የተጋድሎው አይዲዮሎጅ ምን እንደሆነ ይነገረን! በተለይ ለአ/ግንቦት ሰባት (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ

አንድ ድርጅት ምንነቱ የሚመዘነው አንድም ድርጅቱ በተቋቋመበት አላማ፣ ድርጅቱን በሚመሩት የሰዎች አይነት፣ሰዎቹ የድርጅቱን አለማ ወደ ጫፍ ለማድረስ ያላቸው ቁርጠኝነት እና ይኽ ድርጅቱ ከራሱም ባሻገር ከሌሎች መሰል ተቋማትም ሆነ እታገልለታለሁ ከሚለው ማህብረሰብ ጋር ያለው ቀጥተኛ ግንኙነት ጭምር ነው።Patriotic Ginbot 7 fighters in action

ወያኔ በዚህ ስሌት ሲመዘን የድርጅቱ ጠንሳሽና አንኳር ናቸው የሚባሉቱ ሰዎች በዘመን እርዝመት የማይጠግግ በጸረ ኢትዮያዊነት ይልቁንም በጸረ አማራና ኦርቶዶክስ ሽንት ተቦክተው የተጋገሩ ናቸው።ይኽን አላማ ዳር ለማረስ የሚያስችል ደግሞ በቂ ጥላቻ አላቸው። በአስራ ዘጠኝ ስልሳ ስምንት የተጻፈው የደደቢቱ ማኔፌስቶ እስከ አሁን ያልተሰረዘው ለዚህ ነው። ጠንካራ ጎናቸው ነው ከተባለ የወያኔ ጠንካራ ጎን ይኼው ጠላቴ ብሎ ባሳመረው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያለውን አቋም ዛሬም ከአራት አስርተ አመታት ቦሃላ እንኳን ሳይቀር በጥርሱ ነክሶ እንደያዘ መቆየት መቻሉ ነው።ይኽ ማለት ትሃት ወያኔ፣ ኢህ አዴግ ብሄር-ብሄረሰቦች፣ ቦናፓርቲዝም፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲና ህዳሴው ሽህ አይነት ስም ይሰጠው እንጅ በመርህ ደረጃ የወያኔ አይዲዮሎጅ አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ማጥፋት መሆ ዛሬ ለማንም ጠርቶ የወጣ እውነት ሆኗልና ለክርክር የሚጠፋ ጉልበት የለም።

በሌላ በኩል ይህን ሰይጣናዊ አላማ ተፈጻሚ ለማድረግ ከፊት የተሰለፉት እነዚህ የስርአቱ ጉምቱዎች ከድቁርና፣ ከበታችነት ስሜት፤ ከጥላቻና ከችጋር ሰቀቀን የወጡ መሆናቸው፣ በታሪክ አጋጣሚ አንድ ግዜ እጃቸው ላይ ከገባው ስልጣን ውጭ ሌላ ነገን የማየት አቅም ማጣታቸው ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቢወጡ ሌላ ሊሆኑ የሚችሉት ምንም አይነት ማንነት የሌላቸው፤ ከጸጋ በታች እራቁታቸውን የተወለዱ መሆናቸው ነው። እንዲህ አይነት ሰዎች ደግሞ ከስልጣን ወንበራቸው ላይ ተጣብቆ ለመሞት ካላቸው እልህ የተነሳ ዛሬ በምናየው ደረጃም ሆነ ነገ በሚገለጠው የከፋው ማንነታቸው ቢከሰቱ ሊደንቀን አይገባም።

