የወያኔ ኣገዛዝ ጎንደርን ከ3 ሸንሽኖ ለማዳከም የጠነሰሰው ሴራ – ኣዳነ ኣጣናው

 

ወያኔ ጎንደርን ከ3 የመክፈል ሴራ ኣጉል ልፋት ቢሆንም፣ አርምጃው ያለጥርጥር የቀቢጸ ተስፋ እርምጃ  ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ጭቆና፣ ኣድሎ ፣ ርስትን ማዛባት አና የለየለት  የተቀናጀ ቡዳናዊ-ምዝበራ ኣንገፍግፎት በቃኝ  ሲል፣ ወያኔ በኣንጻሩ የህዝቡን ኣመጽ ያዳከመ መስሎት መንግስት ነኝ ከሚል ኣካል የማይጠበቅ የቅቢጸ-ተስፋ አርማጃዎችን መውሰድ ጀምሯል፡፡ ሰሞኑን ይህ  የቅቢጸ-ተስፋ ኣሳፋሪ አርምጃ  ለወያኔ የእግር-ረመጥ በሆነው በጎንደር ህዝብ ላይ ኣነጣጥሮ፤ የስሜን-ጎንደርን ኣስተዳደር ወደ 3 ዞኖች ለመሸንሸን መዘጋጀቱን ለወያኔ ቅርበት ያለው ሪፖርተር ጋዜጣ በሰሞናዊ-እትሙ ዘግቧል፡፡

ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ፣ወያኔ አንደ-ነብስ ኣባቶቹ ፋሽስት-ጣልያን  አና የአንግሊዝ ቅኝ-ገዥዎች አንደኣደረጉት ሁሉ፣ የህዝብን ጥያቄ በኣግባቡ ከመመለስ ይልቅ በተቃራኒው ይባስ ብሎ፤ ህዝብን በጎጥ፣በመንደር፣  በኣዉራጃ፣ በክፈለ-ሀገር አና በቑንቑዋ  ክፍፊሎ በማናቆር የኣገዛዙን አድሜ ለማራዘም  መፍጨርጨሩን  ተያይዞታል፡፡ኣሁን ኣሁንማ፣ ወያኔ ሀፍረቱን አና ይሉንታውን ኣሟጦ የቀረው ነገር ቢኖር አንደ ኣለቆቹ የአንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች በደቡብ ኣፍሪካ አና በሌሎች ቅኝ-ተገዥ ኣፍሪካ ሀገራት  ላይ አንደቀለዱት ሁሉ ወያኔም  “ የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን የማስተዳደር ብቃት የለውም” ብሎ ቡድኑ አራሱን በቑሚነት የማንገስ ኣዋጅ ማወጅ ብቻ ነው፡፡

ስሜን-ጎንደር ሲባል፡-  4 ኣዉራጃ ኣስተዳደሮችን ያጠቃልላል ፡ ወገራ ፣ ጎንደር ፣ ጭልጋ ፣ ስሜን ሲሆኑ፣ ዞኑ በወያኔ-ወረራ የተያዙትን 4 ወረዳዎች ማለትም፤  ወልቃይት፣ ሰቲት-ሁመራ፣ ከፊል ጠገዴ አና ከፊል-ጠለምት 4 ወረዳዎችን ሳይጨምር፣ 20 ወረዳዎች ያቀፈ ነው፡፡ ስሜን-ጎንደር በቆዳ/በመሬት ስፋት፣በህዝብ ብዛት አና በተፈጥሮ ሀብት ኣሁን የወያኔው ኣገዛዝ አንደ ቅራጫ-ስጋ  መታትሮ  ኣማራ-ዞኖች ብሎ ከሚጠራቸው ዞኖች ሁሉ የላቀ ነው፡፡

ከ22 ኣመት በፊት ስሜን-ጎንደር፣ ከሁመራ አስከ ኦሜደላ 475 ኪሎ ሜትር ርዝመት በ70 ኪሎ ሜትር (በትንሹ)ጎን ስፋት ለርሻ አጅግ ኣመቺ በሆነና በተጠቀጠቀ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነ በዱር-ኣራዊት ሀብትም የታደለ  ኣካባቢ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ከሁመራ -ወልቃይት ከወልቃይት- ተከዜ ወንዝ ድረስ አና  ከሁመራ – ዳንሻ (ወልቃይት ጠገዴ) አንዲሁ አጅግ ለም መሬትን ያቀፈ ነበር፡፡

