የነጋድያኑን አድማ ወደ ዐመፅ ቀይሮ ወያኔን ካለማስወገድ ሌላ መፍትሔ የለም! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ወያኔ የነጋድያኑ አድማ እየተባባሰ የሚሔድ እንጅ የማይቀዘቅዝ መሆኑን ሲያውቅ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ማስተካከያ እንደሚያደርግ ቃል እየገባና እየለፈፈ ይገኛል፡፡ ነጋዴው ኅብረተሰብ ይሄንን የወያኔን የመደለያ ቃል አምኖ የተያያዘውን አድማ ወደ ዐመፅ ከመቀየር መታቀብ እንደሌለበትና ብቸኛው መፍትሔ ይሄው መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ግብር የጨመረው አማራጭ ስላጣ እንጅ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አስቦ አይደለምና ነው፡፡ ወያኔ አማራጭ ቢኖረው ኖሮ እንዲህ ሕዝብ ጥርሱን በነከሰበት፣ ከሕዝብ ጋር በተፋጠጠበት ሰዓት ቢችል እንዲያውም ግብር ይቀንስ ሌላም ሌላም የማባበያ የመደለያ እርምጃዎችን ይወስድ ነበር እንጅ ጭራሽ እንዲህ ሕዝብን በጣም በሚያስቆጣ መልኩ ግብር እየቆለለ አያሸክምም ነበረ፡፡

ከሚገርማቹህ ነገር ነጋዴው “የተጣለብን ግብር ፈጽሞ የመክፈል አቅማችንንና ገቢያችንን ያገናገበ አይደለም!” ይበለው እንጅ የወያኔ ፍላጎት ግን ጭራሽ ከዚህም በላይ የሆነ ግብር በነጋዴው ላይ መጫን ነበር ፍላጎቱ፡፡ ነገር ግን አሁን ካለበት አሳሳቢ ሁኔታ አኳያ ይሄንን ቢያደርግ “በገዛ እጀ በአንገቴ ላይ ገመድ ማጥለቅ ማለት ነው!” ብሎ በማሰቡ “ተመጣጣኝ ነው!” ያለውን ነገር ግን ከነጋዴው ኅብረተሰብ የመክፈል አቅምና ገቢ አንጻር ፈጽሞ ተመጣጣኝ ያልሆነውን ግብር ሊጭን ችሏል፡፡

በነገራችን ላይ ወያኔ ግብር ብቻ አይደለም የሚጨምረው፡፡ ሁሉንም በተመሳሳይ ሰዓት ማድረጉ “ችግር ይፈጥርብኛል!” ብሎ ስላሰበ ነው እንጅ ቀረጥንም ከእጥፍ በላይ ለመጨመር አስቧል፡፡ የሸቀጦች ዋጋ አሁን ያለበትን ደረጃ እያያቹህት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ጣሪያ ነክቷል፡፡ ይሄ ዋጋ ከእጥፍ በላይ ሲጨምር ደግሞ እንዴት ሊሆን እንደሚችል አስቡት! እስትንፋስ ያለውን ሁሉ ጸጥ ነው የሚያደርገው፡፡ ወያኔ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚሰማው አካል ቢሆን ኖሮ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር እጅ ሰጥቶ “ተረከቡኝ! እኔ አልቻልኩም! ያዋጣል ብየ የያዝኩት መመሪያና የአሥተዳደሬ ሥርዓት እንዲህ ዓይነት ችግሮችን ፈጥሯል፣ ወድቄያለሁ (ፌይል አድርጌያለሁ) ላይሆን ነገር ይሄንን ችግር እቀርፋለሁ ብየ ሕዝብን በከፍተኛ ግብርና ቀረጥ ማስጨነቅ ማሰቃየት የለብኝምና ይችላል ችግራችንን ይቀርፍልናል የምትሉትን አካል ምረጡና አስቀምጡ!” ብሎ ሥልጣኑን ያስረክብ ነበረ፡፡ ነገር ግን ወያኔ እንደምታውቁት ፍጹም ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማይሰማውና የአስተሳሰቡ መሠረት “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” የሚለው የአህያ አስተሳሰብ በመሆኑ ይዞን መቀመቅ ለመውረድ ያስባል እንጅ ሥልጣንን የማስረከብ ፍላጎት የለውም፡፡

