Ethiopia: ዉድ የአማራ ልጆች (ዶ/ር አቤል ጆሴፍ)

ከፌስ ቡክ እንድለይ ያስገደደኝ ነገር ክብሬ ስለተነካ ወይም ፎቶዬን ጥቂት ወረበሎች ለጥፈዉ ስም ለማጥፋት ስለሞከሩ አይደለም፤ እንደዛማ ቢሆን ኑሮ የግንቦት ሰባትና የወያኔ ቡችሎች ፎቶዬን ለጥፈዉ ለማሸማቀቅ በሞከሩ ጊዜ ነበር ከፌስ ቡክ ሆነ ከትግል አለም የምሰናበተዉ።ለማታዉቁኝ ጎንደሬ ነኝ፤ ከጎንደርም ከጀግናዉ የቆላ ወገራ ጸለምትና ሰሜን ጃናሞራ ህዝብ ለራበዉ እንጀራ ለጠገበዉ ጥይት ከሚሰጥዉ የተወለድኩ፤ በአማራነቴ ሆነ በኢትዮጵያዊነቴ የምኮራ ግለሰብ ነኝ።

እኔ አንድ ተራ ሰዉ ነኝ፤ ከኔ ክብር ይልቅ የአማራ ህዝብ ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚበልጥ እረዳለሁ፤ ይሁንና ከሁሉም ነገር ያሳሰበኝና ተስፋ ወደ መቁረጥ አዝማሚያ የወሰደኝ፤ የአማራዉ የራስ አድን እንቅስቃሴ፤ አማራን ከወያኔ መዳፍ ለማዳንና የራሱን ህልዉና ሆነ ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሆነ ሳይሆን፤ ሆነ ተብሎ አማራዉ ኢትዮጵያን አፈራርሶ የራሱን መንግስት ለመመስረት ተደርጎ ሲቀርብ በመመልከቴና፤ ይህን ተግባር የሚያራምዱት በግንባር ቀደምት አማራ ነን ባዮች መሆናቸው ነዉ።

እንደሚታወቀዉ የአማራዉ ትግል በትግራይ ፋሽሽቶች ከተደቀነበት የጅምላ ጭፍጭፋ እራሱን ማዳን ትግል እንጅ ወያኔና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንደሚፈልጉት ኢትዮጵያን አፈራርስ ትንንሽ ሃገሮች ለማቋቋም አይደለም። ሃ እራስን ማዳን ነዉ እንዲሉ አማራዉ መጀመሪያ እራሱን ከጥቃት መከላከል፤ ከዛም እንደሁኔታዎች በሂደት መስመር የሚያስዛቸውን ነገሮች የራሱን ጥቅምና ህልዉና በማይጋፋ ሁኔታ ማስያዝ ነዉ የሚሆነዉ።

በዚህም ሂደት ዉስጥ ከሌሎች ኢትዮጵያኖች ወገኞቹ ጋር በሰላምና ጥቅሙን በማይጋፋ ሁኔታ የጋር መንግስት መስርቶና ሁሉም በየመጠኑ ተወካይ የሚኖርበት፤ የህዝብ ድምጽ የተከበረበትና ሰዉ ሳይሆን ህግ ወይም ህገ መንግስት ንጉስ የሆነበት ስርአት መስርቶ መኖር የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፤ ያ ካልሆንነና አብሮ የመኖር በሩ ተዘግቶ፤የሁሉም ህዝብ ፋልጎት ተነጣጥሎ መኖርና የየራሱን ትንንሽ ሃገር መስርቶ መኖር ከሆነ ደግሞ አማራዉ የራሱን ሃገር መስርቶ ይኖራል።

የአማራን የራስ አድን ትግል ኢትዮጵያን አፍራሽ ትግል አድርጎ ማቅረብ፥

ይህ ሁኔታ ወያኔ የከፈፍለህ ግዛዉ ተግባሩን ለማጠናከር የሚጠቀምበትና አማራዉ መሬትንህን ነጥቆ የራሱን ሃገር ሊገነባ ነዉ በማለት አማራ መንግስት እንመሰርታለን ባዮች በካርታቸው ባጠቃለሉት ህዝብ ላይ ከፈተኛ ቅስቀሳ እንዲያደርገና የነሱን ጸረ አማራ ድጋፍ ለማግኘት የሚጠቀምበት ነዉ፤ ስለዚህ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች እንዲኖሩና አማራዉ ኢትዮጵያን አፍርሽ ተብሎ እንዲቀርብ እየተደርገና ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች ከነበራቸው በላይ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ እንዲያሳድሩና; አማራ መጣብህ አይነት ማስፈራሪያ ወያኔ እንዲጠቀም እየተደረገ ነዉ።