የሰላማዊ ትግል ክሽፈት

ባለፉት እሩብ ምዕተ አመታት ለውጥ ለማምጣት በአገራችን ውስጥ የተደረጉት ሰላማዊ ትግሎች በሙሉ ጸሃይ እንደገላመጠው ጉም በነው የጠፉትበት ምክንያቱ ዛሬም ይህንን አጀንዳ መኖሪያ ያደረጉት የጆሊ ባር አካባቢ ፖለቲከኞች እንደሚሉት “ሰላማዊ ትግሉ በሚገባ ስላልተፈተሸ” አይደለም። መሰረታዊ ችግሩ ከላይ በደምሳሳው የተቀመጠው የወያኔ ባህሪ ነው። ከሰብ አዊ መብት ተሟጋች እስከ ነጻው ፕሬስ ጋዜጠኛ፣ ከዋልድባ ምናኔ እስከ ተዋዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሁሉም ያልተቻሉባት፣ ይልቁንም አገሩን መግዛት ከጀመሩ ከሁለት አስርተ አመታት ቦሃላ ሳይቀር ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ስምንት ሁለት ፐርሰንት የፓርላማ ወንበር ይዘው አንድ ግርማ ሰይፉ ጸጉረ ልውጥ ሆኖ ስለገባባቸው የተፈጠረባቸውን ስጋት ብሎም ቀሪ የተስፋ ጭላንጭል የማይታይበት መሆኑን ያየነው ነው።ይልቁንም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምርጫ “ካልኩሌቲቭ ሪስክ” ነው ብሎ የደመደመ፣ “በምርጫ ስልጣን ለመያዝ የሚያስቡ ካሉ እግር እስኪያወጡ መጠበቅና ጠብቆ በመቁረጥ ስሌት የምንሄድ መሆኑን ይወቁት” ብሎ ግልጥ ባለ አማርኛ የድጅቱን እውነተኛ ባህሪ “ከውስጥ ከፍቶ ያሳየው” የስርዓቱ አፈ ሊቅ ተክሎት የሄደው የመርዝ ሰንኮፋ ዛሬም ከአራት ኪሎ አልወጣምና ህመሙ ይቀጥላል።

ቢሆንም ግን ይህን የወያኔ ቀይ መስመር ከቁብ ባለመቁጠር በየግዜው ለሽንገላ ያህል በምትከፈተው ከመርፌ ቀዳዳ በቀጠነች ወሽመጥ ውስጥ ተጉዘው መብታቸውን ለማስከበር የሄዱት ሁሉ እንዲህ መንገድ ላይ ባክነው እየቀሩም እየተነሱ በየትኛውም መንገድ ይሁን ብቻ “ዲሞክራሲያዊ መብታችንን እናስከብራለን” ብለው ትግል ውስጥ የገቡት ሰዎች ሁሉ ይሕንን መብታቸውን ለማስከበር እንደ ብርታታቸው፣ የአላማቸው ጽናት፣ አለማቸውን የተረዱበትና እንዲሁም ለራሳቸው ባላቸው ክብር ልክ ከሰማይ በታች የቱንም ያህል ዋጋ እየከፈሉ እዚህ ደርሰዋል። አንድ ግዜ ለመርህ መቆምን፣ የህይወት ፍልስፍና አድርገው የተቀበሉ ሰዎች ደግሞ በአምባገንኖች ስር ወድቀውም እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሻቸው ድረስ ያመኑበትን እየተናገሩ መሞታቸው የሚጠበቅ ነው።እንዲህ አይነት ሰዎች ወደዚህ አይነት ድምዳሜ ላይ የሚደርሱት በመሞትና መብትን ተገፎ በመኖር መሃል ምንም አይነት ልዩነት የለውም በሚለው አቋማቸው የተነሳ ከነ ክብራቸው ለመሞት በሚኖራቸው ቁርጠኛ ውሳኔ ነው። ይኽ ነገር እሩቅ ሳንሄድ በነ እስክንድር ነጋ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ በቀለ ገርባ፣ፕ/ሮ መስፍን ወልደ ማርያም፣ አበበ ቀሲቶና በመሳሰሉት ያየነው እውነት ነው:: ነገር ግን እነዚህ ከላይ ስማቸውን የዘረዘርናቸው ሰዎች በሙሉ አንዳቸውም ቢሆን ላመኑበት ነገር የህይወት ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ የሆኑትን ያህል ሌላው ቢቀር አስረው የሚገርፏቸውን ሰዎች ሳይቀር ለመግደል የሚያስችል የህሊና ዝግጅት ግን የላቸውም።እንከተለዋለን የሚሉት ፕሪንሲፕል (መርህም) ደግሞ አይፈቍድም። የሰላማዊው ትግል ፍልስፍና የቆመበት ይህ የሜታፊካል አለም ውበት የሚመስል አስተምህሮ ደግሞ ያለመታደል ሆኖ እንደ ወዩኔ ባሉ ጋንግሪኖች አይን ሲታይ እንደ “ደካማ ጎን” መወሰዱ ነው ችግሩ፤ይህ የሰላማዊ ትግል በሽታችንን ያላገናዘበ የሃኪም ፕሪስክሪብሽን መሆኑ ነው የእኛም እዳ::

