠመው ቁጥር፣ ዓላማውንና ቆሜለታለሁ የሚለውን ሥርዓት እንደ እባብ ገላ በሌላ በመተካት ጊዜ ይገዛል። ከማኦ ዜ ዱንግ እስከ ኤንቨር ሆጃ፣ ከካርል ማርክስ እስከ ሌኒን፣ ከሂትለር እስከ ደቡብ አፍሪቃ የአፓርታይድ አገዛዝ ያሉትን ርዕዮተ-ዓለሞች ካንዱ ወደ ሌላው ከብርሃን ፍጥነት በፈጠነ ሁኔታ በመቀያየር ኅልውናውን ለማራዘም ይሞክራል። የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት ያራመደው በዘር ጥላቻ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካና አገሪቱንና ሕዝቡን በነገድ ሸንሽኖ ያደረሰው ጥፋት፣ በተለይ ከ2007 እስከ 2009 ዓም ያሉት ዓመታት ሕዝቡ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ስለሆነበት፣ የአገዛዙን የአፈናና የእመቃ መዋቅር በመበጣጠስ በየአቅጣጫው ያስነሳው ተቃውሞ የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ ከሥሩ እያናጋው በመምጣቱ ምክንያት «አልሸሹም ዘወር አሉ» ዓይነት እና፣ «የጥልቅ ተሐድሶው» መገለጫ እንዲሆን የታሰበ የመንግሥት የአደረጃጀት ለውጥ ለማድረግ የታሰበና ወደዚህም ግብ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ በመሰማት ላይ ነው።

በግልጽ እንደሚታወቀው፣ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ሰንቆት ለተጓዘበት ዓላማ ማስፈጸሚያ አድርጎ የተጠቀመው  የመንግሥቱን አደረጃጀት በቋንቋ ልዩነት ላይ የተመሠረተ አፋዊ ፌደራላዊ  አደረጃጀት መከተሉ ነው። በቋንቋ ልዩነት ላይ የተመሠረቱት እነዚህ «የፌደራል መንግሥት አካላት ናችሁ» የተባሉትም በፈለጉትና ባሻቸው ወቅት «መገንጠል እንፈልጋለን» ብለው ባሰቡ ጊዜ መገንጠል እንዲችሉ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 39(1) የመገንጠል መብታቸው የተከበረ እንዲሆን ተደንግጓል። በዚህ ሕገ-መንግሥት የፌደራል መንግሥቱ መቀመጫ የሆነ በራሱ የፌደራል መንግሥቱ  ቁጥጥር ሥር የሆነ መዲና የሌለው መሆኑም ይታወቃል። ይህም በመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ የመስፋፋትና የልዩ ልዩ የግንባታ ሥራዎች «በኦሮሚያ መንግሥት ሙሉ ፈቃድ» ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በማድረጉ፣ ለከተማዋ ዕድገት እንቅፋት ከመሆን አልፎ፣ በኦሮሞ ብሔርተኞችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ደም ያፋሰሰ ክስተት መስተናገዱ ይታወሳል። ችግሩም  ዛሬም እልባት ያላገኘ መሆኑ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የትግሬ-ወያኔ «ኦሮሚያ» ብሎ በከለለው አካባቢ የተቀሰቀሰው የሕዝብ እንቢተኝነት ለበርካታ ሰው ሕይዎት ማለፍና በብዙ ሚሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት ውድመት መንስዔ መሆኑ አይዘነጋም። በደብረዘይት ከተማ «የእሬቻ» በዓል አከባበር ላይ በግፍ ሆን ተብሎ በተዘጋጀ ሤራ ያለቀውን ሕዝብ ማስታወሱ ብቻ ለዚህ አባባል ከበቂ በላይ ማሳያ ነው።

በኦሮሞ ብሔርተኞች የተቀነቀነውና ለአንድ ዓመት ያህል የዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ የትግሬ-ወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር በመበጣጠስ በአገዛዙ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ በማየሉ፣ አገዛዙ አቅዶት የነበረውን የአዲስ አበባን የማስፋፋት ዕቅድ ለጊዜውም ቢሆን እንዲያቆም ከመገደዱም በላይ፣ በኦሕዴድ የዘመናት አገልጋዮቹ ላይ የመረረ እርምጃ እንዲወስድ አድርጎታል። በሌላ በኩል ለ42 ዓመታት ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የቀሰቀሰው ሕዝባዊ ማዕበል፣ የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ ከምንጊዜውም በላይ ጥያቄ ውስጥ ያስገባው በመሆኑ፣ አገዛዙ ሕገመንግሥቱን አግዶ የአስቸኳይ ወታደራዊ አዋጅ አውጆ፣ አገሪቱን በወታደራዊ አገዛዝ ሥር አድርጎ፣ «ጠላቴ ነው» ያለውን ሁሉ እንደፈለገ በጠራራ ፀሐይ በማሰርና በመግደል በሕዝቡ ላይ የመከራና የስቃይ ናዳ እያወረደበት ይገኛል። ይኽም ሆኖ፣ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እየበረታ እንጂ፣ እየላላ ባለመሄዱ፣ የትግሬ-ወያኔ ለጊዜውም ቢሆን ጊዜ መግዣ ይሆነኛል ብሎ ያሰበውና ለ25 ዓመታት አጥልቆት የነበረውን «የማንነቴ መገለጫ ነው» ያለውን የቋንቋ ፌደራሊዝም አውልቆ በክፍለ-ሀገራት ማንነት ላይ የተመሠረት ፌደራላዊ አስተዳደር ለመመሥረት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ።

እንደመረጃዎቹ አባባል ከሆነ፣ ወያኔ ከገጠመው አጣብቂኝ መውጫ ይሆነኛል ብሎ ያሰበው፣ በዘጠኝ ክልላዊ መንግሥታትና በሁለት የከተሞች አስተዳደር ያዋቀረውን የቋንቋ ፌደራሊዝም ሽሮ፣ በ39 ክፍለ-ሀገሮች የተዋቀረ ፌደራዊ መንግሥት የመተካት ዕቅድ እንዳለው ያመለክታል። በመረጃዎቹ መሠረት ወያኔ ለ26 ዓመታት የድሉ ቁንጮ አድርጎ ይመለከተው የነበረውን የቋንቋ ፌደራሊዝም አፍርሶ፣ «ከእሾህ ወደ ጋሬጣ» ዓይነት የሆነ፣ መነሻውን ቋንቋ ያደረገ፣ ነገር ግን፣ ትግራይ ሲቀር በስተቀር ቀደም ሲል በክልላዊ መንግሥትነት አካቷቸው የነበሩትን ወረዳዎችና አውራጃዎች በሠፈሩባቸው ነገዶች ስም የክፍለ-ሀገር ደረጃ በመስጠት፣ ለበለጠ የርስ በርስ ግጭትና ብጥብጥ፣ አገሪቱንና ሕዝቡን ሊያቋርጥ ወደማይችል ትርምስ ሊከት የሚችል ሁኔታን የሚፈጥር አደረጃጀት የተከተለ እንደሆነ «ክፍለ-ሀገራት» ብሎ የሰየማቸው አካባቢዎች ሁኔታ ያሳያሉ። የትግሬ-ወያኔ ለተነሳበት ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ ማብረጃና ለሥልጣን ዕድሜዬ መራዘሚያ ይሆነኛል ብሎ የፈጠራቸው አዲሶች ጠቅላይ ግዛቶች የሚከተሉት ናቸው።

 

ተራ ቁጥር

ከፍለ-ሀገራት

ተራ ቁጥር

ክፍለ-ሀገራት

1

ትግራይ ክፍለ-ሀገር

21

ኢሉባቡር ክፍለ-ሀገር

2

አፋር ክፍለ-ሀገር

22

ሶማሊ ክፍለ-ሀገር

3

ወልቃይት-ጠገዴ-ሑመራ ክፍለ-ሀገር

23

ጋምቤላ ክፍለ-ሀገር

4

ቤጌምድር ክፍለ-ሀገር

24

ቤንሻጉል-ጉምዝ ክፍለ-ሀገር

5

ጭልጋ-መተማ ክፍለ-ሀገር

25

ቤንቺ ማጂ ክፍለ-ሀገር

6

አገው-አዊ ክፍለ-ሀገር

26

ሸካ ክፍለ-ሀገር

7

ጎጃም ክፍለ-ሀገር

27

ከፋ ክፍለ-ሀገር

8

ባሕርዳር ዙሪያ ክፍለ-ሀገር

28

ደዋሮ ክፍለ-ሀገር

9

ባቲ-ሰንበት ክፍለ-ሀገር

29

ኦሞቲክ ክፍለ-ሀገር

10

ወሎ ክፍለ-ሀገር

30

ጋሞጎፋ ክፍለ-ሀገር

11

ሸዋ ዐማራ ክፍለ-ሀገር

31

ኮንሶ ክፍለ-ሀገር

12

ቦረና ክፍለ-ሀገር

32

ሲዳማ ክፍለ-ሀገር

13

አርሲ ክፍለ-ሀገር

33

ጌድዎ ክፍለ-ሀገር

14

ባሌ ክፍለ-ሀገር

34

ጉራጌ ክፍለ-ሀገር

15

ሐረርጌ ክፍለ-ሀገር

35

ስልጢ ክፍለ-ሀገር

16

አዲስ አበባ ዙሪያ ክፍለ-ሀገር

36

ሐዲያ ክፍለ-ሀገር

17

ጉጂ ክፍለ-ሀገር

37

አላባ-ከምባታ-ጠምባሮ ክፍለ-ሀገር

18

ወለጋ ክፍለ-ሀገር

38

ወላይታ ክፍለ-ሀገር

19

ሸዋ ክፍለ-ሀገር

39

ቡርጂ-ዲራሸ-አማሮ ክፍለ-ሀገር

20

ጅማ ክፍለ-ሀገር

 

