ታጋይ ዘመነ ካሴ ለህክምና ከኤርትራ መውጣቱ ተዘገበ

 

(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግምቦት 7 ታዋቂ ታጋይ የሆነው ዘመነ ካሴ ለህክምና ከኤርትራ መውጣቱ ተዘገበ:: ታጋዩ ለረዥም ጊዜ በሕይወት አለ ወይስ የለም? በሚል በሶሻል ሚዲያ ሲያጨቃጭቅ ቆይቷል::

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የታጋይ ዘመነ ካሴን መውጣት ይዘግብ እንጂ የት ሃገር እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አልታወቀም:: ዘ-ሐበሻ ቀደም ሲል ለታጋይ ዘመነ ካሴ የውጭ ህክምና እየተሞከረለት እንደሆነና ወይ አሜሪካ ወይ አውሮፓ እንደሚሄድ መዘገቧ አይዘነጋም::

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች በየሄዱበት ከተሞች የታጋይ ዘመነ ካሴን ሁኔታ ሲጠየቁ ቆይተዋል:: ከነዚም መካከል የአርበኞቹ አመራር አባል የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ በሚኒሶታ ለቀረበላቸው ጥያቄ ታጋዩ ህክምና እንደሚያስፈልገውና በሕይወት እንዳለ መናገራቸውንና ይህንንም ቭዲዮ ዘሐበሻ ማስተናገዷ አይዘነጋም:: (https://www.youtube.com/watch?v=zzInIQNqnlc)

ሙሉቀን በዘገባው “የወንድማችን የአርበኛ ዘመነ ካሤ ጉዳይ አሳስቧችሁ በተለያየ መንገድ ከኤርትራ ወጥቶ ሕክምና እንዲያገኝ ብዙ ስትደክሙና ስታስቡ የነበራችሁ ወገኖች ዘመነ በአሁኑ ሰዐት ከኤርትራ መውጣቱን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን፡፡ ሆኖም ዘመነ ካሤ አሁንም ድጋፍ ያስፈልገዋል፤ እንዴትና በምን መልኩ መደገፍ እንዳለበት በዝርዝር እናሳውቃለን፡፡ ለዘመነ መሠረታዊ ወጭዎችና ከኤርትራ እንዲወጣ በገንዘብ ድጋፍ ያደረጋችሁልንን ወገኖች ከልብ እናመሰግናለን፡፡” ብሏል::

ስለ ታጋይ ዘመነ ካሴ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኘን እናካፍላችኋለን::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s