” ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች ” [ቬሮኒካ መላኩ]

የሮሙ ቄሣር ኔሮ በዕብሪት ልቡ አብጦ ሮማ ከተማ ላይ እሳት ለኩሶ ከተማይቱን በእሳት ስትጋይ እየተመለከተ ሠገነቱ ላይ ቁጭ ብሎ ሙዚቃ እየሰማ እና ክራሩን እየተጫወተ ሰው ሁሉ ነፍሱን ለማዳን ሲራወጥ ከተማይቱም አመድ ሲትለብስ እየተመለከተ በደስታ እየሳቀ ግርግሩን ይመለከት ነበር።
ለቀናት ለተራቡ አንበሳና ነብር ክርስቲያኖችን ወርውሮ ኮለሲዩም ስታዲዮም ውስጥ -ዳቦና ጨዋታ ለተራው ሕዝብ በሚባለው ፍልስፍና- በአውሬዎች ሲቦጫጨቁ ቄሣሩ ከትዳር ጓደኛዋ ጋር ወይኑን እየተዝናና ይጎነጭ ነበር ።
በፈሪነትና የሚታወቀውና በክርስቲያኖች የመንፈስ ጥንካሬና ጀግንነት የበታችነት ስሜት የሚሰቃየው ልቡን የሚያርደው ኔሮ በእብሪትና በሰው ስቃይ የሚደሰተው አንድም ቀውስ ስለነበር ነው በሌላ በኩልም ከተጠናወተው የበታችነት ስሜት የሚድን እየመሰለው ነበር።

አውስትሪያ ቬና ተወልዶ ጀርመን ውስጥ ስልጣን በመያዝ አውሮፓን በደም ጎርፍ ያጥለቀለቀው የጀርመኑ ቀውስ አዶልፍ ሂትለር በ 1933 ስልጣን ላይ እንደወጣ በርሊን አደባባይ ተሰብስቦ ለሚጠብቀው ህዝብ ወደ መነጋገሪያ ሰገነቱ በመውጣት “ማንም የማይበግረን ንፁህ ዘሮች ነን። እኛ የአሪያን ዘሮች ለቀጣዩ 1ሺህ አመታት አውሮፓን በበላይነት እንገዛለን !” ብሎ ሲጮህ ደጋፊዎቹ በስሜት ሰክረው እጃቸው እስኪላጥ ያጨበጭቡ ነበር ። ለአንድ ሺህ አመታት የታቀደው ሶስተኛው ሪህ በመባል የሚታወቀው ናዚ በ 12 አመታት አከርካሪውን ተመትቶ 1945 ግብአተ መሬቱ ተፈፀመ።

የቀድሞው የህውሃት መሪ መለስ ዜናዊ 1983 ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ መቀሌ አደባባይ ለተሰበሰበው የትግሬ ህዝብ ” እንኳን ከእናንተ የወርቅ ዘሮች ተወለድኩ! ” እያለ በእብሪት ስካር ሲጮህ መቀሌ አደባባይ የተሰበሰበው የትግሬ ህዝብ እጁን እስኪደክመው አጨበጨበ ። በስሜት የተቃጠሉትና መጭው ጊዜ የሚያመጣውን መከራ ያልተገነዘቡት የወያኔ ደጋፊዎች በዚያ መርዛማ ንግግር አታሞ ሲመቱ እንደሰነበቱ ይታወሳል።

እስር ቤት 99% ገራፊዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው… ግድግዳ ግፉ ይሉንና ሲያቅተን እኛ ትግሬዎች እንዲህ ነን ይሉናል ” ይሄን የተናገረው ትናንት ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ሃብታሙ አያሌው ነው። ይሄን ንግግር ቀጥታ በፌስቡክ በሚተላለፈው Live ስሰማው የአዶልፍ ሂትለርና የመለስ ዜናዊ ንግግርን አስታወስኩኝ።

ወያኔዎች በሸአቢያ ታንክ ታጅበው አዲስአበባ እንደ ገቡ የፃፉት መፅሃፍ ” ተራራን ያንቀጠቀጠው ትውልድ ” የሚል ነበር ።
በዚህ አስቂኝ መፅሃፍ የሌላቸውን ጀግንነት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊግቱት ሲሞክሩ አላማቸው ራሳቸውን ማግዘፍና ሌላውን የማሳነስ ስትራቴጅ እንደሚከተሉ አመላካች ነበር ። ባለፉት 40 አመታት ወያኔዎች የትግራይ ህዝብ ከሌላው የተለየ DNA እንዳለው ሲግቱት ኖረዋል ። ይሄ ነገር በጣም አስቂኝ ነው። የእነሱ የሆነ ሁሉ የተለየ ጀግና አ ንደሆነ አምነዋል ። ደሳለኝ እያሉ የሚጠሩት እና መቀሌ ሃውልት የሰሩለት አህያቸው በአለም ላይ ካሉት አህዮች በተለየ ምርጥ ጀግና ነው ብለው የሚያስቡ አስቂኝ ፍጥረቶች ናቸው። ባዶነታቸውንና ቦቅቧቃነታቸውን በባዶ ፕሮፓጋንዳ ሊያሰማምሩት ቢሞክሩም እውነታውን ሊበሸፍንላቸው አልቻለም። ተራራን አንቀጠቀጥን ያሉት ወሽካቶች ተራራ መካከል የተወለዱ አይጦች እንደሆኑ በግሃድ ታየ።

ወያኔ ባለፉት 25 አመታት የአለም ታሪክ አንቅሮ የተፋውን የ19ኛውን ክፍለ ዘመን መርህ እንደገና ተግባራዊ በማድረግ አናሳነታቸውን ፣ የአእምሮ ዝቅተኛነታቸውንና የበታችነታቸውን በ ” አርያን ዘር ምርጥነት ተረት ” ቢቀባቡትም ሊሰራላቸው አልቻለም ። ለመቶ አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ እርስ በርሱ እያጣላን እኛ እየገዛን እንኖራለን ብለው እቅድ ቢነድፉም ህልማቸው ወደ ቅዤት ተቀይሮ ኮማ ውስጥ ይገኛሉ።

እስከ ባለፉት ሁለት አመታት ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ አይነቱ ዘግናኝ ድርጊት ከንፈር ከመምጠጥ ያላለፈ ምላሽ ሲሰጥ አልታየም ነበር
ወያኔዎች በ 19ኛው ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የሚመሩና የ21ኛው ክፍለዘመን ዘመን የሚኖሩ እንስሳቶች ናቸው። የወያኔ ባህሪ ፋሽስት ፣ ጠባብ ብሄረተኛ ፣ዘረኛ ፣አንጎላቸው ያልዳበረ ነው።።

ወያኔዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳያቸውን ትእግስት እንደ ፍርሃት በመቁጠር በጣም ንቀውት ነበር ። ጀግኖቹ እኛ የትግራይ ልጆች ብቻ ነን፥ ሌላዉ ፈሪና የማይረባ ነዉ እያሉ እንደሚናገሩና ከዛም ተጨማሪ የሚያደርጉት ግፍ ለንቀታቸዉ ምስክር ነዉ።
በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት የጀርመን ናዚዎች የአለምን ህዝብ በመናቅ፤ እኛ የአርያን ዘሮች ነን አለምን መግዛት ያለብን በሚል እብሪት ተነሳስተዉ ነበር የሁለተኛዉን የአለም ጦርነት የለኮሱት ።
እብሪት ከዉድቀት ትቀድማለች እንዲሉ፤ እብሪተኞቹ የናዚ መሪዎች የተማመኑበት ሰራዊታቸዉ፤ በጀግናዉ የሶቬየት ህብረት ቀዩ ጦር አከርካሪው ተመትቶ እንደጉም ሲተን፤ መድረሻ ነበር የጠፋቸዉ ። ተቀናቃኝን ገጥሞ የክበር ሞት ከመሞት ይልቅ የገዛ ህይወታቸዉን ግማሾቹ ሲያጠፉ የተቀሩት ደግሞ እግሬን አዉጭኝ ብለዉ ነበር የፈረጠጡት።

የወያኔ ባህሪም ከናዚዎች የተለዬ አይደለም፤ የኢትዮጵያን ህዝብ በመናቅና ምን አባቱ ያደርገናል በሚል እብሪት ተነፋፍተዉ ህዝቡን እያሰቃዩትና ከሰዉ ተራ እንዲወጣ አድርገዉታል።
ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከት የተጨቆነ፤ እና ነፃነትን የተራበና የተጠማ ህዝብ መነሳቱ የማይቀርና፤ ለችግሩ መንስኤ የሆኑትን መፋረዱ የማይቀር መሆኑ እየታየ ነው። የትግሬ ህዝብም ዶዜጁ ከበዛው የፕሮፓጋንዳ ሃሽሽ እየነቃ ይመስላል።
እስከ አፍንጫዉ የታጠቀዉን የናዚን ጦር የሶቪየት ህብረት ቀዩ ጦር አከርካሪውን እንደሰበረው ሁሉ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን የወያኔ ጦር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዜና ዘጋቢ IRIN የተራራ ላይ አንበሶች ብሎ የጠራቸው የጎንደር ገበሬዎች በነፍስ ወከፍ መሳሪያ መድረሻ እያሳጡት እንደሆነ እየተሰማ ነው።