በዚህ የስልጣኔ ብርሃን በሰፈፈበት የመረጃ ዘመን በብዙ የአለማችን ክፍል “ለዲምክራሲና ፍትህ ግንባታ” ተብለው በተደረጉ አያሌ ትግሎች ውስጥ ለዲሞክራሲያዊ መብት ብሎ ወደ መገዳደል ደረጃ የሄደ ትግል ጎልቶ የታየበት አጋጣሚ የለም። ጉዳዩ እንዲህ ከፍ ያለ የሞራል እሳቤ የሚጠይቀውን ቀርቶ ሰው በመሆን ብቻ አብሮን እንዲኖረን ግድ በሚሆንበት በጣም ተራ የሆነ የሰብዓዊነት ደረጃ እንኳን ከሰው የተፈጠሩ ለመሆናቸው አፋችንን ሞልተን በማንናገርላቸው በላኤ ሰቦች መሃል የሞራል ሰው ሆነው በመገኘታቸው ብቻ የሰላም ፈርጦቻችን የዘንባባ ዝንጣፊን ይዘው ነገር ግን እንዲሁ እንደ ወንጀለኛ አይከፍሉ ዋጋ እየከፈሉ የውሻ ሞት መሞታቸው ሰላማዊ ትግል ብለው ለሩብ ምእተ አመት የያዙት መንገድ በእርግጥም እንደ አገር ለገባንበት ስር የሰደደ ማጥ የታዘዘ ግዜው ያለፈበት አንቴዢያን መሆኑን የከፈልነው ዋጋ ከበቂ በላይ ምስክር ነው።እንቁው በእሪያው ስር መውደቁ ነው እውነታው::

ህዝባዊ እንቢተኝነት

ህዝባዊ እንቢተኝነት ሲባል አንድ አምባገነን መንግስት በሰላማዊ መንገድ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ፈቃደኛ አልሆን ሲል ህዝቡን የትግሉ አካል በማድረግ ተቃውሞውን ከሰላማዊ ሰልፍ እና ከመሳሰሉት የትግል ዘዴዎች ወደ ህዝባዊ ንቅናቄ (እምቢተኝነት) ከፍ በማድረግ መንግስት ለሚያወጣው ማንኛውም አይነት ደንብና ስርአት ተገዥ ባለመሆን ስልጣን ላይ ያለውን አካል አስገድዶ የፈለጉትን ማስፈጸም ወንም ከስልጣን እንዲወርድ እስከ ማድረግ ይሄዳል።

ይሕ ነገር አንጻራዊ ነጻነት ባለባቸው አገሮች ውስጥ በብዛት የሚሰራበት “የብርቱካን አብዮት” የሚባል ጤናማ የሆነ መንገድ ነው። ነገር ግን በዚህም ደረጃ ተሄዶ መብትን ለመጠየቅ አንድ አገር የሚኖረው የመንግስት ባህሪ፤ የህብረተሰቡ የንቃት ደረጃ; እንዲሁም ወጥ እና ግልጽ የሆነ አጀንዳ ያስፈልጋል። በኛ አገር በተለያየ ግዜ ተሞከረው እየከሰሙ የቀሩት የህዝባዊ እንቢተኝነት ጥያቄዎች ስማቸው እንደሚያመለክተው ህዝባዊ አልነበሩም፤ ወይንም አገራዊ አጀንዳዎች አይደሉም።

