የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ አመራር አባላት በሲሳይአጌና ትኩረት ላይ የሰጡትን ቃለምልልስ – ያሬድ ጥበቡ

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ አመራር አባላት በሲሳይአጌና ትኩረት ላይ የሰጡትን ቃለምልልስ በጥሞና አደመጥኩት ። እናም ሃዘን ተሰማኝ ። ታዳሚዎቹ ወያኔ የተንገዳገደ መሆኑንና ሥልጣንም እጃቸው ላይ ሊወድቅ እንደሚችል የተገነዘቡ ቢሆንም፣ አሁን የተፈጠረውና በመባባስም ላይ ያለው ፖለቲካዊ ድቀት ምንጩ ምን እንደሆን የተረዱ አይመስሉም ።

ያሬድ ጥበቡ

እኔ እስከሚረዳኝ ድረስ የአሁኑን የፖለቲካ ድቀት አይነተኛ የሚያደርገው የሥርአቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሥልጣናቸው መልቀቅ ነው ። ይህን በዱሮ ማርክሳዊ ትንተና አለባብሶ፣ ሥርአቱ ሊወድቅ ስለሆነ፣ መርከቡ ከመስጠሙ በፊት የሚዘሉ የመጨረሻዎቹ አድርባዮች ድርጊት አድርጎ ዶክተር ብርሃኑ መተንተኑ ገርሞኛል። የፖለቲካ ሀሁ ካለማወቅ የሚመነጭ ጀብደኝነት ይመስላል ። አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣ ለማ መገርሳና ዶክተር አቢይ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያላቸውን ተቀባይነት ካለመረዳት የመነጨ ይመስለኛል ። ይህም በፖለቲካ ጥላቻ ከመጨፈን የሚመጣ ችግር ይመስለኛል ። በእኔ እምነት አንድ መረዳት ያለብን ነገር ቢኖር፣ የብአዴንና ኦህዴድ አመራሮችና አባላት የሚያስተዳድሩትን ልዩ ሃይልና ፖሊስ ከህዝብ ጋር እንዲተባበር ባይፈቅዱ በነዚህ ክልሎች የሚታየው ህዝባዊ ተቃውሞ በእንጭጩ ይቀጭ ነበር ። የኢአን አመራሮች ይህን ሃቅ ቢረዱ ኖሮ ኦህዴድንና ብአዴንን ተላላኪ፣ አድርባይ ወዘተ በሚሉ ቅፅሎች ባልጠሩዋቸው ነበር ። እነዚህ አመራሮች ለራሳቸው ለመዋሸት ፈቃደኛ ካልሆኑ በስተቀር፣ በኦሮሚያና አማራ ክልል የተነሱትንና ያሉትን ህዝባዊ ተቃውሞዎች ራሳቸው እንዳልመሩዋቸውና እንዳላደራጁዋቸው ያውቃሉ። ይህም እውነት ከሆነ፣ ለዚህ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ሃገራዊና ኢህአዴግ ውስጥ ያሉ ሃይሎችንና የማህበራዊ ሚዲያ የጎበዝ አለቆችን እንደማመስገን፣ ማውገዝን የመረጡም ይመስላል ።

በተለይ ብርሃኑ የማህበራዊ ሚዲያ ጎበዛዝትን ለምን ግንቦት 7 ከኦጋዴን ድርጅት ጋር በተናጠል ያደረገውን ስምምነት ተቻችሁ፣ ለምንስ ኦዴግ ከወያኔ ጋር ለመደራደር ካርቱም ሄደ ብላችሁ ፃፋችሁ በማለት፣ የህፃን ፖለቲካ ብሎ እስከማንቋሸሽ ደርሷል። በሚዲያ ነፃነት አይን ሳየው በሁለቱም ጉዳዮች ላይ የተነሱት ትችቶች ተገቢና ብርሃኑ እታገልለታለሁ ከሚለው የዴሞክራሲ መብት ጋር የተቆራኙ ናቸው ። የወያኔ የፖሊትቢሮ አባል የነበረው ሙሉጌታ ጫልቱ የተገኘበት ስብሰባ ላይ አቶ ሌንጮ ሲገኝ ፣ ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ መመለሱ ስለሚታወቅ፣ ያ ለጥርጣሬ በር ቢከፍትና መነጋገሪያ ጉዳይ ቢሆን፣ ይህን በበጎ አይን እንደማየት፣ አገራዊ ንቅናቄውን ለማዳከም እንደተደረገ አድርጎ መተርጎም ከአምባገነናዊ አስተሳሰብ የሚመነጭ ችግር ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሊታረምም ይገባል። ከዛሬ እንዲህ ከተባለ ነገ ሥልጣን ሲያዝ፣ ሌላ ዙር የአምባገነንነት አዙሪት እንደማይቀጥል ምን መተማመኛ አለን? ለዚህም ነበር፣ ኢሳትን ካሁኑ የመፃኢቱ ኢትዮጵያ ሚዲያ ተምሳሌት አድርጉት፣ የድርጅት አፈቀላጤ አይሁን ብለን ስንወተውት የከረምነው ።

