በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ዲን በማዕከላዊ እየተሰቃየ ነው

ተመራማሪ የሺወንድም ሹምዬ ከጎንደር የመጣ ዘመድ አሳድረሃል በሚል በማዕከላዊ እየተሰቃየ ነው፤ Brannamedia

አገዛዙ የዐማራ ወጣቶችን፣ ምሁራንና ፖለቲከኞችን በግፍ ማሰር ቀጥሎበታል፡፡ በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ የዐማራ ተወላጆች ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በጂምላ እየታሠሩ በማዕከላዊ የቶርቸር ሰለባ ሆነዋል፡፡

ወጣቱ ምሁር የሺወንድም ሹምዬ በወያኔ የቶርቸር ሰለባ ከሆኑ የዐማራ ምሁራን አንዱ ነው፡፡ ጥር 12 ቀን 2009 ዓ.ም ጠዋት ከቤተ ክርስቲያን ደርሶ ሲመለስ በትግሬ ደኅንነቶች ተይዞ ወደ ማዕከላዊ ከገባ አራት ወራት አልፈውታል፡፡ ከአራት ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ቀርቧል፤ እስካሁን በማዕከላዊ ቶርቸር እየተፈጸመበት ነው፡፡

ተመራማሪ የሺወንድም ሹምዬ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በሜዲካል ቴክኖሎጅ የትምህርት ዘርፍ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቀ ሲሆን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ዲን በመሆን ያገለግል ነበር፡፡ የሺወንድም በበርካታ ዓለም አቀፍ የትምህርት ጆርናሎች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎችን ያሳተመ ሲሆን  በአሜሪካን አገር ከሚገኘው ሚቺጋን ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር አንድ ለአገር የሚጠቅም ጥናት በማጠናቀቅ ላይ ነበር፡፡ ወጣቱ ተመራማሪ ወደ አሜሪካን ተጉዞ በሚቺጋን ዩንቨርሲቲ ጥናቱን ያቀረበ ሲሆን መጠናቀቅ የሚገባቸውን ጉዳዮች ለመጨረስ ወደ አገር ቤት በተመለሰ በ15ኛ ቀኑ ወደ ማዕከላዊ ገብቶ የቶርቸር ሰለባ የሆነው፡፡

ወጣቱ ተመራማሪ በማዕከላዊ ቀርቦበት የነበረው ክስ ‹‹ለዐማራ ታጋዮች የዩንቨርሲቲ ምግብ እንዲያገኙ አድርገሃል›› የሚል ቢሆንም የሺወንድም የተማሪዎች ዲን እንጅ የምግብ ክፍል ኃላፊ አለመሆኑን በማስረዳቱ ክሱም እንደማያስኬድ ሲታወቅ የክስ ጭብጡ ተቀይሯል፡፡ በተቀየረው ክስ ‹‹ከጎንደር የመጣ አሸባሪ አሳድረሃል›› በሚል አዲስ ፋይል ተከፍቶበት በቶርቸር መካከል ፍርድ ቤት እንደሚመላለስ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ወጣት ተመራማሪው የሺወንድም ከጎንደር የመጣ አብሮ አደግ መምህር ጓደኛውን የጥምቀት ዕለት አግኝቶት ከቤቱ አብረው ያደሩ ሲሆን መምህር ጓደኛውም እስካሁን አብሮ በማዕከላዊ በስቅይት ላይ ነው፡፡ የሺወንድምን ከእናቱ፣ ከእህቱና ከባለቤቱ ውጭ ማንም ሰው መጠየቅ አይችልም፡፡ በአራት ወራት ውስጥ በአማራነቱ ብዙ ስቃይና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ከሚችጋን ዪንቨርሲቲ ጋር እየሠራው የነበረው ጥናታዊ ጽሑፍም ተቋርጧል፡፡

ዘረኝነት – የሐይማኖት መሪዎች መለዮ

 


በዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ*

በምድረ ኢትዮጵያ ዘረኝነት የሚሉት ወረርሽኝ ከምንም ጊዜ በላይ ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱ የአደባባይ ምስጢር ነው። በተለይ በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ያለ ምንም በቂ ምክንያት አንድን ሕዝብ ወይም ብሔር አብዝተው የሚጠሉበት ሁኔታ በግልጽ እያየንና እየሰማን እንገኛለን። እንድህ ዓይነቱን ኃላ-ቀር እና የወረደ አስተሳሰብ አጥብቀን መዋጋት ይኖርብናል። ምላሱን አዳጠው መሰለኝ የሆነ ቀን አንድ ሰውዬ፡-

‹‹እነኝህ ለማኝ ትግሬዎች ችግር አለባቸው!›› ስል በገዛ ጆሮዬ ሰምቼ ኖሮ፤

‹‹ችግር ያለው ትግሬ፣ ካምባታ፣ ኪኩዩ፣ ኦሮሞ፣ ዶርዜ፣ አማራ፣ ሃድያ፣ ጉራጌ፣ ሉዎ፣ አሻንቲ….አይደለም! ችግር ያለው የሰው ልጅ ራሱ ነው፤ የሰው ልጅ ራሱ ለራሱ ጥያቄ ነው፤ ጭፍን ጥላቻ የበለጠ ያራርቀናል እንጅ የትም አያደርሰንም! የጥቂት ሰዎች ድርጊት የአንድ ብሔር ማንነት መገለጫ ሊሆን አይችልም፤ ለምሳሌ፡- አማራ—ነፍጠኛ፣ ኦሮሞ—ወራሪ፣ ጉራጌ—አጨበርባሪ…ወዘተ እያሉ ሕዝቡን ግራ የሚያጋቡ ሰዎች አሉ፤ አንድን ሕዝብ ስብናውን መወረፍ አግባብነት የለውም፤ እናም የቅድመ-ጥቅላሎት ሕፀፅ ፈጽመሃል…››

አልኩት!

እንዳለጌታ ከበደ ይህንን ጉዳይ እንድ ስል ነበር የታዘበው፡-

‹‹አንዳንዱ የዚህ ትውልድ አባል- ከአባቶቻችን ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው መሰረት ልበል?) የስድብ ሃብታም ነው፤ የሚተርበው ብሔር አያጣም፤ ሌላውን አሳንሶ አስጐንብሶ ካላሳየ እሱ ቀና ቢል እንኳን የሚታይ አይመስለውም፤ ልቡ በነቀፌታ የተሞላ ነው፤ አንዳች የስድብ መንፈስ-በየቤቱ- በየቤተመንግስቱ- በየቤተ ክርስትናውና በየቤተ እስልምናው ሰፍኗል፤ የሆነውን ብሔር ለይቶ፣ የሆነውን ወገን አግልሎ፤ ‹እኛ ካልተሳተፍንበት የልማት እስክስታው አይሰምርም፤ እኛ ካልደሰኮርንለት አምላክ ቸርነቱን አያዘንብም› ማለት የተለመደ እየሆነ ነው! ለመጪው ትውልድ ‹በደም› የሚመለስ የቤት ስራ እየተውን ያለ ይመስለኛል፤ የመጪው ትውልድ አባላት እኛ በመጣንበትም ሆነ አባቶቻችን በተመላለሱበት የመሰዳደብ መንገድ ባይሄድ እንመርጣለን፤ እኛ ፈትለንና ገምደን ያቆየነው፣ አለባብስን ያረስነው ነገር ነገ ከነገ ወዲያ ‹… ያልተዘጋ ፋይል አለ!› ብለው በጥይት ቋንቋ እንዲነጋገሩ መፍቀድ የለብንም- ሰርተን በቆየንላቸው መንገድ ደም እንዳያጐርፍበት፤ ሰርተን ባቆየንላቸው ተቋማት ስድብ እንዳይፈበረኩበት ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል፡፡ አዎን፤ ሁላችንም ስድቦች ወደ መጡበት የሚመልስና ወደሚመለከተው ክፍል የሚያዘዋውር ጽ/ቤት በየህሊናችን ልናቋቁም ይገባል፤ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በብዙዎች ልቦና ላይ የማይታይ ቁስልና ሰንበር እንዲታተም አድርገናልና!››

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ግን የእግዝአብሔርን ሕዝብ እናገለግላለን የሚሉ የኀይማኖት አባቶች የችግሩ አካል በመሆን ‹ወንገልን› በ‹ወንጀል› ለውጦታል። እነኝህ ፈርሳዊያን እና የሕግ መምህራን ፓስታ እየበሉ ወይንም ቢራ እየተጐነጩ ይህንን ጉዳይ ፈጽሞ አይወያዩበትም ማለት አይቻልም፤ ጠንቅቀው ነው የሚያውቁት—የእኛ አድርባዮች! ነገር ግን፣ እስከ ዛሬ ድረስ ዘረኝነትን በግልጽ ለመተቸት አይደፍሩም። አንድ የኀይማኖት መሪ የወጣለት ዘረኛ ሆኖ እያሌ ዓይኑን በጨው ታጥቦ እንዴት ‹
‹እግዝአብሔር ፍቅር ነው›› በማለት ይሰብካል? ያሳፍራል እኮ! አንድ ቄስ ወይም ፓስተር በአጠገቡ ካለው ወንድሙ ጋር ሠላም ሳይፈጥር ‹‹የእኛ እግዝአብሔር የሠላም አምላክ ነው!›› ብሎ ክላሽ ማንጣጣት ነውር አይደለም እንዴ!? የጥምቀት ውሃ ከሰው ልጅ ባህል ‹በላይ› መሆኑን ያልተቀበለ/ያላመነ አንድ አገልጋይ ‹‹ሁላችንም በምስጢረ ጥምቀት የእግዝአብሔር ልጆች ሆነናል›› ብሎ ቤተ-መቅደስን ማጣበብ ስበዛ ሌብነት፣ ሲያነስ ደግሞ ድንቁርና ነው! ሌብነት ይብቃን አቦ!

ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ በሃይመኖት ተቋማት ውስጥ ያለአግባብ መበልጽግ ባሕል ከሆነ ፤ የመልካም አስተዳደር እጦት ከተንሰራፋ ፤ የውሸት ባሕል ከነገሰ፤ አድሏዊነት፣ ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ጨቋኝነት ሥር ከሰደደ፣ በገዳማት ውስጥ በሠላምና በፍቅር አንድ ላይ አብሮ መኖር ካልተቻለ፣ መደማመጥና መነጋገር ጠፍቶ መናናቅ ብቻ ከሆነ፣ የአብሮነት መንፈስ የሚባል ነገር ከጠፋ፣ ሥራ የሚከፋፈለው በዝምድና እና በዘር ከሆነ ቤተ-ክርስቲያንን የሌቦች ዋሻ ሆናለች ማለት ነው! 
ስለዝህ፣ ዘረኝነት በግልጽ መተቸት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል። ለምን ይዋሻል! ሕዝቡ ቆንጨራ እስከሚያነሳ መጠበቅ የለብንም! በሩዋንዳ ምድር በተደረገው የዘር ጭፍጨፋ የቄሶች (እኔ መቀሶች ነው ሚላቸው!) እጅ ነበረበት። በእርግጥ እነኝህ የኀይማኖት መሪዎች ትምህርት ቤት ተመላለሱ እንጅ አልተማሩም፤ መጽሐፍና ማንበብ የቻለ ሁሉ ‹ተምሯል› ማለት አይደለም! እንዴታ! የሰባት ዓመት የዩኒቨርስቲ ትምህርት የአንድን ሰው አስተሳሰብን ካልቀየረ እኮ የጭንቅላት ጥቅም ለ‹ቆብ› ብቻ ነው የሚሆነው! አርስጣጣልስ (Aristotle) ልክ ነበር— ‹‹ልብን ሳያስተምሩ ጭንቅላት ብቻ ማስተማር ዋጋ-ቢስ ነው!››
የሆነ ሆኖ አጐስቲን ካሬኬዝ (Augustine Karekezi) የሚባል አንድ ኢየሱሳዊ ቄስ (a Jesuit priest) የሩዋንዳውን አሳዛኝ ክስተት በምገርም ሁኔታ እንደሚከተለው አስፍሮ ነበር፡-

“My faith as a Christian has been affected seriousely, in the sense that I cannot realize that such evil could happen in a country where so many people are Christians and where there are so many Catholics, over sixty five perecent, with such influence in education. What have we been doing as Christians and as priests? How can we preach the love of God, the compassion of God, in this situation? All these questions derive from an experience of the deep mystery of evil, evil that is so consistent and so strong that its power is prevailing”

ስለዝህ፣ የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ኋላፍነት አለባቸው! ሕዝቡ በቆንጨራ እየተጨራረሰ ዝም የሚትሉ ከሆነ፣ በፈጣሪና በሕግ ፊት ተጠያቅዎች ናችው። እምነትና ፀሎት ብቻ በቂ አይደለም። ሰይጣንም እኮ እግዚአብሔር የዘለዓለም ኗር መሆኑንና ታላቅ አምላክ መሆኑን ያምናል። ግን መልካም ሥራ የለውም፤ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው! የእግዝብሔር ቃልም የሚላችው ይህንኑ ነውና፤ “ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ ተጸይፌውማለሁ፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም።የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።” (አሞጽ 5፤ 22-24) ይህ ማለት፣ አንድም፣ የሚተሰብከውን ኑር እንጅ፣ ፈሪሳዊ አትሁን፤ ሁለትም፤ ‹‹ከመጠምጠም መልካም-ሥራ ይቅደም›› ማለት ነው። ‹‹ፂም በማሳደግ ቢሆን ፍየል ትሰብክ ነበር›› እኮ!!

አዎን! በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ውስጡን ዘረኝነት የሚሰብኩ ወይም የሚያቀነቅኑ ቀጣፊ ቄሶች አሉ፤ እንድ ዓይነቱን የአስተሳሰብ ሽርሙጥና ከወድው በቆራጥነት መዋጋት አለብን፤ አዎን! እነኝህ አስመሳይና አድርባይ ‹መቀሶች› እሳት ከሚተፋው የፍልስፍና ብእር ማምለጥ አይችሉም! እየተከታተልን እናጋልጣለን!
ሠላም፣ ፍቅርና አንድነት ለሀገራችን ኢትዮጵያ እያልኩኝ፣ በሃይለመለኮት መዋእል ግጥም ልሰናበታቸው!

ምን ጠቀመዉ ቃየል—የመሳሪያ ቋንቋ
ሰጠመ ጠፋ እንጂ—ባቤል ደም አረንቋ
መኢኑም አባተ—ሰመረ መረሳ
ኦቦንግ አብዱል ከሪም—ጋቸኖ ቶሎሳ
አብረኸት ምንትዋብ—ኛዳክም ጋዲሴ
በላህ በነብዩ—በሶስቱ ስላሴ
ሰይፉም ዶማ ይሁን—ሞርተሩም አንካሴ

*Yoseph Mulugeta Baba (Ph.D.) can be reached at:
kankokunmalimaali@gmail.com

ወያኔ አማሮቹን መቀሌ ላይ አፍኖ በመደብደብ ምን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት አሰላ? | ሸንቁጥ አየለ

 

ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከዚህ ዓለም የተለዩበትን 18ኛ ዓመት አሥመልክቶ የወጣ መግለጫ

አያሌው ፈንቴ
ግንቦት6ቀን2009ዓ.ም.

ሰማዕቱ ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደዬስ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት(የመዐሕድ)ፕሬዝዳንት የዛሬ 18ዓመት ግንቦት 6ቀን 1991ዓም(እ አ አ ሜይ 14ቀን 1999ዓም) በፔንሲልቫንያ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ፊላደልፊያ አሜሪካ አገር በህክምና ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም እንደተለዩ ይታወቃል።በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣በተለይ ደግሞ የአማራው ሕዝብ ይህን ዕለት አስቦት የሚውለው በታላቅ ሀዘንና ቁጭት ነው።

ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከዚህ ዓለም የተለዩበትን 18ኛ ዓመት

ክቡርነታቸው ለኢትዮጵያ ሀገራዊና ሕዝባዊ አንድነት እንዲሁም እኩልነትና ዲሞክራሲያዊ ሕይወት ግኝት የከፈሉት አቻ የለሽ መሥዋዕትነት፣በታሪክ ዓምድ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ከመያዙም ባሻገር፣ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የሚኖር ነው።

ፕሮፌሰር! ከትግሬ ዘረኞች ሥልጣን መያዝ ጋር ተያይዞ የመጣው የጎሳ ፖለቲካ ገና ከመነሻው ችግር ሊያሥከትል እንደሚችል በግልፅ ከመናገር አንሥቶ የመከራ እሳቱም ሲቀጣጠል ያንን ለማጥፋት በቀዳሚነት የተሰለፉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ።ለምሳሌ በ1983ዓም የትግሬ ዘረኞችና ዕድምተኞች ያካሄዱትን የኢትዮጵያን ሀገራዊና ሕዝባዊ አንድነት የመናድ ተግባር፣የኮንፈረንሱን ምንነትና ተልዕኮ በጀግንነት በመዋጋት ድምፃቸውን አጉልተው ያሠሙ ጀግና ነበሩ።

በ1984ዓም ዐማራው በአርባጉጉ፣በበደኖ፣በአረካ፣በአሰቦት ገዳም፣በአሩሲ ነገሌና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ህይወቱ እያለ ዓይኑ ሲጎለጎል፣ሕይወቱ እያለ ቆዳው ሲገፈፍ፣ሕይወቱ እያለ ሥጋውን ቆርጠው “ብላው እያሉ” ሲያሰቃዩት፣ሕይወቱ እያለ ቤት ዘግተው ሲያቃጥሉት፣ሕይወቱ እያለ ወደገደል ሲወረውሩት፣ሕፃናት ከእነቤተሰቦቻቸው ሲታረዱ፣የዕርጉዞች ሆድ ሲቀደድና ሽሉ ሲጣል፣ የዐማራው ልጃገረዶች ሲደፈሩ፣ሲዋረዱና ተማርከው በባርነት ሲያገለግሉ፣አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉና ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ የዘር ማጥፋት ሰቆቃዎች ሲፈፀሙበት፣ፕሮፌሰር አሥራት አይተው እንዳላዩ፣ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነው ማለፍ አልቻሉም።

በዚህን ጊዜ ዐማራው አለሁ ባይ ተቆርቋሪ የሌለው መሆኑን ተገንዝበው፣አጋር ሊሆኗቸው ከሚችሉ ወገኖች ጋር ዐማራውን ከጨርሶ ጥፋት ለማዳን በሚቻልበት ጉዳይ መክረው መዐሕድን በመመሥርት፣ቀን ጨልሞበት አለሁ ባይ ወገን አጥቶ በደም ተጨማልቆ የሚቃትተውን ዐማራ “የሚያሥጥልህ ሕግና ሥርዓት የለም፣ሞት ወይም ሕይወት ብለህ ራሥህን አዘጋጅተህ ባላጋራህን ተቋቁመህ ባለህ ኃይል ተከላከል” በማለት በሥነ ልቦና ገነቡት።

ፕሮፌሰርም በአንድ ወቅት እንዳሉት  በአራት እግሩ በመሄድ ላይ የነበረው ዐማራ አንገቱን ቀና አድርጎ በሁለት እግሩ መሄድ ጀመረ።ይህም የመጀመሪያው የፕሮፌሰር አሥራት ቆራጥ አመራር የሕይወት ፍሬ  ውጤት ነበር።በዚህን ጊዜ የትግሬ ዘረኞች  የፕሮፊሰር እንቅስቃሴ ሥላስደነገጣቸው እግር በእግር ክትትሉን ተያያዙት።

ፕሮፌሰር! ዙሪያ ገባውን በጠላት ተከብበው  ሲዋከቡ፣ ችግርና ፈተና ሳይበግራቸው፣ከፊት ለፊታቸው የተጋረጠውን ግዙፍ ኃይልና አደጋ ከምንም ሳይቆጥሩ፣በዚህ በቀውጢ ሰዓት ከማንም ቀድመው ፣የአገር ግንጠላ ወደፊት የሚያስከትለውን ችግር አሻግረው አይተው ሀቁን በመናገር እና በአማራው ላይ የሞት፣የመታሰርና የመሰደድ አደጋ  ማጥላቱን አሥመልክቶ፣ለአገርና ለሕዝብ ዘላቂ ሰላም፣ለፍትሕና እኩልነት ያለማወላወል በቁርጠኝነት በመቆም ሳይቃጠል በቅጠል በማለት እምቢ ለሀገሬ፣እምቢ ለወገኔ፣እምቢ ለዳር ደንበሬ፣ብለው በታላቅ ቆራጥነት መታገላቸው አርአያነቱ ምንጊዜም የማይረሳ ነው።  

በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት፣በህዝቡ የጋራ ዕድልና ተስፋ ላይ ዘወትር በማሴር ላይ ያለው ፀረ-አማራው የትግሬው ቡድን፣ ፕሮፌሰር አሥራትን  ከጎጃም ከመጡ ገበሬዎች ጋር በመዐሕድ ጽህፈት ቤት በመሰብሰብ የአድማ ወንጀል ፈፅመሀል” በሚል የሀሰት ክስ መሥርቶ 2ዓመት ፈረደባቸው፣ “ደብረ ብርሃን ላይ ሕዝብ የሚቀሰቅስ ንግግር አድርገሃል በሚል አንድ ሌላ ክስ መሥርቶ 3ዓመት ፈረደባቸውየጎጃም፣የጎንደርንና የሰሜን ሸዋን ሕዝብ ለአመፅ አዘጋጅተሃል”በሚልም ወንጅሎ፣ ባንዲት 80እሥረኞች በሚገኙባት ዛኒጋባ 81ኛው እሥረኛ ሆነው  ከገቡ በኋላ ለበርካታ በሽታዎች ተዳረጉ።ይሄ ቢታወቅም በጊዜው አሥፈላጊውን ህክምና በመነፈጋቸው በሽታው ሥር እየሰደደ ሄዶ አሥጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ ሆስፒታል ገብተው ተስፋ በሌለው ሕክምና ቆይተው፣ነገ ዛሬ ህይወታቸው ያልፋል ሲባል ወደውጭ አገር ተልከው አሁንም ተስፋ በማይሰጥ ሕክምና ቆይተው አረፉ።

ዘረኞቹ ትግሬዎች!  ፕሮፌሰር አሥራትን በፈጠራ ወንጀል አሥረው  አምስት ዓመት አንገላተውና አሠቃይተው በቁመና ከገደሏቸው በኋላ በማምጠጫ ዕድሜያቸው ወቅት ለይስሙላ ህክምና ወደውጭ አገር ማስወጣታቸው በዘረኞቹ ላይ የሚመጣውን ተቃውሞ ለማርገብ የሚረዳቸውና የፖለቲካ ትርፍ የሚያሥገኝላቸው መሥሏቸው ይሆናል ግን አይደለም። ይህ ድርጊት የሚያሳዬው ዘረኞቹ፣በአማራው ሕዝብ ላይ ያላቸውን መረን የለቀቀ ጥላቻና ፋሽስታዊ ተልዕኮ በመሆኑ፣ቁጣችን አይሎ፣ጥርስ እንድንነክስ ተገደናል።

በማይቀረው የሠው ልጅ መጨረሻ በሆነው ሞት በአካል ከእኛ የተለዩን ፕሮፌሰር አሥራት፣ጉልበታቸውን፣ዕውቀታቸውን፣ገንዘባቸውንና ዕምነታቸውን፣ብሎም  ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት፣ ለአገርና ለሕዝብ አንድነት ሲሉ ነበር።ዘረኛውን ወያኔን ግን በልበሙሉነትና በጀግንነት ሲታገሉ አልፈዋል።

