ኢት-ኢኮኖሚ – የኢህአዴግ የግል ማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት!!! ‹ወዶ ዕዳ!!!› ‹እያዩ ገደል!!!› ‹ቡሌ ሴና!!!› – ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

(ክፍል ሦስት)

አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን ተቀEማት፣በኢትጵያ ብሄራዊ ባንክ  የተመዘገቡ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ የሚያሰባስቡት ከደሃው ህብረተሰብ ዘንድ ነው፡፡ ማክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች ለድህነት ቅነሳ እንደሁም ኃብትና ንብረት ማፍሪያ በአነስተኛ የብድር አቅርቦትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሥራ እንዲፈጥሩና የቁጠባ ባህል  እንዲያዳብሩ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ በሌሎች አገሮች ልምድ መሠረት ማክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለደሃ የህብረተሰብ ክፍል፣ ብድር በማቅረብ፣በዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ በማበደር፣በብሄራዊ ባንክ ቁጥጥርና ህግና ደንድ መሠረት ሥራቸውን እንዲከውኑ ይደረጋል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽንስ ዋነኛ ዓላማዎች ውስጥ በህብረተሰቡ ውስጥ ድህነትን ለመቀነስና ደሃ የህብረተሰብ ክፍሎች ገቢያቸውን ከፍ እንዲያደርጉ የግብርና ምርታቸውን እንዲያሳድጉ፣ሌላ የገቢ ምንጭ በመፍጠር የቤት ዕቃቸውንና ንብረት እንዲያፈሩ ማድረግ ነው፡፡  ይህን ዓላማ ለማሳካት ደግሞ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትን በህብረተሰቡ ውስጥ ማስፋፋትና ዘላቂ የማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽኖችን በሃገሪቱ ሁሉ መመሥረት  ዋነኛ መርሃቸው ነው፡፡ ኢንስቲቲውሽኖቹ ህብረተሰቡን ያሳተፉ፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ ገበሬዎችን ወዘተ በማሳተፍ የቁጠባ ባህልን የሚያበረታታና ዘለቄታ ያለው የገንዘብ ምንጭና ተደራሽነት ያለው ስራ መከወን ነው፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽኖችን፣ ለደሃው ህዝብ ዘለቄታዊ የገንዘብ ምንጭ በመሆን አገልግሎት መሥጠት ዋነኛ ዓላማቸው ሲሆን፣ የተቀEማቱ የትርፍ ማግኛ ሥራ ዋነኛ ዓላማቸው አይደለም፡፡

የህወኃት/ኢህአዴግ የግል የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን ተቀõማት በኢትዩጵያ ባለፈው 26 ዓመታት፣

የፋይናንስ ዘርፍ አደረጃጀት፤ የአነስተኛ የብድርና ቁጠባ የባንክ አገልግሎት  አሰጣጥ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደደረሰ የተለያዩ ድርሳናት ስለ ማይክሮፋይናንስ ድርጅቶች ያተቱትን ጥናታዊ ዳሰስ እንቃኛለን፡፡ በኢትዩጵያ 34 የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን ተፈጥረዋል፡፡ በሃገራችን የማይክሮ ፋይናንስ ተማት፣ የፋይናንስ ዘርፍ የተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎች አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጎል፡፡ በኢትዩጵያ የማይክሮ ፋይናንስ ተማት አፈጣጠር በአውራው ፖለቲካ ጃንጥላ ስር የተደራጁ ሲሆኑ፤ አንዳንዱ በብሄር፣ አንዳንዱ በፓርቲ፣ ሌላውም በሃይማኖት የተቋቋሙ ናቸው፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተማት አገልግሎት በየክልሎቹ የፖለቲካ ፓርቲ ስር የተዋቀሩ ያለተወዳዳሪ እንዲሠሩ የተፈቀደላቸውና እውነተኛ ውድድር ላይ ያልተመሠረቱና ለአገር በቀል የፋይናንስ ገበያ እኩል ሜዳ ያላገኙ የማይክሮ ፋይናንስ ተማት ናቸው፡፡ በዙህ ያልተስተካከለ የማይክሮ ፋይናንስ ተማት ገበያ ውስጥ አምስቱ የማይክሮ ፋይናንስ ተማት በገዠው ፖለቲካ ፓርቲ ቀንበር ሥር የሚዘወሩ፣ ህብረተሰቡን በመበዝበዝና አድሎዊ ሥራ በመሥራት እንዲሁም የአንድ ለአምስት አደረጃጀትና የስለላ ሥራ ላይ በመሠማራት ያገለግላሉ፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ መንግስታዊ የግል የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን ተቀõማት በግብርና ዘርፍ ኤክስቴንሽን መርሃ-ግብር ለገበሬዎች የምርጥ ዘርና የኡሪያና ዳፕ ማዳበሪያ ብርድ በማቅረብ ብድር መክፈል ያልቻሉ ገበሬዎችን በሬዎች በመሸጥ 8.7 ሚሊዩን አርሶአደሮችን በረሃብ አለንጋ የከተቱ የብድር ተቀõማት ናቸው፡፡ እነዚህ መንግስታዊ የግል የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን ተቀõማት በሃገሪቱ 467,000 ሽህ የብድር ደንበኞችን 92 በመቶ በማቀፍ ደሃ አርሶአደሮችን ያራቆቱ፣በተደጋጋሚ ድርቅ ያስጠቁ፣ ከልጆቻቸው ጉሮሮ ነጥቀው ኃብትና ንብረታቸውን ያከማቹ ማፍያ ድርጅቶች ናቸው፡፡ በአምስቱ የማይክሮ ፋይናንስ ተማት፣ ቢዝነስና በንግድ ሥራ ብድር እየተመቻቸላቸው ተጠቃሚ የሆኑ ሚሊየነር የሆኑ ሹማምንትና ካድሬዎች ብዙ ናቸው፡፡

