አይነኬ የህወሓት ጀነራሎች!!! በኮንትሮባንድ የሰከሩ፣የደም ገንዘብ!!! ክፍል አንድ – ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

‹‹በፊት በፊት እኛን መመርመር አይቻልም” ያሉ የዘመናችን የመንግስት ተቋማትን አይተናል፡፡ ይሄ እንግዲህ የፖለቲካ አይነኬዎች መፈጠራቸውን ያረጋግጥልናል፡፡ መሬት የዘረፉ እጃቸውን ቸብ ቸብ ተደርገው፣ ተቀጡ ተብለው ወዲያው ይለቀቃሉ፡፡ አንድ ሞባይል የመነተፈ ግን አደገኛ ቦዘኔ ተብሎ ከ2 ዓመት በላይ ይታሰራል፡፡ የፖለቲካ ኃይልና የዘረፋ ኃይል ውህደቱ ከፍተኛ ነው፡፡ “ይሄ የኔ ሰው ነው፤ አትንካው” የሚባልበት የአይነኬዎች ስርአት ነው የምለው ከዚህ አንፃር ነው፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

የህወኃት የጦር አበጋዝ  መንግስት፣“ይሄ የኔ ዘር ነው፤ አትንካው” የሚለውን ወያኔ የኢትዩጵያ ህዝብ ከስሩ መንግሎ መጣል በሃገር የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ነው፡፡ ዘውጌኛ የትግራይ፣የሶማሌ ወዘተ ጠባብ ብሄረተኛነት በሰፊ ኢትዩጵያዊ ብሄረተኛነት መተካት አለበት፡፡ በሕወሓት በተቀናበረው ሴራ፣ የሱማሌ የጦር አበጋዞች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሱት አደጋ፣ የሞት፣ የስደት፣ የመፈናቀል፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ጥቃቶች አብሮ በኖረው ህዝብ ዘንድ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያልፋል፡፡ የወያኔ የፖለቲካ ሴራ ተጋልጦ የሱማሌና የኦሮማ ህዝብ አብረው ይኖራሉ፡፡ የህወኃት ጄነራሎች እነ ጄነራል አብርሃም ወልዴ (ካርተር) በሱማሌ ክልል ውስጥ ስውር መሪዎች በመሆን፣ አብዲ ኢሊ በመሾም  ልዩ የፖሊስ ኃይል በማደራጀት የፖለቲካ አይነኬዎች በመፍጠር  ከሱማሌ የጦር አበጋዞች ጋር ሽርክና መስርተዋል፡፡ የኢኮኖሚ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በኮንትሮባንድ ንግድ በተለይም በጮት፣ ማእድን ኃብት፣ የቁም እንሰሳትን ወዘተ በድንበር ዘለል ንግድ በማካሄድ የውጪ ምንዛሪ ዶላር በማከማቸት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረዋል፡፡ ለዘመናት አብረው የኖሩትን የሱማሌና የኦሮሞ ህዝብ በማጣላት ከሱማሌ ክልል የኦሮሞ ተወላጆችን በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠር ህዝብ ከኖረበት ቀየ እንዲፈናቀል አድርገዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ የእንቢተኝነት ትግልን ለማኮላሸት ህወኃት የጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ የመከላከያ ሠራዊቱ ጣልቃ አልገባም፣ እንዲውም ከፍተኛ የኦህዴድ አመራሮች ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል፡፡  የህወኃት በትረ ሥልጣኑን የማቆየት አንዱን ብሄር ከሌላው በማጋጨት በተለይም የአማራና የኦሮሞ ህዝብን በማጣላት ስልቱ ከሽፎበታል፡፡ በዚህም የተነሳ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በምድረ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሱማሌ የጦር አበጋዞች መንግስት በመፈልፈል የአናሳ ብሄራት ህብረት በመፍጠር፣ ለልዩ ፖሊስ ኃይል መሣሪያ በማሳታጠቅ የኦሮሞ ህዝብ ላይ በማዝመት ታሪክ ይቅር የማይለው በደል በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌሎችም የኢትዩጵያ ክልሎች ተመሳሳይ የጦር አበጋዞች መንግስት፣ በህወኃት መፈጠራቸው አይቀሬ ነው፡፡