አሪስቶትል! ሥለጀግንነት ሲናገርለታላቅነት ተግባር ራሱን ያዋለ ሠው፣የሠብዓዊ ክብር ዓርማ ነው ብሎ ነበር።

ጀግኖች ግብና ዓላማ ቀርፀው የሚራመዱ በመሆናቸው ድፍረት፣ልበሙሉነትና አይበገሬነት መለያቸው ሥለሆነ ታላቅነት ከውስጣዊ ጀግንነት ሥሜታቸው ሥለሚመነጭ ምንጊዜም ከትግሉ ግንባር በቅድሚያ የሚቆሙ የትግል ፋና ወጊዎችና ገድል ፈፃሚዎች ናቸው።መከራና ፈተና አይበግራቸውም።ድሎት አያታልላቸውም።ለህዝብ ኖረው፣ሥለሕዝብ ታግለው፥ለሕዝብ ሲሉ ሕይወታቸውን ሠጥተው ያልፋሉ።

በየዘመናቱ ያለፉ መሪዎችንና የሀይማኖት አባቶችን፣ለምሳሌ የእነአቡነ ጴጥሮስንና የእነአፄ ቴዎድሮስን ተጋድሎ ሥናጤን፣የጠላትን ቅሥም ሰብረው የኢትዮጵያዊንትን የጀግንነት ገድል አሥመዝግበው ማለፋቸውን እናስታውሳለን። አፄ ቴዎድሮስ!ለጠላት እጄን አልሰጥም ብለው በጀግንነት እንደተሰው ለማንኛችንም ገሀድ ነው።ፕሮፌሰር አሥራት! የእነዚህ ትውልዶች አደራ ተረካቢ በመሆን ለህይወታቸው ሳይሳሱ ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጠው አልፈዋል።

ኢትዮጵያ በሽዎች ለሚቆጠሩ ዘመናት የነፃነት ባለቤት ሆና የኖረችበት የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋናውና አንዱ ኢትዮጵያ የጀግኖች መሀን አለመሆኗና ጀግኖች ልጆቿ በተለያየ ቦታና ጊዜ በከፈሉት መሥዋዕትነት እንደነበር ታሪክ ይመሠክራል።የክቡር ፕሮፌሰር አሥራት የመስዋዕትነት ትግል ለዚህ በቂ መረጃ ነው።

ሥለሆነም ለአማራው ህልውና፣ለሀገር ሉዐላዊነትና ለህዝብ አንድነት ቀናኢ የሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ታሪክና ትውልድ የማይረሳው ተግባር ፈፅመው ያለፉት ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ፣ከዚህ ዓለም የተለዩበትን 18ኛ ዓመት አሥመልክቶ በታላቅ ሀዘንና ቁጭት አሥቦት እንዲውል እያስታወስን፣ይህን ዕለት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋና ድል ጋር አያይዞ የሚከበርበት ወቅት አሁን ባለው የጊዜና የሁኔታ ውስብስብነት ቢዘገይም አይቀሬ መሆኑን ሳናሰምርበት አናልፍም።

አሥራት የዘመናችን ታላቅ ሠው፣የፅናትና የልበሙሉነት፣የሀቀኝነትና የብልህነት፣የአርቆ አስተዋይነትናሚዛናዊነት ተምሳሌት በመሆን በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ልብ በህያውነት የሚታወሱ ናቸው።

ዛሬ ፕሮፌሰር አሥራት ቢያልፉም፣ዓርማውን አንግበው፣በአይበገሬነት ሞትን እየሞቱ  የሚታገሉ እንደ እንጉዳይ የፈሉና እሳት የላሱ ሚሊዮን አሥራቶች መፈጠራቸው ሊያኮራን ይገባል። የሚሊዮን አሥራቶች መፈጠር ቢያስደስተንም፣ትግሉ እሥካሁን የተናጠል  ነው።

በዚህ አጋጣሚ ላሥታውስ የምፈልገው  እነክቡር ፕሮፌሰር አሥራት መዐሕድን  ያቋቋሙት እዚያው እሳቱ ካለበት አገር ውስጥና ሕዝቡ መሀል በመሆኑ፣ወሳኝ ሚና እንደነበረው ይታወቃል።መሆንም የነበረበት ይኸው ነው። እኛም በውጭ ሀገራት የምንኖር አማራዎች፣በየምንኖርባቸው ሀገራት የመዐሕድ የድጋፍ ኮሚቴዎች  አቋቁመን፣አገር ቤት የተቋቋመውን  የእነፕሮፌሰር አሥራትን መዐሕድ፣በገንዘብና በሎቢ ድጋፍ  እንረዳ ነበር።የምንታዘዘውም ሌሎች ጉዳዮች ሲኖሩ ትብብራችንን እናሳይ ነበር።

ዛሬም ውጭ አገር ከምንኖረው የሚጠበቀው ይኸው ነውና እንወቅበት እላለሁ። መዐሕድ ጥሩ መሪም ሥላጋጠመው  በአጭር ጊዜ ውሥጥ የሕዝብ ድጋፍ አገኘ፣በወቅቱ ያራመደው የሰላም ትግል ብቻ በመሆኑ ተጠቂ ሆነ። መዐሕድ  እንደነበረው የሕዝብ ድጋፍ መሣሪያ አለመታጠቁ ነው እንጂ ቢታጠቅ ኖሮ ድሉ የራሱ ይሆን እንደነበር አልጠራጠርም።

ታዲያ ዛሬ እየገደልኩ እሞታለሁ በሚል የአማራ ተጋድሎዎች ግብ ግብ ላይ እሥከሆኑ ድረስ፣የአገርቤቱ ትግል አንድወጥ እንዲሆን  ሁላችንም እንተባበር፣እንረባረብ። ይህ አገር ቤት እንደእነፕሮፌሰር መዐሕድ ከሕዝቡ መሀል  የሚኖር ድርጅት ወሳኝ ሚና መጫወት ይችላል።እኛ  ውጭ አገር የምንገኘው ደግሞ  የሲቪክም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶች  አገር ቤት ለሚንቀሳቀሰው አንድ ኃይል የደጋፊነት  እንጅ፣ የወሳኝነት ሚና ሥለማይኖረንየገንዘብና የሎቢ ተግባራት ላይ መረባረብ ይገባናል እላለሁ።

ይህ መሠረታዊ የሆነ የትግል ሀ ሁ እንደሆነ ለማንኛችንም የተሰወረ ሥላልሆነ፣ የተናጠሉ ትግል  በአንድነቱ ትግል እንዲተካ  መልዕክቴን አሥተላልፋለሁ። ይህ ዓይነቱ  አካሄድ ብቻ ነው  ለአማራው ወገናችን ጥርጊያ መንገድ በመክፈት ፋይዳ ኖሮት ለድል የሚያበቃው።

ዛሬ ላለንበት ሁኔታ በትምህርት ሠጭነት  ያገለግል ዘንድ አንድ ነገር መጥቀስ እገደዳለሁ።ይኸውም በአንድ ወቅት “ መዐሕድን በመደገፍ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የተቋቋምነው ድርጅቶች ወደአንድነት መጥተን አንድ የአውሮፓ ቦርድ እንመሥርት” በማለት አንደኛው የድጋፍ ድርጅት የጥሪ ደብዳቤ ይልክልናል። ደብዳቤውም በጊዜው የተቋቋሙትን ድርጅቶች ይጠቅስና አንዱን ድርጅት ይዘለዋል።ይህ ደብዳቤ ለእነፕሮፌሰር አሥራት መዐሕድም ተልኳል።ይህንን ዝግጅት ለሚያዘጋጀው የድጋፍ ድርጅት ደውዬ ከመካከላችን አንዱ ድርጅት እንደተረሳ ሥጠቅስ፣ የተሰጠኝ መልስ “እሱ ኢሠፓ ነው” የሚል ነበር።ትክክል አለመሆኑን ሥላመንኩበት ሃሳቤን አቀረብኩ ግን አልሆነም።ከዚያም በቀጥታ ለፕሮፌሰር አሥራት ደውዬ “እንዲህ የሚል የጥሪ ደብዳቤ ደርሶናል”ሥላቸው።አዎን “ለእኛም ደርሶናል፣ድርጅት ተፈጥሮ ልርዳችሁ ሲለን፣ደሥ ይለናል፣የሚፈጠረው ግን ችግር ለመፍጠር ከሆነ ባይፈጠር ይሻላል”ነበር ያሉት።

በመጨረሻ! የአሥራትን ውለታ እንዴት እንከፍላለን ሥንል፣ የትግል ዓርማቸውንና የመንፈስ ጥንካሯቸውን ተላብሰን በመታገል ነው።በኢትዮጵያ ምድር የዓሥራት ዓላማ ተግባራዊ እሥከሚሆን  ድረስ ትውልድ ሁሉ ትግሉን መቀጠሉ ውለታ ከፋይነቱን የሚያረጋግጥ ይሆናል።

የሰማዕቱ የአሥራት ሥራ ህያው ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል!

ለአማራው ህልውናና ለነፃነት የሚደረገው ትግል እሥከድል ይቀጥላል!

ሞት  ለፀረ-አማራዎች

አያሌው ፈንቴ

 

 

 

የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ የህይወት ታሪክ!

                                       የአሥራት ዕድገትና ትምህርት

ፕሮፌሰር አሥራት ሰኔ 12 ቀን 1920 ዓም ከአባታቸው ከአቶ ወልደየስ አልታዬና ከእናታቸው ከወ/ሮ በሰልፍ ይዋሉ ፅጌ  በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ:: ሦስት ዓመት ሲሆናቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ድሬዳዋ ሄደው የቤተክርስቲያን ትምህርት በመከታተል በሰባት ዓመት ዕድሜያቸው ዳዊት ደግመው አጠናቀዋል::አስተማሪያቸው የነበሩት አለቃ ለማ ወልደ መስቀል እንደመሰከሩት ፕሮፌሰር አሥራት በጣም ጎበዝ ተማሪ ስለነበሩ ዓመት ሳይሞላቸው ወንጌልን ከነቁጥር ከፍካሬ እስከነቢያት በመድገማቸው  ዲቁናም ተቀብለዋል::  በዕድሜያቸው ሳይሆን በትምህርት ባሳዩት ብልጫ የተማሪዎች አለቃም ነበሩ::

ፈረንሣይ ት/ቤት ገብተው ዘመናዊውን ትምህርት ለመከታተል በመሰናዳት ላይ ሳሉ ኢጣልያ አገራችንን ሥለወረረች ትምህርታቸው ሊሰናከል በቅቷል:: የካቲት 12ቀን 1929 ዓም ኢጣልያ አዲስ አበባ ውስጥ በአካፋና በዶማ በግፍ ከጨፈጨፋቸው ብዙ ሽህ የነፃነት ሰማዕታት ኢትዮጵያውያን መካከል የፕሮፌሰር አሥራት አባት አንዱ ናቸው:: እናታቸውም በህመም ሞቱ:: አያታቸው ቀኛዝማች ፅጌ ወረደወርቅ በግዞት ወደኢጣልያ አገር ተወስደው ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ ወደአገራቸው ተመልሰው ፕሮፌሰር አሥራትን ከድሬዳዋ ወደአዲስ አበባ አመጧቸው:: ፕሮፌሰርም ለአምስት ዓመት ያህል ከቤተሰብና ከአካባቢ ከሚገኘው ትምህርት በስተቀር መደበኛ ትምህርት ለመከታተል አልቻሉም ነበር:: ኢጣልያ ከተባረረም በኋላ እስኪረጋጋ ድረስ በሚል ለዘጠኝ ወራት ያህል አልተማሩም::

 

ከዚህ በኋላ በ1934 ዓም በተፈሪ መኮነን ት/ቤት በመግባት ዘመናዊውን ትምህርት መከታተል ጀመሩ::ፕሮፌሰር አዲስ አበባ ከመጡ ጀምሮ ከአያታቸው ተለይተው አይውሉም ነበር።  አያትና የልጅ ልጅ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ተያይዘው ነበር  የሚዘዋወሩት። አሥራት ከልጅነታቸው ጀምሮ ብልህና ያስተማሯቸውን ወዲያውኑ የመቀበል የላቀ ተሰጥኦ ነበራቸው:: ጠላት እንደወጣ ራዲዮ በየአደባባዩ ተተክሎ ስለነበር አያታቸው አሥራትን ራዲዮ የተናገረውን አዳምጠው እንዲመጡ ሲልኳቸው በጥሞና አዳምጠው የሰሙትን ሁሉ ለአያታቸው ልቅም አድርገው ይነግሯቸው ነበር::

 

አያታቸው አሥራትን በፍትህ አዋቂነታቸው ያደንቋቸው ስለነበር በቤተሰብ መካከል አለመግባባትና ጥል ሲፈጠር ሁኔታውን ሰምተውና  አመዛዝነው ዳኝነት እንዲሰጡ ያዟቸው ነበር:: አያታቸውም አሥራትን በክርስትና ስማቸው ”መልአከ ብርሃን” ነበር የሚሏቸው:: ”ሀገራችን ጥበብ የሚያውቁ ልጆች ቢኖሯት እኮ ትልቅ ሀገር ነበረች….የማይናቅ ሕዝብና ባህል አላት”እያሉ የሀገር ፍቅርና የወገን አንድነትን መሠረትና ጥቅም ያስተምሯችው ነበር::ፕሮፌሰር አሥራት ስለሕግና ፍትህ ግንዛቤ ማግኘትና ጽኑ የሀገር ፍቅር ስሜት በልባቸው መንደድ የጀመረው በዚያ ጊዜ ነው::

 

በተፈሪ መኮነን ት/ቤት የዛን ጊዜው የትምህርት ደረጃ እንደዛሬው አልነበረም:: ት/ቤቱ እስከ 30 የሚደርሱ ክፍሎች ሲኖሩት ጎበዝ የሚባል ተማሪ የሚገባው አነስተኛ ክፍል ውስጥ ነበር:: 30ኛው ክፍል ማለት ዝቅተኛው  ሲሆን  1ኛ ክፍል ከፍተኛው የጎበዞች ክፍል ነበር:: በመጀመሪያ አሥራት ቀደም ብለው ንባቡንና ሌላውንም ተምረውት ስለነበር ሲፈተኑ ጥሩ ውጤት ስላገኙ 13ኛ ክፍል  ገቡ::በዚሁ ዓመት ከተማሪዎች ሁሉ ልቀው በመገኘታቸው ወደ 1ኛ ክፍል ተዛወሩ:: በ1935 ዓም ከጠቅላላው የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች አንደኛ በመውጣታችው የካሜራ ሽልማት አገኙ::

 

በዚሁ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ዕድል አግኝተው ወደግብፅ አለክሳንድሪያ ሄዱ::በቪክቶሪያ ኮሌጅም ገቡ::የሀገር ናፍቆትና የበዓላት አለመጣጣም ቢያስችግራቸውም ትምህርቱን በሚያስደንቅ ሁኔታ አጣደፉት:: መጀመሪያ ላይ ያስገቧቸው በዝቅተኛ ደረጃ በሚገኝ ክፍል ቢሆንም በመጀመሪያ ”ተርም” ባገኙት አስደናቂ ውጤት ወደ2ኛ ደረጃ ተሸጋገሩ::ጎበዝ ተማሪ በኮሌጅ የመኝታ ክፍሎች ሀላፊ ይሆን ነበርና አሥራትም ኃላፊ ሆኑ::አብረዋቸው የተማሩትን የዮርዳኖስ ንጉስ የነበሩትን ሁሴንንና ሌሎችንም ያስጠኑ ነበር::

 

አሥራት ትምህርት የመቀበል ችሎታቸው የላቀ መሆኑ የሚያስደንቅ ነበር::ቀደም ብሎ ያልተጤነውና በኋላ ላይ ጎልቶ የታየው ግን ለሃይማኖታቸው ያላቸው ጽናትና  አትንኩኝ ባይነታቸው ነው::አሥራት በሰው ሀገር ያውም በአረብ ሀገር ግብፅ ”በፆም አልበላም” በማለት የትምህርት ቤት ሀላፊዎቻቸውን ያስቸግሩ ነበር::በአንድ ወቅት ብላቴን ጌታ ሎሬንሶ ትዕዛዝ ግብፅ ሄደው ሳለ ”አሥራት በፆም አልበላም ብሎ አስቸገረ” ተብሎ ተነገራቸው::

 

ሎሬንሶ አሥራትን አቅርበው ”እኛ እንኳን እንበላ የለም አንዴ አንተም መብላት አለብህ”በማለት ምክርና ግሳፄ ቢሰጧቸው ”እርስዎ ገደል ቢገቡ እኔ ገደል እገባለሁ ወይ?” በማለት ቁርጥ ያለ መልስ ሰጥተዋቸዋል::

አሥራት በግብፅ የአምስት ዓመት ቆይታቸው ከፍተኛ የትምህርት ውጤት አግኝተዋል::እንግሊዝ ሀገር ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችለውን የሁለት ዓመት ትምህርት ያጠናቀቁት በአንድ ዓመት ብቻ ነበር::በዚሁ ውጤታቸው ወደእንግሊዝ ሀገር ሄደው ስኮትላንድ በሚገኘው ኤደንብራ(ኤደንበርግ)ዩኒቨርሲቲ ገቡ።

 

በወቅቱ ከነበሩት የትምህርት ሚኒስትራችን ሳይቀር በዩኒቨርሲቲው የህግ ትምህርት እንዲከታተሉ ቢታዘዙም አልተቀበሉትም::ልባቸው የፈቀደውና ፍላጎት ያደረባቸው የህክምና ሙያ ማወቅን ነበርና የህክምና ትምህርት ለመከታተል ወሰኑ::ህክምናን የመረጡበት ምክንያት

 

(1ኛ )የታመሙ እናታቸው ሆስፒታል ገብተው መሞታቸው፣(2ኛ)አንድ ጊዜ ከግብፅ ለዕረፍት ወደሀገራቸው መጥተው ሳሉ ታመው ሆስፒታል ገብተው ሲታከሙ ብዙ ስዎች እየሞቱ እሬሳቸው ሲወጣ ማየታቸው፣ (3ኛ) ”የፈረንጅ ጥበብ ማወቅ”የሚለው የአያታቸው ምክር በውስጣቸው ማደሩ የመሳሰሉ ነበሩ::

 

                                      

                                               አሥራትና ህክምና

 

አሥራት በኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የህክምና ተማሪና ከጠላት ወረራ በኋላ ወደውጭ ሀገር ከተላኩት ኢትዮጵያውያን መካከል 42ኛው ነበሩ::ከስድስት ዓመት በኋላም ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመረቁ::ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአንድ ዓመት ያህል በሁስፒታሉ ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተው በ1947ዓም መደበኛ ሥራቸውን በልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል ጀመሩ:: ከፋሽስት ወረራ በኋላ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሐኪም ናቸው::

 

በፋሽስት ወረራ ወቅት ጠላትን ካስጨነቁት ስመ ጥሩ አርበኞች መካከል አንዱ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁ ሥላሴ ነበሩ::ደጃዝማች ፀሐዩ ጠላት ተባሮ ነፃነት ከተመለሰ በኋላ የጤና ጥበቃ ሚኒስትርነቱ ሥራ ከነበራቸው ችሎታ ጋር እንደማይጣጣምና ለእርሳቸው እንደማይመጥን ስለተገነዘቡ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ሥራውን እስከሚረከቧቸው ድረስ ኃላፊነቱን ለፈረንጆች አሳልፎ ላለመስጠት ቀን ይጠብቁ ነበር::ጊዜው ደረሰና የተማሩ ኢትዮጵያውያን ብቅ ማለት ጀመሩ::

 

”እኛ በአርበኝነት ይህችን አገር ከኢትዮጵያ ጠላቶች ሥንጠብቃት ከረምን።አሁን የተማራችሁት ኢትዮጵያውያን ተገቢውን አመራርና ኃላፊነት ለመውሰድ ስለመጣችሁ በጣም ተደስተናል::እኔም ከፈረንጆቹ እጅ እንዳይወድቅ ስጠብቅ የነበረውን ይህንን የጤና ጥበቃ ሚኒስትርነቱን መቀመጫ ተረከብ::ለአስረካቢነት ያበቃኝን አምላክ አመሰግነዋለሁ::በጣም ደስ ብሎኛል::ይህንንም ለግርማዊ ጃንሆይ አስረዳለሁ” በማለት ደጃዝማች ፀሐዩ ለፕሮፌሰር አሥራት ነገሯችው::

ደጃዝማች ፀሐዩ ይህንን ቢሉም ሥልጣኑን እንዲረከቡ የተጠየቁት ሐኪም ፈቃደኛ አልሆኑም::ይበልጥ ለአገርና ለወገን መሥራት የሚያስችላቸው በቀጥታ በህክምናው ሞያ ተሰማርተው መገኘቱ እንደሆነ አስረዱ::ደጃዝማች ግን አረኩም::ብቻ የወንበሩ ርክክብ ሳይሆን ቀረ::ሐኪሙም በቀጥታ በሙያው ውስጥ ገቡበት::ዕውቅ ሐኪም ለመሆንም በቁ::

 

የአምስት ዓመት የሕክምና አገልግሎት ከሰጡ በኋላ እንደገና ወደ ብሪታንያ ሄደው ኤደንብራና ኢንግላንድ ውስጥ በሚገኙት ሮያል ኮሌጅ ኦፍ ሰርጀንስ በቀዶ ሕክምና ልዩ ትምህርት ተከታትለው አጠናቀቁ::ይህን ለመከታተል ቀደም ብለው መሄድ ነበረባቸው::ይህን አስመልክተው በአንድ ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላችው ጥያቄ  ሲመልሱ ”አያቴ ያማችው ነበርና እኔ በሌለሁበት የሞቱ እንደሆን እፀፀታለሁ ብዬ ዘገየሁ:: ደህና እየሆኑ ሳያችው ግን ሄድሁ:፡  ብቻ እድለኛ አልነበርኩም ሞቱ! ሳልቀብራቸው ቀረሁ”በማለት በቁጭትና በፀፀት መልሰዋል::

 

አሥራት ከፍተኛ የቤተሰብ ፍቅር አላቸው::ይህ ፍቅር ጠንካራ የወገን መውደድን ትቶላቸው አልፏል:: በልዕልት ፀሐይና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች በሰርጀንና በዋና ሰርጀንነት/የቀዶ ጥገና ሐኪምነት/ ከሰላሳ ዓመታት በላይ ሕመምተኞችን በቅንነትና ባለመታከት አገልግለዋል::

በአገራችን የህክምና አገልግሎቶችና ልዩ ልዩ ጥናቶች ውስጥ በሃላፊነት ደረጃ ከመካፈላቸውም በላይ በቀድሞው “የኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ” የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ የሕክምና ፋካልቲ ዲንም ነበሩ::

የሕክምና ዳይሬክተር በነበሩበት ጊዜ የልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል ተስፋፍቶና ተጠናክሮ እንዲገኝ በብርቱ ጥረዋል:: በኢትዮጵያ እራሳቸው ያልተሳተፉበት ዋና ዋና የህክምና ፖሊሲ  አወጣጥና አገልግሎት አልነበረም ብሎ መናገር ይቻላል::

 

ፕሮፌሰር አስራት ባሳለፉት ሠላሳ ዓመታት   የህክምና ዘመን  ውስጥ የአያሌ ሕሙማንን ሕይወት ስለማትረፋቸውና ለሙያቸው ከፍተኛ ፅናት ያላቸው ስለመሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ:: በቀን እስከ አስራ ስምንት ሰዓት ድረስ የሰሩባቸው ጊዜያት በርካታ ናቸው:: በተለይም ልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል በነበሩበት ወቅት መኖሪያቸው በቅጥር ግቢ ውስጥ ስለነበር የጠናበት በሽተኛ ከመጣ እርሳቸው መጠራታቸው የግድ ነበር:: የተረኝነት ጉዳይ የለም::

 

                                        ስለሞያቸው ምሥክርነት

 

-በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎቸ የራሳቸው ምስክርነት አላቸው። በወቅቱ ለረጅም ዓመታት ፀሐፊያቸው የነበሩ እንዲህ ይላሉ። ”ከእርሳቸው ጋር በፀሐፊነት ለረጅም ጊዜ ሠርቻለሁ።ሌት ተቀን ይሠራሉ።የሕክምናውንም የአስተዳደሩንም ሥራ ይሠራሉ። የምሳና የቁርስ ጊዜ ማክበር  የሚባል ነገር የለም።የእርሳቸውን ሁኔታ እያየሁ የምሳ ሰዓቴን ለመሠዋት ተገድጃለሁ። በታካሚዎቻቸውም ሆነ በሥራ ባልደረቦቻቸውም ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ አላቸው።ከሁሉ የሚደንቀኝ ደክሞኛል ማለትን ያለማውቃቸው ነው።”

 

-በልዕልት ፀሐይና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎቸ ሰላሳ ዓመታት ያገለገሉት ሲስተር አልማዝ ለማ  ፕሮፌሰር አሥራትን የሚያውቋቸው ከነርስነት ሙያ ተማሪነታቸው ጊዜ ጀምሮ ነው። ”ፕሮፌሰር አሥራት ለሕመምተኞቻቸው ታላቅ አክብሮት አላቸው። ሰው አይመርጡም ።በሥራው ዓለም ከወጣትነት ጀምሮ እስከተለየኋቸው ጊዜ የማይሰለቹና የማይደክሙ ባለሙያ ሆነው ነው ያገኘኋቸው።ከባድ የልብ ኦፕራሲዮን ካደረጉም ወዲህ አልተለወጡም።ሌት ተቀን የሚሠሩባቸው ጊዜያት በርካታ ናቸው። በጣም እናከብራቸዋለን።ለሙያቸው ከፍተኛ ፍቅር ስላላቸው እኛንም አርዓያነታቸውን ለመከተል አስቸለውናል።

 

በሽተኞችም በእርሳቸው ላይ ያላቸው እምነት በጣም የላቀ ነው።ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ከአርባ ምንጭ የመጡ አንድ ታካሚ አዛውንት <አሥራት የሚባል ጠበል ፈልቋል ስላሉኝ ነው ወደዚህ የመጣሁት> ያሏቸውን አስታውሳለሁ።በርሳቸው ላይ ያላቸውን አመኔታና ከበሬታ ለመግለፅ ያሉት እንደሆነም እረዳለሁ፧ የቀዶ ሕክምናውን ጥበብ ከመካናቸውና መሥራት ከመጀመራቸው በፊት ሁለገብ ሐኪም ነበሩ።ያዋልዱም ነበር።”ይላሉ ሲስተሯ።

 

-ዶክተር ሥዩም ዮሴፍ ፕሮፌሰር አሥራትን ከሃያ ስድስት ዓመታት ጀምሮ ያውቋቸዋል።የፕሮፌሰር አሥራት የሕክምና ተማሪም ነበሩ። ”ፕሮፌሰር አሥራት አስተማሪዬ ነበር።እንከን የማይወጣለት አስተማሪ ነው።ተማሪው ማግኘት ያለበትን እውቀት አግኝቷል ብሎ ካላመነ ከክፍሉ ንቅነቅ አይልም።ለሙያው ከፍተኛ ፍቅርና አክብሮት አለው።ሕይወቱን በሙሉ ለዚህ ተግባር ያዋለ ነው።ሕመምተኛም ሲሰቃይ ይሰቃይል፡ ሲታመም ይታመማል። ሰብዓዊነትን የተላበሰ ነው።

የተጣራ ሥራ ነው የሚሠራው።ሱፐር ሰርጀን ነው።አስፈላጊውን የቅድሚያ ምርመራ ሳያካሂድ ቀዶ ሕክምና አያደርግም።ከቀደደ በኋላም ደህና ነው ብሎ በሽተኛውን አይተውም። በተለይ ሰባ ሁለት ሰዓት እስኪሞላ በቀን አራት ጊዜ ያህል ተመላልሶ ይጠይቃል።ከዚያ በኋላም የበዓላት ቀን ሳይመርጥ ይጠይቃል።

በሽተኛን በጎሳው በሃይማኖቱ ወዘተ አይመርጥም።ለሰው ሕይወት ከፍተኛ ዋጋ ይሰጣል ። በበሽተኞቹም ሆነ በሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ አክብሮትና አድናቆትን የተቸረና የተወደደም ነው።ላመነበት ነገር ከቶውንም ወደኋላ አይልም፧በብዙዎች ባለሙያዎች ዘንድ እንደ አባትና አስተማሪ የተከበረና የታፈረም ነው። እርሱ አይናገረው እንጂ ችግረኞችን በገንዘብ ጭምር ይረዳል።” ብለዋል ዶክተር ሥዩም።

 

-አንድ የ18 ዓመት ዕድሜ ያለው የግሪክ ወጣት ለሽርሽር ናዝሬት ሄዶ በድንገት በጥይት ይመታል።አዲስ አበባ መጥቶ አሥራት የቀዶ ጥገና ያደርጉለታል።ቀዶ ሕክምናውን ያደረጉት እርሳቸው በመሆናቸው በከተማው ያሉት የግሪክ ኮሙኒቲ አባላት ተደናግጠዋል።

በሦሥተኛው ቀን ዶክተር አሥራት ለኮንፈረንስ ውጭ አገር መሄድ ስለነበረባቸው የልጁን ሁኔታ ለቀሩት ሐኪሞች አደራ ብለው ሄዱ።ይህንን አጋጣሚ ያገኙ የግሪክ ኮሙኒቲ አባላት ከግሪክ አገር ግሪካዊ ፕሮፌስር እንዲመጣ የጃንሆይን ፈቃድ ይጠይቃሉ።ተፈቀደላቸውና ግሪካዊው የሕክምና ፕሮፌሰር መጥተው የልጁን ሁኔታ መርምረው ከተገነዘቡ በኋላ ለሐኪም ቤቱና ለጃንሆይ ”ከመገረምና ከመደነቅ በቀር የምጨምረው ነገር የለም።እዚህ አገር እንዲህ ያለ ነገር ከተሠራ እኔ ለምን ተጠራሁ? ” ብለው ወደአገራቸው ተመለሱ።

 

-በፕሮፌሰር አሥራት ድንቅ ችሎታ የተደነቁት ግሪኮች ብቻ አልነበሩም እንግሊዞችም ተደንቀዋል አድናቆታቸውንም በፅሁፍ ገልፀዋል።እንግሊዛዊቷ ወይዘሮ ማግደሊን ዋይን ወደኢትዮጵያ መጥተው በአደጋ ምክንያት ከሞት አፋፍ ላይ ይደርሳሉ። ፕሮፌሰር አሥራት ቀዶ ሕክምና አድርገው ሁለት ቀን አውለው ካሳደሯቸው በኋላ ሴትዮዋ ለንደን ደርሰው ሕክምና ላይ እንዳሉ ሞቱ ።

ይሁንና ፈረንጆቹ የሴትዮዋ ነፍስ እስከዚያ ቀንም ድረስ መሰንበቱ በአሥራት ችሎታ መሆኑን ተገንዝበው ፕሮፌሰርን አደነቋቸው።ይኸውም ይታወቅ ዘንድ የብሪታኒያ አምባሳደር ከፃፉት ሌላ የብሪታኒያ ቆንሲል የፃፈው ትርጉም እነሆ ”ተወዳጁ አሥራት  በቅድሚያ የኒክ ታይለር እህት በደረሰባቸው አሰቃቂ አደጋ ወቅት ላሳዩት ደግነትና ወደር ለማይገኝለት ችሎታዎ ጥልቅ ምስጋናዬን በብሪታኒያ ቆንስል ስም አቀርባለሁ።መጨረሻው ጥሩ እንደማይሆን ብገምትም ከአደጋው በኋላ በትንሹ ሕይወታቸውን ሁለት ጊዜ እንዳቆዩላቸው ተረድቻለሁ።

የፈፀሙት የላቀ ተግባር ሁሉ ከፍተኛ አድናቆት አሳድሮብኛል።በሙያዎ ለፈፀሙት ምግባር አስፈላጊ ሲሆን የሚያስፈልግዎን እንዲገልጹልኝ በክብሮት አስታውቃለሁ።በአሁኑ ጊዜ ገንዘብ ምንም አይደለም። ከዚህስ ይልቅ ለእኛ ትልቁና አስፈላጊያችን ደግነትዎ ችሎታዎና የችግራችን ተካፋይነትዎ ነው። እንደገና አመሰግነዎታለሁ።”

 

-“ዕውቁ የቀዶ ሕክምና ሀኪም ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ካሉበት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንድገባ ተወሰነና ረቡዕ ቀን ተኛሁ። ባለቤቴ በሦሥት ቀኔ መጣች፡፤…..ኢትዮጵያዊ ያገቡ እንግሊዛዊ ሌት ተቀን ይንከባከቡኝ ነበር።…ሦስት የብሪታንያውያን ኮሚዩኒቲ አባሎችም ደም ሰጡ።ይህ ሁሉ እንክብካቤ ግን ትርፍ አንጀቴን መንጥቀው ከገላገሉኝ ካለ ተደናቂው ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ምንም አልነበረም።” ጆናታን ቴሌ(ዘጋርዲያን ጋዜጣ)

 

-“35ዓመት ሙሉ ባደረጉልኝ ጥረት ይኸው የቀረው አንድ እግሬ በእሳቸው ኃይል ቆይቶልኛል።አሁን ልጆቼን የማሳድገውና የምኖረው በዓሥራት ነው።በዕውነት ልዩ ሠው ናቸው።ሰው አክባሪና ደግ ፍጡር ናቸው።ዕድሜ ለአሥራት። የሚገርመኝ የሁሉንም ሥራ ይሠራሉ።ግን አይደክሙም።” አቶ ሀብታሙ በቀለ

 

-”..10ዓመት ሙሉ ስታመም ዘጠን ጊዜ ኦፕራሲዮን አድርገውኛል። እንደሳቸው ሕሙማኑን እጅግ የሚወድ ለሰው ነፍስ አጥብቆ የሚጨነቅ አላየሁም።..”  አቶ አጥናፉ ተሰማ

 

እኚህ በችሎታቸው የሚተማመኑ የሕክምና ባለሙያ በሳል ትሁትና ቆፍጣናም ናቸው።አንደበታቸው ቁጥብ ግን አሳማኝ ነው።የሚያወጧቸው ሃሳቦች ደርዝ አላቸው። ከነጥቡ ውጭ አይዘልም። የማስታዎስ ችሎታቸውም የዋዛ አይደለም።ወደኋላ ተመልሰው ቀንና ዓመተ ምህረት ጠቅሰው ድረጊቱን መዘርዘር ይቻላቸዋል። ነገር ፈጥኖ ይገባቸዋል። በአሁኑ ጊዜ የተላበሱት አረጋዊ ስብዕናቸው አክብሮት እንዲቸራቸው አድርጓቸዋል።በንግግራቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ኃያልነት ባግባቡ ሳያነሱ አያልፉም።ስለሥራቸውም አድናቆት ሲሰጣቸው ”ብቻየን አላደረግሁትም ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር እንጂ ” ማለትን ይደጋግማሉ።

 

በ1972ዓ.ም.ደርግ ፕሮፌሰር አሥራትን በዘመቻ ሥም ወደምፅዋ ልኳቸዋል።ውስጥ አዋቂዎች ዛሬ እንደሚናገሩት በወቅቱ የተላኩት ”አድሀሪ” በሚል ሰበብ እንዲገደሉ ሁኔታዎች ለማመቻቸት ነው ይላሉ።ፕሮፌሰር ሞትን አዝለው በዘመቻው ላይ በትጋትና በጥንካሬ ተካፍለዋል።የዘመቱት ለማከም እንጅ ለመዋጋት አይደለም።አዎ በውቅቱ ያከሙት የኢትዮጵያን ወታደር ብቻ አልነበረም።የሻዕቢያን ወዶገብና ምርኮኞች ጭምር ነበር።

 

በወቅቱ  ዘርና ጎሳ ሃይማኖትና እምነት ሳይለዩ የፖለቲካ ወገናዊነት ሳያሳዩ የኢትዮጵያን ልጆች ሁሉ እኩል አክመዋል።ፕሮፌሰር አሥራት ሕይወት ለማትረፍና ከሥቃይ ለማዳን የማያደርጉት የለም።ለበሽተኞቻቸው ያላቸው ፍቅርና የሚያደርጉት እንክብካቤ እጅግ ከፍተኛ ነው።

 

አብረዋቸው ከሚሰሩት የሥራ ባልደረቦቻቸው ይልቅ ለበሽተኞቻቸው ያደላሉ።በሥራ ዋዛ ፈዛዛ የለም።ትንሽ ጥፋት ከተሰራ ይቆጣሉ።በሕይወት ቧልት አይውቁም። ማንም ይሁን ማን ትክክል ያልሠራ ከመሰላቸው መናገራቸው አይቀርም።ፈረንጅ ይሁን አበሻ ዶክተር ይሁን ነርስ በሥራ ይሉኝታ የላቸውም።

ስህተት አይተው ስለማያልፉ የምትፈራቸው አንዲት ነርስ ጧት የለበሰችውን ከሰዓት በኋላ ለውጣ  ትመጣለች።ታዲያ ጓደኞቿ ”ጧት ሌላ ለብሰሽ አሁን ይኸን ምን አስለወጠሽ?”ይሏታል።”አሁን ከዶክተር አሥራት ጋር ነው የምሠራው”ትላለች። ”ታዲያ ቢሆንስ ”ይሏታል። ”የጧቱ ጠበብ ያለ ነበር አሁን ይህን ሠፊ ልብስ የለበስኩት ዶክተር ሲቆጡኝ ስለሚያልበኝ እንዳይጣበቅብኝ ብዬ ነው” በማለት ተናግራለች።

በሽተኞቻቸው ዘንድ ሁል ጊዜ ሳቂታና ፊታቸው እንደበራ ነው። ”በሽተኛ አይጉደልበት ፣በሽተኛ አይከፋ ፣የተቻለው ሁሉ ይሟላለት ” ነው የሚሉት።በሽተኞች የአሥራትን ሕክምና ብቻ ሳይሆን የእጅ ዳበሳቸውንም ጭምር ይወዱታል።የሥራ ባልደረቦቻቸው ”የበሽተኛ ጠበቃ ”ይሏቸዋል።

 

                                           ሥራት በፖለቲካ ውስጥ

በ1983ዓ.ም.የደርግ መንግሥት ወድቆ ኢሕአዴግ ሲተካ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋካልቲ ዲን ነበሩ።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በመረጧቸው መሠረት በሰኔ 1983ቱ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዋል። በኮንፈረንሱ ላይ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል የሚፈቅደውንና”መገንጠል” የኢትዮጵያ የወደፊት መተዳደሪያ እንዲሆን የሚያረጋግጡትን አንቀጾች የተቃወሙ ብቸኛ የጉባዔ ተሳታፊ ነበሩ።በተለይ ስለኢትዮጵያና ስለኤርትራ ታሪክ የተሰጠውን ትንተና የማይቀበሉት መሆኑን ገልፀዋል።

”ይህ ጉባዔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ምንም ጉዳይ ሊወስን ሊያግድ ወይም ሊሰርዝ አይችልም። ሆኖም የኢትዮጵያን የአሁኑን ተጨባጭ ሁኔታ በመመርኮዝ የወንድማማቾች ደም መፋሰስ የቆመ በመሆኑ አሁን የሰፈነውን የሰላምና የዲሞክራሲያዊ ሂደት መሠረት በማድረግ፡ የኢሕአዴግና የሕዝባዊ ግምባር ሀርነት ኤርትራን ልዩ ግንኙነት በመጠቀም ወንድማማችና እህትማማች በሆኑት ሕዝቦች መካከል የዘለቄታ ቅራኔ እንዲወገድና በኢትዮጵያዊነትና በይቅር ለእግዚአብሔር መሠረት በአስቸኳይ የሚስማሙበትን  መንገድ መፈለግ ለመሸጋገሪያ መንግሥት ተቀዳሚ ተግባር እንዲሆን ጉባዔው እንዲያሳስብ ይህን ሀሳብ በአክብሮት አቀርባለሁ ” ነበር ያሉት።

ከዚህ ኮንፈረንስ በኋላም የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን በመወከል በተቋቋመው የሽግግር መንግስት በተወካዮች ምክር ቤት አባልነት እንዲሰሩ ተደጋጋሚ ጥሪ ተደርጎላቸው አልተቀበሉትም።የኤርትራን መገንጠል በግልጽ መቃወማቸውና ተቋቋመ በተባለው የተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ላለመሳተፍ የወሰዱት ቁርጠኛ አቋም በወያኔና ሻዕቢያ ጥርስ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ!  የአገር መፍረስ የአንድነት መናጋት የታሪካችን መደለዝ አንገበገባቸው።በተለይ ዐማራው ዐማራ ሆኖ በመፈጠሩ ብቻ በያለበት በግፍ መገደሉ መዘረፍ መታሰሩ መሰደዱ ሊሸከሙት የማይችሉት ስቃይ ሆነባቸው።ይህን አገር የማፍረስ ኢትዮጵያውያንን በዘር በጎሳና በጎጥ እየለዩ እርስ በርስ የማጫረስ አፍራሽ ፖሊሲ በሰላማዊ ሁኔታ ለመታገል የመደራጀትን አስፈላጊነት አመኑበት።

ሥለዚህም ቆርጠው ከተነሱ ወንድሞቻቸው ጋር በመመካከር መዐሕድን አቋቋሙ።በፕሬዚዳንትነትም መሩት። መዐሕድና ፕሮፌሰር አሥራት ታሪካዊ አንድነታችን ይከበር፡ ዐማራውን አትግደሉት አትረዱት አታንገላቱት ሰበዓዊ መብቱን አትንፈጉት በማለት ተከራከሩ። ለመንግስት አካላት፣ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፣ለዓለም ሥላም ወዳድና ሰባዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ሁሉ አቤት አሉ። ”ዴሞክራሲያዊ ነኝ ”ባዩን ወያኔን  እርቃኑን አስቀሩት።

ኢሕአዴግ የመዐሕድንና የፕሮፌሰር አሥራትን እርምጃ አልወደደም። ገና ከጅምሩ ”ነፍጠኞች፣ ትምክህተኞች፣ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎች ” ወዘተ …እያለ ማውገዝ ጀመረ።መዐሕድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍ ያለ ሕዝባዊ ተቀባይነትን አገኘ። የኢሕአዴግ ጥላቻና ጥቃትም አደገ። በተለይ ከ1985ዓ.ም.ጥር ወር ጀምሮ ግልጽ ጥቃት ሠነዘረ።አባላትና መሪዎችን መግደል  ማቁሰል ማፈን ማሰርና ማስፈራራቱን በመንግሥት የመገናኛ ብዙሀን  በሠፊው በሚሰራጭ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አስደግፎ አጧጧፈ። አሥራትም የዚህ ጥቃት ኢላማ ሆኑ። ከጥር 1985ዓ.ም. ጀምሮ በፀጥታ ኃይሎች ሥውር ክትትል ይደረግባችው ጀመር። በሁለትና በሦሥት መኪናዎች ዙሪያቸውን እየተከበቡ ግራ እንዲጋቡ እንዲጨነቁና እንዲፈሩ ለማድረግ ተሞከረ።ሰበብ ተፈልጎ ክስ ተመሠረተ ።ከሕግና ከሥርዐት  ራሳቸውን ያራቁ ለመምሰልም በመንግስት መገናኛ ብዙሀን ሳይቀር ”ካሉበት ለሕግ እንዲቀርቡ ”የሚል ጥሪም ተላለፈ።

ታህሣሥ 11ቀን 1985ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ከተማ በተደረገው ሕጋዊ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ”የጦርነት ቅስቀሳ ”ተባለና ፕሮፌሰር አሥራት በፖሊስ ታሰሩ።በ50ሽህ ብር ዋስትና ተለቀቁ።

ከጎጃም ከመጡ ገበሬዎች ጋር በመዐሕድ ጽህፈት ቤት በመሰብሰብ የአድማ ወንጀል ፈፀሙ የሚል ሌላ ክስ ተመሥርቶ ጉዳዩን የቀጨኔ አውራጃ ፍርድ ቤት በቀዳሚ ምርመራ ማየት ጀመረ ።

ከሐምሌ 12 ቀን 1985 ዓ.ም. ጀምሮ የዋስትና መብት ተነፍጓቸው በእስር እንዲቆዩ ተወሰነ።ጉዳዩ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ቀርቦ ከ 43 ቀናት እሥር በኋላ በ 30ሽህ ብር ዋስትና ተለቀቁ። ይህ ክስ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ መደበኛ ክርክር ሲደረግበት ከቆየ በኋላ ከሰኔ 20ቀን 1986 ዓ.ም. ጀምሮ በሁለት ዓመት እሥራት እንዲቀጡ ተወስኖ ወደ ወህኒ ወረዱ። በደብረብርሃኑ ንግግር ክስ ከውህኒ ቤት ወደ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ ከቆዩ በኋላ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ታህሣሥ 18 ቀን 1987ዓ.ም. የሦሥት ዓመት እሥራት ተፈረደባቸው።

መስከረም 10 ቀን 1987ዓ.ም. በዋለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ በመገኘት የሁለት ወራት ናፍቆቱን ለመወጣትና የእንኳን (የ67ኛ የልደት በዓላቸው)  አደረሰዎ የመልካም ምኞት መግለጫ ስሜቱን ለማስተላለፍ በፍትህ አደባባይ በተገኘው ደጋፊያቸውና ወዳጅ ዘመዳቸው ላይ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎቸ የፈፀሙት ድብደባ እንግልትና እሥራት የፕሮፌሰርን ህሊና ስላቆሰለው ”ጠበቃ አያስፈልገኝም።ምንም ክርክር ሳያስፈልግ ቅጣቱ ይሰጠኝ። ” በማለት ለፍርድ ቤቱ በማመልከታቸው ችሎት ተዳፍሯል በሚል 6ወራት እሥራት ተፈረደባቸው።ይሁንና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቀርቦ ወደ አሥር ቀናት ዝቅ ብሏል።

ሰኔ የፕሮፌሰር አሥራት የልደት ወር ነው። ለወህኒ የበቁትም በዚሁ በሰኔ ወር ነው። 67ኛ የልደት በዓላቸው ሰኔ 11ቀን ሲሆን፧ የእስር ቀናቸው ደግሞ ሰኔ 20 ቀን ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ”በጎጃም በጎንደር በሰሜን ሸዋ የተደራጁ የወንበዴ ቡድኖች አሰማርታችኋል።”በሚል ከሌሎች ተከሳሾች ጋር አራተኛ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ፕሮፌሰር እስካሁን ድረስ ከ100 ጊዜ በላይ በፍርድ ቤት ቀጠሮ ተመላልሰዋል።ስድብ ማስፈራራት ማሳደድና ማሰር የፕሮፌሰር አሥራትን ቁርጠኝነትና ሕዝባዊ ወገናዊነት የበለጠ አጠናከሩት እንጂ አላዳከሙትም።

ፕሮፌሰር አሥራት ሰውን በሰውነቱ ይወዱታል።የችግሩና የመከራው ተካፋይ ናቸው።እንደቁጡነታቸውና አትንኩኝ ባይነታቸው አይደሉም።የሰው ችግርና ብሶት በቀላሉ ነው የሚገባቸው። ሰውን ለሥልጣኑ ወይም ለገንዘቡ ሲሉ የተለየ አክብሮትና እንክብካቤ አያደርጉም።ሀብታምና ሥልጣን አላቸው ከሚባሉት ይልቅ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ያከብራሉ።

አሥራት ተንኮልና ልታይ ልታይ ባይነት የለባቸውም።ውሸትና ውሸታምን አጥብቀው ይጠላሉ።አንድ ሰው ሲዋሽ ከያዙት እንደሰው አይቆጥሩትም።ማንኛውንም ነገር በእርግጠንነት ማወቅ ይፈልጋሉ።”መስሎኝ ነው ” የሚል መልስ የሚሰጣቸውን አይወዱም።በተፈለገው መንገድ ቢነገራቸው የሚያሳምናቸው ሆኖ ካላገኙት አይቀበሉትም።

