መንግስት ከብዙ ጉትጎታ በኋላ የሦስት ቀን ብሔራዊ የሐዘን ቀን አወጀ | መንግስት ያመነው የሟቾች ቁጥር 72 ደርሷል | “200 ሰዎች ሞተዋል” – ነዋሪዎች

 (ዘ-ሐበሻ) መንግስት ብሔራዊ የሃዘን ቀን እንዲያውጅ ስንት ሰው መሞት አለበት? ሲሉ ኢትዮጵያውያን አደጋው ከደረሰበት ዕለት ጀምሮ ሲጠይቁ ነበር:: ዘ-ሐበሻን ጨምሮ የተለያዩ ድረገጾች እና ሶሻል ሚድያዎች መንግስት ብሔራዊ የሐዘን ቀን እንዲያውጅ ከፍተኛ ውትወታ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን ዛሬ የተሰበሰበው የኢሕ አዴግ “ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” የ3 ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን አውጇል::

“የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በቆሻሻ ክምር መደርመስ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን አወጀ” በሚል መንግስታዊ ሚድያዎች ባስተላለፉት መረጃ መሰረት “አዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በደረሰው የቆሻሻ መደረመስ እስከ ዛሬ ዕለት ድረስ 72 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡” ብለዋል:: ሆኖም ግን መንግስት ያመነው ቁጥር ትንሽ መሆኑን እና በትንሹ ከ200 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ::

እንደ መንግስት ሚድያዎች ዘገባ “ምክር ቤቱ ዛሬ ባኬሄደው መደበኛ ስብሰበ ነው ከነገ መጋቢት 6‑9፣2009 ድረስ ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ እንዲቆይ ያወጀው ፡፡”

በዚህ አደጋ ከአንድ ቤተሰብ እስከ 5 ሰው ሞቷል:: ሕጻናት አልቀዋል::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s