 

{1} የጦር አበጋዝ ማለት የግል ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብትን የሚያካብት ተዋናይ ሲሆን በአንድ ሃገር፣ያለው መንግስትና መንግስታዊ መዋቅሮች ጠንካራ ባልሆነበት አካባቢ የሚፈለፈል የጦር አበጋዝ ነው፡፡(ማኪንሌይ፣2007)‘Warlord’ is a term which used to describe a specific period of China’s history but which has re-emerged as a label during the last three decades (MacKinlay, 2007). The definition of a warlord differ, but most authors agree that a Warlord is an actor who accumulate power and wealth for private means by using military force in an environment where the formal state has little or no control (Reno, 1998, MacKinlay, 2007). በኢትዮጵያ ወታደራዊው መንግስት ሲዳከምና በየቦታው ከአማፂያን ጋር ጦርነት ሲገጥም ድንበር ላይ ያሉ ግዛቶች የሚያገናኛቸው መስረተ ልምት መንገድ፣ ባቡር ወዘተ ያልዘመነ በመሆኑ ምክንያት የመንግስት ሥልጣንና ኃላፊነት እየተዳከመ ሲሄድ ቀየው በአካባቢው በሚገኙ የጎሳ የጦር አበጋዞች (የጎበዝ አለቃዎች) ህወኃት፣ሻብያ፣ኦነግ ወዘተ ቁጥጥር ስር ወደቀ፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዩጵያ ታሪክ ከ1960 እስከ ከ2010ዓ/ም እስካሁን ያለው አገዛዝ የወያኔ ‹‹ዘመነ-ጦር አበጋዞች  መንግስት›› እንደ አሸን የተፈለፈሉበት ዘመን  እንደሆነ ጥናታዊ ፁሁፉ ያስረዳል፡፡

2} ‹‹የፖለቲካ የማንነት ጥያቄ›› Identities Politics

በአፍሪካ የዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት ፅንሰ ሃሳብ ዋነኛና አንገብጋቢ የፖለቲካ ጥያቄ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ዘውጌ ብሄረተኛነት፣‹‹በማህበራዊ ጭብጦች ላይ ሳይሆን፣ በዝርያ፣ በወገን መመሳሰል ላይ የተመሠረተ ብሄርተኛነት››ነው፡፡ (አንዳርጋቸው ፅጌ ገፅ310) በዘመነ-ጦር አበጋዞች በጎሳ፣ በነገድ፣ በዘር፣ በዘውግ፣ በክልል (የደም ግንኙነት፣ የዘር ሃረግ፣ የቌንቌ፣ ወዘተ) ላይ የተከለሉና የተመሠረቱ አንድ ዘርን  በውትድርና በማሠልጠን፣ በማደራጀትና ተዋጊዎች በመመልመልና በሌሎች ዘሮች ላይ በማስነሳት፣የፖለቲካ ሥልጣን ለመጨበጥ የማንነት ጥያቄን ሽሮ መብሊያቸው አደረጉት፡፡ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦይዝም ቀመስ የሆኑ የጦር አበጋዞች በስመ ሶሻሊዝም የብሄር ብሄረሰብን ጥያቄ በማራገብ የጀሌውን ደቀ መዝሙር ህሊና አጠቡት፡፡ የጦር አበጋዞቹ እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ  የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡

በኢትዩጵያ ውስጥ በዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት  በጉጠኛነት፣በዘውገኛነትና በዘር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች መኃል፤ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ(ህግሓኤ)፣ኤርትራ አርነት ግንባር(ኤአግ)፣ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት)፣ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ(ግገሓት)፣የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ)፣የኦሮሞ እስላማዊ ነፃ አውጭ ግንባር(ኦእነግ)፣ምዕራብ ሶማልያ ነፃ አውጭ ግንባር(ምሶነግ)፣በሱማሌ (ኦኤንሌኤፍ) በጋንቤላ()፣የሲዳማ አርነት(ሲአን)፣ ቤኒ-ሻንጉል()፣አፋር ነፃ አውጭ ግንባር(አነግ) ወዘተ ማዕከላዊውን መንግስት በማዳከም ስልጣን የሚቆጣጠሩበት ስርዓት ሆነ፡፡ በዘመነ-ጦር አበጋዞች በነፃ አውጭ ስም፣ በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግላቸው ሎሌ ጦር ሰራዊት ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን በማደራጀትና በመመልመል ተግባር ላይ ተሰማሩ፡፡ የጦር አበጋዞቹ በግለሰቦችና በተለያዩ ቡድኖች ላይ ጥላቻን በመፍጠር የራሳቸውን የጦር ሰራዊት በማቆቆም ጥቅማቸውን ያስጠብቃሉ፡፡ እንደ ቶማስ ገለፃ ከሆነ፣የጦር አበጋዞቹ ሚና የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት ጋር ይወዳራል፡፡ ‹‹የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት አመሰራረቱ፣ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ  ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም  ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡››(ቶማስ 2005 ገፅ 79)

Constructivism is a social theory that underlines the importance of studying the ideational dimension in international relations, such as norms and knowledge. The main ideas of Social Constructivism is that these collectively held ideas are socially constructed and are therefore able to change in different contexts. Identity is one of those concepts, which has been socially constructed and is therefore malleable in distinct situations. Warlords are often using identity as a means to mobilize and recruit fighters to their private armies, or to create hostility between different groups of individuals in order to advance their own interests. The warlord’s role can be compared to that of the identity entrepreneur’ as defined by Thomas et al.:“An identity entrepreneur is an individual or group of individuals who find it desirable, profitable or otherwise utilitarian to create and reinforce group identities. They will specifically seek to exploit such volatile situations and will do so by reinforcing existing cleavages or create new ones“ (Thomas et al. 2005, p. 79).

One of the most efficient ways of creating new and enforcing existing identities is by confronting them to a real or made-up threat against the individuals of a certain group. This was the method used to reinforce the hostility between Hutus and Tutsis in Rwanda, before and after the genocide. By constructing a threat of extermination and nourishing it with speeches and symbols in the same direction, leaders of the Hutu extremists managed to reinforce existing cleavages in such a way that it could mobilize genocide.