ሥለምግብ ብዙ አይጨነቁም። ለዛውም ቢሆን የአገራቸውን ምግቦች ይመርጣሉ። የኢትዮጵያን የባህል ሥርዓት ጠንቅቀው እንደማወቃቸው ዋና የሥርዓቱ ተከራካሪና ተከታይም ናቸው።የሚወደድ የአነጋገር ስልት አላቸው።ማንም ከእርሳቸው ጋር ቢነጋገር ዓይኑን ለመስበር እስኪያቅተው ድረስ ይመስጣል።

በንግግራቸው ውስጥ እንግሊዝኛ ደባልቀው መናገር አይወዱም።የሙያ ቃል እንኳን ሲገጥማቸው ግልፅና አጭር የአማርኛ ቃል ይፈልጉለታል። ከሙያቸው ውጭ በንባብ ያዳበሩት ሰፊ ግንዛቤ አላቸው።

ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ!  (1ኛ) የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የፈረሰኛ ደረጃ፣  (2ኛ) የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን የፈረሰኛ ደረጃ፣  (3ኛ) የአብዮታዊ ዘመቻ ዓርማ፣  (4ኛ) ዓለም አቀፍ የወርቅ ሜርኩሪ / በግል አስተዋጽኦ/    (5ኛ)  የቀይ ባህር ኒሻን አንደኛ ደረጃ  ተሸልመዋል።

እድሜያቸውን ለሕዝብ አገልግሎት የሰጡት ምሁር አሁንም አገርና ሕዝብን ለመታደግ፡ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።ላደረጉት አስተዋጽኦ ግን የተሸለሙት እሥር ነው።እሥራቱ ከሚወዱት ሕዝብ የለያቸው በአካል ብቻ ነው። እሳቸውም ”በወህኒ ቤት አጥር ተከልዬ አካላዊ የመንቀሳቀስ ነፃንቴ ቢታገድም ምንጊዜም ቢሆን ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ነፃነት ያለኝ ሃሳብና ጭንቀት ሊታሰር አይችልም”ብለዋል።

በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚገኙ አባላትና ደጋፊዎች ለሰላምና ዲሞክራሲ ለሰብዓዊ መብት መከበር የቆሙ ወገኖች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።በዓለም ዙሪያ ለምሳሌ በአሜሪካ በአውሮፓ ወዘተ… በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።ምስላቸውን ያዘሉ ካኔትራዎች ፖስት ካርዶች መለዮዎች ማስታወሻ ደብተሮችና አጀንዳዎች በዓለም ዙሪያ ተሰራጭተዋል።አሥራት ይፈቱልን የሚሉ መዝሙሮች ተዘምረዋል። አሥራት ግን አልተፈቱም። በክስ ላይ ክስ ነው የተከተላቸው።

በፍርድ ቤቱ የቀጠሮ ቀን አሥራትን ያሉ ሁሉ በፖሊስ ተደብድበዋል፧ታስረዋል፧በዝናብ በፀሐይና ብርድ ተሰቃይተዋል። ”አሥራት የቁርጥ ቀን ልጅ የቁርጥ ቀን መሪ ” ”ማንዴላ ” ”ጋንዲ” እያለ መፈክር አሰምቷል። በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የአንድነት ደጋፊዎች ሁሉ ከጎናቸው ቆመዋል።

የውጭ አገር ሰዎችም ባሉበት ሆነው ፕሮፌሰር አሥራት እንዲፈቱ ጥረዋል።የ1987 ዓ.ም. የገና በዓልን አስመልክቶ ከአሥራ ሁለት ሽህ በላይ የእንኳን አደረሰዎትና የይበርቱ ፖስት ካርዶች በወህኒ ቤት አድራሻ ልከውላቸዋል።

በአሜሪካ አገር በየዓመቱ በሚዘጋጀው የኢትዮጵያውያን የባህልና የስፖርት በዓል በተቀዳሚ የክብር እንግድነት በተከታታይ ለሁለት ዓመት ተጋብዘዋል።

 

እንደሚታወቀው ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት  በፈጠራ ክሶች  ተከሰው ከእሥር ቤት ወደፍርድ ቤት፣ከፍርድ ቤት ወደእሥር ቤት እየተመላለሱ ባሉበት ወቅት በደረሰባቸው እንግልትና የትግሬ ዘረኞች አረመኔያዊ  ተግባር  ህመምተኛ ሆኑ። በበሽታው ሲሰቃዩ ከቆዩ በኋላ፣ለይስሙላ ህክምና ይሰጣቸዋል እየተባለ በሀኪም ቤት ምልልስ ብቻ ከፍተኛ መጉላላትና የሞራል ጥቃት እንዲደርስባቸው ከመደረጉም ባሻገር ህመሙም ቀስ በቀስ እየጎዳቸው እንዲሄድ ሆን ተብሎ ተሠራበት።

ዘረኛው የትግሬዎች አገዛዝ! ክቡር ፕሮፌሰር አሥራትን እንደማይድኑ (ቀድሞ እንደገደላቸው)ካረጋገጠ በኋላ የሚመጣውን የሕዝብንና የዓለምን የተቃውሞ ገፅታ ለማርገብና ሠብዓዊ መሥሎ ለመታዬት፣በወቅቱ እንዳይታከሙ ተደርጎ በሞት አፋፍ ላይ ከደረሱ በኋላ ወደውጭ አገር ለከፍተኛ ህክምና ተላኩ ተብሎ ተነገረ።ይህም ለፖለቲካ ጠቀሜታ ሲባል የተደረገ እንጅ እንዲድኑ አልነበረም።

ክቡር ፕሮፌሰር አሥራትም በማይቀረው የሠው ልጅ መጨረሻ በሆነው ሞት ግንቦት 6ቀን 1991ዓም(እአአ ሜይ 14ቀን 1999ዓም) በፔንሲልቫንያ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ፊላደልፊያ አሜሪካ አገር በህክምና ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም ተለዩን።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣በተለይ ደግሞ የዐማራው ሕዝብ ይህን ዕለት በየዓመቱ አሥቦት የሚውለው በታላቅ ሀዘንና ቁጭት ነው።

                               ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ከተናገሯቸው አንዳንዶቹን ለላሙና !

ፕሮፌሰር! መዐሕድ የተመሠረተበትን 2ኛ ዓመትና የወጣቶችን ምክር ቤት ምሥረታ ምክንያት በማድረግ  ከአደረጉት ንግግር እና በሌሎች ጊዜያት ከተናገሯቸው የተወሰዱ አንዳንድ ትውሥታዎች፣

-”በእንደዚህ ያለ አሥጨናቂ የሆነ የመከራ ጊዜና ወቅት፣ራሱን ደፍቶ፣ያልከፋው መስሎ፣ሆደ ሠፊ በመሆን የተጣለበትን መከራ ሁሉ ሳይቸኩል ችሎ፣ፈጣሪውን ለምህረት እየተማፀነ፣ራሱንም ሳያጋልጥ ለመፍትሔ በሥልት የእሚሠናዳ ታላቅ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው።” “ኤሕአዴግ በገባበት ጊዜ የፖሊስ ሠራዊት በመበተኑ ያለ ፖሊስ፣ፍርድ ቤት በመበተኑ ያለ ፍርድ ቤቶች፣ለአንድ ዓመት ተኩል በእሚያሥገርም ፀጥታ እራሱን ጠብቆ በመኖሩ፣መንግሥት ነኝ ባይ የ እማያሥፈልገው ጨዋ ሕዝብ መሆኑን አሥመስክሯል።”

-”ዛሬ ታላቁ የዐማራው ጠላት ዐማራው ነው።አንዳንድ የደላውና  ዐወቅሁ ባዩ፣የዐማራ ድርጅት በመቋቋሙ አልሥማማምእያለ ሲዋልል፣ሌላው ደግሞ በጠቋሚነት፣በአሳባቂነት፣በአድርባይነት፣በገዳይነት የገዛ ወንድሙን ለዕለት ሆዱ ፍላጎት ሲልከፍተኛ በደል እያደረሰ ነው።እሥካሁን ድረስ የተሠራው ተሠርቷል።ከእንግዲህ ወዲህ ግን እንደነኚህ ያሉትን፣ጠላትነታቸውንእንዲያውቁ ማድረግና ይሉኝታም ስፍራ የሌለው መሆኑን በጥብቅ ልናሳስብ እንወዳለን።በሌላ በኩል ሌላው የዐማራ ክፍልተኮላሽቶና ተኝቶ በማንቀላፋት ላይ ይገኛል።ይህ ክፍል ቢቃጠልም እንኳ ሊሠማው ስላልቻለና አልነቃም ብሎ ስለቀረ፣ያለውዕድል እንደሚባለውዐማራው ሲተኛ የሚበላው ጅብ ነው።””

-”አንዳንዶቻችንም በተመቻቹ መቀመጫና አልጋ ላይ እየተንፈላሰስን፣እንደተለመደው የጭራ ፀጉር መሰንጠቅና በዳመና ላይ ፎቅ በመሥራት ጊዜያችንን ሥናሳልፍ፣ ”አህያ ወይም ሀድጊ”በመባል መሳለቂያነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣የዋህነትም ጭምር ብቻ ሳይሆን በሃገርና በወገን ላይ ከፍተኛ በደል ማድረስ መሆኑን ተደጋግሞ የተመሠከረለት ነው።”

-”የተማርንና ለመማራችን የምሥክር ወረቀት የያዝን ሥለሆነ ባለሙሉ መብት ነን የማለት ዘመኑ አልፎ  ከአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ጋር አክትሟል።ዛሬ ሥራችን  አቋማችንና ሃሳባችን በሁላችንም ላይ የእሚጠራ ምሥክር መሆኑን እንገንዘብ።ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቃተ ሕሊና የላቀ በመሆኑ፣ምንም በአፈሙዝ ልጓም ምክንያት ግፊቱ ባይሰማንም ወደፊት የእሚጠይቁንና የእሚፋረዱን ብዙ መሆናቸውን ከአሁኑ መገንዘብና ለወገን ተገቢውን አስተዋፅዖ ማድረግ ብልህነት ነው።”

-”የታሪክ አጋጣሚ ሆነና በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያኖች በጎሣ፣በዘር፣በሃይማኖትና በቋንቋ በመለያየት ተከባብሮና አንድ ሆኖ የኖረው ሕዝብ ያለፍላጎቱ አንድነቱ እንዲናጋ ከመደረጉም በላይ የኔ ብሎ የሚኖርበት አገርም ወደማጣት እየተገደደ ነው።ሆኖም ዛሬ በዚህች ሃገር በቀሎች መሣሪያነት ብንጎዳም፣የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ፣ኢትዮጵያ እንደሆነች ሊያጠፏት የእሚቅነዘነዙት ይጠፏታል እንጂ እናት ሃገር ኢትዮጵያን ጠብቀው፣እንደ እንጉዳይ በእሚፈሉ ጀግኖች ልጆቹዋ በአንድነቷ ታፍራና ተከብራ እንደምትኖር የእማያጠራጥር መሆኑን ሙሉ ዕምነቴን አረጋግጣለሁ።”

-”..ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ችግር፣ ሃሳብና ሃዘን ላይ ይገኛል።እንደ እርግማን ይሁን ወይም በፍርድ ቤት እንደተፈረደበት ይመስል እነኚህን ችግሮች የሚያባብስ እንጂ የሚያሻሽልለት አንዳችም አጋር አላገኘም።…”

-“…የፖለቲካ ባለሥልጣኖች ከክፋት ወደደግነት እንዲመለሱ…ኃላፊነት ተሰምቷቸው ለሕግና ለሕዝብ ፍላጎት እንዲገዙ…በሰላማዊ መንገድ ለማሳመን በአጋጠመኝ ዕድል  ሁሉ ድምፄን ከማሰማት አልቆጠብም።…”

– “…ለሀገሩና ለወገኑ ክብርና ደህንነት ደረቱን ለጥይት በመሥጠት የቆረጠው አርበኛም ያለቀኑ አልወደቀም፣አልሞተም።እንዲያውም ከተፈጥሮ ሞቱ በኋላም ቢሆን በታሪክ ውስጥ እየኖረና ኢትዮጵያንም በታሪክ እያኖረ ነው።…”

-”መዐሕድ ለዚህች  ሀገር ሕዝብ በአጠቃላይና ለብሶተኛው ዐማራ ሕዝብ ፍትህ ከመጠየቅ ባሻገር ያቀረበው ሌላ ጥያቄ የለም።…”

-”የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ተከብሮ፣ሕዝቡ በእኩልነትና በወንድማማችነት አብሮ የሚኖርበት ሥርዓት እንዲሰፍን ማድረግ  የአሁንም ሆነ የወደፊት መሠረታዊ ዓላማው ነው።”

-”..እርግጥ ነው መዐሕድ ነፃ መሬት ወይም የታጠቀ ሠራዊት የለውም።ሆኖም የመዐሕድ ነፃ መሬት የእያንዳንዱ ዐማራና የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ ልብ መሆኑን እንድትገነዘቡልን እንወዳለን።…”

-”…ሌላው የመዐሕድ ችግር ሁሉም እንደሚያውቀው ማንኛውንም የኢትዮጵያ ችግር በዐማራው ላይ እንደሚላክኩት ሁሉ ኢሕአዴግ እንዳይጋለጥበት  የሚፈልግባቸውን  ችግሮች ሁሉ በመዐሕድ ላይ ማላከክ የተለመደ ነው።..”

-“…ዛሬ የኤርትራ ጉዳይ ፈንድቷል።እኔ መጀመሪያ ጠላት ተደርጌ የተወሰድኩት የኤርትራን የመገንጠል ጉዳይ በሰኔ የሽግግር ኮንፈረንስ ላይ ትክክል አይደለም ብዬ  ሥለተቃወምኩ ነው።ይኸው ዛሬ ከመንግሥት ጀምሮ እሥከታች ድረስ ሁሉም የሚያጨበጭብበት ጉዳይ ሆኗል።ይፋቱ ካላችሁ ደግሞ ፍቺውን በደንብ በህግ አድርጉ፣አንጠልጥሎ መተው ሌላ ጣጣ ያመጣል ብዬ ነበር።ይኸውና ዛሬ መጣ።”

-“የአካባቢው ሃገሮች፣የወዳጅና የጠላት መንግሥታት፣የዓለም አጠቃላይ ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ፣በመጨረሻ ኢትዮጵያ በሚያመቻት ጊዜ ሉዓላዊነቷን ማስከበር አለባት””    ጥቅምት 1991ዓ.ም.

                                  ሥለፕሮፌሰር አሥራት ሌሎች ሠዎችስ ምን ይላሉ?

-”..ከሃያ ዓመት በላይ አውቃቸዋለሁ።ለፕሮፌሰር አሥራት ከፍ ያለ ግምት አለኝ።ሥራ የማይሰለቹ ማንኛውንም የሕክምና ጥያቄ የማይንቁ ባለሙያ ናቸው… ፕሮፌሰር ያካበቱትን የሙያ ጥበብ አሠራሩንና አስተሳሰቡን ለምደው የራሳቸውን (ወጥነት ያለው ቱባ) ሥራ ማውጣት የሚችሉ ናቸው።…የኢትዮጵያን ባህል ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው።”    ፕሮፌሰር ነቢያት ተፈሪ

-”…የአሥራት የልጅነት መምህሩ ነኝ፣የኔታ ነው የሚለኝ፣ያከብረኛል፣አለቃም አድርጌው ነበር። ረጋ ያለ፣ከሰው ተግባቢ፣ሰው አክባሪ ፣ሲጠየቅ የሚናገረው በቀላሉ ይገባሃል፣ኩራት አያውቅም፣ጠባዩ ያው ነው። አሁን እኔ 93 ዓመቴ ነው፣ በ85 ዓመቴ  ይኸን ሆዴን ተቀድጃለሁ።የቀደደኝም አሥራት ነው እናንተ ፕሮፌሰር ብላችሁታል፣አዳነኝ።አሥራት በራዲዮ <አስተማሪዬን አክሜ ያዳንሁት በጣም ያስደስተኛል> ብሎ ሲናገር በአገሩ ተሰማ።ታዲያ እንዴት ኮራሁ መሰለህ።አሥራት ሰዓት ሸልሞኛል፣ገንዘብም በየጊዜው ሠጥቶኛል።እኔማ ድሮም ድሮም ልጅ ሆኖ ትልቅ ሠው እንደሚወጣው ተረድቻለሁ።..”  የፕሮፌሰር አሥራት የልጅነት መምህር አለቃ ለማ ከስድሳ ዓመት በፊት የነበረውን አስታውሰው ከተናገሩት(በ1981ዓ.ም.)

-”እኔ በመሠረቱ ለአማራው መቆርቆር የጀመርኩት ሻዕቢያ፣ወያኔና ኦነግ አዲስ አበባ ከመግባታቸው ቀደም ብሎ ኦነግ ወለጋ ውስጥ ከ300 በላይ አማራዎችን ብቻ መርጦ “ለሰብሰባ ትፈለጋላችሁ”ብሎ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ከሰበሰበ በኋላ በላውንቸር ከጨረሰበት ጊዜ  አንሥቶ ነው።አዲስ አበባም ከገቡ በኋላ የአማራው ሰቆቃ  እየከፋ ሲሄድ፣የእነክቡር ፕሮፌሰር አሥራት  መዐሕድ ብቅ ብሎ ለአማራው ጥብቅና ሲቆም የተሰማኝ ደሥታ ወደር አልነበረውም።በዚያን ጊዜ በአካባቢዬ ሥለአማራው አፉን ሞልቶ የሚናገር ሥላላጋጠመኝ፣ማንና እነማን ለአማራው እንደሚቆረቆሩ ለማወቅ እጅግ በጣም ከባድ ነበር።ነገር ግን  የአማራው ሰቆቃ ውሥጥ ውስጡን የሚሰማቸው ወገኖች ይኖራሉ የሚል የግል ግምት ነበረኝ።

ያም ሆነ ይህ  በአካባቢያችን በግልፅ ሥለአማራው  ለመናገርና ለማውራት  በማይታሰብበት ወቅት፣”አማራን አሥጨርሶ የሚመጣ አንድነት በአፍንጫዬ ይውጣ” በማለት፣በድፍረትና በቁጭት ገፈታትሬ በመውጣት፣የአካባቢዬ ህብረተሰብ ፈለገም አልፈለገም፣ወደደም ጠላም፣የአማራው ተቆርቋሪና ደጋፊ እንደሆንኩኝ እንዲያውቅ ተገዷል።በዚህን ጊዜ የተወሰነው አማራ  “የኢትዮጵያ አንድነት ነው እንጅ  እንዴት አማራ ትላለህ” በሚል በተግሣፅና በማናናቅ ሲተቸኝ፣አንዳንዶቹ ደግሞ “እኛ ተደባልቀናል፣አሁን ከየትኛው እንሁን?”ሲሉ፣ሌላው ክፍል ደግሞ “አማራ ብሎ መነሳት ዕብደት ነው” እያለ ቢተችም፣ከሁሉም የከፋውና መሰናክል ፈጣሪዎቹ  “ከአማራ ተፈጥረናል” የሚሉት  ነበሩ። ዛሬም ቢሆን ችግር ፈጣሪዎቹ እነሱው ናቸው።በሌላ በኩል ግን ባይናገሩም ውስጥ ውስጡን ደስ የሚላቸው አማሮች  እንደሚኖሩ ገምቻለሁ።

ይህ በዚህ እንዳለ  መዐሕድ በተቋቋመበት ዓመት 1984ዓም ፕሮፌሰር አሥራት ሥዊድን  አገር ሥቶክሆልም ከተማ ለሥራጉዳይ መጡ። አንዲት እህታችን (ለነገሩ የእሷም ዘሯ አማራ ነው፣ግን የአማራው ጉዳይ እንደማይመለከታት ነው የገባኝ) “አንተ አማራ!አማራ!  ትላለህ፣ፕሮፌሰር አሥራት እዚህ አገር መጥተውልሃል”ትለኛለች። አድራሻቸውን እንዳገኘሁ ሄጄ አገኘኋቸው። አነጋገራቸው፣ተግባቢነታቸው ብሎም ራሳቸውን የማያከብዱ ሰው ሆነው ሳገኛቸው በጣም እረካሁ።

እሥከዚህ ጊዜ ድረስ በአካባቢዬ አይንህ ላፈር እየተባልኩም ቢሆን በፊት ለፊት ብቻዬን አማራ ከማለት በሥተቀር፣ሌሎች የሚደግፉ ሥለመኖራቸው  ምንም ፍንጭ ሥላላየሁ፣የድጋፍ ድርጅትም ለማቋቋም አልደፈርኩም ነበር። ታዲያ ፕሮፌሰርን በግሌ አግኝቼ ቁምነገሮችን ከተለዋወጥን በኋላ  “ብችል ሰዎች ካገኘሁ እሠዬው ነው፣ ካልሆነ ግን ትግሉ ጊዜ ሥለማይሠጥ አንዳንድ ለጊዜው የቅርብ ሠዎችን ፈልጌ የድጋፍ ኮሚቴ አቋቁማለሁ”  አልኳቸው።”እሱን እናንተው ወሰኑ” አሉኝ።ከመሠናበቴ በፊት ተዘጋጅቼና አሥቤበት ሥለሄድኩኝ “ሁለት ሽህ(2000)ዶላር ብዙም ባትሆን፣ለመዐሕድ የሥራ ማካሄጃ ትረዳ ዘንድ” በሚል ሥሠጥ፣”አደርሳለሁ” ሲሉኝ፣ደስ ብሎኝ ወደ ቤቴ  ተመለስኩ።እሳቸውም ወደ ኢትዮጵያ  እንደተመለሱ ሳይውል ሳያድር ደብዳቤ  ፅፈው “ያችን የቸርከኝን በተገቢው ቦታ አውለናታል” ብለው ሲልኩልኝ የበለጠ አንጀቴን በሉት፣ምክንያቱም ትንሽ ነው፣ ትልቅ ነው፣ ብለው ሳይንቁ  ቁምነገር ሥላሳዩኝ ነው ።

ከዚያም  በኋላ የአንድነት ጋዜጣ እየመጣ ሲበተን ሠዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፣የድጋፍ ድርጅትም ለማቋቋም በቃን።አብሮ የመሥራት ሁኔታችንም ዳብሮና አምሮ ሲጓዝ ኖሮ እሳቸው ሲታሰሩ ድርጅቱም አብሮ መታሠር ጀመረ።

ፕሮፌሰርን አሜሪካ አገር ፔንሲልቫንያ ሆስፒታል ለመጠየቅ ሄጄ  እንዳየኋቸው እንባዬ ቀደመኝ።ከክፍሉ ወጣሁ።ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተመልሼ ገባሁ።  “ጤና ይሥጥልኝ ፕሮፌሰር”አልኳቸው።ጤና በነበሩበት ወቅት ብዙ የሥልክ ልውውጥ እናደርግ ሥለነበር፣የህመሙ ብርታት በድምፄ እንዳይለዩኝ ይታገላቸው ይሆን  ብዬ ሥለተጠራጠርኩ፣ “ማን እንደሆንኩ አወቁኝ” ብዬ ሥጠይቃቸው፣”መች አጣሁህ”  አሉኝ።   ትንሽ ቆዬት ብለው “ገደሉኝ አይደለም” ሲሉ ተደመጡ።ይህንን መሥማት የበለጠ ያደማል።

ምኞቴና ፍላጎቴ እንዲድኑ፣ተጨባጩ ሁኔታ ደግሞ እንደማይድኑ እየተሟገቱኝ ዕርሜን አውጥቼ  ተመለስኩ። መጀመሪያ ስዊድን  ሀገር በመጡበት ወቅት ሳገኛቸው የተጎናፀፍኩትን ደስታ፣አሜሪካ ሀገር ሂጄ በሀዘን ለውጨው መጣሁ።”     አያሌው ፈንቴ