 

 

ከሰንጠረዡ መገንዘብ እንደምንችለው ክፍለ-ሀገራዊ ክፍፍሉ የተሠመረው ሦስት ነገሮችን መሠረት በማድረግ ነው። እነዚህም ቋንቋ፣ የጥንቱ ክፍለ-ሀገሮች፣ አውራጃና ወረዳዎችን መሠረት ያደረጉ ሆነው እናገኛቸዋለን። አሥራ ስምንቱ(18) ቋንቋን መሠረት አድርገዋል። አሥራ አንዱ(11) የቆዳ ስፋታቸው የጥንቱን ክፍለ-ሀገሮች አያካት እንጂ፣ በስም ደረጃ የጥንቱን ስማቸውን እንዲይዙ ተደርጓል። አሥሩ(10) የጥንቶቹን አውራጃና ወረዳ ስሞች እንዲይዙ ሆነዋል። ይህ አስተዳደራዊ መዋቅር እና አደረጃጀት በዚህ መልክ እንዲሆን አስፈላጊ ያደረጉት ከትግሬ-ወያኔ ዓላማ አኳያ የሚከተሉት እንደሆኑ መገመት ይቻላል።

 

 

 1. የአደረጃጀት ለውጡን አስፈላጊ ያደረገው መሠረታዊ ምክንያት በመላ አገሪቱ ከሁሉም በላይ በጎንደርና በጎጃም ክፍለ-ሀገሮች፣ እንዲሁም የትግሬ-ወያኔ «ኦሮሚያ» ብሎ በከለላቸው ክፍለ-ሀገሮችና አውራጃዎች በተከታታይ የዘለቀው ሕዝባዊ እንቢተኝነት የትግሬ-ወያኔን መንግሥታዊ መዋቅር ሽባ በማድረጉና በትግሬ-ወያኔ ኅልውና ላይ ከፍተኛ አደጋ የጋረጠ ስለሆነ፣ የሕዝባዊ እንቅስቃሴውን አቅጣጫ ለማሳት፣ የተቃዋሚ ቡድኖችን የትኩረት አቅጣጫ ለማዛባት፣ በዚህም ወያኔ እንደ እባብ አፈር ልሶ ራሱን መልሶ የሚያጠናክርበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው።
 2. በቋንቋ መነሻነት የተካለሉት አሁን የሚታወቁት ክልሎች በሕዝብ ብዛት እና በተለያዩ በተፈጥሮ ሀብቶች ከትግራይ ስለሚበልጡ፣ በሕዝብ ተወካዮች እና በ«ብሔር/ብሔረሰቦች» ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ወያኔ እንደ እስከ ዛሬው የፈለገውን የማስወሰንና ያሻውን ሁሉ የራሱ የማድረግ አቅሙ ጥያቄ ውስጥ የከተተው በመሆኑ፣ ያን ለማዛባትና በሁለመናቸው ከትግራይ ያነሱና የኮሰመኑ አዳዲስ ማንነቶችን ለሌሎች አላብሶ፣ የትግራይ የበላይነት በሁለመናው መልኩ እንዲቀጥል ለማስቻል ነው። ከዚህ ላይ ሊስተዋል የሚገባው ባለፉት 26 ዓመታት «ትግራይ» ተብሎ ከተከለለው ክልል የተቀነሱት ከጎንደር ክፍለ-ሀገር የነጠቃቸው አራት ወረዳዎች ብቻ ናቸው። ይህም በአዲስ መልክ ከተደራጁት 39 ክፍለሀገሮች ጋር ሲነፃጸር ትግራይ በቆዳ ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት ከሁሉም የበላይነቱን እንድትይዝ ያደርጋል። በየትኛውም መልኩ፣ በዚህ የክፍለ-ሀገሮች ፌደሬሽን ውስጥ 5 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ከትግራይ ሌላ ሊኖር አይችልም። ይህም በሕዝብ ተወካዮችና በ«ብሔር/ብሔረሰቦች» ምክር ቤቶች ውክልና ከፍተኛ ቁጥር የሚኖረው የትግሬ ሕዝብ ነው። በዚያው መጠን የአገሪቱ በጄት ከፍተኛ መጠን ያለው የሚመደበው ለትግራይ  ይሆናል። ይህም በሁለተናዊ መልኩ የትግሬ-ወያኔ ትውልድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሕይዎት ውስጥ እንደ እስካሁኑ የበላይነቱን ይዞ እንዲቀጥል ያደርገዋል።
 3. ሌላውና ለዚህ ዓይነቱ ጥቃቅን መንግሥታት መፍጠርና በክፍለ-ሀገራት ላይ ለተመሠረተ ፌደሬሽን መመሥረት የትግሬ-ወያኔን ያስገደደው ምክንያት፣ «ኦሮሚያ» ብሎ የከለለው አካባቢ ተወላጅ የሆኑ ብሔርተኞች፣ «እንደ ቁጥራችንና ብዛታችን የመንግሥትና የሕዝብ የሥራ ቋንቋ ኦሮሚኛ ይሁን፤ ወሣኝ የሆኑት የመንግሥት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሥልጣን በኦሮሞዎች ይያዙ፤ ይህ ካልሆነ ግን፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 39 በተሰጠው የመገንጠል መብት መሠረት እንገነጠላለን» በማለት የጀመሩት የመገንጠል እንቅስቃሴ እያየለ በመምጣቱ፣ ይህን «የሕዝብ ቁጥርና የተፈጥሮ ሀብት የበላይነት ያለን እኛ ነን» በማለት፣ በኦሮሞ ብሔርተኞች የተፈጠረውን የትምክህተኝነትና የጠባብነት እብጠት ለማስተንፈስ የታቀደ ይመስላል።ከአዲሱ የክፍለ-ሀገሮች ክፍፍል ለመገንዘብ እንደሚቻለው፣ በትግሬ-ወያኔ ላይ የጠነከረ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ያሉትን «የኦሮሚያና የዐማራ ክልሎችን» አፍርሶ፣ በፍጥነት እየጎለበተ የመጣውን ኦሮሟዊ እና ዐማራዊ ማንነትን ለማጥፋት አልሞ የተነሳ እንደሆነ ያስረዳል። ክፍፍሉ ከመሠረቱ ሦስቱን ክልላዊ መንግሥታትን፣ ማለትም፦ «ኦሮሚያን፣ ዐማራንና ደቡብን» እንዳልነበሩ አድርጎ ያጠፋል። በአንድ ክልላዊ መንግሥት ተዋቅረው የነበሩት ዐማራ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ በተከታታይ ለዘጠኝ፣ ለአሥርና ለአሥራ ሦስት ተሸንሽነዋል። የቆዳ ስፋታቸውና ያካተቱት የሕዝብ ብዛት በነበረ መልኩ ሊሆን እንደሚችል ቢታሰብም፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ሶማሊ እና ቤንሻንጉል-ጉምዝ የነበራቸውን ስም ይዘው እንዲቀጥሉ ተደርጓል። ሐረሪ እንደ ጥንት ጧቱ በሐረር ክፍለ-ሀገር የተካተተ ይመስላል፤ በአዲሱ የክፍለ-ሀገር አደረጃጀት ራሱን ችሎ አልተጠቀሰምና።ማንም ሊገነዘበው እንደሚችል፣ የትግሬ-ወያኔም ሆነ፣ የኦሮሞ ብሔርተኞች፣ በተለይም ኦነግ፣ ሳያስቡት የማዕከላዊ መንግሥትና የአንድነት ኃይሉ ባልጠበቁት ወቅትና ፍጥነት ከሥልጣን መወገድ በፈጠረላቸው ድንገተኛ የሲቃና ደስታ ስሜት ተውጠው፣ ሁለቱም ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ ቡድኖች፣ የኋላውን ወይም መጭው ምን ሊሆን እንደሚችል ሳያንሰላስሉ፣ አገሪቱን ከነባር የአደረጃጀትና የግንኙነት ባህል አውጥተው፣ በቋንቋ ልዩነት ላይ የተመሠረተ የፌደራል አደረጃጀት እንድትከተል አደረጉ። ለዚህም የኦሮሞ ብሔርተኞች ዮሐን ክራፍ የተባለው የጀርመን ሚሽነሪና ሰላይ፣ መካከለኛውን አፍሪካ የጀርመን ቅኝ ግዛት ለማደረግ በተሰጠው ተልዕኮው መሠረት፣ ተልዕኮው መሳካት የሚችለው «በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩትን ጋሎች (ኦሮሞች) አንድ የጋራ መታወቂያ ክልል ሰጥቶ፣ መግባቢያ ቋንቋቸውም አንድ ዓይነት እንዲሆን ማደርግ ነው» ሲል ድምዳሜ ላይ ደረሰ።

   

  ለዚህ ድምዳሜውም፣ ኦሮሞዎች ሊኖሩበት የሚገባውን ክልል «ኦርማኒያ» ሲል፣ ቋንቋቸውን «አፈ ኦሮማ» እንዲባል ለጀርመን መንግሥት ሀሳብ ማቅረቡ ይታወሳል። ይህን እንግዲህ በ18ኛው ክፍለ-ዘመን  አጋማሽ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኦሮሞ ብሔርተኞች  የዐማራውን ነገድ እንደ ቅኝ ገዥ፣ ምኒልክን እንደ ጥቁር ናዚ በመሳል የራሳቸው የሆነና «ኦሮሚያ» የሚባል ግዛት ከኢትዮጵያ በመገንጠል ለመመሥረት ሲንቀሳቀሱ መኖራቸው ይታወቃል።