Government supported MFIs have contributed largely to the growth and development of the MFI industry. Among the 20 registered MFIs, six are supported by the regional governments of Tigray, Amhara, Oromia, Southern People’s Nation, Addis Ababa, and Benishangul. The regional government of Dire Dawa has an application pending with the National Bank of Ethiopia. Regional governments support these MFIs financially and through grassroots level government administrative organizations. MFIs supported by the regional govern-ments typically have extensive geographic spread across weredaswithin their regions. A large majority of their clients are from rural households (except Addis Ababa region). One feature of the government supported MFIs is that they offer both agricultural and non-agricultural credit. A portion of the agricultural credit is extended under a somewhat controversial government agricultural extension program to provide term credit for seeds and fertilizer. Recent figures show that government backed MFIs have approximately 467,000 outstanding clients, or 92 percent of all microfinance clients in Ethiopia. በ2000 እኤአ በኢትዩጵያ የአነስተኛ ማይክሮ ፋይናንስ ተቀõማት የኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች የግል ንብረቶች በመሆን ያላቸው ካፒታልና ብድር የወሰዱ አባላቶች ቁጥር በመረጃ ያስቃኛል፡፡

{1} አማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ A mhara Credit and Savings Institution (S.C)፣ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ንብረት የሆነው የአማራው ጥረት፤የልማት ማህበርና መልሶ ማቋቋም ድጋፍና በአቶ ታደሰ ካሣ( Deputy Head of Government፣Head of Capacity Building Bureau,Amhara National Regional Government) እና በአቶ መኮንን የለምወሰን መስራችነት( General Manager, (Bahir Dar)) በ09/04/97 እኤአ ባህር ዳር ከተማ የተመሠረተ ሲሆን፣ በ2000 እኤአ የአማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ 103.2 ሚሊዩን ዶላር 694,993 ብድር የወሰዱ አባላት ነበሩት፡፡

{2} ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ንብረት የሆነው የኦሮሚያው ቱምሳ፤የልማት ማህበርና መልሶ ማቋቋም ድጋፍና በአቶ ተሸመ ለገሰ መስራችነት በ04/08/97እኤአ አዲስ አበባ የተመሠረተ ሲሆን፣ በ2000 እኤአ ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ 30.8 ሚሊዩን ዶላር 165,464 ብድር የወሰዱ አባላት ነበሩት፡፡

{3} ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ህዝባዊ ወያኔ ሃርነነት ትግራይ (ህወኃት)ንብረት የሆነው የትግራዩ ኢፈርት፣ የልማት ማህበርና መልሶ ማቋቋም ድጋፍና በአቶ ዩሃንስ ገብረመስቀል መስራችነት በ28/04/97 እኤአ መቐለ ከተማ ውስጥ የተመሠረተ ሲሆን፣በ2000 እኤአ ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን96.3 ሚሊዩን ዶላር 397,000 ብድር የወሰዱ አባላት ነበሩት፡፡

{4} ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ፣የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ) ንብረት የሆነው የደቡቡ ወንዶ፤ የልማት ማህበርና መልሶ ማቋቋም ድጋፍና በአቶ ሙስማ ቻሊ መስራችነት በ01/10/97 እኤአ አዋሳ ከተማ ውስጥ የተመሠረተ ሲሆን፣በ2000 እኤአ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ፣ 31.4 ሚሊዩን ዶላር 327,888 ብድር የወሰዱ አባላት ነበሩት፡፡

{5} አዲስ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ በህወኃት/ኢህአዴግ ንብረት በሆነው የልማት ማህበርና መልሶ ማቋቋም ድጋፍና በአቶ አዋሽ አብተው መስራችነት በ27/01/00 እኤአ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተመሠረተ ሲሆን ፣በ2000 እኤአ አዲስ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ 30.8 ሚሊዩን ዶላር 165,464 ብድር የወሰዱ አባላት ነበሩት፡፡

