ፓርላማው በሕወሓት የሚመራው ቡድን እየፈጸመ ያለውን ዝርፊያ አበረታታ

የገዥው መደብ ፓርላማ፣ ሜቴክ የተባለው ድርጅት እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ገለጸ፡፡ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውን እና ያዮ የተባለውን የማዳበሪያ ፋብሪካ እየገነባ የሚገኘው በህወሓት ጄኔራሎች የሚመራው ብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሲሆን፣ ፋብሪካውን ለመገንባትም በቢሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎበታል፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ ፋብሪካው ተጨማሪ ገንዘብ ከማስወጣት ውጪ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡

የፋብሪካው ግንባታ የተጀመረው ከዓመታት በፊት ቢሆንም፣ እስካሁን ግን ስራው ከ46 በመቶ ከፍ ሊል አልቻለም፡፡ በኦዲት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰው፣ ሜቴክ ፋብሪካውን ገንብቶ ሳይጨርስ ተጫማሪ ቢሊዬን ብሮችን የጠየቀ ሲሆን፣ ገንዘቡ ይፈቀድለት አይፈቀድለት እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ የተጠየቀው ገንዘብም፣ ገና ላልተሰራ ስራ መሆኑ የድርጅቱ ውንብድና ምን ያህል ከፍ እንዳለ አመላካች ነበር፡፡ ፓርላማው ስራ በመጓተቱ ድርጅቱን ሊወቅስና ሊገስጽ ሲገባ፣ ጭራሽ ተደናንቀው መለያየታቸው ድርጅቱ በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ይሁን እንጂ፣ የህወሓት ሰዎች እንደፈለጉት የሚጋልቡበት መሆኑን እንዳስመሰከረ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

ሜቴክ ያለ ጨረታ ከተረከባቸው የግንባታ ስራዎች መካከል ስኳር ፋብሪካዎች የሚጠቀሱ ሲሆን፣ አንድ የስኳር ፋብሪካ ለመገንባትም ከስምንት ዓመታት በላይ እየፈጀበት ይገኛል፡፡ ይህ እየታወቀ በጉዳዩ ላይ ተወያየው ያለው ፓርላማ፡- ‹‹ኮርፖሬሽኑ በርካታ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እየገነባ በመሆኑ፣ አብዛኞቹ የተሻለ አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ፡፡›› ብሏል፡፡

ያዮ የተባለው የማዳበሪያ ፋብሪካ እየተገነባ ያለው በ530 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፣ ገና ግንባታው ከ46 በመቶ ከፍ ሳይል ሜቴክ የ60 በመቶ ክፍያ ጠይቋል፡፡ ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት የህወሓቱ ሰው ሜ/ጄ/ል ክንፈ ዳኘው፣ ለስራው መጓተት የሰጡት ምላሽ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው ቢሉም፣ ምክንያታቸው የማያሳምን ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ድርጅቱ ካለው እንዝላልነት እና ዘራፊነት የተነሳ፣ የሀገር ሀብት በማባከን ላይ መሆኑ፣ ከፍተኛው ችግሩ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በግንቦት ወር ላይ ዋና ኦዲተር፣ ፓርላማ ቀርቦ ሜቴክ ገንዘብ እያባከነና ላልሰራውም ስራ ተጨማሪ ገንዘብ እየጠየቀ መሆኑን ለፓርላማው አባላት አስረድቶ ነበር፡፡ ሆኖም በትላንትናው የፓርላማ ውሎ፣ አባላቱ ይህን ጉዳዩ አንስተው የድርጅቱን ስራ አስኪያጅ ከመጠየቅ ይልቅ፣ ጭራሽ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን መግለጻቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡

 

የዜናው ምንጭ ቢቢኤን ራድዮ ነው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s