በቶጎ በፀጥታ ኃይሎችና ተቃዋሚ ሰልፈኞች በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተገደሉ

  • ቪኦኤ ዜና

Map of Togo, Africa

Map of Togo, Africa

ቶጎ ውስጥ በፀጥታ ሃይሎችና የፕሬዚደንት ፎሬ ኛሲኒቤ አገዛዝ እንዲያበቃ በጠየቁ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ።

ቶጎ ውስጥ በፀጥታ ሃይሎችና የፕሬዚደንት ፎሬ ኛሲኒቤ አገዛዝ እንዲያበቃ በጠየቁ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ።

ዛሬ የቶጎ የፀጥታ ሚኒስትር ኮሎኔል ዳሜሄሚ ያርክ በሰጡት መግለጫ ዋና ከተማዋ ሎሜ ውስጥ አንድ ሰው ሦስት ሰዎች ደግሞ ሁለተኛ ትልቁዋ ከተማ በሆነችው ሶዶኬ ውስጥ መገደላቸውን ገልፀዋል።

ከትናንቱ ግጭት በተያያዘ ስልሳ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መታሰራቸውንም ባለሥልጣኑ ጨምረው አስረድተዋል።

ተቃዋሚ መሪዎች እኤአ ከ2005 አባታቸው ኛሲኒቤ ኢያዴማ ካረፉ በኋላ ሥልጣን የጨበጡትን ያሁኑን መሪ በመቃወም የሁለት ቀን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የአሁኑ ፕሬዚደንት በህገ መንግሥቱ የተደነገገው ፕሬዚደንታዊ የሥልጣን ዘመን ገደብ እንዲሰረዝ ያቀረቡትን ሃሳብ በመቃወም በሀገሪቱ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀስቅሰዋል።

ፕሬዚደንቱ ያቀረቡት ሃሳብ ከተሳካላቸው ቢያንስ እአአ 2030፣ ለቀጣዮቹ አሥራ ሁለት ዓመት መንበረ ሥልጣኑ ላይ ተደላድለው ለመቀመጥ ይመቻቸዋል። አባትየውም ቢሆኑ ከ1968 እስካረፉበት 2005 ዓመተ ምህረት ድረስ ሥልጣን ላይ ቆይተው ነው ለልጃቸው አምቻችተው ያለፉት፣ ሰላሳ ሰባት ዓመት ገዝተዋል።

Advertisements

በሐፍረታቸው የሚኮሩ ብአዴኖች!

በሐፍረታቸው የሚኮሩ ብአዴኖች! Muluken Tesfaw

የላይ ጋይንት ወረዳ ብአዴኖች ሊያፍሩበት የሚገባቸውን ገመና በአደባባይ ሲመጻደቁበት አየሁ፤ አፈ ቀላጤያቸው እንዳለው ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ ነው ነገሩ፡፡ በዚህ መልኩ ስንት ዐማሮች በየቦታው እንደጠፉ እግዜር ይወቀው፡፡


መሠለ ጌታሁን የተባለ ጉብል የሃምሳ አለቃ ፍቅሬ አሉላን ልጅ ለማግባት ቀን ቆርጦ ድግስ እየተደገሰ ነበር፤ የሰርጉ ዕለት ጥር 7 ቀን 2009 ዓም ተወስኖ ለድግስ የሚሆን ቅቤ ከደብረ ታቦር ለመግዛት ሰርጉ 20 ቀናት ያክል ሲቀሩት ታኅሳስ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ከነፋስ መውጫ ተሳፈረ፡፡ ምስኪኑ ሙሽራ መሰለ ጌታሁን ግን ነገሮች በአሰበው መልኩ አልሔዱለትም፡፡
ደብረ ታቦር ሂዶ ቅቤ ለመግዛት ሲያማርጥ የትግሬ ደኅንነቶች መጥተው ይይዙታል፤ መታወቂያ ተጠይቆ ሲያሳይ ትውልድ ቦታው ኮምቦልቻ መኖሪያው ደግሞ ላይ ጋይንት ወረዳ መሆኑን አዩ፡፡ ለትግሬ ደኅንነት ዐማራ መሆን ብቻውን በቂ ቢሆንም ደብረ ታቦር አመጽ ለማስነሳት ተልከህ የመጣህ ነህ ብለው ከሃያ ሽህ ዐማሮች ጋር ወደ ብር ሸለቆ የቅጣት ቦታ ወሰዱት፡፡ ለነዚህ አረመኔዎች ሰርጌ በሦስት ሳምንት ውስጥ ነው፤ ሙሽሪት ትጠብቀኛለች የሚባል ነገር አያሳዝናቸውም፤ እንዲያውም ሰርጉን በማስተጓጎላቸው ደስታ ይሰማቸዋል!
የመሰለ ጓደኞች የገባበት ጠፋቸው፤ የሙሽሪት ቤተሰቦች ተጨነቁ፡፡ ለፖሊስ አመለከቱ፤ ጉዳዩን የያዘው የትግሬ ደኅንነት በመሆኑ የዐማራ ፖሊስ የማወቅ መብት አልነበረውም፡፡ በዚህ መካከል በላይ ጋይንት ወረዳ ቀበሌ 13 አንድ ምስኪን ዐማራ ተገድሎ ይገኛል፡፡ ብዙ ጊዜ በደኅንነት የሚገደሉ ሰዎች ማንነታቸው እንዳይታወቅ ተደርገው አካላቸው ይበላሻል፤ መታወቂያና ማንኛውም ዶክመት ይቃጠላል፤ ስለዚህ ይህ የማን እንደሆነ ያልታወቀ አስከሬንን ፖሊስ የመሰለ ጌታሁን ነው በሚል ለቤተሰቦቹ አስረከበ፡፡ ቤተሰብ አልቅሶ የካቲት 03 ቀበረ፡፡ በድፍን ጋይት እግዚኦ ተባለ፤ ገደ ቢስ ሙሽራ ተባለች ሙሽሪትም፡፡
ብር ሸለቆ ከ6 ወር በላይ ሲደበደብ የከረመው አቶ መሠለ ጌታሁን ከ6 ወራት የስቅይት ጊዜ በኋላ ነሐሴ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ከብር ሸለቆ ተለቀቀ፡፡ ሙቷል የተባለው ተዝካር የተበላበት ሰርጉ የተሰረዘው እሱም ከሕይወት መዝገብ ሕወሓት የሰረዘው ጌታሁን ጊዜ ሳያጠፋ ጋይንት ተከሰተ፡፡
የብአዴኖች ሐፍረተ ቢስ ሥራ አሁንም ይቀጥላል፤ መሠለ ጌታሁንን ወደ ብርሸለቆ የተወሰድኩት በሕገ ወጥ መሣሪያ ዝውውር ተከስሼ ነው በል፤ ይህን ካላልክ ግን መልሰን እናስርሃለን ይባላል፤ አለላቸውም፡፡
እንግዲህ ይህን የሚያሳፍር ዜና ነው የብአዴኖቹ ኮምዩኒኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት በኩራት የፖሊስን ጀብደኝነት ጠቅሶ የዘገበው፡፡ ቢያንስ እንኳ ተገድሎ የተገኘውን ሰው ማንነት መለት አልቻሉም፡፡
ማፈሪያዎች!