በኢትዩጵያ የነዚህን የአነስተኛ ማይክሮ ፋይናንስ ተቀõማት የንግድ እድገት በማየት እውን ለደሃው ህብረተሰብ ድህነትን ለመቅረፍ ሳይሆን ለትርፍ የቆሙ መሆናቸውን ማስተዋል ይቻላል፡፡ከተቀEማቱ ተበድሮ መክፈል ያልቻለ ዜጋ የቤት ንብረቱ ተሸጦ፣በሬው ተሸጦ ወዘተ እንዲከፍል በማድረግ የተገኘ ትርፍ መሆኑ ገሃድ ነው፡፡  ከ2000እስከ 2013 እኤአ ባለው 13 ዓመታት ያሳዩት እድገት የትየለሌ ነው፡፡ በኢትዩጵያ  የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት መረጃ፣ድረገጾች በመዝጋትና በመንፈግ ይታወቃሉ ለዚህ ነው በተገኘው መረጃ ብቻ ላይ ተመርኩዘን የምናቀርበው፡፡ ሌላው ተቀEማቱ የኦዲት ሪፖርት አድርገው አያውቁም እንዲሁም ለህዝብ በሚዲያና በጋዜጦች የኦዲት ሪፖርት አቅርበው አያውቁም፡፡

በ2000 እኤአ በኢትዩጵያ  የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት አጠቃላይ ካፒታል፣ብድር የወሰዱ አባላት·        በ2000እኤአ 292.5 ሚሊዩን ዶላር (የውጪ ምንዛሪ ተመን አንድ ዶላር=8.15 ብር ነበር)ስለዚህ 2 ቢሊዩን 384 ሚሊዩን ብር ብድር ያበደሩ ሲሆን፣ የፋይናንስ ተቀEማቱ 1,750,809 ብድር የወሰዱ አባላት ነበራቸው፡፡

·        በ13 ዓመታት ውስጥ ያካበቱትን አጠቃላይ ካፒታል፣የኃብትና ንብረት ክምችት፣እንዲሁም የቁጠባ ተቀማጭ ገንዘብ በማየት እነሱ ሲያድጉ 8.7 ሚሊዩን ህዝቡ በተለይ የምርጥ ዘርና የማዳበሪ ዕዳ ያልከፈሉ ገበሬዎች  እዳቸውን ለመክፈል በሬቸውን እየተሸጡ ለርሃብ ተዳርገዋል፡፡ በጥናቱ ገበሬዎች  ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ነበር፡፡

·        በኢትዩጵያ  የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት፣የብድር ወለድ ምጣኔ ከ9.9 እስከ 18 በመቶ መሆኑ ደሃውን ህብረተሰብ ሊከፍል በማይችለው ዕዳ ውስጥ ከቶት ማህበራዊ ቀውስ አስከትሎል ማለትም ለጎዳና ተዳዳሪነት፣ ለሥራ አጥነት፣ ለሽርሙጥና፣ ለስደት፣ ወዘተ ተዳርጎል፡፡ የገጠሩና የከተማው ህዝብ አንዱ የስደት ምክንያት የነዚህ ተቀEማት ዓይን ያወጣ ብዝበዛ ነው፡፡       

በ2013/14 እኤአ በኢትዩጵያ  የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት አጠቃላይ ካፒታል፣የቁጠባ ተቀማጭ ገንዘብ፣የብድር አቅርቦትና ንብረት  

·        አጠቃላይ ካፒታል፣ እንደ ብሄራዊ ባንክ መረጃ መሠረት በ2013/14 የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት አጠቃላይ ካፒታል 5.7 ቢሊዩን ብር ሲሆን 24.6 በመቶ መጨመሩ ተገልፆል፡፡

·        የኃብትና ንብረት ክምችት፣የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት አጠቃላይ የኃብትና ንብረት ክምችት 24.5 ቢሊዩን ብር ሲሆን 38.6 በመቶ መጨመሩ ተገልፆል፡፡

·        የቁጠባ ተቀማጭ ገንዘብ፣የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት አጠቃላይ  የቁጠባ ተቀማጭ ገንዘብ፣13 ቢሊዩን ብር ሲሆን የአባላቱ ቁጥር 2.6 ሚሊዩን በ2012 እኤአ እንደደረሰ ተገልፆል፡፡

·        በኢትዩጵያ እነዚህ የመንግሥት ፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ዘርፍ በተለይ  አምስቱ የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት ማለትም፣ የአማራ፣ ደደቢት፣ ኦሮሚያ፣ ኦሞና፣ አዲስ ፋይናንስ ተቀEማት  93.6 በመቶ የቁጠባ ተቀማጭ ገንዘብ፣ እንዲሁም 90 በመቶ የብድር አቅርቦትን ድርሻ ይቆጣጠራሉ፡፡