በኢትዮጵያ ባህልና ልማድ ክብር ለማግኘት የግድ ሃይል ያስፈልጋል። ሃይል ከሌለ ክብር የለም። ክብር ከሌለ ህይወት የለም። በልመና ወይም በድርድር ክብርና ነፃነትን ማግኘት ህልም ነው።
ትናንት ጦርና ጋሻ ፣አንካሴና ጎራዴ፣ውጅግራ ጠበንጃና ምንሽር የያዙ ብሎኮና ነጠላ በርኖስና ካባ የደረቡ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ነፍጠኞች መድፍና መትረየስ ቦንብና ዘመናዊ ጠበንጃ ሽጉጥና ሴንጢ ይዘው ታጥቀው በጥይት ሊቆሉአቸው መለዮ ኮፊያቸውን አድርገው መሽግው የጠበቋቸውን ፋሽስቶች ድል ነስተው አሳፍረው የመለሱ ወገኖቻችን ዛሬም የእነዚህን አገር በቀል ፋሽስቶች እብሪት እየደረመሱት ይገኛሉ።

በላዬ ሰቦቹን እንዴት እንስፈራቸው? (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ

“ካኒባሊዝም” ስርዎ ቃሉ የሚመዘዘው “ካሪብ” ከሚለው የስፓኒሽ ቃል ሲሆን ትርጉሙም የሰውን ስጋ የመመገብ ልማድ ያደረጉ ስዎችን ለመግለጥ የሚያገለግል ነው፤: እኔ የሰውን ስጋ የሚበሉ ሰዎች እንዳሉ ለመጀመሪያ ግዜ የሰማሁት በልጅነት በዕለተ ሰንበት ከተዓምረ ማርያም ሲነበብ ነው፤ ልጅነት አቅመቢስ አድርጎን ኖሮ በግዜው ባንረዳውም ቅሉ ሃይማኖት ነውና ተቀብለነው ኖረናል።

Ethiopia, TPLF officials

በማስከተልም በበረራ ቁጥር 571 እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1972 መስመሩን ስቶ ላቲን አሜሪካ የበረዶ ግግር ጋር ተጋጭቶ በወደቀው የዩራጋይ አውሮፕላን ውስጥ ከአደጋው የተረፉት ተሳፋሮች ለብዙ ቀናት በበረዶው ውስጥ ተይዘው በከረሙ ግዜ ህይወታቸውን ያተረፉት አንድ ያንዱን ስጋ እየበላ እንደነበር ወደ አማርኛ በተተረጎመው “የተራራው ምርኮኞች” በሚል መጸሃፍ ተጽፎ ካነበብነው ጀምሮ ቦብ ጊዶልፍ በሰራው አንድ ዶክሜንተሪ ውስጥ በምእራብ አፍሪካ ያሉ ሰዎች በጣም የሚወዱት ጓደኛቸው ሲታመምና የማይድን ሲመስላቸው እራሳቸው ቀድመው እንደሚበሉት በቦታው ተገኝቶ የታዘበውን ትራጀዲ በምስል አስደግፎ ያቀረበው ዘግናኝ ታሪክ፤ ከኮንጎ ጫካዎች እስከ ላቲን አሜሪካዎቹ ደሴቶች፣ ከስታሊን ግራድ ላይ በጀርመን ወታደሮች እስከ አስራ ዘጠኝ ስልሳው አሰቃቂው የቻይና የእረሃብ አመታት የተፈጸሙ የሰውን ስጋ ለምግብነት የዋለበት ጥቁር ታሪክ መዘርዘር ይቻላል።

ቦካሳ የተባለ የሴንትራል አፍሪካ አምባገነን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹን በማሰር ወይም በመግደል ብቻ የሚረካ አልነበረም። ይልቁንም በማይክሮዌቭ ጭምር እየጠበሰ ይበላቸው እንደነበር ዘገባዎቹ ገሃድ ወጥተዋል። ይኽ ሰው ስልጣን በያዘ ማግስት የአገሪቱን ፋብሪካዎች በመውረስ በራሱና በሚስቱ ስም ያደረገ ሲሆን ብዛታቸው አምስት መቶ ገደማ የሚሆኑ የአንድ አንደኛ ደረጃ ትቤት ተማሪዎች በሚስቱ ስም ከተመዘገበው ፋብሪካ በአንዱ የተመረተውን ዩኒፈርም “ከለሩን አልወደድነውምና አንለብስም” በማለታቸው የተነሳ ነፍሰ ገዳዮቹን ልኮ ሁሉንም ህጻናት በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ ያስገደለ አረመኔ ነበር። ሃይማኖት ነፍስን ብሎም ባህልና ልማድን ጭምር የሚቀርጽ በመሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አንዳቸውም ቢሆን በኛ ደረጃ እንደ ማህበረሰብ በኦሪያትዊ ትውፊት መኖርን ያልጀመሩ፣ ሐዲሱም ያልሰረጸባቸው፣ይልቁንም ዘግይቶ ከተጫነባቸው (ሃይማኖት) ይልቅ የራሳቸው ወደ አውሬነት ደረጃ የወረደ ባህል ገኖባቸው የወጡ ሆኑ እና ምንም አደረጉ ቢባል ብዙም ላያስደንቅ ይችላል።

በሃይማኖት መኖር ኋላቀርነት ነው ተብሎ፤ ከምስራቅ በተነሳው የኮሙኒዝም ሰደድ ሰላባ መሆን በጀመርንበትና እኛም ግራ እጃችንን በቀሰርንበት የለውጥ ማእበል ዋዜማ ገና በወራዙትነት እድሜያቸው ወደ አሲምባ ያቀኑት ዶር ብርሃኑ በአንድ ወቅትከ ሌሎች ስድስት የኢህአፓ አባላት ጋር መከሰሳቸውንና ጉዳዩ እዛው ጫካ ውስጥ በነበረው የኢህአፓ ወታደራዊ ችሎት መታየቱን፤ እሳቸው እድሜያቸው ገና ልጅ በመሆኑ በይቅርታ መታለፋቸውን እና የቀሩት ስድስቱ ላይ ግን የሞት መፈረዱን ብቻ ሳይሆን የሞቱን ፍርድ የፈረዱትም ሆነ ግድያዩ የፈጸሙት በቅርብ አብረዋቸው የኖሩት የገዛ ጓደኞቻቸው መሆናቸውን፤ ከሁሉም በላይ ግን የገዳይ ስኳዶቹ ልጆቹን ዘወር አድርገው ጫካ ውስጥ ከገደሏቸው ቦሃላ ያለ ምንም የሰቀቀን ስሜት ከሟቾቹ አስከሬን ላይ ልብሳቸውን አውልቀውና የተሻለውን መርጠው ለብሰውት እንደተመለሱ ማየታቸውን፤ የለጋነት እድሜያቸውን የሰውለት፣ዱር ቤቴ ብለው በረሃ ድረስ የተከተሉት፣ እህታቸው አዲስ አበባ ላይ የኢህአፓን አባላት ስም ዝርዝር አሳልፋ ላለመስጠት ሳይናይድ ታብሌት ውጣ በእራሷ ላይ እርምጃ የወሰደችለት፤ ያ “ክብሩ ወ ቅዱስ” ያሉት ኢህአፓ እውነተኛ ማንነቱን በጫካ ውስጥ ሲያዩት ከእርሱ ጋር ያላቸው ግንኙነት ያን ቀን እንደተበጠሰና በሱዳን በኩል አድርገው አሜሪካን መግባታቸውን ብሎም እንደዛ ያሰከራቸውን ነገር ምን እንደነበር ማርክሲዝምን በማንበብ መልስ ፍለጋ ሲቆፍሩ እንደ ነበር በአንድ ወቅት ይፋ ባደረጉት ግለ ታሪክ አንብበናል።

ከደደቢት ተነስተው ሚኒሊክ ቤተመንግስት የደረሱት የትግራይ ገዢ ጉጅሌዎች እስከ ሲኦል ዳርቻ ድረስ ጠልቀው በመውረድ እራበን ብለው የገዛ ጓደኞቻቸውን በሳንጃ ዘልዝለው ጥሬያቸውን መብላታቸውን እንዲህ ወቅቱ ደርሶ ለህዝብ ጆሮ ሲደርስ ዶር ብርሃኑ አልሰሙም ማለት አይቻልም። እነ አንበጣና በለሶቹ በላየሰቦች ሆነው ነገር ግን በሰው ልብስ ተሸፍነው ጭምር ሆነው አዲስ አበባ መድረሳቸው ብቻ ሳይሆን ዛሬ ደግሞ ከሰው አይንና ጆሮ ተከልለው ማእከላዊ በሚባል ምድራዊ ገሃነም ውስጥ እየፈጸሙት ያለውን ሰቆቃ ለመናገር ቀርቶ ለመስማት የተፈቀደ እንዳልሆነ ሓብታሙ አያሌው ለምስክርነት በቅቶ አድርሶናል።

በላዬ ሰቦቹ ኑሮ ያደረጉትን ጸያፍ ግብር በሃይማኖት ታንጾ ያደገው ጨዋ በቃላት አውጥቶ ለመናገር አቅም ሲያጥረው ብናይ አይገርምም። ሃብታሙ አያሌው ትናንት በጨዋ ትርጉም ተነስቶ አረመኔዎቹን በሰውኛ መስፈርት ለክቶ; የተጻፈ “ህገ መንግስት” አለ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ሊታገል ተደራጀ። በአደባባይ ከሚለፈፈው እንቶ ፈንቶ ጀርባ ያለውን መራር እውነት ግን ለማየት ማእከላዊን ጨምሮ በብርሸልቆ፣ በባዶ ስድስትና በመሳሰሉት ምድራዊ ገሃኖሞች ውስጥ ያለውን እውነት ማየት እንደሚያስፈልግ ዛሬ ከሃብታሙ የተሻለ ሚዛን ደፊ ምስክር የሚኖር ያለ አይመስለንም።

ማንም በአገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል ታግዬ ከዚህ አውሬ መብቴን እነጥቃለሁ የሚል ቢኖር በዚህ ስሌት ማየት ያለበት ይመስለኛል። ዶር ብርሃኑ ነጋ ትናንት በአሲምባ ያዩንትን ብሎም ቀጣዩን የፖለቲካ ህይወታቸውን እስከ መጨረሻው የቀየረውን የያን ግዜ የልጅነት ገጠመኛቸውን ከእነዚህ በላዬ ሰቦች መራር ተፈጥሮ ጋር አነጻጽረው አንድ ቀን የበኩላቸውን እንደሚሉን ተስፋ አደርጋለሁ….