በረከት ስሞንንም የተቃዋሚ ሀይሉ መሪ ለማድረግ ያቀደ የሚመስለዉ የባዶ ጮህት ፕሮፖጋንዳ:- 

Sponsored by Revcontent

የሕወሃት የበላይነት በውዴታ አሊያም በግዴታ ያበቃል! | ስዩም ተሾመ


ስዩም ተሾመ

በሕገ መንግስታዊ የፌደራል ስርዓት በምትመራ ሀገር፣ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በአራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፤ ህወሓት፥ ብአዴን፥ ኦህዴድ እና ደኢህዴን ጥምረት የሚመራ ሆኖ ሳለ፣ በሀገሪቱ ለሚስተዋሉ ፖለቲካዊ ችግሮች ህወሓትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ አድሏዊነት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን፣ ይሄ እውነታ እንጆ አድሏዊነት አይደለም። ሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ የፌደራል ስርዓቱና ተቋማት፣ እንዲሁም የክልል መንግስታትና ተቋማት የሚተዳደሩበት ሕግ፥ ስርዓትና መዋቅር በህወሓት የፖለቲካ መርህና አመለካከት ላይ የተመሰረተ ነው።

የፖለቲካ ጨዋታውን ሁሉም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ይጫወታሉ። የጨዋታውን ሕግ በማፅደቁ ሂደት ሁሉም ተሳታፊዎች ነበሩ። ነገር ግን፣ ሕጉ የተረቀቀበት ፅንሰ-ሃሳብ የህወሓት ነው። ይህ የጨዋታ ሕግ የኢፊዲሪ ሕገ መንግስት ሲሆን የሕገ መንግስቱ መሰረታዊ መርሆች ደግሞ በህወሓት የብሔር ፖለቲካ መርህና አመለካከት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በመሆኑም የፌደራሉ መንግስትና ተቋማት ይህን የፖለቲካ መርህና አመለካከት ተግባራዊ ለማድርግ የተቋቋሙ ናቸው።

የሕጎች ሁሉ የበላይ እንደመሆኑ፣ በሁሉም ደረጃ የሚወጡ አዋጆች፥ ደንቦችና መመሪያዎች ለሕገ መንግስቱ ተገዢ መሆን አለባቸው። ነገር ግን፣ የሕገ መንግስቱ ትርጉምና ፋይዳ በህወሓት የፖለቲካ መርህና አመለካከት ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ፣ ለሕገ መንግስቱና ለመንግስታዊ ስርዓቱ ተገዢ መሆን ለህወሓት ተገዢ ከመሆን ጋር አንድና ተመሳሳይ ነው።

በአጠቃላይ፣ በሀገሪቱ ለሚስተዋሉ ፖለቲካዊ ችግሮች ከተቀሩት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለየ ህወሓት ተጠያቂ የሚሆንባቸው ምክንያቶች፤ አንደኛ፡- መንግስታዊ ስርዓቱ በህወሓት የፖለቲካ መርህና መመሪያ የተመሰረተ ስለሆነ፣ ሁለተኛ፡- ይህ የፖለቲካ መርህና አመለካከት ፍፁም ስህተት ስለሆነ፣ ሦስተኛ፡- የሥልጣን የበላይነቱን ለማስቀጠል እጅግ አደገኛ የሆነ ሸርና አሻጥር እየፈፀመ ስለሆነ። እነዚህን ችግሮች አንድ ላይ አያይዤ በአጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ።