MFIS TOTAL CAPITAL DEPOSIT MOBILISATION, CREDIT PROVISION AND ASSETS The NBE annual report (NBE 2015b) suggested in 2013/14 the overall performance was positive and total capital had increased by 24.6% (to Birr 5.7 billion) while assets grew by 38.6% (to Birr 24.5 billion). At the same time, deposit mobilisation and credit provision had expanded. According to the second quarterly report for 2015 (NBE 2015a) MFIs mobilised Birr 13 billion in the form of savings. However, although the number of active clients has been increasing (2.6 million, by the end of 2012), MFIs operating in Ethiopia are estimated to have met less than 20% of the demand for financial services (Wolday 2012). The overwhelming majority of the population has no access to financial services, but by providing financial services to micro-enterprises in both urban and rural areas, MFIs are a key route to financial inclusion (Zwedu 2015). Nevertheless, MFIs are expected to provide much of the financial intermediation for communities with low access to formal financial institutions over the coming years. Microfinance provision in Ethiopia is highly concentrated, with the five largest MFIs (Amhara, Dedebit, Oromia, Omo and Addis Credit and Savings Institutes) together accounting for 93.6% of the savings and 90% percent of the credit of the MFI sector. The strength of the regional MFIs means that there is a low level of competition in the industry. ( Inclusive Growth: Ethiopia Country Report)

ኢህአዴግ ፓርቲዎች የተፈበረኩ ማይክሮ ፋይናንስ ተቀማት  Party machine MFIs  በኢትዩጵያ በኢህአዴግ ፓርቲዎች የተፈበረኩ የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት በመንግስታዊ ዘርፍነት፣ በክልል ፓርቲዎቹ ንብረት ባለቤትነትና የሚንቀሳቀሱትም በካድሬ አባሎቻቸው ነው፡፡ እነዚህ ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች ንብረት የሆኑ የአውራው ፓርቲ የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽንስ  ድርጅቶች ከኢትጵያን ብሄራዊ ባንክ ፍቃድ ተሰጥቶቸው በአዲስአበባ ከተማና በክልሎች ውስጥ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ {1} አማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣{2} ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣{3} ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ {4} ኦሞ ማይክሮፋይናንስ፣ {5} አዲስ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ {6} ቢኒ-ሻንጉል ጉሙዝ ማይክሮ ፋይናንስ  {7} ድሬ ዳዋ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽንስ  በዋናነት ሲገኙበት ሁሉም በነፃነት በግሉ ዘርፍ  የተመሠረቱ የብድርና ቁጠባ ተቀEማት እንደሆኑ ለህብረተሰቡና ለዓለም ህብረተሰብ በውሽት ይተውናሉ፡፡  በአጥኝዎቹ በተለይ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ባገኙት ከህዝብ ቃለምልልስ መረጃ መሠረት እነዚህ የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት መነሻ ፍሬ ካፒታላቸውን ያገኙት ከክልል መንግሥት፣ ከክልል በጎአድራጎትና መልሳ ማቀEቀEም ተቀEማት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማቱ፣የክልሉ መንግሥት፣ ሹማምንትና ካድሬዎች ዋናዎቹ ባለአክሲዩኖች/ ሼር ሆልደርስ ተጠቃሚ ሲሆኑ የሚገኘውን ትርፍና የፋይናንስ ገበያ ከፍተኛ ድርሻ ‹በደሃ ስም› በመነገድ ይገኛሉ፡፡ The MFIs we section in this category are all owned and run by regional governments and party members of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRDF).These are namely Amhara Credit and Saving Institution S.C, Addis Credit and Saving Institution S.C., Benishangul Gumuz Micro finance S.C, Dedebit Credit and Saving Institution S.C., Diredawa Micro finance Institution S.C, Omo Micro finance Institution S.C, and Oromia Credit and Saving Institution S.C. They all act and reach the mass and international community as ‘independent’ MFIs,  however, the populous we interviewed in the Amahra and Oromia region perceive them rather as ‘partial’. These MFIs received their major funding (seed money) from their respective regional governments and endowments . The regional governments and their top cadres are the major shareholders in these MFIs making them the highest profit makers out of these so called ‘pro poor’ MFIs.  ( “Poor Helpers” or “Poor Killers?”

አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቀEማት የገንዘብ ምንጭ Source of funds

የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት የገንዘብ ምንጭ አንደኛ ከአባላቱ ተቀማጭ የገንዘብ ቁጠባ የሚገኘው 50 በመቶ ድርሻ ሲኖረው፣ ሁለተኛ ከክልል መንግሥታት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የውጭ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ቤተክርስቲያኖች፣ ሌሎች ድርጅቶች የሚሠጦቸው የገንዘብ ምንጮች ናቸው፡፡‹‹Overall, savings as a percentage of outstanding portfolios exceed 50 percent (IFAD 2001). As an important service for clients and source of funds for MFIs, savings mobilization will remain central to their future strategies.Besides savings, donated equity finance from regional governments has been a critical source of capital for government supported MFIs. Other sources of donated equity finance for MFIs include donor organi-zations, foreign NGOs, churches, other associations and (Annex 1).Support for equity capitalization of MFIs from international donors has been relatively modest to date. Up to now, Sida is one of the few bilateral (or multilateral) donors to provide large amounts of capital funding through its support for the Amhara Credit and Savings Institutions (ACSI). Most donor organizations have preferred to support capacity building. So far, loans – soft and commercial – have not played a role as a source of MFI funds. This is all about to change if/when the Interna-tional Fund for Agricultural Development’s (IFAD’s) Rural Financial Intermediation Programme (RUFIP) is approved. This program will provide large amounts of capital funds to MFIs through both loans and grants (Annex 2).

አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቀEማት የጋራ ብድር አሰራር ስርዓት (MFIS GROUP LENDING METHODOLOGY)

ማስረጃው በተጠናቀረበት ጊዜ በኦሮሚያ 242 እና በአማራ 229 አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ቅርንጫፍ ተቀEማት  ሲኖራቸው ተደራሽነታቸው ደግሞ 80 በመቶ በገጠርና 20 በመቶ በከተማ መሆኑ ታውቆል፡፡ የብድር አገልግሎት አሰጣጡ የቡድን ከ5 እስከ 7 አባላቶች በጋራ ኃላፊነት ለንግድና ለግብርና ዘርፍ ብድር መበደር ሲችሉ አንዱ አባል ለሌሎቹ ወይም ሁሉም በመያዣነት (collateral) ተጠያቂ ናቸው፣እንዲሁም ብድር የመክፈልም ኃላፊነት የተጣለው ፣በቡድኑ አባላቶች የጋራ ኃላፊነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ አንዱ ባጠፋ ሌላው ተጠያቂ የሚደረግበት የጋራ ብድር አሰጣጥ ስርዓት በሌላው አገር የሌለና ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ዘይቤ ነው፡፡ At the time the data was recorded, Oromia and Amhara had the largest number of branches, 242 and 229 respectively, and both had a predominately rural focus (with less than 20% urban clients). The most popular financial products were loans intended for business or agriculture, which used the group lending methodology. These entry-level group solidarity loans, where typically 3-7 members provide collateral or a loan guarantee through a group repayment pledge, are frequently regarded as the first step towards the use of proper banking services, enabling farmers or MSEs to build up the credit history necessary to be eligible for an individual loan (Wolday 2012).

የባህር ማዶ ሃገራት ተሳትፎ፣Foreign Participation ሞኒተሪና የባንክ አዋጅ ቁጥር 84/1994 ዓ/ም የኢትዩጵያ የንግድ ህግ የውጪ ዜጎች የባንክ ንግድ ውስጥ በኢትዩጵያ ያግዳል፡፡ በባንከ ዘርፍ አንድ ግለሰብ ከ20 በመቶ የአክሲዩን ድርሻ በላይ ሊኖረው አይችልም ብሎ ደንግጎል፡፡ በፋይናንስ ዘርፍ የውጪ ኢንቨስትመንት በየትኛውም መንገድ የተከለከለ እደሆነ ተፅፎል፡፡‹Monetary and Banking Proclamation No. 84/1994 of the Ethiopian Business Law precludes a foreign national from undertaking banking business in Ethiopia, and no person is permitted to own more than 20% of a banking company’s shares. Financial foreign investment, including the banking business in whatever form, is prohibited.›

የአምስቱ አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቀEማት የብድር ወለድ ምጣኔ ከ9.9 እስከ 18 በመቶ ነው! (LENDING INTEREST RATES OF THE FIVE LARGEST MFIS VARY FROM 9.9% TO 18% ) የአምስቱ ማይክሮ ፋይናንስ ለተበዳሪ አባሎቻቸው ለአንድ ግለሰብ ብድር ከፍተኛው ጣሪያ 5,000 ብር ሲሆን  የብድር ወለድ ምጣኔ ከ9.9 እስከ 18 በመቶ ነው፡፡ (አነስተኛ የፋይናንስ ተቀEማት ከአደጉ በኃላ አንድ ግለሰብ 10,000 ብር ለተቀEማት ሥራ ማስኬጃና ልዩ ልዩ ወጪዎች ከፍሎ ከፍተኛው ጣሪያ 50,000 ብር ብድር መውስድ ይችላል፡፡)የተቀEማቱ ደንበኞች፣ የተአነስተኛና ጠቃቅን ኢንተርፕራይዝ፣ አነስተኛ ነጋዴዎች፣ የግብርና ዘርፍ፣ የቤት ሰሪዎች ማህበራት፣የግሩፕ/የቡድን  ብድር መሥርተው በከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ይበደራሉ፡፡

