ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ! ቀኑ ለመሸበት ወያኔ ዕድሜ ላለመስጠት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቁርጥ

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

መቸም አለመታደል ሆነብን እና “የሞኝ ለቅሶ፤ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ ለአርባ ዓመት ከአንድ አናሳ ማህበረሰብ የወጣ አናሳ ቡድን መላ አገራችንን ለመበጣጠስ በሺ የሚቆጠሩ ንጹሃን ወገኖቻችንን በግፍ ሲጨፈጭፍ ከንፈርን መምጠጥ ልማዳችን ያደረግን ጥቂቶች አይደለንም። ወያኔም በየአንዳንዳችን ሥነ ልቦና ዘልቆ በመግባት ውስጣችንን ጭምር በባለቤትነት ጠፍሮ እንደያዘ በመገመት ዛሬም እንደ ትናንቱ የግፍ ጭፍጨፋውን ቀጥሏል።ye gondar hibret

የዛሬው የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወኔ ግን ወያኔ በሚያስበው ስሌት፤ ሊያኮላሽ ባሰበው የዘር ከፋፍለህ ምታው መንገድ የሚጠለፍ ሳይሆን፤ ሆድ ብሶት፤ የዘረኝነት ሥራዓት መሮት በነፃነት ጥማት የተንቀለቀለ ማህበረሰብ መብቱን ሳያከበር ድሉን ሳይቀዳጅ ክንዱን ላይንተራስ ቆርጦ የተነሳ ሕዝብ እያቀጣጠለው ያለ የትግል እሳት ነው። በማንኛውም አገር የወደቁትን የጨካኝ አምባገነኖች ታሪክ እንዳየነው ሁሉ የኛም አገር አረመኔዎች በድንቁርና እና በድርቅና እየተጓዙ ያሉት ያው በተመሳሳይ መልኩ ጉድጓድ እስኪወርዱ እየገደሉ ማለፍን ነው።

ሰሞኑንም መጠቅለያው የውድቀት ከፈኑ በመዘርጋት ላይ መሆኑን እያወቀ ከራስ እስከ እግሩ በሽብር የተዋጠውን ቀኑን ያራዘመ መስሎት በኦርሚያ አካባቢ ከመቸውም ጊዜ በላይ አገር አቀፍ ቅርጽ ይዞ እየተቀጣጠለ ያለውን የመንግሥት ተቃውሞ እንቅስቃሴ አቅጣጫውን ለማስቀየር በኢሉባቡር ክፍለ ሀገር በጫንጩ ወረዳ በቡድን ለተደራጁ ክፍሎች ሽፋን በመስጠት በአማራ ብሔረሰቦች ላይ የተፈፀመው አረመኒያዊ ጭፍጨፋ እጅግ አሳዝኖናል። ይህ ጭፍጨፋ በመንግሥት የዘረኝነት ሕግ ከለላ ሥር የተጠለሉ የመንግሥት ካድሬዎችና የደህንነት ሰዎች በአማራ ተወላጆች ላይ ያደረጉት አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የመጀመሪያው ባይሆንም፤ የሰሞኑ ግን ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ላይ ቆሞ ይህን መሰሪና ጨካኝ ፋሽስታዊ ቡድን ማስወገድ አማራጭ የሌለው የትግል ምዕራፍ ላይ በሆንበት ወቅት በመሆኑና ይህን አንድነታችን ለማበላሸት የተጠነሰሰ ተንኮል በመሆኑ ሁሉም ወገን አጥብቆ ሊያወግዘው ይገባል።

ዘረኝነትን መርህ ባደረገ የወያኔ ጭፍጨፋ በበደኖ፤ በአርባ ጉጉ፤ በወለጋ፤ በጉራ ፈርዳ ፤ በወልቃይት ጠገዴ፤ በጠለምት፤ በአርማጭሆ; በጋይንት፤ በደብረታቦር፤ በጎንደር፤ በሮቢት/ጋባ፤ በጭልጋ/መተማ/ሽንፋ፤ በወገራ/እንቃሺ፤ በቆላ ወገራ፤ በበለሳና በስሜን ወዘተ፤ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ የአማራ ተወላጅ አልቋል። በየትኛውም የአገራችን ክፍሎች በዘር ኃረጋቸው ምክንያት በግፍ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን በታሪክም በህግም ተጠያቂውና ዋጋ ከፋዩም ማንም ሳይሆን፤ ወያኔ ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቸውም በላይ ካሳለፋቸው የወያኔ የተንኮል ተመክሮዎች መማር እጅግ አስፈላጊም ወቅታዊ ጥያቄም ነው። አሁን እየተደረገ ያለው ሁሉንም ጎሳዎች ያቀፈ የመንግሥት ተቃውሞ አፈሙዝ ወደ እርስ በርስ ፍጅት ለማዞር ወያኔ ቀን ከሌት እየሰራበት ያለ የመጨረሻው ተንኮል ነው። ይህ ተንኮል እኛ ከምንለው በላይ ዘልቆ በስሜን ሸዋ፤ በሰላሌ፤ በመርሐቤቴ እንከን የሌለውን ፍጹም ሰላማዊ ሰልፍ ለማንደፋረስና ሁከት አስነስቶ በወታደር ኃይል ሕዝቡን እንዲፈጅና የሰልፉን ዓላማ ለማሳት የወያኔ ምልምሎች በሰው ንብረትና ህይዎት ላይ ጥፋት ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ በሕዝብ ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ግልጽ ማስረጀ ነው።

