ፎረም 65፦ አደራዳሪ የሌለው ድርድር ፡ ዶክተር የሌለው ሆስፒታል ነው – ፎረም 65

 

አገራችን ባለፈው ዓመት ካለፈችበት ህዝባዊ ተቃውሞዎች አንፃር ኢሕአዴግ ከህጋዊ አገራዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ማድረግ እንደሚፈልግ መግለፁ ለብዙዎቻችን ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ነበር።

ሆኖም በቅድመ ድርድር ሂደቱ ወቅት ኢሕአዴግ ያሳየው አካሄድ ሚጠቁመው ከድርጅቱ አመራር ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ያለችበትን አደገኛ ሁኔታና ሂደት በአግባቡ ያላጤኑ ፥ አደጋውን አለባብሰው ማለፍ የመረጡ ፥ ብቃትና አቅም የሌላቸው ፅንፈኛ ጥቂቶች ፡ የድርድር ተስፋውን እያጨለሙት መሆኑን ነው።

ኢሕአዴግ ከደርግና ከአፄው ስርዓት ያልተማረው ዋና ቁምነገር ሁሉን ተቆጣጥሮ ፡ ሁልጊዜ እያለባበሱ ማለፍ እንደማይቻል ነው። እስከ መጨረሻው ሰጥቶ መቀበልን ያልፈለገው ደርግ ዛሬ የታሪክ አመድ ሆኗል። በፍጥነት ተሃድሶ ማድረግ ያልፈለገው የአፄው ስርዓት ዛሬ የሚገኘው በጥቂት አረጋውያን ትዝታ ውስጥ ብቻ ነው።

ኢሕአዴግና አባላቶቹ ሊያስተውሉት ሚገባው ፡ በአገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ምልክት እንጂ መንስዔ እንዳልሆነ ነው። እሳት ላይ የተጣደ የጀበና ውሃ እሳቱ እስካለ ድረስ መፍላቱንና መንተክተኩን ይቀጥላል።

ገዢው ፓርቲ በተፈበረኩ የስራ ዕድል ቁጥሮች ፕሮፓጋንዳ ፡ በጅምላ እስራትና በ”አይደገምም” የአስገድዶ ቃልኪዳን ማስገባት ፡ ከስሩ የተቀጣጠለውን እሳት በቋሚነት ማስቆም አይችልም። እሳቱ እሳካለ ድረስ ውሃው ደጋግሞ ይገነፍላል።

ለዚህ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ግልፅ ፣ አሳታፊ ፣ ሚዛናዊና በገለልተኛ አካላት የሚመራ ድርድር ማድረግ ብቻ ነው።

ገዢው ፓርቲ ድርድሩ ያለአደራዳሪ ይደረግ ማለቱ የሚያሳየው አንዳንድ የኢሕአዴግ አመራሮች ድርድሩን እንደለመዱት ለፓለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም ማሰባቸውን ከመሆኑም በላይ ፡ ባለፉት 25 ዓመታት የታየውን የኢሕአዴግን ‘የኔ መንገድ ብቻ’ አፍራሽና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ነው።

ይህ የኢሕአዴግ አንዳንድ ፅንፈኛ መሪዎች አኪያሄድ በፓለቲካ ድርጅት ያልታቀፉ ፣ ለአገር የሚያስቡ ቅንና የመደራደር ዋጋና ትርጉም የተገነዘቡ ዜጎች ኢትዮጵያ የሏትም ከሚል አስተሳሰብ የተነሳ ሲሆን ፡ ይህ አስተሳሰብ በህዝብ ላይ አመኔታን ካለመጣልና ህዝብን ከመናቅ የመነጨ ነው።

አደራዳሪ የሌለው ድርድር ማለት ዶክተር የሌለው ሆስፒታል ማለት ነው። ውጤቱ ኪሳራ ነው። አገራችን ያለችበት አደጋ የሚታያቸው አስተዋይና አርቆ አሳቢ የኢሕአዴግ መሪዎችና አባላት የራሳቸውንም ሆነ የድርጅቱን ህልውና ማስከበርና ማስቀጠል ሚችሉት ድርድሩን በገለልተኛ አደራዳሪዎች እንዲመራ በማድረግ ብቻ ነው።

ድርድሩ ከፓለቲካ ፍጆታ ያላለፈ ከሆነ ግን በሌሎች አገሮች ያየነውን የህዝብ ሰቆቃ ለመድገም ጥቂቶች የቆረጡ መሆናቸውንና ፡  በኢሕአዴግ ውስጥ ይሄው አፍራሽ አስተሳሰብ የበላይነቱን ይዞ ገዢው ፓርቲ ሌሎች ቀደምት ስርዓቶች የተጎናፀፉትን ውድቀት እየተጠባበቀ መሆኑን ያመላክታል።

ለተተኪው ትውልድ መግባባትን እናውርስ።

ፎረም 65

በአማራዊነት መንፈስ ላይ ጀምበር አትጠልቅም | ቬሮኒካ መላኩ

 

በአለም ላይ የሚነገር አንድ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ የፖለቲካ ምሳሊያዊ አባባል (Maxim) አለ ። ” ዘላቂ ሰላምን የምትሻ ከሆነ ለጦርነት ተዘጋጅ ” ይላል። ጥንካሬህን አይተው ጠላቶችህ ይፈሩሃል። ድል አድራጊነትህን ገምግመው የሚፋለሙህ ይጠፋሉ እንደ ማለት ነው።
ቻይናዊው የጦር ጄነራል፣ ስትራቴጂስት እና ፈላስፋ ሰን ዙ. በበኩሉ
” ጠላትን ለይቶ ማወቅና በጠላት ላይ ቁርጥ አቋም መውሰድ የድል ግማሽ ያህል ነው፡፡ ” አይነት አባባል አለው ፡፡ የአማራ ህዝብ ደረጃቸው ይለያይ እንጅ የተለያዩ ጠላቶች ነበሩት አሁንም አሉት ። ከዋናው ጠላቱ ወያኔ ጀምሮ ጥቃቅን ጠላቶች ነበሩት አሁንም አሉት ።

በአሜሪካ አገር የመጀመሪያው የጥቁሮች ጋዜጣ በ 1827 ዓ.ም ሲቋቋም እንደ ታላቅ መሪ መፈክር አድርጎ የተነሳው << ለእኛ ማሰቡን ፣ለራሳችን መናገሩን ለእኛ ተውልን… … የራሳችንን ታሪክ ከማንም የበለጠ ለመናገር የምንችለው እኛው ነን> > የሚል ነበር ።
በአጭሩ ለማለት የፈለጉት ለራሳችን ጉዳይ ሞግዚት አያስፈልገንም የሚል ነበር ። እኔም ዛሬ በዚች አጠር ያለች ጦማሬ አማራ ስለራሱ ለመናገር ሞግዚት አያስፈልገውም ምክንያቱም ትከሻችን ጭንቅላታችንን ለመሸከም አይከብደውም የሚለውን አፅንኦት በመስጠት አማራዊነት ግቡን ይመታ ዘንድ አንዳንድ ጠቃሚ የምላቸውን ነጥቦች ለመዳሰስ እሞክራለሁኝ።

ባለፉት 25 አመታት አንዳንዶች የሉም ብለውናል። የደረሰብን አሰቃቂና ኢሰብአዊ ድርጊት የፈለገውን ያህል አስከፊ ቢሆንም አሁን ባለንበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን ።
አሁን አሁን አማራ ሳይሆኑ የአማራን ማሊያ ለብሰው ጨዋታውን የሚያደፈርሱት ብዙ ናቸው ። አንደ ብአዴን ያሉት አማርኛ ተናጋሪ ህውሃቶች አማራ ሳይሆነ አማራን ወክለው “አማራ ለሺህ አመታት የጨቆናቸውን ብሔር ብሔረሰቦች ስህተቱን ያርማል” ይሉናል። እኛ የምንኮራበትን የሺህ አመታቶች የኋላ ታሪክ እነሱ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ስህተት አድርገው ይደሰኩራሉ ። እነዚህ የዘመናችን ፕሮፓጋንድስቶች የሚሰድቧቸው አባቶቻችን የመላ ጥቁር ህዝብና የሦስተኛ አለም መመኪያ የሆነውን የአድዋን ጦርነት በጀግንነት በመዋጋት የኮሎኒያሊዝምን ተስፋፊነት በመግታት በባርነት ሥር ይማቅቁ ለነበሩት የትግል አርአያ በመሆን የድል ችቦን አቀጣጥለው ነፃነትን አስገኝተዋል። ይሄን አኩሪ ታሪክ እነሱ ቢያጣጥሉት እና ቢንቁት አይደንቀንም ። የነፃነትን ዋጋ የሚያውቀው ነፃ ህዝብ ነው። አማራ ደሞ እንደ ስያሜው ትርጓሜ ነፃ ህዝብ ነውና ነፃነትን ያከብራል።


የአፍሪካን ነፃነት እና በራስ መተማመን ጠርበው ቀርፀው እዚህ ካደረሱ ህዝቦች በዋናነት የሚጠቀሱት አማሮች ናቸው።
ከአማራ ህዝብ አብራክ ወጡ የተባሉት የኢትዮጵያ ነገስታት ኢትዮጵያን ሲገዙ ባንድራቸውን ከህንድ ውቅያኖስ እስከ የመን ተክለው ነበር። የግሪክ አማልክት ሳይቀሩ ሰርተው ሰርተው ሲደክማቸው ለእረፍት የሚመጡት ወደ እኛው የጊዮን ምንጭ አባይ ነበር ። የአማልክቶች አባት የሆነው ታላቁ ዚየስ በሰለቸውና በደከመው ቁጥር ” እስቲ ወደነዚያ መልከ መልካምና ደጋግ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ልሂድ ” ነበር የሚለው ።

በረጅሙ የስልጣኔ ጉዞው የራሱን ፍልስፍና ያበቀለው የአማራ ህዝብ ለአፍሪካ ህዝቦች የኩራት ምንጭ ነበር።
መላው አፍሪካ አህጉር ታሪኩን በአፈ ታሪክ ሲቀርፅ ኢትዮጵያውያን ታሪካቸውን በሚፃፍ ቋንቋ ይዘግቡ ነበር ። በአማራዎቹ አማርኛ ቋንቋ ።
አማራ ለ 85 ብሄር ብሄረሰብ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹና እህቶቹ በአፍሪካ ብቸኛ የሆነውን አማርኛና ግእዝ ያበረከተ ህዝብ ነው ።ለዚህም ምስክሩ አማርኛ መላው ሀገሩ መነገሩ ነው።
ተወደደም ተጠላም ዛሬ ራሱ አማርኛ በአፍሪካ ውስጥ የራሱ ፊደል ያለው ብቸኛው ቁዋንቁዋ ነው። ነገ የሚያንቀሳቅሰው ከተገኘ የአፍሪካ ህብረት የስራ ቁዋንቁዋ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም።

የሶስት ሺ ወይም ከዚያ በላይ እድሜ ያለው ታሪክ ባለቤቶች ብንሆንም ረዥም ትግል እና ብዙ መስዋእት ብንከፍልም ለውለታችን የተከፈለው ጠላትነትን ነው።
በአለም ታዋቂነትና ክብር ለኢትዮጵያ የሰጡትን የቀድሞ ስልጣኔ መስራች ህዝቦች ብንሆንም ያገኘነው ምላሽ ” ትምክተኛ “የሚል ነው።
ሙሴ በሲና ተራራ ፣ ክርስቶስ በታቦር ተራራ እና ቡድሃ በሂማሊያ ተራራ የሰበኩትን ፍቅርን እና አንድነት በኢትዮጵያ ብንሰብክም ያተረፍነው ጥላቻን ነው።ምናልባት የአማራ ጥፋት ነው ከተባለ ይህችን ድንቅ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከስንቱ ቅኝ ገዥና ፋሽስት ጋር እየተጋደለ እዚህ ማድረሱ ነው።

የህውሃት ፋሽስቶች በኢትዮጵያ ለደረሰው ኢኮኖሚያዊና ማሀበራዊ ችግሮች ሁሉ አማራን ተጠያቂ በማድረግ ፀረ አማረነት አይነተኛ የትግል መሳሪያቸው አድርገው ተጠቅመውበታል።
ጠላትን ፈጥኖ አለማወቅ ከባድ ጉዳት የሚያስከትል ስህተት ነው። አማራ ጠላቱን ቀልጥፎ አለማወቁ ዋጋ አስከፍሎታል። አማራ እኮ ግብፅን በግዮን አባይ ውሀ ብቻ ማንበርከክ ይችላል! እንዴ አማራ እኮ ጣልያንን ያንበረከከ ህዝብ ነው።

እናም አማራ ሀያል እንዲሆን አራት ነገሮች የግድ ያስፈልጉታል።
1~ ጠንካራ አእምሮ
ምሳሌ እንደ እራኤላውያን ~ ጠቅላላ የእስራኤል ቆዳ ስፋት ሰሜን ሸዋን አታክልም ። በህዝብ ቁጥር ካሰላናቸው ደሞ የአዲስ አበባ ከተማን ነዋሪ አያክሉም ነገር ግን የአለምን ፖለቲካና ኤኮኖሚ የሚዘውሩት እነዚህ ህዝቦች ናቸው። ለዚህ ምስጢሩ አንድ እና አንድ ነው ይሄውም በትምህርት የዳበረ አእምሮ ባለቤት ህዝቦች መሆናቸው ነው።
2~ ጠንካራ ኢኮኖሚ (እንደ አሜሪካውያን)
3~ ጠንካራ መከላከያና ብሄርተኛ ሰራዊት(እንደ ሩሳውያን)
4 ~ ጠንካራ ነፃ የአማራ ሚዲያ(እንደ አሜሪካው CNN)።
እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ከሞላ ጎደል ያንድ ሀገር የጥንካሬ መስፈርት ናቸው ። የአማራ ህዝብ እነዚህን ተሞክሮዎች በመውሰድ የቀደመ ገናናነቱን የማይመልስበት ምክንያት አይኖርም።

እርግጥ ዛሬ አማራ ህዝብ የወደፊቱዋ ኢትዮጵያ እርሾ ይሆኑ ዘንድ ዘመን የሚሻገር ህልም አስጨብጦ በመንፈስ የወለዳቸው ልጆች ዛሬ ህልሙን እውን ለማድረግ ቆርጠዋል። በውነት ቃሉን ጠብቀው፤ እርሱን ብለው በማያሻማ ቋንቋ አፎቱን ከሰገባው አዉጥተዋል። እኛም ያባቶቻችን ልጆች ነን ብለዋል።
ዛሬ አማራዊነት ከስጋና ከደም በላይ ነዉ። አማራዊነት መንፈስ ነው። ሚሊዮኖች ሊሞቱለት ከፊት የቆሙለት አይዲዮሎጅ ነው።። አማራዊነት በጥቁሩ ሰማይ ላይ እንደ አጥቢያ ኮከብ የሚያንጸባርቁ ኮኮቦች ። በአማራዊነት መንፈስ ላይ ፀሃይ አትጠልቅም እኛም ቅዤት የሌለበት ጤነኛ የአማራን ነፃነት እናልማለን።

‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚነሳው ሠርተፊኬት ሰጥተንና ሸልመን ስናረጋግጥ ነው››

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማውጣትና በማስፈጸም ሰላም የማስፈንና የዜጎችን መብት የማረጋገጥ ሥራ፣ በሕዝቦች የተመሰከረለት መሆኑን የአዋጁ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ባቀረበው ሪፖርት አስታወቀ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ወርዶፋና ሌሎች አባላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም በተመለከተ ያደረጉትን ቁጥጥርና ክትትል ማክሰኞ መጋቢት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ለፓርላማ አቅርበዋል፡፡

በአገሪቱ የተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ በመንግሥት፣ በግልና በሕዝብ ንብረት ላይ አስከፊ ውድመት ማድረሱንና በወቅቱ ባይገታ የሚያደርሰው ውድመት የከፋ ሊሆን እንደሚችል አቶ ታደሰ አስረድተዋል፡፡

ሁከትና ብጥብጡ ድንገተኛ በመሆኑ አንዳንድ የአቅርቦት ችግሮች ተከስተው እንደነበር፣  ከዚህ ውጪ በመንግሥት በኩል የተከናወነው ሥራ ውጤታማ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር የዋሉ ዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለመጠበቅና ሰላምን ለማረጋገጥ የተከናወነው ሥራ ውጤታማ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በመጀመሪያዎቹ ወራት በተወሰኑ አካባቢዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ታይተው እንደነበር አክለዋል፡፡

‹‹በምርመራ ወቅት የተወሰኑ ፖሊሶች በማስፈራራትና በማስገደድ የእምነት ቃል እንዲሰጥ ያደርጉ ነበር፡፡ ድርጊቱ የታየው በአዋሽ ሰባት፣ በአላጌና ዲላ ባሉት ማዕከላት ነው፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቦርዱ ከየማዕከላቱ ከሚገኙ ተጠርጣሪዎች ጋር ባደረገው ውይይትና ከሚመጡ ጥቆማዎች፣ ግለሰቦች በቂም በቀል እንደታሰሩና አንዳንዶች ደግሞ በወንጀል ቢሳተፉም ያልተያዙ መኖራቸውን መገንዘብ በመቻሉ ለኮማንድ ፖስቱ በምርመራ እንዲጣራ መላኩን አስረድተዋል፡፡

በዳለቲ ማረሚያ ቤትና በይርጋለም አፖስቶ ማሠልጠኛ በቂ የሕክምና አገልግሎት አለመኖሩ ታይቶ እንደነበርና ቦርዱ ባደረገው ሁለተኛ ክትትልና ቁጥጥር ወቅት ችግሩ መፈታቱን ገልጸዋል፡፡

በሁለተኛው ዙር ክትትል ወቅት በሁሉም ማዕከላት ችግሮቹ የተፈቱ ቢሆንም፣ በመጀመሪያው ዙር በአዋሽ ሰባትና ብር ሸለቆ የተሃድሶ ማዕከላት ከመጠጥ ውኃ አቅርቦት ጋር የተያያዘ ችግር መስተዋሉን ገልጸዋል፡፡