-”ስለፕሮፌሰር አሥራት ብዙም የማውቅ ባልሆንም በሙያቸው፣በኢትዮጵያዊነታቸውና በወገን አፍቃሪነታቸው አኩሪ ሥም እንዳላቸው አውቃለሁ። መቼም የሰው ልጅ ከሞት የሚቀር ባይሆንም የእርሳቸው ዜና ዕረፍት ከምንም በላይ የሚያሳዝነኝ በአንድ ምክንያት ብቻ ነው።ይህንን ያቀጣጠሉትን የትግል ፍሬና የወገናቸውን መልካም ሕይወት ደርሶ ሳያዩት በማለፋቸው ነው።”     የአንድ ቢሮ ፀሀፊ

-”ፕሮፌሰር አሥራት እኮ ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው የተፈጠሩ አይደሉም።ለሕዝብ ተፈጥረው ሕዝብን አገልግለው ለሕዝብ የተሰው ታላቅ አርበኛ ናቸው።”የመርካቶ ነጋዴ

-”..ብዙዎች ሥለህክምና ሙያቸው ይመሰክራሉ።በእርግጥ ይህ ሁሉ ምሥክርነት ቢያንሳቸው እንጂ የሚበዛባቸው አይደለም።እኔ ደግሞ በመዐሕድ አውቃቸዋለሁ።ደፋር፣ሃሳባቸውን በተገቢው መንገድ በግልፅ ቋንቋ ማስረዳት የሚችሉ፣ሰው አክባሪ፣ድካምን የማያውቁ፣ለቆሙለት ዓላማ የመጨረሻውን መስዋዕትነት የከፈሉ ጠንካራ መሪ ናቸው።..”  የመዐሕድ አባል

7.”ማጣት እንጂ ማቆየት ባልታደለች ሃገር ውስጥ ተፈጥረው ሳይጠገቡ ያለፉ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ነበሩ።”         ያሩሲ ወርቅ

                       

ከ235 ሚሊዬን ብር በላይ ያጭበረበሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሪፖርት አናደርግም አሉ

 

20 የሚደርሱ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ235 ሚሊዬን ብር በላይ ቢያጭበረብሩም፣ ስለ ጉዳዩ ሪፖርት አናደርግም ማለታቸው ተጠቆመ፡፡ ከሃያዎቹ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ገንዘቡን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ሪፖርት ያደረጉት ሁለት መስሪያ ቤቶች ብቻ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ግን ገንዘቡን የት እንዳደረሱት ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ ይሔ ሁሉ ገንዘብ የተሰወረው በስድስት ወር ውስጥ ብቻ ሲሆን፣ ጉዳዩን በተመለከተም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሪፖርት እንዲደረግለት ከሁለት ወር በፊት ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡


በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ እና በመንስግት ስር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ ገንዘብ ማጉደላቸውን ጠቅሶ ለከተማዋ አስተዳደር ምክር ቤት ሪፖርት አቀርቦ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር፣ በሪፖርቱ ላይ እንዳመለከተው ከሆነ፣ የገንዘብ ጉድለትን ጨምሮ፣ ያለደረሰኝ የደመወዝና የአበል ክፍያ መፈጸም፣ ከደንብና መመሪያ ውጪ የሆኑ ጨረታዎችን ማካሔድ፣ የንብረት አለማስመለስ እና የመሳሰሉ ችግሮችን ጠቅሷል፡፡ የገንዘብ ማጭበርበር የፈጸሙ መስሪያ ቤቶች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ስለ ጉዳዩ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጊዜ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን፣ አሁን ባለው መረጃ መሰረት ግን ሪፖርት ሳይቀርብ ሶስት ወራት ተቆጥረዋል፡፡
ከፍተኛ ገንዘብ በማጭበርበር የከተማዋን የመንግስት መስሪያ ቤቶች በግንባር ቀደምነት የሚመራው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሲሆን፣ 137 ሚሊዬን ብር በተለያዩ ሰበቦች ቀርጥፎ መብላቱን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ ከህግ ውጪ የ13 ሚሊዬን ብር ዕቃ ግዢ በመፈጸም እና ግዥውን ተገን በማድረግ በሚሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ በማጭበርበር ደግሞ የከተማዋ ስምንት መስሪያ ቤቶች ተጠቅሰዋል፡፡ ከስምንቱ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና አዲስ ዙ ፓርክ የተባሉት ከፍተኛ ገንዘብ በማጭበርበር የመንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤትን በሁለተኝነት ይከተላሉ፡፡
የዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት፣ የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት እና ራሱ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገንዘብ ያጭበረበሩ መስሪያ ቤቶች ሆነው መገኘታቸው ከዚህ ቀደም መገለጹ አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ 237 ሚሊዬን ብር ካጭበረበሩት 20 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ፣ 18ቱ ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርት ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
ምንጭ: BBN news

ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! (በላይነህ አባተ)

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

እነዚህን በሰባራ ድልድይ የዘፍጥረትን ሁለተኛ ወንዝ እንደ አእዋፋት በሰማይ የሚሻገሩ ሰዎች አይቶ በሚችለው አተነፋፈስ እማይተነፍስ እንደ ግዑዝ እስተንፋስ አልባ ሊባል ይችላል፡፡ ይህን ምስል እንኳን አእምሮን ተሸክሞ እሚዞርን ሰው ደመ-ነፍስን አንጠልጥሎ እሚንቀሳቀስ ከብትንም “እህህ…” አሰኝቶ እሚያስተነፍስ ይመስለኛል፡፡ ይህንን የሕዝብ ኑሮ አይቶ “እህህ…” ያላለ ወይም በሚችለው መንገድ ያልተነፈሰ ከእእምሮው በተጨማሪ ከከብቶች የሚጋራውን ደመ-ነፍሱንም መፈተሽ  እንዳለበት ይሰማኛል፡፡ ይህንን የሰቆቃ ኑሮ በቃላት ለመግለጽ አስራ ሁለት ሕዋሳት የሚያስፈልጉ ይመስለኛል፡፡

ለማኝ ገዥዎች እንደዚህ ዓይነቱን ሰባራ ድልድይ እያሳዩ ማሰሪያ ገንዘብ ለግፍ ወንበር ካበቋቸው ጌቶቻቸው ገንዘብ እንደሚረጠቡ ይታወቃል፡፡ የተረጠቡትን ገንዘብና ይህ ሕዝብ የሚከፍለውን ግብር ግን እነዚሁ ለማኝ ገዥዎች ፎቅ ይሰሩበታል፣ ለሚስቶቻቸው ንግድ ይከፍቱበታል፣ ልጆቻቸውን ያንቀባርሩበታል፤ የተረፈውንም ሲፈረጥጡ ሊውጡት ከምዕራብ ጌቶቻቸው ባንክ ያስቀምጡታል፡፡

በተመሳሳይ መንገድ ይህ ሕዝብ ለታቦት እሚያስገባውን ሥለትና አስራት ተገዳላይ ‘ፓትርያሪኮች’ና ሐሳዊ “ጳጳሳት” እየሞጨለፉ ፎቅ ይሰሩበታል፤ በሉመዚን ይንቀባረሩበታል፤ ጮማ ይቆርጡበታል፤ ዘመድ አዝማዳቸውን ያንደላቅቁበታል፡፡ ይህ ሕዝብ “ከዚህኛው የግዮን ዳር እዚያኛው ጫፍ ካደረስከኝ ጠቦቴን ሸጬ እከፍልሃለሁ”ን እየተሳለ የሚያስገባውን ስለት የ”አባ” ገረ መድህንና የ”አባ” ማትያስ ጋሻ ጋግሬዎች  እንደ ጩሉሌ ሲልፉት ኖረዋል፡፡ ገዳም አፍርሰው ኒዮርክ የተደበቁት “አባ” ዘካርያስ መጀመርያ “በአባ” ገረ-መድህን ጋሻጋግሬዎች ያዘረፉት በሚሊዮን እሚቆጠር የእናቶች ስለትና አሁን ደግሞ እኒሁ ዘኬኛው ዘካርያስ ከየዋህ ዲያስፖሮች ሰብስበው ለ”አባ” ማትያስ የሰጡት በሚሊዮን እሚቆጠር ገንዘብ ለእነደዚህ ዓይነቱ ዝርፊያ ምሳሌ ይሆናል፡፡

ይህ ነፍሱ በገመድ ያለች ሕዝብ በቀን አስራ ስድት ሰዓት እየሰራ ሰሜኑንም ደቡብንም ምስራቁንም ምእራቡንም ማኛ፣ ማርና ቅቤ ሲመግብ ሺህ ዘመናት አስቆጥሯል፡፡ እንዳለመታደል ግን ይህ ሕዝብ መርፌ እንደ ወጋው ፊኛ ትእቢታቸውን አስተንፍሶ በመለሳቸው ነጫጭባዎች የተመረዙ ያምሮ በሽተኞች በመሶሎኒ ድምፅ ማጉያ “አማራ ጨቋኝ” እያሉ መጮሁን አላባራ ብለዋል፡፡ እነዚህ ያምሮ በሽተኞች ያገር ሰው መስለው ወንበር ተቆናጠው ይህንን ከክርስቶስ በቀር ማንንም የማይፈራ ሕዝብ ከቅረርቶው፣ ከፉከራውና ከነፍጡ አርቀው ለግርፋት፣ ለምክነት፣ ለባሰ ድህነት፣ ለስደት፣ ለባርነትና ለእጅ አዙር ቅኝ-ተገዥነት ዳርገውት ይገኛል፡፡

እጁ አመድ አፋሽ የሆነው ይኸ ሕዝብ ግን ዛሬም በመሶሎኒ የማደጎ ልጆች የመጣበትን የጥፋት ውሀንና እሳተ ገሞራ ተቋቋሞ ብሉይን ከሀዲስ አዋህዶ ይኖራል፡፡ በሞሰሎኒ የማደጎ ልጆች ከምድር እየተሰመረውን የሞሶሎኒ ክልል አሻፈረኝ ብሎ በሙሴ የተሳለውን የዘፍጥረት ካርታ ሙጥኝ ብሏል፡፡ የሞሶሎኒን ደቀ መዛሙርት ኮከብ እምቢኝ ብሎ ለኖህ የታየውን ቀስተ ደመና ከመርከቡ ደቅኖ መቅዘፉን ቀጥሏል፡፡ የዲያብሎስን ክልልና አጥር አፍርሶ ቅዱስ መጽሐፍ እንዳዘዘው በሁለተኛው ወንዝ ተሳስሮ በኤደን ለመኖር ገመዱን ዘርግቷል፡፡ ምንም ምድራዊ ኃይል ሊበጥስ ያልቻለውን  ወንድማማችነትና እህትማማችነት በዓባይ ወንዝ በተዘረጋው ገመድ አጥብቋል፡፡

እንዲያው ለመሆኑ ተለያይቶ ከመኖር ወድቆ መፈጥፈጥን እሚመርጥ እንደዚህ ዓይነት ሕዝብ  በየትኛው ዓለም ታይቷል? እንደ መንታ ጽንስ በአንድ የእትብት ገመድ ተሳስሮ በአንድ ማህጸን እሚዋኝ እንደዚህ ዓይነት ሕዝብ በየትኛው አሀጉር ተፈጥሯል?

ይህ ከመለያየት ሞትን የመረጠ ሕዝብ ለውጪም ሆነ ለውስጥ ጠላቶች ምን ያስጠነቅቃል? ለእኛ ገመድን ለመገናኘትና ለመያያዝ ሳይሆን ለመጓተትና ለመጠላለፍ ሃምሳ ዓመት ለተጠቀምነውስ ምን ያስተምራል? “አማራ ጨቋኙ”ን በኦፔራ ዜማና በሞሶሎኒ ቫዮሊን ለሚዘፍኑት በሽተኞችስ ምን ፈውስ ያቀርባል? በአማራ ጨቋኙ ዘፈን ምክንያት በወልቃይት፣ በደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በወለጋ፣ በሁመራ፣ በራያ፣ በመተከል፤ በጉራ ፈርዳና ሌሎችም ሥፍራዎች ለረገፉት፣ ገደል ለተጣሉት፣ ለታረዱት፣ ለተቃጠሉት፣ ለታወሩት፣ ለተቆመጡት፣ ለመከኑት፣ ለተፈናቀሉት፣ ለተራቡት፣ ለተጠሙት፣ ለተራቆቱት፣ ለተሰደዱትና ባርያ ለሆኑት ፍትህ የመፈለግ ሂደትስ ምን አስተዋፅኦ ያደርጋል?

መንግስት ባልነበረበት ወቅት ራሱን አደራጅቶ ጣልያንን እንኳን ምሽግና ካምቦ ድንኳን ተክሎ ለማደር ፋታ ያልሰጠ ይህ ሕዝብ ስንት ክፍለ-ዘመን እጁ አመድ እያፈሰ ይኖራል? አማራ ጨቋኝን ኦፔራ ዜማ በሚያንቆረቁሩት አረመኔዎች ደሙን ካፈሰሰበትና አንጥንቱን ከከሰከሰበት ምድር ስንቴ ይባረራል? ምን ያህል ጊዜስ “ጨቋኙ አማራ!” እየተባለ ጠላትን ሊፋለም ከመሸገበት ገደል ይወረወራል? የሌላውን ሀዲድና ድልድይ እየሰራ እርሱ ስንት ዘመን በገመድ መጓዝ ይቀጥላል?

እንደ ፍካሬ እየሱስ መደገም ያለባት የክቡር አቶ ሀዲስ አለማየሁ ትዝታ እንደምታስረዳው በሁለተኛው የጣልያን ወረራ ወቅት ከዚህ ሁለተኛውን ወንዝ በገመድ ከሚሻገሩት ወላጆችና አያቶች የተውጣጡ ሃምሳ ሺ ያህል የጎጃምና የጎንደር አርበኞች እንደልማዳቸው ትግሬን ነፃ ሊያወጡ ዘምተው ነበር፡፡ እንደሚታወቀው እነዚህን ትግሬን ነፃ ሊያወጡ የሄዱትን አርበኞች ኃይለስላሴ ጉግሳና ሰራዊቱ አምባሻ ትተው ፒዛ እየቀረደዱና አማራ ጨቋኝን በከበሮ እየደለቁ ከግራዚያኒ አብረው ወጓቸው፡፡ በትግሬም የግራዚያኒና የባንዶች ኃይል ሲያይል ነፃ ሊያወጡት ከሄዱት ትግሬ ሥልታዊ ማፈግፈግ አድርገው ደቡብ ምዕራብ መሽገው ነበር፡፡ ድካም፣ ርሃብ፣ በሽታና እልቂት ሳይበግራቸው ከፋና ወለጋን ነፃ ሊያወጡ ሞክረው ነበር፡፡ ዳሩ ግን የወለጋው ገዥና ሰራዊትም ጪኮ ትተው መኮሮኒያቸውን እየዛቁና አማራ ጨቋን እየደለቁ ነፃ ሊያወጧቸው የሄዱትን አርበኞች ከሞሶሎኒ ሰራዊት ጋር ሆነው ወጓቸው፡፡

የጨቋኙ አማራ ጣጣ ከዚህ አልቆመም፡፡ እነ አባ ጆቢር የአማራን ራስ ቆርጦ ላመጣ 30 ብር እሰጣለሁ እያሉ በዚያ አካባቢ ያለውን አማራ በኛ ዘመን በጉራ ፈርዳ እንዳየነው ንብረቱን እየቀሙ አባረሩት፡፡ (ትዝታ ገፅ 166-167). አማራ ይኸው ነው! ነፃ አውጥቶም ሽልማቱ ሞት የሆነ ሕዝብ ነው! ከሞት የተረፈው አንዳንዱም የገጠመው ረጅሙን ወንዝ በገመድ መሻገር ነው!

እኔም ከልጅነቴ እስካሁን ያስተዋልኩት ይኸንኑ የአማራ እጅ አመድ አፋሽነት ነው፡፡ በሶማልያ ወረራ ወቅት ይኸው በገመድ እትብት የተሳሰር ሕዝብ ሆ! ብሎ በራሱ ፈቃድ ሃረርጌ ተምሞ ገባ፡፡ ከአንደኛ ትምህርት ቤቴ አጠገብ ገበያ ውስጥ የድምፅ ማጉያው “አገርህ ተደፍራለች! አገርህን ጠላት ወሯታል” ሲል ሊሸጡ ያመጡትን እህልና ከበት በትነው ቤተሰቦቻቸውን ሳይሰናበቱ እያቅራሩና እየፎከሩ ከቀረበላቸው ክፍት መኪና የገቡት አርበኛ ወገኖች ዛሬም ከዓይኔ ናቸው! መኪናው ሞልቶ በመቅረታቸው ጸጉራቸውን የነጩት ጎበዛዝትና “ግንባር-ግንባሩንን ብላችሁት በድል ተመለሱ” እያሉ የተንጎራደዱት ወይዛዝርት ዛሬም በህሊናዬ ይመላለሳሉ፡፡

እነዚህ ወይዛዝርት እንደተመኙትም አርበኞች ከመደበኛው ጦር ጋር ቀደምት አባቶቻቸው የፈጸሙትን ጀብዱ ደገሙ! የሞሶሎኒን ድንፋታ እንደ ፊኛ እንዳስተነፈሱት አባቶቻቸው የሲያድ ባሬን በእንግሊዞች የተደፈደፈ ታላቋ ሶማልያ ቅዠትና ረጅም እጅ አሳጠሩ፡፡ እነዚህ አርበኞች ከድል መልስ ኢትዮጵያን ወግተው ባህር አልባ እንዳደረጓት ከንቱዎች ሁመራና ዳንሻ ለም መሬት አልተሰጣቸውም፡፡ ብዙዎቹ በችጋርና ሊደን በሚችል በሽታ አለቁ፡፡ እድሜውን የሰጣቸው አንዳንዶቹም ዓባይን በዋናና በገመድ እየተሻገሩ ኑሮን ይገፋሉ፡፡ ደማቸውን ያፈሰሱበት ሃረርጌም የእነዚህን አርበኞች ቋንቋ ለሚናገሩት ዜጎች ፊት ነስቷቸው የሰቀቀን ኑሮ ይኖራሉ፡፡ በሃረርጌ አማራ ዛሬ ድምፅ ብቻ ሳይሆን የመኖር ዋስትናም አጥቷል፡፡ አማራ በሃረርጌ የመኖር ዋስትና እንደሌለው የበደኖን ታሪክ ያስታውሷል፡፡

ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! ነፃ ባወጣው አገር መኖር እሚነፈገው ሕዝብ ነው! ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! “ነፃ አውጥቼሃለሁ!” እሚል ጉራ እየነዛ እንደ መሶሎኒ ደቀመዛሙርቶች የሊጥ እቃ ሳይቀር እየዘረፈ ከትውልድ ቦታው እማያግበሰብስ ፈርሀ-እግዚአብሔር ያለው ሕዝብ ነው፡፡ ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! እንኳን ሰላማዊ ሕዝብ ጠላቱንም ከቤት እሚያሳድር እንጅ ገደል እማይወረውር ብሩክ ሕዝብ ነው! ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! “ራሴን ሳለማ ሌላው ሕዝብ ይድማ”ን የማያልም በህሊና የተካነ ሕዝብ ነው፡፡ ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! ለሌሎች ሀዲድና ድልድይ እየሰራ ራሱ በገመድ ትልቁን ወንዝ እሚሻገር ነው፡፡ ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! ለሌላው ሆስፒታል እየሰራ እርሱ በአባሎና በወጌሻ እሚታከም ነው፡፡ ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! እርሱ በሁለት እንጨት እየተጋዘ ሌላውን በአንቡላስ ሆስፒታል እሚያደርስ ነው፡፡ ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! እርሱ በበሽታ እየረገፈ ገዳዮቹን በፈረንጅ ሆስፒታሎች እሚያሳክም ነው! ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! እርሱ ቅጥቅጥ እያበራ ፈጣሪ የባረከለትን ቅዱስና ግርማ ሞገስ ያለው ወንዝ ለሌሎች መብራት ማፍለቂያ እሚፈቅድ ነው፡፡ ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! በኩሊና ደመና አርሶ እያመረተ እንደ ጠላት እሚቆጥሩትን ሳይቀር በአውሮጳና አሜሪካ ጤፍ አስነግዶ ቱጃር እሚያደርግ ነው!  ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! እስከ መቼ እንደሚጨቁን ባላውቅም ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! ይኸው ነው! ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! በመለኮት ኃይል ሁለተኛውን ወንዝ እንደ አእዋፍ በሰማይ እየተሻገረ ኑሮውን እሚገፋ፤ ሲሞትም በወሰካ ተሰቅሎ እሚቀበር፤ ሞቷል ሲሉት ግን እንደ ክርስቶስ እሚነሳ ሕዝብ ነው! ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው! ይኸው ነው!

 

ግንቦት ሁለት ሺ ዘጠኝ ዓ.ም.