የአማራዉን ስብስብ የወሮበላ ስብስብ ማስመሰል፥

በዚህ ላይ ወያኔ ካድሬዎችን በማሰለፍ አማራ መስለዉ እንዲሳደቡና በተለይም ከአማራ ህዝብ የማይጠበቁ ጸያፍና አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም የአማራዉ ስብስብ ተራ የወሮበላ ስብስብና በሌሎች አስተዋይ አማራዎች ድጋፍ እንደሌለዉ አድርጎ ለማቅረብ ከፈተኛ ዘመቻ እያደረገ ነዉ፤ ለዚህም ተግባሩ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ብዙ የአማራ ልጆች የስድብ ባለሙያወች ሆነዉ ወጥተዋል፤ በተለይም የአማራ ምሁራንና በሳል ሰዎች ወደ ትግሉ ጎራ እንዳይቀላቀሉ ሆን ተብሎ የሚሰራ ተንኮል ነዉ።

የአማራ ጸንፈኞች መኖር ሌሎች ጽንፈኞችን ማሰፈራሪያ ይሆናል፤

ይህ የተሳሳተ ግንዛቤ ነዉ ምክንያቱም ጽንፈኞችን የሚፈራዉ በሌላ ጎራ ያለው ጽንፈኞ ሳይሆን፤ አብሮ የመኖር ፍላጎት ያለዉ ህዝብ ነዉ። በሌላ ጎራ ያለዉ ጽነፈኛማ የመገንጠል አላማ ስላለዉና አብሮ የመኖሩን ሰንሰለት የሚበጣጥስለት ከሌላዉ ጎራ ጽንፈኛ መኖሩ የራሱን ፍላጎት ያጎለብትለታል፤ ደስም ይለዋል፤ ህዝቦችን ለዘመናት አስተሳስሮ የኖረዉን መረብ ሌላ መጋዝ ይዞ የሚቆርጥለት ሲያገኝ እንዴት ነዉ የሚፈራ፤ ድግስ በድግስ ይሆናል እንጅ።

ወያኔ ሆነ ሌሎች አምባገነኖችን የሚያስፈራቸው በህዝቦች መካከል የሚኖረዉ የጠነከረ ግንኙነት ነዉ፤ ለዛም ነዉ ወያኔ ሁሌ በርግጠኝነት በአማራን በኦሮሞ ህዝብ መካከል ያለዉ ግንኙነት ምንም አይነት ጥንካሬ እንዳይኖረዉ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራዉ፤ ምክንያቱም ሁለቱ ህዝቦች በጋር ጠላት ላይ ቢነሱ፤ የወያኔ ቀን ቁጥር እንደሚሆን ያዉቀዋል።

ለጽፈኞች መልሱ ጽንፈኝነት ሳይሆን፤ ጽንፈኝነትን ያጋለጠና የራስን ፍላጎት ያስጠበቀ ህዝባዊ ድጋፍ ያለዉ አቋም መያዝ ነዉ፤ ሁለት ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸው መሳሳብ አይችሉም፤ ስለዚህ ይህ የጽንፈኛ አቋም ወያኔም ሆነ የ ኦሮሞ ጽንፎኞች የሚያስቡት ኢትዮጵያን አፈራርሶ ትንንሽ መንግስት መመስረት ህልም እዉን እንዲያደርጉ የሚረዳና ጽንፈኛ ተግባራቸውን በ አማራዉ ህዝብ ህጋዊነት እንዲያገኝ የሚረዳ አካሄድ ነዉ። እናነተም ተገንጠሉ እኛም እንገነጠላለን ነዉ ነገሩ።

