የዮናታን ተስፋዬ መከላከያ ምስክር ዶ/ር መረራ ጉዲና ፍ/ቤት ቢቀርቡም ምስክርነት ሳይሰጡ ቀሩ

 

የዮናታን ተስፋዬ መከላኪያ ምስክር እንዲሆኑ በሰባተኛው ጊዜ ቀጠሮ የተገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ ፍ/ቤት ቢቀርቡም ሁለተኛው ምስክሩ አቶ እስንድር ነጋ (ጋዜጠኛ) ሊቀርብ ባለመቻሉ ለነገ መጋቢት 7 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

አቶ እስክንድር ነጋ ፍ/ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት ለማስረዳት
የተገኙት ምክትል ሳጅን እንዳሻው ተስፋዬ እንዳሉት ምስክሩ በተደጋጋሚ ፍ/ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ባለመስጠታቸው ከሃላፊያቸው በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት ሳያመጧቸው መቅረቱን ተናግረዋል፡፡

ለፍ/ቤት ሳያሳውቁ ምስክሩን አለማምጣት እንደሚችሉ የተጠየቁት ምክትል ሳጅን እንዳሻው ተስፋዬ ከአለቃቸው በተሰጣቸው ትዕዛዝ ብቻ ሳያመጧቸው መቅረታቸውን ደግመው ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ፍ/ቤት የቀረቡትን መከላኪያ ምስክር ዶ/ር መረራ ጉዲና እስከዛሬ ለምን እንዳልቀረቡ ከዕለቱ የመሃል ዳኛና የፍ/ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት በሪሁን የተጠየቁት ኢንስፔክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው ዶ/ር መረራ ጉዲና ወደ ማረሚያ ቤት ከተላኩ በኋላ የትኛው ማረሚያ ቤት እንዳሉ ማወቅ ባለመቻላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ካኪ ጃኬት፣ጂንስ ሱሪ እና ነጠላ ጫማ በካልሲ አድርገው ዘግይተው ፍ/ቤት ለተገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ለምን እንደመጡ ያስረዷቸው የመሃል ዳኛው ከእሳቸው ጋር ምስክር የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ ባለመቅረባቸው ለነገ መጋቢት 07 ቀን 2009 ዓ.ም ከረፋዱ አራት ሰአት ተኩል መቀጠሩን ተነግሯቸው ፍርድ ቤቱ ለአዳር ተቀጥሯል፡፡

ዜናው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ነው

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s