የትግራይ ገዥ ጉጅሌ የማንነታችን ውሃ ልክ አይደለም! (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ

ወያኔ አህዮችን እያረደ ወደ ቻይና ለመላክ የሚያስችል ኢንቨስትመንት ገንብቶ ማጠናቀቁን ተከትሎ በተነሳው ነውጥ ህብረተሰቡ ለሞራል ልዕልናው መከበር ያሳየው መረባረብ የሚያኮራ ነው።ይኽ እኩይ ስርዓት አገሪቱ እንደ አገር ያቆሟትን የሞራል መሰረቶች ለሩብ ምእተ አመት ሲያወላልቅ ህዝባችን ያሳየው ትእግስት አይሉት ቸልተኝነት የት እንዳደረሰው ከፍሬው እየታየ ነው። ወያኔ ዛሬ ወርዶ-ወርዶ የጋማ ከብቶችን ወደ ማረድ የደረሰው ከፊት መስመር የነበሩትን ማንነታችን አፍርሶ ከጨረሰ ቦሃላ ነበር።Right an Wrongs

መቶ ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት አገራችን ዛሬም ሰማኒያ አምስት ከመቶ የሚሆነው ህዝባችን በዋናነት የሚኖረው በገጠር ነው። ዛሬም የገበሬው ኑሮ አፈር መግፋት ነው። አፍሪካ ውስጥ ያለው የአስፋልት መንገድ እርዝመት አንድ ላይ ቢደመር አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ውስጥ ያለውን መንገድ ያህል እንደማይሆን ባንድ ወቅት የ አይ ኤም ኤፍ ጆርናል ላይ ያነበበኩ ይመስለኛል። ኢትዮጵያ ደግሞ ተርታዋ በአፍሪካም ደረጃ ቢሆን የጭራው ደረጃ ላይ መሆኗ ይታወቃል።ስለዚህ ዛሬም ብቻ ሳይሆን በመጭው ዘመን ሳይቀር ገጠሩን ከከተማ የሚያገናኘው የአገራችን ኤንትሬ በሉት ባብሩ የጋማ ከብቱን መሰረት ያደረገ መሆኑ ግልጽ ነው። በዚያ ላይ አህያ በተፈጥሮው እንደ ሌሎቹ የቤት እንስሳቶች ቶሎ ቶሎ የሚዋለድ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ከተወለደም እንዲሁ አድጎ በቶሎ ለጭነት አገልግሎት የሚያሰማሩት እንስሳ አለመሆኑን ለሚያስብ አካል እንዲህ አይነቱን የንግድ ዘርፍ “ስራ” ተበሎ ፈቃድ ሲስጥ በህብረተሰቡ የኑሮ ውድነት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጫና ለማስላት የኢኮኖሚክስ “ሀ -ሁ” ማወቅ አይጠይቅም።

ሰሜን ኮርያን በማስናቅ መቶ ፐርሰንት የፓርላማ ወንበር መያዙን በኩራት የሚናገረው ይኽ አልዛይመር ባለባቸው የሚመራ መንግስት አህያ ማረድ እንኳን በራሱ በአገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ መጸሃፍ ውስጥ የተከለከለ በመሆኑ ለይስሙላም የህግ ማሻሻያ ማድረግ አለብኝ ብሎ ለማስመሰል የሰራው ድራማ አለመኖሩን ለተመለከተ በዚህች አገር እየሆነ ባለው ነገር ላይ ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጠ አመላካች ነገር ነው። የፓርላማውን ወንበር ብቻውን ይዞ ከማንም ሰው ምንም አይነት የተለየ ሃሳብ ላለመስማት ሲባል ብቻ ድንቁርናን በራሱ ላይ በአዋጅ ከዘፈዘፈ መንግስት ነኝ ባይ እንዲህ አይነት እግርና እጅ የሌለው ዜና መስማታችን ሊያስደነግጠን አይገባም። በቶሎ ካልተወገደ ደግሞ ውሎ ባደረ ቁጥር ነገ የምንሰማው ጉድ ከዛሬው የከፋ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም።

ኦሪት፣ ክርስትና እና እስልምና የህብረተሰቡ ስነ ልቦና የማእዘን ዲንጋይ በሆኑበት አገር አህያ የሚያርድ ሰራዊት ሲፈጠር የአገራችን የንግድ ማእከላት ከግለሰቦች እጅ ባልወጣበት እና ማእከላዊነትን የጠበቀ ፍራንቻይዝ ኢንቨስትመንት ገና ባልተጀመረበት አገር ውስጥ እንዲህ አይነት አስተሳሰቦች ወደ ህብረተሰቡ ውስጥ ዘልቀው መግባት ሲጀምሩ ማንም ሰው ቢሆን ነገ በልኳንዳ ቤት የተሰቀለውን ስጋ በሉት በሆቴል ውስጥ ገብቶ የሚያዘውን የምግብ አይነት ቀርቶ ከገባያ በቁሙ ገዝቶ የሚያርደውን በግና በሬ መጠርጠር ቢጀምር ምን የሚደንቅ አይሆንም። አንጻራዊ በሆነ መልኩ የአገራችን የንግድ ልውውጥ የቆመው በመንግስት የህግ ቁጥጥር የጥራት ደረጃ ሳይሆን የሰዎችን ማተብ ብቻ ተስፋ ያደረገ እንደ መሆኑ ይህ መተማመን ደግሞ አንድ ግዜ መሰበር ሲጀምር በንግዱ ህብረተሰብ ላይ የሚፈጥረው የስነ ልቦና ቀውስ ቀላል አይሆንም።

ባህላዊ፣ ትውፊታዊ፣ ሃይማኖታዊ ብሎም ታሪካው እሴቶቻችን በወያኔ ጫማ የሚሰፈሩና ወያኔ ትናንት ከደደቢት አምጥቶ ያደላቸው እቃዎቻችን አይደሉም። እነሱ ትናንት አህያ እየነዱ አዲስ አበባ ደርሰው ዛሬ ዘመናዊ መኪና መንዳት ስለጀመሩ የአግራችን ገበሬ አህያ አያስፈልገውም ማለት አይደለም። እነርሱ ጉግማንጉግ ስለሆኑ ሰው እምነት አልባ ሆን ማለት አይደለም። እነሱ ቁንጣን ስለያዛቸው ሰው ደልቶታል ማለት አይደለም። ባጠቃላይ መሰረታዊው የአገራችን ችግር ከላይ የተቀሙጡት ጥቂት የገዥው መደብ ጉጅሌዎች ቀሪውን የኢትዮጵያ ህዝብ እራሳቸው ዘርፈው በገነቡት የገንዘብ አቅምና የተመረዘ ሰብእና እየለኩ በህግ ስም እያመጡ የሚደፉት መመሪያ በማንነታችን እና በህልውናችን ላይ ጋንግሪን እየሆነ መምጣቱ ነው። በመሆኑም በዚህ ዙሪያ የሚደረጉ ተጋድሎዎች ሁሉ ለማንነት ከሚደረገው ትግል ተለይተው ሊታዩ አይገባም። ጉዟችን እስከ ቀራኒዮ ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s