በተረፈ፣ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ሲጀምር የጠየቀውን የአማራ ድርጅቶች በአገራዊ ንቅናቄው አለመካተት ጉዳይ መልስ ሳያገኝበትም ሆነ ሳይገፋበት መተው ግር የሚል ነበር ። መሃል ላይ ቪዲዮ ስትሪሙ ሲቋረጥ አምልጦኝ እንደሆን እንጃ፣ ግን የተመለሰ አይመስለኝም ። የአገራዊ ንቅናቄው ጉድለት ሆኖ የሚታየው አንዱ ጉዳይ ሁለቱን ታላለቅ ክልሎች እወክላለሁ የሚሉ የአማራና ትግራይ ታጋዮች የሌሉበት መሆኑ ነው ። እነ ዶክተር አረጋዊ በርሄንና ግደይን የመሰሉ ሰዎች በስደት ላይ ተደራጅተው እየታገሉ ባሉበት ሁኔታ፣ እነሱን ለማካተት ሳይሞከር ስለሽግግር ማውራት ግር የሚል ጉዳይ ነው ። ሁለቱን የኢህአፖ ድርጅቶችና መኢሶንን ሳያካትቱ ስለ ሽግግር ማውራት ባዶነት ነው ። ብዙ መሠራት የሚገባቸው ጉዳዮች ስላሉና ከጊዜ ጋርም ሻሞ ይዞ ሊሰባሰብ የሚችለውን ሁሉ ማሰባሰብ ስለሚገባ፣ ስለሽግግር ከማውራት ተቆጥቦ ስለህብረትና ቅንጅት ማሰላሰሉ ተገቢ ሆኖ ተሰምቶኛል ።

በመጨረሻም ዶክተር ብርሃኑ የዲፕሎማሲ ሥራን አስመልክቶ የተናገረው እጅግ ግር የሚል ነው ። በራሳችን ሥራና አቅም እንጂ በፈረንጆቹ ላይ መመካት የለብንም የሚለው መልእክት መሰጠት የነበረበት፣ ግንቦት ሰባት ሲጀመር ከዛሬ ሰምንት አመት በፊት እንጂ ዛሬ ሥርአቱ ተገዝግዞ የዲፕሎማሲ ሥራው ከፍተኛ ትኩረት በሚጠይቅበት ወቅት መሆን አልነበረበትም። ይህ ሰው አይወደንም፣ ወይም ጥጋበኛ ነው አብረነው ልንሰራ አንችልም ብለው ተስፋ እንዲቆርጡበት ከማድረግ ውጪ የሚፈይደው ነገር ያለ አይመስለኝም ። በኢትዮጵያ ድህነትና አደጋ፣ ምእራባውያኑን ገሸሽ ማድረግ አይቻልም፣ አስገድደው ነው በጉዳያችን ጣልቃ የሚገቡት፣ በጥንቃቄ መያዝም ይኖርባቸው ይመስለኛል። ቪዲዮውን አዳምጬ እንደጨረስኩ የተሰማኝን ስሜት፣ እንደወረደ ነው ያቀረብኩት፣ እመለስበት ይሆናል።

ቀሪ ንብረታችን ኢትዮጵያችን ናት። ኢትዮጵያችንን እናስብላት አናቁስላት፤ አናድማት፤ አናራቁታት! ~ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

“ቀሪ ንብረታችን ኢትዮጵያችን ናት። ኢትዮጵያችንን እናስብላት አናቁስላት፤ አናድማት፤ አናራቁታት!” ~ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

አንድ ነገር መጥፎም ጥሩም የሚያደርገው ተጠቃሚው ነው:: እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሲፈጥር ኦሪት ዘፍጥረት ስታነብቡ እግዚአብሔር የፈጠረውን በጎ እንደሆነ አየ ይልና ሌላውን ፍጥረት ሲፈጥር ጥሩ ነው ጥሩ ነው እያለ አልፎ ሰውን ሲፈጥር የዛሬውን አያድርገውና እጅግ በጣም ጥሩ አለ ዛሬ መጥቶ ቢያይ ግን እጅግ በጣም መጥፎ የሚል ይመስለኛል በእርግጥ እርሱ እንደኛ አይደለም ተሸካሚ ነውና አይልም።