የዳግማዊ ወያነ ወይም የሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) የትጥቅ ትግል የጀመረው የትግራይ ህዝብን የለውጥ ፍላጎት የብሔርተኝነት ስሜት በመቆስቆስ እና በራስ የመወሰን መብትን ዓላማ በማድረግ ነው። የቀድሞ የህወሓት (TPLF) መስራችና አመራር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) የድርጅቱን የትጥቅ ትግል አጀማመርና የንቅናቄ ስልት “…the prevalence of the TPLF at this stage of the struggle was attained by its rigorous mobilization of the people based on the urge of ethno-nationalist self-determination on the one” በማለት ገልፀውታል።

ነገር ግን፣ ከህወሃት ብሔርተኝነት በስተጀርባ ለራስ ብሔር ተወላጆች የተሻለ ክብርና ዋጋ መስጠት፣ ለሌሎች ብሔር ተወላጆች ደግሞ ያነሰ ክብርና ዋጋ በመስጠት ላይ የተመሰረተ ነው። የትጥቅ ትግሉን ለማስጀመር በትግራይ ህዝብና የፖለቲካ ልሂቃን ስነ-ልቦና ውስጥ እንዲሰርፅ የተደረገው የአክራሪ ብሔርተኝነት ስሜት ዛሬ ላይ ወደ የተበዳይነትና ወገንተኝነት ስሜት ፈጥሯል። ከደርግ ጋር በተካሄደው ጦርነት የተፈጠረው ጥላቻና የጠላትነት ስሜት ዛሬ ላይ ወደ ፍርሃትና ጥርጣሬ ተቀይሯል።

የዘውግ ብሔርተኝነት እና በራስ የመወሰን መብት ሕዝባዊ ንቅናቄን ለመፍጠር (mobilization) ተጠቅሞ ወደ ስልጣን የፖለቲካ ቡድን የተበዳይነትና ጠላትነት አመለካከት ያለው፣ ማንኛውንም ዓይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በፍርሃትና ስጋት የሚመለከት ይሆናል። በሕወሃት መሪነት የተዘረጋው መንግስታዊ ስርዓት ከላይ የተጠቀሱት አሉታዊ ተፅዕኖዎች ያረፉበት ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ሕወሃት ከሀገሪቱ ሕዝብ ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ያለውን የሕብረተሰብ ክፍል የሚወክልና በጦርነት ወቅት በተፈጠረ ከፍተኛ የተበዳይነት፥ ጠላትነትና ፍርሃት አመለካከት የሚመራ ድርጅት እንደመሆኑ በድርጅቱ መሪነትና የፖለቲካ መርህ ላይ ተመስርቶ የተዘረጋው ሕገ መንግስታዊ ስርዓት የሕወሃትን የስልጣን የበላይነት የማስቀጠል ዓላማ ያለው ነው።

ሁለተኛ እንደ ሕወሃት ያለ የፖለቲካ ቡድን ሌሎች አብላጫ ድምፅ ያላቸው ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች ተመሳሳይ የፖለቲካ ንቅናቄ እንዳይጀምሩ ማድረግ አለበት። ምክንያቱም አብላጫ ድምፅ ያላቸው ማህብረሰቦች ተመሳሳይ የፖለቲካ ንቅናቄ ማድረግ ከቻሉ የአነስተኛ ብሔር የስልጣን የበላይነትንና ተጠቃሚነትን በቀላሉ ያስወግዱታል። ስለዚህ አብላጭ ድምፅ ያላቸውን ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በጎሳ፥ ብሔርና ቋንቋ በመከፋፈል የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ እና የተቀናጀ ንቅናቄ እንዳይኖራቸው ማድረግ አለበት።

እንዲህ ያለ የፖለቲካ ቡድን የቆመለትን የአንድ ወገን የስልጣን የበላይነትን ሊያሳጣው የሚችል ማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ ለውጥና መሻሻል፣ ሃሳብና አስተያየት ተቀብሎ ለማስተነገድ ዝግጁ አይደለም። በተለይ ደግሞ በመንግስታዊ ስርዓቱ ላይ ምንም ዓይነት የማሻሻያ ሃሳብና ድርድር ለማድረግ ፍቃደኛ አይደለም። በዚህ ምክንያት፣ ላለፉት 25 ዓመታት ሕወሃት/ኢህአዴግ ከብዙሃኑ የሕብረተሰብ ክፍል የሚነሳውን የመብትና ነፃነት ጥያቄ በኃይልና በጉልበት ለማፈን ጥረት አድርጓል።

በመሰረቱ ሕወሃት የስልጣን የበላይነቱ በሕገ መንግስቱና በፌደራል ስርዓቱ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ በዚያ ረገድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል ለማድረግ ዝግጁ አይደለም። በመሆኑም እያንዳንዱን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በፍርሃትና ጥርጣሬ ይመለከታል። የሕዝቡን የመብትና ነፃነት ጥያቄ በኃይልና በጉልበት በማዳፈን ብዙሃኑ የሕብረተሰብ ክፍል እና የፖለቲካ ልሂቃን መንግስትን እንዲፈሩ፣ በዚህም የስርዓቱን ሕልውና ለማስቀጠል ጥረት ያደርጋል።