 

የጣናው ሞገድ ተጫዋቾችና የመቀሌው አደጋ – ከሙሉቀን ተስፋው

ጨዋታው ተጀምሯል፤ በመቀሌ አዲ ሀቂ እስታዲየም ከመቀሌ ዩንቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች እና ከባሕር ዳር መኪና ኮንትራት ይዘው የመጡ ዐማሮች የጣናውን ሞገድ ለመደገፍ እስታዲዮም ገብተዋል፡፡ እስከ 60ኛ ደቂቃ የጣናው ሞገድ በባዕድ ምድር 1 ለ0 እየመራ ነበር፡፡ 60ኛው ደቂቃ ላይ ዳኛው አላስፈላጊ ቅጣት ምት ለመቀሌዎች ሰጠ፡፡

 

የጣናው ሞገድ ተጫዋቾች አይሆንም ብለው ተቃወሙ፤ የሚሰማቸው አልነበረም፡፡ አገሩም፣ ሥልጣኑም ሁሉም ነገር የአንድ ወገን ነበርና በቅጣት ምት እኩል ውጤት ይዘው ቀጠሉ፡፡ በስታዲዮሙ የነበሩ ትግሬዎች በጅምላ ዐማራን መሳደብ ጀመሩ፡፡ ‹‹ትምከተኛ፤ ነፍጠኛ….›› የማይሰማ የማሸማቀቂያ ስድብና የሥነ ልቦናዊ ብዝበዛ አልነበረም፡፡ በጠቅላላው የመቀሌ ትግሬ ለስድብ የወጣ እስኪመስል ድረስ፡፡

የመቀሌ ከተማ ተጫዋቾች የባሕር ዳር ከነማዎች ላይ ሆን ብለው መትፋት ጀመሩ፤ ቢሆንም እስካሁን የጣናዎቹ ትዕግስትን አሳይተዋል፡፡ ቆይተው 4 ቁጥር ተጫዋችን በእግራቸው ረግጠው ሰበሩት፤ የቀይ መስቀል ሰዎች አልጋ ይዘው ገቡ፡፡ የተጎዳውን ዐማራ ተሸክመውት ከወሰዱ በኋላ ሰብአዊነት በሌለው መልኩ በቁማቸው ሲጥሉት የጣናው በረኛ ተመለከተ፡፡ ለምን ይህን ታደርጋላችሁ ብሎ ጠየቀ፡፡ በዚህም ድብድብ ተፈጠረ፡፡

ሰባት ተጫዋቾች በሰው አገር ላይ ደማቸውን አፈሰሱ፡፡ ከደጋፊዎች ቁጥራቸው ያልታወቀ እንዲሁ ተደበደቡ፡፡ ከባሕር ዳር ተጫዋቾችንና ደጋፊዎችን ይዘው የሔዱ አውቶቡሶች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፤ በጠገቡ ትግሬዎች፡፡ ያም ሆኖ የተጎዱ ተጫዋቾች ወደ መቀሌ አይደር ሆስፒታል ተወሰዱ፡፡

የመቀሌ ዩንቨርሲቲ አይደር ሆስፒታል የሥራ ባልደረባ የነበረ ዶክተር ሀብታሙ የተባለ ዐማራ ሕክምና በሚሰጥበት ጊዜ ተጠልፎ ተወስዶ ታሰረ፡፡ እስካሁን እንኳ የት እንደታሰረ አልታወቀም፡፡ የዩንቨርሲቲ ተማሪ ዐማራዎች ድጋፍ ሰጥታችኋል ተብለው በመታወቂያ እየተለዩ ታሰሩ፤ ሌላም ሌላም፡፡

ሌሊቱን መኪና በማፈላልግ የባሕር ዳር ከነማ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች አደሩ፤ የዐማራ ክልል ባለሥልጣናት መኪና እንዲልኩ ቢጠየቁም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አልቻሉም፤ የትግሬ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች በተደበደቡት ላይ የጥፋተኛነት ክስ ሲሰፉ ዋሉና አደሩ፤ እንዲያውም የመቀሌን ከተማ ሕዝብ ትግስት አደነቁ፡፡

ዛሬ ጠዋት የትግራይ ጋዜጠኞች ወደ ተጎዱት የጣናው ደጋፊዎችና ተጫዋቾች በመሔድ ጥፋቱ የእነርሱ መሆኑን መናገር ካልቻሉ እንደማይወጡ ነገሯቸው፡፡ ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ምንም ላይናገሩ ተስማምተው ወደ  ባሕር ዳር መኪና ተከራይተው ጉዞ ጀመሩ፡፡

የመለስን ልቃቂት አይቶ – ሰው እንዲት ያድራል ተኝቶ (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

የፖለቲካ የበላይነትን በማረጋገጥ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ወሳኝ መሆኑ ጥናትና ምርምር የሚጠይቅ የተለየ እውቀትም የሚሻ ጉዳይ አይደለም፡፡ፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም  ሰው ሊያውቀው የሚችል ጉዳይ ነውና፡፡ አበውም “ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ” ይላሉ፡፡ ቁም ነገሩ ታዲያ ማወቁ ሳይሆን መተግበሩ ነው፡፡ እናም ወያኔ  ይህን አውቆ ጠቀሜታና አስፈላጊነቱን ተረድቶ በኢኮኖሚ የበላይነት ፖለቲካውን ለመቆጣጠርና የሥልጣን እድሜውን ለማረዘም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ባለሥልጣናት ለራሳቸው መጦሪያ ለልጆቻቸውም ተንደላቆ መኖሪያ የሚሆን ሀብት ማከበታቸውን የአቶ ኤርምያስ ለገሰ የመለስ ልቃቂት መጽኃፍ በመረጃና በማስረጃ አሳይቶናል፡፡Yemeles Likakit book cover

የወያኔ እውቀት ይሁን የሌላው አስተውሎት ማጣት፣የወያኔ ድፍረት ይሁን የሌላው ፍርሀት፤የወያኔ ይሉኙታ ቢስነት ይሁን የሌላው አድር ባይነት፣ የትኛው ሚዛን ደፍቶ ለዚህ እንዳበቃን ባይታወቅም (እያወቅን ባናውቅም) አናሳው ወያኔ ኢትዮጵያውያንን በቁማችን ገፎናል፤ አይናችን እያየ ማስተዋል፣ጆሮአችን እየሰማ ማዳመጥ ተስኖን ተቃውሞ ቁጣችን ከሰልስት ግፋ ቢል  ከሳምንት የማያልፍ ሆኖ ኢትዮጵያን ያለማንም ሀይ ባይ ዘርፏታል፡፡

ተጽፎልን አንብበን፣ ተነግሮን ሰምተን የማይቆጨን በመሆናችንም ሲሻው በህግ ሽፋን ካልሆነም በምን ታመጣላችሁ እብሪት ዝርፊያውን በአይነትም በመጠንም እያሳደገና እያሻሻለ መጥቷል፣ይቀጥላልም፡፡ “የናቁትን ሀገር በአህያ ይወሩታል” እንዲሉ አዩን ለዩንና ዝርፊያቸው ሳያንሰን ስለ መዝርፊያ ድርጅቶቻቸው ማንሳት መሀይምነት ነው በማለት እስከ መሳደብ ደረሱ፡፡

በማላዘን- ምንም ነገር አይሆን፣

ሀያ አምስት አመት ሙሉ ወያኔ ዘረፈ፣ገደለ፣ አሰረ፣ወዘተ እያለ የሚያላዝነው ወገን በማላዘን አይደለም ነጻነትን ማግኘት ዝርፊያን ማስቆም አንደማይቻል እንዳልተቻለም መረዳት ባለመቻሉ ወይንም ባለመፈለጉ ዛሬም እዛው ላይ ቸክሎ ማላዘኑን ቀጥሏል፡፣”ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሉም ይሄዳል” የሚለው አባባልም  ድርጊትም እንደዚሁ ቀጥሏል፡፡ወያኔ የሚፈጽመው ሁሉ መፈጸም ያለበትን ነገር ሆኖ ሳለ ወያኔ ለምን እንዲህ ያደርጋል እያሉ መጠየቅም ሆነ  ተዘረፍን ታሰርን ተገደልን እያሉ ማላዘን “ከእባብ እንቁላል ርግብ መጠበቅ” የሚሉት አይነት ነው፡፡

እኛስ ምን አደረግን፣

ወያኔ ዓላማ ያደረገውን፣ ለግቤ ይበጃል ያለውን፣ ያመነበትን ዝርፊያም ሆነ ግድያ፣ማሰርም ሆነ ማሰደድ ፈጽሟል እየፈጸመ ነው፣ወደ ፊትም ይቀጥላል፡፡ይህን እያነሱ የአዋጁን በጆሮ እንዲሉ ከመጮህና ከማላዘን እኛ ምን አደረግን ምንስ አላደረግንም ብሎ ራስን መጠየቅና ወያኔን መገዳደር የሚያስችል አቅም በመፍጠር ትግሉንና በእምነት በጽናት መያዝ ነበር የሚሻለው፡፡ግና በአብዛኛዎቻችን ዘንድ ይህ የለም፡፡ ነገረ ስራችን ወያኔ በአደባባይ የሚፈጽማቸውን ነገሮች የተደበቁና የማይታወቁ ይመስል እነርሱን እያነሳን ብሶት ማውራት፣ማላዛን በዚህም ትልቅ ገድል የፈጸምን ያህል ረክተን ለሽ ብለን መተኛት ነው፡፡እኛ ያልተዘረፍን ማን ይዘረፍ? እኛ ያልተናቅን ማን ይናቅ ?፣እንደውም አንዳንዶቻችን “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ  አብረህ ዝረፍ” የሚለውን ብሂል ተከትለን ለሚጣልልን ፍርፋሪ የሀገር ሀብት በማዘረፍ ተባባሪ ሆነን እንሰለፋለን፡፡

በኤርምያስ ለገሰ የመለስ ልቃቂት መጽኃፍ በበቂ ማስረጃ የተገለጸውን ዘረፋ በምንም ተአምር ወያኔ ብቻውን ሊያከናውነው አይቻለውም፡፡ አንድም ራሳቸውን ለወያኔ አሳልፈው በሰጡ ሆድ አደር ሎሌዎች ተባባሪነት ሁለትም በብዙሀኑ (እኛ) ግዴለሽነት ነው ጠመንጃ ነካሾቹ ባለ ቢሊዮን ብር ጌቶች ለመሆን የበቁት፡፡ ስለሆነም አስር ጣታችንን ወደ ራሳችን አዙረን ማየትና መጠየቅ እስካልቻልን ድረስ ብሶት በማውራትና በማላዘን ሀያ ስድስት አመት ያመጣነው ነገር የለም ወደ ፊትም አናመጣም፡፡ወያኔ ማድረግ ያለበትን ነው የሚያደርገው፣እኛስ? ለዚህ ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል፣

ከቢቢኤን ራዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉ የወያኔ ሁለት የቀድሞ ጀነራሎች የተናገሩት ራሳችንን ለማየት ችግራችን በአብይና ወቅታዊ ማስረጃነት  ሊቀርብ ይችላል፡፡ ቃለ ምልልሱን ጨርሶ የማደመጥ ትእግስቱም አቅሙም አልነበረኝም‹፡፡ ከወያኔ ከተለዩ ከአስር አመት በላይ የሆናቸውና ይህንንም ግዜአቸውን በአስመራ  ከትመው ያሳላፉት እነዚህ ጀነራሎች እንደ ጦር መኮንነታቸውና አንደ ወያኔም ተቀዋሚነታቸው ይሄ ነው የሚባል ነገር ስለመስራታቸው ሳንሰማ ስለ ወያኔ ማንነትና ምንነት ስለህዝቡ ድካም ሊነግሩን ይዳዳቸዋል፡፡

“ወያኔ በሰራለት ከረጢት ውስጥ ተከቶ የሚገኘው ሰራዊት” ሲሉ ከረጢቱን በመስፋቱ የእነርሱ ድርሻ ስለመኖሩ የሚያስታውሱ አይመስሉም፤ ጦር አስከትለው አስመራ ገብተው አስር አመት ምንም አለማድረጋቸው ሳይታወሳቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንክሮ ባላተቋረጠ ሁኔታ ትግሉን ቢያቀጣጥል ሰራዊቱን ወደ እርሱ ማምጣት እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ ጠያቂውም እናንተ ምን አደረጋችሁ፣ ለትግሉ ከህዝቡ በፊት እናንተ አትቀርቡም ወይ፣ ስንቶች የተደላደለ ህይወታቸውን ጥለው ለትግሉ ራሳቸውን አሳልፈው ሲሰጡ እናንተ የጦር መኮንን ሆናችሁ ከትግሉ ርቃችሁ ወያኔን ለማውገዝም ሆነ ህዝቡ እንዲህ ቢያደርግ ብሎ ለመምከር የሞራል ብቃት ይኖራችኋል ወይ ወዘተ ብሎ መጠየቅ በተገባው ነበር፡፡ ራስን የማየት፣ የመጠየቅ ብሎም የድርሻ ተጠያቂነትን የመውሰድና ይቅርታ የመጠየቅ ነገር እንዲለመድ ጋዜጠኞች ትልቁ ሀላፊነት አለባቸው፡፡ወያኔን ማውገዝ የተቀዋሚነት መገለጫ መሆኑም ማብቃት አለበት፡፡ከብዙ ውግዘት ዋይታና ጩኸት ትንሽ ተግባር ነው ውጤት የሚያስገኘው፡፡ለዚህ ደግሞ ወያኔን ለአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያበቃውን ድርጊት መለስ ብሎ ማስታወስ በቂ ነው፡፡

ሌላው በየትኛውም የለውጥም ሆነ የነጻነት ታሪክ ህዝብ ሆ ብሎ ወጥቶ የታገለበት ሀገርም ዘመንም የለም ሊኖርም አይችልም፣ ጥቂት የቆረጡ የጸና ዓላማና እምነት ያላቸው ግንባር ቀደሞች ባደረጉት ትግል እንጂ፡፡ ስለሆነም የድርጅት መሪ ተብሎ አንድም ተግባር ሳይፈጽሙ እንዲሁም የወያኔ ተቀዋሚ ነን ብለው የትከሻ ማእረግ ደርድረው ከሹመቱ ጫፍ ጀነራልነት ደርሰው ብዙ ሲጠበቅባቸውና ሊያደርጉ ሲችሉ ምንም ሳያደርጉና አለማድረጋቸውንም ከምንም ሳይቆጥሩ ህዝብን ለመውቀስና ለመክሰስ የሚደፋፈሩበት ሁኔታ መገታት አለበት፣ለዚህ ደግሞ ጋዜጠኞች ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡

በወያኔ ተበልጠናል፣

አመንም አላመንም በወያኔ ተበልጠናል፡፡ሀያ አምስት አመት ቀጥቅጦ እየገዛን ያለን ድርጅትና መሪዎችን እንዲሁም አቶ ኤርምያስ በመጽኃፉ የነገረንን ዘረፋ የፈጸሙ ሰዎችን የተለያየ ስም እየሰጠን ስንሳደብና ስንዘልፍ ራሳችንን እየሰደብንና እየዘለፍን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ ብዙዎች  የወያኔ ባለሥልጣኖችን መሀይሞች በማለት ይገልጹዋቸዋል፡፡እነርሱ መሀይም ከሆኑ እኛ በመሀይም የምንገዛውስ? እነርሱ ምንም እንበላቸው ምን  እየገዙን ነው፣ ሀገሪቱን  ዘርፈው የሀብት ጣራ ላይ ደርሰዋል፡፡ እኛ ደግሞ ተበልጠናልና ዘረፋውን ማስቆም አገዛዙን መገላገል አልቻልንም፡፡ ምንም ይሁን የበለጠን ሀይል በመስደብ በማንቋሸሽ በመዘለፍ አለያም በማላዘን የሚመጣ ነገር የለም‹,፤ በልጦ በመገኘት እንጂ፡፡

የለውጥ አዋጅ!!!…. እንቢልታው ይነፋ! ነጋሪት ይጎሰም! | ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

 

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
Email:- solomontessemag@gmail.com http://www.semnaworeq.blogspot.com

እደግመዋለሁ፡፡ እደጋግመዋለሁ!!! “የለውጥ አዋጅ፣ ይታወጅ!!!” እንቢልታው እየተነፋ፣ ነጋሪቱም እየተጎሰመ፣ በለውጥ ረጅም ጎዳና ላይ ለመዝመት እንነሳ!!! ረጅሙን ጉዞ፣ እልህ አስጨራሹን ጉዞ፣ አሁኑኑ እንጀምረው፡፡ አዎን!!! ነጋሪቱ ይጎሰም!!! እንቢልታውም ይነፋ!!! ለለውጥ የተዘጋጃችሁ ሁሉ፣ ማቄን ጨርቄን ሳትሉ፣ አቅማችሁ የፈቀደውን፣ ቤታችሁ ያፈራውን፣ ስንቅና ትጥቃችሁን ይዛችሁ ውጡ!!! ለውጡ፣ ያለያንደንዳችን በጎ አስተዋፅኦ ፍጹም አይሳካምና-ኑ ውጡ፡፡ ኑ!!! ታገፈጡ፡፡ ለውጥን ራሱንም ተጋፈጡት! እንቢልታው ሲነፋ፣ ነጋሪቱም ሲጎሰም፣ በሰመመን እንቅልፍና ዱካክ ውስጥ ሆናችሁ፣ የቀን ቅዠት ከሚንጣችሁ፣ “ኑ!!! ውጡ!!!” ይላችኋል ለውጡ!!!
የለውጥ አዋጅ ሲታወጅ፣ ነጋሪቱ ሲጎሰም፣ እንቢልታውም ሲነፋ፣ በሰመመን ድብርት ውስጥ፣ ካለ ሆኖ የሚያንቀላፋ፣ ወየውለት፡፡ ዝቅ ብሎ ባቱን! ከፍም ብሎ አንገቱን! ይቆርጠዋል-የታሪክ ሰይፍ፣ ይወገዳል ከመጪውም ሰልፍ! አዎን! ትልቅ ታሪክ ያለን፣ ለሺህ ዘመናት የኖርን፣ ለጽድቅና ለክብር፣ ቀን ከሌት የተጋን፣ ትልቅ ሕዝብ ነን፤ ማንም ያልደፈረን፡፡ አሁንም ቢሆን፣ አንገታችንን ያልደፋን፣ በክብር ተመልተን፣ ልዕልናችንን ይዘን፣ ወደፊት የምንጓዝ፣ ዘላለማዊዎች ነን፡፡ ዓለም ስትለወጥ፣ ከዘር አባዜ ወጥታ፣ የእያንዳንዱን ሰው መብት፣ ስትሰጥ እኩል በኩል ገምታ፤ ባረጀና ባፈጀ ወግ ውስጥ ታስረን፣ በዘር አባዜ ስንገላመጥ፤ ባለማቀፍ ሴራ ጥርስ ውስጥ፣ ገብተን እንደማንሰለቀጥ – ምንም ዋስትና የለንም፡፡ ስለዚህም፣ የለውጡ አዋጅ እንዲታወጅ፣….. ነጋሪቱ ይጎሰም!!! እንቢልታውም ይነፋ!!!

የአዋጁን ጥሪ ለመስማት፣ ካለ የማዳመጥ ችግር ያለበት፤ የለውጡን ዘማች ሰልፈኞችም ለማየት፣ ካለ የማየት ችግር ያለበት፣ ቱርጁማን ይቀጠርለታል፤ ግን፣ መከተል አለበት፡፡ ለውጡ ማንንም አይመርጥም፤ ማንንምም አይጥልም፡፡ የታሪክ ሚዛን ነው፤ ሁሉንም ይሰፍራል፡፡ የታሪክ ጎዳና ነው፤ ሁሉንም ያስኬዳል፡፡ የታሪክም ሰልፍ ነው፤ ሁሉንም ይጣራል፡፡ “ኑ! ተቀላቀሉኝ፣ እንዳትቀሩብኝ” ይላል፡፡ የምንጓዘው ወደ ግለሰብ ነፃነት ነው፤ የምንዘምተው ወደ እኩልነት ነው፡፡ እያንዳንዳችን “በሕግ ፊት” እኩል ወደ ምንዳኝበት፤ እያንዳንዳችን በሀገር ጉዳይ ላይ እኩል ወደ ምንተችበት፤ እያንዳንዳችን በብሔራዊ ጥቅማችን ላይ እኩል ወደ እምንሰማበት፤ ወደዚያ መፃኤ ግብ፣ ባንድነት የምንተምበት ሰዓት አሁን ነው፤ አሁን ነው!!! የለውጥ አዋጅም የሚታወጅበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ አልሰማሁም ብሎ የሚቀር ካለ፣ አላየሁም ብሎም የሚያመነታ ካለ፣ ከፍርድ አያመልጥም፤ ምንም እንኳን እንጦሮጦስ ቢሰጥም-ከፍርድ አያመልጥም፡፡ በስደተኝነት ቢያላክክ፣ በምንተዳዬም ቢብሰከሰክ፣ ከፍርድ አያመልጥም፡፡ ፍርዱም የታሪክ ነው፤ ትዕዛዙም አዋጅ ነው፡፡ አዎን! ነጋሪቱ ይጎሰም!!! እንቢልታውም ይነፋ!!! ድው…! ድም….!!! ግው-ግም!!! ግው-ግም!!!

የአዛውንቶችና የአንጋፋዎች ተግሳጽና ምክር የሚደመጥበት፤ የጎልማሶችና የባልቴቶች ሚና የሚወደስበት፤ የወጣቶችና የታዳጊዎች አቅም ጎልቶ የሚወጣበት ወቅት፣ አሁን ነው፡፡ አሁን ነው፣ አዲሱንና ግዙፉን ኢትዮጵያዊነት የምናድሰው፡፡ ያሻንን የምናመርትበት፤ የሚያዋጣንንም የምንነግድበት፤ የሚያስፈልገንን የምንገበይበት፤ ልባችን የወደደውን የምንቀስምበት፤ የፈቀድነውንም የምንጽፍበት፤ “ማለት ያለብንንም ሁሉ የምንናገርበት” ወቅት እንዲመጣ ከፈለግን፣ የለውጥ አዋጁ መታወጅ አለበት፡፡ የአዋጁም ማብሰሪያ፣ እንቢልታው ይነፋ! የሰልፉም ማጀቢያ፣ ነጋሪቱ ይጎሰም! ኢትዮጵያዊነት ጸንቶ እንዲኖር፣ ከዓለም እስከ-ዓለም፣ ለዘላለም-ዓለም፣ እንቢልታው ይነፋ!!! ነጋሪቱም ይጎሰም!!! ድው…!!! ድም….!!! ግው-ግም!!! ግው-ግም!!!

ለውጡ — አርበኞችን ይሻል፤ በእውቀትና ክህሎት የታጠቁትን፡፡ ለውጡ — ከያኒያንን ይሻል፤ ከስር ከስር ተከታትለው የሚያነውሩትን፡፡ ለውጡ — ገንቢዎችን ይሻል፤ ግሩም መሠረት የሚጥሉለትን፡፡ ለውጡ — አንጥረኞች ይሻል፤ አሽሞንሙነው የሚያስጌጡትን፡፡ ለውጡ — ዘማሪዎች ይሻል፤ ግነን-ፍነን የሚሉትን፡፡ ለውጡ — ፈካሪዎች ይሻል፤ የዕለት ውሎውን የሚዘግቡለትን፡፡ ለውጡ — ተኳሾችን ይሻል፤ እንዳይናቸው ብሌን የሚጠብቁትን፡፡ ለውጡ — ቀሳውስትን ይሻል፤ ሑዳዴን የሚይዙለትን፡፡ ለውጡ — ሼኪዎችን ይሻል፤ ሮመዳን የሚፆሙለትን፡፡ ለውጡ — ዘማሪዎችና ዘያሪዎችን ይሻል፤ በየእምነታቸው የሚታደሙለትን፡፡ ለውጡ — ቆንጃጅትንና ጉብሎችንም ይሻል፤ ጉዞውን የሚያስቀጥሉለትን፡፡ አዋጁ ትዕዛዝ ነው፤ ማንም የማይቀርበት፡፡ ስለዚህም፣ ነጋሪቱ ይጎሰም! እንቢልታውም ይነፋ! ላዲሱ ዘመን፣ ላዲሱ ተስፋ!!!

በስደትና በእንክርት አዙሪት፣ በባዕድ አገር የምንሳቀቅበት፤ ውጡና ግቡ የማንባልበት፣ በቀቢፀ-ተስፋ ውስጥ ሆነን፣ ጉፋያ አካላችንን የሚወዘወዝበት፤ በቆዳችን ቀለምና በክሳታችን የምንለካበት፤ ሰብዓዊ ክብራችን ታውቆ፣ በምልዓት የምንገንበት፤ ያ ዘመን እንዲጀመር፣ ጎሑም ፈክቶ እንዲቀድ፤ አዋጁን አዳምጠን፣ አለብን ምላሽ መስጠት፡፡ ሥራዎችን ተከፋፍለን፤ መሪዎችን አስቀድመን፤ አማካሪዎቻችን መርጠን፤ ከሳሽና ፈራጆችን፣ አቃቤዎችንም ይዘን፤ ስንቅ አቅራቢዎቻችንን፣ አበዛዎቻችንን አውቀን፤ ቀያሾቻችንን እና ተላሚዎቻችን አደራጅተን፤ ለቃፊሮቻችንን እና ለሕገ-ደንባችን፣ ከልባችን ታዘን፤ አንጋሽና ቀዳሾችን፣ ወይዛዝርቱንም ይዘን፤ ወደማይቀረው መፃኤ-ዕድል በጋራ መሄድ አለብን፡፡ ይህ ነው፣ ምኞታችን! ይህም ነው፣ ራዕያችን! የቁም ቅዠታችንንና የቁም ሰመመናችንን፣ እንደጦስ ዕቃ ጥለን፤ ባዲስ መንፈስ፣ ባዲስ ወኔ፣ በብጽአት ተመልተን፤ ወደምሉዑ ዘመን፣ በድል መጓዝ ነው አለብን፡፡ ስለዚህም፣ እንቢልታው ይነፋ! ነጋሪቱም ይጎሰም! ድው…!!! ድም….!!! ግው-ግም!!! ግው-ግም!!!