ዋናዉ ቁም ነገር ግን ትንንሽ ሃገራት መመስረቱ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ አይነት ክልሎች በዉል ያልታወቁበትና ህዝቦች ተሰባጥረዉ በሚኖሩበት ምድር ሃገር ምስረታዉ ቀጣይ የእርስ በእርስ ጦርነት እንደሚያስከትልና ሃብስ (Hobbes- war of all agisnt all) እንዳለዉ ጦርነቱ ሁሉም ከሁሉም ጋር የሚዋጋበት ይሆናል፤ ማለትም ቀጣይና የማያባራ ጦረንት ይገጥመናል።

የአማራ ድርጅት መኖር፤

የ ኢትዮጵያ የፖሊትካ ትግል ዉስብስብ የሆነ ስለሆነ፤ በርግጥ የሚኖረዉ አማራጭ ሁለት ነዉ፤ አብሮ መኖር ወይም ያዉ ትንንሽ ሃገሮችን መስርቶ መኖር።

አብሮ የመኖር ሁኔታ በርግጥ በ አብዛኛዉ የሚደገፍና በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አይነት ድሃ ሃገር ህዝቦች አብሮ መኖሩ ከመበታተኑ ጠቀሜታ ይኖረዋል፤ ለዚህም ሁሉም ብሄሮች ተስማምተዉ የሁሉንም ጥቅም ማስጠበቅ የሚችልና አድል ኦ የሌለዉ፤ ሁሉም የየራሳቸው ተወካይ የሚኖርበት፤ አንዱ የ አንዱን ጥቅም የምያጋፋበት የጋር መንግስት መመስረቱ ወሳኝ ነዉ።

በዚህም የጋር መንግስት ምስረታ አማራዉ የራሱን ድርጅት ኑሮት ከሌሎች ጋር በወንድማማችነት የራሱን ጥቅም በማስጠበቅ የሚቀጥለበት ሁኔታ ይኖራል፤ ለዛም ነዉ አማራዉ በ አማራነት ተደርጅቶ የ አማራዉን ህዝብ ፍላጎት ማስጠበቅና አማራዉ ከጥቃት መከላከል የግድ የሚለዉ።

እንደ ኢትዮጵያ አይነት በብሄር የተከፋፈለ ሃገር የግድ የብሄር ድርጅቶች መኖር ያስፈልጋል፤ ያ ማለት ግን ህብረ ብሄር ድርጅቶች አይኖሩም ማለት አይሆንም።

ይሁንና የ አማራዉ የብሄር ድርጅት መኖር የግድ የሚልና አማራዉ ከሌሎች ጋር በሚፈጥረዉ የጋር መንግስት የራሱን ድርሻ የሚወጣበትና ጥቅሙን የሚያስጠብቅበት ስለሆነ፤ የ አማራ ድርጅት መኖሩ ክርክር ዉስጥ የሚገባ አይሆንም።

ሃገር ምስረታ

ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነዉ አበዉ ሲሉ ምን ለማለት ፈልገዉ ነዉ፤ አንድ ነገር ስትሞክረዉ ነዉ እንጅ ሳትሞክረዉ ቀላል ነዉ የሚመስልህ ለማላት ፈልገዉ ነዉ።

አንዳንዶች ሃገር መመስረት እንደ ኬክ መቁረስ አቃልለዉ ሲያዩት እንመለክታለን፤ ይህ የተሳሳተ አመለካከት ብቻ ስያሆን፤ ግንዛቤ የጎደለዉ አ እሞሮ የሚያፈልቀዉ ቅዥት ነዉ።

ሃገር ምስረታ በተለይ ከስለጣኔ አለም ለተጣላዉ አፍሪካ ከባድ መሆኑን መረዳትና ሃገር መሰረትን ያሉት ኤርትራያኖች ለምን የ አዉሮፓንና የ አርብን መንገዶች እንዳጣበቡና፤ በሜድትራንያንና በቀይ ባህር ስንቶቹ ህየወታቸው እንዳለፈ መወቅ የግድ ይላል።

