የታሪክ መፃጉእዎች _____ [ቬሮኒካ መላኩ]

የታሪክ ተመራማሪዎች ብዙ ጊዜ አንዳንድ ክስተቶች እንዴትና ለምን እንደተፈጸሙ ይጠይቃሉ ። የታሪክ ሊቃውንት የየራሳቸው አስተሳሰብና መሠረተ ቢስ ጥላቻ ይኖራቸው ይሆናል። በዚህም ምክንያት ሥራቸው በአብዛኛው የጸሐፊውን አመለካከት የሚያንፀባርቅ የታሪክ አተረጓጎም ይሆናል።

ታሪክ በየትኛውም አገር ከመዛባት አልፎ የሚበረዝበት ጊዜ አለ። ይሄ የሚከሰተው ታሪክ የፖለቲካ መሳሪያ በሚያደርጉ ቡድኖች ግለሰበችና መንግስታት ነው።
ለምሳሌ Truth in histroy የተባለው መጽሐፍ እንደሚለው ከሆነ በቀድሞይቱ ሶቭየት ኅብረት “የትሮትስኪ ስም ከታሪክ መዛግብት በሙሉ እንዲፋቅ በመደረጉ የዚህ ኮሚሳር ሕልውና ጨርሶ ጠፍቷል።” ትሮትስኪ ማን ነበር? በሩስያ የቦልሼቪክ አብዮት መሪ ሲሆን ከሌኒን በስተቀር በሥልጣን የሚበልጠው አልነበረም።
ሌኒን ከሞተ በኋላ ትሮትስኪ ከስታሊን ጋር ተጋጨና ከኮምኒስት ፓርቲ ተወገደ። በኋላም ተገደለ። አልፎ ተርፎም ስሙ ከሶቭየት ኢንሳይክሎፔድያዎች ተፋቀ። የሚያጋልጡ መጻሕፍትን እስከማቃጠል የሚደርሰው ይህን የመሰለ ታሪክን የማዛባት ድርጊት በብዙ አምባገነን መሪዎች የተለመደ ተግባር ሆኗል ። ኢትዮጵያም ውስጥ ባለፉት 25 አመታት የኢትዮጵያንና የአማራን ታሪክ ለመበረዝና ለማጥፋት ብዙ ስራ ተሰርቷል።
…..
The journal of Oromo studies የምትል እና በዶ/ር አሰፋ ጃለታ ኤድተርነት የሚዘጋጅ journal በአጋጣሚ እጄ ገብቶ ማንበብ ጀመርኩ ። ይሄን መፅሄት ያነበበ ሰው ምርጥ ምርጥ ታሪካዊ ልቦለድና ተረት ጠግቦ ይተኛል ። ተረቶቹ ለህፃን ልጅ ግን አይሆኑም ትንሽ ትራጄዲ ይበዛቸዋል ።
አንዱ ርእስ ” Colonized nations ” ይላል ።ገና ርዕሱን ሥመለከት ተረቱ ተጀመረ አልኩና ” የላምበረት ” ብየ ማንበቤን ቀጠልኩኝ ።