በእውነት በዚህ ዓለም ላይ መብትና ግዴታ መኖር አለበት ብዬ እላለሁ አሁን የብሔር ብሔረሰቦች መብት የሚለው እሰማለሁ ለመንግስት መጠቆም የምፈልገው ጫፏ ላይ ግዴታ የሚል ቢጨመርና የብሔር ብሔረሰቦች መብትና ግዴታ ቢባል፤ ሁልግዜ የምናገረው አንድ አባባል አለችኝ “ሰው ምንም መብት ከሌለው ባሪያ ነው፤ ምንም ግዴታ ከሌለው ደግሞ የአእምሮ በሽተኛ ነው!” አሁን የአእምሮ በሽተኛ ታውቃላችሁ ሰርግ የሚጠራው የለም ለቅሶ ቀረህ ብሎ የሚወቅሰውም የለም። ምክንያቱም ግዴታ እንዳንለው ግዴታ የለበትም ባሪያ እንዳንለው መብት የለበትም። እኛ ደግሞ የአእምሮ በሽተኞችም አይደለንም ባሪያዎችም አይደለንም። ስለዚህ መብትና ግዴታ አለ ብዬ አምናለሁ። እንግዲህ በፌስቡካችን ምን እንደሚደረግ ከኔ በላይ እናንተ ታውቁታላችሁ ተጠቃሚ አይደለሁም ተጠቃሚ ያልሆንኩት አያስፈልገኝም ብዬ አይደለም መብራት ስለሌለኝ ነው። እናም መብራት ያላችሁ ተጠቀሙበት ግን እኔ አውሮፓና አሜሪካ ስሔድ ከገንቢነቱ ይልቅ አፍራሽነቱ ነው ብዙ የሚታየው፤ አሁን ለፍቶና ደክሞ ያገኘ ሰውና ለፍቶና ደክሞ ያላገኘ ሰው አወጣጡ እኩል አይደለም። ለፍቶ ያላገኘ ሰው ውስኪ ሊያወርድላችሁ ይችላል እንደውም ውስኪ ቤት ሁሉ ሊከፍትላችሁ ይችላል። ግን ሳያስበው ነውና ያወጣው ነገ ተመልሶ ያለቅሳል ፤ እናም መብትና ግዴታውን የሚያውቅ ትውልድ መፍጠር አለብን። ይቅርታን ብንሰብክ፤ ፍቅርን ብንሰብክ፤ ሕዝቡን ብናግባባው፤ ብናደማምጠው፤ እንደው ረሐቡ ሳያንሰው፤ ጥሙ ሳያንሰው፤ ብርዱ ሳያንሰው፤ ድህነቱ ሳያንሰው፤ የቤት ማጣቱ ሳያንሰው፤ ለዘይት ለስኳር ወረፋ መጠበቁ ሳያንሰው፤ እንደው እውነት ለመናገር ተግባብቶ እንኳን ስቆ እንዳያድር አደረግነው ። ድሮ ቆሎ ቆርጥሞ ቡና ጠጥቶ ጨጓራው እየተላጠ እንኳን እፎይ ብሎ ይተኛ ነበር። ዛሬ ከአውሮፓ ከአሜሪካ የሚፈስሱት መረጃዎች የቡና ስኒ የሚያሰብሩ ናቸው ጀበና የሚያሰብሩ ናቸው። እናም በጣም ከባድ ስራ እየተከናወነ ነው።
የ3000 ዓመት ታሪካችን በሙሉ ገድለን የሚያስፎክሩ ናቸው፡፡ አሁን ሬድዮ ቴሌቪዥን ተመልከቱ በዓል ሲመጣ በተለይም እነዚህ የድልና የአሸናፊነት በዓላት ሲከበሩ ሁልጊዜ ምን ያህል እንደተገደለ ምን ያህል እንደቆሰለ እንለፍፋለን፡፡ እስኪ ደግሞ ምን ያህል እንዳቆሰልን መለፍለፉን አቁመን፤ ገድለን መፎከሩን አቁመን። ሁለተኛውን አማራጭ ደግሞ እንሞክረው እስኪ ቆም ብለን ፍቅርን ሰብከን እንሞክረው፤ ይቅር ተባብለን እንሞክረው።

ባለፈው በየክፍለሐገሩ ትንሽ ግጭት ነበር፤ አሁን ግጭቱ ቆሟል ግን ደግሞ ግጭቱን ከሰዎች ጭንቅላት አጥበው የሚጥሉ የሐይማኖት ሰዎች የታሉ? እውነቱን ለመናገር፤ ሕዝቡ ኪሱ እየተራቆተ፤ እየተራበ መኪና የገዛላቸው ካህናት፤ ጳጳሳት፤ ፓስተሮች ፤ ኡላማዎች ምን ያደርጉለታል? …, በአውሮፓ አንድ ጥያቄ እየተነሳ ነው ይባላል ታውቃላችሁ ፈረንጆቹ የእምነት ተቋሞቻቸውን ላይ ምን ስላደረጉልን ነው ገንዘብ የምናዋጣው? ምን ፈጠሩልን? የሞራል ዝቅጠት፤ የስነ ምግባር ዝቅጠት፤ ባዶነትን ነው ያተረፈልን፤ ታንቀን ብንሞት በጭንቀት ብንታመስ ራሳችንን ስናጠፋ አልደረሱልንም የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው። ስለዚህ አየሩን ተራራውን የሚቋቋም መኪና ከተገዛልን መቀሌ ጎንደር ባህርዳር ቆላ ደጋውን እየወረድን በተለይም እንደየ እምነታችን መስበክ አለብን።