ከዛሬ ጀምሮ በላዬ ሰቦቹ ስል የትግራይ ገዥ ጉጄዎቹን መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንዲታወቅ ይሁን!

የኢትዮጵያ ጀግና ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ትምህርት ይሁኑን! ሕወሃት የጣላቸው አርበኞቻችን ይከበሩ! ከሕግ ውጭ የሚረገጡት ዜጎቻችን ፍዳ ያብቃ!

በከፍያለው ገብረመድኅን Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በሕይወት ዘመናቸው ከሃገር ጠላቶች ጋር 3,500 ዘማቾች አስከትለው በመፋለም – በአምስቱ ዓመታት የጣልያን ወረራ ወቅት አንዴም ሳይማረኩ – ከሞት ጋር ተፋጠው የኖሩ ሰው በመሆናቸው፣ ከዚያም በኋላ 17 ጊዜ በተለያዩ ጊዜያት ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ስለሆኑ፣ እንደገናም በተላኩባቸው የሃገር ሰላምና ደኅንነት ማስከበር ሥራ ከጠላት ጋር መፋለምን አልፈው፣ ከሰባት ዓመት በፊት በነበሩበት ሁኔታ ምን እንደተሰማቸው በሸገር ጋዜጠኛዋ ኅሊና አዘዘ ለተደረገላቸው ጥያቄ በ2010 የ89 ዓመቱ ‘የበጋው መብረቅ’ ሌ/ጂነራል ጃገማ ኬሎ የሠጡት መልስ የሚከተለው ነበር:-

“እንግዲህ እግዚአብሄር የሠጠኝን ጸጋ በትዕትሥት ሕመሜን እየቻልኩ እየታገስኩ እሄዳለሁ፤ ምንም ችግር የለም፤ አሁን ደግሞ ሥቃይ የለም ዋናው ነገር – ከዚህ [እግሬ] ማንከስ በስተቀር -… እበላለሁ፤ እጠጣለሁ፤ ሌሊት እተኛለሁ! ፈጣሪዬን አመስግናለሁ!”

ሚያዝያ 9/2017 የሕወሃቱ ፋና ስለኢትዮጵያዊው ጀግና ሌ/ጄኔራል ጃገማ ኬሎ በ96 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉን ምክንያት በማድረግ የተዘገበው ዜና በዜናነቱ መቅረቡ ብቻ አስደስቶኛል።

ምክንያቱም ለሕወሃቶች ትግራዊ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ይህን ያህልም መዘገቡ በእነዚህ 26 ዓመታት ያልተለመደ ነው። በአንድ በኩል ሃገራችን ባለውለታ ዜጎቿን የማከበርና የመንከባከብ ባህሉ የሌላት መሆኗ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ መሆኑኑ እየታወቀ፣ ይህ ዜና የተጠናቀረው ይባስ ብሎ በዘረኛው ዘመነ ሕወሃት የዘረኝነቱ ችግር ከምንጊዜውም በላይ በተጠናከረበት ወቅት ነው።

ከዚህ በታች የሠፈረው የጆሲ ቪዲዮ ጥር 15/2017 ዓ.ም. የተቀረጸ ሲሆን፡ መነሻውም የገናን በዓል ጄኔራሉ በተኙበት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ውስጥ ስጦታዎችን በማበርከት ለማክበር የታቀደ የሚያስደስት የሚያሳዝንም ዝግጅት ነው።

ከአሳዛኙ ነገሮች መካከል፡ በሕይወታቸው ዘመን በተለይም በጡረታ ተገልለው በነበሩባቸው 36 ዓመታት – እርሳቸው ለሃገራቸው ካደረጉት አስተዋጾዖ አንጻር ለጤናቸው እንኳ እምብዛም እንዳልተደረገላቸው፣ ለአምስት ዓመታት አስታማሚያቸው የነበረችው የመጨረሻ ልጃቸው ምህረት ጃገማ ኬሎ የሚሰማትን ቅሬታ ከዚህ በታች ባለው ቪዲዮ ውስጥ በጨዋነት ታሰማለች!

በ1,398 ብር ጡረታ የአርበኞች ማኅበር ደግሞ ብር 600 እየከፈላቸው ከእጅ ወደ አፍ የኑሮ ትግል ሕይወት እንደመሩ የመጨረሻ ልጃቸው ቅሬታዋን በኩራት በመዋጥና ኃዘኗን የኅብረተሰባችንን ውድቀት በሚያሳይ መልክ – ማንንም ሳትወነጅል – አሰምታለች!

ድህነት ነውር አይደለም! ትልቁ የሃገራችን ነውር ግን ሃገራችን የልጆቿን ውለታ በልታ ልጆቿ ችግር ውስጥ እንኳ ሲወድቁ ጀርባዋን የምትሰጥ መሆኗ ነው።

ምነው ለጂነራል ጃገማ መንገድ ወይም ትምህርት ቤት ወዘተ በስማቸው አልተሰየምም ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ እንደማይኖር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል! ለዚህ ነው የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ያለበት – በጎ ፈቃዱ ካለ – ፖሊሲውን በአስቸኳይ መቅረጽና አስፈላጊውን የመንግሥት ተቋም መመሥረት ያስፈልጋል!

ድርጊቱ ቀርቶ በምኞት ደረጃ እንኳ ሃገራችን ትልቅ ብትሆን፣ ዛሬም በዚህ በዘገየ ወቅት ጀግናው ጄኔራል ጃገማ ላይ ከደረሰው ትምህርት በመውሰድና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ባለታሪክ አስተዋጽዖ በቅንነትና በሕጋዊ መመሪያነት ሃገሪቱ ወሮታ ለመክፈል እንድትችል ወደ ፖሊሲ መሸጋገሩ ግድ ይላል!

እስከ መቼ በግለሰብ ዜጎች ዕርዳታ፣ ጥቂቶች በጎ ፈቃድ የጎደላቸው በሕዝብና ሃገር ንብረት ፈላጭ፡ ቆራጭ ሆነው በዘረፋቸው በሚንደላቀቁባት ሃገር?

በሌላ በኩል፣ ሃገር አገልግለው በጡረታ የተገለሉ ግለሰቦች ልዩ አሰተዋጾዖች ታሳቢ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን፡ ዜጎች በኢትዮጵያ መብቶቻቸውን የተገፈፉ መሆናቸውን እናውቃለን፤ በምሬት ስንመሰክርም ኖረነናል! ይህ ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ እጅግ በማስቆጣቱ ላለፉት 16 ወራት የተነሳውን ገሃድ ግብግብና አሁን ደግሞ – ‘የጥልቅ ተሃድሶ’ ፖለቲካ ትያትሩ ቀርቶ – ውስጥ ለውስጥ የሚግመው ቁጣ ልብ ሊባል ይገባል!

ለምሣሌም ያህል፣ የሕግ እሥረኛ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ሆኖ ሲረገጥና ሲደበደብ እንዲሁም ሕክምና ሲከለከል፣ በሕይወት ያሉት የሕወሃት ባለሥልጣኖቻቸው፡ ዘመዶቻቸውና ጓደኞቻቸው በመንግሥት ወጭ ውጭ ሄደው እንዲታከሙ ሲደረግ፡ ለውጭ ፖለቲከኞች (ደቡብ ሱዳንና ሶማልያ) በመንግሥት ወጭ ቤቶች ተሠጥተዋቸው ተደላድለው እንዲኖሩ ሲደረግ የዜግነት ትርጉሙ ምን ይሆን?