1 የእስላሞቹ ድምጻችን ይሰማ የሶስት አመት ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ በዛው በሃይማኖታዊ የውስጥ ጉዳይ ባለ አስተምኽሮ የተነሳ በመሆኑ ማንም ከነርሱ ውጭ ላለ ሰው ምክንያቱ በቂ ሆኖ ሌላውን ዋጋ እንዲከፍልላቸው የሚጋብዝ አልነበረም።

2 የኦሮሞ ህዝባዊ እምቢተኝነት ጥያቄ መነሻ ምክኛቱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ነው።

3 የአማራው ጥያ ቄ መነሻ ያደረገው ወልቅይትን በመሆኑ ይኽ የወልቃይት የመሬት ትያቄ ከ አማራው ብሔር ውጭ ላሉት የህብረተብ ክፍሎች ያን ያህል አንጀትን የሚያላውስ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ የመሆን እድሉ አናሳ ነው።ይልቁንም ዛሬ በጎንደር የተጀመረውን ህዝባዊ ተጋድሎ ተስፋ የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን የመኖራቸውን ያህል “ነፍጠኛ ዳግም ሊመጣብን ነው” በሚል እንደ ትግራዩ ገዥ ጉጅሌ ሁሉ ሱሪያቸው መበላሸት የጀመረባቸው ጎሰኞችና ምእራባውያን ጭምር ጮኸቱን ሲያራግቡት እያየን ነው።

አገራዊ ትግሉ የግድ የሚሆንበት ዋነኛ ምክኛት ምንድን ነው?

፩ አንደኛ ህዝባዊ(ፖፑላር) ነው፤ በብዙ ፈተና ውስጥ አልፎ ለሽህ አመታት እራሱን አስከብሮ እዚህ መድረስ የቻለው ኢትዮጵያዊነት ምንም እንኩዋን ወያኔ አመጣሽ በሆነው የዘመኑ የጎሰኝነት አስተሳሰብ የቆሰለ ቢመስልም አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያዊነት ባለው የተከታይ ቁጥር፣ በካበተው የአቸናፊነትና የስነልቦና የበላይነት፣ ነገ ለምንናፍቃት አገራችን የሚሰጠው የተሻለ ዋስትና እና በሌሎችም በርካታ ምክኛቶች አሁንም ተወዳዳሪ የሌለው የመታገያ ማእቀፍ እና መድረሻ ግብ ጭምር ነው።

፪ አገራዊ አጀንዳው አማራውን ህዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚያሳትፍ መሆኑ እና አማራው ዛሬም ከራሱ ክፍል ውጭ በብዙ የአገሪቱ ክፍል ተሰራጭቶ መኖሩና አገሪቱን ድርና ማግ ሆኖ ማስተሳሰር መቻሉ; እንዲሁም ህዝባዊ ተጋድሎው የጀመረበት የአማራ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚኖረው የጎንደር የጎጃም ፣ የወሎና የሸዋን ህዝብ እንኩዋን ብንወስደው በየትኛውም መልኩ ድህረ ወያኔ በምንገነባት አገራችን ላይ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለመቀጠል ችግር የሌለበት የህብረተስብ ክፍል መሆኑ አንዱ የዚህች አገር ተስፋ ነው።

