”የበላይነት የለም” – የሕወሓቶች ድንቁርና መልዕክት | ከመሳይ መኮንን


ከመሳይ መኮንን

የህወሀት ሰዎች አሁንም ”የበላይነት የለም” የድንቁርና መልዕክታቸውን እያሰተጋቡት ነው። አንድ ነገር ከሌለ የለም ነው። አለ የተባለው የምርም ስላለ፡ መደበቅ የማይቻል ስለሆነ ነው። የበላይነቱ ደግሞ ወደስነልቦና ደረጃ ከፍ ብሎ ”ትግራዋይነት” ከህግም በላይ ሆኖ የማያስጠይቅበት ዘመን ላይ ለመድረሳችን ሺ አስረጂዎችን በማቅረብ ማሳየት ይቻላል። የክበበው ገዳ ሸምሱ የቀልድ ክሊፕ ላይ የገብረመድህን ገጸ ባህሪ ዕውነታውን ያንጸባርቃል። ክበበው ያንን የገሀዱ ዓለም ነጸብራቅ በኮሜዲ መልክ ያቀረበው ‘ጽንፈኛ’ ስለሆነ አይደለም። አንድ ሰው እንዳጫወተኝ የኢትዮጵያ ሹፌሮች ትራፊክ ሲይዛቸው የትግርኛ ሙዚቃ ይከፍታሉ። ትራፊኩ ያን ሲሰማ እጅ ባይነሳም ክስ የሚባል ነገር አይሞክራትም። የበላይነቱን ሹፌሮቹም፡ ትራፊክ ፖሊሱም የሚያውቁት ብቻ ሳይሆን የሚኖሩበት መራር ሀቅ ነው። ሰሞኑን አንድ የህወሀት ጋዜጠኛ፡ ደብረጺዮን የሚባል ድፍን ያለ፡ ለዛ የሌለው ደረቅ ባለስልጣንን ያናገረበትን ቃለመጠይቅ፡ ወደላይ እየገፋኝ ቢሆንም አዳመጥኩት። የሰውዬው ነገር ያው የታወቀ ነው። ግግም ያለ፡ ከጀርባው በቆመው የጦር መሳሪያ ልቡ ያለመጥን ያበጠ፡ የመንደር ጎረምሳ ባህሪ የተጠናወተው ነው። በጣም ይቀፋል። የሚከተለውን የፖለቲካ መስመር ስለማልደግፈው ብቻ አይደለም። በቃ! ድንቁርናን ዕወቀት አድርጎ እየተኮፈሰ፡ የለበጣ ፈገግታ ሳይለየው 1 ሰዓት ሙሉ የሚያወራ ሰው ስለሆነ ነው። ቁጭ ብሎ ሲያወራ ጡጦ ላልጣለ ህጻን የሚናገረው ተረት እንጂ ያለአቅሙ ለተሸከመው ስልጣን የሚመጥን አይደለም። የሚጠይቀው ‘ጋዜጠኛ’ም የትግራይ የበላይነቱን ”የጽንፈኞች” መዝሙር አድርጎት እየደጋገመ ሲጠይቅ ሰማሁት። አልገረመኝም።

ለማንኛውም ይህን የተበላ ዕቁብ ደግመው ደጋግመው ያነሱታል። ውሸት ሲደጋገም ዕውነት ይሆናል የሚለውን የጆሴፍ ጎብልስን መመሪያ ይወዱታል። ”ኢህአዴግ የትግራይ የበላይነት የለም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ስለዚህ በቃ…. ከእንግዲህ የለም” ይሉሃል እየተመላለሱ። የበላይነቱ በአዋጅና በነጋሪት ጉሰማ የሚጠፋ ይመስል?! ህወሀት በጉባዔ፡ በግምገማ፡ በስብሰባ፡ በኮንፈረንስ፡ በሲምፖዚየም ጋጋታ የሚያጠፋው መስሎት ነጋ ጠባ ”የበላይነት” የለም ቢልም የሚጠፋ ዕውነታ አይሆንም። መሬት የረገጠ፡ ለ26 ዓመታት ከኢትዮጵያውያን ጋር የከረመ፡ ይሄ ስርዓት እስካለ ድረስ የሚቀጥል ሀቅ ነው። የስነልቦናው ጉዳይም ወደትውልድ የተሻገረ በመሆኑ በነገዋ ኢትዮጵያ ላይም ጠባሳው ችግር መሆኑ አይቀርም።

የትግራይ የበላይነት የህወሀቱ ጋዜጠኛ እንዳለው የጽንፈኞች መዙሙር አይደለም። በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ በህንፍሽፍሽ ላይ የተናገረው ሀቅ ነው። በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የማይደበቅ ሆኖ የሚታይ ዕውነት ነው። የበላይነቱ እጅና እግር አውጥቶ፡ ስጋ ለብሶ፡ በሰፈር መንደሩ የሚንጎማለል ነው። ከመቀሌ እስከሞያሌ፡ ከጅጅጋ እስከ ወለጋ፡ በአራቱም ማዕዘናት ጓዳ ድረስ ዘልቆ የገባ ጉዳይ ነው። ሃይለማርያም በማርያም እየማለ ቢሰብክ የማይቀየር፡ ደብረጺዮን በአቡነ አረጋዊ ገዝቼአለሁ እያለ ቢማጸን የማይጠፋ፡ አባይ ጸሀዬ የደደቢት ሰማዕታት አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋኝ ብሎ ቢለምን የማይተወን፡ የሶማሌው ፕሬዝዳንት በ”ወላሂ” ቢምል የማይለቀን ነገር ነው። እንደባህር ከሰፋው ይህ ዕውነታ መሀል የቀድሞዎቹን ትተን የሰሞኖቹን እናንሳ።

” በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም የተሰየመውና ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የተደረገበት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት ተመረቀ። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ክንደያ ገብረሂወት ኢንስቲትዩትን ትናንት በመረቁበት ወቅት እንደገለፁት ኢንስቲትዩቱ የመለስ ዜናዊን ራዕይ እውን ለማድረግ የሚተጉ ወጣት ተማራማሪዎችን ለማፍራት ታስቢ ተደርጎ የተገነባ ነው።” የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
”በጥቅምት ወር በተለያዩ ክልሎች ለሚካሄደው የአሥራ አንድ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች ግንባታ 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት ተመደበ።”
”የአማራ ክልል በደብረታቦር ለ7 ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል ያስገነባውን ማረሚያ ቤት አስመረቀ ።”

ህወሀቶች ለአቅመ ማሰብ ለደረሰ ሰው የማይመጥን ለዛቢስ ፕሮፖጋንዳውን ደግመው ደጋግመው ከመናገር ወደ ኋላ አይሉም። ”የትግራይ የበላይነት የለም” የሚል መልዕክት የሚያስተጋቡ ሰልፎች በተለያዩ ክልሎች ከማስደረግ የሚመለሱም አይደሉም። ወደ ”ትግራይ ተበድላለች” ዜማ ቀይረው የመጡትም በፕሮፓጋንዳ ጭነት ህዝብ እናሳምናለን ከሚል ተራ ስሌት ተነስተው ነው። አሁንም በድጋሜ ልጥቀስው። እናንተ ለመደበቅ ብትፍጨረጨሩም በፋብሪካዎችና ዘመናዊ ኢንዱስትሪዎች ብዛት መሬቷ ሊሰምጥ የደረሰባት የትግራይ ክልል ዕውነታውን መቼም አትደብቀውም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s