በቅርቡም ሌሎች ዐይኖቻችንን ያስረጠቡ ሁኔታዎችን እናስታውሳለን። ለምሳሌም ያህል፦

    (ሀ) ለሃገራቸው በደማቸውና በውድ ሕይወቶቻቸው ዳር ድንበሮቻችን የዋጁ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ዛሬ በመንገድ ላይ ለማኝ እንዲሆኑ የተደረጉት ለቁጥሮቻቸው ማነጻጸሪያ የሚሆነው፥ እዚያ የደፋቀቸው የሕወሃት ክፋትና ተንኮል ጥልቀት ብቻ ነው። የሚገርመው ነገር ሃገር ላይ ባዕዳን ኃይሎችም ሆኑ የውስጥ ተጻራሪ ኃይሎች በሕውሃት ላይ ክንዳቸውን ሲያነሱ፡ ሕወሃት አሁንም ጭምር ለልመና ለዳረጋቸው የቀድሞ መከላከያ አባላት የእናት ሃገር ጥሪ ያቀርባል።

(ለ) ብዙ የሃገር ጀግኖች ውጭ ሃገር ተሰደው ከርመው፡ ሬሣቸው ሃገራቸው መጥተው እንዲቀበሩ የሕወሃትን ፈቃድ ጠየቀው ለአፈራቸው የበቁት ቁጣራቸው ጥቂት አይደለም! ለአሜሪካ F-5E የጦር አውሮፕላን ታላቁ ማስታወቂያ የተሠራው – ኒውስዊክ እንደዘገበው – በ1970ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን፣ ይህም የሆነው ብርቅዬ የሆኑት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተዋጊዎች ባከናወኑት የአየር በአየር ውጊያ ጀግንነት ነበር። ስማቸው ከሚጠቁሱት መካከልም ብሔራዊ ጅግናው እነጄኔራል ለገሠ ተፈራ (የአየሩ ነብር) ጭምር ይጠቀሳሉ! በጋራም ሆነ ከጄነራል ተፈራ መማረክ በኋላ፥ የሶማልያን የመጨረሻዋን የጦር አውሮፕላን ደምስሰው ሶማልያ ሁለተኛ ኢትዮጵያን በአየር ኃይል እንዳትተናኮል ያደረጉት አብራሪ ጄኔራል ባጫ ሁንዴ ካሃገራቸው ርቀው ሬሳቸው እንኳ በ2015 የሃገራቸው መሬት ላይ ሳያርፍ ቀርቶ አሜሪካን ሃገር በካሊፎርኒያ ኦክላንድ ውስጥ ተቀብረዋል።

(ሐ) እኔ በሥራም ሆነ በስም የማላውቃቸው አያሌ የቀድሞ ጦር አባሎችና ሲቪል ሃገር ወዳዶች ለሃገር ከፍተኛ መሥዋዕትነት ቢከፍሉም፡ አብዛኞቹም ምናልባት፡ ሃገራቸው በውስጧ ብታነባላቸውም እንደወጡ ቀርተዋል። ይህ መቆም አለበት! ሃገር የሁሉም ዜጎች ናት!

ምነው ሃገራችን የወላድ መካን ለመሆን ተገደደች? ይህ ዛሬ በኛም ሆነ በሃገራችን ሕዝብ ፊት ወንጀል ነው፤ በተለይም፡ የሕወሃት ሹማምንት ሥልጣን ስለተቀራመቱ – ብዙ ጥፋቶችንና ወንጀሎችንም ፈጽመው – በ$25 ሚልዮን የግል የሚሆኑ የጡረታ ዘመናዊ ቤቶች ሲሠራላቸውና ሃገሪቱም አይታ በማታውቀው መጠን የአንደኛው ዓለም ያህል ጡረታ እንዲከፈላቸው፡ የጤና ኢንሹራንስ ፖሊሲ ሲሠላላቸውና መኪናዎች ከነሾፈሮች እንዲመደቡላቸው የጡረታ መብቶቻቸው ሲደነገጉ – የጄኔራል ጃገማና ሌሎች መሰሎችን መጣል የታዘበ ዜጋ ‘ሃገሬ የቀበረሽ በላ …’ የሚለውን ቢያስታውስ ምን ያስደንቃል!

እውነቱን ለመናገር – ከላይ ከአጀማመሬ እንዳልኩት – ዛሬ በሕወሃቶች አንደበት ጂኔራል ጃገማ ኬሎን በዚህ የሕየውታቸው ዕልፈት ወቅት “በኢትዮጵያ ታሪክ ታላቅ ሥፍራ ያላቸው” – ፋና እንዳስቀመጠው – ተብሎ መዘገቡ በእውነትም ያንን አንጸባራቂ የጀግንነትና መሥዋዕትነት ትግል ታሪክ በመቀበል ይሆን፡ የፖለቲካ ጨዋታ መለየት አስቸጋሪ አድርጎታል።

ሕወሃት ሰብዓዊነት የሌልው ድርጅት ስለሆነ፡ ምናልባትም የሞተ ሰው አይመለስም በሚለው አባባል በመጽናናትም ሊሆን እንደሚችል አልጠፋኝም። ሆኖም በደፈናው ከመራገም፣ እኔም እስቲ ይሁን ብዬ ደስ ብሎኝ ዜናውን እሁድ ጠዋት ሚያዝያ 9/2017 አነበብኩት!

መሻሻላችሁን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በዚያ አስቀያሚ ‘ጥልቅ ተሃድሶ’ ቅጥፈት ሳይሆን፡ እስቲ ለአንዴ እንደ ‘መንግሥት’ ለመናገር፣ ለማስተዳደርና ሃገርንና የሕዝብን ሕይወት ለማሻሻል ፍላጎት እንዳደረባችሁ በተግባር አሳዩ!

ሁለት ጉዳዮችን ነው ያነሳሁት፦

(ሀ) ሁሉንም ዜጎቻችንን በኢትዮጵያውያነታችው ብቻ አክብሯቸው

(ለ) ለአርበኞቻችንና ለባለአስተዋጾ ከዋንያን ዜጎች ድራጎቶቻቸው ሕዝብ በከበሬታ መንግሥት መብት ላይ በተመሠረተ የወሮታ ክፍያ በሕግ ይክፈላቸው

(ሐ) ሕወሃቶች በዜጎቻችን ላይ የምትፈጽሟቸውን አረመኔያዊ ተግባሮች አቁሙ፤ በእሥር ቤት በሕግ እሥረኞች ላይ የሚፈጸሙትን ማሠቃየቶችን ጭምር። ጠላቶቻችሁን አላቆማቸውም፡ እናንተንም ከመጠላት ውጭ ያተረፈላችሁ ነገር የለም። አሁን ባለው ሁኔታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሕወሃቶች ላይ የቁጣውን እሳት ለመለኮስ ቀን ጠባቂ ሆኗል ከደረሰበት ጥቃትና ዘረፋ በመነሳት – ምንም እንኳ ይህ ከታሪካችን ጋር የማይሄድ ባህሪ ቢሆንም!

ምናልባትም ሁኔታዎች ተለዋውጠው ሕወሃቶች እንደዜጋ ማሰብ ከቻሉ፡ በዚህ ረገድ የሚወጣውን ፖሊሲና ሕጎች ከጄኔራል ጃገማ ኬሎ ስም ጋር አያይዙት! ለሁሉም ነገር መንስዔ አለው!መሻሻልም በዚህ ምክንያት የምንፈልገው ለውጥ ሊመጣ ይችላል።

ጎሲ እግዚአብሔር ውለታህን በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ይከፈልህ፡ ከበሬታህ ይብዛ ይዳብር!

“ነገረ ኢትዮጵያ አልበም ! ” — (ይድነቃቸው ከበደ)

“ነገረ ኢትዮጵያ አልበም ! ”

FB_IMG_1491396708003የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ፣ “ኢትዮጽያ” የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ ሥራ ያልተነገሩ፣ ግን መታወቅ ያለባቸው እውነታወች።

የቴዲ አፍሮ 5ኛ አልበም እነሆ ለህዝብ ሊደርስ የቀናት ጊዜያት ቀርተውታል።ቴዲ ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ደጋግሞ ያነሳል፣ ሕዝቦቿ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በአንድነት ለዳር ድንበሯና ለሉዐላዊነቷ የከፈሉትን ከፍተኛ መስዋዕትነትና የአርበኝነት ውሏቸውን ፣ የቋንቋና የባህል ውበቷን፣ የሃይማኖቶችና የትውፊቶች ባለፀጋነቷን ፣ .. ጥንታዊነቷንና የሰው ልጅ መገኛ ቀደምትቷን በልዩ ዜማ ይመሰክርላታል ይቀኝላታል ይዘፍንተላታል ኢትዮጵያን።

በኢትዮጵያ አልበም ውስጥ የተካቱት ዘፈኖች ሁሉ። በአማርኛ ቋንቋ የተዜሙ ናቸው። የሙዚቃ ቅንብሩን ሙሉ በሙሉ የሃገራችን ታዋቂ የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት ነው። በተለይም የሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጳውሎስ አብላጫውን ስራ ሰርቷል። አቤል የተወዳጆቹን የጎሳዬ ተስፋዬን፣ የፀዴንያ ገ/ማርቆስንና የበርካታ ታዋቂ ድምፃውያንን ስራዎች ያቀናበረ ነው። ዝነኛው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅም በቴዲ ኢትዮጵያ። አልበም ላይ አሻራውን ያሳረፈ ሲሆን እንዲሁም ተወዳጁ አቀናባሪ አማን ሌላው ተሳታፊ ባለሙያ ነው።

አልበሙ ለህዝብ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው በትንሳኤ።ሳምንት በሚውለው በዳግሚያ ትንሳኤ (ሚያዚያ 14 /15 ቀን 2009 ዓ/ም) ነው። የቴዲ ማኔጅመንት አባላትና አልበሙን ለማከፋፈል ውል የፈፀሙት አካላት “ኢትዮጵያ” የሚለውን ዘፈን (Track) ብቻ ለትንሳኤ ለሕዝብ ለማድረስ ፍላጎት አላቸው። በዚህም መሰረት ለትንሳኤ ዋዜማ ቅዳሜ ሚያዚያ 7 ቀን 2009 ዓ/ም ለህዝብ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

የሃገር ውስጥ የአልበም ሽያጩን በተመለከተ ከቴዲ ማኔጅመት ጋር ውል የፈፀሙት አካላት በውላቸው መሰረት በሃገር ውስጥ 3 የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ለመስራት የተስማሙትን ታሳቢ በማድረግ ለጊዜው 4 ከተሞች በዕቅድ ደረጃ ተይዘዋል። እነሱም በመዲናችን አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ደሴና ሃዋሳ ሲሆኑ ጊዜው ሲደርስ ከደሴና ከሃዋሳ አንዱ ከተማ ላይ የሙዚቃ ኮንሰርቱ ይካሄዳል።