በዳለቲ ማረሚያ ቤትና በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም፣ የጤና ችግር ያለባቸውና በዕድሜ የገፉትን ተጠርጣሪዎች ለይቶ ቶሎ መልቀቅ ላይ መዘግየት በመኖሩ መፍትሔ እንዲሰጥበት ለኮማንድ ፖስቱ ምክረ ሐሳብ ቀርቧል ብለዋል፡፡

አቶ ታደሰ፣ ‹‹ከእንግዲህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚነሳው ሠርተፊኬት ሰጥተንና ሸልመን ስናረጋግጥ ነው፡፡ ብዙ ሊስተካከሉ የሚችሉ ጉዳዮች አሉ፡፡ እኛ የወደቁ ተቋማትን ገና እየገነባን ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‘አዋጁ መቀጠል አለበት’ የሚሉ ሐሳቦችን ከሕዝብ አስተያየት መቀበሉንም ቦርዱ ለፓርላማው ገልጿል፡፡

‹‹በመንግሥት በኩል የተሠራው ሰላምን የማስፈንና የዜጎችን መብት የማረጋገጥ ሥራ በሕዝቡ የተመሠከረለት ነው፤›› ብለዋል አቶ ታደሰ፡፡ ተመሳሳይ ሐሳቦች በፓርላማው አባላት ቢነሱም፣ በዋናነት ቦርዱን የገጠሙት ችግሮች ምንድን ናቸው የሚለው ጥያቄ ለቦርዱ አባላት ቀርቧል፡፡ በበጀትም ሆነ በትብብር እክል እንዳልገጠማቸው አቶ ታደሰ ገልጸው፣ አምቦ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩትን ለመጎብኘት ደብዳቤ እንዲያመጡ ከመጠየቃቸው ውጪ የገጠማቸው የጎላ ችግር እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ተሃድሶ ወስደው የተለቀቁ 26,659 መሆናቸው ተገልጿል፡፡ 4,966 ደግሞ ለሕግ እንዲቀርቡ በመለየታቸው በሕጋዊ መንገድ እየተስተናገዱ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሐሙስ መጋቢት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ በፓርላማ የመንግሥት አስተያየትና ምላሽ ይሰማል፡፡ በተጨማሪም አዋጁ ይራዘም ወይም አይራዘም እንደሆነም ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዜና- ሪፖርተር

አግድም ያደገው የጎሳ ፖለቲካችን! (ክፍል አንድ) – በመስከረም አበራ

አስራ ሰባት አመት በበረሃ የተመላለሰው ህወሃት/ኢህአዴግ የተራበውን ስልጣን በእጁ ካደረገበት 1983 ዓ.ም ወዲህ በሃገራችን ሁለመና የናኘው የጎሳ ፖለቲካ አሁን አሁን ‘መጨረሻችን ምን ይሆን?’ የሚያስብል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ጎረቤት ሱማሌን ዝንጀሮ ያየው ክምር ያስመሰለው፣ ደቡብ ሱዳንን የዋይታ ምድር ያደረገው፣ ሩዋንዳን ከልብ የማይወጣ ፀፀት ያሸከመው የጎሳ ፖለቲካ እኛም ቤት አግድም እያደገ ነው፡፡የጎሳ ፖለቲካችን አግድም አደግነት በገለጫው ብዙ ነው፡፡

አያት ቅድም አያቶቻችን ኢትዮጵያ የተባለችውን ሃገር ከነክብሯ ለመጭው ትውልድ ለማስረከ ያደረጉትን ከአእምሮ በላይ የሆነ ክቡር እና ድንቅ መስዕትነት ማቃለል፣ማሳነስ፣ ማጣጣል ወይም ሌላ ትርጉም መስጠት የጎሳ ፖለቲካችን አግድም አደግነት ሁነኛ መገለጫ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ተጠራርቶ  ለሃገሩ ነፃነት ሲል  የሞት ገበያ ላይ የዋለበትን የአድዋ ድል በማክበር ፋንታ የጎሳ ፖለቲካ የለከፋቸው የእኛ ወንድም እህቶች የራሳቸውን አሞሌ ሊያቃልሉ ይታጠቃሉ፡፡ግማሾቹ ‘የአድዋ ድል ከሁለት ጨቋኝ አንዱን የመምረጥ ጉዞ ነበር እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ጣዕምገብቶት ያደረገው አልነበረም’ ሲሉ ሌሎቹ ‘የአድዋ ድል ባይኖር ኖሮ ኤርትራዊያን ሆድ ብሷቸው አይገነጠሉም ነበር’ ይላሉ፡፡ሌላው የባሰበት ደግሞ ‘የአድዋ ድል የአፄ ምኒልክን ጨቋኝነት የጋረደ ክፉ ጥላ ነው’ ባይ ነው፡፡

የጎሳ ፖለቲካችን አግድም ማደግ ሌላ መገለጫ ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትን ቀላል እና ርካሽ በሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ሆይ ሆይታ ብቻ ድምጥማጡን ለማጥፋት ከንቱ መፋተር ነው፡፡ ብዙዎች የሞቱለትን፣ እልፎች በኢህአዴግ እስር ቤት አሳር መከራ የሚያዩለትን ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ማጓጠጥ፣ ዋጋውን ማቃለል፣ አመጣጡን አኮስሶ የፈረደበት የአማራ ህዝብ ብቻ ንብረት ማድረግ  ከጀማሪ የማህበራዊ ሚዲያ ፖለቲከኛ  እስከ ፕሮፌሰር ተብየ የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች የሚላዘን የማይቀየር ችኮ ሙዚቃ እየሆነ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያዊነትን መጥላትም ሆነ መካድ የማንኛውም ግለሰብ መብት ሆኖ ሳለ ‘ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም’ ማለት ግን ‘እኔ ያልሆንኩት እና ያልወደድኩት ነገር ህልውና የለውም’ እንደማለት ያለ ራስን ያለመግዛት ምልክት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቆምኩለት የሚሉትን ጎሳ ማንነት በተመለከተ አሉታዊ ለመሰላቸው ነገር ሁሉ እንደሚታመሙት  እንደዛው እነሱ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትን ላይ ክፉ ደግ ሳይመርጡ አፋቸውን ሲያላቅቁ ራሱን ከኢትዮጵያዊ ዜግነት ብቻ ጋር ያጋመደውን  ዜጋ ሁሉ እንደሚያሳምሙ ማወቅ አለባቸው፡፡ የስሜት ፈረስ በጋለባቸው ቁጥር በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ላይ የመደንፋት  መብቱ እንደሌላቸውም ማወቅ አለባቸው፡፡እስከ ሽበት ሽምግልና የተማሩት ትምህርት ሌላው ቢቀር ይህን ሊገልፅላቸው ግድ ነው፡፡

ረዘም ያለ ዘመን እንደማስቆጠሩ ቆምኩለት ለሚለው የኦሮሞ ህዝብ ይህ ነው የሚባል ተግባራዊ ነጥብ ማስቆጠር ያልቻለው የኦሮሞ ብሄርተኞች እንቅስቃሴ የተሳካለት ነገር ቢኖር ማናቸውንም የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅሞ ጩኽት ማበርከቱ ላይ ነው፡፡ የጩኽቱ ማድመቂያ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ላይ ያለው የብዙሃንነት ነገር ነው፡፡ ተግባር ይበልጥ በሚሰምርባት በዚች አለም ተግባሩ ላይ እምብዛም የሆኑት የኦሮሞ ብሄር ፖለቲካ አቀንቃኞች ‘ብዙሃን ነን’ የሚለውን ትርክታቸውን ተንተርሰው ብዙ ይተልማሉ፡፡ መገንጠሉን ይሞክራሉ! ለዚህም ቻርተር ከትበው ወገናችን ያሉትን ብቻ ታዳሚ ያደረጉ፣ አስገራሚ ንግግር የተደረገባቸው ተከታታይ ዝግ ስብሰባዎች ያደርጉ ይዘው ነበር፡፡

የእነዚህ ስብሰባዎቹ ተፈጥሮ፣የተብላሉባቸው ሃሳቦች፣የመግለጫዎቹ ይዘት የብሄር ፖለቲካችን አካሄድ የደረሰበትን እንዳይሆን የሆነ ጉዞ አመላካች ነበሩ፡፡ በስደት ላይ ያሉ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ ተሰብስበው ‘ኢትዮጵያን አፈራርሰን የኦሮሚያ ሪፐብሊክን እንገነባለን፤ የኦሮሚያን ሪፐብሊክ መገንቢያው ብቸኛው ወለልለም የኢትዮጵያ ፍርስራሽ ነው’ ተብሎ ሲታዎጅ ‘በሃገርቤት ያለውም ሆነ በስደት ያለ ነገር ግን በስብሰባው ያልታደመ ኢትዮጵያዊነቱን የሚወድ ኦሮሞ የለም ወይ?’ ብሎ ለማሰብ የጎሳ ፖለቲካው አግድም አደግነት አይፈቅድም፡፡ በዘሁ ጉደኛ ስብሰባ በአይን የሚታይ ወታደር በሌለበት፣ስለትጥቅ ትግል ቀደም ብሎ ባልተነሳበት ሁኔታ ባለ አራት ወታደራዊ እዝ ጣቢያዎችም እንደሚዋቀሩ ታውጆ፣ ለሰላማዊ ትግል የሚታሰር የሚፈታውን ኦቦ በቀለ ገርባን የወታደራዊ እዞቹ ራስ አድርጎ ሲሾም ቢያንስ በኢህአዴግ እስርቤት ላለው አቶ በቀለ ገርባ ሌላ የክስ አንቀፅ ማዋጣት እንደሆነ ለማሰብ የጎሳ ፖለቲካችን ደመነፍሳዊ ሩጫ ስክነት አይሰጥም፡፡ ተግባሩ ላይ ቄሱም ዝም መፅሃፉም ዝም ሆነ እንጅ በዛ ሰሞን ‘ኦሮሚያ የራሷ ወታደራዊ ሃይል ኖሯት ነው ከሌሎች ኢትየጵያዊያን ጋር መነጋገር ያለባት፤ሌሎቹን ክልሎችም የምንመክረው ይህንኑ ነው’ ብሎ ነበር የወታደራዊ እዙ ምክትል ተደርጎ የተሰየመው አቶ ጃዋር መሐመድ፡፡

 

የ “ብዙሃን” እና “ታላቅ ህዝብነት” ተረክ

የኦሮሞ ብሄርተኘነትን የሚያቀነቅኑ ልሂቃን ፍላጎት ለዘብ ሲል ኦሮሞ የገነነባት ኢትዮጵያን መመስረት አለያም ኦሮሚያን ገንጥሎ የኦሮሚያ ሪፐብሊክን መመስረት እንደሆነ ከንግግራቸው መረዳት ቀላል ነው፡፡ የዚህ ክርክር መነሾ አንድም የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ  ሲበደል ኖሯል የሚል ሲሆን ሌላም የኦሮሞ ህዝብ በሃገሪቱ የሚይዘው የቁጥር ብዙህነት እና በክልሉ ይገኛል የተባለው ግዙፍ የተፈጥሮ ሃብት ነገር ነው፡፡እነዚህ ክርክሮች ጥያቄ አያጣቸውም፡፡

የኦሮሞ ዘውጌ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ ልሂቃን የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለው ድርሻ መበደል የበዛበት እንደሆነ እርግጠኞች በመሆናቸው የቂም ፖለቲካ በማፋፋሙ ላይ ይበረታሉ፡፡ የሰፈነባቸው የተበዳይነት ስነ-ልቦና በራሳቸው በኩል እንደ እምቦቃቅላ ህፃን ሁሉም እንዲያባብላቸው የመፈለግን ዝንባሌ ሲያላብሳቸው በሌላው ላይ(በተለይ በኢትዮጵያ ብሄርተኝነት አቀንቃኞች ላይ) ደግሞ የፈለጉትን ክፉ ደግ የመናገር መብት ያላቸው አድርጎ እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለው ድርሻ መበደል ብቻ ነው የሚሉ አሳቢዎች ይህንኑ ባይተዋርነታቸውን የሚደግፍላቸው ከሚመስላቸው ቦታ እመር ብለው  ታሪክን ይተርካሉና የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወራሪ ሆኖ የቆየበትን ዘመን ባላየ ያልፉታል፡፡ይህ እንደዋዛ የሚያልፉት የታሪክ እውነታ ግን አሁን ብዙሃን ነን ለሚለው ተረካቸው መሰረት የጣለ በመሆኑ እነሱ እንደሚፈልጉት በሽፍንፍን መታለፍ የሌበት ነገር ነው፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የሰፈረበት መሬት የኢትዮጵያን አብዛኛ ክፍል የሚይዝ እንደሆነ ጠቅሰው፣ ክልሉ የያዘው የተፈጥሮ ሃብትም አያሌ እንደሆነ ተናግረው ‘ታላቅ ህዝብ ነንና የኢትዮጵያን ሁለመና መዘወር አለብን’ ለሚሉ የኦሮሞ መብት አቀንቃኞች መቅረብ ያለበት ወሳኝ ጥያቄ እድሜ አለሙን ሲበደል ኖረ የሚሉት የኦሮሞ ህዝብ አሁን የሚኖርበትን ሰፊና ለም መሬት የያዘው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ መልሱ የታወቀ ቢሆንም ለመድገም ያህል በመካከለኛው ዘመን ማብቂያ አካባቢ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ በተከሰተው የህዝብ ቁጥር መጨመር የተነሳ የኦሮሞ ህዝብ ሃይልን ተጠቅሞ በተለያየ አቅጣጫ ባደረገው በግዝፈቱ በአፍሪካ ጭምር በሚነሳ መስፋፋት ነው፡፡ በመስፋፋት የተያዘን መሬት ይዘውት እንደ ተወለዱት የአካል ክፍል የራስ ብቻ አድርጎ፤መሬቱ በያዘው የተፈጥሮ ሃብት ሲኩራሩ፣ ‘ብዙሃንነት ያለኝ በመሆኔ የሃገሪቱን ሁለመና ካልዘወርኩ እገነጠላለሁ’ ሲባል ታሪክን ወደኋላ ቆጥሮ የኦሮሞ ህዝብ ወደዚህ መሬት ከመስፋፋቱ በፊት መሬቱ ላይ እንኖር ነበር የሚሉ ሌሎች ህዝቦች ክርክር ቢያነሱ ለመልሱ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

ሌላው ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ በመስፋፋት የያዘው መሬት የራሱ ንብረት ነው የሚሉ የኦሮሞ ብሄርተኝነት አቀንቃኞች የኦሮሞ ህዝብ በመካከለኛው ዘመን እንዳደረገው ባለ መስፋፋትም ሆነ በተለያየ መንገድ ኦሮሚያ ላይ ሰፍረው የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ህዝቦችን  ሲፈልጉ የሚያፈናቅሉ ሲሻቸውም ወደ ገደል የሚወረውሩ የመሆናቸው ነገር ነው፡፡ መስፋፋት ባለቤትነትን ካጎናፀፈና የኦሮሞን ህዝብ በመስፋፋት የያዘው መሬት ባለቤት ዳደረገው ከኦሮሞ ሌላ ኦሮሚያ ላይ የሰፈረ ህዝብ የሰፈረበት አካባቢ ባለቤት የማይሆነው ለምንድን ነው?! በኦሮሚያ መገንጠል አለመገንጠል፤በኦሮሞ ልሂቃን  የኢትዮጵያን ፖለቲካ በዋናነት የመዘወር አለመዘወር ለተተኪ አምባገነንነት ወንበር በመቋመጥ ዙሪያ ያለው ሃሳብ ሳይደመጥ እንዲጨፈለቅ የሚፈረድበት በየትኛው ዳኛ ነው?! ኦሮምኛ ሳይናገር በኦሮሚያ ክልል መገኘቱ ብቻ ወንጀል ሆኖ ወደገደል ያስወረወረው፣ ኮሽ ባለ ቁጥር ስጋት የሚወርሰው ባይትዋር የመሆኑ ነገር እንደትክክል የሚወሰደውስ እንዴት ባለ ፍርድ ነው?!