በእርግጥ ፍርሃት (fear) የሕወሃት መርህና መመሪያ ነው። ሆኖም ግን፣ በየትኛውም ግዜ፥ ቦታና ፖለቲካዊ ስርዓት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ፖለቲካዊ ጥያቄ እኩልነት (equality) ነው። የሁሉም መብትና ነፃነት እስካልተከበረ ድርስ ዜጎች የእኩልነት ጥያቄን ከማንሳት ወደኋላ አይሉም። እንደ ሕወሃት ያሉ ጨቋኞችም የመብትና ነፃነት ጥየቄ ባነሳው የሕብረተሰብ ክፍል ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ ጥያቄው ዳግም እንዳይነሳ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ። ይሁን እንጂ፣ ሕወሃት ከሚፈጥረው ሽብርና ፍርሃት ይልቅ እድሜ ልክ በተገዢነትና ጭቆና መኖር ይበልጥ ያስፈራል።

ዛሬ የሕወሃትን የሰልጣን የበላይነት የሚቃወም፣ በጭቆና ተገዢነት መኖር የሚጠየፍ ትውልድ ተፈጥሯል። ስለዚህ፣ ወይ የሕወሃት የበላይነት በለውጥና ተሃድሶ ያበቃል፣ አሊያም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ በሕዝባዊ አመፅና አምቢተኝነት ይፈርሳል። በመሆኑም የሕወሃት የበላይነት በውዴታ አሊያም በግዴታ ያበቃል። ሰሞኑን በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች የሚታየውን ሕዝባዊ ንቅናቄ በሸርና አሻጥር ወደ ሁከትና ብጥብጥ በመውሰድ የለውጡን እንቅስቃሴ ለማዳፈን የሚደረገው ጥረት ሁለተኛውን የለውጥ ጉዞ ከማፋጠን የዘለለ ትርጉምና ፋይዳ የለውም።

ኢትዮጵያዊነት፤ የአንድነትና የዝንጉርጉርነት ወግ – ቴዎድሮሥ ኃይለማርያም (ዶ/ር)

1. ኢትዮጵያዊነት ማለት ምንድነው?

ይህ ጥያቄ የራሷን የኢትዮጵያን ያህል አንጋፋ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን በየዘመናቱ ሲጨነቁና ሲጠበቡበት ቢኖሩም ፣ በተለይ ባለፉት ሃምሣ ዓመታት የሀገራችን ህልውና የተንጠለጠለበት ጉዳይ መሆኑ አያከራክርም፡፡ ነገር ግን የጥያቄውን ዕድሜ ጠገብነትና ግዝፈት ያህል ፣ ቀጥተኛና አጥጋቢ ምላሽ ፈልገን ለማግኘት እንቸገራለን፡፡ ‹‹ኢትዮጵያዊነት ምንድነው?›› ብለን የቅርብ ባልጀሮቻችንን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ረዥም ዝምታ ነው፡፡ በቃ ኢትዮጵያዊነትማ ኢትዮጵያዊነት ነው! ለብዙዎቻችን ኢትዮጵያ የህይወታችን አካል እንጂ የምንመራመርባት ርዕስ አይደለችም፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት ነው?

ኢትዮጵያዊነት በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ መሆን ማለት ነው፡፡ የአንዲት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ፣ ህዝብና መንግሥት ማንነት ነው፡፡ በርካታ ሁለተኛ ኢትዮጵያዊነት ማለት በኢትዮጵያ ማንነት ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ ብሄርተኝነት ነው፡፡ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቅርፅ ፣ ይዘትና አቅጣጫ የሚነድፍና የሚመራ ፍልስፍና ነው፡፡ በዚህ መልኩ ኢትዮጵያዊነት የህዝቧን አንድነት ፣ የመንግሥቷን ቀጣይነት ፣ የግዛቷን ሉአላዊነት ፣ የዜጎቿን እኩልነት የሚያቀነቅን የአብሮነት አስተሳሰብ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በርዕዮታዊ ፣ ባህላዊና ታሪካዊ አንድነት ላይ የቆመ ብሄርተኝነት ነው፡፡

በአጭሩ ኢትዮጵያዊነት የአንድ ሀገራዊ ብሄር ማንነትና ፍልስፍና ነው፡፡ ስለዚህ እንደማንኛውም ብሄርነት የስሜትም የፖለቲካም ማህበረሰብነት ድምር ነው፡፡ በአንድ ወገን ተንተርሶ ወደፊት የሚመጣውን እጣ ፈንታ ተስፋ የሚያደርግ ማህበረሰቦች በረዥም ታሪካዊ መስተጋብር ያዳበሩት ቤተሰባዊ ሥነ-ልቡናና ራሳቸውን ከሌሎች የሚለዩበት ማህበራዊና ህሊናዊ ድንበር ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ነገዳዊ ፣ አውራጃዊ ፣ እምነታዊ ፣ መደባዊ የመሳሰሉ ዝንቅና ውስብስብ ድሮችን አካትቶ በዘመናት የተሸመነ ባለ ህብረ ቀለም ካባ ነው፡፡ የሀገር ፍቅር ፣ አርበኝነት ፣ ህዝባዊነት ፣ ብሄራዊ ስሜት በሚሉት ሊገለፅ ይችላል፡፡