የመጀመሪያው ኮንሰርት አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያ አዲስ አመት ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን ቀጣዩ በሳምንቱ ባህርዳር እንደሚደረግም ይጠበቃል። ቴዲ አፍሮ በዘንድሮው የማኀበረ ግሩያን ዘረ ኢትዮጵያ 25ኛ አመት ልዩ የክብር ሽልማት ተሸላሚ በመሆኑ ሽልማቱን ለመረከብ ከቤተሰቡና ከወዳጅ ጓደኞቹ ጋር በሜይ ወር መጨረሻ ወደ አሜሪካ ይሄዳል።በአሜሪካ
ቆይታውም ሲያትል ዋሺንግተን በሚካሄደው የዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው ፌስቲቫል ላይና በአንዳንድ የአሜሪካ ከተሞች በጉጉት ለሚጠብቁት አድናቂዎቹ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ አዲስ አመት ከመድረሱ አስቀድሞ ባሉትም ቅዳሜዎች በጥቂት የአውሮፓ ከተሞች አዲሱንና የማይሰለቹትን ቀደምት ስራዎቹን ለማቅረብም ዕቅድም አለ።

በመላው አለም የሚገኙ የቴዲ አድናቂዎች በጉጉት የሚጠብቁትን ይህን ታሪካዊ አልበም በተመሳሳይ ቀንና ሰዐት ለገበያ ለማቅረብ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፤ በተለይም ከአገር ውጭ ለሚኖረው የሙዚቃ አፍቃሪ አልበሙ በአገር ውስጥ ለገበያ በሚቀርብበት በዚያው ዕለት የአልበሙ ተቋዳሽ ይሆናል ማለት ነው። እስካሁን ድረስ አልበሙን በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአውስትራሊያ ለማከፋፈል ፍላጎት ካለቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እየተደረገና ከተወሰኑትም ጋርም ውል የተፈፀመ ነው።

በሃገር ውስጥ የማከፋፈሉንና የማሳተሙን ድርሻ የወሰዱት አካላት የአልበሙን ማስተር ከአርቲስቱ ተቀብለው ወደ ህትመትና ማባዛት ሂደት የገቡ ሲሆኑ ፣ የህትመቱን ሃላፊነት በመውሰድ በኩልም በሃገር ውስጥ በቅርብ ጊዜ በዱከም ኢንዱስትሪ ዞን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የድምፅና የምስል ኮምፓክት ዲስኮችንና ዲቪዲዎችን ለማተም የተቋቋመው ቆልያ ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች ድርሻ ይሆናል።

ቀደም ብሎ በተለቀቀው የአልበሙ ፖስተር ዙሪያ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡበት የከረሙ ሲሆን በተለይም በስዕላዊ ማስታወቂያው ላይ ጦርና ጋሻ ይዘው የሚታዩትን አርበኛ፤ የራስ ነሲቡ ዘአማኑኤል መደበኛ ያልሆነው ጦር አባል የነበሩ ተዋጊ አርበኛ ናቸው።አርበኛ ራስ ነሲቡ እ.ኤ.አ በሜይ 1936 ዓ/ም የኢትዮጵያን ልዑካንን በመምራት ወደ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ በመምጣት በሊግ ኦፍ ኔሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ ሲሆን፣ ህይወታቸው ያለፈውም በዚያው አመት በጥቅምት ወር በረዷማዋ የስዊዘርላንድ ከተማ ነው።

የዚህ መረጃ ምንጭ © አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ ነው። እኔም (ይድነቃቸው ከበደ) ይህ ጠቃሚ መረጃ ለተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አድናቂዎችና አክባሪዎች እንዲዳረስ። ይህን አድርጊያለሁ። ለድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ካለኝ አክብሮት ብቻ ።

አዎ ! ፍቅር ያሸንፋል !!!

‹የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም ምክንያት ሆኗል›› IRIN

ሙሉቀን ተስፋው

ብራና ሬዲዮ – Branna Radio፤ መቀመጫውን በስዊዘርላንድ ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት የተቀናጀ የዜና አውታር (IRIN) በዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዞ ወጥቷል፡፡ የዜና አውታሩ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አራት ወራት መራዘም ብቸኛ ምክንያት መሆኑን በዝርዝር ያስረዳል፡፡ መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓ.ም የታተመው የኢሪን ዘገባ በጎንደርና በባሕር ዳር አስጎብኝ ግለሰቦችን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የመንግሥት ኃላፊዎችንና የተለያዩ ዜጎችን እንዲሁም በአሜሪካ የተለያዩ ዪንቨርሲቲዎች ተመራማሪዎችንና የኢትዮጵያን ተወላጆች በማነጋገር የሰበሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው ገዥው ቡድን በከተማ ያለውን አመጽ የተቆጣጠረው ቢሆንም በገጠር ያለው የዐማራ ታጣቂዎች የእግር እሳት ሆነውበታል ብሏል፡፡ 

የወልቃይት የዐማራ የማንነት ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ የዐማራ ተጋድሎ ተዋናኝ ገበሬዎች መቼም ቢሆን ትግላቸውን እንደማያቆሙ በየቦታው ያነጋገራቸው ዜጎች በአጽንኦት አስረድተዋል፡፡ ከ20 ሺህ በላይ ወጣቶች ታስረው የስቃይ ሰለባ ቢሆኑም እንዲሁም በብዙ ቦታዎች ያለው አመጽ የቆመ ቢመስልም በሰሜን የዐማራ ገበሬዎች መራር የትጥቅ ትግል ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እየሄደ ነው ይላል የኢሪን ዘገባ፡፡

በነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ባሕር ዳር በግፍ ወደ ትግራይ የተወሰደውን የወልቃይትን ሕዝብና መሬት ለማስመለስ ጩኸቱን ያሰማውን የዐማራ ሕዝብ የአገዛዙ ወታደሮች በጥይት ደብድበው ከ52 በላይ ሰዎችን ገደሉ፤ የዐማራ ተጋድሎ በተቀጣጠለባቸው ሳምንታት ብቻ ከ227 በላይ ዜጎች በጥይት ተገደሉ፤ ይህን ተከትሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ ይላል የዜና አውታሩ ዝርዝር ምልከታ፡፡
ይኼው የዜና አውታር በጎንደር ያሉ የሃይማኖት አባቶችንና ግለሰቦችን አናግሮ ‹‹በጎንደር ስለ አርበኛው ጎቤ መልኬና የወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በፍቅርና በኩራት የማያወራ የለም፤ ገበሬዎች ለማንነታቸው ሕይወታቸውን ከመስጠት ወደ ኋላ አይሉም፤ ዐማራነት ካልተከበረ ወደ ኋላ የሚል የለም›› እንዳሉት በዳሰሳው አስፍሯል፡፡
(ሙሉ የዜና አውታሩን ዘገባ ለመመልከት ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑትhttp://www.irinnews.org/…/ethiopia-extends-emergency-old-an…)

የኢትዮጵያ ጉዳይ እጅግ አደገኛ የሚባል ደረጃ ደርሷል። ምን ይደረግ? (የጉዳያችን ወቅታዊ ሃሳብ)

የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማችሁ የስርዓቱ አካላት፣የተቃዋሚ ኃይሎች እና መላ ህዝብ ኢትዮጵያ መንግስት እንዲኖራት በቶሎ መነሳት ይጠበቅባቸዋል