ስሜን-ጎንደር ዞን በከብት ሀብትም  በመታደሉ ከራሱ ፍጆታ ኣልፎ የስሜን ሱዳንን እሩብ  1/4  በላይ የስጋ ፍጆታን በገበያ ይሸፍናል፡፡ በዞኑ ሰሊጥ፣ሙጫ/እጣን፣ ጥጥ፣ማሽላ፣ቀርቀሀ/ሽመል አና ቅመማ-ቅመሞች በስፍት ያመርታል፡፡ በውሀ ሀብትም አንዲሁ አጅግ በጣም የታደለ ሲሆን፣ ኣገር ውስጥ የሚቀሩትን ወንዞች ትተን ኢትዮጵያን ተሻግረው ወደ ሱዳን የሚፈሱ ከዞኑ የሚፈልቁ ወንዞች ብቻ ብናሰላ (1) ግዋንግ (2)ሽንፋ (3)ተከዜ (4) ኣንገረብ (5)ገንዳ-ዉሀ የመሳሰሉ ደንበር ዘለው ኣንድ ሊትር ዉሀ አንኩዋ ለኢትዮጵያ ልማት ሳይውሉ በከንቱ ለሱዳን በየኣመቱ በቢሊይን-ኪቢክ ውሀ ይገብራሉ ፡፡

ወያኔ 26 ኣመታት ሲገዛ ለኣንድ ደቂቃም ቢሆን ከላይ የተጠቀሱትን ወንዞች ለማልማት ይቅር አና ወንዞቹ መኖራቸዉንም የሚያውቅ ኣይመስልም፡፡ በሌላ በኩል ግን፣ ለምሳሌ፣ የኤርትራ አና የትግራይን ድንበር ኣዋሳኝ የሆነው የመረብ ወንዝን (በጋ ይደርቃል) በኣካባቢው ሰላም ኣለመኖሩ እየታወቀ አና ሰላም ከመረጋገጡ በፊት፣ ወያኔ ከወዲሁ “የመረብ ወንዝ ተፋሳስ ልማት ድርጂት” የሚል ተቑዋም  ኣቁቁሞ ብዙ ሚሊዮን ብሮችን ለጥናት ማባከኑን ስንመለከት አንገረማለን፡፡ የጎንደር ደን በኣሁኑ ስኣት በወያኔ ባልተጠና 20 ኣመት ሙሉ በገፍ-ሰፈራ፣ ከሰል ማክሰል አና ሱዳን አንደልቡ ደንበርን ተሻግሮ ደን መጨፍጨፍ ተደማምሮ በተካሄደ ያላሰለሰ ጭፍጨፋ በዉስጡ የሚገኙ ብርቅ የዱር አንሰሳትን ጨምሮ የሀገር ሀብት በገፍ ወድሟል፡፡

ስሜን-ጎንደርን ከ 3 የመሸራረፉ ዋና ኣላማ በዋናነት የጎንደርን ህዝብ ነጣጥሎ ለማዳከም ሲሆን ቀጥሎም በኣካባቢው የሚካሄደውን ጸረ-ወያኔ አንቅስቃሴ-ሀይልን ከፋፍሎ ለመምታት ብሎም ለማጥፋት ያሰበ ነው፡፡ይህ የወያኔ ጸረ-ጎንደር አርምጃ ቅኝ ገዥዎች ተገዥዎችን ለማዳከም ሲጠቀሙበት የነበረ ስልት ነው፡፡ የወያኔ-የነብስ ኣባት የሱዳኑ ኣልበሽርም፣ የዳርፎሩን  ኣመጽ ለመግታት ዳርፎርን ከ 3 ከፋፍሎ ብዙ ጉዳት ማድርሱ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡

ወያኔ ጎንደርን ለመሸንሸን የሰጠው ምክኒያት ሪፕርተር አንደዘገበው (1)ልማትን ለማምጣት (2) ዞኑ ሰፊ ስለሆነ የሚሉ ሰንካላ ምክኒያቶች ናቸው፡፡የሚገርመው እኒህ ወያኔ ያቀረባቸው ምክኒያቶች በ 26 የኣገዛዙ ኣመታት ጊዜ ውስጥ ያልነበሩ ሲሆኑ፣ ኣሁን ወያኔ ችግር ውስጥ ሲገባ በ11ኝው ስኣት ላይ ብቅ ያሉ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ጎንደርን የመሸራረፍ አርምጃ፤ ወያኔ የኣማራ አና የትግራይ ህዝብ ተጣሉ ብሎ ያዞ አንባ በረጨ ማግስት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አርምጃው ከጀርባው እኩይ ኣላማ አንዳለው ኣጠራጣሪ ኣይደለም፡፡ በዚህ ኣጋጣሚ ሊጠቀስ የሚገባው ጉዳይ ቢኖር፣ የትግራይ ህዝብ አና ኣማራው በረጅም ኣብሮ የመኖር ታሪካቸው ውስጥ አንደጎሳ ተፈራርጀው የተናቕሩበት ጊዜ ለኣንድ ሰከንድም ቢሆን ኑሮ ኣያውቅም፡፡ በእርግጥ የወያኔ መሪዎች፣ ወልቃይትን አና እራያን ከመጠቅለል ኣልፈው ጎንደር ላይ ሰራዊት ልከው ደም ቢያፈሱም ቅሉ፣ ለወንጀሉ ተጠያቂዎቹ አራሳቸው የጦር ኣዝማቾች አነ ኣባይ ወልዱ ብቻ ናቸው፡፡

በስሜን-ጎንደር ዞን፣  በጣልያን ጊዜ ከተገነቡ ኣዉራ-መንገዶች ዉጭ የተገነባ ነገር የለም፡፡ በመብራት፣ በትምህርት-ቤት፣በመንገድ ፣ በከተማ ልማት አና በውሀ ኣገልግሎት፤ ወያኔ ዞን ብሎ ከሰየማቸው  ዞኖች ሁሉ ኽዋላ የቀረ ነው፡፡ ዞኑን የማግለል አና የማዳከም ሂደት በኣጋጣሚ የመጣ ሳይሆን በደንብ የተጠና አና ስልታዊ ሴራ ያዘለም ነው፡፡ ከጎንደር ከተማ ውጭ፣በዞኑ የከተማን መስፈረት የሚያሟላ  ኣንድም ከተማ የለም፡፡

(1) ልማትን ለማምጣት ህዝብን መከፍፈል አንደቅድመ ሁኔታ ቀርቧል፡፡ ህዝብን በብዙ ዞኖች መከፍፈል በራሱ ልማት  ያመጣል የሚል የተሳሳተ ፍልስፍና ተቀባይነት የሚኖረው በትልእኮ Open University  በተገኘ የትምህርት መመዘኛ በያዙ ግለሰቦች የተጨናነቀው በወያኔው ኣመራር ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ልማት አና ሰላም የሚመጣው በዋናነት ህዝብ ይወክለኛል ብሎ ያመነበትን ኣመራር በነጻ  ያለ ተጽእኖ በፍላጎቱ ሲመርጥ አና ህዝቡ በኣመራሩ አምነት ሲኖረው ብቻ ነው፡፡  በ26 ረጅም የወያኔ የኣገዛዝ-አድሜ ውስጥ ልማት ጠብ ሲል ያላየ የጎንደር ህዝብ በኣዲስ መልክ ልከፋፍልህ አና ላልማህ ማለት የቀልዶች ሁሉ ኣዉራቀልድ ነው፡፡

(2) ስሜን-ጎንደር ሰፊ ስለሆነ መሸንሸን ኣለበት፡-  (1) ከ30 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በኣንድ ኣስተዳደር ስር ጠርንፎ ባህርዳር ድረስ ህዝብ ለኣቤቱታ ረጂም ጉዞ ተጉዞ ደጅ አንዲጠና የደነገገ ፣ (2) ከ30 ሚልዮን ህዝብ በላይ በኣንድ ኣስተዳደር ስር ጠርንፎ  ኣዳማ/ናዝሬት ድረስ ለኣቤቱታ አጅ አንዲነሳ የደንገገ የወያኔ ስርኣት ዛሬ ዞር ይልና፤  የስሜን-ጎንደር 4 ሚሊዮን  ህዝብን ለማስተዳዳደር ስፍቶብናል አና ይሸንሸን ይለን ጀመር፡፡ አዚህ ላይ አግረመንገዱን መነሳት ያለበት ጉዳይ ቢኖር ፣በጎንደር መሬት ለምነት አና ስፋት የቀናው ወያኔ ሰሞኑን ለብዙ ኣመታት ሲያደባ ከቆየ በሁዋላ ሱዳን የጠየቀውን ለም መሬት ለማስረከብ ካርቱም አና ባህርዳር ላይ ሙሉ ስምምነት ተደርሷል፡፡ይህ የመሬት ማስረከብ ስራ ከተፈጸመ በኻላ ወያኔ የውጭ-ንግዱን በፖርት-ሱዳን አንዲጠቀም ቃል ተገብቶለታል፡፡