  በመሆኑም ሁለቱ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች ትናንትን ከዛሬ፣ ዛሬን ከነገ ጋር አጣጥመው ሳያዩ፣ በድንገተኛ ድል ተሳክረው፣ ኦሮሞዎቹ በየትኛውም ጊዜ ዕውን ይሆናል ብለው ያላሰቡትና ከሰማይ እንደወረደ መና የሚቆጥሩት መልካም አጋጣሚ ተፈጠረላቸው።

  የትግሬ-ወያኔም ትግራይን ለመገንጠል መሬት ነክሶና ቆንጥጦ የተዋጋ ቢሆንም፤ እንዲዚያ ባለ ፍጥነት የመላው ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሥልጣን ባለቤት እሆናለሁ ብሎ ባልጠረጠረው መንገድ ሥልጣን ከመሀል መዳፉ ገባለት። ለሥልጣኑ መደላደልና ባጭር ጊዜ ውስጥ ዕውቅና ለማግኘት ሲል፣ ኦነግ የጠየቀውን፣ በራሱ ሰው በሌንጮ ለታ በተረቀቀ የሽግግር መንግሥት ቻርተር፣ የራሱ «ኦሮሚያ» የተባለ ክልል የአገሪቱ ሁለንተናዊ ሀብት ጎተራ የሆኑትን ክፍለ-ሀገሮች ጠቅሎ በመስጠት፣ ኦሮሚኛን የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ፈቀደለት። ይህንንም ድላቸውን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ለተያያዙት የዘመናት ትግል የዓላማቸው መዳረሻ አድርገው ቆጠሩት። ሁለቱ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች ኢትዮጵያን የማጥፋት የዓላማቸው ብቸኛ ማረጋገጫ መስፈሪያቸው የዐማራው መጥፋት እንደሆነ በማመን፣ በዐማራው ላይ ሰብአዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶቹና ጥቅሞቹን ከመንጠቅና ከመግፈፍ አልፈው የእርዳ ተራዳ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሰላባ አደረጉት። በዚህም ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፋ አደረጉ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ ሀብት ንበረታቸውን ተነጥቀው ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ እንዲባረሩ ተደረጉ።

  ሆኖም ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ ስለማይጣላ፣ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ዐማራን ለማጥፋት ይበጀናል ባሉት መንገድ ሽርክና የፈጠሩት ቡድኖች፣ የኢትዮጵያን ሀብት በመካፈሉና ወሣኝ የሥልጣን ቦታዎችን በመያዝ ረገድ የአንበሣውን ድርሻ ለእኔ፣ ለእኔ በማለት ወደ ጦርነት ገቡ። ኦነግም ሳያስበው ጨብጦት ከነበረው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ዕምብርት ውስጥ በወያኔ ተግፍትሮ እንዲለቅ ተገደደ። ይህም መላው የኦሮሞ ብሔርተኞች «የያዝነውን አጣን»፣ በሚል ስሜት በዮሐን ክራፍ የተነደፈላቸውን «ኦሮሚያ» የሚባል አገርና «ኦሮሚኛ» የሚል የጋራ ቋንቋቸውን የትግሬ-ወያኔ የፈቀደላቸው በመሆኑ፣ የትግሬ-ወያኔን የኦሮሞ ሕዝብ ባለውለታ እንደሆነ በመቁጠር በጠላትነት የሚመለከቱት አልሆኑም። በመሆኑም በሺህዎች የሚቆጠሩትን የኦሮሞ ልጆች ገድሎና አስሮ ሲያሰቃይ፣ የሚያወግዙት ዐማራውን እንጂ፣ የትግሬ-ወያኔን አይደለም። ይኸም ሆኖ፣ «ብልጥ ልጅ የሰጡትን ይዞ ያለቅሳል» እነደሚሉት፣ የኦሮሞ ብሔርተኞች የያዙትን ይዘው ከማልቀስ ወጥተው፣ «ኦሮሚያን» ለመገንጠል በመንቀሳቀሳቸውና ይህም የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ ሁለንተናዊ አቅም እያዳከመው በመምጣቱ፣ ይህን በሕዝብ ቁጥር እና በተፈጥሮ ሀብት የበላይነት ስሜት «የሰከረውን» የኦሮሞ አክራሪ ብሔርተኛ ቡድን ፍላጎት ለማስተንፈስ ትናንት ያለዕውቀት፣ ያለማስተዋል፣ «የናንተ ነው» ብለው የሰጧቸውን «ኦሮሚያ» የተባለውን ክልል መንጠቅና «ኦሮሚያ» የተባለ አገር እንመሠርታለን የሚለውን የኦሮሞ ብሔርተኞች ፍላጎት ወደ ቀን ቅዠትነት ለመለወጥና ለትግሬ-ወያኔ ዕድሜውን ለማራዘም የሚያስችል የኃይል አሰላለፍ ለውጥ ለማድረግና የተወሰነውን አንድነት ኃይል በመክፈል ድጋፍ ሊያስገኝልን ይችላል ብሎ የትግሬ-ወያኔ ያዘጋጀው የሌላ ዙር ማታለያ ይመስላል።

  በሌላ በኩል እየተጠናከረ የመጣውን የዐማራ የኅልውና ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ በአውራጃ፣ በወረዳና በክፍለ-ሀገር ዐማራውን ከፋፍሎ ለማዳከምና የትግሬ-ወያኔን የአገዛዝ ዘመን ለማራዘም እንደሆነ መጠራጠር አይቻልም። ምክንያቱም ዐማራው ለክፍለ ሀገር፣ አውራጃና ወረዳ ማንነቱ የጎላ ቦታ ስለሚሰጥ፣ በዚህ ስስ ስሜቱ በመግባት፣ ከዐማራዊ የኅልውና ጥያቄው ለማፋታት እንደሆነ ይታመናል። በዚህም የተነሳ «የዐማራ ክልል» ብሎ ከልሎት የነበረውን አካባቢ በዘጠኝ ክፍለ-ሀገሮች ሸንሽኖታል።

   

   

   

  ይህ በ39 ክፍለ-ሀገሮች ላይ የተመሠረተ ፌደደራላዊ የመንግሥት አደረጃጀት እንደታሰበው በሥራ ላይ ከዋለ የሚከተሉት ጥቅሞችና ጉዳቶች ይኖረዋል።

  ጥቅሞች፦

   1)    በተፈጥሮ ሀብትና ሆን ተብሎ በተዛባ የሕዝብ ቆጠራ «በሕዝብ ቁጥር የበላይ ነን» በማለት፣ «ሁሉም ለእኛ ይሁን»፣ «ምኒልክ ጥቁር ናዚ ነው» በማለት ዐማራን ለማጥፋት ከትግሬ-ወያኔ ጋር የተባበሩትን የኦሮሞ ብሔርተኞች እብጠት በእጅጉ ያስተነፍሳል። «ኦሮሚያ» የሚለው ዮሓን ክራፍ ወለድ የግዛት ስም ያከትማል። የተስፋየ ገብረአብ «የቡርቃ ዝምታ» የወለደው የአኖሌ ሀውልት እንዲፈርስ በር ይከፍታል።

  2)     አማርኛ ቋንቋን ከመንግሥትና ከሕዝብ የሥራ ቋንቋነት ለማስጥፋት የሚደረገውን ሤራ ያከሽፋል። አማርኛ ከሞላ ጎደል የሁሉም ክፍለ-ሀገራዊ መንግሥታት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ተጽዕኖ ያሳድራል።

  3)     የየነገድና የጎሣቸው አለቃ/መሪ ለመሆን ለሚጓጉ የወያኔ ጀሌዎች ወደፊት ወንበር እንዲመጡ ሠፊ በር ይከፍታል። የመንግሥት መሪዎች ነን የሚሉት ከ9 ወደ 39 ያሳድጋልና!

   

  ጉዳቶች፦

   1)    በሁሉም ዘርፍ የትግሬ-ወያኔን የበላይነት ያጠናክራል። ይህም የትግሬ-ወያኔ «ለመቶ ዓመታት በተከታታይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ቁንጮ ላይ እኖራለሁ» ሲል ያቀደውን ሤራ ተግባራዊ ለማድረግ ይጠቅመዋል። ውጤቱም የኢትዮጵያዊነት የጋራ ዕሴቶች ተሟጠው እንዲጠፉ ሠፊ ዕድል ይሰጣል።

  2)     እስካሁን በሥልጣን ሽኩቻው ያልገቡ የሕዳጣን ነገዶች ልሂቃንን ወደ ሽኩቻው እንዲገቡ በር ይከፍታል። ይህም የእርስ በርስ ጦርነቱና ንትርኩ የበለጠ ነዳጅ እንዲያገኝ የሚረዳ በመሆኑ፣ አዲሶቹ ክፍለ-ሀገራዊ ክፍፍሎች በድንበር፣ በነገድ፣ በበጄት ድልድል፣ በልማት ቅደም ተከተል ወዘተርፈ በመሳሰሉት እርስ በራሳቸው በመናቆር የትግሬ-ወያኔ ገላጋይ መስሎ በመግባት ንትርኩን በማባባስ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ጫና በማብዛት «የትግሬ-ወያኔ የተሻለ ነው» እንዲባልና አገዛዙን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዕድል ይሰጠዋል።

  3)     የኢትዮጵያዊነት መገለጫና መታወቂያ የሆኑትን አስተዳደራዊ ክፍፍሎች በማዛባት የሕዝቡን የነበረ ማንነቱን ያሳጣል።

  4)     ክፍፍሉ «የኦሮሚያ» የተሰኘ አገር እንመሠርታለን ብለው ሌት ተቀን የሚጥሩትን የኦሮሞ ብሔርተኞች የዘመናት ሕልም የሚያጨልም በመሆኑ ተቃውሞአቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያደርጋል። ይህም የሰላምና መረጋጋት ጠንቅ ይሆናል።