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት በተራው አርጅቶ ሲዳከም፣ ዴሞክራሲ አልዋጥልህ ሲለው፣ ህገመንግሥቱን በህገ-አራዊትነት ሲተካ፣ በስብዓዊ መብቶች ጥሰት ሃገሪቱን ዜጎችን እስርቤት ሲያደርግ፣ የጅምላ መቃብር በየቦታው ቆፍሮ ተቃዋሚዎቹን ሲቀብር ሁለት አስርት አለፈው፡፡ ዛሬ በየክልሉ ከአማፂያን ጋር ጦርነት በመግጠም የወያኔ መንግስት ሥልጣንና ኃላፊነት ‹‹ላንባው ተነቃነቀ!!! የወያኔ መንግሥት ወደቀ!!!››ተባለለት፡፡ የህወሓት መንግሥት እየተዳከመ ሲሄድ ቀየው በአካባቢው በሚገኙ የጎሳ የጦር አበጋዞች (የጎበዝ አለቃዎች)   ቁጥጥር ስር ወደቀ፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዩጵያ ታሪክ ከ1997 ጀምሮ እስከ 2008ዓ/ም እስካሁን ያለው ዘመን ለነጻነት፣ እኩልነትና ለፍትህ በሚታገሉ የክልል ነፃ አውጭዎች፣ የጎበዝ አለቆች በየቦታው ወያኔን የቁም ስቅሉን እያሳዩት ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር የጎበዝ አለቆቹ ህብረብሄር ሆኖ መታገል ለሃገሪቱ መጪው እድል ወሳኝ ሲሆን ከወያኔም ተምረው በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ ‹‹የጦር አበጋዞች መንግሥት›› ሥርዓት ከታሪክ ሙዚየም ውስጥ እንደ ‹‹ዘመነ-መሣፍንት›› መቀመጥ የቀጣዩ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡፡ ወያኔ  ከትግራይ ይዞት የመጣው የትግራይን ገበሬ ለጦርነት አሰልፎ ነው! ነገም የአማራው ነፃ አውጪ አማራውን ገበሬ አስታጥቆ ይፋለማል፣ የኦሮሞው የአርነት ታጋይ የኦሮሞውን ገበሬ አስታጥቆ ይዘምታል፣ የሱማሌው፣ የአፋሩ፣ የወላይታው ወዘተ እንዲሁ በየዘሩ ይቃኛል፡፡ ወገን አዙሪቱ ክብ ነው!!! ከአንዱ የጦር አበጋዝ የዘር አገዛዝ ወደ ሌላው እያልን የሃያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን በተረትና በቀረርቶ ‹‹የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች፣ ልጆቾም ያልቃሉ እሶም ትሞታለች!!!›› እተዘፈነልን (9 ክልሎች) መሆናቸውን ልብ ይበሉ! ወጣቶች እየተገደሉና እየተሰደደዱ፣ ሴቶች እህቶቻችን እየተደፈሩና እየኮበለሉ፣ ህጻናት በርሃብ የሚሞቱባት፣ መውለድ እንጂ ማሳደግ ያማይችሉ ወላጆች፣ በርሃብ ዓለም ያወቀንና ከአፍሪካ አንደኛ መሆናችን፣ የክልሎች የድንበር ግጭት የሚፈበረክበትና ጦርነት የማያባራባት ሃገር ውስጥ መኖራችን ግድ ይላል፡፡ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የሃገራቸውን ፖለቲካ የማያውቁ የሥልጣን ሱሰኞች፣ ካድሬዎችና ጀነራል መኮንኖች፣ ሹንባሽ ምሁራን፣ ሆድአደር ባለሃብቶችና ሁላችንም  በታሪክ ተጠያቂዎች ነን፡፡ በተለይ አድርባይ ወገንተኛ ጋዜጠኞች፣ ሙያና ፖለቲካ በመለየት ሙያዊ ሥነ-ምግባር በማክበር፣ ከወያኔ መንግሥት መወገድ በኃላ ምን ዓይነት ሥርዓት መገንባት አለበት በሚል ርዕስ ራዕይ ያላቸውን ምሁራንን በማነጋገር እንደ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ መጪውን ዘመን ብሩህ ተስፋ ዴሞክራሲያዊ ባህልን በማስተማር፣ የኃይማኖት እኩልነትን፣ የዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ መንግሥታዊ ስርዓትን    አወቃቀር፣ የፖለቲካ ልዩነትን በውይይት የመፍታት የሠለጠነ ጥበብ፣ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ዘርፎች የማክሮና የማይክሮ ፖሊሲዎች በማስረጃ ተንትኖ ለህዝብ ማሳወቅ፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የምሁራን ኃላፊነት  ይሆናል፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች፣ የድረ-ገፅ ዓምደኞች ወዘተ የጥላቻ ፖለቲካን ከማራገብ ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ከመፍጠርና ከዘር ፍጅት ቅስቀሳ የሃገራችንን ህዝብ መጠበቅ ታሪካዊ ሓላፊነት አለባቸው፡፡

 