ወያኔ ስለ ልማት ሲያወራ ብዙ ትዝብቶችን ይቀሰቅሳል፡፡ የወያኔ ሹሞች፣ በሙስና፣ በግል-ወዳጅነት ብሎም በተቀናበረ ሎቢይ/Lobby፣ በየኣመቱ ብዙ ሚልዮን ብር ወጪ መድበው እነሱ ይቀርበናል እንወደዋለን ብለው ለፈረጁት ዞኖች በገፍ ለኣመታት ያለዩልኝታ ባጀት መድበው ሲያባክኑ አና በግልጽ ሲያደሉ እናውቃለን፡፡ እንዳውም ታሪካዊቷን የጎንደር ከተማን ሌሎች ዞኖች ከኽዋላ ተነሰተው በሁሉም መልክ አንዲበልጧት አና አንዲያዳክሟት የተጠነሰሰውን  ሴራ ሁሉ የምናውቅ ኣይመስላቸውም፡፡ የሚገርመው በዞኑ የሚገኘው ብቸኛ የጎንደር ዩንቨርሲቲ አንኩዋ ከቀጠራቸው ሰራተኞች ውስጥ 68% ከስሜን ጎንደር ዞን ውጭ የመጡ ናቸው፡፡

ወረዳዎችን ከማስፋት አና ከማጥበብ ዉጭ ኣልፎ  የስሜን-ጎንደርን ኣህዳዊ  የኣስተዳደር ኣካል አንደኣምባሻ በዞን መቆራረስ የለየት የወያኔ የጠላት አርምጃ መሆኑን ከወዲሁ በግልጽ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ጎንደርን የማዳዳከም አና ብሎም የማጥፋት እኩይ የወያኔ ህልም አንዲሳካ የሚተባበሩ ሁሉ ነገ በህዝብ ፊት አና በታሪክ ተጠያቂ መሆናቸውን ከወዲሁ በኣንክሮ ፣ በጥሞና ደግመው-ደጋግመው ቢያጤኑት ታሪካዊ ስህተት ከመፈጸም ይታቀባሉ፡፡  ለወያኔ መሳሪያ ኣለመሆን አድሉ ኣሁን እንጂ ነገ ኣይደለም፡፡ ታርክ ነገ እነማን ነበሩ ማለቱን አና ፍርድ መስጠቱን ለኣንድም ሰከንድ ቢሆን ልንዘነጋው ኣይገባም፡፡ ዛሬ ኣልፎ ነገ መኖሩን መዘንጋት የለብነም፡፡ወያኔ አንደማንኛውም ጨቁኝ ኣገዛዝ ወደ ታሪክ ትቢያ መውረዱ ኣይቀሬ መሆኑን ልንጠራጠር ኣይገባም፡

የኢትዮጵያ የፓለቲካ መሰረታዊ ችግር ሌፈታ አና የጋራ መግባብት ሊመጣ የሚችለው ወያኔ ሲወገድ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ያረጀው፣ ሙስናን በግለስራነት የተካነው፣ ህዝብን በጎሳ ከፍፍሎ ኢትዮጵያዊነትን ያዳከመ ብሎም ኢትዮጵያን ለመበታተን ሌት ተቀን ከ40 ኣመት በላይ ብዙ ድንጋዮችን የፈንቀለው የትግራይ ነጻ ኣውጪ ድርጅት/ህወሀትን ወደ ታሪክ ትቢያ መለወጥን ኣስፈላጊ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይም  ነው፡፡ስሜን-ጎንደርን ከ3 አንዳኣንባሻ የመከፈል ሙከራ የወያኔ ኣገዛዝ ከመጨረሻ ሳኣት ላይ መድረሱን ኣበሰሪ ምልከት ነው፡፡

ሰፊው ህዝብ ያቸንፋል፡፡

=================

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s