እዚህ ላይ ትልቅ ሃቅ ይፋለሳል! የኦሮሞ ህዝብ በታሪክ አጋጣሚ በሃይል ተስፋፍቶ በሰፈረበት ለም መሬት ላይ ከተፈጥሮ ቱርፋት ላይ እየተጠቀመ፣ እንዳሻው እያመረተ መኖሩ አልበቃ ብሎ መሬቱን እስከመገንጠል መብት እንዳለው የሚከራከሩ ሰዎች ለሌላ ብሄር ሲሆን ኦሮሚያ ላይ ሰፍሮ መኖርን እንኳን ሊከለክሉ ሲቃጣቸው ሚዛናዊነታቸውን ያጣሉና በሌላው ብሄር ዘንድ እንደ ስጋት ቢቆጠሩ አይገርምም፡፡አሁን አሁን ልጆቻቸው በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች  ሲመደቡ የሚያለቅሱ ወላጆች እየበረከቱ የመጡት ለዚሁ ነው፡፡ ‘ኦሮሞ ሲሞት ሌላው ለምን ዝም ይላል?’ ለሚለው ጥያቄ ግማሽ መልስ ያለውም እዚሁ አሳቤ ውስጥ ነው፡፡

የኦሮሞ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ ዜጎች መበደል ስነ-ልቦና ለራስ በማዘኑ ላይ ብቻ አቁሞ አስቀርቷቸው ይሄን ሁሉ ሃቅ ተረጋግተው በሚዛናዊ የህሊና ፍርድ እንዳያዩት ሳያደርግ አልቀረም፡፡ ለዚህም ቢሆን ወሳኙ ነጥብ ፊውዳሊዝም ለረዥም ዘመን ተንሰራፍቶ በኖረባት፣የሰብዐዊ መብት እና የዲሞክራሲ ጉዳይ ድሮ ቀርቶ ዘንድሮ ውሃው ባልሞቀባት ሃገር  ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተበደለ ማነው? የሚለው ነው፡፡የበደል ውድድር ሚዛን ይውጣ ከተባለ ደግሞ ሁሉም የጎሳ ፖለቲከኛ የመጣበት ጎሳ መዓት እንደወረደበት አድርጎ ማሰቡ አይቀሬ ነው፡፡ በጋራ ወደፊት ለመራመድ የድሮው የበደል ዶሴ ክብደት ቅለት መጣራት ካለበት ሌላው  ህዝብም የኦሮሞ ህዝብ ሲስፋፋ አደረሰብኝ የሚለውን በደል ለመስማት የመዘጋጀት እርጋታ ያስፈልጋል፡፡እዚህ ስክነት ላይ ከተደረሰ ደግሞ አፄ ምኒልክ የሚብጠለጠሉበትና ኢትዮጵያ ተሰርታ ያለቀችበት የተስፋፊነት ወንጀል በመካከለኛው ዘመን ገንፍሎ ሃገሪቱን አጥለቅልቆ በነበረው የኦሮሞ ህዝብ ቤትም እንዳለ ለማዎቅ ይቻላል፡፡ጦርነት እና መጋደል የኦሮሞን ህዝብ ጨምሮ ሁሉም ተስፋፊ የሚያደርገው ልማድ እንጅ አፄ ምኒልክ እና ወታደሮቻቸው ብቻ የኦሮሞን ህዝብ መከራ ለማሳየት አቅደው ያደረጉት ነገር እንዳልሆነ ለመረዳት ስክነት ይጠይቅ ይሆናል እንጅ ይሄን ያህ ውስብስብ ነገር አይደለም፡፡

ሁለተኛው የኦሮሞ ብሄርተኝነት አቀንቃኞች ክርክር የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ብዙ በመሆኑ ወደፊት የምትመሰረተዋ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ህዝብን ጥቅም ያስቀደመች መሆን አለባት የሚለው ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ብዛት የማይካድ ሆኖ ሳለ በዚህ አውድ ብዙሃንነት የተተረጎመበት መንገድ ከዘመናዊው የዲሞክራሲ መርህ እሳቤ አንፃር ሲገመገም ስህተት ያዘለ ነው፡፡ አሁን አለማችን በደረሰችበት የስልጣኔ ደረጃ ሳቢያ የተወሳሰበውን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ ስንክሳር አቻቻይ በሆነ ሁኔታ ለማስኬድ ዲሞክራሲያዊ ፖለቲካዊ ዘይቤ ፍፁም ነው ባይባልም ተሻይ እንደሆነ የሚያከራክር ነገር አይደለም፡፡በዲሞክራሲያዊ የፖለቲካዊ ዘይቤ ብዙሃንነት የሚበየነው ተመሳሳይ ቋንቋን በመናገር ሳይሆን ተቀራራቢ ሃሳብን በመጋራት ነው፡፡ በሌላ አባባል የብዙሃንነትን  ግዝፈት የሚያገኙ ሰዎች በልበ-ልቦናቸው መርምረው በያዙት አቋም እና በተስማሙበት ሃሳብ ምስስል/ቅርርብ እንጅ መርጠው ባልተወለዱበት ፣አውጥተው አውርደው እንሁን ብለው ባልሆኑት የብሄር ተመሳሳይነት አይደለም፡፡

ሳይንሳዊ እና ዘመናዊ በሆነው የዲሞክራሲያዊ አሰራር እሳቤ መሰረት ቋሚ ብዙህነት የሚባል ነገር አለመኖሩ ሌላው የኦሮሞ ዘውጌ ፖለቲከኞችን የብዙሃንነት ክርክር አፍራሽ እሳቤ ነው፡፡ በአንድ ሃሳብ ላይ ተስማምተው ለተወሰነ ሃሳብ ሲሆን ብዙሃን በመሆን ሃሳባቸው ገዥ ሃሳብ እንዲሆን ያደረጉ ሰዎች በሌላ ሃሳብ ላይ ሊለያዩ ስለሚችሉ የቀደመው ብዙሃንነታቸው ፈራሽ ይሆናልና የሰዎች ብዙሃንነት እንደሃሳቦች ተለዋዋጭነት የሚወሰን እንጅ ቋሚነት ያለው ነገር አይደለም፡፡ ስለሆነም ሰዎች አንድ አይነት ቋንቋ ስለተናገሩ ብቻ ሁሌ በአንድ ልብ አስበው በአንድ አፍ የሚያወሩ የዘላለም ማህበርተኞች አድርጎ ማሰቡ የሚያፈነግጠው ከዲሞክራሲያዊ እሳቤ ብቻ ሳይሆን ከሰው ልጅ ተፈጥሮም፤አሁን አለማችን ከደረሰችበትሁለንተናዊ ውስብስቦሽ አንፃር የሰውልጅ ማንነት እና ፍላጎት ከሚነሳበት በርካታነት ጭምር ነው፡፡ እንዲህ በተወሳሰበች አለም የሰዎችን የማንነት ክር በበረከተበት ዘመን  አንዷን የማንነት ክር(ቋንቋን) ብቻ ስቦ አውጥቶ ከአቅሟ በላይ የሁሉ ነገር ወሳኝ ማድረግ ልክፍት የዘውግ ፖለቲከኞ ወደ ስልጣን መንደርደሪያ መንገድ ካልሆነ አዟዙሮ የማሰብ ችግር ይሆናል፡፡

የቁጥር ብዛትን ተንተርሶ ትልቅ ህዝብ ነን የሚለው በአብዛኛው በአማራ እና በኦሮሞ ዘውግ ፖለቲከኖች ዘንድ የሚደጋገመው ተረክም ከመሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶች ጋር ጠብ ያለው ንግግር ነው፡፡ ትልቁን ፖለቲከኛ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ ብዙ ፖለቲከኞች የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፋንታ በጎ ለማድረግ ሲሉ በሚያነሱት ምክረ-ሃሳብ የሚያነሳሱት የአማራ፣የኦሮሞ እና የትግሬ የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኖች ሊያደርጉት ስለሚገባ ነገር ነው፡፡ አማራና ኦሮሞ በዛው በመከረኛ ብዙ ቁጥርነት ነው ቢባል እንኳን የትግራይ ልሂቃን ደግሞ ጠብመንጃ አንግተው አንጋች ማበርከታቸው ከብዙ ቁጥርነት ታስቦላቸው መሰለኝ በሶስተኝነት መነሳት ያለበት ባለ ብዙ ቁጥሩ የሶማሌ ህዝብ ተዘሎ እነሱ የተተኩት! ይህ አስተሳሰብ አንድም ለኢትዮያዊነቱ ብዙ ያዋጣውን አሁንም በኢትዮጵያ ላይ ክፉ ሲያወራ የማይሰማውን የአፋር፣የደቡብ፣ የጋምቤላ ወዘተ ህዝቦች ከምንም ያልቆጠረ ክፉ አግላይ አስተሳሰብ ከመሆኑ የተነሳ እነዚህ ሰዎች ይህን ምክረ-ሃሳብ ሲሰሙ ምን ይሰማቸዋል ተብሎ ተዟዙሮ ያልታሰበበት ግንፍልተኛ እና እብሪተኛ አካሄድ ነው፡፡ ሁለተኛው የዚህ እሳቤ ችግር እራሱን ከማንም ዘውግ ጋር የማይፈትል፣ከፍ ሲል ሰው ነኝ ዝቅ ሲል ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚቆጥረውን ዜጋ በምድር ላይ ያልተፈጠረ የሚያስመስል አንድ ስማቸውን የረሳሁት ፈረንጅ  በአንድ ወቅት ትዝብታቸውን ሲያስቀምጡ “ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካ ጎሳ ነው፤ ጎሳ ደግሞ ቋንቋ ነው” ያሉትን የሚያጠናክር አስተሳሰብ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ፖለቲካ ዘር እና ቋንቋ ብቻ አይለም! ይልቅስ በሃሳብ ላይ የቆመ እልፍ ያለ ፖለቲካ  እሩቅ ያስኬዳልና እርሱ ለኛ ያስፈልገናል!  ለወደፊቷ ኢትዮጵያም የሚበጀው ይሄው ነው፡፡

በመስከረም አበራ(e-mail address- meskiduye99@gmail.com)

የዴሞክራሲ አብዮትን “በኢኮኖሚ አብዮት” ማጨናገፍ አይቻልም!

 

ባለፈው ሳምንት “የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት፡ በስህተት ላይ ስህተት በመድገም ስህተትን ማረም” በሚል ርዕስ አንድ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። በፅሁፉ ዙሪያ ከተሰጡኝ አስተያየቶች ውስጥ በአብዛኛው “ፅሁፉ የኢኮኖሚ አብዮቱን ዓላማና ግብ በትክክል አይገልፅም” የሚሉ ነበሩ። በመሆኑም ጉዳዩ በዝርዝር ለማብራራት እየተዘጋጀሁ ሳለ የአማራ ክልል ተመሣሣይ የኢኮኖሚ አብዮት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የሚገልፁ ዘገባዎች ወጡ። በዘገባው መሰረት የአማራ ክልል “ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር” የተሰኘ ግዙፍ አክሲዮን ማህበር እየተቋቋመ መሆኑንና በተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች 22 ፕሮጀክቶችን ለይቶ ወደ ሥራ ሊገባ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ ፅኁፍ በሁለቱ ክልሎች “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል የተጀመረውን እንቅስቃሴ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ጋር አያይዤ በዝርዝር ለመዳሰስ እሞክራለሁ።

በመሰረቱ ባለፉት ጥቂት አመታት የኢትዮጲያ የውጪ ንግድ እያሳየ ያለው ማሽቆልቆል እየተባባሰ መጥቷል። በዘንድሮው ግማሽ ዓመት ከውጪ ንግዱ ዘርፍ ይጠበቅ የነበረው የውጪ ምንዛሪ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተገኘው ግን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ሊገኝ ከታቀደው 56% ብቻ ነው። በ2008 የበጀት ዓመት ሊገኝ ከታቀደው ውስጥ 67.7% ብቻ የተገኘ ሲሆን ይህም በ2007 የበጀት ዓመት ከተገኘው በ139.3 ሚሊዮን ዶላር ያነሰ ነበር።

ከጥቂት ቀናት በፊት መንግስት ችግሩን ለመፍታት ከላኪዎች ጋር ስብሰባ አድርጎ ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) መሪነት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ለውጪ ንግዱ ማሽቆልቆል በምክንያትነት ከተጠቀሱት ነጥቦች ውስጥ የመንግስት ቢሮክራሲያዊ አሠራር የፈጠራቸው ችግሮች ትልቁን ድርሻ ይዘዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በሀገሪቱ የተከሰተው የውጪ የፀጥታ ችግር፣ በፀጥታው መናጋት የተፈጠረው ሥጋት ለውጪ ንግዱ መቀዛቀዝ ዋቢ መደረጋቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል።

በጠ/ሚ ፅፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጲያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳነት አቶ ሰለሞን አፈወርቅ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፤ “ዋናው መሰረታዊ ለውጥ ትርፍ ምርት እንዲመጣ ማድረግ፣ አዲስ ምርት ወደ ኢኮኖሚው ማምጣት መቻል እንዲሁም ከውጪ የሚገቡ ምርቶች የሚተኩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት መቻል ነው’ ብለዋል። አያይዘውም “ስንዴ ከውጪ እያስመጡ ያንን ለዱቄት ፋብሪካዎች ሰፍሮ በመስጠት ለውጥ አይመጣም” ብለዋል። እንደ እሳቸው አገላለፅ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የግብርና ጥሬ ዕቃዎችን በላክ ላይ የተመሰረተውን የውጪ ንግድ ወደ ኢንዱስትሪ ምርቶች ማሸጋገር አስፈላጊ ነው። ነገር ግን፣ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው ሪፖርት የኢንዱስትሪ ምርቶች የውጪ ንግድ እየቀነሰ መሆኑንና ለዚህም የግብዓት አቅርቦት፣ የጥራት ችግር፣ የመንግስት አገልግሎቶች የአሰራር ቅልጥፍና አለመኖር እና የገዢ ኩባኒያዎች በተለያየ ምክንያቶች ውል መሰረዝን በምክንያትነት ጠቅሷል።

በአጠቃላይ፣ የሀገሪቱ የውጪ ንግድ በየአመቱ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት የተጠቀሱትን ነጥቦች በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል። አንደኛ፡- የመንግስት ቢሮክራሲያዊ አሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች፣ ሁለተኛ፡- በሀገሪቱ የተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር፣ ሦስተኛ፡- አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ናቸው።

በተለይ የውጪ ንግዱ ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ ምክንያት ውጥረት ውስጥ የገባው የኢህአዴግ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 14/2009 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ “የአማካሪ ምክር ቤት” ለማቋቋም ወስኗል። ከዚህ ጎን-ለጎን፣ የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በየፊናቸው “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን ለይተው ወደ ስራ ገብተዋል። ስለዚህ፣ መንግስት በፌደራልና በክልል ደረጃ የሚያደርገው እንቀስቃሴ ከውጪ ንግድና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማት ጋር በተያያዘ የተጠቀሱትን ችግሮች በዘላቂነት መቅረፍ ይችላል? ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ከላይ የተጠቀሱት ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከወቅታዊ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ አያይዞ መመልከት ያስፈልጋል።

በተለይ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ ለተፈጠረው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር ዋናው ምክንያት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የታየው የአመፅና ተቃውሞ እንቅስቃሴ ነው። ከ60% በላይ የሀገሪቱ ሕዝብ በሚኖርባቸው እነዚህ ሁለት ክልሎች የተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር የኢህአዴግ መንግስትን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንዲያውጅ አስገድዶታል። ለአመፅና ተቃውሞ አንቅስቃሴው ዋናው ምክንያት የዜጎችን ሕገ-መንግስታዊ መብትና ነፃነት ባለመከበሩ፣ የመንግስት ሥራና አሰራር በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ የእኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በማስነሳት ነበር። ስለዚህ፣ በሀገሪቱ ለተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር ዋናው ምክንያት የኢህአዴግ መንግስት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ማክበርና ማስከበር፣ እንዲሁም በመንግስታዊ ሥርዓቱ ውስጥ የሚስተዋለውን ስር-የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ ስለተሳነው ነው።

 

ሀገሪቱ የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር የተዳረገችበት ምክንያት የኢህአዴግ መንግስት በዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ረገድ ከሕዝቡ የለውጥና መሻሻል ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ ስለተሳነው። ስለዚህ፣ የኢህአዴግ መንግስት መልካም አስተዳደርና ቀጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መገንባት ስለተሳነው፣ እንደ ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል፣ ለንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶችና ድርጅቶች አስፈላጊውን አገልግሎትና ድጋፍ እየሰጠ አይደለም። የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት ከተጠቀሱት ሦስት መሰረታዊ ችግሮች ውስጥ አንደኛው “የመንግስት ቢሮክራሲያዊ አሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር” ነው። ስለዚህ፣ አንደኛው ችግር ዋና መንስዔ ራሱ የኢህአዴግ መንግስት ነው።
በተመሣሣይ፣ በመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ረገድ የሚደረገው ጥረት ሲጨናገፍ ሕዝቡን ለአመፅና ተቃውሞ፣ ሀገሪቱን ለፀጥታና አለመረጋጋት ችግር ዳርጓታል። የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት ከተጠቀሱት መሰረታዊ ችግሮች ውስጥ ሁለተኛው “በሀገሪቱ የተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር” ነው። በድጋሜ ለሁለተኛው ችግር ዋና መንስዔ ራሱ የኢህአዴግ መንግስት ነው።

እስካሁን ድረስ የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ የመጀመሪያ ሁለት ችግሮች ዋና መንስዔ ራሱ የኢህአዴግ መንግስት እንደሆነ ተመልክተናል። በመቀጠል ደግሞ በሦስተኛ ለይ የተጠቀሰው “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግርን የኦሮሚያና አማራ ክልላዊ መስተዳደሮች ተግባራዊ ማድረግ ከጀመሩት የኢኮኖሚ አብዮት ጋር አያይዘን በዝርዝር እንመለከታለን።

የኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተዓምራዊ ለውጥ ያመጣል፣ ለብዙ ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል፣ …ወዘተ በሚል እሳቤ በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ ገብተዋል። ለምሳሌ፣ የአማራ ክልላዊ መስተዳደር “የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበርን” 25 በመቶ ድርሻ የአክሲዮን ድርሻ እንደሚገዛ ተጠቅሷል። በተመሣሣይ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር በኢኮኖሚ አብዮቱ ከሚቋቋሙት የአክሲዮን ድርጅቶች ውስጥ እስከ 35% የአክሲዮን ድርሻ ሊኖረው እንደሚችል በማህበራዊ ድረገፆች ላይ እየተገለፀ ይገኛል። እንደ ማንኛውም መንግስት ሁለቱም ክልላዊ መስተዳደሮች ከሕዝብ ከሚሰበሰበው በስተቀር የራሳቸው የሆነ የገቢ ምንጭ የላቸውም። ስለዚህ፣ ሁለቱም የክልል መንግስታት ከሕዝቡ በግብርና ቀረጥ መልክ የሰበሰቡትን ገንዘብ የቢዝነስ ተቋማት አክሲዮን ድርሻ ለመግዛት አውለውታል።

በኢኮኖሚ አብዮቱ የሚቋቋሙት በአገልግሎት፣ ማምረቻና ግንባታ ዘርፍ የሚሰማሩ የቢዝነስ ድርጅቶች ናቸው። የአማራና ኦሮሚያ ክልል መንግስታት የእነዚህን ድርጅቶች የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት በኢኮኖሚው ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ ስለመግባታቸው ጥርጥር የለውም። ስለዚህ፣ ይህ ጣልቃ ገብነት የኢህአዴግ መንግስት ከሚያራምደው የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንፃር ምን ያህል ተቀባይነት አለው?፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ከማሻሻል አንፃር ምን አስተዋፅዖ ያበረክታል? ከዚህ ቀጥሎ፣ እነዚህንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እና ከገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት (market economy) አንፃር የአማራና ኦሮሚያ ክልል መንግስታትን ጣልቃ ገብነትና ውጤታማነት በዝርዝር እንመለከታለን።

ከገበያ መር ኢኮኖሚ (market economy) ስርዓት አተገባበር ጋር ተያይዙ ብዙ አከራካሪ ጉዳዮች መኖራቸው እርግጥ ነው። በዋናነት ግን፤ “መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ መግባት የለበትም” እና “መንግስት በተመረጡ የኢኮኖሚ መስኮች ጣልቃ መግባት አለበት” የሚሉት አመለካከቶች የሚጠቀሱ ናቸው። የኢህአዴግ መንግስት የመጀመሪያውን የኒዮ-ሊብራሊዝም አቀንቃኞች አመለካከት እንደሆነ በመጥቀስ “መንግስት በተመረጡ የኢኮኖሚ መስኮች ጣልቃ መግባት አለበት” የሚለውን አመለካከት እንደሚያራምድ ይታወቃል። ስለዚህ፣ የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት በኢኮኖሚው ውስጥ እያደረጉት ያለውን ጣልቃ ገብነት ከኒዮሊብራሊስቶች እይታ ሳይሆን ከራሱ ከኢህአዴግ መንግስት እይታ አንፃር መመልከት ይኖርብናል።

ከላይ እንደተገለፀው፣ የኢህአዴግ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ “መንግስት በተመረጡ የኢኮኖሚ መስኮች ጣልቃ መግባት አለበት” የሚለው ነው። በኢኮኖሚ አብዮቱ በሚቋቋሙት ድርጅቶች አማካኝነት የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ የአገልግሎት፣ ማምረቻና ግንባታ ዘርፎች ውስጥ ጣልቃ በመግባት ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን፣ የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስታት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ጣልቃ መግባት ያለባቸው መቼ ነው?