አባላቶች የግዴታና የፍቃደኝነት ቁጠባ፣ (COMPULSORY AND  VOLUNTARY SAVING) የመተግበር ግዴታ አለባቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይሄ የብድር ምጣኔ ዝቅተኛ ነው ቢሉም፣ የብድር ተቀEማቱን ወጪ አይሸፍንም ቢሉም፣ የእኛ አድርባይ ምሁራን በየዓመቱ ከደሃው ህብረተሰብ በዘረፉት ትርፍና ከሚገነቡት ፎቅ ቢሮዎችና ቅርንጫፍ አነስተኛ ባንኮች እንዲሁም ከሚቀጥሩት የሠራተኛ ብዛት በደሃው ስም፣ እራሳቸውን እንደጠቀሙ  የምጣኔ ኃብት ጠበብት መሆን አይጠይቅም፡፡ አዲስ ማይክሮ ፋይናንስ፣በአንድ ሚሊዩን ብር ካፒታል የተመሠረተው ድርጅት ዛሬ 800 ሚሊዩን ብር ካፒታል እንደደረሰና እድገቱም፣በሰማንያ ሽህ ፐርሰንት ሲመነደጉና፣በዓመት በአማካይ 47 ሚሊዩን ብር በላይ ትርፍ ሲዝቁ በቀበሌና ገበሬ ፍርድ ሸንጎ የደሃውን ገበሬ በሬ ሸጠው፣ የጉልት ሻጮን የቤት ዕቃ ሸጠው የተገኘ ኃብት ነው፡፡

ደሃ አዳኝ! ወይስ ደሃ ገዳይ!!! “Poor Helpers” or “Poor Killers?”

እነዚህ ‹ደሃ አዳኝ› የተባሉት የአነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቀEማት አገልግሎት ለማግኘት ተጠቃሚ ብድር ተበዳሪ አባላቶች መንግሥትን እንዲደግፉና የገዢውን ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ተጠይቀው ፍቃደኛ ባልሆኑት ላይ የሚፈጸም፤ የማግለል፣ የአድሎና የማስፈራራት ሥራዎች እንዳሉ ተረጋግጦል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማቱ ከመንግሥታዊ ድርጅቶች ጋር ማለትም ከቀበሌ ፅህፈት ቤቶች፣ ከሴቶች፣ ወጣቶች ማህበራት፣ ከገበሬ ማህበራት ጋር በጣምራ በመስራት የፖለቲካ ሥራና የስለላ ሥራ ‹አንድ ለአምስት› አደረጃጀት በህብረተሰቡ ላይ የስለላ ተግባር እንደሚፈጽሙ በአጥኝዎች ተረጋግጦል፡፡ ብድር መክፈል ያልቻሉ አባላት በቤተሰብና በብድናቸው ብድራቸውን እንዲከፍሉ ተመክረው በመጨረሻው በመንግሥታዊው የቀበሌ የፍርድ ሸንጎ ቀርበው ይዳኛሉ፡፡  ዳኞቹ የህግ ትምህርትና ዕውቀት ስለሌላቸው ፍትሃዊ ያልሆነ፣ የዝምድና ስራ፣ አድሎና  ጉቦ በመቀበል ይሰራሉ፡፡ በቀበሌ የፍርድ ሸንጎ ፍርደ ገምድልነት ብድር የወሰዱ አባላቶች የቤት ንብረታቸው ተሸጦ ዕዳ እንዲከፍሉ ተደርጎል፣በሬቸው ተሸጦል፣ በዚህም ምክንት ህይወታቸውን ያጠፉ፣ ለጎዳና ተዳዳሪነትና  ለሽርሙጥና ሥራ የተዳረጉና ለእስራት የተዳረጉ ይገኛሉ፡፡ “The regime uses MFIs to present itself as a capitalist, liberal government, pro poor, and socially responsible as well while it fundamentally uses them as grassroots organisations of spying and controlling the community.” Says an Ethiopian, Associate Professor of Development Studies, opting to remain anonymous.MFIs are sarcastically described in the colloquial of clients and non clients of MFIs in Amhara and Oromia regions respectively as ‘Wedo Eda’,‘Eyayu Gedel’ and ‘Bollo Senee’ both literally translated as ‘entering a hole’. This describes how MFIs are viewed within the local community, explaining their ‘suicidal’ nature.

የኢትዩጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ተቀማት አጭር ጥናት Ethiopia MFIs study 