  5)     «በደቡብ ብሔር/ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል» ተካተው የነበሩትንና አንድ ዓይነት ማንነት ለመፍጠር ይጥሩ የነበሩትን ነገዶችና ጎሣዎች ሁኔታ በመቀየር፣ በትናንሽ ማንነቶች ስለሚተካ፣ የወደፊት እጣ ፋንታቸው ወደማያቋርጥ ክፍፍልና ብጥብጥ የሚመራቸው በመሆኑ፣ ኑሮአቸው የጎሰቆለ እንዲሆን ያደርጋል። በዚህ ክልል ተጠቃለው የነበሩት እንደ ወላይታ፣ ሃዲያ፣ ከምባታ፣ ጉራጌ፣ ወዘተርፈ ዓይነት ነገዶችና ጎሳዎች ከፍተኛ የመሬት ጥበት ያለባቸው በመሆኑ፣ የእነርሱን ተዘዋውሮ የመሥራት መብት በእጅጉ በማጥበብ ለከፋ ድህነት ይዳርጋቸዋል።

  6)     አዲሶቹ ክፍለ-ሀገሮች አዲስ ማንነት ያጠለቁ ስለሆኑ፣ የየአካባቢዎቹ ልሂቃን ማንነታቸውን ለማስረገጥና በሕዝቡ ዘንድ ለማስረጽ የሚደረገው ሠፊ ጥረት የሕዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ከትግሬ-ወያኔ ላይ እንዲነሳ በማድረግ፣ የትግሬ-ወያኔ አገርና ትውልድ የማጥፋት ዓላማው ያላንዳች ሀግ ባይ እንዲቀጥል ሠፊ በር ይከፍትለታል።

  በጥቅሉ የታሰበው የ39 ክፍለሀገራዊ ፌደሬሽን በሥራ ላይ ከዋለ እነዚህና መሰል ሁኔታዎች ሊከተሉ እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል። ይህ ያንድ በኩል ዕይታ ነው። ሁሉም በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ወገን ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚታየውንና የሚሰማውን ለሕዝብ ዓይንና ጀሮ ቢያደርስ አንድ የተጨበጠ ቁምነገር ላይ መድረስ ስለሚቻል ሕዝቡን በአንድ አቅጣጫ ለማሰለፍ ይረዳልና ያለንን አስተያየት እንወርውር

  ኢትዮጵያ በጀግኖች እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች! 

  ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

  ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

  ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት!

እግዚአብሔር ማልቀስ ሲያምረው ጎጃሜን ይገላል፤ መሳቅ ሲያምረው ደግሞ ትግሬን ያጠግባል! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እኔ የምለው! አባባሎቻችንን ወይም ሥነቃሎቻችንን ማን ነው ግን የሚፈጥራቸው? በጣም እኮ የሚገርም ነገር ነው፡፡ አንድ እኮ አይስቱም!

ለምሳሌ፦ በርእስ የጠቀስኩትን እንይ “እግዚአብሔር ማልቀስ ሲያምረው ጎጃሜን ይገላል፤ መሳቅ ሲያምረው ደግሞ ትግሬን ያጠግባል!” ይባላል፡፡ አሁን እግዚአብሔር የሚስቅና የሚያለቅስ ሆኖ አይደለም እንዲህ መባሉ፡፡ ነገር ግን ጎጃሞች ሐዘናቸው መረር ስለሚል፣ ለቅሷቸው አንጀት ስለሚበላና ሙሾ ባወረዱ ጊዜ “እንባ ደረቅ፣ አረመኔ!” የተባለን ሰው እንኳ ሳይቀር በለቅሶ የሚያንፈቀፍቁ በመሆኑ፤ ትግሬ ሲጠግብ ደግሞ የሚሠሩትን ከማጣታቸው የተነሣ በጣም የሚገርም፣ ሆድ አስይዞ በሳቅ የሚያንፈረፍርና ፈጽሞ የማይጠበቅ ነገር ማድረጋቸውን በአጽንኦት ለመግለጥ ነው እንዲያ መባሉ፡፡

ይህች ጥጋብ የምትባል ነገር የስንት ነገር መለኪያ መሣሪያ ናት መሰለቻቹህ! አንድ ሕዝብ ወይም ኅብረተሰብ በሳል፣ አስተዋይ፣ ብልህ፣ አዋቂ፣ የተረጋጋ ሰብእና የያዘ፣ ጨዋ፣ ባለ አእምሮ፣ በራስ መተማመን ያለው ነው የሚያሰኘው ጥጋብን የቻለ፣ ጥጋብ እሚሠራውን የማያሳጣው እንደሆነ ነው፡፡ እንዲህ የሆነ ኅብረተሰብ በጣም የበሰለ፣ ክብርና ኩራት ያለው፣ የጠለቀ ወይም ስር የያዘ በሳል የሕይዎት ምልከታ ፍልስፍና እምነትና ሥልጣኔ ያለው፣ ከፍ ያለ የሞራል (የቅስም) ልዕልና ያለው፣ ከሕይወት ተሞክሮው ብዙ የተማረ ጥንታዊ ማኅበረሰብ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

በእርግጥ ከዚህ ቀደም ከላይ የጠቀስኩላቹህን አባባል ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ በርካታ ነገሮች ያጋጠሙኝ ቢሆንም በቀደም ቅዳሜ ምሽት (የካቲት 11,2009ዓ.ም.) ታዲያስ አዲስ በተባለ የሸገር ራዲዮ (ነጋሪተወግ) የመዝናኛ ዝግጅት ላይ የሰማሁትም ቀላል አላስገረመኝም፡፡ አንዱ ነው አሉ (ስሜ አይጠቀስ ብሏል ተብሎ ስሙ አልተጠቀሰም) አዲስ ከወጣው የኤደን ገ/ሥላሴ የዘፈን አልበም (ጥራዝ) ውስጥ “አንደኛው ዘፈን ከሕይዎቴ ጋር ስለተገናኘ አስደሰተኝ!” ብሎ በዚህች ዘፈን የተነሣ አንዷን የዘፈን አልበም (ጥራዝ) በ50ሽህ ብር እንደገዛ “የምሽቱ የመዝናኛ ዜና!” ብለው አወሩልን፡፡

አይገርምም? አይደንቅም? በዚህ ሀገሪቱ ስንት ሚሊዮን (አእላፋት) ዜጎች ተርበው ስቃይ ላይ ባሉበት ወቅት!፣ በኑሮ ውድነት የተነሣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በችጋር እየተጠበሰ ኑሮ እንደ እሬት ምርርርርር ባለው ሰዓት! እንዴት ያለ ጥጋብ ቢሆን ነው እንዲህ ዓይነት ነገር የሚያስፈጽም?

ደሞ ምንአለ ጥጋባቸውን ሳናይ ሳንሰማባቸው እዛው በየቤታቸው ቢያስቀሩት? የንቀታቸው ንቀት ዓይተንና ሰምተን እንድንቃጠል እንድንጨስ የጥጋብ ድርጊታቸውን በአደባባይ ያደርጉታል! ለነገሩ የጥጋብ አንዱ መገለጫው ይሄ አይደል? ቦታና ሰዓት ሳያስለይ ማጨማለቅ! የመረጃ ጉዳይ ይሆናል እንጅ እርግጠኛ ነኝ ከዚህ የከበደ ብዙ ለማመን የሚያዳግት “ጉድ!” የሚያሰኝ ነገር የምታውቁ በርካቶች ትኖራላቹህ፡፡ ከኛ ሰፈርም አንድ ትግሬ አለ ልጁን በርቀት መቆጣጠሪያ (ሪሞት ኮንትሮል) በምትሽከረከር የአሻንጉሊት መኪና (ተሽከርካሪ) አስቀምጦ ሰፊ ግቢው አልበቃ ብሎት ከግቢ ውጭ እየተወነነ ሲያንሸራሽረው የማየው፡፡ ከዚህ ሰው ቤት ከሚወጣ ቆሻሻ ላይ እያነሡ የየዕለት ምግባቸውን የሚመገቡ ልጆች አሉ፡፡ እነሡ ሳይፈታትሹት የቆሻሻ ከረጢቱን ለቆሻሻ አንሺዎች አያስነሡም፡፡ ብቻ ጥጋብን በተመለከተ እያንዳንዱን የማውቀውን ትግሬ ተረቱን በሚያረጋግጥ መልኩ ያልታዘብኩት የለም፡፡

ኧረ ተዉ! ተዉ! ተዉ! ተዉ! አስቡ! አስተውሉ! እግዚአብሔርን፣ ግፍንና ጡርን ፍሩ!፣ የደሀ ድሀ ወይም ከድህነት ወለል በታች የሆነ ሕዝብ ባላት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ መሆናቹህን አስቡና ጥጋባቹህን በልክ አድርጉት? ሠርቶ ንጹሕ ላቡን ጠብ አድርጎ ያገኘ ሰው እንኳን በንጹሕ ገንዘቡ ለሚያደርገው የሰው ዓይን የሚያስገባ ነገር ለማድረግ ይሳቀቃል! በዚህ ሕዝብ ላይ ለመኩራራት በፍጹም አይደፍርም! እናንተ ሀገረንና ይሄን ድሀ ሕዝብ ገፍፋቹህ! ዘርፋቹህ! በምታካብቱት የግፍ ገንዘብ እንዲህ ባጠገባቹህ ምስኪን ሕዝብ አናት ላይ ትቀዝኑበታላቹህ? ምን ያህል የሞራል (የቅስም) ድሀና ገለባ ብትሆኑ ነው እንዲያው ጥቂትም እንኳ መሳቀቅና ሐፍረት የሚባል ነገር የማይታይባቹህ???
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!!! ሰአሊ ለነ ቅድስት!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

