ታክስ ከፋይ ነኝ – ተዎልደ ግርማ

በነጮቹ ሀገር ዜጎች አስተዳደራዊ በደል ሲደርስባቸው እንዲሁም ከመንግስት የሚገባቸውን አገልግሎት ሳያገኙ ሲቀሩ እኔ “ታክስ ከፋይ ነኝ (I am a tax payer)” በማለት በደላቸውን ሲገልፁ ይስተዋላሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ህዝባዊ ተቆርቋሪነት የሚሰማቸው መሪዎችም አግባብነት የጎደለው የመንግስት ወጪን እና ብክነት ሲመለከቱ “ይህ የታክስ ከፋዩ ገንዘብ ነው” በማለት ፈፃሚ አካላትን እንዲሁም ተቋማትን ሲኮንኑ ይስተዋላሉ፡፡ በመሆኑም ባደጉ ሀገራት ታክስን መሰወርም ሆነ ማጭበርበር እንዲሁም የህዝብ ገንዘብን አግባብነት በጎደለው መልኩ ማባከን ትልቅ የህግ ቅጣትን ያስከትላል፡፡ ለአብነት ያክል በአህጉረ አሜሪካ አንድ ታክስ የሰወረ ዜጋ የግለሰብ ህይወት ካጠፋ ዜጋ ባላይ የህግ ቅጣት ይጣልበታል ምክንቱም ታክስ የሰወረው ግለሰብ በመላው የአሜሪካ ህዝብ ላይ የግድያ ቅጣት እንደሞከረ ይቆጠራል እና ፡፡ በመሆኑም ባደጉ ሀገራት ምንም እንኳ ታክስ ማጭበርበር እና መሰወር የለም ባይባልም መጠኑ ዝቅተኛ ሲሆን ዜጎቻቸውም ታክስ በመክፈላቸው አንፃራዊ ኩራት ይሰማቸዋል፡፡ በየጊዜው በሚያኪሂዱት ሀገራዊ ምርጫም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ለመጣል የሚያቅዱት የታክስ መጠን እና አይነት የዜጎቻቸውን ቀልብ ሲስብ ይስተዋላል፡፡

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስመለስ ሰመኑን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እንዲሁም በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከታከስ ጋር ቁርኘት ያላቸው ህዝባዊ አድማዎች እየተስተናገዱ ነው ፡፡ አልፎ አልፎም የንግድ ቤቶቻቸውን ክርችም አድርጎ በመዝጋት ቅሬታቸውን የገለፁ ከተሞችም አልጠፉም፡፡ እናማ እኔም ከታች የተዘረዘሩ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ ሃሳቤን መግለፅ ፍለኩ፡፡ ለመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የሚሰበሰበው የታክስ መጠን እንደተባለው አውን የስራ ፍላጎትን የሚጎዳ ነው (cannon of productivity) ወይስ የፍታሃዊነት(cannon of equality) ችግር አለበት? ለምንስ ህዝባችን ስለ ሚከፍለው ታክስ ኩራት አይሰማውም? የሚሉ ጥያቄዎች ላይ አስታየቴን ለማንፀባረቅ እሞክራለው፡፡

የሀገራችን ኢኮኖሚ የሚያመነጨው የታክስ መጠን የስራ ፍላጎት እና ተነሳሽነት ላይ ያለውን ተፅኖ ለመለየት የሌሎች ሀገራትን ተምከሮ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ የበለፀጉ ሐገራት የሰለጠነ የሰው ሀይል እና በቂ የሆነ ተቋማዊ እና ቴክኖሎጂካዊ አቅም ስላላቸው በአማካኝ 34 ፕርሰንት የሚሆነውን የአመታዊ ሐገራዊ ምርታቸውን በታክስ መልክ ይሰበስባሉ (In developed country on average tax revenue accounts for 34 of their GDP) ፡፡ ለአብነት ያክል ታክስ በታላቋ አሜሪካ በአመታዊ ሀገራዊ ምርት ሲለካ 26 ፕርሰንት የሚደርስ ሲሆን በዴንማርክ እስከ 48 ፕርሰንት ይደርሳል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከታክስ የሚሰበሰበው ገንዘብ በአመታዊ ሀገራዊ ምርት ሲለካ ከ 13 ፕርሰንት ያነሰ ነው፡፡ ይህም ኢኮኖሚው በሚያመነጨው ገቢ መጠን ታክስ እየተሰበሰበ አለመሆኑን የሚያሳይ ሲሆን እንደ አኔ አመላከከት በአጣቃላይ በሀገራችን የታክስ ትልቅነት የስራ ፍላጎትን የመጉዳት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይህም ማለት ግን ከአቅማቸው በላይ ታክስ እንዲከፍሉ የተገደዱ ዜጎች የሉም ማለት ግን አይደለም ምክንያቱም የታክስ አጣጣል ስርዓቱ ግምታዊ እና በመረጃ የተደገፈ ባለመሆኑ፡፡

