በበደልከው ልክ ትቀጣለህ!!

 


አንዳንድ ቀን ምህረትን እንዲሁ የምትገኝ የሚመስልህና የሰማይ ደጆች የተከፈቱ ያህል የሚሰማህ አለ።አንተ በአምላክህ ላይ ባለህ ተስፋ ሁልን ጥለህ በሱ ተከልለሃል እና ።ስለምትበላው ስለምትጠጣው አታስብ ይሆናል ።ግን መቼም ቢሆን ምንም ሞልቶልህ አያቅምና ክፍተትህን ገዶሎህን እንዲሞላ በተማፅኖ ከአምላክህ ስር ወድቀህ ኤሉሄ ኤሉሄ ብለህ መጮህ ግድ ነው ።ከዛም እንደ ሃሰብህ ሳይሆን እንደሃሳቡ መልካም የሆነውን ሁሉ የሚያደርግልህ አምላክ አባት ለልጁ አንደሚራራ በላይ እራርቶ የጠፋውን ተክቶ የጎደለውን ሞልቶ ይስጥሃል ። ግን ሰው ነህና ጎዶሎ ሁሌም አለህ ።ግን አትርሳ የመጀመሪያውን አመስግን ።ሁሌም ቀድሞ በተሰጠህ ነገር ላይ ደጋግመህ አመስግን።ቸል አትበል ።አትደናገጥ።በስጦታ ተቀብለሃልና ከአንተ ለሚሹ ቁረስ ።አበርክት ።ክርስትና ነውና ስም ብቻ አይኑርህ ።የሰጠህን አወቅ።ምንም ሳታደርግ ሁሉን የሰጠህ ከሌሎች አንተ ስለበለጥክ አደለም ።ስለጠየክ ተሰጠህ ።አንተ ተስፋቸው የሆንክላቸውን ቸል አትበል ።ባቅምህ ስጥ።አታማር ።እግዚያብሔር አንተ በደል ስትሰራ ስታዝነው ታገሰህ እንጂ አልተማረረብህም ።አስክትመለስ ጠበቀህ እንጂ አላጠፋህም ።ዝም አለህ ማለት እርሱ የሰጠህን ሃብት ፤ንብረት ፤’ስልጣን አቅም ለሌላቸው በትር መግዣ አታድርገው።ትልቁ ክፋት አሱ ነውና ፤በምድር በሰው ፊት በሰማይ በገሃነብ ትቀጣበታለህ ።ልብ በል ስንቶች ወይም እነማን እንዴት ስም አጠራራቸው ጠፋ ብለህ ከቀደሙት ተማር።ለምንስ ገሚሱ በቤት ሲኖር ገሚሱ በውጭ የሚላስ የሚቀመስ አጣ ብለህ እራስህን ጠይቅ።በጦር ብዛት ፡በዘመድ ብዛት ፤በገንዘብ ብዛት ፡ብቻ በአለህ አትመካ።እርሱ ሁሉን አድራጊ ፈጣሪ ጌታ ከሁሉ በላይ አለና ።ለቀደሙት የተደረገው ሁሉ፡ለቀደሙት የሆነውን ሁሉ፤ ለአንተ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም ።”ሰው ወደደ እግዚያብሔር ወደደ፤ሰው ጠላ እግዚያብሔር ጠላ” ነውና ልብ በል ።ግለሰብ ብትሆን ፤ህዝብ ብትሆን ፤መንግስት ብትሆን ፤ሁሉንም ብትሆን በሰጠኸው ልክ ትቀበላልህ።በበደልከው ልክ ትቀጣለህ ።
መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልን።

መኳንንት ታዬ(ደራሲና ፀሃፊ)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s