አስቸኳይና አዋጭ መልእክት በሳውዲ ዓረቢያ ላሉ ወገኖቻችን! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሳውዲ ዓረቢያ “በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሬ የገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞች!” ያለቻቸውን የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ያለ ተጠያቂነትና ቅጣት በሰላም ወደየሀገሮቻቸው እንዲመለሱ የሰጠችው የሦስት ወራት የጊዜ ገደብ ሊቋጭ ከሦስት ሳምንታት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል፡፡ እዚያች ሀገር ከአምስት መቶ ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ይነገራል፡፡ ከእነኝህ ውስጥ አዋጁ የማይመለከታቸው ወገኖች የሉም ባይባልም በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡
የዛሬ አራት ዓመት ሳውዲ ዓረቢያ በተመሳሳይ አዋጅ ወገኖቻችንን ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ እንዲወጡ ስታደርግ፣ በኃይል እያሰረች አስከፊ ግፍ ወደሚፈጸምባቸው ወኅኒ ቤቶቿ ስትወረውር፣ በየጓዳው እንደ በግ እያረደች ስትጥል እዚህ ሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ወገኖቻችንን አሰድዶ ለዚህ አሳር፣ አስከፊ ግፍና መከራ በዳረጋቸው የወያኔ አገዛዝና በግፈኛዋና ውለታ ቢሷ ሀገር ሳውዲ ዓረቢያ ላይ ተቀስቅሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ውለታ ቢሷ ሀገር ማለቴ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሳውዲ ዓረቢያ ለእስልምና ተከታዮች ያበረከተችውን እስልምናንና በሀገሪቱ ዛሬ ድረስ በሥልጣን ላይ ያለውን የእስልምናን ነቢይ የመሐመድን ቤተሰቦች (ንጉሣዊ ቤተሰቦች) ከመጥፋትና ከሞት ታድጋ ዛሬ ላሉበት ደረጃ ያበቃች ታላቅ ባለውለታ ሀገር ነበረች፡፡ ዓረቦቹ አዙሮ የሚያይ አንገት፣ የሚያስብ ጭንቅላትና እግዚአብሔርን የሚያውቅ፣ የሚፈራ፣ የሚያመልክ ልቡና ቢኖራቸው ኖሮ ለሀገራችንና ለሕዝቧ ለዚያ ለዋልንላቸው ውለታ የሚሰጡን ወይም ሊሰጡን የሚገባ ምላሽ፣ የሚከፍሉት ዋጋ በፍጹም ይሄ እንዳልሆነ መረዳት መገንዘብ በቻሉ ነበር፡፡ ዓረብ አንገት፣ ጭንቅላትና እግዚአብሔርን መፍራት የሚባል ነገር የለውምና በባለውለታቸው ሀገርና ሕዝብ ላይ ከጥንት ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍ ሲፈጽሙብን ኖረዋል፡፡ ፍርዱን ለአንዱ አምላክ እንተወዋለን፡፡

ወያኔ በብልሹ አሥተዳደሩ፣ ሀገሪቱን የራሱ ወገኖችና የደጋፊዎቹ ብቻ በማድረጉና ዜጎችን “ደጋፊዎቸ አይደላቹህም! ወይም የተቃዋሚ ደጋፊዎች ናቹህ!” በሚል አንባገነናዊ ወይም ኢዲሞክራሲያዊ (ኢመስፍነ ሕዝባዊ) ፣ ኢሕትሐዊ፣ ኢሕገመንግሥታዊ እና ኢሰብአዊ ምክንያት ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ሠርተው መብላት እንዳይችሉ በማድረጉ በመከልከሉ፣ ያላቸውን የዜግነት፣ የፖለቲካ (እምነተ አሥተዳደር) እና የሰብአዊ መብቶችን የሚያስጠብቁበት የሚያራምዱበት፣ ሀገር ካሉባት ፈተናዎች ተላቃ ለዜጎች የምትመች ሀገር እንድትሆን የዜግነት ግዴታቸውንና አስተዋጽኦዋቸውን ማበርከት የሚችሉበት ፖለቲካዊውን (እምነተ አሥተዳደራዊውን) ምኅዳር ፍጹም ዝግ አድርጎ መፈናፈኛ፣ መላወሻ በማሳጣቱ ምክንያት የሀገራቸውና የእነሱ እጣ ፋንታ ተስፋቢስ ቢስ ቢሆንባቸው ጊዜ ሀገር ጥለው ለመሰደድ ተገደው ሞትን ፊት ለፊት እየተጋፈጡና ከጎን ወንድም እኅቶቻቸውን በመራራና ዘግናኝ ሞት ተነጥቀው እጅግ አስቸጋሪና ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ አልፈው በስንት መከራና አሳር ከደረሱበት ሀገር አብዛኛዎቹ እዚያ ለመድረስ ያወጡትን ገንዘብ እንኳ ባልመለሱበት ሁኔታ ውጡልን ለተባሉት ወገኖቻችን አዝኖ አስቦ ተቆርቁሮ ሳይሆን ወገኖቻችን እንደዛሬ አራት ዓመቱ በተመሳሳይ ኢሰብአዊ ሁኔታ ዘንድሮም ሳውዲዎቹ ወገኖቻችንን ከሀገራቸው እንዲወጡ በሚያደርጉበት ወቅት “ተመሳሳይ ተቃውሞ ይቀሰቀስብኝና በዚህ አሳሳቢ ወቅት ሌላ ችግር ላይ ሊጥለኝ ይችላል!” በሚል ሥጋት ወገኖቻችንን የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት እንዲወጡ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ከጥቂቶች በስተቀር እንዲመለሱ ሊያደርግ አልቻለም፡፡