፫ ፊደል የቆጠረውና በአብዛሃኛው የአገሪቱ ታላላቅ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ ጨምሮ በወያኔ ዘመን የጎሳ ተስቦ ቫይረስ እየተወጉ በነሳሞራ ጫማ ልክ ከተሰሩት በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከሚኖሩት ገና በለጋነት የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚኖሩት ውጭ አሁንም የአንድነት ሃይሉ የምርጫ ጉዳይ የማይሆንባቸው በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ሌሎቹ ግብዓት ናቸው። ከምንም በላይ በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩት አንጋፋ የ ሃይማኖት ተቋማት ዛሬም ድረስ በመርህ ደረጃ የወያኔን የጎሰኝነት ቀንበር ሰብረው የወጡና በ አደባባይ ኢትዮጵያዊነት የሚሰበክባቸው መሆናቸው ሌላው የወያኔን የመበታተን እቅድ ፈተና ውስጥ የጨመረ ነገር ነው፤ለዚህም አንዱ ምሳሌ ከቤተመንግስቱ አወቃቀር በላይ ከ አንድ ጎሳ በተመዘዙ ሰዎች እግር ተዎርች የተቀፈደው የኢትይጵያ ኦርቶክስ እንኳን እስካሁን ድረስ የሚከተለው ነባሩን የክፍለ ሃገር አውቃቀር እንጅ ወያኔ ይዞት የመጣውን የክልል አደረጃጀት ያልተቀበለው መሆኑ ነው።በአጠቃላይ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች በማጣመር የወያኔን የጎሰኝነት ግድግዳ ውልቅልቁን ለማውጣት የአንድነት ሃይሉን ብቸኛው አማራጭ ያደርገዋል።ይኽ ሁሉ የህብረተሰብ ክፍል በጣም ኮንሰርቫቲቭ በሆነ ስሌት ቢደመር አገሪቱ ካላት ህዝብ ከሶስት እሩብ በላይ የሚሆን ተጽእኖ ፈጣሪ ሃይል ሊሆን እንደሚችል ደረትን ነፍቶ መናገር ይቻላል።

የነጻነት ሃይሉ አይዲዮሎጅ ምንድን ነው?

ካሁን በፊት ለዶር ብርሃኑ የቀረበላቸው አንድ ጥያቄ “ወያኔም ድሮ ጫካ እያለ ስለ ዲሞክራሲ ያወራ ነበረ፣ ነገስ እናንተም አዲስ አበባ ስትገቡ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንደምታቆሙ ዋስትናው ምንድን ነው” የሚል ነበር፣

እርሳቸው የሰጡትም መልስ በደምሳሳው “ኢህአፓንና ወያኔን ጨምሮ በኢትዮጵያ ታሪክ ነፍጥ አንስተው ጭካ የገቡት በሙሉ ለዲሞክራሲ ብለው ሊታገሉ አልነበረም፤ከፊሉ ሶሺያሊስት ኢትዮጵያን ከፊሎቹ ደግሞ ጠባብ የሆነ የራሳቸውን የብሄርተኝነት ጥያቄ ለማራገብ የገቡ በመሆናቸው የህዝብን ጥያቄ መመለስ ቢሳናቸው አይገርምም። በኔ እምነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ብሎ በረሃ የገባ ድርጅት በ አገራችን ታሪክ የ አርበኛች ግንቦት ሰባት ብቻ ይመስለኛል፤ እና ዋስትናው ከዚህ መሰረታዊ እሳቤ ላይ ይመነጫል” ነበር ያሉት።አቶ ነአምን ዘለቀም ደግሞ እኛን ያሰባሰበብ የዲሞክራሲና የፍትሕ ጥያቄ እንጅ ዘር አይደለም” ብለው ይሕንኑ ጥያቄ ተመሳሳይነት ባለው መልኩበሌላ መድረክ ላይ ለማጠናከር ሞክረዋል።

ሁለቱ የአ/ግንቦት ሰባት አመራሮች ይኽን አባባል እንደ ፖለቲካኛ ከላይ ጨልፈው ለተራው ህዝብ የተናገሩትና ለፖለቲካ ፍጆታ የዋለ አነጋገር (ክራፍትድ ስፒች) ወይንስ የግል እምነታቸው ነው? በእርግጥ ይህ ነገር መሬት ላይ ወርዶ ዘገር የነቀነቀውን አርበኛ ሁሉ የሚጨምር ነው ወይንስ አይደለም ? ቅድም ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው ላለፈው እሩብ ክፍለዘመን በአገራችን የተካሄዱት ሰላማዊ ትግሎች ሁሉ ለምን ሊሰሩ እንዳልቻሉ ግልጽ ለማድረግ ተሞክሯል። በዚህ መስመር “ለፍትህና ለዲሞክራሲ” ብለው የታገሉት የጸረ ወያኔ ፓርቲ አባላትም ሆነ የሲቪክ ኢንስቲቱሽን አመራሮች ከአሰፋ ማሩ ጀምሮ እስከ ሳሙኤል አወቀ ሁሉም በየደረጃቸው በህይወትም በእስራትም በስደትም ዋጋ ከፍለዋል። አንዳቸውም ግን ለመሞት ያሳዩትን ድፍረት ያህል ወያኔን ለመድገድል ግን ምንም አይነት የመንፈስም የሆነ የአላማ ዝግጁነት እንደሌላቸው አይተናል።በወያኔ ዘመን እንደ ድስት ገንፍለው እራሳቸውን ያበላሹ ተቃማዋሚዎች ሁሉ ስለ ማንዴላና ስለ ማህተመ ጋንዲ በመለቅለቅ ወረቀት ሲያባክኑ ኖረው የትም ያልደረሱት በዚሁ ምክኛት የተነሳ ነው::የአግንቦት ሰባትን ጨምሮ በየጢሻው ነፍጥ ያነሱት ድርጅቶች ሁሉ የተወለዱት ከእንዲህ አይነቱ የውርደት ማህጸን መሆኑ ግልጥ ነው::