በሌላ ወገን የሚቀዳጁት ህጋዊ ሰውነት ነው፡፡ ለመላው ኢትዮጵያውያን አስገዳጅነት ያለው ማንነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በግዛተ መንግሥቱ የሚገኙ ዜጎች ሁሉ በብሄራዊ ማህበሩ አባልነት በቀጥታ በስሜት ከኢትዮጵያዊነት ቢነጠልም ፣ በሌላ ብሄራዊ መንግሥት ሥር ካልገባ በስተቀር ፖለቲካዊ ዜግነቱ አብሮት ይኖራል፡፡ አነዚህ ሁለት የስሜትና የፖለቲካ ገፅታዎች መሳ ለመሳ የሆኑበትና ፍጹም ብሄራዊ አንድነት ያለው ሀገር የሚገኘው በተምኔታዊው ዓለም ብቻ ነው፡፡ መተሳሰሪያው የጋራ ባህል የሆነ ፣ ያለፈውን እድልና ፈተና የጋራ ስብዕና መንፈስ ይህ ረቂቅ ማህበራዊ ሥነ-ልቡና በትውልድ ነው፡፡ ሰዎች በኢትዮጵያዊ ዜግነት ይወለዳሉ እንጂ ፣ ኢትዮጵያዊ ልሁን ብለው አይጠይቁም፡፡ ሁን ተብለውም አይጠየቁም፡፡ ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ማለት ብቻ ኢትዮጵያዊነታቸውን አይሰርዘውም፡፡ አንድ ንዑስ ማህበረሰብ ወይም የህብረተሰብ ክፍል በተለያዩ ምክንያቶች

ኢትዮጵያውያንም ስለሀገራቸው ፣ መንግሥታቸውና ብሄራዊ ማንነታቸው የሚኖራቸው ስሜትና ቅንዐት ፣ በማንኛውም ወቅትና በመላ ሀገሪቱ ወርድና ቁመት ወጥና ያልተዛነፈ ሊሆን አይችልም፡፡ ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም ፣ በዋነኝነት የመንግሥቱ ፖለቲካዊ ቁመና በተለዋወጠበት ታሪካዊ ፍጥነትና ስፋት ልክ ፣ በማዕከሉና ዳርቻው ወይም በነባሩና አዲሱ መካከል ባህላዊና ትዕምርታዊ ትስስር አለመደርጀቱ ነው፡፡ ይህ ልዩነት ዋነኛው የባዳነትና የባይተዋርነት መንስኤ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን በየዘመኑ ‹‹ማነው ኢትዮጵያዊ?›› ለሚለው ጥያቄ የሚሰጡት መልስ ፣ በስሜታዊውና ፖለቲካዊው ድንበር መካከል ያለውን ርቀት ይወስናል፡፡ ጉዳዩ የአንድ ሀገር ብሄራዊ ህብርና ጥንካሬ መለኪያ በመሆኑ ፣ የኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ዋነኛ ተግባርም ልዩነቱ እንዲጠብብ መጣር ነው፡፡ መድረሻ ግቡ ደግሞ ብሄራዊ ቀጣይነትና ህልውናን ማረጋገጥ ነው፡፡

2. የኢትዮጵያዊነት ህልውና አዕማዶች ኢትዮጵያዊነት ከኢትዮጵያ ጋር የተቆራኘ ማንነትና ፍልስፍና ነው ብለናል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና ደግሞ እጅግ ተፃራሪና ፅንፈኛ የብሄርተኝነት አመለካከቶች የሚንጸባርቁበት ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ በአንዱ ጥግ ኢትዮጵያ ጥንትም የነበረች ወደፊትም የምትኖር ዘላለማዊ ናት፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!››፡፡ በሌላው ደግሞ ኢትዮጵያ ከተወሰኑ ቡድኖች ምኞት ውጭ ህልውና የሌላት ምናባዊ ፍጡር ናት፡፡ ሆኖም እነዚህ የእምነት እንጂ የታሪክ ድምዳሜዎች አይደሉም፡፡

ኢትዮጵያ ታሪካዊ ህልውና ያላት ሀገር እንጂ ዘላለማዊም ምናባዊም አይደለችም፡፡ ኢትዮጵያዊነትም ይህን ሀገራዊ ህልውና የሚያንፀባርቁ የበርካታ ነገሮች ድምር ውጤት ነው፡፡ ረቂቅም ግዙፍም ፣ ህሊናዊም ነባራዊም ፣ ታሪካዊም ባህላዊም ፣ ፖለቲካዊም ማህበራዊም መልኮችና ዘርፈ ብዙ መገለጫዎች አሉት፡፡ የአንድ ብሄርተኝነት መንፈስና ባህሪ የሚወሰነው እነዚህ በተለያየ ደረጃ በሚቀየጡበት ውስብስብ ሚዛን ቢሆንም ፣ ዘመን የማይሽራቸው የኢትዮጵያዊነት ህልውና አዕማዶች ህዝብ ፣ ሀገርና መንግሥት ናቸው፡፡ ሥርወ ቃሉ ግዕዝ የሆነው ‹‹ብሄር›› የነዚህ ሶስት አካላት ድምር ነው፡፡