በርእሱ ሥር ሥለ አፄ ምኒልክ የግዛት መስፋፋት እና ውጤቱ ይዘረዝራል ። ዋናው ምንጫቸው ሩሲያዊው ደራሲ አሌክሳንደር ቡላቶቪች የፃፋቸው መፅሃፍት ናቸው ። በአጋጣሚ የዚህን ደራሲ ሥራዎች እኔም ቀደም ብየ አንብቤቸዋለሁኝ ። የኦሮሞ ልሂቃን ብዙ ጊዜ አፄ ምኒልክ የተበታተኑ የቀድሞ የኢትዮጵያን የደቡብ ፣ ደቡብ ምእራብና ደቡብ ምሥራቅ ግዛቶች ለመመለሥ ያደረጉትን ዘመቻ በተመለከተና በዘመቻው የደረሰውን ጉዳት ሲፅፉ እንደ ማጣቀሻ የሚጠቀሙበት ሩሲያዊውን አሌክሳንደር ቡላቶቪችን ነው ። እነ ዶክተር አሰፋ ጃለታን ጨምሮ ብዙዎቹ ቡላቶቪችን ይወዱታል ። በሚፅፉት ልቦለድ ታሪክ ውስጥ ቡላቶቪች እንድህ ብሎ አሌክሳንደር እንደዛ ብሎ እያሉ በፅሁፎቻቸው ውሥጥ ሥሙን መሰንቀር የተለመደ ነው ።
.
አሌክሳንደር ቡላቶቪች ከ1888 ጀምሮ እሥከ 1904 ድረስ አራት ጊዜ እየተመላለሰ ኢትዮጵያን የጎበኘና በአፄ ምኒልክ ዘመቻ የተሳተፈና በአካል ተገኝቶ ዘመቻውን የታዘበ በፅሁፍም ያሥቀረ ደራሲ ነው ።
የኦሮሞ ልሂቃን የቡላቶቪችን ፅሁፎች እየጠቀሱ ሲያቀርቡልን አሌክሳንደር ቡላቶቪች ሥለገለፃቸው የኢትዮጵያ ገናናነት ፣ ሥለ አፄ ምኒልክ ሃያልነት ፣የአመራር ብቃት ፣ ሥለ ሃገሪቱ የሥልጣኔ ፈር ቀዳጅነት ፣ በአፄ ምኒልክ ዘመቻ የተቀላቀሉት የደቡብ ደቡብ ምእራብ እና ደቡብ ምሥራቅ ግዛቶች ቀድሞውንም የኢትዮጵያ ግዛቶች እንደነበሩ የፃፈውን ይዘሉታል ።
.
አሌክሳንደር ቡላቶቪች በመፅሃፎቹ ቁልፍ የታሪክ ክሥተቶችንም ዘግቦልን አልፏል የኦሮሞ ህዝብ ፍልሰትን በተመለከተ እንደዚህ ይለናል ” በ16ኛው ምእተ አመት መሬት የጠበባቸው ዘላን የኦሮሞ ጎሳዎች እንደደራሽ ውሃ ኢትዮጵያን በደቡብ በኩል አጥለቅልቀው በጊቤ በዴዴሳ፣ በአባይና በአዋሽ አካባቢ ያሉትን ለም መሬቶች ያዙ ” ይለናል ። ይቀጥልና ….” የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ግዛትም ሁለት ቦታዋች ተከፈለና ደቡባዊ ክፍል ለብዙ ምዕተ አመታት ከሰሜኑ ተነጥሎ ቆየ ። በ19ኛው ክዘ አጋማሽ ላይ ኢትዮጵያ አድስ ህይወት መዝራት ጀመረች ። በአፄ ቴወድሮሥ የተጀመረው ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ትልም በአፄ ዮኅንስ ቀጥሎ በአፄ ምኒልክ ፍፃሜውን አገኘ ” ይለናል ።
…..
እነሱ እንደማጣቀሻ የተጠቀሙት መፅሃፍ ” Colonized Nations ” ተብሎ በጆርናሉ ላይ የተፃፈውን ቅጥፈት ውድቅ የሚያደርግና በ19ኛው ክዘ ወደ መአካላዊ መንግሥት የተቀላቀሉት አካባቢወች ቀድሞም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ግዛቶች እንደ ነበሩ እዛው ተፅፎላቸዋል ።
የቡላቶቪች ሁሉም ጥራዞች በሚዛናዊነት ቢገመገሙ የምኒልክ የቀድሞ የሃገሪቱን ግዛቶች ወደ ማእካላዊ መንግሥት ለመመለሥ የተደረጉት ዘመቻወች በሰብአዊነትም በሌላም በአሜሪካና በአውሮፓ ለምሳሌ በጀርመን እና ጣሊያን ከተደረጉት እጅግ ሰብአዊ እንደነበር መገንዘብ ይቻላል ።
…..
ለምሳሌ አፄ ምኒልክ ከማእከላዊ መንግስት ለአመታት ተነጥለው ቆይተው የነበሩ ግዛቶችን ለመቀላቀል ያካሄዱትን ዘመቻ አንዱን እንመልከት ።
ከጅማ ጀምሮ እሥከ ኬንያ ድንበር ኦሞ ወንዝ እና ቱርካና ሃይቅ ድረስ ለማስገበር ግዳጅ ከተሰጣቸው የአፄው የጦር አዛዥ ራስ ወልደ ጊዮርጊሥ ነበሩ ። ከራስ ወልደ ጊዮርጊስ ጋር ሩሲያዊው ድፕሎማት እና መልእክተኛ አሌክሳንደር ቡላቶቪች ለ10 ወራት ከራስ ወልደ ጊዮርጊሥ ጋር ሰራዊት ጋር ዘምቶ የታዘበውን የዘመቻ ሂደት With the armies of Menilik በሚል ርእስ በመፅሃፍ ፅፎታል ።