በመሆኑም አ/ግንቦት ሰባትን ጭምሮ የጸረ ወያኔ ትግሉን የተቀላቀለ ማንኛውም አካል የወያኔ አይዲዮሎጅ ኢትዮጵያን ማጥፋት መሆኑን ከልቡ የተቀበለና ከሰማይ በታች ከነዚህ ሰዎች ጋር የሚደረግ ምንም አይነት ድርድር ማለት እባብን አስለምዳለሁ አይነት ሞኝነት መሆኑን ከልቡ የተቀበለ ነው ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ነገር ግን እኒህ በቁማቸው ቀርቶ በክተውም መቃብራቸው ጋሬጣ የሚሆኑ እርጉማንን ለማስወገድ የማንከልሰው የማንሰልሰው አንድ ወጥ የሆነ የትግል አይዲዮሎጅ እንደሚያስፈልገን ግልጽ ሊሆን ይገባል።በዚህ መንገድ ከሄደን አርበኞች ግንቦት ሰባት “ማስገደድ ወይንም ማስወገድ” ሲለው የከረመው ባለ ሁለት መንታ ስሌት ከፖለቲካ ፍጆታ በላይ አልፎ የማይሄድ የጠዋት ጤዛ መሆኑን ቢያንስ የዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ እንዳይሰማው በአማርኛ ሹክ ሊለን ይገባል።

አይዲዮሎጅ መኖሩ ጥቅሙ ምንድን ነው፣

የአይዲዮሎጅ ትግል ለፍትህና ለዲሞክራሲ እንደሚደረግ ትግል ማንም እንደፈለገ የሚተረጉመው፣ ማንም እንደፈለገ የባልተቤትነት ድርሻው አድርጎ የሚወስደው፣ ንብረትነቱ የሁሉም የሆነ ማለት አይደለም። የዲሞክራሲና የፍት ሕን ጥያቄ መሰረት አድርገው የሚጀመሩ ትግሎች ዋነኛ ችግራቸው ከጸሃይ መውጫ እስከ ጸሃይ መግቢያ ያለ በቁመተ አዳም የተፈጠረ ሁሉ የራሱ አልማና እራእይ አድርጎ ሊወስዳቸው የሚችላቸው የወል ንብረት መሆናቸው እኛ ኢትዮጵያያውያን እንደ ህብረተሰብ ዛሬ ለገባንበት ግብግብ የሚመጥኑ ወይንም ቤት የሚደፉ ጥያቄዎች አይደሉም። ለኛ ዛሬ የዲሞክራሲ ጥያቄ ማለት የፍት ህ ጥያቄ ማለት የቅንጦት (ሌክዠሪ) ጥያቄ መሆኑን በየቀኑ ወደ መቃብር የምንገፋው ሰዎች ቀርቶ አለም ያውቀዋል። ዛሬ የእኛ ትግል በዳርዊም ቲዎሪ ዘ ሰርቫይቫል ኦፍ ዘ ፊተስት የመኖር እና ያል፤አ መኖር ጥያቄ በሆነበት ሁኔታ በጠባቡ የሚተረጎም፤ ግልጽና የማያሻማ፣ በጸረ ወያኔ ጎራ ያለነውን ሰዎች ብቻ በ አንድነት የሚያስተሳስር ወጥነት ያለው አይዲዮሎጅ የሚያስፈልገው በሚከተሉት ተጨ፣ማሪ ምክኛቶች ነው።