 

ወያኔ የመጨረሻውን እርሾ እየጋገረ ነው (መስቀሉ አየለ — ክፍል ፪)

መስቀሉ አየለ

መንግስትታ ሲባሉ ከውጭ በሚደረግብቸው የጦርነት ግፊት ብቻ እንደማይወድቁ የቀደሙትን ሁለት መንግስታት ተሞክሮ እንደ መነሻ እናያለን። እነርሱም ከውጭ ከነበረባቸው ተጽእኖ ይልቅ የውስጣዊውን ቅራኔ አስታርቆ መሄድ ተስኖዋቸው ከውስጥ በኩል በስብሰው እንደ ወደቁ ግልጽ ነበር።Snake on Tigrayan People's Liberation Front (TPLF) logo

እንደ መነሻ

የንጉሱ አስተዳደር በጣም ባህላዊ በሆነ አስተምህሮ ውስጥ የነበረው እና ባመዛኙ በጣሊያን ወረራ ዘመን በተጋድሎ ባለፈው አብዛሃኛው ማህበረሰባችን እንዲሁም ዘመናዊ ትምህርት ቀመስ ሆነው አለምን እንደ ሰደድ እሳት እያጥለቀለቀ በመጣው የኮሚኒዝም ጽንሰ ሃሳብ የሰከሩ አዲሱ ትውልድ መካከል ያለውን ተቃርኖ አስታርቆ ወደ ፊት ለመሄድ ተሳነው። ምክኛቱም የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ላይ የተሞከረው የ1953 መፈንቅለ መንግስት ንጉሱ ላይ ጥሎት ያለፈው ጠባሳና ያን ተከትሎ በዙሪያቸው ላይ ያሉትን ካቢኔቶች አምኖ መጓዝ በተሳናቸው ሰዓት አገሪቱን የተሰራችበትን የህብረተሰብ ድርና ማግ እንዲሁም የአለማቀፍ ፖለቲካውን የሃይል አሰላለፍ ምን መልክ እንደነበረው እንኩዋን በቅጡ ያልተረዱ እራሳቸውን “ደርግ” ብለው በመጡ አንድ መቶ ሃያ ያህል አስር አለቆች እጅ የንጉሱ ተሰልቅጠው ሽንት ቤት መቀበር የሶስት ሽህ አመት የእድሜ ባለጸጋ የሆነው ሞናርኪ ፍጻሜ ሆነ እንጅ ብዙ የተወራለት የተማሪዎች ንቅናቄ ለነጉሱ ውድቀት ይኽ ነው የሚባል አስተዋጾ አሳድሮ ነበር ማለት አይቻልም። በወቅቱ የተጻፉትን ኩታ ገጠም የታሪክ ድርሳናት ብናያቸው በጣም ጽንፈኛ ከሚባለው የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች ህብረት እንኩዋን ውስጥ ይወጡ የነበሩት መግለጫወች ብናያቸው በግብር ይቀነስ፣በመሬት ላራሹና በመሳሰሉት ነገሮች ላይ የአካሄድ ለውጥ እንዲደረግ እንጅ አንድም ግዜ ንጉሱ ይውረዱ የሚል ጥያቄ አንስተው እንዳልነበር ያስረዳሉ።

ደርግም ቢሆን ምንም አንኩዋን አንድ ብሎ ስልጣን ላይ ከዎጣበት ቀን ጀምሮ ከሱማሌ፣ ኢህአፓ ኢዲዩ ሻቢያ ወያኔ ሱዳን (አሜሪካ በሚሰራው የፕሮክሲ ጦርነት) ሁሉ ተጠምዶ የነበረ ቢሆንም ለርሱ መውደቅ ግን ትልቁን አስተዋጾ ያደረገው ከውጭው ይልቅ የውስጡን ቅራኔ አቻችሎ መሄድ የተሳነው ቀን ነው። በተለይም በተለይም የግንቦት ስምንቱ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ የአገሪቱ ስመ ጥር ወታደራዊ መኮንኖች ላይ ያ ሁሉ ፍጅት የፈጸመ ቀን ደርግ የገዛ እጁን በጎራዴ እንደ ቆረጠው ግልጽ ነበረ። በወቅቱ የአገሪቱ መከላከያ ጦር ከአምስት መቶ በላይ እዝ የነበረው ሲሆን ይሕንን ሁሉ ቦታ ለመሸፈን ምንም አይነት የወታደረዊ እውቀት ልምድ የሌላቸውን የፖሊስ ሻለቆች ሳይቀር በነበራቸው ታማኝነት ብቻ እየመዘነ በወታደሩ ላይ ጀነራል አደርጎ እንዲሾም መገደዱ እንዲሁም ያለ አንዳች ጦርነት ትግራይን በሙሉ ለወያኔ ለቆ ሲወጣ ኤርትራ ውስጥ የነበረውን ከሶስት መቶ ሽህ ያላነሰ የአገሪቱ የጀርባ አጥንት ነው የሚባለውን ሜካናይዝድ ጦርና ድፍን የኤርትራን ህዝብ ለማስተዳደር ማንኛውንም አይነት ስንቅ እና ትጥቅ ከመሃል አገር የሚወስድበትን ብቸኛ መንገድ መዝጋት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አደጋውን ማየት ያልቻለ እውር አመራር፣ ይልቁንም ኢትዮጵያን በምታህል ከድህነት ወለል በታች የሆነች አገር የነበሩዋትን ጥቂት ቦይንግ አውሮፕላኖች ወንበራቸው እየታጠፈ ስኩዋር፣ ዘትይ፣ ዱቄት፣ መሳሪያ፣ ወዘተ ሁሉ ከባህርዳ አየር ጣቢያ ወደ አስመራ በማመላለስ ክፍተቱን ለመሙላት የተሞከረበትን እብደት ጤናማ ዜጋ ሆኖ ማሰብ አይቻልም።በእርግጥም ደርግ ከዚህ ቀን ቦሃላ በየትኛውም ግንባር ላይ የማጥቃት ሙከራ ሳያደርግ ይልቁንም ራሱን በራሱ ግዝግዞ በመብላት ላይ ተጠመደ እንጅ ወያኔ እንደሚለው ነገሩ ተራራውን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሆኖ ስለመጣበት አልነበረም። ለዚህም ማስረጃው ለአስራ ስድስት አመት ያህል ሲዋጋ ያላስደፈራቸውን ከምጽዋ እስከ መሃል አዲስ አበባ ያሉ መሬቶች ሁሉ በመጨረሻው አንድ አመት ውስጥ ብቻ እንደ ውሃ ሙላት በፈጠነ ኩነት ያስረከበበት የውድቀት ቁልቁለት ነበር።

በዚህ ላይ የቀዝቃዛውን ጦርነት ማክተም ተከትሎ አለም ላይ እየተቀየረ የመጣው የሃይል ሚዛን ማጋደልና የጎርብቾቭ አስተዳደር በመንግስቱ ኃይለማርያም ላይ ጀርባውን መስጠት ሲጨመርበት ደርግ የወደቀው በጦርነት ሳይሆን እንደ መሬት ስበት ወደ ውስጥ ሰንጎ በሚይዝ የራሱ ተቃርኖ አርጅቶ በወደቀ ግዜ ከወያኔ ውጭ የተደራጀ አካል አልነበረምና ትግራይን ሊገነጥል ደደቢት የገባው ቫይረስ አንዲት ትልቅ አገር ከነሙሉ ታሪኩዋና ሙሉ በረከቷ ድንገት እጁ ላይ ወደቀችለት።

ወያኔ

በየትኛውም መመዘኛ ስናየው ወያኔ ደግሞ ከቀደሙት መንግስታት ጋር ፈጽሞ ሊወዳደር በማይችል ከፍተኛ የሆነ ተቃርኖ ብቻ ሳይሆን በጣም የመረረ ቀውስ ውስጥ የተዘፈቀ፣ መኖሪያ ፈቃዱን በየ ሃያ አራት ሰዓቱ የሚያድስ ቡድን ሆኖ መውጣቱ አሌ አይባልም። በግድያ፣ በአገር ክህደት፣ በዘረፋና በኑፋቄ ከድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የማይታረቅ ልዩነት ውስጥ የወደቀው ይህ ጎጥን መሰረት ያደረገ የአናሳዎች ስብስብ በቡድን አባት ተከፋፍሎ እድሜውን ለማራዘም እየሞከረ ነው። ለዚህም ሁለት የሃይል አሰላልፍ ነጥሮ እንደ ወጣ ባለፈው ሰሞን ለማሳየት የሞከርኩ ሲሆን ይኸውም አኩርፈው ከወጡት ሰየ አብራሃና ኩባንያው በተጨማሪ የምእራብ መንግስታትን ከኋላው ያሰለፈው በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የህወሃት የፖለቲካ ክንፍ በአንድ በኩል በሳሞራ የኑስ የሚመራው መከላከያ ሃይልና የትግራይን ክልል ከነ ሚኒሻው ጠቅልሎ የሚዘውረው የአባይ ወልዱ ቡድን በሌላ በኩን መቧደናቸውን ገልጨ ነበር።

በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ቡድኖች የሃይል ቀጠናቸውን በማስፋት ሁለቱም ቡድኖች ክልሎችን በየስራቸው ለማሰለፍ በሩጫ ውስጥ የሰነበቱ ሲሆን የሳሞራ የኑስ በኮማንድ ፖስቱ ሽፋን የኦሮሚያን ክልል ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥሩ ስር ሲያደረገ የሶማሊያን ክልል በተመለከተ ግን ወትሮም የሳሞራ የግል አሽከር የሆኑ ጀነራሎች የቢዝነስ ሃብ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