አሌክሳንደር ቡላቶቪች በመፅሃፉ እንዳስቀመጠው ዘመቻው እጅግ ሰብአዊ እንደነበርና ብዙው የደቡብ ግዛቶች በሰላምና ብዙ ሰው ሳይሞት ወደ ማእከላዊ መንግሥት እንደገቡ ገልፆታል ። እስኪ ከመፅሃፉ ካገኘሁት ውስጥ በዘመቻው ጊዜ ራስ ወልደ ጊዮርጊሥ የገበሩ ግዛቶችን እንደት ባለ ፍትሃዊ መንገድ ያሥተዳድሩ እና ዳኝነት ይሰጡ እንደነበር አሌክሳንደር ከፃፈው ውስጥ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ ።

አሌክሳንደር እንደሚከተለው ይለናል ፦ . ” ሰኔ 15 ቀን 1890 ዓ.ም. ራስ ወልደ ጊዮርጊስ ዳኝነት ላይ ሸንጎ ተቀምጠው ነበር ። የራሥን ጥብቅ ትእዛዝ በመተላለፍ ከአገሬው ሕዝብ ከብት ዘርፈው ሲያርዱ የሚገኙ ወታደሮችም ተከሰው ይቀርቡ ነበር ። አማሮች (ሐበሾች) በጾም ላይ ሥለነበሩ በአብዛኛው የሚያዙት ኦሮሞዎች ነበሩ ። ጥፋተኞች አሥር አሥር ጅራፍ የሚፈረድባቸው ሲሆን ቅጣቱ ሲፈፀምባቸው ጅራፉ እንደ ጥይት ሲንጣጣና ሰዎቹ ሲጮሁ በሰፈሩ ሁሉ ይሰማ ነበር ። ምንም ሳይበድለው የአገሬውን ሰው ለመግደል ጥይት ተኩሶ የሳተ አንድ ወታደር አርባ ጅራፍ ተገረፈ ። መሳቱ በጀው እንጅ ባይስተው ኖሮ የሞት ቅጣት እንደሚፈረድበት ጥርጥር አልነበረውም ። ( ከአፄ ምኒልክ ሰራዊት ጋር ) አሌክሳንደር ቡላቶቪች . ገፅ 201 ።

ታሪክ ጸሐፊዎች ሊኖራቸው ከሚችለው መሠረተ ቢስ የሆነ ጥላቻ በተጨማሪ ታሪክ በምናነብበት ጊዜ ግምት ውስጥ ማስገባት የሚኖርብን ሌላው አስፈላጊ ነገር የጸሐፊውን ዓላማና ፍላጎት ነው። ከዚህ በላይ የተጠቀሰው የኦነግ የታሪክ ቀዶ ጥገና ጥሩ ምሳሌ ነው ።
ማይክል ስታንፎርድ A companion to the study of histroy በተባለው መጽሐፋቸው “በባለ ሥልጣኖች ወይም ሥልጣን ለማግኘት ይጣጣሩ በነበሩ ወይም የእነዚህ ወዳጆች በሆኑ ሰዎች የሚጻፉ ታሪኮችን በጥርጣሬ ዓይን መመልከት ይገባል” ብለዋል ።

ዛሬ “በቅኝ ግዛት ያልወደቀች ለነጭ አገዛዝ ያልተንበረከከች” ብለን የምንመጻደቅባት ይህች ኢትዮጵያን ነፍጠኞች እንዳቆዩን ማንም የማይክደው ሀቅ ነው። በዛሬ ገዥዎች እንዲነገር አይፈልግም እንጂ በአወሮፓዊ ማንነት ሳይበረዝ የአሁን ብሔር ብሔረሰቦች ባህላቸውና ቋንቋቸው እንዲጠበቅ ያደረጉት አሁን እያስጨፍራቸው ያለው ኢህአዴግ ሳይሆን በተለያዩ አውደ ውጊያወች ላይ የነጭን ቅስም የሰበሩት ነፍጠኞች ነበሩ።ጊዜው የተገላቢጦሽ ሁኖ የኢትዮጵያን ህልውና ካስጥበቁት አባቶቻችን ይልቅ እርስበርስ የትገዳደሉበት የግንቦት ፳ ባለድሎች ታሪካቸው ጎልቶ ይነገራል። ዛሬ ታሪካችን ታሪክ ቀደው በሚሰፉ በሚበርዙና በሚደልዙ የታሪክ መፃጉእዎች እጅ ላይ ወድቋል። አኩሪ ታሪካችንን ይቀጥል ዘንድ ሁላችንም ሃላፊነት አለብን።

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s