{1} አማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን ( Amhara Credit and Savings Institution (ACSI)  ለ17 አመታት በድህነት ቅነሳ መርሃግብር ተሰማርቻለሁ የሚለው ተቀõም በህዝብ ዘንድ፤‹ወዶ ዕዳ!!!›( ‘Wedo Eda’) በመባል ይታወቃል፡፡አማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን ጀነራል ማናጀር መኮንን የለውምወሰን፣ኢህአዴግ ብአዴን በቸረው የተፈቀደ ፍሬ ካፒታል የተመሰረተ መሆኑን ግን ደብቀዋል፡፡ የብድርና ቁጠባ ተቀõሙ በባህር ዳር ከተማ ዋና መሥሪያ ቤቱን ፎቅ ገንብቶል እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቶል፡፡ በ2017 እኤአ የድርጅቱ ሠራተኛች ቁጥርም ከ60 ወደ  12,200 ሽህ አሳድጎል፡፡ እንደ ማናጀሩ ገለፃ የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጅ በመተግበር ድህነትን በመቀነስ በ2025 እኤአ ሃገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ ሃገራት ጎራ ለመቀላቀል አቅዶል፡፡ የአማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን 50 በመቶ ለመንግስት የግብርና ልማት ድጋፍ ያደርጋል፡፡ አማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን 4459511 ሚሊዩን ደንበኞቹ ከ8 ቢሊዩን ብር ተቀማጭ ገንዘቡ  በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ማስቀመጡ ተመዝግቦል ብለዋል፡፡ (የነፍስ ወከፍ አማካይ 1,794 ብር ተቀማጭ ገንዘብ አስቀምጠዋል) ድርጅቱና ሌሎች ሦስት ተመሳሳይ የፋይናንስ ተቀEማት 13 በመቶ የገንዘብና ቁጠባ አገልግሎት ሽፋን  ተደራሽነት በአማራ ክልል ውስጥ አላቸው፡፡ Amhara Credit and Saving Institution (ACSI), General Manager Mekonnen Yelewumwosen for his part said the Institution has upgraded its human power from 60 in 1997 to 12, 200 in 2017…. “Our Institution has 50 percent contribution to the agricultural development of the state,” he stated….According to the General Manager, its 4,459,511 clients have saved more than eight billion Birr in last Ethiopian fiscal year—which ended on July 7.

{2} ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን (Oromia Credit and Savings Institution (OCSI) ከተቆቆመ አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በድህነት ቅነሳ መርሃግብር ተሰማርቻለሁ በውሽት ቢልም ተቀõም በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ፤‹ቡሎ ሴና!!!› (‘Bollo Senee’)በመባል ይታወቃል፡፡ የአነስተኛ የብድርና ቁጠባ ባንክ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሁለት በመቶ ሽፋን ብቻ እንዳለው ተገልፆል፡፡ በ2011 እኤአ 1ቢሊዩን 280ሚሊዩን አጠቃላይ ካፒታል፣ 242 ቅርንጫፎች፣503,000 ብድር የወሰዱ ደንበኞች ነበሩት፡፡ተቀõሙ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ማለትም፣ ኬር ኢንተርናሽናልና፣ካቶሊክ ሪሊፍ ስርቪስ፣ ግሊመር ኦፍ ሆፕና ሲአይዲአር በጎአድራጎት ድርጅቶች የብድር ተቆሙ እርዳታ አግኝቶል፡፡( Care International, Catholic Relief Services, A Glimmer of Hope, CIDR etc.)

{3} ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን (Dedebit Credit and Savings Institution (DECSI)

በህወሃት የፖለቲካ ድርጅት በ1987 የተመሠረተው (ትእምት) ኢፈርት የንግድ ድርጅት  ሁለት ክንፎች፤ አንደኛው ክንፉ የኢንቨስትመንት መዓከል ሲሆን ሁለተኛው ክንፉ ደግሞ በጎአድራጎት ማዕከል ነበር፡፡ ህወሓት የኢኮኖሚ ምሶሶ የሆነው ኢፈርት የቢዝነስ ኢምፓየር በኢትዩጵያ የግሉን ዘርፍ ባለኃብት ሥራዎችን በመንጠቅ የሃገሪቱን የፋይናንስ፣ የመሬት፣የማዕድን ኃብት በሞኖፖል የሚቋጣጠር የማፍያ ድርጁት ነው፡፡ በ1994 እኤአ በመንግሥታዊ ባልሆነ የበጎአድራጎት ድርጅት(“NGO”) ስም የተመሠረተው  Rural Credit Scheme of Tigray (RCST)  ብሎም ማህበረ ረድኤት ትግራይ (Relief Society of Tigray (REST) 1997 እኤአ ወደ ‹ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን. ወይም ‹‹ደደቢት ትካል ልቓሕን ዕቀEርን አ/ማ›› በሚል ስያሜ  ተመሰረተ፡፡ ደደቢት ያገለገሉ ጀነራል ማናጀር በአቶ ዩሃንስ ገብረመስቀል/ አቶ አታክልቲ ኪሮስ፣ ከህወኃት ኢህአዴግ ሬስት  በቸረው የተፈቀደ ፍሬ ካፒታል እንደተመሰረተ ገልጸዋል፡፡ የብድርና ቁጠባ ተቀõሙ በመቐለ ከተማ ዋና መሥሪያ ቤቱን ፎቅ ገንብቶል እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ 142 ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቶል፡፡ በ2011 እኤአ ካፒታሉን በማሳደግ  1 ቢሊዩን 800 ሚሊዩን ብር መድረሱ ተገልፆል፡፡ እንዲሁምደደቢት ብድርና ቁጠባ 397,000 ብድር የወሰዱ አባላት እንዳሉት ተገልፆል፡፡  የደደቢት  በትግራይ ክልል ውስጥ የ84 በመቶ ሽፋን ሲኖረው ከመላ ሃገሪቱ ከፍተኛውን የሽፋን ድርሻ እንዳለው ተረጋግጦል፡፡ ለደደቢት፣ ከዓለም ዓቀፍ ለጋሾች ዘንድ ከተበረከተለት ንዋይ መኃል የኒዘርላንዱ ኖቪብ፣ የኖርዌጂያን ህዝባዊ እርዳታ፣ ሴስኦኤስ ፋይም ቤልጅየም ሉዘምበርግ በጎ አድራጊዎች ይገኙበታል፡፡Thus, following the legal framework provided by the national proclamation in 1996 (proclamation 40/96), RCST was transformed into a quasi-private ‘business oriented’ microfinance institution in 1997 and subsequently renamed Dedebit Credit and Saving Institution (DECSI). Like many MFIs, DECSI has benefited from international donor funding, particularly at early stages. Among its notable donors are NOVIB (the Netherlands), Norwegian People’s Aid (Norway), and SOS Faim (Belgium and Luxembourg).

