ሐምሌ ፭ ፪፼፰ (July 11 2016)! – “የታገልኩት አምባገነን ስርዓት ለማስወገድ እንጅ ማንኔትን ቀይሬ ትግሬ ለመሆን አይደለም።” ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ

(ቬሮኒካ መላኩ)

• “የታገልኩት አምባገነን ስርአት ለማስወገድ እንጅ ትግሬ ለመሆን አይደለም።” ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ

• “እኛ አማራነታችን በማመልከቻ ለማምጣት አይደለም የምንታገለው”  አታላይ ዛፌ

• “አማሮች ምንም እንኳን ለጊዜው ያመኑ ቢመስሉም አመች ጊዜ መርጠው ለማጥቃት አድብተው ይጠባበቃሉ።” ሩዶልፎ ግራዚያኒ

• “በማይቆጣጠሩት የፍጥነት ደረጃ እያደገና እየጨመረ የመጣውን አማራ የሚባለውን ብሄር ገስጋሴ እኛ አውሮፓውያን ፖሊሲ አውጥተን በአጭር ካልቀጨነው አፍሪካን አልፎ ለአውሮፓውያን መስፋፋት ትልቅ እንቅፋትና ተጋዳሮት እንደሚሆን አትጠራጠሩ።” Baron Roman Prochazka.

መሬት እንደ ንብረት ተቆርሶ አይወሰድ፣
ወልቃይት አማራ ነው ሁሌም የትም አይሄድ።

ዛሬ ብትወስዱት ነገ ይመለሳል፣
ታሪኩን ተነጥቆ ማንስ ይቀመጣል።

ከጥንት እስከ ዛሬ ከቀን እስከማታ፣
አማራ በወልቃይት አይወጣም ጡረታ።

ገና መች ገባችሁ የአማራ ማንነት፣
ክብር እንደሆነው ለመብቱ መሰዋት።

የተብላላው ገነፈለ ። የተናፈቀው ደረሰ ።ጎንደር አመፁን ባረከው። የአማራ አርሶአደር የሀምሌ ጎርፍ ሆነ።ግምባር ለግምባር ከአጋዚ ጋር ገጠመ። ደመቀ የሚባል አብሪ ኮኮብ የፌደራል ፖሊስ መለዮ ከነጭንቅላታቸው ቀነጠሰው ። ቦደሰው። ሀምሌ 5 ቀን 2008 አም የነፃነት ጉዞ መጀመሪያው ችቦው ተለኮሰ።

አንድ ህብረተሰብ ባላሰበውና ባልጠበቀው አይነት ከአንድ መራራ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሶሻል ቀውስና ክስረት ውስጥ ድንገት በተዘፈቀ ጊዜ በግለሰቦችም ሆነ በማሀበረሰብ ላይ ብዙ አሳዛኝና አስቀያሚ ድርጊቶች ይፈፀማሉ። ድህረ ግንቦት 20 ኰድኩዶ ካስወለደው የቀውስ ዱብ ዕዳዎች አንዱ ባለፉት 25 አመታት በአማራ ላይ የደረሰው ዱብዳ ነው። አማራ ተከዜን አሻግሮ አራት ኪሎ ባደረሳቸው ለምድ የለበሱ የተኩላ መንጋ ባለፉት አመታት ሲነከስና ሲዘነጠል ኖሯል። አማራ በእነዚህ አመታት የደረሰበት ቀውስና ክስረት ምን ያህል የሚጎመዝዝ መራራ ሰፍነግ መሆኑን እኛ ከአማራ ከአብራኩ የወጣን ልጆቹ በደንብ እንገነዘባለን።

ይህን ሁሉ ስቃይ ሲቀበል የኖረ የአማራ ሕዝብ፣ የውስጡን ረመጥ በአደባባይ ለማሰማት በአገኘው አጋጣሚ ሲያጉረመርም ነበር ።

አማሮች በጭቆና ብዛት ገመምተኛ የሆነውን ስሜታቸውን ለማስታመም በውጭም በውስጥም እስከ ሀምሌ 5 መባቻ ድረስ በየፊናቸው እንጉርጉሮ ማሰማት ጀመሩ። ሀምሌ 5 ሌሊት ለአመታት ሲበስል እና ሲንተከተክ የነበረው የአማራ ህዝብ አመፅ እንደ እሳተ ገሞራ ፈነዳ ። በዚች ታሪካዊ ቀን አማራ የመጨረሻውን መጀመሪያ የትግል ጉዞ ጀመረ።

የአማራ የፀረ ወያኔ አገዛዝ ትግልና የነፃነት ገድል ተመዝግቦ በሚገኝበት ምእራፍ ውስጥ ሀምሌ 5 ልዩና ሰፊ ምዕራፍ ይዛለች። ባለፉት አመታት አማራ ብዙ ጊዜ ወድቆ ተነስቷል።አለቀለት ሲባል አገግሟል። ጠላቶቹ ቀብረነዋል ሲሉ ነፍስ ዘርቷል። ያን ሁሉ ዘመን አልፎም ዛሬ የነፃነት መንገድ ይዞ ለሌሎች መሰሎቿ በአርአያነት የሚጠቀስ የጀግንነት ተምሳሌት ሆኗል።