በገዢው ፓርቲ የኢኮኖሚ ፖሊስ መሰረት መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ መግባት ያለበት “የገበያ ውድቀት” (market failure) ሲኖር ነው። አንዳንድ የዘርፉ ምሁራን ሁኔታውን፤ “Government legitimacy in a market economy arises from market failures” በማለት ይገልፁታል። “የገበያ ውድቀት መቼ ነው የሚኖረው?” ለሚለው ደግሞ አራት ዋና ዋና ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። እነሱም፣ 1ኛ፡- የምርትና አገልግሎቶች ማምረቻ/ማቅረቢያ ወጪ ከተጠቃሚዎች የመክፈል አቅም በላይ ሲሆን (Incomplete markets)፣ 2ኛ፡- የትክክለኛ መረጃ አቅርቦት ችግር ሲኖር (Information failures)፣ 3ኛ፡- የሕዝብ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለመገንባት ሲሆን (Public goods)፣ እና 4ኛ፡- ውጫዊ የሆኑ አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ተፅዕኖዎችን በምርቱ የገበያ ዋጋ መመለስ የማይቻል ሲሆን (Negative/ positive Externalities) ናቸው።

ከላይ ከተጠቀሱት አራት መሰረታዊ ምክንያቶች አንፃር፣ የኦሮሚያና አማራ ክልላዊ መንግስታት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ለመግባት በወሰኑባቸው የአገልግሎት፣ ማምረቻና ግንባታ ዘርፎች “የገበያ ውድቀት (market failure) አለ” ማለት አይቻልም። ምክንያቱም፣ የግልና የማህበር ቢዝነስ ተቋማት በተጠቀሱት የኢኮኖሚ መስኮች ለመሰማራትና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዳቸው የገበያ ችግር የለም። ስለዚህ፣ የሁለቱም ክልል መንግስታት “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ለመግባታቸው የገበያ ውድቀትን በምክንያትነት መጥቀስ አይችሉም። ስለዚህ፣ የአማራና ኦሮሚያ ክልል መንግስታት “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ጣልቃ የገቡት የገበያ ውድቀት በሌለበት ሁኔታ ነው።
የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት የገበያ ውድቀት በሌለበት ሁኔታ በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ መግባታቸው እንደተባለው በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተዓምራዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ? የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት ያዋሉት የሕዝብ ገንዘብ የዘርፉን ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ወደ ተሻለ ደረጃ ያሳድገዋል? በዘርፉ ካሉት የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በምርትና ጥራት ተወዳዳሪ ሆነው ትርፋማ ይሆናሉ? በአጠቃላይ፣ የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት የተጠቀሰውን “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግርን መቅረፍ ይችላሉ? በዚህም፣ እንደተባለው ለብዙ ሺህ የአማራና ኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና አርሶ አደሮች የስራ ዕድልና የገበያ ትስስር ይፈጥራሉ?

በመሰረቱ፣ መንግስት ከምንም ይሻላል እንጂ ከማንም ግን አይሻልም። ምክንያቱም፣ ምንም ነገር ከባዶ ይሻላልና ምንም ዓይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሌለበት የገበያ ውድቀት (market failure) ውስጥ መንግስት ጣልቃ ቢገባ ይመረጣል። ነገር ግን፣ የገበያ ውድቀት በሌለበት መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ሲገባ ግን በፍፁም ውጤታማና ተወዳዳሪ ሊሆን አይችልም። ምን ግዜም ቢሆን መንግስት በምርታማነትና ጥራት ከግል ተቋማት የተሻለ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ፣ የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት የኢኮኖሚ አብዮት ለውጪ ንግድ ማሽቆልቆል ምክንያት የሆነውን “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግር ከመቅረፍ አንፃር የጎላ አስተዋፅዖ አያበረክትም።

የገበያ ውድቀት በሌለበት ሁኔታ የመንግስት ሥራና ድርሻ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ቢዝነስ ተቋማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። በዚህም፣ የመንግስት ዋና የሥራ ድርሻ የፀጥታና አለመረጋጋት ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ሁኔታ መፍጠር እና የመንግስትን ሥራና አሠራር ወደ ላቀ ደረጃ በማሻሻል የተቀላጠፈ የአገልግሎትና ድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋት ነው። የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እንዲያሽቆለቁል በምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ ሦስተኛው “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግር ነው። በመሆኑም፣ ለሀገሪቱ የውጪ ንግድ ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ የሄደበት ምክንያት የፌደራልና ክልል መንግስታት ድርሻና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ስለተሳናቸው ነው። በተለይ የአማራና ኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደሮች እንደ መንግስት የሚጠበቅባቸውን ሥራና ኃላፊነት በሚገባ ባለመወጣታቸው ምክንያት ተፈጠረ ችግር ነው። አሁንም ከህዝብ ከተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት ውጪ በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ በመግባት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

በመጨረሻም፣ አብዛኞቹ የአማራና ኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከላይ ከተገለፀው የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ይልቅ የአብዮቱ ዓላማና ግብ ላይ ማተኮር ይቀናቸዋል። ስለዚህ፣ አብዛኞቹ “የኢኮኖሚ አብዮቱ ከተቀመጠለት ከግብ (objective) አንፃር መታየት አለበት” የሚል መከራከሪያ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ወይም ደግሞ ከላይ በኢኮኖሚ አብዮቱ አማካኝነት የሁለቱ ክልል መንግስታት ጣልቃ በሚገቡባቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ “የገበያ ውድቀት አለ” የሚል መከራከሪያ ሊቀርቡ ይችላሉ። ነገር ግን፣ “Market Efficiency and Government Intervention” በሚል ርዕስ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ በጉዳይ ዙሪያ የሚከተለውን ሃሳብ አስቀምጧል፡-

“Though the presence of, market failure implies that there may be a scope for government intervention, it does not imply that a particular government program aimed at correcting the market failure is necessarily desirable. To evaluate government program one must not only take into account their objectives but how they implement it.” Journal of International Business and Economics, Vol. 3(1), June 2015

በእርግጥ በኢኮኖሚ አብዮት አማካኝነት ለብዙ ሺህ የአማራና ኦሮሚያ ወጣቶች የሥራ እድል እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የተቀመጠው ግብ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን፣ የሁለቱ ክልላዊ መስተዳደሮች በኢኮኖሚው ውስጥ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት መመዘን ያለበት ካስቀመጡት ግብ አንፃር ብቻ ሳይሆን ከፕሮግራሙ አተገባበር ጭምር መሆን አለበት። ለብዙ ሺህ የአማራና ኦሮሚያ ክልል ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር የሚቻለው እንዴት ነው?፣ የመንግስት ዕቅድና ፕሮግራም በምን ላይ ማዕከል ያደረገ ሊሆን ይገባል? ሁለት የዘርፉ ምሁራን “Human Capital and Sustainability” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ እንዴት ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር እንደሚቻልና የመንግስት ዕቅድና ፕሮግራም ትኩረት በምን ላይ መሆን እንዳለበት እንደሚከተለው ይገልጻሉ፡-

“Contrary to popular belief, the principal source of new jobs is social development, not economic policy. Public stimulus programs, manipulation of the money supply and interest rates can certainly have short-term impact, but it is the growth and development of society that serves as the foundation and context for economic growth. Full employment can be achieved by broad-based social strategies that accelerate social development, including measures that improve the quality and quantity of education and training, promote entrepreneurship and self-employment, increase the speed of communication and transportation, encourage research and innovation, and more fully utilize the power of social organization, e.g., the Internet.” Journal of Sustainability ISSN 2071-1050

ከላይ በጥቅሱ ውስጥ እንደተገለፀው፣ ለወጣቶች ተጨማሪ የሥራ እድል ለመፍጠር መሰረቱ “ማህበራዊ ልማት” (social development) ነው። ለዚህ ደግሞ መንግስት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ዋና ትኩረት በሰው ሃብት ልማት ላይ መሆን አለበት። በመሆኑም፣ የመንግስት ሥራና ኃላፊነት፤ ተግባር ተኮር ትምህርትና ሥልጣና መስጠት፣ ሥራ ፈጣሪነትን ማበረታታት፣ የተቀላጠፈ የብድር አገልግሎት መስጠት፣ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አቅርቦት ጥራትና ተደራሽነትን ማሳድግ፣ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ማበረታታት፣…ወዘተ የመሳሰሉ የድጋፍ ተግባራትን በማከናወን በሀገሪቱ ወይም በክልሉ የሰው ኃብት ልማት ማረጋገጥ ነው።

ስለዚህ፣ ለብዙ ሺህ ወጣቶች የሥራ-ዕድል ከመፍጠር አንፃር የመንግስት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ትኩረት ማድረግ ያለባቸው የሰው ሃብት ልማት ነው። ነገር ግን፣ የአማራና ኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ከሰው ሃብት ልማት ይልቅ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ላይ ማዕከል ያደረገ ነው። በመሆኑም፣ የሁለቱም ክልሎች የኢኮኖሚ አብዮት ግቡን አይመታም።

በአጠቃላይ፣ በኢኮኖሚ ውስጥ ለሚስተዋለው ችግር ዋና መንስዔው ያለው የሀገሪቱ ፖለቲካ ነው። የኢትዮጲያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር ደግሞ የኢህአዴግ መንግስት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ማክብር/ማስከበር አለመቻሉ ነው። በተለይ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች እየታየ ያለው ሕዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ዋና መነሻ ምክንያቱ የኢህአዴግ መንግስት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ማክበርና ማስከበር፣ እንዲሁም በመንግስታዊ ሥርዓቱ ውስጥ የሚስተዋለውን ስር-የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ ስለተሳነው ነው። “3ኛው ማዕበል፡ የልማታዊ መንግስት ፈተና” በሚለው ፅሁፌ በዝርዝር እንደገለፅኩት ይህ የአመፅና ተቃውሞ እንቅስቃሴ በትክክለኛው ግዜና ሁኔታ ውስት የተነሳ የዴሞክራሲ አብዮት ነው።

ይህን የዴሞክራሲ አብዮት አስፈላጊውን ለውጥና መሻሻል በማድረግ በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ ከተሳነን ሀገሪቷን ወደ ባሰ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ይከታታል። ሕዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱና ነፃነቱ እንዲከበር፣ የመንግስት ሥራና አሰራር እንዲሻሻል፣ ስር የሰደደው የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲቀረፍና የብዙሃኑን እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ የሚያነሳቸውን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በኢኮኖሚ አብዮት ምለሽ ለመስጠት መሞከር ችግሩን ከማባባስ የዘለለ ፋይዳ የለውም።

በአጠቃላይ፣ አንደኛ፡- የኢኮኖሚ አብዮቱ የዴሞክራሲ አብዮቱን ለማጨናገፍ ያለመ ነው፣ ሁለተኛ፡- የኢኮኖሚ አብዮቱ ግቡን አይመታም፣ ሦስተኛ፡- የኢኮኖሚ አብዮቱ አለመሳካቱ የዴሞክራሲ አብዮቱን መልሶ ያቀጣጥለዋል። ምክንያቱም፣ የዜጎች ሕገ-መንግስታዊ መብትና ነፃነት እስካልተከበረ እና የመልካም አስተዳደር ችግር በዘላቂነት እስካልተቀረፈ ድረስ፣…ወዘተ አሁን በውጪ ንግዱ ላይ እየታየ ያለው ማሽቆልቆል ወደ አጠቃላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ይስፋፋል። የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሲቀዛቀዝ ፖለቲካዊ ችግር ያስከትላል፣ በዚህም ሕዝቡ ለአመፅና ተቃውሞ አደባባይ ይወጣል። ስለዚህ፣ የዴሞክራሲ አብዮት በኢኮኖሚ አብዮት አይጨናገፍም!

አዲስ አበባ በውሃ፣ በመብራት እና በነዳጅ እጥረት እየተሰቃየች ነው

 

(ዘ-ሐበሻ) በአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ የውሃ፣ የመብራት እና የነዳጅ እጥረት ነዋሪዎቿን እያጎሳቆለ እንደሚገኝ ከሃገር ቤት የመጡ መረጃዎች አስታወቁ:: በአዲስ አበባ የውሃ እጥረት ችግር ተባብሶ የቀጠለው ለከተማዋ የውሃ አቅርቦት የሚያገለግሉ ጉድጓዶች በመድረቃቸው ምክንያት መሆኑን የህውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ማስታወቁ ይታወሳል::


መስሪያ ቤቱ ይህ ችግር ተቀርፏል በሚል በመንግስት ሚዲያዎች ቢናገሩም የውሃ እጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተዘግቧል:: በተለይም በአሁኑ ወቅት ጐተራ፣ ሳሪስ አቦ፣ ቂርቆስ፣ ስታዲየም፣ ቦሌ፣ ሃያ ሁለት፣ ቤተ-መንግሥት አካባቢ፣ የካ ጣፎ ኮንዶሙኒየም፣ የካ ሃያት፣ ወሰን ግሮሰሪ፣ ካራ ስላሴ፣ ሽሮ ሜዳ፣ ፈረንሣይ ለጋሲዬን፣ ቤላ፣ ካዛንቺስና ላንበረት መናኸሪያ አካባቢዎች የውሃና የመብራት እጥረት ነዋሪውን እየፈተነው ነጋዴዎችም የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በተቀላጠፈ መንገድ ማካሄድ እንዳልቻሉ ተገልጿል::

በሌላም በኩል አዲስ አበባ ከውሃና ከመብራት እጥረቱ በተጨማሪ የነዳጅ እጥረት ነዋሪውን እያማረረው መሆኑ ተሰማ:: ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ ነዳጅ ለመቅዳት ረዥም ሰልፍ እና ጋዝ ማደያዎች በራፍ ላይ እንደሚያድሩ የሚገልጹት ምንጮች የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈጠረ ምንም ችግር የለም ቢልም ነዋሪው ግን የ ዕለት ተ ዕለት ተግባሩን እንዳያከናውን ችግር ፈጥሮበታል::
መንግስት ማንን እንደሚዋሽ አይገባንም የሚሉት አስተያየት ሰጪ አሽከርካሪዎች እነርሱ በሚድያ እጥረት የለም እያሉ ሕዝቡ ግን ጋዝ ማደያዎች ላይ ተኮልኩሎ ይውላል ሲሉ ተናግረዋል

 

አማራው ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል… (ተሻለ መንግሥቱ)

ተሻለ መንግሥቱ (teshalem1@gmail.com)

ከዐይን በላይ የሚታመን ባለመኖሩ “ማየት ማመን ነው” ይባላል፡፡ እኔም አየሁ፤ አመንኩም፡፡ እናም አልሁ – “ወያኔ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን በተለይም በአማሮች ላይ የሚፈጽመው ድንበርየለሽ ግፍና በደል በመጨረሻው የዞረ ድምር ምን ያመጣብን ይሆን?” አሳሳቢና አስጨናቂ ጥያቄ ነው፡፡ የዚህን የወያኔን ዘመን ፍጻሜ ለማየት ብዙዎቻችን የችግሩ ገፈት ቀማሾች ብንጓጓ እስካሁን ከምናውቀውና ከዚህ በታች ከምነግራችሁ አስደንጋጭ መረጃ አንጻር አይፈረድብንም፡፡The Amhara people and Ethiopian regime (TPLF)

