በላዬ ሰቦቹን እንዴት እንስፈራቸው? (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ

“ካኒባሊዝም” ስርዎ ቃሉ የሚመዘዘው “ካሪብ” ከሚለው የስፓኒሽ ቃል ሲሆን ትርጉሙም የሰውን ስጋ የመመገብ ልማድ ያደረጉ ስዎችን ለመግለጥ የሚያገለግል ነው፤: እኔ የሰውን ስጋ የሚበሉ ሰዎች እንዳሉ ለመጀመሪያ ግዜ የሰማሁት በልጅነት በዕለተ ሰንበት ከተዓምረ ማርያም ሲነበብ ነው፤ ልጅነት አቅመቢስ አድርጎን ኖሮ በግዜው ባንረዳውም ቅሉ ሃይማኖት ነውና ተቀብለነው ኖረናል።

Ethiopia, TPLF officials

በማስከተልም በበረራ ቁጥር 571 እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1972 መስመሩን ስቶ ላቲን አሜሪካ የበረዶ ግግር ጋር ተጋጭቶ በወደቀው የዩራጋይ አውሮፕላን ውስጥ ከአደጋው የተረፉት ተሳፋሮች ለብዙ ቀናት በበረዶው ውስጥ ተይዘው በከረሙ ግዜ ህይወታቸውን ያተረፉት አንድ ያንዱን ስጋ እየበላ እንደነበር ወደ አማርኛ በተተረጎመው “የተራራው ምርኮኞች” በሚል መጸሃፍ ተጽፎ ካነበብነው ጀምሮ ቦብ ጊዶልፍ በሰራው አንድ ዶክሜንተሪ ውስጥ በምእራብ አፍሪካ ያሉ ሰዎች በጣም የሚወዱት ጓደኛቸው ሲታመምና የማይድን ሲመስላቸው እራሳቸው ቀድመው እንደሚበሉት በቦታው ተገኝቶ የታዘበውን ትራጀዲ በምስል አስደግፎ ያቀረበው ዘግናኝ ታሪክ፤ ከኮንጎ ጫካዎች እስከ ላቲን አሜሪካዎቹ ደሴቶች፣ ከስታሊን ግራድ ላይ በጀርመን ወታደሮች እስከ አስራ ዘጠኝ ስልሳው አሰቃቂው የቻይና የእረሃብ አመታት የተፈጸሙ የሰውን ስጋ ለምግብነት የዋለበት ጥቁር ታሪክ መዘርዘር ይቻላል።

ቦካሳ የተባለ የሴንትራል አፍሪካ አምባገነን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹን በማሰር ወይም በመግደል ብቻ የሚረካ አልነበረም። ይልቁንም በማይክሮዌቭ ጭምር እየጠበሰ ይበላቸው እንደነበር ዘገባዎቹ ገሃድ ወጥተዋል። ይኽ ሰው ስልጣን በያዘ ማግስት የአገሪቱን ፋብሪካዎች በመውረስ በራሱና በሚስቱ ስም ያደረገ ሲሆን ብዛታቸው አምስት መቶ ገደማ የሚሆኑ የአንድ አንደኛ ደረጃ ትቤት ተማሪዎች በሚስቱ ስም ከተመዘገበው ፋብሪካ በአንዱ የተመረተውን ዩኒፈርም “ከለሩን አልወደድነውምና አንለብስም” በማለታቸው የተነሳ ነፍሰ ገዳዮቹን ልኮ ሁሉንም ህጻናት በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ ያስገደለ አረመኔ ነበር። ሃይማኖት ነፍስን ብሎም ባህልና ልማድን ጭምር የሚቀርጽ በመሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አንዳቸውም ቢሆን በኛ ደረጃ እንደ ማህበረሰብ በኦሪያትዊ ትውፊት መኖርን ያልጀመሩ፣ ሐዲሱም ያልሰረጸባቸው፣ይልቁንም ዘግይቶ ከተጫነባቸው (ሃይማኖት) ይልቅ የራሳቸው ወደ አውሬነት ደረጃ የወረደ ባህል ገኖባቸው የወጡ ሆኑ እና ምንም አደረጉ ቢባል ብዙም ላያስደንቅ ይችላል።