ባለ ሰባት ነጥብ ሃሳቦች ቀርበዋል።

  • ጉዳያችን /Gudayachn 
  • መጋቢት 27፣2009 ዓም (April 5,2017)
  • NEW PROPOSAL IN AMHARIC TO ESTABLISH TRANSITIONAL GOVERNMENT IN ETHIOPIA 
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ጎማ ከእዚህ በላይ ኢትዮጵያን ሊያሽከረክር አይችልም።ኢትዮጵያ ካለ አንዳች ለውጥ አንዲት ቀን መቆየት የማትችልበት ደረጃ ላይ ነች።በሀገር ውስጥ እና ዙርያዋን እየሆነ ያለው ሁሉ መንግስት የሌላት ሀገር የሚል ስም የሚያሰጥ፣ስርዓት አልበኝነት ከምንገምተው በላይ የሚሄድበት ትልቅ ዕድል አለ።ሕወሓት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያን የመምራት አቅም አይደለም እራሱን ብቻ ተሸክሞ መራመድ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።እራሱን መሸከም አለመቻል ብቻ ሳይሆን እርስ በርሱ በገባው ቅራኔ መንገዱ ሁሉ ታጥሮበታል።የውስጥ ቅራኔው መስፋት ቀድሞ ከነበረው ደካማ አቅም በባሰ እጅግ ደካማ በሆነ የሰው ኃይል ከወዲያ ወዲህ ያለ አንዳች ሥራ እየተንገላወደ ነው።
ይህ ከአቅም በታች የሆነ የሰው ኃይል ከዋናው የህወሓት አስኳል ጋር በመሆን ኢትዮጵያን በአራቱም ማዕዘን ዘረፋውን አጧጡፈውታል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የልማት ባንክ በቢልዮን የሚቆጠር  ገንዘብ ዕዳ ውስጥ ገብቷል።ስርዓት አልበኞቹ ባለስልጣናት ከአቶ ሃይለማርያም ጀምሮ ኢትዮጵያን የግል ንብረታቸው አድርገው የመንግስት ስራን  ከሚገመተው በላይ አቡክተውታል።በአባይ ወልዱ የሚመራው የትግራይ ክልል (በእራሱ ለማዕከላዊ መንግስት ባለፉት አመታት ሲያደረገው እንደነበረው ሁሉ) የእራሱ የዘመነ መሳፍንት ዓለም ፈጥሮ በእያንዳንዱ የኢትዮጵያዊ መንግስታዊ እና የግል ድርጅቶች የውስጥ ጉዳይ ሁሉ  እየገባ እያመሰ እና እየዘረፈ ነው። የስርዓቱ አስተዳደር መዋቅር ተበጣጥሶ ሁሉም የእራሱን ሕግ በሚገዛው ቀበሌ ውስጥ ገዢ ሆኗል።የአዲስ አበባ አስተዳደርን ብቻ ብንወስድ እታች ቀበሌ ያለውን ሥራ የመምራትም ሆነ የመቆጣጠር አቅሙ ወርዶ ሰዎች ከሰሜን በመጣ እና ባልመጣ አነጋገር እየተለየ  ያልነበረሕግ የሚሰራበት ደረጃ  ላይ ተደርሷል።
የሱማሌ ክልል ከአዲስ አበባ ጋር ከሚያደርገው ግንኙነት ይልቅ ከሞቃዲሾ የሚመጡ ኮብራ መኪናዎች ይቀርቡታል።ክልሉ የኢትዮጵያን የቁም ከብት እና ጫት እንዲሁም ፍራፍሬ እየሸጠ በምትኩ የጦር መሳርያ እየሸመተ ነው።ይህ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያን ድንበር ከፓኪስታን እና ከአፍጋኒስታን የመጡ አሸባሪዎች ሳይቀሩ እንደፈለጉ የሚገቡበት እና የሚወጡበት የውሃ መንገድ አስደርጎታል።አቶ ሃይለማርያም ኢትዮጵያን የመምራት አይደለም ፒያሳ ስላለው ጉዳይ አያውቁም።ከጀርባ እየመራ ነው የሚባለው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ እርስ በርሱ ለመመታታት ሰዓታትን እየጠበቀ ነው።አቦይ ስብሐት እራሳቸው ግራ ተጋብተው ደጋግመው የሚወዱትን ሬድ ሌበል ውስኪ ከመጎንጨት በቀር የሚሰሩት ግራ ገብቷቸዋል።
ከጎንደር እና ጎጃም በእየሰዓቱ  የሚመጣው ዜና የኢህአዴግ/ህወሓት ወታደር የሆነ ሁሉ ጥቃት እየተፈፀመበት እንደሆነ ነው።ሰራዊቱ እራሱ ጎንደር ላይ ለመዝመት አንዳች ፍላጎት የለውም።ምክንያቱም ዘመቻው እራሱ ምክንያታዊ ሳይሆን በሕወሓት እብሪት የተፈጠረ እሳት መሆኑን ሰራዊቱ ይስማማበታል።ይህ ሁሉ ጉዳይ ያስጨነቀው ሕወሓት የሱዳኑን ፕሬዝዳንት ዛሬ አዲስ አበባ ድረስ ጠርቶ ማናገር ይዟል።የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር እራሳቸው አዲስ አበባን ሲረግጡ ከእዚህ በፊት ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ሲመጡ የሚያውቁት ሀገር አልሆነባቸውም።አሁን ለውጥ ለውጥ የሚል ሽታ እና የስርዓቱ ባለስልጣናት አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ የተደናገጠ ፊት ብቻ ነው የተመለከቱት።ጉብኝታቸው ሁሉ የውሸት ስለሆነባቸው የሚያደርጉት ውል ሁሉ የማይረጋ መሆኑን ስሜታቸው እንደነግራቸው ከፊታቸው ይነበባል።
የኢትዮጵያ ዙርያ ያሉ መሬቶች በአረብ ሀገር ወታደሮች እየተከበቡ ነው።ከሱማሌ እስከ አሰብ ድረስ ጂቡቲን ጨምሮ ከእዚህ በፊት ሰራዊታቸውን ከሀገራቸው ውጭ አስፍረው የማያውቁ የአረብ ሀገሮች በሙሉ የኢትዮጵያን በሕወሓት ደካማ እና በዘር ላይ የተመለከተ መንግስት እጅ መውደቅ ተመልክተው  ዙርያችን ሰፍረዋል።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ጉዳይ ተሞክሮ እዚህ ግባ የማይባል ልምድ በሌላቸው ግለሰብ እጅ በመውደቁ ሚንስትሩ  ዛሬ ለምክር ቤት ያለፈ የስድስት ወር ሪፖርት ሲያቀርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደረጃ መነገር የማይገባቸው ቃላት ሲጠቀሙ መመልከት የብስለት ብቻ ሳይሆን  የዓለም አቀፍ እውቀት እና ልምድ ማነስ ምን ያህል ኢትዮጵያን አፈር ድሜ እንዳስገባ ለመረዳት ቀላል ነው።
የምጣኔ ሃብቱ ድቀት የድሀውን እና የደሞዝተኛውን የመግዛት አቅም ከተጠበቀው በታች አውርዶታል።በመምህራን ደረጃ የመኖር እና አለመኖር ግብግብ ውስጥ ስለገቡ ሰልቫጅ ልብስ መንገድ ላይ በመሸጥ ከማስተማር ሙያቸው በተጨማሪ  የሚሰሩ መምህራን አዲስ አበባ ላይ መኖራቸው የእዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ሰምቷል። በእዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ መጨመሩን ሮይተርስ በለቀው ዘገባ አረጋግጧል።የዓለም ባንክ ከውሃ እና ፍሳሽ ጋር በተያያዘ በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ብድር መፍቀዱ ትናንት ቢሰማም ብድሩን ለማግኘት በእራሱ ብዙ ደረጃዎች አሉት።ስለሆነም ለአሁኑ የህወሓት የውጭ ምንዛሪ ጥማት ሊደርስለት አይችልም።የዓለም ባንክ ይህንን የሚያደርገው የቻይና እጅ በበለጠ እንዳይረዝም ከማሰብ ውጭ የብድር መመለስ አስተማማኝ ዋስትና ኖሮት አይደለም።
እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ኢትዮጵያን በደርግ ዘመን ከነበረችበት ደረጃ እና አሁን በሕወሓት ዘመንም  ካለንበት አስከፊ ደረጃ በባሰ ሁኔታ ሀገሪቱን ይዞ የሚወርድ አደገኛ ደረጃ ነው።ስለሆነም ምን መደረግ አለበት? ሙስናው የኢትዮጵያን ሀብት እየዘረፈ፣ባእዳን ጥርሳቸውን እያሳዩን ሀገራችንን ሲያጠፉ እንመልከት? ወይንስ ኢትዮጵያን ለማዳን የሚጠበቅብንን  ለመስራት በቁርጠኝነት እንነሳ? ደግሞስ ማን ምን ይስራ?
ኢትዮጵያን ለማዳን አሁን  ምን ያድርግ?
የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ምጣኔያዊ ሀብት እና ማኅበራዊ ሁኔታ ላለፉት 26 አመታት በኢህአዴግ/ሕወሓት እጅጉን ቆስሏል።ይህ ቁስል ለመጠገግ ቢያንስ ሁለት ዓመታት ይፈልጋል።ይህንን ታሳቢ በማድረግ ከሕወሓት መውደቅ በኃላ ወድያው ጤናማ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ በእራሱ ሞኝነት ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያን ለማዳን ደረጃ በደረጃ ምን ይደረግ?
1ኛ/ ከኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት፣ከኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ከስርዓቱ ጋር ያልተነካኩ እና የቆሸሸ ስም የሌለባቸው የሃይማኖት ተወካዮች፣ምሁራን፣ከበሬታ ከህዝብ ያገኙ ዜጎች ያቀፈ ጊዚያዊ የኢትዮጵያ መንግስት በቶሎ አዲስ አበባ ላይ መመስረት አለበት።ይህ ጊዜያዊ መንግስት ለሁለት አመታት የሚቆይ (ዓመቱ ግምት ነው። ሊያንስ ይችላል) መሪ የዜጎች የጋራ መርህ ያወጣል።
 
ይህ እንዴት ይችላል? ሕወሓት ስልጣን ይለቃል ወይ? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን።ሆኖም ግን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ የተረዱ የሰራዊቱ አባላት እና የህዝብ ንቅናቄ ሁሉ ሕወሃትን ማስገደድ አለባቸው።ይህ እንደሚሆን እራሳቸው ህወሐቶችም በሚገባ ያውቁታል።በማንኛውም ደረጃ የሚነሳ የስልጣን ነጠቃ እንደሚኖር ያውቃሉ።አሁን የቀረው መረረኝ ብሎ የቆረጠ የሰራዊቱ አባል እና ሕዝብ እራሱን ባጭር ጊዜ አደራጅቶ የመነሳቱ ጉዳይ ብቻ ነው።
 
2ኛ/ ይህ ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መንግስት በቅድምያ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከሁሉም የሀገሪቱ ግጭቶች ገለልተኛ የሆነ የሁሉ ጠባቂ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ስራዎችን ይሰራል።ምክንያቱም ግዝያዊ መንግስት ሲመሰረት በአንዳንድ ክልሎች አንዳንድ ግጭቶች ዕለቱን አይቆሙም።ለምሳሌ በሰሜን ጎንደር እና ትግራይ፣በኦሮሞ እና ሱማሌ መካከል ያሉት ግጭቶች እና መስል ግጭቶች ሕወሓት ወለድ እና ቀደም ብሎ የነበረ ታሪካዊ ሂደት ስላላቸው ሰራዊቱ የሁሉንም ችግር የሚያዳምጥ እና የሚጠብቅ በቅድምያ ግን የኢትዮጵያን አንድነት እና ድንበር ጥበቃ አስተማማኝነት ላይ ያተኩራል።
 