በሌላ በኩል የአማራ ክልል ደግሞ በጌታቸው አሰፋ በሚመራው ቡድን ውስጥ የወደቀ ሲሆን ለዚሁም ዋነኛው ምክኛት እነ ገዱ አንዳርጋቸው ከነ አባይ ወልዱ ጋር የነበራቸው ስር የሰደደ ቅራኔ ለነጌታቸው ቡድን የመግቢያ ቀዳዳ እንደፈጠረላቸው ይታወቃል።

ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የቀረው የዚህ ቅራኔ የመጨረሻ የትንቅንቅ ቀጠና አዲስ አበባን መቆጣጠር ሲሆን ኮማንድ ፖስቱም ሆነ የጌታቸው አሰፋ ክንፍ በየወረዳው የየራሳቸውን ምህዋር በማስፋት ላይ በመጠመድ አዲስ አበባን ከመቆጣጠር ባሻገር አንዳቸው አንዳቸው ውስጥ ሰርገው በመግባትና ደጋፊዎቻቸውን በማስከዳት ጭምር ውስጥ ተዘፍቀዋል።

ለማጠቃለል ያህል የዚህ ፍጥጫ ሁለተኛው ምዕራፍ አዲስ አበባን በመቆጣጠር ላይ በሚያደርጉት የፍጻሜው ጦርነት የሚወሰን በመሆኑ ለሁለቱም ቀላል እንደማይሆን እያየነው ነው።ይቀጥላል።

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17448/#sthash.cp3HL8ll.dpuf

ፓርቲዎች የሚፈርሱት — በራሳቸው አባላት (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ምክንያት የሆነኝ ከተቀዋሚው ጎራ የማይጠፋውና ሰሞኑን ከሰማያዊ ፓርቲ ሰፈር እየተሰማ ያለው መወነጃጀልና መፈራረጅ ብሎም ሰማያዊ ፓርቲን ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ ሊያፈርሱት ነው የሚለው ጩኸት ነው፡፡Semayawi party to welcome Andinet members

ትውስታ፤  የሰማያዊ  ውስጣዊ ችግር ተባብሶ ለአየር መብቃት በጀመረበት ወቅት ሰማያዊ ይድን ይሆን! በሚል  ርዕስ ባቀረብኩት ጽሁፍ የፖለቲከ ስህተትና የሳንባ ነቀርሳ ጠንቆች የተመሳሳይነት ባህርይ አላቸው፡፡ ሁለቱም ችግሮች በለጋነታቸው ወቅት ከተነቃባቸው ችግሮቹን የማስወገድ ዕድል ከፍተኛ ነው፡፡ችግሮቹ ሥር ከሰደዱ በኋላ የሚደረገው መሯሯጥ ግን ፈውስ የማስገኘቱ ሁኔታ አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን የማይቻልም ሊሆን ይችላል፡፡ የሚለውን  የእንግሊዝ ጠ/ም  የነበሩትን የማርጋሪት ታቸርን አባባል ጠቅሼ፣ 

የጽሁፌ ዓላማ “አውቀውት ግን ድፍረት በማጣት አለያም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ሆኖባቸው ያላወቁትን በሽታቸውን ከነምክንያቱና ምልክቱ በማሳየት ደፍረው በበሽታቸው ላይ እንዲነጋገሩና መድሀኒቱንም ሁሉም አንደ ህመማቸው መጠን እንዲወስዱ ለማበረታታት” መሆኑን ገልጬ፣ “ነገር ግን ለዚህ ፈቃደኝነቱም ዝግጁነቱም ድፍረቱም ያላቸው ምን ያህል ሰዎች  አንዳሉ አላውቅም፡፡ ቢሆንም  ቀብሩ ላይ ከማልቀስ ከበሽታው እንዲፈወስ የሚቻለውን ማድረጉ ይሻላልና  የአኔን ልወጣ፡፡” በማለት የሰማያዊ ፓርቲን በሽታ ምንነት፣ የጅማሬውን መቼነትና እንዴትነት በማስረጃ አመላክቼ፣ መፍትሄ ያልኩትንም እንዲህ በማለት ገልጬ ነበር፡፡

“በውስጥም  በውጪም ያላችሁ አባላትም ሆናችሁ ደጋፊዎች  ጎራ ለይታቹሁ በሽተኞቹን ወደ መቃብር የሚገፋ ሆይ ሆይታችሁን አቁሙና  በሽታቸውን እንዲያውቁ መድሀኒቱንም እየመረራቸውም ቢሆን እንዲውጡ ለማበረታታት ከቻላችሁም ለማስገደድም ትጉ፡፡ መድሀኒቱ ግልጽ ቀጥኛና በሀቅና በድፍረት የሚካሄድ ውይይት ብቻ ነው፡፡   ይህ ካልሆነ  የቻላችሁ በአካል ያልቻላችሁ በማህበራዊ ድረ-ገጽ ለቀብሩ ትገናኛላችሁ፡፡ እኔ ግን  ፈጣሪ  መልካሙን ለመስማት ያበቃን ዘንድ እመኛለሁ፡፡”

ነገር ግን ቀደምቶቻቸው በሄዱበት መንገድ ከመሄድ ሊወጡ ያልቻሉት የሰማያዊ አመራሮች በርስ በርስ ሽኩቻ እየተናጡ ፓርቲያቸውን ለአደጋ ዳርገው ያንኑ  ከትናንቶቹ የወረሱትንና በደንብ የተለማመዱትን መዘላላፍ መፈራረጅ እና ወያኔን መክሰስ እያሰሙን ነው፡፡ እነርሱ ቤታቸውን ለማቃጠል እሳት ሲጭሩ ወያኔ እንዲያጠፋላቸው ያስቡ ነበር? ፕ/ር መረራ ስለ ፖለቲከኞቹ ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “የፓርቲዎቹ መሪዎች በቀላሉ የመከፋፈል ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ባለመተማመን በሀሜት ይወድቃሉ፡ የሚያገኙትን ትርፍ እንኳን ሳያውቁ ወደ መከፋፈል ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ፡፡”(  እንቢልታ ጋዜጣ ቅጽ 1 ቁ27)

ከወያኔ ምን ይጠበቃል፣

መጠሪያቸው ተቀዋሚ፣ ዓላማቸው ወያኔን ማስወገድ፣ ግባቸው ሥልጣን መያዝ መሆኑን አውጀው ፓርቲ መሰረትን የሚሉ ሰዎች በየግዜው የሚያሰሙት ወያኔ አፈረሰን፣ ከፋፈለን አዳከመን፣ የሚለው ጩኸታቸው በአበባ ምንጣፍ እንዲቀባላቸው፣ እየኮተኮተ እንዲያሳድጋቸው ብቻ አይደለም  ሲጣሉ ፍትሀዊ ብይን እንዲሰጣቸው ሳይቀር  ይመኙ ወይንም ያስቡ ነበር እንዴ የሚያሰኝ ነው፡፡

ከመነሻው የሚቃወሙትን ኃይል ማንነት፣ ምንንት፣ አቅምና ተንኮል በሚገባ ተረድተው እቅዳቸውም ሆነ ዝግጅታቸው ከግማሽ በላይ እራሳቸውን ከወያኔ በመከላከል ተግባር ላይ ያተኮረ ማድረግ ነበረባቸው፡፡ እነርሱ ግን ትናንትም እንዳየነው እነሆ ዛሬም እያየንና እየሰማን እንዳለነው በተቃራኒ ፓርቲያቸውን ለጥቃት ያጋልጡና ወያኔ አንዲህ አደረገን እያሉ የአዞ አንባ ያነባሉ፡፡

በአንድ ቤት ውስጥ በቤተሰብ አባልነትም ይሁን በደባልነት አብረው የሚኖሩ ሰዎች አምባጓሮ አንስተው በዚሁ ምክንያት እሳት ቢቀጣጠልና ርምጃቸውን እየለካ፣ ድምጻቸውን እያዳመጠ  በቅርብ የሚከታተላቸው ባላጋራቸው አጋጣሚውን ተጠቅሞ እሳት ማጥፊያ ውኃ ይዞ የደረሰ መስሎ ነዳጅ  ጨምሮ ቢያቀጣጥለውና ቤቱ አመድ ቢሆን ቤቱን አቃጠለ የሚባለው  ማነው?

በሰሞነኛው የሰማያዊ ጉዳይ በማጀቢያነት እየተገለጸ ያለው አንድነት የፈረሰው፣  መኢአድና ሰማያዊ ወደዛው እያመሩ ያሉት  በራሳቸው አባላትና ደጋፊዎች በተለይም አመራር ላይ በነበሩና ባሉት ሰዎቻቸው ነው፡፡ ይህን የራስን በሽታ አውቆ መድሀኒት ለመፈለግ ድፍረቱም ብቃቱም ባለመኖሩ የራስን ድክመት በወያኔ አረመኔያዊ ድርጊት እየሸፈኑ የዛሬዎቹም የትናንቶቹ በተጓዙበትና ለውጤት ባልበቁበት ጎዳና እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲ ወንበር ሥልጣን ሆኖ ሽኩቻ ፡፡

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ወያኔ አፈረሳቸው /አዳከማቸው እየተባሉ ተደጋግመው የሚነሱት መኢአድና አንድንት ሲሆኑ አሁን ሰማያዊም እየተቀላቀለ ነው፡፡ ከፖለቲካው ሆያ ሆየ ጨዋታ ወጣ ብሎ፣  ድጋፍና ተቃውሞን በጭፍን ጥላቻና ፍቅር ማድረጉን ለደቂቃ ገታ አድርጎ ዙሪያ መለስ ማየት ለቻለ ሰው እነዚህ ፓርቲዎች የፈረሱትም ሆነ እየፈረሱ ያሉት በራሳቸው በተለይም አመራር ላይ በነበሩና ባሉ ሰዎቻቸው መሆኑን ለመረዳት ብዙ ጥረት አይጠይቀውም፡፡ ብዙ መረጃ በቅርብ ማግኘት ይቻላል ከታሰበበት፡፡ እኔ ዝርዘር ውስጥ ሳልገባ ትንሽ ማሳያ ላቅርብ