፩ በአይድዮሎጅ የታሰረን ትግል ቃል ኪዳኑ ያደረገ ሰው ለችግሩ እርግጠኛ የሆነ መፍትሄ አለኝ ብሎ ያምናል።

፪ ይህ ሰው በምንም አይነት መልኩ አንድ ግዜ ጠላቴ ነው ብሎ ያሰመረው አካል ላይ ምንም አይነት ብዥታ ስለማይኖረው እርሱን እስከመጨረሻው ድረስ ተናንቆ ጉድጓድ ሳያስገባ አይመለስም።ለዚህም አላማው ተፈጻሚነት ከሰማይ በታች የማይከፍለው ዋጋ የለም። መስዋእትነት የጥልቅ እምነት መራራ ውጤት ነውና።

፫ የጸረ ወያኔውን አይዲዮሎጅ አንድ ግዜ እንደ ሃይማኖት የተቀበለ ሰው ሃላፊነቱን ወደ ሌላው አይገፋም። ባጭሩ ትግሉን ለመምራት ከኔ የተሻለ የመብትም የሞራል የበላይነት ያለው የለም ብሎ ስለማያምን በሌላ ከሰማይ በታች ባለ ቁሳዊ ሃይልም ይሁን መከራ ተደልሎም ይሁን ተሸንፎ በህይወት ለመትረፍ ሲል ትግሉን አቻችሎ ለማለፍ (ኮምፕሮማይዝ የማያደርገው) የማይሞክረው ወይንም ለድርድር የማያቀርብው ለዚህ ነው።ይኽ የገባንበት ትግል ደግሞ ለመሞት ብቻ ሳይሆን ለመግደልም ዝግጁ የሆነ ታጋይ ያስፈለገበት ምክንያት የምንታገለው ጠላት መቶ ሚሊዮን ሰው ለመግደል በቂ ጥላቻ ያለው እኩይ መሆኑን ነው።

በእኔ እምነት ሁለቱ ከፍተኛ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ያገናኘን ዘር ሳይሆን ስለዲሞክራሲና ፍትህ ያለን የጋራ አመለካከት ነው ሲሉ መነሻ ሃሳባቸው ለነገይቱ ኢትዮጵያና ለዚህ መከረኛ ህዝብ ነገ ቢኖረው የሚመኙለት ራእይ እንጅ እለቱን ዱር ቤቴ ብሎ ያስገባቸው አለምን ያስካዳቸው መሰረታዊ ምክንያታቸው ብዬ ለማመን ይከብደኛል። ነው ከተባለ ግን በደንብ አስበውበታል ለማለት ይቸግረኛል።ለምን ቢባል መሬት ላይ የወረደዉን እና ዘገር የነቀነቀውን እያንዳንዱን ታጋይ የህይወት ታሪክ እና ለምን “ጥራኝ ዱሩ” እንዳለ ቢጠየቅ አንዱም ቢሆን “ዲሞክራሲን የፍትህ ናፍቆት ነው ሊል እንደማይችል ከብዙዎቹ አርበኞች የህይወት ታሪክና በውስጣቸው ከሚንተገተገው እልህ መረዳት ይቻላል። ሁሉም ልብ ሰባሪ ታሪክ አለው፤ እራስን በጾም በጸሎትና በትጋሃ ሌሊት እየቀጡ አለምን ክደው በዋልድባ መንነው የመኖር መብታቸውን ካጡ ሰማያዊያን ጀምሮ ሳላሳ ሶስት ዘመዶቹ እስከ ተገደሉበት የወልቃይት ተወላጅ በአይነት የማይሰማ ሰቀቀን የለም።ለአብዛሃኛው በረኸኛ ይኽ ትግል የግል ጉዳይ (በጣም ፐርሰናል) ነው:: ሁሉም በረሃ የወረደው ለበቀል ነው። ውርደት ጥፍሩ ውስጥ ገብቶበት ነው። ለእንዲህ አይነቱ ከፊት ግንባር ላይ ለቆመ አርበኛ ጎልቶ የሚስማማው የነ ማተመ ጋንዲና የነ ማንዴላ አይነት ያለ ችግራችን ልክ፣ ያለ ጠላታችን የክፋት መጠን የተሰራ የሸክላ ግጣም አይደለም። “ጅብ ሊበላህ ሲመጣ ብላውና ተቀደስ” የሚለው የዳርዊን ቲዌሪ እንጅ።

