ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑ እያሉ የሚያላዝኑ ሰዎችን ምን እንበላቸዉ? – ሸንቁጥ አየለ

ለኢሳያስ አፈወርቄ እድሜ መራዘም ጸሎት የያዙ ሰዎች ተክሌ የሻዉ እንዲሞት ጸሎት መያዛቸዉን በአደባያይ እየደሰኮሩ ነዉ::ሳያፍሩ እና ቅር ሳይላቸዉ ተክሌ የሻዉ ደጋግሞ እንዲሞት በአደባባይ እየሰበኩ ነዉ:: ስለ ኢትዮጵያ እቆረቆራለሁ የሚል ቡድን የፖለቲካ ስራዉን ትቶ በአደባባይ ወጥቶ እክሌ ይሙትልኝ ይላል? በእግዚአብሄር ስራ ገብቶ እንዲህ ይፈተፍታል? ምን አይነት ጥላቻ ነዉ? ምን አይነት ስር የሰደደ ነቀርሳ ነዉ?

ጥላቻቸዉ እንዲህ ተራራ ተነካ ምናልባትም ተክሌ የሻዉን ሊገሉት አቅደዉ ይሆን እንዴ? እንዲህ በአደባባይ ተክሌ የሻዉ ካልሞተልን የሚሉት?

ሻቢያ የኢትዮጵያን ተቃዉሞ ለመቆጣጠር የማይፈነቅለዉ ድንጋይ አይኖርም::በኢትዮጵያ ተቃዉሞ ዉስጥ ጎላ ያለ ሰዉ ካዬ ከምድረ ገጽ አጥፍቶ እርሱ የጠፈጠፋቸዉን እና እርሱ የሚቆጣጠራቸዉ ሀይሎች ብቻ ገነዉ እንዲወጡ የማይሰራዉ ደባ የለም::እናም አሁን ተክሌ የሻዉ ጥቂት እየጎላ መጣ መሰለኝ:: እናም መጀመሪያ ተክሌ የሻዉ ይሙት የሚል ጸሎት በአደባባይ ተይዟል::

ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይጨነቃል ይሉሃል::

ተክሌ የሻዉን አናምነዉም::ኢሳያስ አፈወርቂን ግን እናምነዋለን ይሉሃል:: ተክሌ የሻዉ ደርግ ስለ ነበረ አናምነዉም ይሉህና::የኢትዮጵያን ክብር አዋርዶ ኢትዮጵያን ብትንትኗን ያወጣትን ኢሳያስ አፈወርቂን ግን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነዉና እመኑት ይሉሃል::ባንዳ ከባህሪዉ ሁሉ የሚያስጠላዉ እፍረትም የለዉምና ሳያፍሩ የኢሳያስን ሬሳ በአደባባይ ይዘዉ እየዞሩ እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያንን ግን ይሙቱልን : ይጥፉልን ይሉሃል:: እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያንን በደርግነት ይከሷቸዋል::

ደርግ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲጋደል የወደቀ መንግስት ብሎም ወያኔን እና ሻቢያን ልክ ለማስገባት መከራዉን ያዬ የኢትዮጵያ ልጅ እንጅ የኢትዮጵያ ጠላት አይደለም::ደርግ ስህተት ቢሰራም ስህተቶቹን የሰራቸዉ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነዉ እንጅ እንደ ወያኔ እና እንደ ሻቢያ ኢትዮጵያን ለምጥፋት ብሎ አይደለም::

ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲጨነቅ ዉሎ ሲጨነቅ ያድራል ይሉሃል::ለኢሳያስ አፈወርቂ እድሜ መራዘም ጸሎት ያዙ::ለተክሌ የሻዉ ቶሎ መሞት ደግሞ እኛ እያሟረትን ነዉ ብለዉህ ቁጭ:: ጉድ እኮ ነዉ::

ለምደዋላ::እነዋለልኝን መልምሎ እና አሰማርቶ የአማራን ህዝብ እና የኢትዮጵያን ህዝብ ሆድና ጀርባ አድርጎ እስከዛሬ ድረስ መርዛማ ጽንሰ ሀሳብን በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አዕምሮ የጠቀጠቀዉን እና ወያኔን ጭንቅላታን ላይ ያስቀመጠብንን ኢሳያስ አፈወርቂን ሲማልዱ ዉለዉ ሲማልዱ የሚያድሩት ጸረ ኢትዮጵያዉያን ሀይላት እራሳቸዉን በኢትዮጵያ አንድነት ስም ጠርዘዉ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑት ተክሌ የሻዉን ግን አትመኑት የሚል ለቅሶ ያላዝናሉ::ኢሳያስ አፈወርቂ ለምዷል::እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያንን ከኢትዮጵያ ተቃዉሞ በማስወጣት የኢትዮጵያን ፖለቲካ በምናምንቴዎች ቁጥጥር ስር እንዲሆን ማድረግ ለምዶበታል::አሁንም እንደዚያ ማድረግ የሚቻል እየመሰላቸዉ ዘጥ ዘጥ የሚሉ ሀይሎች አሁንም አፍርቷል::

ከስንቱ አስመሳይ እና ባንዳ ጋር እንዋጋ ጃል? ጠላት ላለማብዛት ብዙ ዝም ስንል እያንዳንዱን የሻቢያን ደባ የማናዉቅ መስሏቸዋል:: ለኢሳያስ አፈወርቂ እድሜ መራዘም ጾሎት ይዘዉ ተክሌ የሻዉ ግን ይሙት የሚል መዝሙራቸዉን በአደባባይ ለቀዋል::

ምድረ ጸረ ኢትዮጵያዊነት እና ጸረ አማራ ከህዝባችን እራስ ላይ አልወርድ አሉ እኮ::

ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑት አሉ?….

ሆይ ሆይ….

የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም ደግሞ የአማራን ህዝብ እንዴት ቢንቁት ነዉ ግን ከተክሌ የሻዉ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂን እመኑት እያሉ ሳያፍሩ ልሃጫቸዉን የሚያዘሩት?

ብንከባበር መልካም ነዉ

ከትህትና እና እና ፍቅር በቀር ማንንም የመፍራት መንፈስ የለንም:: እናም እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን አትንኩ::

እዚያዉ ለኢሳያሳችሁ እድሜ መራዘም ጸሎታችሁን ያዙ::እርሱን የከለከላችሁም አታድርጉ ያላችሁም የለም::ከተክሌ የሻዉ እራስ ላይ ግን ዉረዱ::

መከባበሩ ይሻላል !

ልባችን በብዙ ጥቃት የቆሰለ ኢትዮጵያዉያን ነን እና ሌላ ህመም አትጨምሩልን::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s