ስለዚህ ጥላቻውን ቆም አድርገን በተለይም ፌስቡክ እጃችን ላይ የወደቀ ሰዎች ጠመንጃውን ያገኛችሁ ሰዎች የት እንደምትቶኩሱ ብታውቁ፤ አንዳንድ ጊዜ ራስ መጠበቂያ የሚሰጠው ራሱን ለሚጠብቅ ሰው ነው። ሰውን እየተኮሰ ለሚገድል የራስ መጠበቂያ አይሰጥም እና ፌስቡክን በትክክል መጠቀም ብንችል? ይቅርታ ብንሰብክበት፤ ብልፅግና ብንሰብክበት፤ እድገትን ብንሰብክበት…..

ዛሬ አይደለም በፓለቲካው መስክ የእምነት ተቋማት ራሱ የጦር ሜዳ ሆኗል ስንት እንባ ይፈሳል፤ ስንት ዋይታ ይሰማል ይሄ እንባ ደግሞ ተጠራቅሞ ተጠራቅሞ አገር ጎርፍ ሆኖ ይወስዳል። የደሐ እንባ ተጠራቅሞ ጎርፍ ይሆናል።

የአክአብ መንግስት የተገለበጠው በአንድ ናቡቴ ደም ነው ሌላ ጥይት ተተኩሶ ቦንብ ፈንድቶበት አይደለም። ኃጢአት አየበዛ፤ ወንጀል እየበዛ፤ ግፍ አየበዛ፤ ጭካኔ አየበዛ፤ አረመኔነት እየበዛ በሔደ ቁጥር ሰዎች ባዷቸውን ይቀራሉ። ይሞታሉ፤ የተሾሙ ይሻራሉ፤ ያገኙ ያጣሉ፤ ጤነኞች ይታመማሉ። እንደው ወገኖቼ በዚህ በፌስቡክ የተሰማራችሁ እንደው ሌላው የበሰለ ነገር ለመናገር አይደለም። እንደው አስበን ብንናገር ብንፅፍ፤ እኛ ሐገር ኔትወርክ ውድ ነው ታውቃላችሁ የኛ አገር ሰው ምን ያህል ዋጋ ከፍሎ ጊዜውን ሰውቶ ገንዘቡን ከስክሶ እንደሚያነብላችሁ ማወቅ አለባችሁ። አንድ ቪድዮ ባዳመጠ ቁጥር ቴሌ ላፍ ያደርገዋል ኪሱን ያራቁትበታል። ይሄን መስዋእትነት ከፍሎ ፤ ሻይ አልጠጣም ብሎ እናንተ እያዳመጠ ያለ ነውና ከሻይ የበለጠ ልብ የሚይዝ ነገር አእምሮን የሚያሯቁት ነገር ባትፅፉለት እንደውም ምርጥ ፅሁፍ ካጣችሁ ዝም ብትሉ፤ እውነቴን ነው የሚፃፍ ሲጠፋ እኮ ዝም ይባላል። አንዳንድ ሰው ይገርማችኋል እጁ ላይ ስላለ ብቻ መፃፍ ስለቻለ ብቻ የሚፅፍ ሰው ያጋጥመናል።

እንደው በእግዚአብሔር ስም፤ በአላህ ስምም ካላችሁ በአላህ እንደው በሁሉም ስም በምታመልኩት አምላክ ስም ይሁንባችሁ ፌስቡክ እጃችሁ ላይ የወደቀ ሰዎች እዘኑለት።

እንደው እባካችሁ ገንቡን፤ አንጹን፤ አፋቅሩን፤ ደሙን አድርቁት፤ ጥላቻውን አድርቁት፤ ይቅርታ ይሰበክ፤ ፍቅር ይሰበክ፤ እንግባባ፤ እንደማመጥ፤ አንተላለቅ ማንም የለ ማንም ሊኖር አይችልም። በእውነት ምናልባት ዛሬ የምንነጋገራቸው ንግግሮች የዛሬ 10 እና 15 ዓመት እንደ ፀበል ይፈለጉ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

በቀደም አንድ ወንድማችን አንድ ነገር እየነገረኝ ነበር አንድ ጭፈራ ቤት ገባን አለ፤ አንድ ጥናት ያደርጋልና ሊቀርፅ ነው። እዛ ጭፈራ ውስጥ የሆነ አካባቢ ዘፈን እንዳይዘፈን ተባለ በእውነት ቤቴ ገብቼ አለቀስኩ። ለምን ዘፈኑ ቀረ ብዬ አይደለም እንኳን ቀረ የቀረበት ምክንያት ግን ያሳስበኛል። የታገደበት ምክንያት ያሳስበኛል።