በሃይማኖት መኖር ኋላቀርነት ነው ተብሎ፤ ከምስራቅ በተነሳው የኮሙኒዝም ሰደድ ሰላባ መሆን በጀመርንበትና እኛም ግራ እጃችንን በቀሰርንበት የለውጥ ማእበል ዋዜማ ገና በወራዙትነት እድሜያቸው ወደ አሲምባ ያቀኑት ዶር ብርሃኑ በአንድ ወቅትከ ሌሎች ስድስት የኢህአፓ አባላት ጋር መከሰሳቸውንና ጉዳዩ እዛው ጫካ ውስጥ በነበረው የኢህአፓ ወታደራዊ ችሎት መታየቱን፤ እሳቸው እድሜያቸው ገና ልጅ በመሆኑ በይቅርታ መታለፋቸውን እና የቀሩት ስድስቱ ላይ ግን የሞት መፈረዱን ብቻ ሳይሆን የሞቱን ፍርድ የፈረዱትም ሆነ ግድያዩ የፈጸሙት በቅርብ አብረዋቸው የኖሩት የገዛ ጓደኞቻቸው መሆናቸውን፤ ከሁሉም በላይ ግን የገዳይ ስኳዶቹ ልጆቹን ዘወር አድርገው ጫካ ውስጥ ከገደሏቸው ቦሃላ ያለ ምንም የሰቀቀን ስሜት ከሟቾቹ አስከሬን ላይ ልብሳቸውን አውልቀውና የተሻለውን መርጠው ለብሰውት እንደተመለሱ ማየታቸውን፤ የለጋነት እድሜያቸውን የሰውለት፣ዱር ቤቴ ብለው በረሃ ድረስ የተከተሉት፣ እህታቸው አዲስ አበባ ላይ የኢህአፓን አባላት ስም ዝርዝር አሳልፋ ላለመስጠት ሳይናይድ ታብሌት ውጣ በእራሷ ላይ እርምጃ የወሰደችለት፤ ያ “ክብሩ ወ ቅዱስ” ያሉት ኢህአፓ እውነተኛ ማንነቱን በጫካ ውስጥ ሲያዩት ከእርሱ ጋር ያላቸው ግንኙነት ያን ቀን እንደተበጠሰና በሱዳን በኩል አድርገው አሜሪካን መግባታቸውን ብሎም እንደዛ ያሰከራቸውን ነገር ምን እንደነበር ማርክሲዝምን በማንበብ መልስ ፍለጋ ሲቆፍሩ እንደ ነበር በአንድ ወቅት ይፋ ባደረጉት ግለ ታሪክ አንብበናል።

ከደደቢት ተነስተው ሚኒሊክ ቤተመንግስት የደረሱት የትግራይ ገዢ ጉጅሌዎች እስከ ሲኦል ዳርቻ ድረስ ጠልቀው በመውረድ እራበን ብለው የገዛ ጓደኞቻቸውን በሳንጃ ዘልዝለው ጥሬያቸውን መብላታቸውን እንዲህ ወቅቱ ደርሶ ለህዝብ ጆሮ ሲደርስ ዶር ብርሃኑ አልሰሙም ማለት አይቻልም። እነ አንበጣና በለሶቹ በላየሰቦች ሆነው ነገር ግን በሰው ልብስ ተሸፍነው ጭምር ሆነው አዲስ አበባ መድረሳቸው ብቻ ሳይሆን ዛሬ ደግሞ ከሰው አይንና ጆሮ ተከልለው ማእከላዊ በሚባል ምድራዊ ገሃነም ውስጥ እየፈጸሙት ያለውን ሰቆቃ ለመናገር ቀርቶ ለመስማት የተፈቀደ እንዳልሆነ ሓብታሙ አያሌው ለምስክርነት በቅቶ አድርሶናል።

በላዬ ሰቦቹ ኑሮ ያደረጉትን ጸያፍ ግብር በሃይማኖት ታንጾ ያደገው ጨዋ በቃላት አውጥቶ ለመናገር አቅም ሲያጥረው ብናይ አይገርምም። ሃብታሙ አያሌው ትናንት በጨዋ ትርጉም ተነስቶ አረመኔዎቹን በሰውኛ መስፈርት ለክቶ; የተጻፈ “ህገ መንግስት” አለ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ሊታገል ተደራጀ። በአደባባይ ከሚለፈፈው እንቶ ፈንቶ ጀርባ ያለውን መራር እውነት ግን ለማየት ማእከላዊን ጨምሮ በብርሸልቆ፣ በባዶ ስድስትና በመሳሰሉት ምድራዊ ገሃኖሞች ውስጥ ያለውን እውነት ማየት እንደሚያስፈልግ ዛሬ ከሃብታሙ የተሻለ ሚዛን ደፊ ምስክር የሚኖር ያለ አይመስለንም።

ማንም በአገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል ታግዬ ከዚህ አውሬ መብቴን እነጥቃለሁ የሚል ቢኖር በዚህ ስሌት ማየት ያለበት ይመስለኛል። ዶር ብርሃኑ ነጋ ትናንት በአሲምባ ያዩንትን ብሎም ቀጣዩን የፖለቲካ ህይወታቸውን እስከ መጨረሻው የቀየረውን የያን ግዜ የልጅነት ገጠመኛቸውን ከእነዚህ በላዬ ሰቦች መራር ተፈጥሮ ጋር አነጻጽረው አንድ ቀን የበኩላቸውን እንደሚሉን ተስፋ አደርጋለሁ….

ከዛሬ ጀምሮ በላዬ ሰቦቹ ስል የትግራይ ገዥ ጉጄዎቹን መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንዲታወቅ ይሁን!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s