እንደአጠቃላይ እውነት ጨካኝ መንግሥታት የሚዘወሩት(የሚሩት) በክፉ መንፈስ ነው፡፡ ከመነሻው መናፍስት ሁለት መሆናቸውን ልብ ይሏል – ያዋጁን በጆሮ እንዳትሉኝ እንጂ፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት ሚዛን በደፋ ሁኔታ ዓለምን እያንቀጠቀጠ በመግዛት ላይ የሚገኘው መንፈስ ከሁለቱ አንዱ የሆነው ክፉው መንፈስ መሆኑን ለመረዳት ዓለምን ለአፍታ ያህል በምናባችን ቃኘት ማድረግ ብቻ በቂ ነው፡፡ እዚች ግድም /Positive Energy and Negative Energy የሚባሉትን ፈረንጅኛ ጽንሰ ሃሳቦች አስታውሱልኝ፡፡/ የጨካኙ መንፈስ ብርታትም የደጉ መንፈስ – በተወሰነ ደረጃ ከመከላከል ውጪ – ለማጥቃት ክንዱን አለመሰንዘሩ ነው፡፡ ለዚህም ነው በቅጽበት ውስጥ ጠላቶቹን ድባቅ መምታት እየተቻለው  “ጠላትህን ውደድ፤ እጅ ጠባብህን ለሚፈልግ መጎናጸፊያህንም ጨምርለት፤ ግራህን ለሚጠፋህ ቀኝህንም አዙርለት፤ የሚሰድቡህን መርቅ፣ ወዘተ.” የሚል የፍቅርና የትህትና አስተምህሮ አስተላልፎ ራሱም በመስቀል ተቸንክሮ የሞተው – የዓለም ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትም በዚህ አስተምህሮ ምዕመኗን በመግራቷ ይመስላል ሕዝቡ ሁሉንም ነገር በ”አንተው እንዳመጣኸው አንተው መልሰው” ጸሎት ለፈጣሪ ከመስጠት ውጪ በራስ ተነሳሽነት በጠላትነት የተፈረጀን ኃይል በመጣበት የኃይልና የክፋት መንገድ ለመቋቋም ያለው ፍላጎት እጅግ አነስተኛ ነው፤ ይሄም መንገድ ብዙ እንደጎዳን በጣም ግልጽ ነው፡፡ ይህ ዘመኑን ያልዋጀ አካሄድ ለዘመናችን አካይስቶች የተመቻቸው ይመስላል፡፡ በዚህን ዓይነት ትምህርት የታሸ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ እፍኝ በማይሞሉ ሞራለቢስና ሃይማኖተቢስ ወያኔዎች ሕይወቱ ሲመሰቃቀል ማየት እንግዲህ የሃይማኖትን ካባ እስከማስወለቅ ለሚደርስ የአእምሮ ህመም ቢዳርግ ለፍርድ ማስቸገሩ አይቀርም፡፡ ለነገሩ በዘመነ ግርምቢጥ የዘመን ፍጻሜ ላይ ተቀምጠን ፍትህን መመኘት ሞኝነት ነው፡፡

ይህ ክፉ መንፈስ በሰዎች ሰውነት ውስጥ ግዛት ፈጥሮ ሰዎቹን የርሱ ባሪያ በማድረግ እርሱ የፈለገውን እንዲያደርጉለት የጨለማው ንጉሥ ምድራዊ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደሮችና በመጨረሻውም የመንግሥቱ ወራሽ አድርጎ ይሾማቸዋል፡፡ በዚህ የሹመት ዘመናቸው አንዳችም ሥጋዊ ነገር እንዳይቸግራቸው የምኞታቸውን ጣሪያ እስከማሳካት በሚደርስ አለኝታነት ከነርሱ ጋር ይቆማል፡፡ እነሱም እርሱ የሚፈልገውን የደም ግብርና የስቃይ ቁልል በማስቆጠር ወሮታውን ይከፍላሉ፡፡ መጨረሻቸው ግን በርግጠኝነት አያምርም ብቻ ሣይሆን ከሠፈሩበት ቁና በበለጠ ይሠፈርላቸዋል፡፡ ከዚህ መሠረታዊ ነጥብ አኳያ ወያኔም ሆነ አይሲስ የሚባሉት የመካከለኛው ምሥራቅ ጭራቆችና መሰሎቻቸው (የሀሽሽ ንግድ ካርቴሎችን ጭምር) ቀን ከሌት የሚባዝኑት ርኩሳን መናፍስት አለቆቻቸውን ለማስደሰት ነው፡፡ በተለይ አሁን ሊደበቅ የማይችል እውነት፡፡

በዚህ መሀል ኢትዮጵያና አማራ በግላጭ ተገኙ፡፡ ለክፉ መናፍሰት ጭዳነትም በክፉው የዐውሬው መንፈስ ታጭተው እሳቱ ለማይበርድ፣ ስለቱ ለማይዶለዱም የመከራና ዕልቂት አዙሪት ተጋለጡ፡፡ ይሄውናም እነሱን ያለና ስለነሱ የዘመረ ትግሬም ይሁን ኦሮሞ፣ ጉራጌም ይሁን ከምባታ፣ ወላይታም ይሁን ሳሆ፣ አሪም ይሁን ቦዲ፣ ጠምባሮም ይሁን ሃዲያ… መላው የሀበሻ ምድር ዜጋ የነሱን ዕጣ ፋንታ ሊያገኝ የግድ ሆነ፡፡ “ሀበሻ አይደለሁም፤ ቀብራራ እንቶኔ ነኝ!” የሚለኝ የዘመነ ዕንቆቅልሽን ዝልል ጠጥቶ በሥነ ልቦና የሰከረ ገልቱ መኖሩን አልዘነጋሁምና ለዚህ ዓይነቱ ወፍ ዘራሽ ሰው ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ እዚቺው አደረስኩ፡፡

ክፉ መንፈስ – እየመሰለንና በሁኔታዎች አስገዳጅነት እየተገፋን እንጂ- ዘርና ጎሣ አይለይም፤ የገዛ ልጅንና የቅርብ ዘመድን ሣይቀር ግብር የሚያስገባ(የሚያሳርድ)  የዐውሬ መንፈስ በቋንቋና በዘር ልዩነት ያምናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ የሰው ግርድና አመሳሶ በክፉ መናፍስት የጥቃት ዒላማ ውስጥ ቦታ የላቸውም፡፡ እርግጥ ነው – እንደ ሥልትና ሰውን ለማጭበርበር ያህል ይጠቀሙበታል፡፡ ክፉ መናፍስት የዘር ሐረግ ቢለዩ ኖሮ ወያኔ – ከመነሻው አንስቶ –  “ለምን እንደኛ ‹ጨካኝ› አልሆናችሁም፤ ለምን የነገዳችሁን ውድብ አልተከተላችሁም፤ ለምን  እንደኛ አማራን አልጠላችሁም፤ ለምን ከነፍጠኞች ጋር ትሻረካላችሁ፤ አርቀን እየቀበርነው ያለነውን ኢትዮጵያዊነትንና የኢትዮጵያን ታሪክ ለምን ታነሳላችሁ…” በሚል እጅግ ብዙ ትግሬዎችን ያለ ርህራሄ ባልጨፈጨፉ፣ ባላሰሩ፣ ባላደኸዩና ከሥራና ከኑሮም ባላፈናቀሉ ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ መስዋዕትነታቸው እምብዝም ያልተዘመረለት ኢፍትሃዊነትን በመታገል ሕይወታቸውን ለሀገራዊ አንድነትና ለፍትህ የሰው ትግሬዎች ወደፊት በታሪክ ማኅደር ይነግሣሉ፡፡ እናም ምንም እንኳን ብዙ የወያኔ አጫፋሪ ትግሬ መኖሩ ሃቅ ቢሆንም “ዐይቡን ሳያዩት አጓቱን ጨለጡት” እንዲሉ እንዳይሆንብን ፍርዳችንን እያስተካከልን እንድንራመድ ማስታወስ እፈልጋለሁ – እንዲሁ አሁን ብልጭ ያለብኝ ሃሳብ ነው፡፡ ለማንኛውም ይህን የክፉ መናፍስት ባሕርይ ልብ እንድንል እያሳሰብኩ ወደተነሳሁበት ጉዳይ ልንደርደር፡፡

ደርግ ክፉ ነበር፡፡ (ይህ ነገር ሊሰፋብኝ ነው መሰል) ባይሆን ላሳጥረውና በርሱው ልነሳ ከጀመርኩ አይቀር፡፡ እናም ደርግ እጅግ ክፉ ነበር፡፡ የአገዛዝ ሥልቱ ወታደራዊ ወገናዊነት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ይሁንና በዘር የተመረዘ አስተዳደር አልነበረውም – ቢያንስ እስከመጨረሻዎቹ ዓመታት ድረስ፡፡ Give the devil its due.  ክፋቱ ግን የወያኔን አያክል እንጂ ከዚያ በመለስ ወደር የለውም፡፡ ሁለቱም ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ናቸውና – ከክፋት ምንጭ፡፡እናም ደረጃቸው ይለያይ እንጂ ሁለቱም ዐረመኔዎች ናቸው፡፡

ብዙዎቻችን የምናውቀውን የደርግን ጨፍጫፊነት፣ አሳሪነት፣ ገራፊነት(ወፌላላን የቀመሰ ያውቃታል)፣ ኢ-ሃይማኖታዊነትና ያን ተከትሎ ብዙዎችን ማበለሻሸቱን፣ ግትርነቱን፣ ድንቁርናውን፣…. እንርሳው፡፡ ግን ግን በአሳቻ ሰዓት በዜጎች መኖሪያ ሠፈር ላይ እሳት እየለቀቀ በተለይ ብዙ ሀብትና ንብረት ያወድም እንደነበር መዘንጋት የለብንም – ያ ጠባዩ ከወያኔ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ እንዲያ ያደርግ የነበረውም ቦታውን ይፈልገው ስለነበር ነው፡፡ ምሣሌ – ማርካቶ ቅ. ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢና ድሬዳዋ ውስጥ፡፡

ወያኔ፡፡ ህም! የወያኔ ሁልአቀፍና ወደር የለሽ ጭካኔ ተወርቶ አያልቅም፡፡

በአማሮች ላይ ያወጀውን እስካሁን ያልተነሳ የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት ዐዋጅ እዚህ አናነሳም፡፡

ልባቸው ከአለት ድንጋይ የተሠራው ወያኔዎች አንድን ቦታ መቀማት ሲፈልጉ ወይም አንድን ሕዝብ መበቀል ሲፈልጉ አካባቢውን በእሳት ያጋዩታል፡፡ ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያን ያነደዱ መስሏቸው ብዙ ደኖችንና ጫካዎችን ነዳጅ በመድፋትና አብሪ ጥይት በመተኮስ እንዳቃጠሉ ይታወቃል፡፡ የወያኔዎች ጥፋትና የእግዜሩ ትግስት ደግሞ እጅግ የሚገርሙ ናቸው፡፡ እግዜር የወያኔን ያህል በምድር የታገሠው ቢኖር ምናልባት የሰሜን ኮሪያን የኪም ኢል ሱንግ ሥርዎ መንግሥት ብቻ ነው – በኔ እምነት፡፡ እነሱም እንደኛው ከሦስት ትውልድ በላይ በናቡከደነፆራዊ የቀጥቅጥ አቅልጥ አገዛዝ ሥር ናቸው – እናም እነሱም እንደኛው እጅግ ያሳዝኑኛል፡፡ የእግዚአብሔርንም ትግስት ገደብየለሽነት እንድማር የሚያደርጉኝ እነዚህ ሁለት የዓለማችን ዕንቆቅልሾች ናቸው፡፡ እነሱን ሳስብ – ሁሌም – “እግዜር የት ሄደ?” እያልኩ ክፉኛ እጨነቃለሁ – ግን አማኝ ነኝ ታዲያ፤ ልጅ ከአባቱ ጋር እንደሚጋጭ እኔም ከፈጣሪ ጋር በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ብዙ ጊዜ “እነታረካለሁ”፡፡ በኛና በርሱ መካከል ያለውን የጊዜ ዳይሜንሽናዊ ልዩነት በመጠኑ ስለምረዳ ግን ለጊዜው እጽናናለሁ፡፡ የሀገሬ ሙስሊም  “‹አላህ ዳተኛ ነህ ታስጨርሰናለህ!› የሚለው ለካንስ ወዶ አይደለም”ም እላለሁ፡

በወያኔው ሥውር ትዕዛዝና የወንጀል አቀነባባሪነት በቅርቡ በጎንደር ከ420 በላይ ሱቆች በእሳት ነደዋል፡፡ በዚያው የአማራ ክልል ተብዬው አካባቢ የሕዝብን የመጠጥ ውኃ መርዘዋል፤ ለመመረዝ ሲንቀሳቀሱም እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ እሥር ቤቶችን በአሳቻ ሰዓት በማጋየት የሚፈልጋቸውን ዜጎች አንድዶ ይፈጃል፡፡ በደመ ነፍስ ከእሳት ለማምለጥ የሚሮጡትን ታሳሪዎች ቀድመው በተዘጋጁ ነፍሰ ገዳዮች ይገድላቸዋል፡፡ ይህ የክፋት ዓይነት ዘርን ከመፍጀት ባለፈ ልዩ ስም ሊሰጠው የሚገባው ነው፡፡ ሰለጠነ የሚባለው ዓለም ለእንስሳት መብት ሲቆረቆርና ምግባቸውም ሆነ መጠጣቸው ከሰው ሳይለይ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ሲጥር እዚህ ያሉ ገዢዎቻችን ከእንስሳትም በታች ይቆጥሩናል፤ ድንቁርናቸውና ዕብሪታቸው መለኪያ የለውም፡፡ ወይ ፍርጃ! ምን አጥፍተን ይሆን እነዚህን ዐረመኔዎች እግዜር የሰጠን? ራሳችንን እንጠይቅ፡፡

ወያኔዎች ዜጎችን በእሳትና በናዳ ከቀያቸው ማፈናቀል በጣም የለመድነው የዕለት ከዕለት ተግባራቸው ነው፡፡ አንድን የሚፈልጉትን ቦታ ከነዋሪዎች ለማጽዳት ሲፈልጉ ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ውስጥ በትንሽ ገንዘብ ደልሎ ወይም አስገድዶ ማባረር በአንጻራዊነት “ቅዱስ” ሊባል የሚችል ዘዴያቸው ነው፡፡ ከዚህ የከፋው ግን ጦር ሠራዊት መጠቀም፣ በድንገተኛ እሳት አካባቢውን ማያያዝና የእሳት አደጋ ሠራተኞችና የአካባቢው ሰዎች እሳቱነን እንዳያጠፉ በማገድ ሰውና ንብረትን ማጋየት፣ “ህገ ወጥ ናችሁ” ብሎ በማዋከብ ማስለቀቅ… ዋና ዋናዎቹ የዐውሬዎቹ ወያኔዎች ዜጎችን ከርስታቸው የማፈናቀያ ሥልቶች ናቸው፡፡

አሁን ሰሞኑን ደግሞ በዓይነቱ ለየት ያለ ምናልባትም ሰይጣን ራሱ ሣይቀር ብዙ ሊማርበት የሚችል አዲስ የዕልቂት ሥልት አቀናብረዋል፡፡ ይህም ዜጎች በሥራ ድካም የናወዘ ሰውነታቸውን አረፍ አድርገው በሰላም ሊተኙ  ሲሉ ከነመላ ቤተሰብ የሚያዳፍን ልዩ መሬት ሰርጓጅ ቴክሎጂ በመጠቀም መጨረስ ነው – ተራራ ደርማሽ ድማሚት አጥምዶ አፍሪካዊ ሂሮሽማና ናጋሳኪን በታሪክ ለማስመዝገብ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ሙከራ ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ አካሂደዋል፡፡ “ቆሼ ተራ” በሚባው አካባቢ የታየው ዕልቂት የዚህ አዲስ ሥልት የሙከራ ጅማሮ ነው፤ እነዚህ ሰዎች ጊዜ ካገኙ አዲስ አበባ ሥር አንዳች ነገር አጥምደው ሳይፈጁን አይቀሩም – ቻይና ደግሞ ሣንቲም ካየች የማትታዘዘው ነገር የላትም፤ ነፍሰ በላ የትልቁ ዐውሬና የትንንሾቹ የአጋንንት መንፈስ ታዛዦች ቀኝ ክንድ ናት፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን መቼም ቤተ ሙከራ ከሆንን ቆየን፡፡ ፈረንጆቹ በዐይጥና በጅንጀሮ አንድን ነገር ይሞክራሉ – ወደኛ ሲመጣ ግን በኛው በዜጎች እንዲሞከር ልጆቻቸውን ያዛሉ፤ ክፉ መንፈስ የተጣባቸው ልጆቻቸውና “ልጆቻችን” ደግሞ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለሱም – በሆዱ የማለ አድርግ ያሉትን ያላንዳች ማመንታት ያደርጋል፡፡ “ሴትና ሆድ የላኩት ሞትን አይፈራም” ብዬ ተረታችንን ባሻሽለው የሴቶች መብት ተከራካሪዎች(ፌሚኒስቶች) እንደማይቆጡኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ – የሆኖ ሆኖ “ሆዳም ሰው ፍቅር አያውቅም”ና ገና ብዙ አሣር አለብን፡፡  ወያኔዎች ሁሉንም የአለቆቻቸውን ትዕዛዛት ካለማቅማማት ይፈጽማሉ – ምክንያቱም በደማቸው ውስጥ የተዋሃደው የአጋንንቱ መንፈስ ካለደም ግብር አይጸናላቸውም፤ የሥልጣን ማቆያ ማኅተማቸውም የሰው ደም ነው፡፡ አበቅቴው እስኪሽር የፈለጉትን ቢያደርጉ ከልካይ የለባቸውም፤ የደም ግብሩን እስካላቋረጡና ከትዕዛዝ እስካልወጡ ድረስ ደግሞ ወይም በተቃራኒው እኛ የደጉን መንፈስ ቀልብ የሚስብ አንዳች መልካም ነገር ማድረግ እስካልጀመርን ድረስ አለቃቸው የሆነው የዐውሬው መንፈስ ጦር ከጥፋት ይታደጋቸዋል – በራሳቸው ጊዜ በንነው እንደማይጠፉ ግን እንወቅ – ያ ምኞት ነው፡፡… ለማንኛውም ፈጣሪ የወገኖቻችንን ነፍስ ይማር – ለነገሩ እንዲህ ባልልም ዱሮውን ተምረዋል፤ ሰማዕት ናቸውና፡፡ በግፍ የምትጠፋ ነፍስ የኃጢኣት ሥርየትን በቀላሉ እንደምታገኝ በበኩሌ አምናለሁ፡፡ ግን ወዮ ለግፈኛው! ”በቅሎ ገመዷን በጠሰች” ቢሉ “ማሰሪያዋን አሳጠረች!” ይባላልና እያንዳንዷ የምናደርጋት ክፉም ሆነች በጎ ነገር ዙራ ተመልሳ ከእኛው ደጅ አትጠፋም፡፡

በአማራው አካባቢ እንዲህ ይደረጋል፡፡ ይህን ግፍ ታዘቡ፤ ሁሉም ወገን እንዲያውቀውም አድርጉ፡፡

ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በተለይም የፖሊስና የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተብዬው የአማራ ጎሣ ባልደረቦች፣ የመስተዳድር አካላት ሠራተኞችና የጸጥታና ደኅንነት ባልደረቦች በተልዕኮም ሆነ በምሽት የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲማሩ ፈጽሞ አይፈቀድም – ይህ ዕገዳና ክልከላ ደግሞ በምንም ዓይነት መንገድ ለድርድር አይቀርብም፡፡ እንደሰማሁት በሌሎች በተለይም በትግራይ ክልል ይህ ዓይነቱ ነገር አይታወቅም፡፡ እንዲያውም ከዚህ በተቃራኒ በሀሰትም ይሁን በእውነት ማንኛውም ዜጋ ዲግሪ እንዲኖረው ይበረታታል፡፡ ይህ double standard በአንዲት “ፌዴራላዊት” ሀገር ውስጥ እውን ሆኖ ማየት ከግርምት በላይ ነው፡፡ አንዱን ማስተማር ሌላውን ማደንቆር፡፡ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ፤ አንዱ ዘመድ ሌላው ባዕድ፡፡ ፋሽዝምና ናዚዝም ከዚህ በላይ የለም፤ አፓርታይድ ከዚህ የከፋ በደል በሕዝቦች ላይ አላደረሰም፡፡ ቀን ይፍረድ!