ነጻነት በገንዘብ የማይተምኑት፣ በስጦታ የማይደልሉለት የሰው ልጅ ፍላጎት መሆኑን አማራ ይረዳል። ድህነት፣ ማጣት፣ ችግርና የመሰለው ምንም አይነት መከራ ቢመጣ የአማራ ህዝብ ነጻነትን ለድርድር እንዲያቀርቡ አያደርጋቸውም። ነጻነት ክብር ነው፤ ክብር ደግሞ በምድር ላይ ለሰው ልጅ የተሰጠ ጸጋ ነው። ይህን ደግሞ ከምንም ከማንም በላይ አማሮች ያውቁታል።

ሚስማር ሲመቱት እንዲጠነክር ባለፉት አመታት በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰው በደል እርሾ ሆኖ የህዝቡን ወኔ ይባስ ቀሰቀሰው እንጂ ወደኋላ አልመለሰውም። ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚችሉ እጅግ በርካታ ምክንያቶች ቢደረደሩም ክብርና ነጻነትን ማቆየት ግን ከሁሉ በልጠው አመዘኑ።

ቋንቋ ያልተደባለቀባቸው፣ ቀለማቸው ያልደበዘዘ ባቸው፣ ባህል ያልተሰወረባቸው፣ ውበታቸው ያልተበረዘባቸው የራሳቸው ማንነት ያልጠፋቸው ልጆቻቸው ያለአንዳች ሃፍረት አንገታቸውን አቅንተው በኩራት እንዲቆሙ አደረጋቸው።

እነዛ ብርቱ የአማራ አርበኞች የህዝባቸው መልክ ይቀየር ዘንድ ለጠላት እጅ አልሰጡም፤ አልፈቀዱምና። አማራ ዛሬ ትጥቁን አልፈታም የጠመንጃው አፈሙዝ የጠላትን ፋሽስታዊ ጠረን እያነፈነፈ በመቅጣት ላይ ነው።

በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሰአት አካላዊ ጥንካሬና የሞራል ሀቀኝነት በማሳየት ለሚያምኑበት ነገር እድላቸውንና ህይወታቸውን ለህዝባቸው አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች “ሄሮ ” ወይም ጀግና ይባላሉ ። አማራ በአለፈው ታሪኩ እልፍ አእላፍ ጀግኖችን ያፈራ ህዝብ ነው። ስለሁሉም የአማራ ጀግኖች ለመፃፍ መሞከር አባይን በጭልፋ ቀድቶ አለመጨረስ መሞከር ነውና ለጊዜው የዛሬዋን ቀን ስለሚያስታውሰው አንዱን ጀግና እንዘክራለን። ይህ የአማራ ጀግና ኮሌኔል ደመቀ ዘውዴ ይባላል።

የደመቀ ዘውዴን ክብር ስብእናና ግሑስ ባህርይ አሟልቶ ለመግለፅ እጅግ በጣም ያስቸግራል ። ምንም አይነት የብዕር ሀይል ሊገልፀው የማይችል ሆኖ ይሰማኛል። ኮለኔሉ የነጠረ የጀግና አበጋዝ ነው።

የደመቀ ዘውዴ ምድራዊ ህላዌ ግብ የተነደፈው ለህዝቡ የነፃነት ዋስትና መስጠት ነው። በዚህም ምክንያት የራሱ ግለኛ ኑሮና ህይወት ዶጋመድ ቢሆንና አፈር ድሜ ቢግጥ ጨርሶ ደንታው አይደለም ። ለግሉ ጥቅምም ሆነ ዝና ለራሱ ምቾትም ሆነ ብልፅግና በፍፁም አያልምም። ደመቀ ዘውዴ ነፃ አእምሮና ወታደራዊ ጥበብ ያጣመረ ለሚያምንበት ግንባሩን የማያጥፍ ጀግና ነው።

ኮሌኔል ደመቀ ዘውዴ የወልቃይት አማራ ህዝብ በገዛ መሬቱ በገዛ ወንዙ በመጤዎች የሚደርስበትን ግፍ እና ስቃይ አንገሽግሾት ይሄን ጭቆና አሽቀንጥሮ ጥሎ ለህዝቡ የነፃነት ሻማ ለመለኮስ የተጋ የዚህ ታሪካዊ ቀን አስጀማሪ አብሪ ኮኮብ ነው። ሀምሌ 5 ስትነሳ ደመቀ ዘውዴ ፣አታላይ ዛፌ እና እልፍ አእላፍ ጀግና አማሮች አብረው ይታወሳሉ።

የኮሌኔል ደመቀና ጓደኞቹ መንፈስ ዛሬም ከህውሃት ማጎሪያ አዘቅጥ ውስጥ ሆኖም አማሮችን ይመራል። የወልቃይት፣ የአርማጭሆ ተራራዎች ድምፁን እየተቀባበሉ ያንቆረቁሩታል። ድል አይቀሬ መሆኑን ይዘምሩለታል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s