ስለዚህ ወገኖቼ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ አስፈላጊ ነው። ከድጃም ወለተማርያምም ከሳውዲ አረቢያ ተባርረው መጥተዋል። እነ ከድጃ እስላም ስለሆኑ ሳውዲ አረቢያ ይቅሩ አልተባለም ቀሪ ንብረታችን ኢትዮጵያችን ናት። ለወልደማርያም ቀሪ ንብረቱ ኢትዮጵያችን ናት ፤ ለመንግስትም፤ ለደጋፊም፤ ለተቃዋሚም ኢትዮጵያችን ናት። ኢትዮጵያችንን እናስብላት አናቁስላት፤ አናድማት፤ አናራቁታት። መሬቷ ድንግል ነው አስተሳሰባችን ድንግል ነው። ግን መሬቱ ሲለማ እኛ ባዶ ሆነን መሬቱ የሚጠቀምበት አጥቶ ጠላቶቻችን እንዳይጠቀሙበት በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

“በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ላለ ሰው ትንቢት አትናገር !” – ዳንኤል ሽበሽ

ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን፡ 2010 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትራቸው የፕ/ት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለሕ/ተ/ም ያደረጉትን መክፈቻ ንግግር ተከትለው የሰጡትን ማብራሪያ (brief) አዳመጥኩኝ ፡፡ አንድ ሪፖርት የሚቀዳው ከዕቅድ እስከ ድርጊት ካለው ክፍል ውስጥ መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ ካልዋሸን ወይም ካልተሳሳትን በስተቀር ሪፖርት እውነት መሆን አለበት ፡፡ ከዚህ ሀሳብ ስንነሳ አንገት ስላስደፋን የመንግሥታቸው ሪፖርት ለፓርቲያቸው አባላት (ለፓርላማው) አቅርበውታል ፡፡ የማብራሪያቸው ይዘት ለኔ በብዙ ውሸቶችና በጥቂት አጃቢ እውነታዎች የታጨቀ ነበር ፡፡
እጅግ የመሰጠኝ ግን በፖሊስ አባላት ላይ የሰነዘሩት አስተያየት ነው፡፡ በተለይ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል ስለተፈጠረው ቀውስ በተመለከተ በቀውሱ ውስጥ የተሳተፉ የፖሊስ ሠራዊት የአመለካከት ችግር እና ኪራይ ሰብሳቢ ጥገኞች ናቸው በማለት ነበር የገለጹት ፡፡ እኛ ባለን መረጃ ግን የፖሊስ አባላት አፈሙዙን ወደ መንግሥትና መንግሥት ፖለቲካል አቅጣጫ ላይ ማዞራቸውን እንጂ አንዱ ሌላውን ሕዝብ ለማጥቃት አይመስለኝም ፡፡ ክቡርነታቸው (አጎቴ lol) እንዳሉትም ከሆነም ማለቴ ነው፡፡

“ልጅን ለማረም አስቸጋሪ የሚሆነው ችግሩ ከወላጆቻኀው ጋር ሲኖር ነው” እንደሚባለው ሁሉ የፖሊሶቹ ችግር ነው የተባለው ችግርም የሚቀዳው ከተቀረጹበት ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ አለመለካከታቸው መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ በሊብራል አስተሳሰብ ቢቀረጹ ኖሮ ሊብራልና ዴሞክራቲክ ይሆኑ ነበር እንደ ማለት ፡፡ እንደሚታወቀው ፖሊሶቹ (ልዩ ኃይል) ዕድሜ ክልላቸውን ብናይ እንኳ የሩብ ምዕተ ዓመታት ውጤቶች ናቸው፡፡ በኢሠፓ ወይም በኢህአፓ ማላከክ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ፖሊሶቹ ኪራይ ሰብሳቢ፤ ፀረ ዴሞክራቲክ ወዘተ ከሆኑ ተጠያቂው አሳዳጊዉም ጭምር እንጂ ታዳጊዉ ብቻ አለመሆኑ ሊሰመር ይገባል ፡፡ አሳዳጊው የትግራይ ነፃ አውጪ እና የእጁ ሥራው #አዴ ናቸው ፡፡ የአንድ ወንዝ ምንጩ በየጊዜው ድፍርስ ከሆነ ወራጁ ውሃው እንደት ሊጤራ ይችላል ? ውሃው እንዲጠራ ከተፈለገ የግልና የጋራ ጥረት ያስፈልገዋል ፡፡ በሁሉም በኩል ጥረቱም ትግሉም አሁን የተጀመረ ይመስለኛል ፡፡