ምሥጢር ማውጣት እንዳይሆንብኝ እንጂ አንዳንድ ሠራተኞች እንዴት ባለ የረቀቀ ዘዴ የርቀት ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ከራሳቸው ከሰዎቹ አንደበት ሰምቻለሁ፡፡ በፈተና ወቅት እንኳ ማንነታቸውን ለመደበቅ የሴት ቀሚስ ለብሰውና እንዳረብ ሴት ፊታቸውን በሂጃብ ሸፍነው እስከመሄድ እንደሚደርሱ ነግረውኛል፡፡ ይህ ሁሉ ለምን? ቢማሩ ሀገርንና ወገንን ይጠቅማሉ እንጂ ማንን ይጎዳሉ? ግን ሀገሪቱን የሚገዛው  በተግባሩ ባዕድ ኃይል ሆነና ችግሩ ከዚያ መነጨ፡፡ ጣሊያን ኢትዮጵያውያንን አደንቁሮ ለመግዛት ማንም ዜጋ ከሀሁ ባለፈ እንዳያውቅ ያደርግ ነበር፡፡ መማር ራስን ያሳውቃል፤ መማር አካባቢን ያሳውቃል፤ መማር ዓለምንና ከዚያም ባለፈ እንድናውቅ ያደርጋል፡፡ ያወቀ ሰው ደግሞ ለውስጣዊ ኅሊናው እንጂ ለውጫዊ እንቶ ፈንቶ አያጎበድድም፡፡ ስለዚህም ጨቋኞችና ቅኝ ገዢዎች ዜጎች እንዲታወሩ እንጂ በብርሃን እንዲመላለሱ አይፈቅዱም፡፡ የኛ ነው የሚሉትን ግን ብዙም ባይሆን በተወሰነ ደረጃ ለቀቅ ያደርጉታል፤ ማኪያቬሊያዊ የአገዛዝ ሥርዓት እንዲህ ነው፡፡ በወንድማማቾች መሀል ይህን መሳይ ሽብልቅ የሚቀበቅቡ እነዚህ እርጉም ወያኔዎች ዘር አይውጣላቸው – ለነገሩ እንዴት ብሎስ ይወጣላቸዋል?

አመራሮቹ ግን ይደበቁ አይደበቁ አይታወቅም እንደፈለጉ ይማራሉ – መማር ተብሎ፤ ማይምነት በአሥር ዲግሪ ቢጀቦን ከማይምነቱ ፈቀቅ አይልም፡፡ እነዚህ የወያኔ አሽከሮች ከፈለጉ ከውጪም ሆነ ከሀገር ውስጥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ያሻቸውን ዓይነት ዲግሪ በግዥም ይሁን በእጅ መንሻ ስጦታነት ይጭናሉ – አብዛኞቹ ግን ውስጣቸውም ውጫቸውም ገለባ ነው፤ ዱሮውንስ ሰውነቱን ለእህል ሲል ለወያኔ ያከራዬና የገዛ ወገኖቹን የሚጨፈጭፍና የሚያስጨፈጭፍ ባንዳ ሰው ምኑን ሰው ሆነው?

ዲግሪን ባወጣ የሚቸበችቡ የግል ተቋማት ደግሞ ከገጠር እስከከተማ ሞልተዋል፡፡ ከነዚህም ብዙዎቹ የነሱው የወያኔዎቹ ናቸው፡፡ ከወቅቱ የሀገራችን ራስ ምታቶች አንዱ በተለይ በመንግሥት ተብዬው የወያኔ አስተዳደር ውስጥ ከተራ የቀበሌና የወረዳ ሠራተኛ ጀምሮ እስከ ላይኛው የዕዝ ጠገግ ድረስ የሚመደቡ ዜጎች በፎርጅድ ዲግሪ የተጥለቀለቁ መሆናቸው ነው፡፡ ከጋሪው ፈረሱን እያስቀደሙ በባዶ የዲግሪ ወረቀት መንበሽበሻቸው ለደረጃ ዕድገትና ለደመወዝ ማስተካከያነት ካልሆነ በስተቀር በሥራው ላይ አንድም ነገር አይፈይድም፡፡ ሀገሪቱ በባዶ ጭንቅላት ተወርራ ሥራ እየተበላሸ ተገልጋይ ዜጎችም እየተማረርን ነው፡፡ የስብሰባው ጋጋታ ደግሞ አይጣል ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ሶደሬ ላይ ቀሚስ አያማረጠ አንሶላ ሲጋፈፍ የቢሮው ጸሐፊ ግን “ስብሰባ ላይ ናቸው!” እያለች ሕዝብን ታታልላለች፡፡ ለመናገርም ሆነ ለመጻፍ የሚያስቸግር የዘመንና የትውልድ ኪሣራ ገጥሞን ግራ ተጋብተናል፡፡

በአማራ አካባቢ ተዘዋወሩ፡፡ ከጥቂት የሆቴልና የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች በስተቀር እንደሌሎች ክልሎች በተለይም እንደ‹ኦሮሚያ›ና እንደ ትግራይ የመሰለ የተለዬ የልማት አውታር አታዩም፡፡ መንገድ የለም፡፡ ገበሬው በከፋ ድህነት ውስጥ ተዘፍቋል፡፡ ልጆቹ አይማሩም፤ ተማሩ ቢባልም አሥረኛና አሥራ ሁለተኛን ሳይቀር ዘለቁ ተብለው ፊደልን መለየት አይችሉም፡፡ ዕውር ዕውርን እየመራ ገደል በመግባት ላይ ነው፡፡ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች(mega projects) በአማራው አካባቢ ህልም ናቸው፡፡ አንድ የዚያው አካባቢም ይሁን የሌላ አካባቢ ተወላጅ በአማራው ክልል መራቆት ተቆርቁሮ በልማት ልሠማራ ቢል የመጨረሻ ዕጣ ፋንታው ዕድለኛ ከሆነ በሆነ ሰበብ ወህኒ ቤት ወርዶ እስከወዲያው መማቀቅ ወይም የባሰው ከመጣ “ሀንቲ ጥይት ሃቦ” የምትለዋን በጣም የምናውቃትንና የተለማመድናትን ስብሃት ነጋዊ ገጸ በረከት ሳይወድ የግዱን መሸለም ነው፡፡ ስንክሳራችን ብዙ ነው … ይሁንና ይህ ቀን ያልፋል ጎበዝ! ሲያልፍ ግን ለልጆቻችን ምንና እንዴት እንደምናወራቸው ነው የሚጨንቀኝ፡፡ በተደጋጋሚ እንዳልኩት በቅዠት የመኖር ያህል ነው የአሁኑ ኑሮ፡፡ የሚገርመው ደግሞ የመከራ ሌሊት በቶሎ እንዳለመንጋቱ የኛም የስቃይ ዘመን እጅግ መርዘሙ ነው – ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በኢዮባዊ ቁስል መንፈር ለሰሚ ግራ የሆነ መርገምት ነው፡፡ የክርስቶስ ስቃይ እንኳን ከረቡዕ እስከ ዓርብ ነበር – ለሦስት ቀናት ብቻ፡፡ ለምን የኛን አረዘመብን ታዲያ? ራሳችንን እንጠይቅ፡፡

አማራ በግብርም በነቢብም እንዲጠፋ እየተደረገ ነው፡፡ ልማቱን ተውት፡፡ መንገዱን ተውት፡፡ የንጹሕ ውኃ አቅርቦቱን ተውት፡፡ ትምህርቱንም ተውት፡፡ የጤና ክብካቤውም እርሱት፤ እዬዬም ሲደላ ነውና፡፡ ከሁሉም የሚያሳዝነው እንግዲህ አማራው በገዛ ቀየው በወያኔዎች እየተተካ የከተማዎች ዐይን ዐይን ቦታዎች ሁሉ ለምርጥ የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች እየተሰጡ አማራው በሥነ ልቦናም በኅሊናም በአካልም በመንፈስም ቅስሙ እየተሰበረ ከመጠነኛ መኖር ወደለየለት አለመኖር እየተሸጋገረ መሆኑ ነው፡፡ ወኪሉ ነን የሚሉት አብዛኞቹ የብአዴን ሰዎች ደግሞ ሆዳቸው ከሞላ ለወገኖቻቸው የሚያስቡ አይመስሉም – የአጥንትና የደም ሥሪታቸው ከጅብ ይሁን ከዓሣማ ወይንም ከግዑዙ ድንጋይ ገና በውል አልታወቀም፡፡ ይህ ሁሉ ዐይን ያወጣ መድሎ ሲፈጸም ባይናቸው በብረቱ እያዩ የነሱ ከርስ ባለመጉደሉ ብቻ ለወያኔ እሽክርና ገብተው ወገናቸውን በወያኔ አጋዚ በማስጨረስ ላይ ይገኛሉ – “በሬ ካራጁ” እንዲሉ ነውና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ጭዳነቱ ለነሱም አይቀርም፤ ትንግርተኛ ዘመን ነው በደፈናው፡፡ የሆነ ሆኖ እነሱም ዋጋቸውን ያገኛሉ – ሊያውም ከዋናዎቹ በባሰ፡፡ ያየሁትን ተናገርኩ፡፡ ኃጢኣቱ በኔ ነው፡፡

መቀሌ ፒያሳ ላይ “ሰውነት ክንዴ ወርቅ ቤት” ወይም “ደርበው ሞላልኝ ሥጋ ቤት” የሚል የንግድ ተቋም ካለ ጥሩ ነው፡፡ ወልዲያ ውስጥ መቻሬና ሙጋድ ላይና ደብረ ታቦር ፒያሳ ላይ ግን “ሐጎስ ተወልደ ወርቅ ቤት” እና “ኅሩይ ግደይ ሥጋ ቤት” የሚል ማስታወቂያ እንዳለ በዐይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ – በዚህም የማምነውን ነው የምላችሁ በጣም ተደስቻለሁ (የሰዎቹ ስምና የንግድ ዓይነቶቹ ላይ መጠነኛ መሻሻል እንደተደረገባቸው በትህትና እገልጻለሁ)፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ግን ግንጥል ጌጥ እንዳይሆን ያሰፈልግ ነበር፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ታዲያን “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ”ን አዘውትሮ የሚጠቀምባት ወያኔ የኔ ናቸው የሚላቸው ወገኖቻችን በየትም ሥፍራ ምርጥ ምርጡን እንዲይዙ የህግና የጸጥታ ሁነታዎችን ሲያመቻች ለሌሎች ግን የመጫወቻ ሜዳው ሰበርባራና የጠርሙስ ስብርባሪ የተደፋበት እንደሚያደርገው ሰማይና ምድር ሳይቀሩ በሚገባ ያውቃሉ፡፡

በአማራው አካባቢዎች መብራት ከሚመጣባቸው ጊዜያት ይልቅ የማይመጣባቸው ይበዛሉ፡፡ በዚህን ዘመን በተለይ አማራው እንደ ዜጋ አይታይም – በገዢው መደብ እንደቀንደኛ ጠላት ስለሚቆጠር በተገኘበት ሁሉ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ተፈርዶበታል፡፡ የመንግሥት ሥልጣን መያዝ ይቅርና እንደ አንድ መጻተኛ ርሁቅ ብዕሲ እንኳን በዚህች የጋራ ሀገሩ እንዲኖር አይፈቀድለትም፡፡ በገዛ አገሩ በስደት እንዲኖር፣ እየተሸማቀቀ እንዲኖር፣ ሀብት ሳያፈራ በድህነት እየማቀቀ እንዲኖር፣ በማይምነት ጥቁር መጋረጃ ተሸብቦ በኤሎሄ እንዲቃትት የውጭና የውስጥ ጠላቶቹ ፈርደውበታል፡፡ ደግ ነው፡፡ ከመግፋት መገፋት፣ ከመግደል መሞት፣ ከማሳደድ መሳደድ የማታ ማታ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡ ስለሆነም በተለይ በዚህ የመጨረሻ በሚመስል የመከራ ወፍዳ ዘመን፣ በዚህ ዘመነ መንሱት ለቃላት የሚከብድ ስቃይና እንግልት እየደረሰበት የሚገኘው አማራ እንኳንስ አሳዳጅ አልሆነ፣ እንኳንስ ዘር አጥፊ አልሆነ፣ እንኳንስ ዘር አጽጂ አልሆነ፡፡ እንኳስ የዲያብሎስ ቀኝ እጅ ሆኖ የእግዜርን ፍጡራን አለአበሳቸው ጨፍጫፊ አልሆነ፡፡ የተበዳዮች ወገን መሆን የሚያኮራ ቢሆን ኖሮ ለመንጠባረር የሚቀድመኝ ባልነበረ፡፡ ግን ግን ምድር ጊዜያዊ የስደት ቦታ መሆንዋን እረዳለሁና፣ ይህ ሁሉ ግርግርና ህንፍሽፍሽም አላፊ ጠፊና ይዋል ይደር እንጂ በሌላ ያማረ ነገር እንደሚተካም እገነዘባለሁና በማየው ሁሉ ብዙም አይሞቀኝም፤ አይበርደኝምም፡፡

ከፍ ሲል በጠቀስኩት የአማራው አካባቢ ሕዝቡ እንኳንስ መብራት ጠፋብኝ ብሎ እንደመብት ሊጠይቅ ይቅርና ፀሐይን በሰፌድ ቢጋርዱበት፣ የሚተነፍሰውን አየር በማራገቢያ ቢከሉበት ትንፍሽ አይልም፤ ሁሉንም ችግሩን ለሰጠው ሰጥቶ መልሱን እየተጠባበቀ ያለ ይመስላል – ያም መልስ ቢያንስ እኔን ጨምሮ ለጥቂት ዜጎች ቁልጭ ብሎ ይታየናል፡፡ ጉራ አይደለም፤ ትምክህትም አይደለም፡፡ ይልቁናስ “የሚመካ ሁሉን ማድረግ በሚችል በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይመካ፡፡” የሰው ኃይል ከልኩ አይዘልም፡፡ እስኪበቃን አየነው፡፡ ከመንግሥቱ ኃይለማርያም ይበልጥ ኃይለኛና አስፈሪ፣ ጨካኝና ልበደንዳና  በኢትዮጵያ አልነበረም – እርግጥ ነው እስከ 1983ዓ.ም ድረስ! እርሱ እንኳን ላይመለስ አልፏል፡፡ ዕድሜም እኮ ወሳኝ ነው፡፡ የሚያረጀው ሰውና ሕይወት ያለው ፍጡር ብቻ አይደለም  – ጀግንነትና ፍርሀትም ያረጃሉ፡፡ ጉብዝናና ውርዝትናም በጊዜያቸው ያልፋሉ፡፡ ዝናና ክብርም ጠውልገው ይከስማሉ፤ሞትም ራሱ አርጅቶ ይሞታል፤ ታዲያ የማያልፍ ነገር ምን አለ? ምንም! ሰላም ለኢትዮጵያ፡፡

 

“ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፉም፡፡”(ማቴ. 24፡ 35)

“ታጠቡ፤ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ፤
መልካም መሥራትን ተማሩ፤ ፍርድን ፈልጉ፤ የተገፋውን አድኑ፤ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተሟገቱ።” (ትንቢተ ኢሣይያስ 1፡ 16-17)

በቆሻሻ ቁልሎች ሳቢያ የተመቱ የዓለማችን ከተሞችና የአዲስ አበባው ቆሼ: አንኳር ችግሮች እና የተወሰዱ እርምጃዎች ሲቃኙ | ልዩ ጥንቅር | በታምሩ ገዳ

 


በቆሻሻ ቁልሎች ሳቢያ የተመቱ የዓለማችን ከተሞችና የአዲስ አበባው ቆሼ አንኳር ችግሮች እና የተወሰዱ እርምጃዎች ሲቃኙ | ልዩ ጥንቅር | በታምሩ ገዳ

የአውሬው ፈጫሳዎች – ያየያየ ዪልማ

 

በዚህ አለም የሚታወቀውን ታላቁን ክፉ – “ሰይጣንን” እንደ ብልት ሆነው : አካሉን የሚያሟሉ ሁለት የጭራቅ ውሉዳት፡ ሰው በላዎች ፣ በጋራ ማህተም ያሰሩበትን ስምምነት እንዳነበብኩ ይህ ሆነ፡፡ ተገረምኩ! እንደተገረምኩም እስካሁን አለሁ!!!