ሰሞኑን በሰሜኑ የአገራችን አካባቤ ደግሞ፤ በወልቃይት/ጠገዴ አና በቃፍቲያ ሁመራ አካባቤ ከዘር ጭፍጨፋ የተረፉ የአካባቢው ተውላጆች የንግድ ቤቶች ስማችውን ከአማርኛ ወደትግርኛ መለወጥ አለባችሁ ተብለው ትእዛዙን አንቀበልም ባሉና ለማንነታቸው ቆርጠው የተነሱ ወገኖቻችን ከሥራ ቦታቸው እየተለቀሙ ወደ እስር ቤት መወርወራቸውን ስንሰማ ቁጭታችን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል። ይህን አረመኔ እና ዘረኛ ሥርዓት ለመለወጥና የሰው ልጅ በማንነቱ ተከብሮ እንዲኖር የምናደርገውን ትግል በርትተን እንድንቀጥል እልህ የሚያስገባ እንጅ ተስፋ እንድንቆርጥ አያደርገንም። የሰው ልጅ በተፈጥሮ ያገኘውን ማነንት በግዳጅ ለማስቀየር መግደልና ማሳደድ ከህግም ሆነ ከሞራል አኳያ ተቀባይነት የሌለው የጨካኞች ባሕሪ ነው። እንዲህ ያለውን ጨካኝ አገዛዝ ከድርጊቱ ማስቆም የሚቻለው በተቀነባበርና በተባበረ የሕዝብ ትግል ብቻ ነው።

ዛሬ የወያኔን የግፍ አገዛዝ ማክተሙን እኛ የምንታገለው ብቻ ሳይሆን፤ የዓለም ማህበረሰብ ጠንቅቆ አውቆታል። የነብስ አባቶቹ አሜሪካኖች ጭምር የኃይል ሚዛናቸው የት ላይ እንደሆነ ጠንቅቀው በማዎቃቸው ምክንያት፤ ባለፈው ሳምንት መብቱን ጠይቆ አደባባይ የወጣውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት ከመግደል ተቆጥቦ ሰላማዊ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። ቱባ ቱባ ባለሥልጣኖች መግቢያ ቀዳዳ ፍለጋ ለ40 ዓመት ከጨፈጨፉት ሕዝብ ለመሸሽ ወይም እዳቸውን በቀላሉ ለማወራረድ ወይም ሌላ የማጭበርበሪያ ቀዳዳ ለመፍጠርና በሕዝብ መካከል ገብተው የሕዝቡን እንቅስቃሴ ለመበታተን ከሥልጣናቸው መሰናበት ጀምረዋል። ቀሪዎቹም ደግሞ እንኳን እንደ ኢህአዴግ ጠንክረው ሊቆሙ ይቅርና እንደ ግል ድርጅቶቻቸው (ብአዴን፤ ወያኔ፤ ኦህዴድ) መስማማት ያልቻሉበት ወቅት ላይ ናቸው። ይህን የገማ ሊጠገን የማይችል ጥርስ የመሰለ ሥራዓት ከሥሩ ነቅሎ በዲሞክራሲያዊ መሠረት ላይ የቆመች የጋራ ሀገር ለማቆም የሚቻለው ደግሞ ሁሉም ተባብሮ ለመሥራት የድርሻውን ሲወጣና የወያኔን ሴራ ሲያመክነው ብቻ ነው ብሎ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ያምናል።

ስለሆነም፤ በአሁኑ ሰዓት በኦሮምያ አካባቢ የተቀጣጠለውን የሕዝባዊ እምቢተኝነት በወያኔ ሙሉ ኃይል ርብርቦሽ የወገኖቻችንን ህይወት ቀጥፎ ሌላ የግፍ ዘመን ከማራዘሙ በፊት፤ ባለፈው ዓመት በጎንደር፤ በጎጃም እና በሌሎችም አካባቢዎች እንደተደረገው ሁሉ በጋራ መነሳት ጊዜ የማይሰጠው የነፃነት ደወል ነውና ጥሪያችን ይደረሳችሁ።

በመጨረሻም ዛሬም እንደ ትናንቱ ለትግራይ ሕዝብና ምሑራን ማሳሰቢያችን ሳናስተላልፍ አናልፍም። ይህ በእናንተ ከእናንተ አብራክ የወጣው ወያኔ ለእናንተ መከታና ብልጽግና ቆሚያለሁ እያለ ለሥልጣን ማራዘሚያው ሺፋን ሊያደርጋችሁ ጧዋት ማታ የሚለፈልፈው ለእናንተ ለትግርኛ ተናጋሪዎች አስቦ ሳይሆን ሥልጣኑን ለማሰንበት ብቻ ነው። ወያኔ የትግራይን ሕዝብ እንደማይወክል እናውቃለን ነገር ግን አብሯችሁ ከሚኖረው ቀሪ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ደም እያቃባችሁ መሆኑን ልትረዱት ይገባል። ወያኔ ከመቃብሩ አፋፍ ላይ ቆሟል፤ ነገ ወደ መቃብሩ ሲገባ የትግራይ ሕዝብ ግን ይኖራል። ታዲያ አሁን በናንተ ስም የሚደረገውን ግፍ ልታወግዙና ከወገናችን ጋር አታቆራርጡን ማለት መቻል ነበረባችሁ። እናንተ ግን ዝምታን መርጣችኋል!! ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በስማችሁ በሚቀልደው የወያኔ ቅልብ አጋዚ ጦር በሚደረገው እልቂት እርር፤ ድብን ያለ ሕዝብ ነገ የማይጠፋ እሳት ሆኖ ሊለበልባችሁ እንደሚችል መገንዝብ አለባችሁ። ከሌላው ወገናችሁ ጋር ቁሙና ይህን የወያኔን መንግሥት ተቃወሙ። ይህ አባባላችን እናንተን ለማንገራገር ሳይሆን እየተሄደበት ያለው መንግድ ሀቁን ቁልጭ አድርጎ ስለሚያሳይ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s