ሀ. ህዝበ ኢትዮጵያ ፡- የኢትዮጵያዊነት አልፋና ኦሜጋ ነው፡፡ ህዝብ የሌለው ማንነትና ብሄርተኝነት ሊኖር አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ብሄራዊ አቋም ያለው ማህበረሰብ የሚያስፈልጉትን አበይት መስፈርቶች ያሟላል፡፡ የጋራ ስም ፣ የጋራ ሀገር ፣ የጋራ መንግሥት ፤ አነሰም በዛም የጋራ ታሪክ ፣ የጋራ ህግና ባህል ፣ የጋራ መንፈስና ስብዕና አለው፡፡ ከሁሉም በላይ በጋራ ተስፋ የተሳሰረ ቤተሰብ እንጂ ፣ በልዩነት የተዳበሉ ህዝቦች ጥርቅም አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት በህዝብ ህሊናና የእለት ተእለት ህይወት ሰፊና ጥልቅ መሰረት በመያዙ ምክንያት ፣ አገዛዞች ህልውናቸውን ለማስጠበቅ ጥቃት ቢከፍቱበት ፣ ብሄራዊ መንግሥቱ ቢዳከምና ቢፈራርስ እንኳን በተደጋጋሚ የሚያንሰራራበት አቅምና ዋስትና አግኝቷል፡፡

ለ. ሀገረ ኢትዮጵያ ፡- ማለት ከዚህ ጫፍ እሰከወዲያኛው ወይም ከዚህ ዲግሪ እስከዚያኛው ተብላ የምታበቃ ደረቅግንዛቤ አይደለችም፡፡ በድርቡ ግዛታዊና መልክዐ ምድራዊ ቁመናን ፣ የታሪክና የባህል ማህደርነትን እንዲሁም የወላጅነትንናፈጣሪነትን ባህሪ አሰተሳስራ ትይዛለች፡፡ ሀገረ ኢትዮጵያ ከህዝብና ከመንግሥት የሚዋረስ ስብዕና ያላት ብሄራዊ ምድር ናት፡፡ እናት ሀገር እምዬ ትሰኛለች፡፡ አፈሯ ፣ አየሯ ፣ ወንዞቿ ፣ ጋራዋና ሸንተረሯ ፣ ሌሎችም መደበኛ የተፈጥሮ ገፅታዎቿ ግኡዛን ሳይሆኑ ፣ በህይወትም በሞትም ከማንነት የተቆራኙ የኢትዮጵያዊነት አካላት ናቸው፡፡ በኢትዮጵያውያን መንፈስ ጥልቅ ስሜትን የሚጭሩናበህዝባዊ ትውፊቶች ፣ ግጥሞችና ዜማዎች ፣ በስም አወጣጥ ልማዶች የሚቀነቀኑ ናቸው፡፡ ሀገረ ኢትዮጵያ ለክብሯና ልዕልናዋ ይቀኝላታል ፣ ይዜምላታል ፣ ይፀለይላታል ፣ ይሞትላታል፡፡

ሐ. መንግሥተ ኢትዮጵያ ፡- በዋነኝነት አስተዳደራዊ ተቋሙን ፤ አልፎም ወጉን ፣ ሥርዓቱን ፣ ህጉንና ታሪኩን የሚገልፅ ግንዛቤ ነው፡፡ ልዕለ ዘውጋዊ ተቋምና የብሄራዊ አንድነቷ ማሰሪያ የሆነው መንግሥት ፣ የኢትዮጵያዊነት ጠንሳሽ ፣ የህልውናዋ ዘብ ፣ የሥልጣኔዋ የክብርና ኩራቷ መለዮ ነው፡፡ በአንፃራዊነት መንግሥተ ኢትዮጵያ ዘላቂነት ሲኖረው ፣ አገዛዙ ወይም ፖለቲካዊ ሥርዓቱ ተለዋዋጭ ነው፡፡ ስለዚህም መንግሥታዊ ወይም ይፋዊ ኢትዮጵያዊነት በየዘመኑ የሚነሱ አገዛዞች ባህሪ ፣ ርዕዮታዊ ውዥቀቶችና የሃይልአሰላለፎች ነፀብራቅ ነው፡፡ ከአንዱ ሥርዓተ መንግሥት ወደሌላው ከህዝባዊ ኢትዮጵያዊነት ጋር ሊመሳሰልም ሆነ ሊለያይ ይችላል፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን መንግሥታዊ ብሄርተኝነት የሥልጣን ማስከበሪያ ፖለቲካዊ መሣሪያነት ዝንባሌ አያጣም፡፡