በመቀጠልም የታክስ ግዴታው/Burden በተግባር ትልቅ ሃብት ካለው የህብረተሰብ ክፍል ይልቅ ትንሽ ገቢ ባላው የህበረሰተስብ ክፍል ላይ ይበረታል በተጨማሪም ፍትሃዊነት ይጎድለዋል፡፡ በአማካኝ ከ80-85 ፕርሰንት የሚሆነው የመንግስት ገቢ በታክስ አማክኘት የሚገኝ ሲሆን ከ37 እስከ 40ፕርሰንቱ ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ በሚጣል ቀረጥ፤ ከ26-32 ፕርሰንቱ በሰራተኛው ገቢ እና በንግዱ ማህበረሰብ ትርፍ ላይ በሚጣል ቀጥተኛ ቀረጥ እንዲሁም ከ19-26 ፕርሰንቱ በሽያጭ እቃዎች አና አገልግሎት ላይ በሚጣል ኢ-ቀጥተኛ(Indirect tax) ቀረጥ አማካኝነት የሚሰበሰብ ነው፡፡ ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ የሚጣል ታክስ (import duties)(37-40%) እንዲሁም በሽጣያጭ እቃዎች አና አገልግሎት ላይ የሚጣል(19-26%)ታክስ የሚሰበሰቡበት ከነጋዴው ማህበረሰብ ቢሆንም የሚከፍለው ግን ሸማቹ ህብረተሰብ ነው(Ultimately the bearer of the indirect tax burden is the consumer, not the seller)፡፡

በመሆኑም እንደኔ አመለካከት የታክስ ግዴታውን በአግባቢ እየተወጣ ነው ብዩ የማስበው የህብረተሰብ ክፍል የመንግስት ሰራተኛው/ሲቪል ሰርቫንቱ/ሸማቹ ብቻ ነው፡፡ “ለምሳሌ አንድ በማስተርስ ደረጃ ያለ የዩኒቨርሲቲ መምህር ገቢውን መደበቅ ስለማይችል በወር 2881.5 ብር ወይም በአመት ከሚያገኘው125,250 ብር 34,578 (27.7 ፕርሰንቱን) በታክስ መልክ ይከፍላል (የድርጅት መዋጮ ፣የአባይ ግድብ፣ የወላይታ ልማት ማህበር ምናመን ሳይታሰብ/ሴተረስ ፓሪብስ ማለቴ ነው)” ፡፡ በመሁኑም የንግዱ ማህበረሰብ(በተለይ የደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች) የሚያሰሙትን ቅሬታ የምመለከተው ከተጣለባቸው የታክስ ግዴታ ትልቅነት አንፃር ሳይሆን እኩለነትን በማስፈን ረገድ ፍታሃዊነት ይጎድለዋል በሚል እሳቤ ነው፡፡ እኔ እና አንተ ተመሳሳይ ቢዝነስ ኖሮን አንተ እጅህ በመርዘሙ ትንሽ ታክስ ትከፍላል፤ አንተ ለመንግስት መክፈል የሚገባህን ቀንሰህ ለኢዲተር በማካፈልህ እኔ ከገቢያ ስወጣ አንተ ተሸላሚ ባለሃብት ትባላለህ፡፡

በመጨረሻም እኔን ጨምሮ አብዛኛው የህብረሰተስብ ክፍል ስለሚከፍለው ታክስ ኩራት ሲሰማው አይስተዋልም፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያትነት ከሚጠቀሰው ችግሮች መካከል ዜጎች በሚክፍሉት ታክስ ልክ ተጠቃሚ አለመሆን እና የሚከፍሉት ታክስ በመንግስት ተቋማት አማካኘነት አለአግባብ ሲባክን መመልከት ዋናዎቹ ናቸው፡፡ለመሆኑ ከቀበሌ መታወቂያ ለማግኘት የሚንገላታ ህብረተሰብ፤ ዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮጀክቶች ተጀምረው መጠናቀቅ ሲሳናቸው የተመለከተ ህብረተሰብ፤ የተጠናቀቁ የቤት እና የመንገድ ፕሮጀክቶች ደብዛቸው ጠፋ ሲባል የሚስማ ህበረተሰብ፤ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ህጋዊ ስርዓት ሳይከተል ስለመከፈሉ የሚያውቅ ትውልድ እና ህብረሰተሰብ ታክስ አልከፍልም፤ እረ ከበደኝ ቢል ምን ይደንቃል፡፡ አይደንቅም፤ ግን ወዳጄ እንደ ነጮቹ “እኔ ታክስ ከፋይ ነኝ” እንደማትል ተስፋ አድርጋለው ምክንያቱም እኔ ጥይት ያዥ ነኝ ይሉሃል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s