ሃገር ምሰረታ ብዙ ቅድመ ባንዴራ ማዉለበልብ ወይም መዝሙር መዘመር አይደለም፤ ነገር ግን ቅድመ ሁኔታዎች ያስፈልጉታል፤ ህዝቦች እራሳቸውን የሚያስችል ነገሮች መኖራቸውንና በተለይም አሁን አለም በካፒታሊስቱ ማርኬት ቁጥጥር ስር ባለችበት ሁኔታ፤ ከባርነት ሊያላቅ የሚችለ የሰዉ ሃይል ማለትም አምራችና ፈጣሪ የሆነ፤ ብሎም ብቁ የሆነ አንጡራ ሃብት ያስፈልጋል፤ ይህ በሌለበት ሁኔታ ሃገር ለመመስረት መሞክር በራስ ላይ ገመድ እንደ ማስገባት ይቆጠራል።

ወያኔ በ አማራዉ ትግል ሰርጎ ገብትዋል፥

ወያኔ አማራዉን ጭራቅና ሰይጣን አድርጎ ላለፉት አርባ አመታት የሰራበትና አሁን ደግሞ አማራዉን እንደ ጸረ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያን አፍራሽ አድርጎ በማቅረብ የሌሎችን ብሄሮች ድጋፍ ለማግኘትና አማራዉን ነጥሎ ለመምታት ትልቅ ስራ እየሰራ ነዉ።

ለዚህም ስራዉ ሆድ አደር አማራዎችን መግዛትና በ አማራዉ ትግል ሰርገዉ እንዲገቡ ማድረግ ነዉ።

ጎቤን ከመግደል ጀሞሮ የ አማራ ታጋዮችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ታጋይ አስመስሎ በበርሃም ሆነ በከተማ እንዲሁም በዉጩ አለም ያሰማራቸው ደሞዝተኞች ሞልተዉታል።

ዛሬ የ አማራ ገበሬዎች የሚያደርጉት እንቅስቋሴ በራሱ በገበሬው ማለትም ታጋይ መስሎ በሚቀርበዉ እንዲገታና፤ ግንኙነታቸው እንዲሰናከል እየተደረገ ነዉ።

ለምሳሌ ከወልቃይትና ከጠገዴ ተንቀሳቀሰዉ በዳበት አልፈዉ በለሳ የሚሄዱ የነበሩት ግንኙነታቸው እንዲቋረጥና ሳይታሰብ አደጋ እንዲደርሳባቸው እየተደረገ ነዉ።

ከጃንወራና ከቦዛ በደባርቅ አልፈዉ ጃናሞራ ብሎም ጸለምት እየተንቀሳቀሱ የነበሩት ከፋኞች እንዲሁ እንቅስቃሴ አቸው ተገትትዋል።

በከተማም ሆነ በዉጩ አለም፤ እንዲሁ የ አማራዉን ትግል ለመከፋፈልና አማራን መጥፎ ስም ለማሰጠት ወያኔ ቅጥረኞቹን አሰማርትዋል።

ባጠቃላይ ወያኔ ባለዉ የገንዘብ ጉልበት እየተጠቀመና፤ ሆድ አደር አማራዎችን እየተጠቀመ የ አማራዉ ትግል ከፌስ ቡክ እንዳያልፍ እያደርገው ነዉ።

ለምሳሌ አንዳንድ የ አማራ ድርጅቶች ጎንደር ቦንብ የሚያፈነዱ እነሱ እንደሆኑ ይናገራሉ፤ እዉነቱ ግን ቦንቡን የሚያፈነዳዉ እራሱ ወያኔ ነዉ።

ባጠቃላይ የአማራዉን ትግል ለማኮላሽትና አማራዉን ለመነጠል ወያኔ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ ስለሆነ፤ ለ አማራ ህዝብ እናስባለን የምንል ከስሜት በወጣ ሁኔታ ነገሩን በ አበክሮ መመልከትና፤ በተለይም አስተዋይ ሰዎች ያለዉን ሻጥር ከመጋረጃዉ በስተጀርባ መመልክት ጥሩ ነዉ።

ፖሊቲካ ሳይንስ መሆኑንና አስተዋይ ጭንቅላት የሚፈልግ እንጅ እንዲህ በዘፈቀደ አካኪ ዘራፍ በማለት የሚካሄድ አይደለም።

ዶ/ር አቤል ጆሴፍ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s