በስምምነቱ ላይ አንዱ ፈራሚ ሆኖ የቀረበውና ውክልናውም የኔውን ህዝብ (ኢትዮጵያዊያንን) ያስቀደመው ጉድ፡ ገሃዱ ያገሬ ታሪክ አይቶት የማያውቀው በህዝቡ ላይ ፡ እጅግ ክፉ መሆኑ ከመቼውም በላይ ጠልቆ ገባኝ፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ስም ከፊት አስቀድሞ ስምምነት የተፈራረመው፤ በሰው ደም ፈጫሳ ቃልኪዳኑን ከሰይጣን ጋር እያደሰ መንበሩን የሚፀናው፤ ከጃንሆይ በተመነተፈ ስያሜ እራሱን የሚያስጠራው “ጠሃዩ መንግስታችን” ነው፡፡

ይህ ተራ አውሬ አይደለም፤ ይለያል፡፡ ቀለቡ የንፁኃን ስጋ ፣ የሚጋተው ደግሞ የምንዱባንን ደም ሲሆን፣ ህዝበ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች የገጠር ቀዬዎች፣ ደሃ ከተሜ ሆነ ገበሬው ለስፍራው ሁሉ ሻጋታ በመሆኑ ፡ ከነጭርንቁሱ ይነሳና ከተማ ከገጠር ይልማ ተብሎ የምንዱባኑ ወገኔ ቤት ንብረት ሲፈርስ ጥሪቱ ሲቃጠል፤ ጭቁኑ ህዝብ ሁሉ መና ሆኖበት በስቃይ ለሰማያት ዋይታውን ሲያሰማ፤ የደሃው ህዝብ ጩኸት ለአውሬው የመንፈስ ማንቂያ ሙዚቃው፣ የዚህ ሁሉ የደሃ ጥሪት ቃጠሎ እና የጥቀርሻው ሽታ፣ ለአውሬው ቆሌ የሚያውድ ልዩ የሽቱ መአዛው ፣ ዶጋ ከሚሆነው የወገኔ ጥሪት ደግሞ – የገንዘብ መኸሩ ሆኖለት አውሬው ሃሴትን ይሰበስባል፡፡ በነዚህ ተደጋጋሚ ግፎች የደለበ ስለሆነ ነው አውሬው የታሪካችን ልዩው – የሚል ድምዳሜ ላይ ለሰየም ያበቃኝ፡፡

የዚህ ድምዳሜ ዋነኛ መነሻ የሆነኝ እና የዚህ ሀተታ አስኳል የሆነው ታዲያ፡ በኢሃዲግ እና በአሸባሪው የሶማሊያ አንጃ አል-ሸባብ መካከል ጂሊብ በሚባል የሶማሊያ አንድ ከተማ በ2011 የተፈረመው ስምምነት ነው፡፡ ውሉን እንዳነበብኩ ያልኩት አንድ ነገር ነው፡፡ በዚህ አይነት ስንት ሸፍጥ ይሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተደረገው ብዬ እየዘገነነኝ ብዙ አሰብኩ፡፡ ደግሞም ተስፋዬ ታላቅ ነው፡ እንደዚህ ሁሉንም በሚስጥር ይዘው እንደማይዘልቁት እሙን ስለሆነ፤ የተደረገውን ሁሉ ፈጣሪ በጊዜው ይግለጠው ብዬ፤ ፈጥኜ ብእሬን አነሳሁና ለነብስያዬ ያባሽውን እንትፍ በይ በማለት እነሆ ምስክርነቴን እሰጣለሁ፡፡

እንደዛሬ ኢትዮጵያዊያን በዘርና በጎጥ ልክፍት ታጥነው ተከፋፍለው ልዩነትን ማሳል ሳይጀምሩ እና አንድ ሳሉ፤ “ኢትዮጵያ ተወረረች!” የሚለው፡ “ያ” ሰማያት በአንድ ላይ የሚያስተጋቡት የማይደራደሩበት የመርዶ ድምፅ፤ ልክ የማይክል ጃክሰንን “ትሪለር ሙዚቃ” የመግቢያ ምት ሲሰማ አንዳች ልዩ ስሜት እንደሚወርረው የፖፕ ሙዚቃ አፍቃሪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሆ ብሎ ተነስቶ የፈጫሳ ዶሮ ከሆነበት የወያኔ-ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ በዚህ መንግስት ምሪት የተደረጉ ዋነኛ ክስተቶች በሙሉ ፣ ከፊት ለፊት ገፅታ አመክንዮአቸው በስተጀርባ አስገራሚ የፈጫሳ ሸፍጥ ያጨማለቃቸው ናቸው፡፡

“ያ” ጦርነት፤ የወያኔ-ኤርትራው ማለቴ ነው፤ መነሻ ምክንያቱ ባድመና ዛላንበሳ ሳይሆን- የወያኔና የሻእቢያ በትግል ወቅት የነበረ ሚስጥራዊ ስምምነት በመፍረሱ ነበር፡፡ የኤርትራን ነባራዊ ሁኔታ ቀድሞ ያሰላው ሻእቢያ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ጨው የተበተኑትን ዜጎቹንና የደሃውን የኢትዮጵያ ገበሬ ምርት እንዲሁም አጠቃላይ የኢትዮጵያን ምድራዊ ሃብት ስሌት ውሰጥ ከትቶ ሲያበቃ፡  በኢትዮጵያ ዱቄት ቡኮ አብኩቶ መልሶ ለኢትዮጵያውያን መብል ሸጦ ፤ በትግል ስምነታቸው አማካኝነት ኤርትራን “የአፍሪካ ሲንጋፖር” ሊያደርግ ሲወጥን ቀን እስኪያልፍላቸው እምቢ ያላሉት የወያኔ ፊታውራሪ አውሬዎች፡ ያቺ ታላቅ ኤርትራ- ለምን “ታላቋ ትግራይ” አትሆንም ብለው ከአምስት ቢሊየን በላይ የሚቆጠር የቀድሞው የኢትዮጵያ መገበያያ ብር ሻእቢያ እጅ ላይ እንዳለ ዋጋ ሲሳጡበት ነበር፤ ህዝብ በወያኔ-ኤርትራው ጦርነት አውሬው የመጀመሪያ ፈጫሳውን ያደረሰው፡፡ እንጂ ባድመን ለማስመለስ አልነበረም፤ ባድመማ መች ተመለሰ፡ ከነበረው ተቆርሶ ተሰጠ እንጂ፡፡

ከዚህ የጀመረው የአውሬው የፈጫሳ ልማድ እና ክፋት ያለማባራት አድጎ እና ዳብሮ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ መልክ፤ ያ በሰውም በአምላክም ፊት እንደነብር ዝንጉርጉርነት እስኪለይ ደማቅ የነበረው የኢትዮጵያ ልዩ ማህተብ በአውሬው እየተበጠሰ፡ ሌላ ስውር የክፋት ስፌት በላይዋ ላይ እየተሰፋ፣ ዘመን ተሸጋሪ ውበቶቿ የእርጅና ካባና ስያሜ እየተደረበባቸው ያቺ ጥላሁን ሲገልጽ ሆዳችን የሚባባላት እና የምናውቃት ውቧ ባለፀጋ ቀዬ ግርማዎቿ ሁሉ እንደአበቃለት የእባብ ቆዳ እየተንሰረሰረ በሚጓዝ የማይሰማ የጊዜ ሂደት አውሬው ወዟን አውልቆ እንደጣለው አየሁና አዘንኩ፡፡ ግን ደግሞ እኔ ከማውቀውና ከተጣለው የኢትዮጵያ ግርማ ስር ቆሜ፡ አንዳንድ ሊረሱ የማይችሉ የበላይ ሸንጎ ጉልበትን የሚያሳዩ ነገሮች ትውስ አሉኝና፤ ይቅር በለኝ አልኩ፡፡ አዎ ይህ ሸንጎ ካሻው፡ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሁሉ በወጉ ለሚናገር ሰንደቅ፣ እንዲሁ ለሚያጣቅስ ደግሞ ባንዲራ የሚል ስያሜ ያለውን መለያችንን ፤ በሶስት ደቂቃ ውስጥ ደርዘን ጊዜ ያክል ጊዜ እየደጋገመ ፤ በንቀት ጨርቅ ፣ ጨርቅ ፣ ጨርቅ ፣ ጨርቅ…. እያሉ በማናለብኝነት መጣራት ለሚቀናቸው አገር አልባዎች፤ እንደ ዘመነ ፈርኦን ሰማያት ፈርደው፤ ከተያዙበት ቅፅበት አንስቶ በቢጫ ቁስል መላ አካልን መትቶ፡ እንደ ማንኪያ ቀንጥሶ ሲያፈራርስ በአይኔ ስላየሁ ትውስታው ፈገግ አሰኘኝ እና ተፅናናሁ፡፡

… አምላክ ይግለጥላችሁ! የአዲስ አበባ መንደሮች ስላረጁ ብቻ አልፈረሱም፤ ያፈረሳቸው አንድ ነገር ነው! ነዋሪዎቹ ሁሉ በጋራ የሚያውቁት የሚያስታውሱት (Collective Memory) ይህ ተውስታቸው ደግሞ ለአውሬው ጠንቅ ስለሆነ እንጂ፡፡ ከአድዋ ዘመቻና ድል እስከ ቅርቡ የ1997 ምርጫ ድረስ የሆኑትን ከአህጉር እስከ ሃገር ምድሪቷን የናጡ ማእበሎችን፡ ከነግለታቸው የሚያስታውስ የቁራ እኩያዎች፡ ከማይሞት ትዝታቸው ጋር አንድ ላይ ችምችም ብለው ይኖሩ ስለነበር ነው መንደሮቹ ሁሉ የፈረሱት፤ ተጋንኗል ብሎ የሚል ካለ፡ ለምን ይመስላችኋል ከነ አራት ኪሎ አይነት ፈራሽ መንደሮች የሚፈናቀሉ ምንዱባን እንደ ደንጊያ ካብ አስር ቦታ ተበትነው ሲያበቁ፡ የእውነት ማጣቀሻቸው ኢቲቪ ብቻ በተደረገባቸው አዲሶቹ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዙሪያ የሚያሰፍራቸው ለምን ይሆን… ብቸኛዎቹ እንዳነሳሳቸው የሰፈሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከፍልውሃ ሚካኤል (ልዩ ስሙ-አልታድ) የሰፈሩት ብቻ ናቸው አንድ ላይ የሰፈሩት፤ እነሱንም በሁለት ፖሊስ ጣቢያ ተከብበዋል፤ ይህ ስህተትም አስፋሪው ግለሰብ ስለሆነ እንጂ አውሬው ቢሆን አይስተውም፡ አልደገመውም፡፡

…አባይን ገድቦ የሚያቆም ስፍራ በአማራ ክልል ስላልነበረ አይደለም አባይ ከአማራው ደጃፍ ርቆ እየፈሰሰ ሱዳን ከመግባቱ በፊት ህዳሴ ተብሎ የተገደበው፤ መጀመሪያም ቢሆን አባይን ያክል ጉድ ወንዝ ከጣና ፣ ከጎኑ ደግሞ አማራ የሚባል ብሄር ተፈጥሮ ፈቅዳ በማኖሯ ዘላለም የሚያርረው የአውሬው ቆሽት፡ በአማራ ህዝብ ጥላቻ ጥምቀት በፈጠሙ የአውሬው ፍለፋዮች ሸፍጥ፡ አባይን የወለደውን የአማራን ምድረ-ማህፀን ሾተላይ አድርገው፡ ህዝቡን ባገሩ ካባይ ቆርጠው ማለያየታቸው አባይን አሶሳ ላይ መገደባቸው፡፡ ለዘመናት ግብፅ የኢትዮጵያዊያንን ቁጭትና እንባ ከአሸዋ እየለወሰች በልታ ስትሳለቅ እንደኖረች እንዲሁ፡ አውሬውም ከአማራው ህዝብ ማጣት እና ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ላቦት በተቀማ ገንዘብ ፡ ሲሚንቶ ገዝቶ የቂም ግንብ ገንብቶ፡ በገባው ውል መሰረት ወደ ከርሱ ዶላር ሲያጋብስ አማራውን ይህ በወሰኔ የሚለው ካባይ የሚጣቀስ አንዲት ጥሪት ለመቶ አመት እንዳይኖረው መሆኑ ነው እንጂ፡፡

… “አንቀፅ 39” ያስፈለገው ሌሎች ብሄሮች ማንነታቸው ሊጠፋ ደርሶ ካፋፍ ስለነበረ ነው ወይስ… በጥላቻ “መንበረ-ፀባኦቱ” ደደቢት – በአማራ ጥላቻ ሰልጥነውና ሰይጥነው ለኪዳናቸው ፀጉር ባንጨባረረሩት አውሬዎች የጥላቻ ኪዳን ምክንያት ነው … እዚያ በበረሃ ክፋት ያነገቡት የአውሬው ደቀመዛሙርት ውርስ ገቢር መሰረት፡ ከሁሉ ከሁሉ : አማራ የሚባል ሰደድ እሳትን በውስጡም ህብረብሄራዊ መስተጋብርን ያቀፈችውን ኢትዮጵያን አፍኖ ለማጥፋት የተመረጠ አመዳቸው ስለሆነ ነው እንጂ፡፡ በአውሬው አስተምህሮት መሰረት፡ ኦሮሞነት ከአማራነት በመሰረታዊ የብሄር ይዘት እንደማይለይ ቢያውቅም፤ ለአማራ ያለው አቻ የማይገኝለት በቁንፅል ቲዎሪ ላይ የሚመሰረት ጥላቻ ምክንያት፤ አማራ የሚለውን ስም እንደ ብሄሮች መካነ መቃብር አድርጎ ስለሚቆጥር፡ ለዚህ ብሄረ በላ ሰደድ እሳት ደግሞ ማቆሚያው ይህ አንቀፅ እንዲሆን ስለተፈለገ ነበር፡፡ ይህ እሳት ሸዋን በልቶ አወይቦ መልክ አሳጣው፡ ስለዚህ ትንሷን ትግሬን ሰልቅጦ ሳያጋሳ ማርከሻ የሚሆን አንቀፅ እናርቅቅ፡ ለራሳችንም አያቶቻችን ከሺህ አመት በፊት ያለፉትን ኋላቀር ጎጠኝነትንና፡ በተለይ ጠማማውን ልባችንን እናሰንብት ተብሎ የተበጀ ኢትዮጵያዊነትንን በገሃድ የመካጃ ቅልስ፡ ኢትዮጵያዊነት የሚለውን ጠይም ጥላ ከመሰረቱ የናጋንበት ውል እንጂ፡ የብሄር ብሄረሰቦች ቫለንታይንስ ዴይ እንዳይመስላችሁ!!!፡: “እነሱ” የሚጨፍሩት፡ አውሬው ነሻጣ የሚያመጣ ዜማ በአበል አስጠንቷቸው ነው፡፡

ታላቁ የስነፅሁፍ ሊቅና የስነፅሁፍ ኖቤል ተሸላሚ ታጎር : ባንድ አጋጣሚ ሲናገር፤ “ሁልቆ መሳፍርት የሆነው የሰው ባህሪ አለምን ከነሞላዋ ለየግሉ በውስጡ ተላብሷል፤ የትኛውም የዝህች አለም ጥልቀት ከሰውልጅ ውስብስብ ተሰጥኦ አይልቅም፤ ስለሆነም የአለም እውነታ በሰው ሃቅ ውስጥ ይጠቃለላል!” ብሎ ሰውን ገልፆ ነበር፡፡ …”ቀለም” አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ እና ቀይ ከለሮችን ጠቅልሎ እንደሚወክልና እንደሚገልፅ እንዲሁ፡ – ኢትዮጵያዊም! በባንዲራው ስር የሚታወቅ ነበር: የአውሬው ሸፍጥ ሺህ አመት ወደኋላ አሽቀንጥሮ ጣለን እንጂ፡፡

የማያልቀውን የአውሬውን የሸፍጥ ዝርዝር በዚሁ ገታ ላድርግና ወደመነሻዬ ልግባ፡፡ ለማመን ቢከብድም ይህንን ስምምነት በአይኔ በብረቱ አይቼዋለሁ፡፡ በላቲን ቃላት በሶማሊኛ ቋንቋ የተፀፈው ይህ ስምምነት ጥቅል የሆነ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ድርሻዎች ለሁለቱ ተፈራራሚዎች ተዘርዝሮ የሰፈረበት እንዲሁም ስምምነቱን የሸመገሉትም ሆኑ አውሬው ኢሃዲግን ወክለው የፈረሙትንም ጭምር በሰው ደም ተጠቃሚ የሚያደርግ ሚስጥራዊ ሰነድ ነው፡፡ ተፈራራሚዎቹ የየራሳቸውን ፍላጎት ለማሳካት አላማ ይዘው የመጡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን መንግስት በስምምነቱ ላይ ወክለው ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ አብዲ መሃሙድ ኡመርም ስምምነቱን በማስፈፀም የተገባላቸውን ቃልኪዳን ( እነጉርሱም ፉኛን ቢራን፤ ፉግግን የሚታከኩትን ባለደጋ ለም መሬት የያዙትን የኦሮምያ ስፍራዎችን በሂደት ሊያገኙ በመሆኑ ሽልማታቸውን እያሰቡ) መንግስትን ወክለው የተገኙ ሲሆኑ፡ አልሸባብን የወከሉት ደግሞ ሼክ ሙክታር አብዙቤር የሚል ቲተር ያላቸው የአልሸባብ ሰው ናቸው በባለ ስድስቱ ገፅ የፈጫሳ ምህላ ግርጌ ላይ ፊርማቸውን ያሰፈሩት፡፡

