ትግላችን


ፍፁም አየነው

አገር እና ህዝብ ነፃ የሚወጣው አንዱ ተመልካች ፣ አንዱ ተቀማጭ ፣ ሌላው ታጋይ ሆኖ አይደለም፡፡ ነፃነት የሚገኘው የህዝብ ስሜትንና ፍላጎትን አቀራርቦ ወደ ትግል ሜዳው ማሰለፍ ሲቻል ብቻ ነው፡፡ለዚህ ደግሞ በቅድሚያ ከጥቂቶች ፍላጎት አራማጅነት እና ከቲፎዞ ትግል እራስን መጠበቅ ሚቻል ሲሆን ነው፡፡

ቅድሚያ መሰጠት ያለበት መሬት ላይ ለወረደና እውነተኛ ትግል ላይ ላለው ሃይል መሆን አለበት፡፡ይህ ማለት ደግሞ ከጠላት ባህሪ አንፃር ጠላትን በሚገባው ቋንቋ ለሚያናግረው ህይወት ለሚሸለምበት የነፍጥ የትግል ተዋድቆ መሆን ይኖርበታል፡፡ታዲያ ዛሬ የዘመነ ወያኔ ይህ ግፍና በደል ተራራውን የሰራበት ፣ ሮሮና ጩኸት ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በሀገሪቱ የሚሰማበት ፣ የአገር ሉዓላዊነትና የአገር ፍቅር የጠፋበት አንዱ የዛሬው የዘመነ ህወሃት ወያኔ አገዛዝ ዘመን ነው፡፡ይህ ቅጥ ያጣና የበደል ፅዋ ሞልቶ የፈሰሰበትን አገዛዝን እየታገልን ነው ከተባለ ቅድሚያ እራስን ከፍርሃት አላቆ ለሌሎች ምሳሌ ሆኖ በየትኛውም የትግል ቦታ መንቀሳቀስ መቻል ያስፈልጋል፡፡

ወገኖቼ የእውነተኛ ትግልን ድል ማንም አይቀለብሳትም ስለዚህ ወገኖቼ ከታገል አልቀረ እውነተኛ ትግል እንታገል፡፡ስንታገልም ሆደ ሰፊና ቆዳ ድርጁ ሆነን እንታገል፡፡ሆኖ መታገልንም እኛ ከትግሉ ተምረናል፡፡የጎንዮሽ ትግሉን ትተን ሙሉ ትኩረታችንን የፊት ለፊታችን ያለው ጠላታችን ላይ መሆን አለበት፡፡እንኳን የራሳችንን ወገን የሆነ ዜጋ ይቅርና ባዕድ የሆነን የውጭ ዜጋን ሊያሳምን የሚችል እውነተኛ የሆነ ወደ እዚህ መራራ ትግል ያስገባን ከበቂ በላይ የትግል መነሻ አለን፡፡በተጨማሪም ጤነኛ ሰው መሆን በራሱ ብዙውን ነገር ይመልሳል፡፡

በማስመሰል ለችግሮች ዘለቄታዊ መፍትሄ መፍጠር አይቻልም ፤በመፍርሃትም ሞትን ማምለጥም ሆነ ህዝብን ማዳን አይቻልም ፤በውሸትም አገር ገንብቶ ማፅናት አይቻልም፡፡መፍትሄ የሚሆነው በመከባበር ፣በመቻቻል ፣በአንድነት እና በፅናት የታነፀ እውነተኛ ትግል መታገል ስንችል ብቻና ብቻ ነው፡፡ይህን ስናደርግ ነው የጋራ አገር መገንባትም ሆነ የሁላችንም ጠላት የሆነውን ስርዓተ ወያኔን አሸንፈን የድል ፍሬያችንን ከተሳካልን ልናይም አልያም ልናሳይ የሚቻለው፡፡

እኔ ታጋይ ነኝ፤ያ ማለት ደግሞ የምኮራበትና የምደሰትበት ክቡር አላማ እና ራዕይ አለኝ፡፡እኔ የምታገለው በመከራና በፈተና የነጠረ ፣ በውጣውረዶች በፅናት ተጉዞ አልፎ እየጎመራ በሚገኝ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ነው፡፡ይህን ስል በወጀብ የማይናወጥ ፣በጩኸት የማይናጋ ክቡር የሆነ የሰው ልጅ ህይወቱን ስለ ሰው ልጅ ነፃነት ከሚሰጥበት የተከበረ የትግል መስመር ነው፡፡

እውነተኛ ትግል ያሸንፋል!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s