በህዝብ የሚወደዱ ሰላማዊ የሕዝብ መሪ እጆቻቸው በወያኔዎች ታስሮ #ግርማ_ካሳ

 

የአዉሮፓ ሕብረት ስብሰባ ያደርጋል። በስብሰባው የተለያዩ እንግዶች ይጋበዛሉ። ዶር ብርሃኑ ነጋ እና ዶር መራራ ጉዲና ከተጋባዦች መካከል ነበሩ። እንዳጋጣሚ ሆኖ ሁለቱም ለተጋባዦች በተዘጋጀ ቦታ ጎን ለጎን ይቀመጣሉ። ስብሰባው አለቀ፤ ስምንታት አለፉ። ዶር መራራ ወደ አገርራቸው ይመለሳሉ። “ከዶር ብርሃኑ ነጋ ጎን ተቀምጠሃል፤ በሽብርትኝነት ተግባር ተሰማርተሃል” በሚል አስቂኝ ክስ ወደ ወህኒ ይወሰዳሉ።
ሕወሃቶች እጅግ በጣም ሲበዛ ቂመኞችና በቀለኞች ናቸው። በዶር መራራ ላይ ቂም ከቋጠሩ አመታት አልፏቸዋል። ዶር መራራ ሳይፈሩ ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት ድምጻቸውን የሚያሰሙ በመሆናቸው ህወሃቶች ደስተኛ አልነበሩም። ሰበብ ነበር የሚፈልጉት፣ የአዉሮፓዉን ስብሰባ እንደ ሰበብ ቆጥረው እኝህን ታላቅ ሰው ይኸው በበቀል እያሰቃዩውቸው ነው።

ዶር መራራ በደርግ ጊዜ ወደ ስምንት አመት ታስረው የተፈቱ ናቸው። ለኦሮሞ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሰሩና የደከሙ ፣ ትልቅ አስተዋጾ ያደረጉ ታጋይ ናቸው። በአገር ዉስጥ ሆነው፣ እስር፣ እንግልት፣ ግድያን ሳይፈሩ፣ በድፍረትና በወኔ የሕዝብን ብሶት የሚናገሩ፣ የሕዝብን ጥያቄ የሚያነሱና ለፍርሃት እጃቸውን ያልሰጡ፣ ቀና ብለው የሚኖሩ ሰዉ ናቸው።

ከጥቂት ቀናት በፊት ዶር መራራ ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ የሚያሳይ ፎቶ ተመለከትኩ። ከፊትና ከኋላ በታጠቁ ሰዎች ተከበዋል። እጃቸው ወደ ኋላ በሰንሰለት ታስሯል። ነፍሰ ገዳይ፣ ተደባዳቢና አስቸጋሪ የሆኑ ይመስል።

ወያኔዎች ይሄን ሁሉ እንግዲህ የሚደርጉት በዋናነት የዶር መራራ ጉዲናን ስነ-ልቦና ለማዳሸቅና እርሳቸውን በመንፈስ ለመሰባበር ነው። ሆኖም ግን እንኳን ዶር መራራን ሊሰባብሩ በሺሆች የሚቆጠሩ መራራዎች እንዲነሱ ነው የሚያደርጉት። ሌላው ምክንያታቸው ለተቀረነዉን መልእክት ለማስተላለፍ ነው። “ እያንዳንድህ አርፈህ የማትቀመጥ ከሆነ ፣ ልክ ነው የምናገባህ። እንኳን አንተን ባለም ደረጃ የታወቁት ዶር መራራን አስረናል“ የሚል መልእክት። ነገር ግን የዘመኑ ወጣት ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍርሃትን እያወለቀ የመጣበት ዘመን ነው። ከዝዚህ በኋላ የግፍ ቀንበር ለመሸከም ትከሻ ያለው አይመስለኝም።

ዶር መራራ እጅግ በጣም በሕዝብ የተወደዱ ሰው ናቸው። እርሳቸው መጡ ከተባለ፣ በተለይም በምእራብ ሸዋ ሕዝብ እንደ ማእበል ነው የሚሰበሰበው። እንግዲህ አስቡት በሕዝብ የተወደደን ሰው ነው ወያኔዎች በማሰር ለሕዝብ ያላቸውን ትልቅ ንቀትም እየገለጹ ያሉት። ሰዎቹ በባህሪያቸው ከሕዝብ ፍላጎት በተቃራኒው የሚሰሩ፣ ከሕዝብ ጋር ካልተጣሉ፣ ህዝብን ካላናደዱ፣ የሕዝብን ደም ካልመጠጡ እረፍት የማያገኙ መሆናቸው ነው እያሳዩ ያሉት።

ወያኔዎች ዶር መራራን በማሰርና በማሰቃየት የተጠቀሙ ይመስላቸው ይሆናል። ያሸነፉ ሊመስላቸው ይችላል። ዶር መራራ “ከጫካ ወጡ እንጅ ጫቃ ከነርሱ አልወጣም” እንዳሏችው፣ ሌላውን በማሰር፣ በመግደል፣ በመርገጥ አሽናፊ ለመሆን መሞከራቸው የጫካ ባህሪያቸውን፣ ትንሽነታቸውን ፣ በራሳቸው የማይተማመኑና የበታችነት ስሜት የተሞሉ insecured መሆናቸውን ከማሳየት ውጭ በዘለቂነት የሚያገኙት ምንም ትርፍ አይኖሩም።

ለዶር መራራ እግዚአብሄር ባሉበት ብርታትና ጥንካሬ እንዲሰጣቸው እጸልይላቸዋለሁ። እኝህ የሕዝብ መሪ (የኦሮሞው ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ) ህዝብ እያለ አንድ ቀን በወህኒ መቆየት የለባቸውም። ዶር መራራን እና በሺሆች የሚቆጠሩ አገራቸው በመዉደዳቸው ብቻ በግፍ የታሰሩ ወገኖቻችን ለማስፈታት ሁላችንም በአዲስ መልክ መንቀስቀስ ይኖርብናል። ከንፈር መጣጮችና ጠረቤዛ ደብዳቤዎች ብቻ ሳይሆን፣ በስትራቴጂና በአንድነት መንቀሳቀስ መጀመር አለብን።

የሕዝብ ማእበል ለዶር መራራ ፍቅሩን ሲገለጽና ዶክተሩ ለሕዝብ ንቀት ባላቸው ወያኔዎች እጆቻቸው እንደ ወንበዴ ታስረው የሚያሳዩ ፎቶዎች ይመልከቱ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s