3ኛ/ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ስር ሆነው ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ይመሰርታሉ።ለምሳሌ የሀኪሞች ባለሙያዎች፣የግብርና ሙያ ባለሙያዎች ወዘተ በእየሀገሩ ይደራጃሉ ወይንም የነበረ አደረጃጀታቸውን ያስመዘግባሉ። ሁሉም አደረጃጀቶች ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መንግስት በሚያወጣው የዜጎች የጋራ መርህ ይመራሉ።
 
4ኛ/ ጊዚያዊ የኢትዮጵያ መንግስት ዋናው መንግስት መጣም አልመጣም ነፃ ከመሆን የሚያግዳቸው የማይኖረው የፍትህ አካላት እና የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ለሁሉም የቆመ መሆኑ ላይ አበክሮ ይሰራል።ነፃ የምርጫ ቦርድ የመመስረት፣ የፕሬስ ሕጉ ለሁሉም የሚሰራ መሆኑ ላይ እና የህዝቡ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሕይወት በሽግግር ጊዜው ወቅት እንዳይታወክ አበክሮ ይሰራል።ይህ ማለት በከፍተኛ ደረጃ እርስ በርስ መቃቃር ያቆሰለውን ሕዝብ በበጎ የእርስ በርስ ግንኙነቶች እንዲዳብር በሁሉም መስክ ይሰራል።
 
5ኛ/ ዚያዊ የኢትዮጵያ መንግስ ነፃ ምርጫ (እንደ እዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ) እንዲደረግ የምርጫ ቦርዱ በነፃ እንዲያስደርግ  ሙሉ እገዛ ያደርጋል። የፕሬዝዳንት ምርጫ እንደ ኢትዮጵያ ትልልቅ ብሔሮች ላሉባት እና ሌሎች በርካታ ውሁዳንም ለሚኖሩባት ሀገር  ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት፣ልምድ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ  አቅም ያለው ፕሬዝዳንት ከየትኛውም ብሔር ቢመጣ እና በዙር ለሌላውም ሲደርሰው ላለፉት 26 አመታት የተዘራውን መርዝ ያረክሰዋል።
 
6ኛ/ የኢትዮጵያ ዋናው ምክር ቤት በነፃ ምርጫ ይመሰረታል፣የኢትዮጵያ መጪ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ፣ የውጭ ፖሊሲ እና የአጠቃላይ የልማት አቅጣጫ ይቀየሳል።በመካከለኛው ምስራቅ፣አፍሪካ እና ሌሎች አለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የሚገቡበት አግባብ ይቀየሳል፣በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ቅራኔዎች እንዳይኖሩ የይቅርታ እና የኢትዮጵያዊነት ቀን ይታወጃል። በሀገር ላይ ከፍተኛ በደል የፈፀሙ ግልፅ በሆነ መንገድ ለፍርድ እንዲቀርቡ ያደርጋል።
 
7ኛ/ የኢትዮጵያውያን የጋራ ተቋማት ግንባታ ላይ ያተኮሩ ስራዎች፣የስራ ዕድል ፈጠራዎች፣የስነ-ጥበብ እና ኪነ-ጥበብ እድገት ላይ ያተኮሩ ስራዎች እና ኢትዮጵያን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚችሉ ስራዎች ወደ ተግባር ይቀየራሉ።
 
ከላይ የተጠቀሱት ስራዎች የሕልም ወሬ ያህል የምንገምተው እንኖራለን።ሆኖም ግን አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ጠቃሚው እና እንደ ሀገር የመቀጠል እድላችንን የሚያጎላ ነው።የግድ ካልሆነ ከእንጦጦ ጀምሮ እስከ አራት ኪሎ ድረስ መንገዱ በመድፍ እየታረሰ መገባት ላይኖርበት ይችላል።በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሕዝብ፣ሰራዊቱ እና ተቃዋሚዎች ልብ ለልብ መገናኘት በቂ ነው።ከእዚህ ሲዘል ደግሞ የስርዓቱ አቀንቃኞች ይህ ለመቸውም ቢሆን ከስህተቱ የማይታረም ስርዓት ለማስወገድ እና ለልጆቻቸው የሚተርፍ የደስታ ዘመን ለማስተላለፍ ቁርጠኝነት የተላበሰ ውሳኔ ብቻ ነው የሚፈልገው።ውሳኔ ሕልምን እውን ያደርጋል።ኢትዮጵያን ለማዳን እንወስን ወስኑ !


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

 

ዘወሃቦ ወንዶ ወወለቶ ለደደቢት ርጉመ ለይኩን ( ማስታዎሻነቱ ለሓብታሙ አያሌው)  – መስቀሉ አየለ 

 
በጥቃትና በውርደት ውስጥ መኖር ምን ያህል ያማል።ወኔን አስታውኮ፤ ሃሞትንም ሸንቶ መኖር በቃኝ ለማለት ግፍን የሚያመርቱት ሰዎች እብሪት ከዚህ በላይ ምን ያህል እርቀት መሄድ አለበት ይሆን፣ ማንም ከአባቶቹ ደገኛ ታሪክ የተወለደ ኩሩ ዜጋ፣ ይሄ የአድዋ ድል በዓል በመጣ ቁጥር ያለ ልኩ የተሳፋ ለምድ ለብሶ እራሱን “የአባቶቹ ልጅ” እያለ የሚጠራው  ሁሉ ዛሬ እየሆነ ያለውንና ቃላት ሊሸከሙት የማይቻላቸውን ግፍ  ከአባቶቹ ዜና መዋእል ጋር እንዴት ቢያስማማው ነው ዝምታን የማርያም መንገድ አድርጎ እለቱ አመት እየሆነበት መኖር የቀጠለው?የደገኛ አባቶቸ የጀግንነት ታሪክ ለሽዎች አመታት ያለ ማቁዋረጥ ከአባይ ወንዝ እኩል ሲፈስባት በኖረች አገር ላይ ጥቂት ድኩማኖች በዚህ ደረጃ አገሩን ይፈቱት ዘንድ መንገዱን እንዴት አገኙት? ክፍተቱ የት ላይ ነው የተፈጠረው? በርግጥ ሃብታሙ አያሌው ላይ እና ሌሎች እንደሱ እድሉን ያላገኙ ነገር ግን በምድራዊ ገሃነም ውስጥ እየተቀቀሉ ያሉ ህልቁ መሳፍርት ወገኖቻችን ላይ እየሆነ ያለውን ለማወቅ  ዛሬም ነጋሪ ያስፈልገን  ይሆን? ለመስማት ያልተፈቀደውን ሁሉ ሰምተነዋል። ጥያቄው ይኽ በሃብታሙ አያሌው አንደበት የሰማነው ወደ ካንሰርነት ደረጃ የወረደ የትውልድ ደዌ ዛሬም እንደ ትናንቱ የአንድ ሰሞን የሚዲያ ሙቀት ሆኖ ይቀር ይሆን ወይንስ ሽህ ሚሊዮን ደመቀ ዘውዴንና አርበኛ ጎቤን ፈጥሮ ያልፍ ይሆን..? መርገምቱንስ ብንገላገል ይኽን የግፍ ጽዋ ሲግቱን ከኖሩት እኩያን ጋር እንደ ህብረተስብ አብረን የምንዘልቀው እንዴት ነው? የሚለው ነው።ይኽን የሃብታሙ ቃለምልልስ አዳምጨ እንደጨረስኩ በአይምሮዬ የመጣው ያ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ታሪኩ የተገለጣው ነገደ ኤፍሬማዊ ነበር፣”እግዚኦ እምዉሁዳነ ምድር ንፍቆሙ፤ በህይዎቶሙ”። ሉቃስ፩፮፤፪፭ ይለዋል። ይኽ ታሪክ በትርጓሜ ቤተክርስቲያን እንዲህ ተተንትኖዋል።
ውሁዳነ ምድር ያሰኘው እንደ ምንድን ነው ቢሉ ክህነ ደብረ ኤፍሬም ይለዋል።ሚስቱ ተጣልታው ወደ ሃገሩዋ ብትሄድ እርሱም ተከትሎ ሄደና በደጅ ተቀመጠ። ዘመዶቹዋም “ወንድማችን ሆይ ከሚስጥ እንደሆነ እናስታርቀኻለንና ከቤት ግባ “ቢሉት ገብቶዋል። እርቅም አደረጉለትና አመሰገኖ በነጋታው መንገድ ገባ ይላል።
በጠዋት ቢነሱ እለቱን ይደርሱ ነበር፤መሴፋ ሲደርሱ መሸባቸው። ብላቴናው ከዚህ እንደር አለው። የለም ከዚያ ወንድማችን የሚሆን አለ። አኗኗሩ እንደ ሎጥ ቢሆን ነው፤ለኛ እራት ለከብቶቻችንም ገፈር አንልህም ማደሪያ ብቻ ስጠን እንለዋለን ብለው ወደዚያው አቀኑ።የማን ወገን ናችሁ፣ ወዴት ስትሄዳላችሁ አላቸው፤ ንሕነ ኃለፍተ ቤተልሔም እንሔዳለን፣ ወገናችንም ከነገደ ኤፍሬም ነን አሉት። እናንተ እማ ወንድሞቻችን አይደላችሁምን፣ ግቡ አላቸው። ገቡ።
ራት አግባ ሄዶ እንዲህ ያሉ ሰዎች ገብተዋል ብሎ ለአገሩ ሰዎች ነገረባቸው። ነገረ እሊህ የገባኦን ሰዎች ግብረ ሰዶም የሚሰሩ፤ እንደ ሃብታሙ አያሌው ገራፊዎች መንፈስ ቅዱስ የተጠየፋቸው ናቸው። ተሰብስበውም ሄዱና አሳዳሪውን እንግዶቹን ስጠን አሉት። በሃይማኖት ያለ ነበረና በእግዚአብሔር ስም የመጡ ሰዎችን እንደምን ብዬ ብሎ ባይሆን የኔን ልጅ ወሰዱውት አለ። ያንተን ልጅም የት ልትርቀን አሉት፤ ከዚያም እሽ ሴቲቱን (ሚስቲቱን) ውሰዱዋት እንጅ እሱንስ አልሰጣችሁም ብሎ እርሱዋን ሰጣቸው። እንደ ሻንቅላ እየተፈራረቁ አደሩባት። ዘርም አስክሯት ሞታ አደረች። ባሏ ቢሆን ግን መቸ ነግቶልኝ አይኑዋን አይቻት እያለ ሲጨነቅ አደረ። ከደጅ አጋድመው ጥለዋትም ሄደው ኖሯል። ያለች መስሎት ተነሽ እንሂድ አላት። ዝም አለች፤ ገልጦ ቢያያት ሞታለች። አባቶቻችን ከግብጽ ምድር ከወጡበት ግዜ ጀምሮ እንዲህ ያለ ግፍ ተደርጎ አያውቅም፤ በኔማ አንድ ግዜ ተደርጎብኝ የለምን፤ የሚያሳዝነኝ የእስራኤል ስራት መፍረሱ ነው እንጅ ብሎ በአህያ ጭኖ ወዳገሩ ይዟት ሄደና ስጋዋን ለአስራ ሁለት ቦታ ቆራርጦ ከፍሎ ለአስራ
ሁለቱም ነገደ እስራኤል ልኮላቸዋል።
እስራኤላውያንም “ዘወሃቦ ወንዶ ወወለቶ ለገባኦን ርጉመ ለይኩን ” ብለው እየረገሙ ተነስተዋል። ኢያውሴምም ሲደርሱ መስዋእተ፡እግዚአብሔር ሰውተው የዚህች ሴት ደም እንደፈሰሰ የብድራት መክፈያውን መንገድ ምራን ብለው ሄደው ቢገጥሙዋቸው ስድስት መቶ ሰዎች ብቻ በኮካሃ አሞሬዎች ሲቀሩ ሌሎቹን ከምድረ ገጽ አጥፍተዋቸዋል ይላል።
እንግዲህ በነገደ ኤፍሬም ላይ የደረሰው የልብ ስብራት ከሺህ አመታት በኋላ እዚህ ደደቢት ዋሻ ውስጥ እንደ ክረምት አግቢ ግዜውን ጠብቀው ዳግም በሰው አምሳል በተከሰቱና የክፋታቸው ጥልቀቱ መለኪያ ሜትር የጠፋለትን የገባኦንን ሰዎች የደም ንክኪ በወረሱ ለምጻሞችያ የነው ይመስለኛል።ለውርደታችን ዳርቻ ይኖረው። እኛም ደግሞ ዘወሃቦ ወንዶ ወወለቶ ለደደቢት ርጉመ ለይኩን ብለን ነገደ ኤፍሬማውያን በሄዱበት የበቀል ጎዳና መንገድ መጀመራችንም  የግድ ይሁን።ታሪክም እዚህ ላይ እራሱን ቢደግም የሚከስርበት አይሆንም። አምላከ ኢትዮጵያ የሰናኦርን ሰዎች ባየበት አይኑ ይያቸው።