ወያኔ ይሄንን እጅግ ከፍተኛ የሆነን ግብርና ቀረጥን ሳይፈልግ ለመጫንና ለመጣል የተገደደበት ምክንያት ከዚህ ቀደም ከምዕራባውያን ለጋሾች ያገኘው የነበረው ቀጥተኛ የባጀት (የገንዘብ መደብ) ድጋፍና እርዳታ በከፍተኛ ደረጃ ስለቀነሰበትና መልሶ ለማግኘትም ዕድሉ እንደሌለው ስለተረዳ ነው፡፡ ወያኔ አምና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ተቋም “የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞ መሆን አለመሆኑን ገብቸ አጣራለሁ!” ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ካደረገ ወዲህ ምዕራባውያኑ ለጋሾች እንደከዚህ ቀደሙ እንኳንና ለቀጥተኛ ባጀት ድጋፍና እርዳታ ሊያደርጉ ይቅርና እንደ ድርቅ ላሉ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ጥሪ እንኳ በጎ ምላሽ የማይሰጡ ሆነዋል፡፡ እንደ US Aid (የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት) ያሉ ከፍተኛ የእርዳታ ድርጅቶች ዘግተው እየወጡ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ወያኔ ባጀቱ (የገንዘብ መደቡ) ተቃውሶበት ለከፍተኛ የባጀት (የገንዘብ መደብ) ጉድለት ተዳርጓል፡፡

በየዓመቱ ከሚመደበው የመንግሥት ወጪ (ባጀት) ባለሥልጣናቱ እየዘረፉ ወደየግል ጋዝናቸው የሚያግዙት ከፍተኛ መጠንም ለባጀቱ መቃወስ ትልቁ መንስኤ መሆኑን ልብ በሉ፡፡ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የማይሰማው አገዛዝ ባለበት ሁኔታ እንኳን ሙስናን ዋነኛ የአገዛዝ ሥርዓቱ መሣሪያ አድርጎ እየተጠቀመ ይቅርና ከሙስና የፀዳ ቢሆን ኖሮ እንኳ የተረጋጋ የምጣኔ ሀብት ሥርዓትን መዘርጋት መቻሉ የሚታሰብ አይደለም፡፡ በነኝህ ምክንያቶች ያጋጠመው የባጀት ጉድለት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ነጋዴው የተጣለበትን ከፍተኛ ግብር የሚከፍል ቢሆንም እንኳ ወያኔ የገጠመውን ጉድለት መሙላት አይችልም፡፡ ስለሆነም ወያኔ ከቆየ ይሄንን የቁርጥ ግብር ተመን ካላመደ በኋላ ሩቅ ባልሆነ ጊዜ ፈርቶ የተወውን የመጀመሪያውን የግብር ተመን በነጋዴው ላይ እንደሚጭን መገመት ይቻላል፡፡ በመሆኑም “የተጣለብን ገቢን ያላገናዘበው ግብር ይስተካከልልናል!” ብሎ ተስፋ የሚያደርግ ነጋዴ ካለ ሲበዛ የዋህ መሆኑን ልነግረው እወዳለሁ፡፡