ፖሊሶቻችን የኛ ናቸው ፡፡ እንደ ማንኛው ሰው ሁሉ ዕኩልነትንና ፍትሐዊነትን ይፈልጋሉ ፡፡ እንደ ዜጋ ፍትህንና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ይናፍቃቸዋል ፡፡ ጥሩ ኑሮ መኖር ይፈልጋሉ ብቻም ሳይሆን ያስፈልጋቸዋልም፡፤ በሰው’ ታቸውም በማዕረጋቸውም መከበርን ይፈልጋሉ ፡፡ ያሠማራቸው ሥርዓቱ ከሕዝብ ጋር ባጣላቸው ቁጥር እንደተጣሉ መኖር አይፈልጉም ፡፡ ማንም ተራ ዜጋ እንደሚረዳው በሀገራችን ለተራ እግረኛ ወታደር ይቅርና ለትላልቆቹ ለባለ መሥመር መኮንኖችም ካለው ክብር ይልቅ ለአንድ ቻይናዊ ጉልበት ሠራተኛ ያለው ክብር ይልቃል ፡፡ ለአንድ ኢንስፔክተር፣ ሱፐርኢንተዳንት፣ ኮሎኔልና ወዘተ ከሚሰጠው ሥፍራ ይልቅ ለተራ ጆሮ-ጠቢ ያለው ታአማኝነት ጎልቶ ይታያል … ፡፡ በኀወሓት ዕዝ ሰንሰለት ሥር ተጠርንፈው የሚተነፍሱበትን አጥተው መኖራቸውን ለማንም ግልጽ ነው ፡፡ ነጋ ጠባ ግምገማ ተብየ አውጫጭን ያረሩ ፖሊስ አባላት’ኮ ሁሌም አንገት ደፍተው ይኖራሉ ማለት ለኔ ይከብደኛል ፡፡ ሰዎች ናቸውና አንድ ቀን <… ግን ለምን?…> ብለው መጠየቃቸው አይቀረ ነው ፡፡

በላይ ላያቸው የተቆለሉትና በድሃው ገበሬ ልጅ ደምና በመሬታቸው ቱጃር የሆኑ ዛሬ ላይ የጨዋታ ህጋቸውን ወደ #ቢሊዮኖች ቤት ከፍ ሲያደርጉ (የሠራዊቱን አዛዦችንም ይጨምራል) እነዚህ ሚስክኖቹ ደሞ የታክሲ ሣንትም ጭምር አጥተውና ተርበው በየመንደሩ ሲያዛጉ እንደት ስለሰላም ሊያወሩ ይቻላል? ግዙፉ ሕገመንግሥት ይቅርና የቅርቡን የአለቃ ትዕዛዝ እንደት ብለው ያከብራሉ?፤ ጠ/ሚሩ እንዳሉት ከሆነም ማለቴ ነው ፡፡ በከባድ ሀዘን ውስጥ ላሌ ሰው ትንቢት አትናገር ይባል የለ!? በከባድ አስተዳደራዊ ጭቆና ውስጥ ያለ ሰራዊት፤ የቤት መክፈያ አጥቶ በየካምፑ የሚከራተት ነው ፡፡ የልፋታቸውን ዋጋ በአንፃራዊነት እንኳ መቅመስ ያልቻለ ሠራዊት ፤ ስለ ሰብዓዊነት እየተሰበከላቸው ግን ሰብዓዊ ክብራቸውን ለተነፈጉ ሠራዊት፤ በቅድሚያ ሕገ መንግሥቱን ለመጠበቅም በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ መብቶቻቸው መጠበቅ ይገባል ባይ ነኝ ፡፡ እንዲያውም የሀገራችን ፖሊሶች በባሕልና በሃይማኖት ተፅዕኖ ውስጥ ያደጉና የኖሩ መሆኑ በጀን እንጂ፤ በሥርዓቱ ከሚደርሰባቸው በደል ልክ ቢሆን ኖሮ ምን ሊመፈጠር እንደምችል መገመት አያቅትም ፡፡

በደርግ ጊዜ ከነበረው ከኢት/ያ ሠራዊትም እንዳየነው ከሆነ፤ ቢቸገር ቢቸገር እንኳ መሣሪያ ቢሸጥ ወይም ቢለምን እንጂ መሣሪያውንና ሙያውን ተጠቅመው በእኩይ ተግባር ላይ የማይሳተፍ ነው ፡፡ ይህ ከኢት/ዊ ጨዋነት፣ ከአስተዳደጋቸውና ከግላዊ ባሕርያቸው የሚመነጭ እንጂ ከሙሰኛው፤ ከጨቋኙ፤ ከዘረኛው እና እንዲተኩሱት ከሚያዘው ኃይል አስተሳሰብ የሚመነጭ አይደለም ፡፡ በርግጥ ከሠራዊቱ በኩል ወደ ሕዝቡ ይተኮስ የነበረው ጥይት ለምንና እንደት እንደሆነም አይጠፋብንም ፡፡ ከዚህ በኀላ ግን ሕዝቡም የሠራዊቱ፤ ሠራዊቱም የሕዝቡ ነው !!
በ2005 ዓም በአንዱ ጹሁፌ ላይ ርዕስም ትኩረትም ያደረኩት <ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊቱ ማን አለላቸው?> የሚል ነበር ፡፡

የጠ/ሚ ኃ/ማርም ንግግር የሀገራችንን ነባራዊና ወቅታውዊ ሐቁን ያላገናዘቤ፤ እውነታውን በደንብ ያልዳሰሰ ነበር ፡፡ ሰላም !!