ሕገ መንግሥቱ ዐማራ ሕዝብን አይመለከትም፤ (ሙሉቀን ተስፋው)

(መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም፤ https://www.facebook.com/brannaradio/)፤ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው ጥር 10 ቀን 2009 ዓ.ም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የሰጠው ውሳኔ ነው፡፡

በ2005 ዓ.ም ከመተከል ከተፈናቀሉ የዐማራ ተወላጆች መካከል ሁለት ሰዎች በ2006 ዓም በዶክተር ያቆብ ኃይለ ማርያም አማካይነት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መሥርተው በልደታ ምድብ ችሎት ሲከራከሩ ቆይተው ነበር፡፡ ለዶክተር ያቆብ ኃይለ ማርያም ውክልና ሰጥተው ሲከራከሩ የቆዩት ገበሬዎች ቄስ መሥፍን አስፋው እና አቶ አቻምየለው ደሴ ይባላሉ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ዶክተር ያቆብን በዚህ ጉዳይ አነጋግሬያቸው ነበር፡፡ ‹‹በየቦታው የተፈናቀሉትንና የሚፈናቀሉትን የዐማራ ተወላጆች ጉዳይ በተጠናከረ መልኩ ለመሄድ አሁን የያዝነው ክስ ወሳኝነት አለው፤ ፍርድ ቤቱ መንግሥት ጣልቃ ሳይገባበት ትክክለኛ ውሳኔ ከሰጠ የሌሎች ተበዳይ ዐማሮች ጉዳይ ካሳ መጠየቅ የሚችሉ ከመሆኑም በላይ ቅጣት ካለው ካሁን በኋላ ማፈናቀሉም ሊቆም ይችላል›› ነበር ያሉት፡፡ ሆኖም ውሳኔው ከተሰጠ በኋላ ዶ/ር ያቆብ በጉዳዩ ላይ አሁን ያላቸውን ለማግኘት ሞክረን አልተቻለም፡፡

በጠበቃቸው በኩል የቀረበው የገበሬዎች ክስ 839,600.00 የወደመና የተዘረፈ ንብረት ግምት ሲሆን በተጨማሪም በተሠራባቸው ሕገ ወጥና አረመኔያዊ ተግባር የክልሉ ባለሥልጣናት ተገቢውን ቅጣት አግኝተው የሞራል ካሣም ጭምር እንዲከፈላቸው ነበር፡፡ ከሳሾች በተፈናቀሉበት ቀዬ ከ15 እስከ 20 ዓመት ቤተሰብ መስርተው፣ ልጆችን ወልደውና ሀብት አፍርተው ከመኖራቸውም በተጨማሪ ማናቸውንም የአንድ ዜጋ ግዴታዎች ሳያጓድሉ ቆይተዋል፤ ግብር ይከፍላሉ፤ ምርጫ ይመርጣሉ፣ የልማት ይከፍላሉ ወይም በአጭር አነጋገር ማናቸውንም የሚጠበቅባቸውን ጉዳይ ይፈጽማሉ፡፡ በዚህ ሒደት በ2005 ዓም በማስታወቂያ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ መባሉ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 32 ማንኛውም ዜጋ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራት መብቱን የሚጥስ በመሆኑ ሕገ ወጥ ነው በማለት ነበር የተከራከሩት፡፡

ተከሳሾቹ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር፣ የቤኒሻንጉል ክልል መንግሥትና የመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አስተዳደር ሲሆኑ ያቀረቡት መከራከሪያ ቀድሞ ይኖሩበት አካባቢ መሻኛ አላመጡም እንዲሁም በክልሉ ለመኖር ፈቃድ አልጠየቁም የሚል ነው፤ ወይም የክልሉ መንግሥት እንዲመጡ ጋብዟቸው ስላልሆነ በክልሉ ለመኖር አይችሉም የሚል አንድምታ ያለው መልስ ለፍርድ ቤቱ አቀረቡ፡፡
ምንም እንኳ ከሳሾች ከ15 እስከ 20 ድረስ ሲቆዩ በሕጋዊነት መሆኑ ዕሙን ቢሆንም እስካሁን ባለው በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ማንም ዜጋ በፈለገው አካባቢ በፈለገው ሰዐት መሔድና መኖር እንደሚችል እንጅ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ለመሔድ የፈለገ ሰው የመግቢያ ቪዛ መጠየቅ እንዳለበት ወይም መጀመሪያ ከነበረበት አካባቢ የመውጫ ቪዛ መጠየቅ አለበት የሚል ምንም ዓይነት ሕግ የለም፡፡

ከዓመታት እንግልት በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ግራ የሚያጋባ ከመሆኑም በላይ ሕገ መንግሥቱ የዐማራ ሕዝብን እንደማይመለከት በትክልል ያስገነዘበ ሆኗል፡፡ በፍርድ ቤቱ በውሳኔው ዜጎች በመረጡት ቦታ የመዘዋወር መብት ስላላቸው መፈናቀላቸው አግባብ አይደለም ካለ በኋላ የወደመባቸው ንብረት ካሣ ግን አይከፈላቸውም ብሏል፡፡ ይኸው ችሎት ተጎጅዎች ንብረታቸውን አውድመው ለአፈናቀሏቸው ሰዎች ፍርድ ቤት ለተመላለሱበት ወጪያቸውን መሸፈን አለባቸው ሲል አስደናቂ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ሕገ መንግሥትና የዐማራ ሕዝብ እንዲህ ናቸው፡፡ የሕግ ባለሙያ ሰዎች በዚህ ላይ ተነስታቸው ትንታኔ ብትሰጡበት መልካም ነው፡፡

(ሙሉቀን ተስፋው)