ወያኔ ዜጎች መዋዕለ ንዋይን ለማፍሰስ፣ ሥራ ለመሥራት የራሱ ደጋፊ መሆናቸውን ግዴታ ሳያደርገው ዜጎችን ከሀገር ውጭ ያለውን የተማረውንና ሀብት ያካበተውን ጨምሮ በፖለቲካ (በእምነተ አሥተዳደር) አቋም አስተሳሰባቸው ምክንያት ሳያገል፣ ዕድል ሳይነፍግ በሀገራቸው በነጻነት መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ፣ መሥራት፣ መንቀሳቀስ የሚችሉበት ሁኔታ ቢኖርና ለባዕዳንም ለሀገር ውስጥም መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች አደጋ፣ እንቅፋትና ሥጋት የሆኑት የንግድ ድርጅቶቹ ባይኖሩ ኖሮ ሀገሪቱ የእርዳታና ብድር ጥገኛ ሳትሆን፣ በነጋድያንም ላይ አሰቃቂ ግብርና ቀረጥ መጫን ሳያስፈልግ ከየትኛውም ሀገር በተሻለ የማደግ የመበልጸግ ዕድልና አቅም ነበራት፡፡ ይህችን ሀገር የእርዳታና ብድር ጥገኛ ያደረጋት፣ ያላትን አቅምና ዕድል ያህል ተጠቃሚ ሆና እንዳታድግ እንዳትበለጽግ ያደረጋት የወያኔ ያልተጻፈው አግላይ ፖሊሲ (መመሪያ) እና ውንብድና የተሞላበት የንግድ ድርጅቶቹ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ይሄ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ግን ይሄንን ሁሉ ውጥንቅጥ መቋጫ የሚያበጅለት ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ነጋዴው ኅብረተሰብ የወያኔን በርካታ ግፎች ችሎ አሳልፏል፡፡ ትናንትና ወያኔ ለወገኖቹ ለትግሮች ሹክ ብሎ የንግድ ሱቆችን አማላይ ዋጋ እየከፈሉ የመንግሥትን ቤት ከተከራዩት ላይ እንዲከራዩ ካደረገ በኋላ የተከራይ አከራይ አዋጅን አውጆ አብዛኛውን የንግድ ሱቆች ወገኖቹ ትግሮች ወርሰው እንዲቀሩ ማድረጉን የንግዱ ማኅበረሰቡ ችሎ አሳልፏል፡፡ ነጋዴው ማኅበረሰብ እነኝሁ ሱቆችን እንዲወርሱ የተደረጉት ትግሮች ያለቀረጥና ግብር እየነገዱ ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርገው ከጨዋታ ውጭ ሲያደርጉት አሁንም ችሎ አሳልፏል ወይም ለመቻል እየተንገዳገደ ይገኛል፡፡ ይሄንን የግብር ጫና ግን የንግዱ ማኅበረሰብ ወያኔን በመፍራት ችየ ላሳልፍ ቢል እንኳ ጉሮሮውን ተይዟልና የሚችል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ግብሩ ገቢውንና የመክፈል አቅሙን ያገናዘበ ባለመሆኑ ከየትም አምጥቶ ሊከፍል አይችልምና፡፡ በልቶ ለማደር ደግሞ የግድ መሥራት ስለሚኖርበትና “ሱቄን ዘግቸ እቀመጣለሁ!” የሚለው አባባል የሚያዋጣ ስለማይሆን የንግድ ማኅበረሰቡ የግዱን ጨክኖ መውጣቱና ወያኔን “በቃኸኝ!” ማለቱ የማይቀር ይሆናል፡፡

ስሙ የንግዱ ማኅበረሰብ ተባለ እንጅ ይህ ችግር የማይነካው የኅብረተሰብ ክፍል አይኖርም፡፡ ተጽዕኖው የሸቀጦች ዋጋ ላይ ጎልቶ መታየቱ አይቀርምና፡፡ አንዳንዶች ይህ የግብር ጫና ያተኮረው የቁርጥ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ላይ ስለሆነ ችግሩ የእነሱ ብቻ ሆኖ የሚቀር ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን የቁርጥ ግብር ከፋዩ መሥራት ካልቻለ የደረጃ ሀ ግብር ከፋይ ትላልቅ ነጋዴዎች የሚያስመጡትን ሸቀጥ ማን ይወስድላቸዋል? ስለሆነም ከቁርጥ ግብር ከፋይ ውጭ ያለው ነጋዴም በዚህ ችግር ምክንያት ቀጥተኛ ተጎጂ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ ችግር ምክንያት የሸቀጥ ዋጋ ሰማይን ሊቧጥጥ ነውና አጠቃላይ ሕዝቡም ቀጥተኛ ተጎጂ ሊሆን ነው ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ችግሩ የሁላችንም ነውና በራሱ ችግር ምክንያት ይህችን ሀገርና ይሄንን ሕዝብ እንዲህ ባለ ምስቅልቅል ውስጥ ያሰጠመንን ወያኔን የግድ ከልተን፣ ነቅለን፣ አስወግደን ከችግር መላቀቅ ይኖርብናልና ለራሳችን ብንል እያንዳንዳችን ለዚህ ቆርጠን እንነሣ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s