እዚያ ያሉ ወገኖቻችን ፈርጠም ብለው እያሉ ያሉት ነገር “ሀገራችን ገብተን ምን ሠርተን እንበላለን? እዚያም ሞት ነው የሚጠብቀን እዚህም ያው ሞት ነው! ለሞት ለሞት እዚሁ እንሞታታለን እንጅ አንመለስም!” ነው እያሉ ያሉት፡፡ ከመደበኛው የብዙኃን መገናኛ (Conventional media) እና ከማኅበራዊው የብዙኃን መገናኛ (Social media) የሚገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙትም ወገኖቻችን ያ ሲያንገላታቸውና ሲያሰቃያቸው የኖረ አረመኔ የአሕዛብ የጸጥታ ኃይልና ዜጋው ንክች ቢያደርጋቸው ይዘው ሊወድቁ ለራሳቸው ቃል እንደገቡ ይሰማል፡፡

እውነት ነው ይህች ሀገር የእነሱም ሆና ቢሆን ኖሮ መጀመሪያውኑም በሞት መንገድ ላይ አሳር ፍዳቸውን ዓይተው እንደቅጠል እየረገፉ ለመሰደድ ባልተገደዱም ነበር፡፡ ስላልሆነች ነው የተሰደዱት፡፡ ይሁን እንጅ የገዛ ሀገራቸውን ለፋሽስት (አረመኔ) ወያኔ አስረክበው በሞት መንገድ እንደቅጠል እየረገፉ የተሰደዱ ወገኖቻችን የሰው የባዕድ ሀገር ላይ ተቀምጠው የሀገሩ መንግሥት ሳይወድና ሳይፈቅድ “ውጡልኝ አልፈልጋቹህም!” እያለ ባለበት ሁኔታ በሰው ሀገር ድርቅ ብለው “የፈለገ ይሁን እዚሁ ለመኖርና ላለመውጣት ከአሕዛብ አረመኔ የጸጥታ ኃይልና ጨካኝ ዜጋ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቄ በአረመኔዎቹ ሰይፍ እየተቀላሁ እወድቃለሁ እንጅ በምንም ተአምር አልወጣም!” የማለት ወኔ ካለውና ይሄንን ያህል ለነፍሱ ሳይሳሳ ጨክኖ ለመሞትም የተዘጋጀ ከሆነ መጀመሪያውኑ እንዴትና ለምንስ የራሱን የገዛ ሀገሩን ለወያኔ አስረክቦ በአራቱም አቅጣጫ እንደቅጠል እየረገፈ የገዛ ሀገሩን ጥሎለት ከነ ዓይንና ጥርሷ አስረክቦት ሊሰደድ እንደቻለ ባስበው ባስበው ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡

ወገን ሆይ! እንግዳውስ አንዲት ነፍስህ በባዕድ ሀገር፣ መብትህ ባልሆነ የሰው ሀገር በግድ ካልተቀመጥኩ ብለህ በከንቱ ልታልፍ መሆኗ ግድ ካልሰጠህ ይህች ነፍስህ ለዚህ ሁሉ ውርደት፣ አሳርና መከራ የዳረገህን ጥንተ ጠላትህን ወያኔን አጥፍተህ የሀገርህ ባለቤት ለመሆን ትጠቅማለችና ወገኖቻችን ሆይ እባካቹህ እባካቹህ በከንቱ የአሕዛብ ሰይፍና ምድር አይብላቹህ? በሰላም ወደሀገራቹህ ግቡልንና ያላትን ሀብት በአግባቡና በፍትሐዊ መንገድ መጠቀም ብትችል እንኳን ለእኛ ለዜጎቿ ከፊል አፍሪካን ቀጥ አድርጋ አንደላቃ መያዝ እንደምትችል የሚነገርላትን ውድና ባለጸጋ ሀገርህን ወያኔ ላይ በመዝመትና በዐመፅ በማስወገድ ሀገርህን ለመረከብ፣ የሀገርህ ባለቤት በመሆን ማለቂያ የሌለው ስደትህንና መከራህን እንዲያበቃ እንዲቋጭ ታደርግ ዘንድ ወንድማዊ ጥሪየን በውድ ሀገርህና ሕዝብህ ስም ከታላቅ አክብሮትና ስስት ጋር አቀርብልሀለሁ! እባካቹህ እባካቹህ እኅት ወንድሞቻችን ሆይ! ለሀገራቹህ እጅግ ትጠቅማላቹህና በከንቱ አልቃቹህ አትቅሩብን??? ስለፈጠራቹህ ብላቹህ ከዚያ የአረመኔ ምድር ፈጥናቹህ ውጡልን!!!

ቆይ ቆይ! ይሄንን ያህል ወገን እዚያ ገሃነም ሀገር በየበረሃው በተገነቡ ወኅኒ ቤቶች ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ታጉሮ ማቅቆ ቢያልቅ፣ በየጎሬው አንገቱን በአጋንንት ተቀልቶ ቢቀር የሚጎዳው ማን ነው? ሀገርና ሕዝብ ወይስ ወያኔ ነው የሚጎዳው? ወያኔ ደስ ቢለውና ቢጠቀም ነው እንጅ ምኑ እንዴት ሆኖ ይጎዳል? እና ታዲያ የሀገርንና ሕዝብን፣ የዘመድ ቤተሰብን አንጀን በመሪር ሐዘን ለመቁረጥ፣ ወያኔን ደግሞ ለማስደሰትና አንጀቱን ለማራስ ነው ወይ ገሃነም ውስጥ በአጋንንት ተበልታቹህ ለመቅረት የፈለጋቹህት? እናም እባካቹህ ወገኖቻችን እኅት ወንድሞቻችን ሆይ! እባካቹህ እባካቹህ እባካቹህ???….

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s