የማለዳ ወግ ፣…. የኢድ አልፈጥር እረፍት ፣ የስደተኛው እንግልትና ተስፋ ! – ነቢዩ ሲራክ

* ኢድ አልፈጥር እረፍት በንጉሱ አዋጅ ተራዘመ !
* ተስፈኛው ስደተኛ

ረመዳን ከመግናቱ አስቀድሞ ተማሪዎች ፈተና ወስደው በረመዳን ትምህርት እንዳይኖር በአዋጅ የደነገጉት የሳውዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የዘንድሮው ኢድ አልፈጥር እረፍት ለአንድ ሳምንት እንዲራዘም ትንናት አዋጅ አውጥተዋል ። ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የኢድ አልፈጥር እረፈጥር እረፍት እንዲራዘም በአዋጅ ያዘዙት ትናንት ምሽት መሆኑ ተጠቁሟል ። የሳውዲው ንጉስ ልጃቸውን ልዑል መሀመድን አልጋ ወራሽ ባደረጉበት አዋጅ በመንግስት አስተዳደር በርካታ ሹመትን ለተለያዩ ባልስጣናት ሰጥተዋል ። አዳዲስ አምባሳደሮችም በአዋጅ ሾመዋል ። በቀጣይ ቀናትም ከንጉሱ ተጨማሪ አዋጆች ይጠበቃሉ !

የተስፈኛው ስደተኛ እረፍት …
==================

የሳውዲ ምህረት አዋጅ የፊታችን እሁድ ያበቃል ። የገባው ገብቶ ያልገባው እንዳልገባ ቀርቷል። ለዚህም ፈርጀ ብዙ ምክንታት አለው ፣ 400 ሽህ ህገ ወጥ ስደተኛ አለ ተብሏል ፣ 50 ያልሞና ስደተኛ ብቻ ወደ ሀገር ቤት መግባቱን እየሰማን ነው ፣ ለመግባት ሰነድ በመውሰድ የተመገበው ዜጋ 100 ሽህ አልደረሰም ። ተዘገቦ ቲኬት በማጣት ፣ ካርጎ በመዘጋቱ ካርጎ እቃውን ለማስገባት ላይ ታች ሲል የባጀው ዜጋ በመጨረሻው ሰአት ወደ ሀገር መግባት ቢገልግም እንግልት ሆኖበታል ። ዋንኛ ምክንያቱ ደግሞ የአየር ቲኬት መታጣት ነው ። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች እንደ ጅዳ ቆንስል መረጃ ከሆነ ለተመላሽ ዜጎቻቻችን ተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሳውዲ መንግስት እንዳልተፈቀደ ጠቁሟል። ለተፈጠረው መጉላላትም ቆንስሉ ይቅርታ ጠይቋል !

የጅዳ ቆንስል ሰራተኞች ልክ የዛሬ ሳምንት በሺሜሲ አሻራ መስጫ ስራቸውን ማቆማቸው ይጠቀሳል ። ኮሚኒቲውም እያስከፈለው የሚያቀርበውን ግልጋሎት ማቋረጡን ያለ በቂ ምክንያት አስታውቋል ። ከዚያ ቀን ወዲህ በጣት አሻራ መስጫው ቀንና ሌሊት የሚንገላራው ሰው ደራሽ አልነበረውም ። ለጣት አሻራ ለማድረግ ወደ ሽሜሲ የተጓዘውን ተመላሽ ዜጋ አሻራ ለማድረግ ቀንና ሌሊት እየተንገላታ ነው ። ጉልበተኞች ተሳክቶላቸው ደካሞች ተሰላችተው አሻራ ሳያደርጉ እየተመለሱ ነው ። የአሻራ መስጫው የመጨረሻ ቀን ነገ ሀሙስ ሰኔ 15 ነው ተብሏል። ቀኑ አንዳያልፍባቸው አሁንም በርካቶች የሌቱን ወበቅ የቀኑን የበርሃ ሀሩር ከጾሙ ጋር ተቋቁመው አሻራ ለመስጠት እየታገሉ ነው ። አሻራ የሰጡት ፈግሞ ቲኬት አጥተው በአየር መንገዱ ቢሮ በር ሳይቀር ተኝተው ማደራቸውን ሰምቻለሁ ።

በዚህ ሁሉ መካከል ተስፋ ስደተኛ የሳውዲዎች እረፍት ሲራዘም የእሱ የተስፈኛው ስደተኛ እረፍት የሚጀምርበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀ ነው ። አንድም አሻራ ሰጥቶና ቲኬት ገዝቶ መጓዝ ፣ አለያም የመጣው ይምጣ ብሎ እየጠበቀ ብቻ አይመስለኝም። … ስደት ክፉ ተስፈኛ ያደርጋል ፣ እናም ” ቸር ያሰማን” እልን ንጉሱ ያወጡታል ብለን የምንገምተውን አዳዲስ መመሪያ ፣ መግለጫም ሆነ አዋጅ በአየር ላይ ግምታችን ቸረፈስን በማሳደግ ላይ ነን … ጆሯችን አቅንተንም የተራዘመውን እረፍት ሳይሆን ከስጋት የሚያያወጣንን የሰው ልጅ የተስፋ ቃል በመጠባበቅ ላይ ነን !

ዳሩ ግን ብልጥ ከሆነንን የሰውን ተስፋ ትተን ደካሞች ነንና ወደ አንድዬ ተስፋ አንደበታችን ለምስጋና እናቅናው ! ቅዱስ መጽሐፉ ማቴዎስ በምዕራፍ 11 ቁጥር 28 ” እናንተ ደካሞች፤ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ብሎ ሊያድነን እንጅ ላያጠፋን ቃል ኪዳን የገባልንን አምላክ መማለድ ይበጃል ፣ እነሆ በየሐይማኖታችን በጸሎት እንጽና !

ቸር ያሰማንም እንላለን !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 14 ቀን 2009 ዓም

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/34770#sthash.WcHpctOB.dpuf

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s