የብሄርተኝነት አንዱ ባህሪው የማይከለስና የማይበረዝ ሆኖ መታየት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ብሄራዊ ማንነትየተሸመነበት ባህል ፣ ታሪክ ፣ እሴቶች ፣ ተቋማትና ርዕዮት እንደ ማህበረሰቡ ነባራዊ እጣ ፈንታ መለዋወጣቸው አይቀሬነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአንድ የሆነ ዘመንና የታሪክ አጋጣሚ እንደተወለደ ሁሉ በሂደት ሲያድግና ሲያብብ ፣ ሲቀጭጭና ሲጠወልግ ፣ መልሶ ሲያንሰራራና ሲለመልም እዚህ ደርሷል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከስሟ በስተቀር በነበረበት የዘለቀ ነገር የላትም ለማለት ያስደፍራል፡፡ የኢትዮጵያዊነትማህበራዊና ህሊናዊ ድንበር ብቻ ሳይሆን ፣ የፍፁም ሉዐላዊነቷ ማህደር ሀገረ ኢትዮጵያ ቁመና ጭምር በየዘመናቱ ሃይልአሰላለፍ ሲሰፋና ሲጠብብ ኖሯል፡፡ መንግሥተ ኢትዮጵያ ሲበረታና ሲፍረከረክ ፣ መንበሩ ሲፀናና ሲነቀነቅ ፣ ሰንደቁ ሲወድቅና ሲነሳ በታሪክ ጎዳና አዝግሟል፡፡ የኢትዮጵያዊነት አድማስም የመንግሥቱን እጣ ፋንታ እየተከተለ ሲንሰራፋና ሲኮማተር ፣ መንፈሱ ተግ እልም ሲል ፣ ማዕከሉ ካንዱ ጫፍ ወደሌላው ሲንሸራተት ታይቷል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ በርካታ መደቦችና ንዑስ ማህበረሰቦች በሀገር ግንባታና ብሄራዊ ተልእኮ አራማጅነትተፈራርቀዋል፡፡ በአንድ ወቅት ከብሄራዊ ማንነቱ ጠርዝ ላይ የነበሩ ወደ መሃል የሚመጡበትን እድል አግኝተዋል፡፡ በታሪክአጋጣሚ ማዕከሉን ሲጋፉ የነበሩ በሂደት ለምደውና ተዛምደው ብሄራዊ አርበኛ ሆነዋል፡፡ በተቃራኒው የኢትዮጵያዊነትአስኳል የነበሩ ማህበረሰቦች ፣ እምነቶችና እሳቤዎች ወደ ዳር የተገፉበትም ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በዚህ መፈራረቅ ወቅትመሃሉ ላቅ ደመቅ ፣ ዳሩ ደግሞ ራቅ ፈዘዝ እያለ መታየቱ አልቀረም፡፡

ኢትዮጵያዊነት ካስተናገዳቸው ህልቆ መሳፍርት ለውጦች ሁሉ ሥር ነቀሉ ፣ የብሄራዊ ማንነቱ ገዢ ርዕዮተ ዓለም ቢያንስ ከአራተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ፣ ኢትዮጵያዊነት ከአንድ ብሄራዊ ኃይማኖት ማዕከላዊነት ጋር የተቆራኘ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ትክለ ስብዕናዋ ከኦርቶዶክሳዊ እምነቷ ጠብቆ የተሰራ ፣ ህዝቧም ምድሪቱም መንግሥቷም በእምነት ድርና ማግ የተሳሰረ ፣ እጣ ፈንታዋ በመለኮታዊ ኃይልና ፀጋ የሚመራ ‹‹የክርስቲያን ደሴት›› ሆና ዘልቃለች፡፡ ካህናዊው መደብ በጋራ አስተምህሮ ፣ ቀኖናና ቋንቋ የተሳሰረ የብሄራዊ አመለካከቱ ፅኑ አራማጅ ፣ የታሪኩ ዘጋቢ ፣ የባህሉ ፣ እሴቱና ትዕምርቱ ምንጭ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ኃይማኖትን የብሄራዊ ቤተሰብነት የልደት ካርድ በማድረግ ፣ ይህ ቀዳሚ ማህበረሰብ ራሱን ብሄረ ኢትዮጵያ ብሎ ሲገልፅ ኖሯል፡፡

ከ19ኛው ምዕት አጋማሽ በኋላ መንግሥተ ኢትዮጵያ የጀመረው የዘመናዊነት ሽግግር የብሄረ ኢትዮጵያን ርዕዮተ ዓለም እያደር ያናጋና ፣ አጠቃላይ የማህበረሰቡን አቋምና ባህሪ በሥር ነቀልነት የለወጠ ሂደት ነበር፡፡ ቁምነገሩከመንፈሳዊነት ወደ ዓለማዊነት መዞሩ ነው፡፡ ተልእኮው ከመለኮታዊነት ወደ ዓለማዊነት መቀየሩ ነው፡፡ እምነት አማካይ ቦታውን እየለቀቀ ፣ መንግሥትን ከኃይማኖት የመንግሥቱ ቅርፅ ከአሃዳዊነት ወደ ፌዴራላዊነት ፤ ሥርዓቱ ከዘውዳዊ ወደ ወታደራዊ ወይም ዘውጋዊ መዋዠቁ ሳይሆን ፣ ብሄራዊ ነጥሎ በፖለቲካ ባህሪው እየወሰነ መሄዱ ነው፡፡ ‹‹ሀገር የጋራ ኃይማኖት የግል›› የሚለው ቁልፍ አስተሳሰብ ኢትዮጵያ ከእምነታዊ ወደ ፖለቲካዊና ህጋዊ ማህበረሰብነት መለወጧን የሚያመለክት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና ቀጣይነት ላይ ተፅእኖ ያሳደሩ በርካታና ውስብስብ ምክንያቶች ቢኖሩም ፣ ከሁሉም በላይ ወሳኙ ግን ኢትዮጵያዊነት በየዘመናቱ የሚፈጠሩ አስገዳጅ ሃይሎችንና ሁኔታዎችን ለማስተናገድ የነበረው አቅምና ቁመና ይመስላል፡፡ በተከታዩ ክፍል እንደምናየው በታሪክ የተፈራረቁ በጎም ሆነ መጥፎ ክስተቶችን ፣ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ኃይሎችን ፣ ርዕዮታዊ ወይም ሠራዊታዊ ጫናዎችን ፣ ህዝባዊና መደባዊ ንቅናቄዎችን ወይም ፖለቲካዊና ዘውጋዊ መቀናቀኖችን ፣ ወዘተ የማያቻችልና በቅርፅም በይዘትም ግትርና ወርደ ጠባብ ብሄርተኝነት ቢሆን ኖሮ ፀንቶ ሊቆም ባልቻለ፡፡ የኢትዮጵያዊነት ፅናት ቁልፍ ምሥጢር አቻቻይና ባለ ሰፊ አውድ ፣ ሀገራዊና ዜግነታዊ ብሄርተኝነት መሆኑ ነው፡፡