ነጋሪቱ ሲጎሰም፤ እንቢልታውም ሲነፋ፤ ያኔ ደማችን በትክክል ይሞቃል፤ ወኔያችንም ይግላል፡፡ ለውጥ በባሕሪው፣ ደመ-ቀዝቃዛነትን ይጠላል፡፡ እንደለውጥና እንደነውጥ ያሉት ክስተቶች፣ ደመ-ቀዝቃዛነትን አጥብቀው ይንቃሉ፡፡ ረጋ ብሎ የሚያስብ እንጂ፣ ረግቶ የሚቀርን፣ ለውጣችን አይፈልግም፡፡ ስለዚህም፣ ደሙ-የሚንተከተክ፣ ወኔው የጋለ፣ ቅስሙም ያየለ፣ የብረት ቆሎ ነኝ፣ እንቢኝ! እያለ፤ የሚንተገተግ የንግግር ክህሎት ያለው፣ ጋዜጠኛና ያደባባይ ተናጋሪ፣ በእጅጉ ይፈለጋል፡፡ እጅግ ትጉህና እጅግ ብርቱ የሆኑም ሳይንቲስቶች፣ ከልክ በላይ ያስፈልጉናል፡፡ ያሸነፉትን ሕዝብ፣ በጠላትነት የማየዩ፤ ያጋዟቸውን ሕዝቦች፣ እንበቀል የማይሉ፤ በታሪክ ሕሊና ውስጥ፣ መርምረው “የሚምሩ”፤ በስነ-ምግባር የዕዝ ካምፓቸው ውስጥ፣ ደግነትን የሚያበስሩ፤ ጥላቻን ተራምደው፣ በቀልን የሚሽሩ፤ የለውጥ ሰልፈኞች፣ በሺሆች የሚቆጠሩ፤ ውለው አድረውም፣ ሚሊዮኖች የሚያፈሩ፤ ቢሊዮኖች የሚመሩ፤ ኢትዮጵያውያን ይፈለጋሉ፡፡ ዛሬውኑ-ጉዞአቸውን ያለማመንታት የሚጀምሩ፡፡ ማቄን ጨርቄን የማይሉ፤ ስንቄን ወርቄን ለለውጡ አዋጣለሁ የሚሉ፤ አሁኑኑ ይፈለጋሉ፡፡ ስለዚህም፣ ለለውጡ አዋጅ ማብሰሪያ፣ እንቢልታው ይነፋ!!! ነጋሪቱም ይጎሰም!!! ድው…!!! ድም….!!! ግው-ግም!!! ግው-ግም!!!

ኑ! ወደ አዲሱ ዘመን፣ በምልዓትና በኩራት፣ ዛሬውኑ እንትመም፡፡ ድዉ! ድም! ኑ! የዘረኝነትን እና የጎጠኝነትን ጥንባሳ፤ የሕግ-ጥሰትንና የመድሎን ነቀርሳ፤ በዕርቀ-ሰላምና በምሕረት ወላንሳ፤ ዳግም እንዳያገረሽ፣ መቼም እንዳይነሳ፤ አድርገን እንደምስሰው፣ ከምድረ-ገጽ ሐበሻ፡፡ ኑ! ባንድነት ሆነን፣ የትውልዶችን ያድሎ ሰንሰለት፣ እግረ-ሙቃችንን በጣጥሰን፤ ባልቴትና መበለቷን፣ ባለትዳር ሆነች ፈትቷን፤ ላጤም ሆነች ሳዱላ፣ ባለቡቅራሟንም ይዘን፤ ለወንዶቹ የምንሰጠውን፣ ለሴቶቹም አካፍለን፤ የጋራ ዕድላችንን፣ በጋራ እንድንወስን፤ አሁኑኑ እንቀሳቀስ፣ አሁኑኑ እንትመም….፡፡ ነጋሪቱ ይጎሰም! ይበል ድዉ! ድም! ወላጆቻቸውን በስደት፣ በበሽታና በጣዕረ-ሞት፤ የተነጠቁ ወጣቶች፣ ወላጅ አልባም ሕፃናት፤ አሳዳጊ የሌላቸውም—የእጓለ-ማውታናት፤ ሞጋሳ ሆኑ ጉዲ-ፈቻ፣ ቃልቻም ሆኑ ቦረን-ቲቻ፤ በባሕልና በቋንቋቸው፣ እኩል ወደሚማሩበት፤ ኹሉ-በኵሉኼት፣ የሆነችን የእኩል ቤት፤ በውዴታ እንድናቆም፣ በፍቃደ ሃያል ስሜት፤ መንቀሳቀስ ነው ያለብን፡፡ ስለዚህም፣ እንቢልታው ይነፋ!!! ነጋሪቱም ይጎሰም!!! ድው…!!! ድም….!!! ግው-ግም!!! ግው-ግም!!!

ይኼንን ጀብዱአችንን፣ ከስር ከስር ተከታትለው፤ ለዓለም የሚያበስሩን፤ ይኼንን ድላችንን፣ በመቅረጽ-የሚቀዱልን፣ ጋዜጠኞች፣ አርታኤዎች፣ ዘጋቢዎችና ፀሐፍት፣ ደራሲያንና ተዋንያን፣ ፀሐፌ-ተውኔቶች፣ የፊልም አዘጋጆችና የፊልም ሞያተኞች፣ አሁኑኑ ይፈለጋሉ፡፡ ሰልፈኞችን ባፍላ-ወኔ፣ በግጥምና በዜማ፣ የሚያወድሱና የሚያሞግሱ፣ የለውጥንም መንፈስ፣ ተግተው የሚቀሰቅሱ፣ ሙዚቀኞችና ዳንኪረኞች፤ ገጣሚና አዝማሪዎች፤ አሁኑኑ ይፈለጋሉ፡፡ ለለውጡ ዘፀአት፣ ጉዞ ስንጀምር፤ ሙሴና አሮንን፣ አሲዘናቸው በትር፤ ክርስቶስና ኤልያስም፣ ሲመለከቱ ወደምድር፤ ነብዩ ሞሐመድም፣ ሲፈቅዱልን ከይር፤ ያኔ እናውቀዋለን፣ መለፈፉን አዲስ ተዓምር፡፡ “አላህ”ም አልነው እግዚአብሔር፣ ነውና የዘላለም ስውር ምስጢር፤ ሰልፋችንን ተቀላቅሎ፣ ይሻገራል ወደ አልማር፤ በረከትና ረድኤትን ወደምንነሸነሽበት ሀገር፡፡ ሳንራብና ሳንጠማ፣ ሳናዝንና ሳንከፋ፤ ሳንሞትና ሳንገል፣ ሳንነሳና ሳንደፋ፤ ወደ አብርሆቱ ስፍራ፣ ወዳሰረጽነው ተስፋ፤ ልንደርስ አንችልምና፣ ከቶ አንቁረጥ ተስፋ፡፡ ስለዚህም፣ ይታወጅ የለውጥ አዋጅ!!! እንቢልታው ይነፋ!!! ይጋም — ነጋሪትም ይጎሰም፡፡ ይበል ድው…!!! ድም….!!! ብም-ብም!!! ብም-ብም!!! ድው…!!! ድም….!!! ግው-ግም!!! ግው-ግም!!!

አሁን ላለንበት ዘመን፣ አሁን ለደረስንበትም፤ ባባጣና ጎርባጣ፣ በገደልና በሰርጥም፤ በባሕርና ሸለቆ፣ በሸንተረርና ስምጥም፤ አልፈንና ተርፈን ነው፣ በጃንጥላ አልወረድንም፤ በፓራሹት አልዘለልንም፡፡ ገዢዎቻችንም በሙሉ፣ እንደመና አልወረዱም፡፡ “ስዩመ-እግዜር ነን” ያሉት ሆኑ፤ “ስዩመ-ሕዝብ ዲሞክራቶቹም”፤ ላሉት ክብር ለመብቃት፣ በፓራሹት አልዘለሉም፡፡ የጫኑትን ሃሳብ ይዘው፤ ሸንተረርና ኮረብታውን፣ እንደገመሬ ቧጠው፣ እንደፍልፈል ጉድጓድ ምሰው፣ እንደጃርትም ጭስን ታጥነው’ንጂ፤ ዩፎዎች (U.F.Os) አይደሉም፣ የፈለሱ ከማርሱ ዓለም፡፡ እንቢልታው ሲነፋ! ነጋሪቱ ሲጎሰም! ልቡ ትር-ትር ሳትል፤ ለሰልፉ ወኔው የሚግም፤ ወደ ሙሉው የአልማር ምድር፣ በክብር የሚገባ፣ በሐሴት ለመኖር፤ አሁኑኑ ይነሳ፣ ዛሬውኑ ጉዞ ይጀምር፡፡ ኃያል ሕዝቦች ሆነን፣ በአፍሪካም ሆነ በመላው ዓለም፣ ዳግም ከፍ ብለንና ገነን፣ እንድንወጣ ካስፈለገን፤ ያያት ያባቶቻችንን ሐጢያት፣ መዘክዘኩን ትተን፤ ላልተፈጸመ ታሪክ፣ ሐውልት ማቆሙን ንቀን፤ ላልተሰራውም ግፍ፣ ጣዖት ከማምለክ ታቅበን፤ ራሳችንን እንደጴጥሮስ፣ ለምስዋትነት አጭተን፤ የለውጡ አዋጅ ሲለፈፍ፣ እንቢልታው ሲነፋ፣ ነጋሪቱ ሲጎሰም፤ በጋራ እንንቀሳቀስ፤ ከቶ አንቁረጥ ተስፋ!!! ድው…!!! ድም….!!! ግው-ግም!!! ግው-ግም!!!

አዎን! እንቢልታው ይነፋ! ነጋሪቱም ይጎሰም! ትናንትና ነጋሪትና እንቢልታዎችን ሠርተናል፡፡ ዛሬ ደሞ፣ የሠራናቸውን እንቢልታዎች እንነፋቸዋለን፤ ያበጀናቸውንም ነጋሪቶችም እየጎሰምን አልማር ወደተሰኘው ምድር እንነጉዳለን፡፡ ነገም፣ ኃያል ሕዝብ ሆነን፣ በዓለም መድረክ ላይ በምልዓት እንታያለን፡፡ ኃያል ሕዝቦች ሆነን፣ እምቅ የሆነውን የራሳችንን ሀብት፣ ለቀጣይ ትውልዶቻችን በመቆጠብ፤ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል፣” ከሚል-የወደል አህያ ብሒል፤ ወጥተን እንደሰው ሰብአዊ፣ እንደ መላዕክትም አማናዊ፤ ሆነን የለውጡን አዋጅ መታዘዝ አለብን፡፡ እናም፣ እንቢልታው ይነፋ!!! ነጋሪቱም ይጎሰም!!! ይበል ድዉ! ይበል ድም! ዛሬውኑ እንነሳ! አሁኑኑ አንትመም! በዘመን ጎርፍ ውስጥ፣ ከምንሆን እርም! ይነፋ እንቢልታው! ይጎሰም ነጋሪቱ! ይበል ድዉ! ድም! ምድርና ሰማዩ በወኔ እስኪግም! ድውውውው! ግግግግግም! ምድርና ሰማዩ ዘላለም ያስገምግም! ድው…!!! ድም….!!! ግው-ግምምም!!! ግው-ግምምም!!!

የፍቅር እስከ መቃብር – ፍቅረኞች (በጥበቡ በለጠ)

የዛሬ ፅሁፌን እንዳዘጋጅ የገፋፉኝ ሁለት ነገሮች ናቸው። አንደኛው በፍቅር እስከ መቃብር ላይ ተመርኩዞ የተሠራው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ደብረማርቆስ ከተማ ላይ የተሠራው የታላቁ ደራሲ፣ ዲፕሎማትና አርበኛ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ ዓለማየሁ ሐውልት ነው።

ቴዲ አፍሮ /ቴዎድሮስ ካሣሁን/ ፍቅር እስከ መቃብርን መሠረት አድርጐ ግሩም የሆነ ሙዚቃ አቀንቅኗል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ርዕሠ ጉዳዮችን በተለይም ገፀ-ባህሪያቱን፣ ደራሲውን እና ተራኪውን ወጋየሁ ንጋቱን ሳይቀር ለዛ ባለው ሙዚቃው ሌላ ፍቅር ሰርቶላቸዋል። ፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍ በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ወደር የማይገኝለት ልቦለድ ታሪክ ነው። ፍቅር እስከ መቃብር ዘመን አይሽሬ /Eternal/ ብለን የምንጠራው የጽሑፎች ሁሉ ቁንጮ ነው። ታዲያ ወደዚህ መጽሐፍ ንባብ የገባ ሰው ሁሉ በመጽሐፉ ፍቅር ተሳስሮ እንደሚቀር ይታወቃል። ፍቅር እስከ መቃብር መፅሐፍ በውስጡ ያለው ታሪክ ሲነበብ፣ አንባቢውን ራሱ በፍቅር ወጀብ አላግቶ፣ አላግቶ የፍቅር እስረኛ የሚያደርግ ተአምረኛ መጽሐፍ ነው። ቴዲ አፍሮም በመጽሐፉ ፍቅር ወድቆ ይህን የመሰለ ግሩም ዜማ አቀነቀነ። ከራሳችን፣ ውስጣችን ካለው ታሪካችን ላይ መሠረት አድርጐ ሙዚቃ መስራቱ አንዱ ስኬቱ ነው። እንዲህ ዓይነት ግዙፍ ኢትዮጵያዊ ቅርሶችና ታሪኮች ላይ መሠረት ተደርገው የሚቀርቡ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የታዳሚን ቀልብ በቀላሉ የመውሰድ አቅም አላቸው። ከዚህ ሌላም ከያኒው ራሱ በሀገሩ ታሪክ ላይ ተመስጦ የጥበብ ስራዎቹን ማቅረቡም ምን ያህል የዕውቀት አድማሱም ሰፊ እንደሆነ ማሳያም ነው። አንድ ከያኒ የአገሩን እና የሕዝቡን ታሪክ ሲያውቅ በሕዝቡ ውስጥ ግዙፍ ሆኖ ብቅ ይላል።

ቴዲ አፍሮ ፍቅር እስከ መቃብርን ሲዘፍነው የመጀመሪያው አቀንቃኝ አይደለም። በ1995 ዓ.ም እጅጋየሁ ሽባባው /ጂጂ/ መጽሐፉን መሠረት አድርጋ “አባ ዓለም ለምኔ” የተሰኘ ውብ ዜማ አቀንቅናለች። በዚህ መጽሐፍ ላይ መሠረት አድርጐ ዜማ ማቀንቀን እንደሚቻል ያሳየች ቀዳሚት ባለቅኔ ነች።

ጂጂ ለቴዲ አፍሮ፣ የታላላቅ ርዕሠ ጉዳዮች መነቃቂያው /inspiration/ የሆነች ይመስለኛል። ምክንያቱም ፍቅር እስከ መቃብርን እርሷ 1995 ዓ.ም ተጫውታዋለች። እርሱ ደግሞ በ2009 ዓ.ም ተጫወተው። አባይን በተመለከተ ጂጂ ከ15 ዓመት በፊት አቀንቅናለች። ቴዲ አፍሮ ደግሞ በቅርቡ ተጫውቶታል። አድዋን በተመለከተ ጂጂ በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ ድንቅ አድርጋ አዜመችው። ቴዲ አፍሮ ደግሞ እርሷ ካቀነቀነች ከ13 ዓመት በኋላ አድዋን ውብ አድርጐ ሠራው። ብዙ ነገሮችን ሳይ ጂጂ የቴዲ መነቃቂያ ትመስለኛለች። እርግጥ ነው ሁለቱም አቀንቃኞች የአንድ ዘመን ወኪሎች ናቸው። እነርሱ በተፈጠሩበትና ባደጉበት አስተሳሰብ ውስጥ ነው ማቀንቀን የሚፈልጉት። የርዕሠ ጉዳይ ምርጫቸውም ተመሳስሎ ማሳየቱ ከፈለቁበት ሕዝብና አስተሳሰብ ውስጥ ይመነጫል። ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ እንዳሉት “ነበልባል ትውልድ እየመጣ ነው። ከነዚህም ውስጥ እጅጋየሁ ሽባባው /ጂጂ/ እና ቴዲ አፍሮ ናቸው። የኢትዮጵያን ሙዚቃ ባልተጠበቀ ፍጥነት ወደ ላይ አመጠቁት” ብለው ነበር። ኃይሌ ገሪማ ለጂጂ ሙዚቃ የነበራቸውን ፍቅር ሳስታውስ ወደር አላገኘሁላቸውም።

ወደ ርዕሰ ጉዳዬ ልመለስ። ፍቅር እስከ መቃብር ብዙዎችን በፍቅር የጣለ መጽሐፍ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዲፓርትመንት ውስጥ ላለፉት 50 ዓመታት የጥናትና ምርምር ፅሁፎች ሲሰሩበት የኖረ መጽሐፍ ነው። አያሌ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የድግሪ፣ የማስተርስ እና የዶክተሬት ድግሪያቸውን ለማግኘት ፍቅር እስከ መቃብር ላይ የምርምር ፅሁፎቻቸውን አቅርበዋል። ሌሎች ምሁራን ተመራማሪዎችም ፍቅር እስከ መቃብርን በልዩ ልዩ ርዕሠ ጉዳዮቹ ላይ ተመርኩዘው ጥናት ሠርተዋል። የውጭ አገር ሰዎች ሳይቀሩ መጽሐፉ ላይ ተመራምረዋል። መጽሐፉ በእንግሊዝኛ ቋንቋም ተተርጉሟል። በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ፍቅር እስከ መቃብር የአያሌዎችን ቀልብ በመሳብ ወደር አይገኝለትም። ይህን መጽሐፍ በጥናትና በምርምር ፅሁፎቻቸው ከፍ ከፍ አድርገው የሰጡን ምሁራን ሁሉ ሊታወሱ ሊመሰገኑ ይገባል።

በርዕሴ ላይ “የፍቅር እስከ መቃብር – ፍቅረኞች” ያልኩትም እነዚህን አካላት ሁሉ ለመጠቃቀስ ፈልጌ ነው። በዚህ መፅሐፍ ታሪክ ውስጥ ከሁሉም በላይ “ፍቅር” ናቸው ብዬ የማስበው ደራሲውን ክቡር ዶ/ር ሐዲስ ዓለማየሁን ነው። ይሄን የሁላችንም ፍቅር የሆነውን መጽሐፍ 1958 ዓ.ም ያበረከቱልን የደራሲነት ግዙፍ ስብዕና ሐዲስ ዓለማየሁ እፊቴ ተደቀኑ። አቤት ትዝታ! ትዝ አሉኝ።

በህይወት ዘመኔ እስካሁን በሠራሁበት የጋዜጠኝነት ሙያዬ ቃለ-መጠይቅ ካደረኩላቸው የዚህች አገር ፈርጦች መካከል በእጅጉ ደስ የሚለኝ ከእርሳቸው ዘንድ ሄጄ ስለ ብዙ ነገር ያጫወቱኝ ወቅት ነው። ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁን በ1994 ዓ.ም እና በ1995 ዓ.ም ቃለ-መጠይቅ ያደረኩላቸው ሲሆን፤ ለሦስተኛ ጊዜ ለሌላ ቃለ-መጠይቅ ቀጠሮ በያዝንበት ቀን ህይወታቸው አለፈች። ክቡር ሐዲስ ሆይ ታላቅነትዎ፣ ከሁሉም በላይ ትህትናዎን ፈፅሞ አልረሳውም።

ውድ አንባቢዎቼ፤ እስኪ አንድ ነገር እንጨዋወት። በዚሁ መፅሐፍ ውስጥ ሦስቱን ዋና ዋና ገፀ-ባህሪያት አስቧቸው። ሰብለ ወንጌልን፣ በዛብህን እና ጉዳ ካሣን። እነዚህ ሦስት ገፀ-ባህሪያት አንድም ሦስትም ናቸው። አንድ የሚያደርጋቸው፣ ባሰቡት አቋማቸው፣ ለወደዱት ጉዳይ ፍፁም ራሳቸውን መስጠታቸው፣ በፍቅርና በዓላማ ተገማምደው እስከ ወዲያኛው ማለፋቸው፣ በአንድ ጉድጓድ መቀበራቸው አንድ ያደርጋቸዋል። ፍቅር እስከ መቃብሩም እሱ ነው። ሦስት የሚያደርጋቸው ደግሞ ሦስቱም ከየራሳቸው የኋላ ማንነት እና ተፈጥሮ አመጣጣቸው የተለያየ መሆኑ ነው። እነዚህ ከሦስት ማንነት ውስጥ የወጡ የሐዲስ ዓለማየሁ ፍጡሮች የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፍ ዋልታና ማገር ሆነው እነሆ 50 ዓመታት ሙሉ ተገዳዳሪ ሳይኖርባቸው ብቻቸውን ውብ ሆነው እንዳማረባቸው አሉ።

ሰብለና በዛብህ በሁለት ሰብአዊያን መካከል የሚንበለበል የፍቅር እቶን ውስጥ የተቀጣጠሉ ቢሆንም ከዚያ ባለፈ ደግሞ የሁለት ዓለም ሰዎችን ወክለው የአንድን ማኅበረሰብ አወቃቀር የሚያሳዩ ናቸው። ሰብለ ከባላባት ወገን፣ በዛብህ ከአነስተኛው ማኅበረሰብ ክፍል። የነዚህ ሁለት ዓለም ሰዎች ፍቅር ውስጥ የሚመጣ ጉድ የተባለ ግጭት ፍጭት አለ። እናም ሐዲስ ዓለማየሁ ያንን የማኅበረሰብ አወቃቀር ልዩነትና አንድነት ሊያሳዩን ፍቅር ፈጠሩ። በፍቅር ውስጥ ያለ ማኅበረሰባዊ እቶን ሲፈነዳ ሲቀጣጠል አሳዩን። ጉዱ ካሣ የተባለ ጉድ ፈጥረውም ማኅበረሰቡን የሚያርቅ፣ የሚተች፣ የሚያሄስ፣ ችግሩን ነቅሶ የሚያሳይ እና መፍትሄ የሚሰጥ የሊቆች ሊቅ ወለዱ። የጐጃሙ ዲማ ጊዮርጊስ የቅኔ ዩኒቨርሲቲ ያፈራው ጉዱ ካሣ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ፣ በሥርዓት እንድትገነባ እንዲህ ብሎ ነበር፡-

“የማኅበራችን አቁዋም የተሰራበት ሥርዓተ-ልምድ፣ ወጉ ሕጉ እንደ ሕይወታዊ ሥርዓተ-ማሕበር ሳይሆን ህይወት እንደሌለው የድንጋይ ካብ አንዱ በአንዱ ላይ ተደራርቦ የላይኛው የታችኛውን ተጭኖ፣ የታችኛው የላይኛውን ተሸክሞ እንዲኖር የተሰራ በመሆኑ ከጊዜ ብዛት የታችኛው ማፈንገጡ ስለማይቀርና ይህ ሳይሆን ህንፃው በሙሉ እንዳይፈርስ እንደገና ተሻሽሎ ሰውን ከድንጋይ በተሻለ መልክ የሚያሳይ የህያውያን አቁዋም ማኅበር እንዲሰራ ያስፈልጋል።”

/ፍቅር እስከ መቃብር፤ ገፅ 122/

ለመሆኑ እንደ ጉዱ ካሣ አይነት ማኅበረሰባዊ ፈላስፋ አለን ወይ? አንዱ ሌላውን ተጭኖ መኖር እንደሌለበት የሚነግረን። አንዱ ሌላኛውን ከተጫነ ከጊዜ ብዛት የታችኛው እምቢ ብሎ ይወጣል። የታችኛው ሲወጣ ካቡ ይፈርሳል፤ ሀገር ይፈርሳል እያለ በውብ ምሳሌ ኢትዮጵያን የሚያስተምር የዲማ ጊዮርጊሱ ጉዱ ካሣ ጠቢብ ነበር።

እናም ሐዲስ ዓለማየሁ እንዲህ አይነቶቹን ገፀ-ባህሪያት ፈጥረው፣ የፍቅር ልቦለድ የሆነ መነፅር ሰክተውላቸው ኢትዮጵያን እንድናያት፣ እንድንመረምራት እና የሚያስፈልጋትን ሥርዓት እንድንገነባላት እኚህ ጉደኛ ደራሲ ከ50 ዓመታት በፊት በውብ ድርሰታቸው ነግረውናል። ማን ይስማ!?