3} የጦር አበጋዞች ክልል የማስፋፋት ፖሊሰ

የወያነ ጦር አበጋዞች የኢኮኖሚ ዘርፍ ግንባታ በብሄራዊ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ያተኮረ ሳይሆን በትግራይ ጠባብ ብሄርተኝነት ላይ ያተኮረ ክልላዊ የጦር አበጋዞች ምጣኔ ኃብት ( The economics of warlordism) የተንሸዋረረ የኢኮኖሚ ግንባታ ነው፡፡ ህወሓት ለዓመታት በትግራይ ህዝብ ላይ በጫነው የአማራ የጥላቻ ፖለቲካ የትግራይን ህዝብን ከአማራ፣ከአፋር፣ከኤርትራ፤ከሱማሌ፣ከኦሮሞ፣ከጋምቤላ ወዘተ ህዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፡፡ የህወሓት ክልል በማስፋፋት ድንበር በመግፋት አንዱ ዘር በአንዱ ዘር ላይ ጦር እንዲሰብቅና የጎሪጥ እንዲተያይ የማድረግ የሥልጣን መንበር ለማስጠበቅ፣ ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመንደፍ ነው፡፡ የመለስ ዜናዊ ቅርስና ውርስ (የህወሃግ/ኢህአዲግ መንግስት የኢትዬጵያዊያን ዜጎችን ጭስኛ በማድረግ የገጠርና የከተማ መሬት ሃብትን በሞኖፖል ይዞል፡፡ እንዲሁም የትግራይ ክልል መሬት 65,900  ኪሎ ሜትር ስኮይር ወደ 85,366.53  ኪ.ሜ ስኮይር ያደረሰው ከአማራ ክልል ከወሎና ከጎንደር እንዲሁም ከአፋር ክልል በአጠቃላይ  19,466.53Kmኪሎ ሜትር ስኮይር መሬትና የራስ ዳሽን ተራራንም ወደ ትግራይ ለመከለል እቅድ ሲኖራቸው በአጠቃላይ ወደ ትግራይ ክልል የተከለለው ቦታ የጦር አበጋዞች ክልል የማስፋፋት ፖሊሰ ውጤት ነው፡፡

የጦር አበጋዞች ክልል የማስፋፋት ፖሊሰ በነ ዶክተር ገብረአብ በርናባስ  ጠባብ ዘረኝነት ስሜት ከጎንደር፣ ከወሎ፣ከአፋር ህዝብ ለም መሬት በመንጠቅ ወደ ትግራይ ክልል በማካተት የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ደሃ ወንድሞቹና እህቶቹ የማለያየት ፖሊሲ ውጤት ነው፡፡ ከጎንደር መሬት ሁመራ፣ ወልቃይት ወዘተ የሠሊጥ ለም መሬት ላይ የትግራይ የጦር ጉዳተኛችን በማስፈር፣ የአገሬውን መሬት በግፍ በመንጠቅ የተቃወመውን ህዝብ በመግደል፣በማሰር እንዲሰደድ በማድረግ ኃብቱን ተቆጣጥረዋል፡፡ በ2006 እኤአ 51776 ቶን ሠሊጥ ወደ ውጪ በመላክ 50 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶል፡፡በ 2008እኤአ ከተመረተው 1.3 ሚሊዩን ኩንታል ሠሊጥ 900000 ኩንታል ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ በፖርት ሱዳን በኩል በማውጣት 121.5 ሚሊዩን ዶላር የውጪ ምንዛሪ የትግራይ ክልል እንዳገኘ የትግራይ ክልል እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዶክመንት ይገልጸል፡፡ በተመሳሳይ ከአፋር የጨው ማዕድናት ፋብሪካዎች በመትከል አብዛኛዎቹን የሚቆጣጠሩት የትግራይ ጦር አበጋዞች ናቸው፡፡ እንዲሁም በአፋር የተገኘውን የፖታሽ ማዕድን አምርቶ ለመሸጥ በአፋር በኩል በትግራይ አርጎ ጅቡቲ የሚገባ የባቡር መስመር ዝርጋታ የጦር አበጋዞቹ የኃብት ቅርምትና የመስፋፋት ፖሊሲ ስትራቴጂ ውጤት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢኮኖሚውን እስከተቆጣጠርን ድረስ፣ የመከላከያና የደህንነት አፋኝ መንግስታዊ መዋቅር በመገንባት የኢትዩጵያን ህዝብ በልማታዊ መንግስት ስም ለዘመናት ለመግዛት እንችላለን የሚል የጦር አበጋዞቹ የአናሳ ዘውጌ የስነልቦና ቀውስ ሰለባዎች ናቸው፡፡ ከሌሎች ክልሎች የተነጠቁ መሬቶች፣ሳይውል ሳያድር ወደ ተነጠቁት ክልሎች የመሬት ይዞታ እንደሚገባ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብና ምሁርም ይህን ኢፍህታዊ የመሬት ነጠቃ ማውገዝ ይጠበቅበታል፡፡ የዘውጌ ጦር አበጋዞች ለስልጣናቸው፣ ለዝናቸውና ለገንዘብ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሚሊዩን ህዝብ መስዋት ቢሆን፣ ምድር ቢቃጠል፣ ንብረት ቢጠፋ ደንታ የላቸውም፡፡ warlords are “people who are driven overwhelmingly by personal power, glory, and monetary gain and who are ready to sacrifice thousands of lives, land, and property for that power.”12 Lezhnev claims that the central motivation of the warlord, in addition to monetary resources, is the quest for “wealth, power, and fame.”13 This thesis accepts the idea that warlords share two main characteristics: they have military legitimacy, and they are motivated by political power, wealth, and fame.