ሀገራዊ የጸሎትና ምህላ ጥሪ

ምሕረት ዘገዬ

የሀገራችን ጉዳይ ከድጥ ወደ ማጥም አልፎ ልንገልጸው ቃል ያጣንለት የመቅሰፍቶች ሁሉ ትንግርታዊ ትዕይንት ሆኖኣል፡፡ አንዱ ቀን አልፎ ሌላው ሲተካ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት ሄዶ ዜጎች በቋሚነት ወላፈኑ በማይበርድ ምድጃ ላይ ተጥደው እንዲቃጠሉ ተፈርዶባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የምናደርገው ጠፍቶን ብዙዎቻችን በሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ላይ ክፉኛ ተጨንቀን ተጠበናል፡፡ የዚህች ታሪካዊ ሀገር መጥፋት የሚያስደስታቸው ካልሆነ በስተቀር ጤናማ ለሆነ የዓለም ዜጋ ለኛ ለኢትዮጵያውያን የተደገሰልን መከራ እጅግ ዘግናኝ ነው፡፡ በዚህን ወቅት ሀገር አማን ብሎ የሚተኛ፤ ከዚያም ባለፈ በእህል ውኃ ስካርና ጥጋብ ጮቤ የሚረግጥ ካለ ዓለም ብታልፍ የማያሳስበው ግዴለሽ እንጂ የሚያስብ አንጎል ባለቤት የሆነ ጤናማ ሰው አይደለም፡፡

ዘመናችን በጥቅሉ የጭንቀትና የጥበት መሆኑ ከዓለም አቀፍ አስከፊና አሳዛኝ ክስተቶች በመነሳት በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ የኛ ግን ከሁሉም የባሰ ነው፡፡ ሕንጻ በቦምብ ናዳ ስላልፈረሰ ብቻ ሀገር አማን ነው አይባልም፤ ሰው በመንፈስና በአካል እየፈረሰ ነው፡፡

ጭራሹን ማሰብ የተሳነው የሕወሓት መንግሥት የሚሠራውን አጥቶ በዕብደት ጎዳና እየተመመ ነው፡፡  ወያኔዎች ተስፋ በመቁረጣቸው ሳይሆን አይቀርም የሚሠሩት የክፋት ሥራ ሁሉ ቅጥአምባሩ ጠፍቷል፤ በዓለም ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ዕኩይ ተግባራቸው የዞረ ድምር ያለው መሆኑን በፍጹ ዘንግተዋል፡፡ የጥጋብ  ሞራ ኅሊናቸውን ስለሸፈነው፣ የቂመኝነት አባዜ ልባቸውን ስለደፈነው፣ የዘረኝነት ዝልል አእምሯቸውን ስላሰከረው፣ ለትግራይና ሕዝቧ ቀርቶ ለራሳቸው ነፍስና ለልጆቻቸውና ለልጅልቻቸው የወደፊት ዕጣም ማሰብ አልቻሉም፤ ማሸነፍ ብርቁ የሆነ ሰው ሲያሸንፍ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ትንሽ ሰው – በአስተሳሰብ ማለቴ ነው  – አያሸንፋችሁ፡፡ እነዚህ ከውሻ የማይሻሉ ወያኔዎች የኛን የኢትዮጵያውያንን ብቻ ሣይሆን የሰውን ዘር በሞላ ድብቅ ገመናውን አጋልጠው አወጡት፡፡ እንዲህ ያለ የፈሪ ጭካኔ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡( ከውሻ አለመሻላቸው – ውሻ ሲሸነፍ ተሸናፊው በጀርባው ይተኛና ላሸናፊው ሀፍረቱን ገልጦ ያሳያዋል አሉ፡፡ ያኔ አሸናፊው ማሸነፉን ተረድቶ ማጥቃቱን ያቆማል፡፡ ወያኔ ግን የቆመን ይቅርና የሞተ በድንንና የተቀበረ ዐፅምን በእውኑም በምናቡም እየተፋለመና ራሱ በፈጠረው ጠባብ የስቃይ ዓለም ውስጥ እንዳሣማ  እየተንደባለለ የሚኖር የሰው ልጅ ማፈሪያ ፍጥረት ነው፡፡  ዕድገትና ለውጥ በወያኔ መንደር አይታወቁም፡፡ ከሚያደርሱት ጥፋትና ውድመት አኳያ እንዲህ ማለት የሚቻል አይሆንም እንጂ ወያኔዎች እንደተወለዱ ሞቱ ቢባሉ ያስኬዳል፡፡ ሰው መቼም ሰው ነውና ከዕድሜም ሆነ ከትምህርትና ከተሞክሮ እየተማረ ሕይወቱን አስተካክሎ ይመራል፡፡ እነሱ ግን ከመነሻው አስተዳደግ በድሏቸዋልና – ብዙዎቹ የባንዳ ልጆች እንደመሆናቸው የትውልድ እርግማንም አለባቸውና – አንዴውኑ እንደተጣመሙ በጊዜ ሂደት ሊለወጡ አልቻሉም፡፡ በልጅነት የወረሳቸው የዘረኝነት ልምሻ ሳያስቀብር የሚለቃቸው አልሆነም፡፡ አንድ ሰው ደግሞ በአሥራዎቹ ዕድሜውም በሰማንያዎቹም አንድ ዓይነት ስብዕና ካለው ይህ ዓይነቱ ሰው ከድንጋይ የሚያንስ ግዑዝ ፍጡር እንጂ ሰው ሊባል አይገባውም፡፡ እነአቦይ ስብሃት ነጋና አባይ ፀሐዬ እንግዲህ የጥፋት ፊታውራዎች የሆኑ የእንጨት ሽበቶች ናቸው፡፡ ለመሸበት ለመሸበት ድንጋይና እንጨትም ይሸብታሉና እነኚህን መሰል ዜጎች ሳይፈጠሩ እንደጨነገፉ ቢቆጠር ስህተት የለውም፡፡ ሌሎቻችን ግን ከነዚህ ውሾች መማር አለብን፡፡