አንድነት፤ አንድነት ህመሙ የጀመረው ሊቀመንበሩ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ስትታሰር ነው፡፡ መድሀኒት የሚፈልግለት አይደለም በሽታውን የሚያውቅለት ጠፍቶ ለአምስት አመታት ከተሰቃየ በኋላ በሀገር ቤትም በውጪም የሚኖሩ  ከአመራር እስከ አባል የነበሩ  የግዛቸው ነኝ፣ የበላይ ነኝ በማለት በፈጠሩት የሥልጣን ሽኩቻ በሽታው ተባብሶ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡በመቃብሩ ላይ የቆመው ትእግስቱ አዎሉም በየግዜው በሹመት ላይ ሹመት ሲሰጡት የነበረ ሰው ነው፡፡ ታዲያ ለአንድነት ሞት ቀዳሚው ተጠያቂ ወያኔ ወይንስ የሥልጣን ጥም ያናወዛቸው የአንድነት አመራሮችና የዲያስፖራ ብር ያናወዛቸው አጃቢዎቻቸው፡፡

መኢአድ፤ ስለ መኢአድ ባነሳሁ ቁጥር የሚከነክነኝ የዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ ነገር ነው፡፡ ከቅንጅት አመራሮች ጋር በሀሰት ተከሰው 21 ወራት ታሰሩ፡፡ የመኢአድ ም/ል ሊቀመንበር ሆነው በሥልጣን ሽኩቻ ምክንያት በእነ ኢ/ር ኃይሉ ወንጃይነትና በምርጫ ቦርድ ተባባሪነት በሀሰት ተከሰው 17  ወራት ታስረው ይግባኛቸውን የተመለከተው ፍርድ ቤት  በነጻ አሰናበታቸው፡፡ የራሳቸውን ሰው ያውም ም/ል ሊቀመንበር ከሰው በወያኔ የሚያሳስሩ ሰዎች  የራሳቸው አጥፊነት ተደብቆ እንዴት ወያኔ አፈረሳቸው ይባላል ? ከዛም በኋላ  አቶ አበባው ሊቀመንበር ሆነው  እነ ማሙሸት አማረ በሀይሉ ሻውል ተሸሙ አንጂ በጉባኤ አልተመረጡም ብለው ያንኑ የሚያውቁትን እናም የለመድነውን ፍረጃና ዘለፋ አሰሙን፤  የሚገርመው ነገር አቶ አበባው ተነስተው አቶ ማሙሸት ሊቀመንበር ሲባል ደግሞ አቶ አበባው ባላወኩት ሁኔታ በኢ/ር ኃይሉ ሻውል ተገፍቼ ነው ከመድረክ የተባረርኩት አሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የሁለቱ ቡድን ሲፋተግ ቆይቶ አቶ አበባው ተመልሰው ወደ ሥልጣን መጡ፤ ከዛ ደግሞ ዶ/ር በዛብህ ተመረጡ ተባለ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መዘላለፉ መፈራረጁ መወነጃጀሉ ወዘተ አላባራም፡፡ ወያኔም በምርጫ ቦርድ አማካኝነት በቅርብ እየተከታተለ ኳስ እያቀበለ ሲያጫውታቸው ቆይቶ  ለዶ/ር በዛብህ ቡድን ምሥክር ወረቀት ሰጠ፡፡ ታዲያ ወያኔ ምን እንዲያደርግላቸው ታስቦ ነው አፈረሳቸው አዳከማቸው የሚባለው፡፡

ሰማያዊ፣ በሽታው የጀመረው በቃል የወጣት ፓርቲ እየተባለ  በተግባር ግን በዘልማዱ መንገድ በመጓዝ ሰርጎ ገብ፣ ፓርቲ አፍራሽ፣ አንጃ የሚሉ ቃላት በአመራሩ አካባቢ መሰማት በጀመረበት ግዜ ነው፡፡ ይህ በሽታው ከማጀት አልፎ ለአደባባይ ሲበቃ፣ አመራሮቹ ነገረ ስራቸው ከተለመደው መፈራረጅና መዘላለፍ አልፎ በገንዘብ ብክነት እስከመካሰስ ሲደረስ አረ ምንድን ነው ምክንያቱ፣ መፍትሄውስ ብሎ የሚቻለውን ለማድረግ የጣረ ቢኖር በጣም ጥቂት ነው፡፡ ታዲያ በሥልጣን በሽታ  ጎራ ለይተው በለው ሲባባሉ ከርመው  አሁን የየራሳቸውን ጉዳጉድ ደብቀው ወያኔ አፈረሰን ሲሉ እነርሱ ባያፍሩ እኛ ግን ልናፍርባቸው እንጂ በምንም መልኩ ጩኸታቸውን ልናስተጋባ ፓርቲው ለሞት ከበቃም ለቅሶ ልንቀመጥ አይገባም፡፡ ታሞ ያልጠየቀ ሀኪም ቤት ወይንም ጸበል ለመውሰድ ያልሞከረ፣ መድሀኒት መግዣ ብሎ ድንቡሎ ያረዳ ሲሞት ዋይ ዋይ ማለት ምን ይሉታል፡፡ ድምጻዊ ብዙነሽ በቀለ  “በቁም ሳይጠይቁኝ ስሞት ማልቀሳቸው ውርስ ለማግኘት ነው ሀብታም መስያቸው” ብላ ዘፍና ነበር ፣ ታሞ ሲማቅቅ፣ ወደ  ሞት እያመራ መሆኑ ሲታወቅ ለማዳን ያልጣሩ አንደውም የሞቱን ግዜ የሚያፋጥን ሥራ ሲሰሩ የነበሩ ዛሬ ተነስተው ሊሞት ነው እያሉ ደረት መድቃታቸው  ከሰማያዊ ሞት ምን የሚገኝ ነገር ቢኖሮ ይሆን!

በመጨረሻ አስገራሚ ገጠመኝ፣ ይህችን አስተያየት እየከተብኩ ሳለሁ ሀምሳዎቹን በአጋመሰው ዕድሜየ ሰምቼው የማላውቀው “አይ ዘመን”  የጥላሁን ገሰሰን ዘፈን አገኙሁ፣ ስንኞቹ ከዚህች ጽሁፍ ጋር የተዛመዱ መሆናቸው ነበር ለእኔ አስገራሚ ገጠመኝ የሆነብኝ፡፡ ትንሽ ጀባ ልበላችሁን ልሰናበት፡፡

አይ ዘመን አይ ግዜ- እንደው የኛ ዘመን

የመኖርን ጥቅም ሳናውቅ አጣጥመን፣

ውስብስብ ውልክፍክፍ – ወዲያ ሲሉት ወዲህ

በዘ-ልማድ ብቻ ቀን ይገፋል እንዲህ

በመዋል በማደር ዘመን ያልፋል እንዲህ

ሁሉም ከአንገት በላይ- ሳቅ ጨዋታ ለዛ

ደግ አሳቢ አነሰ ክፋት ተንኮል በዛ፣

መሬት መሬት አየ አይን አቀረቀረ

በቃል ኪዳን መጽናት መተማመን ቀረ፡፡  ዘፈኑ ይቀጥላል እኛ ግን ይብቃን፣ የትናንቱ መንገድ ወዴትም አያስኬድ፡፡

ጠመንጃ ያንቀጠቀጠ ሐሳብ | ከበፍቃዱ ዘ-ኃይሉ

 

“ተራሮችን በጠመንጃ አንቀጥቅጫለሁ” የሚለው ‘ገዢው’ ፓርቲ፣ ለብዕር ግን ይንቀጠቀጣል። የአቶ መለስ (solo) አመራር እና የአቶ ኃይለማርያም የቡድን አመራር ሁለቱም ብዕር ይፈራሉ፣ የጨበጠውንም ይቀጣሉ።

የመለስ ዜናዊ የ21 ዓመታት አመራር “በጻፈው ነገር የታሰረ ሰው የለም” እያለ ይጎርር ነበር። እኛም እንዴት አድርገን መስማት እንዳለብን እናውቅ ነበር፤ ‘ሌላ ወንጀል ፈጥረን ነው በሰበብ የምናስራቸው’ ማለታቸው የሚመስለን ጥቂት አልነበርንም። በአቶ መለስ ጊዜ የተከሰሱ ጋዜጠኞች “አዳፍኔ” ስለሚባሉ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ጽፈዋል። ተከሳሽ ላይ ወንጀል ሲደፈድፉ ዓይን የላቸውም።
አሁን ለሰበብ የሚጨነቅ አመራር የለም። ዝም ብሎ የማሰር ጊዜ ሆኗል – ዓመቱ።

የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 257 በንዑስ አንቀፆቹ ‘በጽሑፍ [እና መሰል ድርጊቶች] አመፅ ማነሳሳትን’ ይከለክላል። በዚሁ መሠረት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የ3 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል፤ ሑሴን አራጌ ሁለት ዓመት እንዳይጽፍ ታግዶበታል። ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ አንድ ዓመት ተፈርዶበታል። ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፍርድ ቤት እየተሟገተበት ነው። ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ታስሮ እየተከላከለበት ነው። እኔ ተከራክሬ ጨርሼ ብይን እየጠየቅኩበት ነው። ዘሪሁን ገሠሠ ተከሶበታል። ወዘተ… እነዚህ ሁሉ (የዘረዘርኳቸው ክሶች እና ተከሳሾች) በጻፉት ጽሑፍ “ተነሳ ባሉኝ መሠረት ተነሳስቼ ይሄን አድርጌያለሁ” የሚል ግለሰብ ወይም ያንን ተከትሎ የደረሰ ጉዳት የለም። እንደማስረጃ የቀረበው የመንግሥት (ዐቃቤ ሕግ) ‘አመፅ ሊነሳ ይችል ነበር’ የሚለው ስጋት ነው። (የኤልያስ ገብሩ ክስ፣ እሱ ዋና አዘጋጅ የነበረበት መጽሔት ላይ አምሳሉ ገብረኪዳን የጻፈውን ጽሑፍ ተቃውመው ያመፁ የጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ያደረሱትን ጉዳት ለማካካስ ያለመ ይመስላል፤ ብቸኛው የሚመስል ሰበብ የቀረበበት ክስም ይሄው ነው። የነጻነት አገር ቢሆን ኖሮ ግን ጋዜጠኛ ኤሊያስ ራሱ መጽሔቱ ላይ ባተመው ጽሑፍ ከሚመጣበት ሐሳብን በአመፅ ከሚሞግቱ ሰዎች አደጋ በመንግሥት መጠበቅ ይገባው ነበር።)
ቀደም ሲል በጠቀስኩት፣ በሰበብ ዘመን “በሽብርተኝነት” ሰበብ 18 ዓመት የተፈረደበት እስክንድር ነጋ እና 14 ዓመት የተፈረደበት ውብሸት ታዬ የሚታወቁት በሐሳቦቻቸው/ጽሑፎቻቸው ነው። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በ1997 ምርጫ ማግስት ስለፍፁማዊ አመፅ–አልባ “ሕዝባዊ እምቢተኝነት” መጽሐፍ አሳትሟል። ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከታሰረ በኋላ በጻፋቸው ሁለት መጽሐፎች ደጋግሞ ያሳየው ለሠላማዊ ትግል ያለውን ታማኝነት ነው። ሁለቱም ተፈርዶባቸው ከታሰሩ በኋላ፣ ከእስረኛ ሁሉ በከፋ አያያዝ ነው ተይዘው እየከረሙ ያሉት። የነርሱ ወንጀል ኢፍትሐዊ ነው ያሉትን መንግሥት በሠላማዊ ትግል መውረድ እንዳለበት መሟገታቸው ነው። ይህንን ደግሞ በአመፅ እስካልሞከሩት ወይም በአመፅ እንዲከናወን እስካልተናገሩት ድረስ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነው። በኔ እምነት ዛሬ ኢትዮጵያ የገባችበት ቀውስ የሚጀምረው ያኔ ነው። መንግሥት መካሪዎቹን ሲያስር። የአንጋፋዎቹ ሐሳብ ሰሚ ሲያጣ! ዛሬ ሁሉም አመፀኛ ሆኗል ማለት ይቻላል፣… በዚህም የተነሳ መንግሥት እጅ ላይ የተረፈው ለስለሳ ትችት ያቀረበውን ሁሉ መጠርጠር ነው።

አሁንም “የፖለቲካ ወንጀል” የሚባል የለም ብሎ የሚከራከረውን መንግሥት በመቃወማቸው ብዙ ሰዎች መታሰራቸው ምሥጢር አይደለም። ምሥጢሩ ‘የሚከሰሱት በምን ወንጀል ነው?’ የሚለው ነው። ጋዜጠኛ እዮኤል ፍስሐ ከታሰረ ከ100 ቀን በላይ ቢሆነውም፣ ክሱን አላወቀም። ጋዜጠቹ ኤልያስ ገብሩ እና አናንያ ሶሪም ከፖለቲከኛው ዳንኤል ሺበሺ ጋር ከ90 ቀናት በላይ የታሰሩት ምን ወንጀል ሠርተው እንደሆነ አልታወቀም። ብዙ ሰዎች “ወንጀል” ብለው የጠረጠሩት ሦስቱም እጃቸውን አጣምረው ተነስተው በለጠፉት የፌስቡክ ፎቶ እንደታሰሩ ነው። ጥያቄው ግን ‘በርግጥ ያንን ምልክት ማሳየት በሕግ ተከልክሏል ወይ?’ መሆን አለበት።

በሰበብ ዘመን፣ አቶ መለስ በድኅረ ምርጫ 1997 “ጣቱን የቀሰረ ይቆረጥለታል” ብለው ሲዝቱ “የመሪ ንግግር ያው ሕግ ነው” ብለን በጣቶቻችን የሁለት ሰው ምልክት ለበራሪ ታክሲ ለማሳየት እስከመፍራት ደርሰን ነበር። አሁንም ታሪክ በሽሙጥ መልክ ራሱን ደግሞ ሁለት እጅ አጣምሮ ማሳየት ሕገ ወጥ ነው በሚል ተፈርቷል። ሕግ ግን ጽሑፍ ይፈልጋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ “አመፅ የሚቀሰቅስ ምልክት ማሳየት” ሲከለክል ምልክቱ ምን እንደሆነ አልጠቀሰም። ሌላው ቀርቶ ባለሥልጣናቱ የሰጡት ማብራሪያ ላይም በምልክት ወይም በገለጻ የተከለከለውን የምልክት ዓይነት ሲያብራሩ አላየሁም። ስለዚህ የእነዚህ ሰዎች መታሰር ከጋዜጠኝነት፣ ፖለቲከኝነት ሥራቸው ጋር የተያያዘ ነው ብለን እንድንጠረጥር ያስገድደናል። ምክንያቱም ወንጀላቸው አልተነገረማ።
እነ ጋዜጠኛ ኤልያስ ያሳዩት ምልክት በርግጥም ተከልክሎ ከሆነ ተቃዋሚነት ተከልክሏል ማለት ነው። እንደሚታወቀው፣ ምልክቱ “ታስረናል” ወይም “ሐሳባችንን የመግለጽ ነጻነታችን ታስሯል” የሚል የተቃውሞ ሐሳባዊ መሟገቻ ነው እንጂ በምንም ዓይነት ከአመፅ ጋር አይያያዝም። ለዚህም ከተቻለ [ሚኒሶታ ሰልፍ የወጡት የኢሕአዴግ ደጋፊ የሶማሊ ተወላጆች በምላሹ እንዳሳዩት ዓይነት] የምልክት ግብረ ምላሽ ሰጥቶ ሐሳቡን በሐሳብ ለማሸነፍ መጣር ነው እንጂ በአዋጅ መገደብ “ተራራ ካንቀጠቀጠ”፣ ጠመንጃ ከጨበጠ ትውልድ ፈፅሞ የሚጠበቅ ነገር አይደለም።

ከላይ የተጠቀሰው ምልክት በአዋጅ የተከለከለው ምልክት ነው እንበል። ቢሆንስ ታዲያ ምልክቱ በተሐድሶ የማይታረም ወንጀል ሆኖ ነው ወይ እነ ጋዜጠኛ ኤልያስ ከተያዙ በኋላ የታሰሩ ሰዎች ለተሐድሶ ሲላኩ እነርሱ ያልተላኩት? ሌሎቹስ?

በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የታሰሩ ሰዎች እጣ ፈንታ ሦስት ነው። ጉዳያቸው ተጣርቶ ነጻ መለቀቅ፣ በተሐድሶ ታርሞ መለቀቅ እና ፍርድ ቤት መቅረብ። ፍ/ቤት ይቀርባሉ የተባሉት እስካሁን አልቀረቡም። እነጋዜጠኛ እዮኤል ዳምጤ የርሐብ አድማ ለአምስት ቀን አድርገው ክስ እንደሚመሠረትባቸውና ለዚህም ልዩ፣ ተዘዋዋሪ ችሎት እንደሚቋቋም ተነግሯቸዋል። ይህ ከተባለም ቆየ። እነኤልያስ ገብሩ ምን እንደሚገጥማቸው ገና አላወቁም። በሰበብ አልባ ዘመን ክስም ይናፍቃል።

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ በ90 ዓመታቸው አረፉ ቀብራቸው በመጪው ሰኞ ቅድስት ስላሴ ቤ/ክርስቲያን በ9 ሰዓት ይፈፀማል

 

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ በ90 ዓመታቸው አረፉ

እናታቸው እንግሊዛዊቷ ሲልቭያ ፓንክረስ ኢትዮጵያ በጣልያን ስትወረር በእንግሊዝ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በማቀጣጠል ተቃውመዋል።ንጉሡ በስደት በነበሩበት ወቅት አብረው ወጥተዋል ወርደዋል። በኃላም ከልጃቸው ሪቻርድ ፓክረስት ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መኖር ጀምረው ሲያርፉ ቀብራቸው በቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ነበር።

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ እናት የኢትዮጵያ ወዳጅ ወ/ሮ ስልቭያ ፓንክረስ 

የስልቭያ ፓንክረስት ልጅ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል እንዲመሰረት ያደረጉ ስለ ኢትዮጵያ ሲፅፉ እና ሲመራመሩ የኖሩ ምሁር ናቸው።ፕሮፌሰሩ ከ1940ዎቹ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መውረድ ድረስ በኢትዮጵያ ከኖሩ በኃላ በ1970ዎቹ መጨረሻ እንደገና ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምርምራቸውን ቀጥለዋል።ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ በ90 አመታቸው ማረፋቸው እና በመጪው ሰኞ አዲስ አበባ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን የቀብራቸው ስነ ስርዓት እንደሚፈፀም ተነግሯል።

እረፍተ ነፍስ ለፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ መፅናናትን ለቤተሰቦቻቸው ይስጥልን።

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ ልጅ ፕሮፌሰር አሉላ ፓንክረስ ግጥም ከእዚህ በታች ይመልከቱ