 

4} በተለያዩ አገሮች ድንበር ዘለል ወንጀሎች(Transnational Crime)

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ድንበር ዘለለል ወንጀሎች ህገወጥ የሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ በተለይ የቁም ከብት፣ ቡና፣ ሠሊጥ፣ ጫት፣ ወርቅ ወዘተ ምርቶች  ወደ ሱዳን፣ሱማሌ፣ ኬንያና ጅቡቲ በድንበር አሻግረው ይሸጣሉ፡፡ የወያኔ የጦር አበጋዞች የጦር መሣሪያዎች ሽያጭ ወደ ሱማሊያ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲና ኤርትራ ንግድ ያከናውናሉ፡፡ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ህፃናቶች ሽያጭ፤የወያኔ መንግስት ለአንድ ህፃን 30 ሽህ ዶላር በማደጎነት በመሸጥ በዓለም ይታወቃል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች የመሬት ነጠቃና ሽያጭ ለህንድ፣ለቻይና፣ለፓኪስታን ለሳውዲ አረብያ ቱጃሮች በመሸጥ ይታወቃላ፡፡ የዕፅ ዝውውር፣የውጭ ምንዛሪ ማሸሽ፣ወርቅና የከበሩ ድንጋዩች ሽያጭ፣ባህላዊ ቅርሳ ቅርሶች ዝርፍያና ሽያጭ በመፈፀም ኃብት ያከማቻሉ፡፡

‘‘In February 2011, Global Financial Integrity released a report titled “Transnational Crime In The Developing World“, which estimates that “the global illicit flow of goods, guns, people, and natural resources is approximately $650 billion”.[13] The report examined the illicit trafficking of drugshumanswildlifecounterfeit goods and currencyhuman organssmall armsdiamonds and colored gemstones, oil, timberfishart and cultural property, and gold. The report found that, in general, transnational crime flourished in developing countries with inequality, poverty and weak governments. ”

United Nations Development Programme

The most recent report was commissioned by the United Nations Development Programme. The report, entitled “Illicit Financial Flows from the Least Developed Countries: 1990-2008” found that “structural characteristics of Least Developed Countries could be facilitating the cross-border transfer of illicit funds,” examined issues with estimating illicit flows, analyzed the magnitude of illicit flows, and “made policy recommendations for the curtailment of these illicit flows”.[14] The report found that about $197 billion had been taken illicitly out of the 48 poorest developing countries and into mainly developed countries between 1990–2008, and that “African LDCs accounted for 69 percent of total illicit flows, followed by Asia (29 percent) and Latin America (2 percent).” Trade mispricing was found account for over 60% of illicit outflows.(Source:-www.gfintegrity.org)

‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው መንግስታዊና ፖለቲካዊ ስልጣን መናጋት ምክንያት ከሀገር እየኮበለሉ ካሉት ባለስልጣናት ሌላ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ እጥረት እንዳለ የሚነገርለት የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ በተለያየ መንገድ ከሀገር እያመለጠ ሲሆን በዚህ ሳምንት ብቻ 1,800,000 ዶላር ከሀገር ሊሸሽ ሲል በምስራቁ የሀገራችን ክፍል መያዙ ታወቀ። ይህ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከኢትዮጵያ ለማውጣት ሲሞኸር የተያዘው የውጭ ምንዛሪ መጠን ለሁለተኛ ግዜ ሲሆን ከወራቶች በፊት 541,771 ዶላር ሊያመልጥ ሲል መያዙ ተሰምቷል። የኦሮሚያ ክልል መገናኛ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ ገንዘቡን ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች መርጃ ይውል ዘንድ የምስራቅ ኦሮሚያ በመፍረዱ በተረጂዎቹ ባንክ ገቢ መደረጉንና ገንዘቡን ይዘው ሊያመልጡ በነበሩት ሁለት ሰዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው የ8 ዓመት እስራትና 100,000 ብር ቅጣት መወሰኑን መግለጻቸው ይታወቃል። የፌዴራሉ መንግስት በውጭ ምንዛሪ እጥረት ተጎዳቻለሁ እያለ የብርን ዋጋ ተመን ዝቅ በማድረግ አጣሁት ያለውን የውጭ ምንዛሪ ለመሰብሰብ በሚራወጥበት ወቅት ይበልጥ የሚያባብሱ ተግባራት ሲፈጸም ማየት ያስገርማል ይላሉ የ1.8 ሚሊዮን ዶላርን መያዝ የሰሙ ታዛቢዎች። የኢትዮጵያ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣንን መግለጫ ዋቢ በማድረግ የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው ገንዘቡን ሲያሸሹ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን የተያዘውም ባገባደድነው ሳምንት እለተ እሮብ ቦምባስ እና ቶጎ ውጫሌ በተባሉ ኬላዎች ላይ እንደሆነ ተብራርቷል።›› ዶላሩ መሸሹን ቀጥሏል $1.8 ሚ. ዶላር ተያዘ Oct22, 2017 አባይ ሚዲያ በወንድወሰን ተክሉ

{5} ከኢትዩጵያ ድንበር ዘለል የቁም እንስሳት ንግድ

ከኢትዩጵያ ከመካከላኛው ምስራቅ አገራቶች አንፃር በቁም እንስሳትና የሥጋ ውጤቶች  ንግድ ትልቅ ጥቅምና ብልጭ ያላት ሃገር ስትሆን የቆላማው ዝርያ በተለይም የቦረና በሬና የሱማሌ ጥቁር ጭንቅላት ያላቸው በጎች ዝርያ በብዙ ደንበኞች ተወዳጅ ናቸው፡፡ ወደ ውጪ የሚላኩ 1.6 ሚሊዩን የቁም እንስሳት በአመት ወደ ባህር ማዶ ገገራት በተለይም የገልፍ አገራትና ግብፅ ይላካል፡፡ የሚገርመው ታዲያ ከዚህ ውስጥ 1.4 ሚሊዩን የቁም እንሰሳት ህገወጥ በሆነ መንገድ ከሃገራችን እንደሚወጣ ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት  በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሱማሊያ በደቡብ ክልሎች በኩል ከኢትዩጵያ ድንበር ዘለል የቁም እንስሳት ንግድ ወደ ሱዳን፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያና ኤርትራ በመላክና በመሸጥ ዳጎስ ያለ የውጭ ምንዛሪ ዶላር በውጭ ሃገራት ባንኮች የዘረፈውን ያስቀምጣል፡፡

Ethiopia has some important comparative advantages in the Middle Eastern livestock and meat markets. The meat characteristics of Ethiopia’s lowland breeds—particularly Boran bulls and Somali Blackhead sheep—are prized by consumers. Geographical proximity to Egypt and the Gulf makes both live animal exports and chilled meat exports possible. Live animal exports are high, as an estimated 1.6 million livestock1are exported from the country annually—although the vast majority of these (approximately 1.4 million) pass through informal channels.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s