{4}የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ፣ Omo Microfinance Institution ከተቆቆመ አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በድህነት ቅነሳ መርሃግብር ተሰማርቻለሁ በውሽት ቢልም ተቀõም በደቡብ ህዝብ ዘንድ፤‹ቡሎ ሴና!!!› (‘Bollo Senee’) በመባል ይታወቃል፡፡ የአነስተኛ የብድርና ቁጠባ ባንክ በደቡብ ክልል ውስጥ የሁለት በመቶ ሽፋን ብቻ እንዳለው ተገልፆል፡፡

{5}አዲስ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን Addis Credit and Saving Institution S.C., ለሁለት አስርታት በድህነት ቅነሳ መርሃግብር ተሰማርቼ ብዙ ደሃን ታድጌለሁ ቢልም ተቀEሙ በህዝብ ዘንድ ፣እያዩ ገደል!!!› (‘Eyayu Gedel’) በመባል ይታወቃል፡፡ የተቀEሙ ጀነራል ማናጀር መስፍን ፍፁም፣በወያኔ በተቸረው የአንድ ሚሊዩን ብር የተፈቀደ ፍሬ ካፒታል የተመሠረተው ድርጅት ዛሬ 800 ሚሊዩን ብር ካፒታል እንደደረሰ ገልፆል፡፡ ኢህአዴግ በሰጣቸው መነሻ ፍሬ ካፒታል እንደተመሰረተ ግን ደብቀዋል፣ዛሬ ደሃውን ዘርፈው በሰማንያ ሽህ ፐርሰንት አድገዋል፣በየዓመቱ በአማካይ 47 ሚሊዩን ብር ትርፍ አግኝቶል፡፡አዲስ ብድርና ቁጠባ ከ200,000 ሽህ ገንዘብ አስቀማጭ ደንበኞቻቸው ሰባት ቢሊዩን ብር በቁጠባ ሲያስቀምጡ፣(የነፍስ ወከፍ አማካይ 35 ሽህ ብር ቁጠባ አስቀምጠዋል) በሌላ በኩል ደግሞ ከ250,000 የብድር ደንበኞቻቸው 10 ቢሊዩን ብር ብድር ሠጥተዋል፣(የነፍስ ወከፍ አማካይ 40 ሽህ ብር ብድር ተበድረዋል) እንዲሁም ከዚህ ውስጥ 2.4 ቢሊዩን ብር ገና የሚሰበሰብ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ተቀõሙ በአዲስአበባ ዋና መሥሪያ ቤቱን ፎቅ ገንብቶል እንዲሁም በኦሮሚያ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቶል፡፡ በ2016 እኤአ የድርጅቱ ሠራተኛች ቁጥርም ከ40 ወደ አንድ ሽህ አሳድጎል፡፡ እንደ ማናጀሩ ገለፃ የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጅ በመተግበር ድህነትን በመቀነስ በ2025 እኤአ ሃገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ ሃገራት ጎራ ለመቀላቀል አቅዶል፡፡ ማናጀሩ ራሳቸውንና ኢህአዴግ ሹማምንትና ካድሬዎችን ወደ መካከለኛ ገቢና ከበርቴነት ቀየሩ እንጂ ደሃውን ህብረተሰብ ቁልቁል እንደቀበሩት ልቦናቸው ያውቃል፡፡ ተቀõሙ  በአዲስአበባና ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የ13 በመቶ ሽፋን ብቻ እንዳለው በጥናት ተረጋግጦል፡፡  “Out of the 200,000 saving clients, seven billion Birr has been saved. Besides, it has 250,000 credit clients who have taken 10 billion Birr in loans. Out of this, 2.4 billion Birr is yet to be collected’’,

ምንጭ

1- Inclusive Growth: Ethiopia Country Report

2-www.microcreditsummit.org.

3-http://www.mftransparency.org/microfinance-pricing/ethiopia/012-OCSSCO/.

4-http://www.oromiamicrofinance.com/

5-“Poor Helpers” or “Poor Killers?” MFI related deaths hike, © By Blogger of Debre Birhan Blogspot, 12-03-2011

6-The Ethiopian Herald, “Microfinance Institutions dev’t alleviating poverty” by tsegay Hagos, 25 AUGUST 2017,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s