(ይቀጥላል)

የሕዝብን ልጆች እየገደሉ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም

በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ሆኖ የተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ ወደ ግድያና ረብሻ መቀየሩ ያጠያይቃል ፤ ያሳስባል፤ ሰላማዊ ሆኖ ሲጀመር ሰላማዊ ሆኖም ሲቀጥል ዝም ያሉትና የሕዝቡን የተቃውሞ ሰልፍ በወያኔ ላይ ሲፈርጁ የነበሩትም አክቲቭስት ነን ባዮች ግድያ ሲጀመር ሰልፉን የራሳቸው አድርገው መዘገባቸው ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ከጅምሩ የተቃውሞ ሰልፉን አስመልክተው ሲዘግቡ የነበሩ ሚዲያዎችን እንደ ትግል ጠላፊ አድርገው መውሰዳቸውም የሚኬድበት የተበላሸ አቅጣጫ ደም ከማስፈሰስ ውጪ ምንም እንደማይፈይድ እያሳየን ነው።

ደም ካልፈሰሰ ትግል የማይመስላቸው የዲያስፖራው ቤንዚሎች የኦሮሞ ወጣቶችን ሞት ለግል ጥቅማቸው ለማዋልና ራሳቸውን ነጸ አውጪ ለማሰኘትና የኦሮሞን ሕዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ ለመለየት ዘረኛ ምላሳቸውን ስለው ቢለፉም የወያኔን እድሜ ከማስረዘም ውጪ ምንም አይፈጥሩም። በተለያዩ መንግስታት የኦሮሞ ምሁራንና ወታደራዊ መኮንኖች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ወሳኝ አካል ሆነው የተጫወቱትን ሚና በማኮላሸት በወያኔ ጉያ ስር የሚሸጎጡ ታዛዥ አሽከሮች ከመፍጠር ውጪ አንዳችም ስራ አልተሰራም። አይሰራምም።

ድንገት እንደ ሙሴ የተገኘውን ኦቦ ለማ መገርሳን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ የወያኔ አጫፋሪ ቅጥረኞች በኦሮሚያ ክልል የጀመሩት ጥፋት ከተጠያቂነት አያድናቸውም። እንደ አባዱላ አይነት የሕወሓት አሽከሮች ስልጣናቸውን ለቀው ከሕወሓት የተሰጣቸውን እኩይ ተልእኮ ለማስፈጸም ደፋ ቀና እያሉ ሲሆን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማስተዳደር ስላልቻለ በጊዜያዊነት አስተዳደሩን ለነኣባዱላ አይነቶቹ ሰጥቶ የቆሰቆሱትን ረብሻ ዝም አስኝቶ ሃገር ወዳዶችን ለማስወገድ የሚኬድበት መንገድ አያዋጣም።ኦሮሚያ የተረጋጋች ሕዝቡም ሰላማዊ ስለሆነ ሕወሓት ያሰማራው የኣባዱላ ቡድን እጁን በኣስመሳይነት ከነከረበት የሕዝብ ትግል ያውጣው። የሕዝብን ልጆች እየገደሉ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም።

#MinilikSalsaw

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ፡፡ ኤምባሲው ደረሰኝ ያለውን ዘገባ ጠቅሶ እንዳስታወቀው በግድያ እና ግጭቱ ተጠያቂዎችን ለመለየት ግልጽ ምርመራ መደረግ እንደሚገባው ሁኔታው ያመለክታል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ሰላማዊ ሰልፎችን የምትመለከተው እንደ ህጋዊ የሀሳብ እና የፖለቲካ ተሳትፎ መግለጫ እንደሆነ ኤምባሲው ዛሬ ያወጣው መግለጫ ያትታል፡፡ በቅርቡ በተካሄዱ በርከት ባሉ ሰልፎች ሰልፈኞች በሰላማዊ ሁኔታ ሀሳባቸውን መግለጻቸውን እና ይህን እንዲያደርጉም የጸጥታ ኃይሎች መታገሳቸውን በአድናቆት እንደሚመለከተው ኤምባሲው ገልጿል፡፡ ኤምባሲው ሁሉም ኢትዮጵያውያን አመለካከታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጻቸውን እንዲቀጥሉ አበረታቷል፡፡ ባለስልጣናትም ይህንኑ አንዲፈቅዱ ጠይቋል፡፡ በጥቅሉም «ኢትዮጵያዊያንን በሚጠቅም ጉዳይ ገንቢ፣ ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታች ብሔራዊ ተዋስዖ» መኖሩን እንደሚደግፍም በመግለጫው ጠቅሷል፡፡