 

የውሉ ይዘት በአጭሩ በተገለፁ ዝርዝር ሃሳቦች የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም እንዲያስጠብቅ የተዘጋጀ ቢሆንም ፤ በጋራ የውል ስምምነቱ ላይ አውሬው ለአሸባሪ አንጃ እውቅና ሰጥቶ የተስማማባቸውን የሽብር ሽርክናዎች እንጂ ስለያንዳንዱ መስመር ማተት አያስፈልግም፡፡

በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከተቀመጡ ግዴታዎች ባጭሩ፡-

 • ….የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ ሶማሊያ ለሚንቀሳቀሰው አልሸባብ ከኪስማዮ ወደብ የሚያገኘውን ጥቅም ጨምሮ ሌሎች እስላማዊ ህግን በህዝቡ ላይ ተግባራዊ እያደረገ የሚሰበስበውን ገቢውን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአንጃው ሊያከብርለትና በምንም መልኩ ጣልቃ እንዳይገባበት፤
 • በጁባላንድ ላይ የተለየ ፍላጎት እያሳየ ያለውን እና ራስ ኮምባኒን ጨምሮ ጁባላንድን እንደ ራስ ገዝ በሶስት የምትከፈል ፌደራላዊ ክልል እንድትሆን ሁሉንም አይነት ድጋፍ ከሚያደርገው የኬንያ መንግስት ጋር የኢትዮጵያ መንግስት እንዳያብር፤
 • በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሚሶም የሚያገኘውን ማናቸውን መረጃዎች ከአልሸባብ ጋር በፍጥነት እንዲለዋወጥ፤
 • የአፍሪካ ህብረትንና ኢጋድን ሁለቱ ተፈራራሚዎች ለሰፈሯቸው ፖለቲካዊ አላማዎች እንዳስፈላጊነቱ በስውር ጥቅም ላይ ማዋል፡ በዚህም ዋነኛዋን የአልሸባብ እንቅፋትን ኬንያን ዋነኛ ኢላማ ማድረግ፤
 • የኢትዮጵያ መንግስት ለአልሸባብ ሎጂስቲካዊና ወታደራዊ ድጋፎችን በቁስ ( ይህ ከመሳሪያ እስከ ተሸከርካሪ የደርሳል) ሊደግፍ ፡ ድጋፉም እንደ አስፈላጊነቱ ደግሞ በሽያጭ ሊያቀርብ ለዚህም ባይዶዋና አፍመደው የተባሉ ስፍራዎችን ለየብስና በጥርጊያ አየር ማረፊያነት የቁስ ማቅረቢያ ስፍራዎች ሆነው እንዲያገለግሉ መስማማታቸውን ወታደራዊ መረጃዎን ለመለዋወጥ የታሰሩ የመገኛኛ የሬድዮ ሞገዶችን ሚስጥራዊ ልውውጥ ያጠቃልላል፡፡
 • የኢትዮጵያ መንግስት ከአጋሩ የሶማሊያ መንግስት የሚጋረውን በዚህ ረገድ ፡ ለአልሸባብ ህልውና ጠቃሚ ሊሆን የሚችል ማንኛውም አስፈላጊ መረጃዎችን፡ ወታደራዊ ደህንነቶቹንም ጭምር በመጠቀም ለአንጃው በፍጥነት እንዲያቀብል የተስማማበት የጋራ ውሉ ካሰፈራቸው አንኳር ሃሳቦች መካከል የሚገኙ ናቸው፡፡

በአልሸባብ በኩል ከተቀመጡ ግዴታዎች ባጭሩ፡-

 • የዚህ ስምምነት ዋነኛ ግዴታ ከኢትዮጵያ ድንበር ውጪ ተበትነው በሰሜን ሶማሊ አቅራቢያ እንዲሁም በዚሁ በጁባ ላንድ የሚገኙ የኦኤንኤሌፍ ቡድንን እና መሰል ሌሎች የኢትዮጵያ መንግስት ጠላቶችን በተመለከተ የተጠናከረ መረጃ የመሰብሰብና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቋሚነት መለዋወጥ፤
 • አልሸባብ ከኤርትራ መንግስት ጋር እንዳለው የሚከስሱ ፕሮፖጋንዳዎችን በአላማ ያለማስተባበል
 • ይህንን ስምምነት ጨምሮ ማናቸውም የሁለትዮሽ ስምምነቶች የአጋር መንግስት መጠሪያቸው የሻእቢያ መንግስት መሆኑ ብቻ እንዲታወቅ ግዴታውን ያለስህተት መጠበቅ
 • የኢትዮጵያ መንግስት ከኦጋዴን እስከ ቡረኦና ላስአኖት(የሶማሊ ላንድ ግዛቶች) ድረስ የሚያደርጋቸውን የየብስ የባህር ንግድ እንዲሁም የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቶች በምንም መልኩ እንዳስተጓጓሉ
 • ይህ ስምምነት ከተፈረመ ጀምሮ የትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ከአንጃው የሚነሳ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይገጥም ታማኝ መሆን
 • ለኢትዮጵያ መንግስት የሚፈፀሙ ማናቸውም ክፍያዎች የአከፋፈል ሁኔታ በኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት ላይ የሚመሰረት እና በሌላ አባሪ ዝርዝር የስምምነት ማእቀፍ የሚከወን መሆኑን መቀበል ለአልሸባብ የቀረቡ የውል ግዴታዎች ናቸው፡፡

ይህንን ስምነት ለፍሬ እንዲበቃ በማድረግ ለአልሸባብ ህልውና በሙሉ ዋልታነት ፊርማ አኑሮ ያረጋገጠው የኢትዮጵያ መንግስት በንፁሃን ደም የደለበ እውነተኛ አውሬ መሆኑን ጨርሼ ያረጋገጥኩት ይሄኔ ነው፡፡ እነዛን ሁሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሶማሊያዊያንን ደም በየቀኑ ከሚያፈስ አሸባሪ ቡድን ጋር ኢሃዲግ ማህተም ማሰሩ መቼም ቢሆን የምገረምበት ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስት ጢምቢራን የሚያዞር የዶላር ናዳ ወደ ጎሮሮው አመት አመት እንዲፈስለት ያደረገ፡ የሽብር ቡድን ስለሆነ መረዳት አይከብድም፡፡ በተለይ ደግሞ ከ2004 አንስቶ እስካሁን ድረስ ጎረቤታችን ኬንያ በዚሁ ቡድን ከልክ በላይ መታመሷ ባንፃሩ ለአልሸባቦች የእኛ አገር ርቋቸው አንዴም ሳይደርሱብን መኖራቸው ሲታይ ምስሉ ግልፅ ሆኖ ይታያል፡፡

አውሬው እስትንፋሱ ክፋት፣ ስጋው ሸፍጥና ተንኮል፣ ድምፁም እንደእባብ ስውርና መርዛም የሚፊለፍላቸውም እፉኝቶች ናቸው፡፡ ሌላ ሊወልድ አይችልም፤ የኢትዮጵያ ልጆች ግን ዘራቸው ከአርያም ቆዳቸውም የማይቀየር ነው፡፡ አሮጌ ጨርቅ ተብሎ የተጣለውን ሊቀየጥ የማይችለውን ቀለመ-አርያም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራቸውን ከአፈሯ ውስጥ ወጥተው ለብሰው ይነሳሉ!!! ምክንያቱ ደግሞ የሃያሉ የአምላክ ቃልኪዳን እንቁ ከሆነችው ከኢትዮጵያ ጋር እንጂ በደም ግብር ከጨቀየ አውሬ ጋር አያብርም፣ እግዚብሄር ፃድቅ ነውና፡፡ ብቻ ልጆቿ አምላካቸውን ድምፅ ሰምተው ይነሱ እንጂ የንፁሃንን ደም እየፈጨሰ ያለው አውሬ ስሪቱ ሸክላ ስለሆነ ከብርቱ የኢትዮጵያ ልጆች ጡጫ አይተርፍም፤ እኔም እንግዲህ ለእውነት ድርሳን ከሚተጉት ጎራ እድል ቀላቅላኝ ብእሬን አንስቼ እነሆ እውነት እንካችሁ ጉድ ብላችሁ ይችን ፀሎት ወደ አርያም አድርሱ እባካችሁ፡፡ …አምላክ ሆይ በቃችሁ በለን! ጠላታችንን ከመርገጫን ስር አስገባ፣ ያቺም ቀን ቅርብ ትሁን፣ አሜን፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡

 

የአማራ ህዝብ የሚፈልገው ቅሪላ የሚጠልዝበት ሜዳ ሳይሆን ዳቦ የሚያስገኝለት ፋብሪካ ነው (ቬሮኒካ መላኩ) 

 


ለዚህ ፅሁፍ የተጠቀምኩት ርእስ ሞገደኛና ስፖርትን ጠል ሊያስመስልብኝ ይችላል። እውነታው እሱ አይደለም። እኔ ራሴ ስፖርት የምወድና ስፖርት ለአንድ ህዝብ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ የምገነዘብ ነኝ። ለዚህ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ብአዴን ሰሞኑን በአማራ ክልል ውስጥ 12 የኳስ ሜዳ ለመገንባት ቃል እንደገባ በመሃበራዊ ሚዲያ ማንበቤ ነው ።
ህውሃት በከባድ በፋብሪካ ቁንጣን በምትሰቃየው ብይ በምታክለው ትግራይ ክልል ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት እቅድ ሲይዝ ። ኦህዴድ ” የኢኮኖሚ አቢዮት ” በሚል መሪ ቃል ለክልሉ ወጣት ስራ የሚያስገኝ የመአድን ማውጫ እና ሰርቪስ ሴክተሮችን ለመገንባት እቅድ ይዞ ሲተገብር ሎሌው ብአዴን የአማራ ወጣት በባዶ ሆዱ ስራ ፈትቶ ኳስ የሚጠልዝበት 12 ስታዴየም እሰራለሁ እያለ ነው።

የብአዴን ነገር ይገርመኛል። ብአዴን አንድ “ታዋቂ ” መዝሙር አለው። ” ያልተንበረከክነው! ” ይባላል  🙂 በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ ውስጥ እንደ ብአዴን ተንበርካኪና ለአሽከርነት የተመቼ ድርጅት የትም አይገኝም ። ብአዴን መንበርከክ ብቻ ሳይሆን በትከሻው የህውሃትን የአንባሻ ዱቄት ተሸክሞ በእንብርክኩ የሚሄድ ድርጅት ነው።

የህውሃት የፖለቲካ ሃሊዮት በፖለቲካው ለዘመናት የበላይነትን ለመቆየት ኢኮኖሚውን እና ሚሊቴሪውን መቆጣጠር የሚል ነው። ይሄን ሃሊዮት ተግባራዊ ለማድረግ ባለፉት 25 አመታት ፍትሃዊ ያልሆነ የሃብት ማግበስበስ ላይ ሲሰማሩ ሌላውን ደግሞ በተለይም አማራውን በድህነት ይማቅቅ ዘንድ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል እያደረጉም ነው ።

CSA (የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክ ኤጀንሲ) በቅርቡ ባወጣው መረጃ ትግራይ ላይ እስካሁን 300 ከፍተኛ ፣ከባድና መካከለኛና ኢንዱስትሪዎች (Medium & Large Scale Industries) የተገነቡ ሲሆን፤ በአማራ ክልል ግን 100 መካከለኛና ዝቅተኛ ኢንዱስትሪዎች (Medium & small scale Industries ) ብቻ ተከፍተዋል። ነገር ግን የአማራ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ከ7 እጥፍ በላይ የሚበልጥ ከመሆኑም በተጨማሪ በጥሬ ዕቃ አቅርቦትም ሆነ ለኢንዱስትሪ ቦታ ምቹነት አማራ ክልል ከትግራይ እጅግ በላቀ መልኩ ተመራጭ የሚያደርጉ ብዙ ሁኔታዎች አሉት፡፡

ለምን እንዲህ ሆነ ተብለው ሲጠየቁ “በኦሮሚያ ክልል እኮ ከትግራይ የበለጠ 320 ኢንዱስትሪዎች ተሰርተዋል” ብለው ይነግሩናል::
ይገርማል! ብይ የምታክለውን ትግራይን ቋጥኝ ከሚያካክሉ ክልሎች አስበልጦና ነፋፍቶ በማሳየት ፍትሐዊ ባልሆነ መልኩ ያገሪቱን ሐብት ለክልላቸው ብቻ ያጋብሳሉ፡፡
አስቡት እስኪ የትግራይን 7 እጥፍ የሚበልጠው ኦሮሚያ 320 ስላለው፤ 7 እጥፍ ያነሰችው ትግራይ ላይ 300 መከፈቱ ፍትሐዊ ነው ብሎ ግግም ማለት ምን አይነት ደረቅነት እና ስግብግብነት ነው ?!

ባለፈው ጆሯችንን እስኪታመም እና አይናችን ሊጠፋ እስኪደርስ በየሚዲያው METEC (የብረታብረት ኮርፖሬሽን) ውቅሮ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ትራክተርን ሙሉ በሙሉ የሚፈበርክ ፋብሪካ ሲከፍት፤ ደብረ-ብርሐን ላይ ደግሞ መገጣጠሚያውን በመክፈት ሜቴክም በበኩሉ ፍትሀዊነት ሰብኮልናል፡፡ እናወዳድርስ ብንል አቅልጦ ማምረትንና የተመረተው መገጣጠም ምን አገናኘው? እንኳን ሊወዳደር የደብረ ብርሐኑ፤ ፋብሪካ ተብሎ ሊጠራ እንኳን አይገባውም!
ያው እንደተለመደው ከትግራይ ፊት concave mirror ደቅነን፤ ከአማራ ፊት ደግሞ convex mirror በማስቀመጥ በአብየታዊ ዲሞክራሲ ወልጋዳ ሚዛን ፍትሃዊነቱን እንድናደንቅ እንገደዳለህ፡፡

ህውሃት የሚመራው መንግስት አላማው አገሪቱንና ህዝቡን በኢኮኖሚ ለማሳደግ ቢሆን ኖሮ እንደ አማራ ክልል ለኢንደስትሪ አመች የሆነ ክልል የትም አይገኝም ነበር ። ለማንኛውም ከባድ ኢንደስትሪ የደም ስር የሚባለው የኤሌክትሪክ ሃይልን ብንመለከት ክልሉ እምቅ ሃይል ያለው ነው ። በአባይ ዋናው ወንዝ ላይ ብቻ 12 ግድቦችና በድምር ወደ 50,000 ሜጋ ዋት የሚደርስ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም ያለው ክልል ነው ።
ኢትዮጵያ 27 የመስኖና አነስተኛ የኤሌክትሪህ ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በአባይ ገባር ወንዞች ላይ በመገንባት 2 ሚሊዩን ሄ/ር መሬት በመስኖ ማልማትና ተጨማሪ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ በማመንጨት ይቻላል።

እውነታው ከላይ የተጠቀሰው ሆኖ እያለ በወያኔ ግልፅ የአፓርታይድ ፖሊሲና በአሽከሩ በብአዴን አስፈፃሚነት የአማራ ህዝብ ከድህነት እንድወጣ አይፈለግም። ህውሃት ከሮም እና ከሌሎች የጣሊያን ከተማ ላይብረሪዎች ፋሽስት ጣሊያን ትከተለው የነበረውን ፖሊሲ ከሸልፍ እያወረደች መተግበር ከቆየች 25 አመታት አለፋት ።

ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ ያደረገው ነገር ከሁሉም ክልል ተመርጠው ወደ ስልጣን እንድመጡ የሚደረጉት መመዘኛቸው በአማራው ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው በመሆናቸው እና ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር መኖር እና ያለመኖር ደንታ የማይሰጣቸው ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ነው።
ብአዴንም ውስጥ ወደ ስልጣን እንድመጣ የሚፈለገው ” በአማራው ላይ ጥላቻ አለው ወይ? ” የሚል ፈተና ከተሰጠው በኋላ ያንን ፈተና ማለፍ ከቻለ በኋላ ነው። አሁን በተግባር እንደሚታየው አለምነው መኮንን የተባለ አሳማ ወደ ስልጣን እንድመጣ የሚደረገው ትግል ይሄን መመዘኛ በመቶ ፐርሰንት ስለሚያሟላ ነው ።

ከአሻንጉሊቱ እና በኢትዮጵያውያን ” ጠ/ሚ አቡሽ ” የሚል ቅፅል ስም በተሰጠው ሃይለማርያም ደሳለኝ ጀምሮ በሁሉም ክልል ያሉት በኦሮሞ በጋንቤላ በሱማሌ በትግራይ በቤንሻንጉል በደቡብ ክልል ያሉት የኢሃዴግ ኣመራሮች ምርጫ በኣማራ ላይ ባላቸው ጥላቻ ብቻ የተመረጡ ናቸው እስካሁን ድረስም ቢሆን ያ አሰራር ቀጥሏል በየትኛውም ክልል በኣማራውም ቢሆን ለአማራው ቀና ኣመለካከት ያለው ሰው ወደ ስልጣን በፍጹም ሊመጣ አይችልም።

አሁን የሚታየው የተቀነባበረና በፖሊሲ የታገዘ አማራውን አንገት የማስደፋት ፖሊሲ ለ40 አመታት በደንብ የተሰራበት ነው። አንድ ሁሉም ግንዛቤ ሊወስድበት የሚገባው የአማራ ህዝብ ይህንን በደሉን ለመርሳት/ ለመተው ቢቸገር እና ቀኑ ሲደርስ ሂሳብ ላወራርድ ቢል ሰው እንጂ መልዓክ አለመሆኑን ማወቅ አለባችሁ ።