1994 ዓ.ም እቤታቸው ሄጄ ቃለ-መጠይቅ ሳደርግላቸው በውስጤ ብዙ ነገር ተመላለሰብኝ። ፍቅር እስከ መቃብር። በዛብህ ሞተ። ሰብለ ከበዛብህ ሌላ ፈፅሞ መኖር አትፈልግም። መነኮሰች። ቆብ ጫነች። እሷም ሞተች። አጐቷ ያ ታላቅ ፈላስፋ ለዕውነት ብሎ የኖረና የሞተው ጉዱ ካሣም ተቀላቀላቸው። እነዚህን ገፀ-ባህሪያት የፈጠሩት ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ እድሜና ጤና ተጫጭኗቸው በተንጣለለው ሳሎናቸው ውስጥ በተዘረጋው የማረፊያ አልጋ ላይ ጋደም ብለዋል። ትክ ብዬ አየኋቸው። ፍፁም ትህትና፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የመቅረብ ተፈጥሯቸው ይሄው እፊቴ ላይ ዛሬም አለ። ይታየኛል።

ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ባለቤታቸው ወ/ሮ ክበበፀሐይ ከሞቱ በኋላ ምንም ዓይነት ትዳር አልመሰረቱም። ብቻቸውን ከቤተሰባቸው ጋር ነው የሚኖሩት። ሳያገቡ፣ የአብራካቸውን ክፋይ ሳያዩ አረጁ። ደከሙ። እናም ገረመኝ። ግን ጠየኳቸው። “ጋሽ ሐዲስ፤ ባለቤትዎ ወ/ሮ ክበበፀሐይ ካረፉ በጣም ረጅም ዓመታት ተቆጠሩ። በነዚህ ዓመታት ግን እርስዎ ምንም ዓይነት ሌላ ትዳር አልመሰረቱም። ይህ ለምን ሆነ? ምክንያትዎ ምንድን ነው?” አልኳቸው።

ጋሽ ሐዲስ የግራ እጃቸውን ከፍ አደረጉልኝ። እጃቸው ላይ ቀለበት አለ። ግራ ስጋባ እንዲህ አሉኝ። ይህን ቀለበት ያሰረችልኝ ክበበፀሐይ ነች። እኔም ለእሷ አስሬያለሁ። እሷ ድንገት አረፈች። እዚህ ጣቴ ላይ ያለው እሷ ያሰረችልኝ ቀለበት ነው። ቀለበቱን አልፈታችውም። ሳትፈታው አረፈች። ስለዚህ ይህን ቀለበት ከኔ ጣት ላይ ማን ያውልቀው? ካለ እሷ፣ ካለ ክበበፀሐይ ይህን ቀለበት ከጣቴ ላይ የሚፈታው የለም አሉኝ።

ለመሆኑ ከዚህ በላይ ፍቅር እስከ መቃብር አለ ወይ? ሐዲስ ዓለማየሁ ማለት የፍቅር እስከ መቃብር መፅሐፍ ዕውነተኛ ገፀ-ባህሪ ነበሩ። የፃፉትን ልቦለድ በእውናቸው የኖሩ የፍቅር አባት ናቸው። ሰብለወንጌል፣ በዛብህ እና ጉዱ ካሣ ማለት ሐዲስ ዓለማየሁ ናቸው። ፍቅርን ፅፈው ብቻ ሳይሆን ኖረውት ያለፉ እውናዊ ፍጡር! ጋሽ ሐዲስ፤ አቤት የስብዕናዎ ግዝፈት! እንዴት አድረጌ ልግለፀው?

የፍቅር እስከ መቃብር ፍቅረኞች በጣም ብዙ ናቸው። በዋናነት ራሳቸው ሐዲስ ዓለማየሁ ናቸው። ሌላው ይህን ታሪክ በጥብጦ ያጠጣን ተራኪው ወጋየሁ ንጋቱ ነው። መፅሐፉ ላይ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ሊቃውንትም የመፅሐፉ ፍቅረኞች ናቸው። ጂጂ እና ቴዲ አፍሮም በመፅሐፉ ፍቅር ወድቀው እኛንም ጣሉን። ፍቅረኛው በጣም ብዙ ነው።

የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሁፍ ጣሪያውን ያሳዩን ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ደብረ-ማርቆስ ከተማ ላይ ሐውልታቸው ከሰሞኑ ቆመ። ምስጋና ለደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ! ይህች ደብረማርቆስ ሌላ እጅግ አስደናቂ ደራሲም ወልዳለች። ተመስገን ገብሬ ይባላል። በብዕሩም ሆነ በዕውቀቱ በዘመኑ ሊቅ የነበረ አርበኛ ነው። ተመስገንን ስጠራ ዮፍታሔ ንጉሴ መጣብኝ። ባለቅኔው፣ ተወርዋሪ ኮከቡ ዮፍታሔ ከዝህቺው ደብረማርቆስ ዙሪያ ሙዛ ኤልያስ ተወልዶ ያደገ የዚህች አገር የቴአትር፣ የመዝሙር፣ የግጥም ሊቅ የሆነ አርበኛ ነው። መላኩ በጐ ሰው የተባለ ልክ እንደ ዮፍታሄ ገናና የነበረ ሊቅም ከደብረማርቆስ ወጥቷል። የዛሬው ትውልድም ሐውልት ብቻ የሚሰራ እንዳይሆን የነዚህን ታላላቅ ሰብዕናዎች ማንነት መከተል ይገባዋል።

በትውልድ ውስጥ እየተቀጣጠለ የሚሄድ ፍቅር የሰጡን ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ በሙዚቃው ጂጂን እና ቴዲ አፍሮን ቀልብ ወስደው ዛሬም እንደ አዲስ ፍቅር እስከ መቃብር ያሰኙናል። አቶ ሐዲስ ከአርበኝነቱ እና ከደራሲነቱ ባሻገር የሰሩትን መልካም ነገር ላስተዋውቅና የዛሬ ጽሁፌን ላብቃ።

ሐዲስ ዓለማየሁ በድርሰት ስራዎቻቸው በኢትዮጵያዊን ዘንድ እጅግ ጎልተው ወጡ እንጂ መተዳደሪያቸው የመንግስት ስራ ነው። የኢትዮጵያን መንግስት በአምባሳደርነት እና በሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው። ከኢጣሊያ ወረራ በኋላ በተቋቋመችው ኢትዮጵያ ማለትም ከ1937 ዓ.ም እስከ 1938 ዓ.ም ድረስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ አምባሳደር ነበሩ። ቀጥሎም በአሜሪካን ሐገር በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ሌጋሲዮን ውስጥ ከራስ እምሩ ጋር ሆነው በአምባሳደርነት ለአራት ዓመታት ሰርተዋል። ኒውዮርክ ውስጥም የኢትዮጵያ አምባሳደር ነበሩ። ቀጥሎም ከኒውዮርክ መልስ ማለትም ከ1953-1958 ዓ.ም በለንደን እና በኔዘርላንድስ ውስጥ አገልግለዋል። ስለዚህ ሐዲስ በዋነኛነት አምባሳደር ነበሩ። በዚህ የአምባሳደርነት ስራቸው ደግሞ የዋሉትን ውለታ ዛሬ እንዘክረዋለን።

የፊታችን ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም 54ኛ ዓመቱን የሚያከብረው የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫው ኢትዮጵያ እንደሆነ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። ለዚህም ደግሞ በተከታታይ የመጡት የኢትዮጵያ መሪዎች አስተዋፅኦም ከፍተኛ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ከመመስረቱ አራት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ነው። ይህ መ/ቤት ታህሳስ 20 ቀን 1951 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ተቋቋመ /ተመሰረተ/።

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እንደ ዋነኛ ዓላማ አፍሪካን ለማጠንከርና ለማጎልበት ኢኮኖሚ ወሳኝ በመሆኑ በጋራ ትስስር ሐገሮች ወደ አንድ አህጉራዊ ህልም መምጣትን የሚያመቻች ተቋም ሆኖ አገልግሏል። ይህም የአፍሪካ ሐገሮች በጋራ ለሚያቋቁሙት የአፍሪካ ሕብረት እንደ መሰረታዊ የመአዘን ድንጋይ ሆኖ አስተዋፅኦ አድርጓል። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሆን የደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር የሕይወት ታሪካቸው ያወሳል።

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከመቋቋሙ በፊት ሐዲስ ዓለማየሁ ኒውዮርክ ውስጥ በአምባሳደርነት ይሰሩ ነበር። እዚያ ሆነው አንድ ነገር አሰቡ። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲመሰረት። ይህን ሃሳባቸውን ለንጉሥ ኃይለስላሴ ፃፉ። በወቅቱ ንጉሡ በጉዳዩ ወዲያውኑ አልተስማሙም ነበር። ሐዲስ ዓለማየሁም ስለ ጉዳዩ ጠቀሜታነት በተከታታይ ደብዳቤ ይፅፉላቸው ነበር።

 

ንጉሥ ኃይለሥላሴ ለምን ወዲያው ሀሳቡን አልተቀበሉትም? አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ውስጥ ከሆነ የበርካታ ሐገር ዜጎችም አዲስ አበባ ውስጥ የስራ ቦታቸው ይሆናል። በዚህ የተነሳ ሁሉንም የሚታዘብ የውጭ ተመልካች ይመጣብናል። ስለዚህ እንቅስቃሴያችን ሁሉ ይፋ ይሆናል። ይሔ ደግሞ ለመንግስት ስርዓት አመቺ አይሆንም በሚል ምክንያት እንደሆነ ይገልፃሉ። በኋላ ግን በአዲስ አበባ ውስጥ እንዲቋቋም ጃንሆይ ፈቀዱ።

ዓፄ ኃይለሥላሴ ከመስማማታቸው በፊት ግን አራት ሐገሮች ጽ/ቤቱ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር። ከእርሳቸው ለአንደኛቸው ሊሰጥ በጥናት ላይ ነበር። በኋላ ኢትዮጵያ ስትጠይቅ ተሰጣት። እንዴት ተሰጣት የሚለውም ሌላው ጥያቄ ነበር።

እንደ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ገለፃ ኢትዮጵያ ጽ/ቤቱ እንዲሰጣት ያደረገችው በዘዴ ነው። ጉዳዩ እንዲህ ነው። ጽ/ቤቱን ገንዘብ አውጥቶ በቋሚነት የሚሰራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነው። የሀገሮች ምላሽ ደግሞ ለጽ/ቤቱ መስሪያ የሚሆን ቦታ መስጠት ብቻ ነው። ሐገሮቹ የመስሪያውን ገንዘብ አያወጡም። ኢትዮጵያ ዘግይታ ጥያቄውን ስታቀርብ ግን አንድ መላ ቀይሳ ነበር። ይህም ቦታውን በነፃ እሰጣለሁ፤ የሕንፃውን ማሰሪያ ወጪም እራሴው እችላለሁ። የተባበሩት መንግሥታት ገንዘቡን አያወጣም አለች። በዚህ ምክንያት ከኋላ የመጣችው ኢትዮጵያ የጽ/ቤቱ ምስረታን በአሸናፊነት ተቀበለች። ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁም በሕይወት ዘመናቸው እጅግ ደስ ያላቸው የዚያን ቀን ነው። ምክንያቱም ከበስተኋላ ሆነው የዚህ ሐሳብ ጠንሳሽም ግፊት አድራጊም እርሳቸው ስለነበሩ ነው።

ዛሬም ከአዲስ አበባ ከተማ ውብ ሕንጻዎች መካከል አንዱ የሆነው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ጽ/ቤት የተመደበው ቦታ 26ሺ ሜትር ካሬ ነው። ስለዚሁ ኪነ-ሕንፃ አሰራር አቶ በሪሁን ከበደ በፃፉት መጽሐፍ እንዲህ ይላሉ¸

ሕንጻው የተለያዩ ክፍሎች አሉት። አንድ የጉባኤ አዳራሽ ፣ የኮሚቴ መሰብሰቢያዎች፣ ስድስት ክፍሎች ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሲዮን ሠራተኞችና ከዚህ ኮሚሲዮን ጋር የሥራ ግንኙነት ላላቸው ለኢትዮጵያ መንግሥት ለጽ/ቤቶች የሚያገለግሉ 140 ክፍሎች፣ ከነዚህ ሌላ ለባንክ፣ ለፖስታ፣ ለቴሌግራፍና ለአየር መንገድ የሚያገለግሉ ክፍሎች አሉት። ዋናው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የዝግጅቱ ፕላን ለሊቀ መናብርቶቹ የመቀመጫዎች ብዛት 8 ለዋና መልዕክተኞች 86፣ ለመልዕክተኞች 168፣ ለታዛቢዎችና ለልዩ ልዩ ወኪሎች 58፣ ለፀሐፊዎች 16፣ ለተርጓሚዎችና ለኦፕሬተሮች 16፣ ለልዩ ልዩ እንግዶች 37፣ ለጋዜጠኞች 106፣ ለተመልካች ሕዝብ 220 በድምሩ 715 መቀመጫዎችን የያዘ ነው።

 

ይህን ለመስራት የወሰደው ጊዜ 18 ወር ብቻ ሲሆን የጨረሰውም ገንዘብ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ብር እንደሆነ አቶ በሪሁን ከበደ “የአፄ ኃይለስላሴ ታሪክ” በተሰኘው መጽሀፋቸው በገፅ 470 ውስጥ ገልፀዋል። በፅሁፋቸው ውስጥ እንዳብራሩት የጉባኤው አዳራሽ የተቀመጠበት ቦታ 3ሺ 600 ሜትር ካሬ፣ ለጽ/ቤቶቹና ለስድስቱ ኮሚቴዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ ስድስት ክፍል የፈጀው ቦታ 5500 ሜትር ካሬ፣ ለባንክ፣ ለፖስታ ቤት፣ ለቴሌግራፍና ለአየር መንገድ መ/ቤት የተሰራበት ቦታ 4500 ሜትር ካሬ እንደሆነ ጽሁፉ ያስረዳል።

ይህን ትልቅ ስራ ያከናወነችው ኢትዮጵያ ናት። ከበስተጀርባ ሆነው ታላቁን ሕልም እውን ያደረጉት ደግሞ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ናቸው። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ታህሳስ 20 ቀን 1951 ዓ.ም ተከፈተ።

ያ ወቅት ለብዙ የአፍሪካ ሐገሮች ጨለማ ነበር። ምክንያቱም ከቅኝ አገዛዝ ገና አልወጡም። በመከራ ውስጥ የሚዳክሩበት ነው። ከነርሱ ውስጥ ዘጠኝ ሀገሮች ብቻ ነፃ ወጥተው ነበር። እነርሱም

1-  ኢትዮጵያ፣

2-  ላይቤሪያ፣

3-   የተባበሩት አረብ ሪፐብሊክ (ግብፅ) ፣

4-   ሊቢያ፣

5-   ሱዳን፣

6-   ሞሮኮ፣

7-   ቱኒዚያ፣

8-   ጋና፣

9-   ጊኒ ነበሩ።

 

ለነዚህ ዘጠኝ ሀገራት የምታበራይቱ ፀሐይ ለሌሎም በቅኝ ግዛት ስር ለሚዳክሩት እንድታበራ ትግላቸውን ቀጠሉ። ሀገሮች ነፃ መውጣት ጀመሩ። ተበራከቱ። አፍሪካ ከባርነት ነፃ የወጣች አዲስ አህጉር ሆነች። ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ.ም ላይ ነፃ የወጡ 32 የአፍሪካ ሐገሮች አዲስ አበባ ላይ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን አቋቋሙ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከዚህም አልፎ የብዙ አስተሳሰቦችና ፍልስፍናዎችም ድምር ውጤት ነው።

 

ለምሳሌ የፓን አፍሪካኒዝም ፍልስፍናዎችን የሚያራምዱ እነ ማርክስ ጋርቬይ፣ ኢትዮጵያዊው የህክምና ሊቅ ዶክተር መላኩ በያን እና ሌሎም ከ1920ዎቹ ጀምሮ የሚያቀነቅኗቸው አስተሳሰቦች እየሰፉ መጥተው የደረሱበት ደረጃ ነው። የአፍሪካ ህብረት! ጉዞው ገና ይቀጥላል። ፓን አፍሪካኒዝም ይመጣል። “United States of Africa” ይመጣል ተብሎም ይጠበቃል።

 

እነ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ሀሳቡ ጽንስ እንዲሆን አድርገዋል። ፅንሱም ተወልዶ እያደገ ነው። በ50 ዓመታት ውስጥ ሁሉም የአፍሪካ ሐገሮች ከቅኝ አገዛዝ ስርዓት ወጥተዋል። ቀጥሎም ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ፖለቲካቸውን፣ ኢኮኖሚያቸውን እያስተሳሰሩ መሔድ እንዳለባቸውም አውቀዋል።

 

የአፍሪካ ሐገሮች ትልልቅ ህልሞችን አልመው ነበር። ለምሳሌ በ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ለ25 ዓመታት የሚቆይ ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴሮቻቸው በኩል አቅደው ነበር። ይህም መሐይምነት ከአፍሪካ ምድር በ25 ዓመት ውስጥ እንዲጠፋ። ምክንያቱም በቅኝ የመገዛቱ አንዱ ምክንያት መሐይምነት ስለሆነ ነው። ግን ይሄ የ25 ዓመታት እቅድ አሁንስ እምን ደረጃ ላይ ነው ብሎ ማየት ከአፍሪካ ሐገራት ይጠበቃል።

 

ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ግን ለንጉሥ ኃይለሥላሴ እዲህ አሏቸው፡- መሐይምነትን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የትምህርት ሚኒስቴር በጀት በጣም ትንሽ ነው። መጨመር አለበት እያሉ በጣም ተከራከሩ። ሳይጨመርም ቀረ። በወቅቱ ሐዲስ የትምህርት ሚኒስቴር ነበሩ። በጀቱ አልስተካከል ሲል ሐዲስ ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ። በኋላም ወደ ለንደን አምባሳደር ሆነው ተላኩ። ሐዲስ ከሄዱ በኋላ የጠየቁት በጀት ተለቆ ነበር። የሚገርም ነው።

አፍሪካ የብዙ ነገሮች ሀብት ባለቤት ነች። ይህን ሐብቷን ተጠቅማ የበለፀገች አህጉር እንድትሆን የህብረቱ ትልቅ የቤት ሥራ ነው። ደራሲ ሐዲስም ከአስር ዓመታት በፊት እንደገለፁት ትምህርት ላይ ብዙ መስራት ተገቢ ነው።

በድርሰቶቻቸው የምናውቃቸው እኚህ ደራሲ ታላቅ ዲፕሎማት እንደነበሩ በጥቂቱም ቢሆን የዛሬው ፅሁፌ ያስረዳል። ሐዲስ ዓለማየሁ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። ከዚያም በምክትል ሚኒስትርነት ማዕረግ ሰርተዋል። በአምባሳደርነት አገልግለዋል። ግን አነሳሳቸው ከቆሎ ተማሪነት፣ ወደ መምህርትን፣ ከመምህርነት ወደ የቴአትር ፀሐፊነት፣ ከፀሐፊነት ወደ አርበኝነት ከአርበኝነት ወደ ዲፕሎማትነት እና ታላቅ ደራሲነት የመጡ ናቸው።

 

በድርስት ዓለም ውስጥ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ፅፈዋል። ለምሳሌ

1.  የትምህርትና የተማሪ ቤት ትርጉም 1948 ዓ.ም

2.  ፍቅር እስከ መቃብር ልቦለድ ታሪክ 1958 ዓ.ም

3.  ወንጀለኛው ዳኛ (ልቦለድ) 1974 ዓ.ም

4.  የእልምዣት (ልቦለድ) 1980 ዓ.ም

5.  ትዝታ 1985 ዓ.ም

 

ከነዚህም ሌላ ኢትዮጵያ ምን አይነት ስርዓት እንደሚያስፈልጋት እና ልዩ ልዩ ቴአትሮችን ከሰላሳ ዓመታት በፊት ሲፅፉ ኖረዋል።

እኚህ ደራሲና ዲፕሎማት በኢጣሊያ ወረራ ዘመን በአርበኝነት ሲታገሉ በፋሽስቶች ተማርከው ወደ ኢጣሊያ ሀገር ተግዘው ታስረዋል። ጣሊያን እስር ቤት ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያ ከፋሽስቶች ወረራ ተላቀቀች። ግን ሐዲስ ከእስር አልተፈቱም ነበር። ሐገራቸውና ህዝባቸው ነፃ ሲወጡ ሐዲስ ገና ነፃ አልወጡም ነበር። በኋላ እንግሊዞች ጣሊያንን ሲወሩ ሐዲስ ዓለማየሁን እና ጓደኞቻቸውን እስር ቤት አግኝተዋቸው ለቀቋቸው። ወደ ሐገራቸው መጥተው የዲፕሎማትነት እና የደራሲነት ስራቸውንም የቀጠሉት ከዚህ በኋላ ነበር።

 

ሐዲስ ዓለማየሁ ከትንሽ ተነስተው ትልቅ ቦታ የደረሱ የትውልድ ተምሳሌት ናቸው። “አባታቸው አለማየሁ ሰለሞን ከጎጃም ክፍለ ሐገር መተከል ወረዳ ኤልያስ ከተባለ የትውልድ አምባቸው ተነስተው ወደ ጎዛምን ወረዳ እንዶደም ኪዳምህረት ድንገት አቀኑ። በዚያው ከወ/ሮ ደስታ ዓለሙ ጋር ተገናኙ። ወ/ሮ ደስታ እንዶዳም ተወልደው፣ እንዶዳም አድገው፣ በኋልም ለወግ ማዕረግ በቅተዋል። ከአቶ ዓለማየሁ ሰለሞን ጋር ትዳር የመሰረቱት በዚሁ ቦታ ነው። በትዳራቸውም ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም የበኩር ልጃቸውን ሐዲስን ወለዱ” ብዙም አብረው ሳይቆዩ ተለያዩ፡ ፈጣሪ ያገናኛቸው ታላቁን ደራሲና ዲፕሎማቱን ሐዲስ ዓለማየሁን እንዲወልዱ ብቻ ነበር። እንኳንም ወለዱት!

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 1951 ተመስርቶ፣ ከዚያም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 1955 ዓ.ም እንዲመጣ ብዙ ውለታ ውለዋል። ዛሬ ሐዲስን የጠቀስነው ከዚሁ አምድ ጋር የተገናኘ በመሆኑ ብቻ ነው። ለምሳሌ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ታህሳስ 20 ቀን 1951 ዓ.ም የተመሰረተ እለት ጉባኤውን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ የተመረጡት ክቡር አቶ አበበ ረታ ናቸው። በኋላ ደርግ የረሸናቸው ሰው ናቸው። ስለ እርሳቸውም ምንም አልተባለም። ሌሎችም ነበሩ። እነ ከተማ ይፍሩ፣ እነ ክፍሌ ወዳጆ እና ሌሎችም።

ደራሲ ሐዲስ አለማየሁ ኢትዮጵያ ምርጥ ደራሲዎችሽን ጥሪ ስትባል ከፊት የሚሰለፉ፣ ኢትዮጵያ ምርጥ ዲፕሎማቶችሽን ጥሪ ብትባል ከፊት የሚመጡ፣ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞችሽን ጥሪ ብትባል ከነግርማ ሞገሳቸው ብቅ የሚሉ የታላላቅ ሰብዕናዎች ባለቤት ነበሩ። ግን ጭንቅ የሚለኝ አንድ ነገር አለ። እንደነ ሐዲስ አለማየሁ አይነት ሰዎችን እያፈራን ነው ወይ? ኢትዮጵያ ሆይ እንደነ ሐዲስ አለማየሁ አይነት ሰዎችን ውለጂ፣ ማህፀንሽም የተባረከ ይሁን።