ለሰላማዊ ትግል ምልክት ከሆኑት ከየንታ መስፍን ወልደማርያም ጀምሮ እስከ አፈ ሙሽራውና ልማታዊው ሰባኪ ዳንኤል ክብረት ድረስ አጼ ቴዎድሮስን እብድ ብለውታል፤ ጨካኝ ነበረ፤ ሰው ገደል ይጨምር ነበረ ወዘተ ለማለት ፈልገው ነው። ነገር ግን ለመቶ አመት ያህል በዘመነ መሳፍንት ጦርነት ተበታትና ስትናጥ ለኖረችን አገር መይሳው በዚያ ደረጃ ጽንፈኛ (ራዲካል) ሆኖባይወጣ ኖሮ በእርግጥ የኽችን የምንሳሳላትን ኢትዮጵያ በቄጠማ ጉዝጓዝ ላይ ተራምዶ ማግኘት ይቻል ነበር ወይ፤ ቴዎድሮስ አንድ አድርጎ ለሚኒሊክ ባያስረክብ ኖሮስ ዛሬ የምንመካበትን የአድዋን ጦርነት ተቋቁመን የነጻነት ምልክት እንሆን ነበረ ወይ፤ መልሱ ግልጽና ግልጽ ነው።

የዛሬውን አያድርገውና ምንም ዛሬ ዜጎቿ ቢክዱትም የዩክሬንን ዋና ከተማ ኬቭን ከናዚዎች መዳፍ ፈልቅቆ ለማውጣትና ወደ ፖላንድ ሰብሮ ለመግባት ስመ ጥሩ የራሽያ ፊልድ ማርሻል ዙኮቭ የስድስት መቶ ሽህ ወታደሮቹን ህይወት መገበሩና ይኽም በሰው ልጆች ታሪክ አንዲትን ቁልፍ ከተማ ለመቆጣጠር ዘ ላርጀስት ኢንሰርክልመንት የተባለውን ገድል መፈጸሙ ድፍን አውሮፓን ከፋሽዝም ነጻ ለማውጣት ከሌኒን ግራድ የሞት ሽረት ቀጥሎ ሁለተኛው አሰቃቂ እልቂት ነበረ።ያለ ደም ስርየት የለም እንዲል ቅዱስ መጸሃፍ።

ዛሬም ቢሆን የወያኔን የመርዝ ሰንኮፋ ለማኮላሸትና የአገሪቱን ህልውና ለማስቀጠል ከነሱ በላይ ኮሶ መሆን የግድ ሊሆን ይገባል ሲባል እንዲሁ ጥላቻ ወይንም አባባል አይደለም። በመሆኑም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ማጥፋት የሚለውን የ1968 የትግራይ ገዥ ጉጅሌ ማኔፌስቶን ለማምከን እነ ሳሞራ ካላቸው ጭካኔ በላይ ጨካኝ የሆነ ስነ ልቦናን ለመፍጥር የሚያስችል እንደ ሃሞት የመረረ የትግል አይዲዮሎጅ ሊኖረን የግድ ነው። ካለበለዚያ ግን እነ አባይ ወልዱ ካላቸው ጭካኔ በላይ ለመጨከን ያልወሰነ “ራሴን የዚህ ስር ነቀል አብዮት አድርጌ ነገ የነጻነት ሻማ እለኩሳለሁ” ብሎ የሚያምን ካለ ግዜውን ባያጠፋና እንደ እናቱ ጥጡን እየፈተለ ባርነቱን ቢለምደው የተሻለ ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s