የቀድሞው የብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋች ሻወር ውስጥ ወድቆ ተገኘ ሕይወቱ አለፈ

ከጌጡ ተመስገን

የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች አሰግድ ተስፋዬ ዛሬ ከጨዋታ በኋላ ወደ መታጠቢያ ክፍል አመራ። ይሁንና በመታጠቢያ ቤት ወድቆ ሕይወቱ አልፏል።
በአያት ሆስፒታል ሕይወቱን ለማትረፍ የተደረገው መረባረብ አልተሳካም።
አሴ ልስልሱ
አንጀት አርሱ !
የተባሉለት እነዚያ ውብ የጥበብ እግሮቹስ? … ኳስ አቁመህ እንኳን ኳስ የሚያምርብህ ጀግና ነበርክ። በኢትዮዽያ እግር ኳስ በስነ ምግባሩ የተቃራኒ ደጋፊዎች እና ተጨዎቾች ሳይቀሩ ይመሰክሩለታል።
ትሁት፣ አክባሪ፣ ተግባቢና የእግር ኳሱ እድገት የሚያሳስበው ሰው ነበር። ከድሬዳዎ የተገኘው አመለ ሸጋው አሰግድ ተስፋዬ፤ ለትውልድ ከተማው ድሬዳዋ ኮካ ኮላ፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለኢትዮዽያ መድን፣ ለኢትዮዽያ ቡናና ለብሔራዊ ቡድን ተጫውቷል።
ከወርቃማ የተጫዋችነት ዘመን ባለፈ በቅርቡ የታዳጊዎች አካዳሚ ከፍቶ ብዙ ተስፈኞችን እያሰለጠነ ነበር።
አሰግድ ተስፋዬ፤ (ሮማሪዮ/ ዢሬስ) የኢትዮጵያ እግር ኳስን በሀዘን የሚሸብብ፣ እግር ኳስ አፍቃሪውን የሚያስለቅስ አሳዛኝ መርዶ ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s