 

የነናቡከደነፆርና የነፈርዖን አረመኔያዊ አገዛዝ ከነዚህ ወያኔዎች በእጅጉ የተሻለ ነው፡፡ እኚያ የጥንት ጨካኞች በእስር ቤት ያዋሉትን ሰው ከፈረዱበት ወይም በፍርድ ሂደት ካዋሉት በኋላ እየደበደቡ እንደማይገድሉት መገመት ይቻላል፡፡ እነዚህ ጉዶች ግን በህግ ጠለላ ሥር ያለን ሰው በእርግጫ ደረት ደረቱን እያሉ ይገድላሉ፡፡ ሰሞኑን በርካታ እስረኞች በዚህ መልክ እየሞቱ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ በውነቱ ወያዎችን ሳስብ ስም አጣላቸዋለሁ፡፡ አመክሮና ምሕረት በሌለው ሁኔታ ተከፍሎ ሊያልቅ ባልቻለው የኋጢኣታችን ውጤት ቅጣትና በጌታ የቁጣ ክምርም አምርሬ አዝናለሁ፡፡ ኧረ አሁንስ በቃችሁ ይበለን! 43 ዓመት???

 

የወያኔዎች ወንጀል የሚከፋው ወንጀል ይፈለስፉና ለሚጠሉት ሰው ያስታቅፋሉ፡፡ “የምትሉትን አላደረግሁም” ሲባሉ እነዚህ የሌባ ዐይነ ደረቆች ንጹሑን ሰው ያልሠራውን ወንጀል እንዲያምንና እንዲፈርምበት ያስገድዳሉ፡፡  በዚህ መልክ እስር የገባን ሰው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ወህኒ ቤት ውስጥ እያለ በእሳት አቃጥለው እንዲሞት ያደርጋሉ፡፡ እራሳቸው እሳት ለኩሰው ባቃጠሉት ወህኒ ቤት ውስጥ የገደሉትን ይገድሉና በሕይወት የተረፈውንና ከእሳት ሊያመልጥ የሚንፈራገጠውን እስረኛ  “ ከወህኒ ሊያመልጥ ሲል ተገደለ” ብለው ያላግጡበታል፡፡ ሊያመልጥ ያልሞከረውንና ለጥይታቸው ሰለባ መሆን ያልፈለገውን ደግሞ በእሳት ለኳሽነት በክስ ላይ ሌላ ክስ መሥርተው ያንገላቱታል፡፡ ለክስም ለሽሽትም ያልተንበከረከከውን የኅሊናና የአካል እስረኛ በእርግጫና በጥፊ በቦክስና በካልቾ እያዳፉ ለሞት ይዳርጉታል፡፡ ወያኔዎች እንደዚህ ናቸው፡፡ ከዚህም ባፈ ሊነገር የማይችል ኢሞራላዊና ኢሃይማኖታዊ የሰይጣን ድርጊት በካቴና በታሰረ ዜጋ ላይ ይፈጽሙበታል፡፡ በበደል ጽዋቸው ውስጥ እያከማቹት ያለውን የግፍ ቁልል ስናይ መቼ ከፍለው እንደሚጨርሱት ይገርመናል፡፡ የፈረደበት ትውልድ ግን ከዕዳው አያመልጥም! ወዮ ለቀኑ በሉ፤ ቀኑ ሲደርስ በደረቅ አበሳ እርጥብ መቃጠሉ የማይጠበቅ ሳይሆን የታሪክ ፍርጃ ነው፡፡ አየና!

 

ተጋሩ ወንድምና እህቶቼ እባካችሁን ከነዚህ የእፉኝት ልጆች ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ፈጣሪ ይህን ሁሉ “ዕድል” ለነዚህ ክፉዎች የሰጠበት አንዳች ምክንያት ቢኖረው ነው፡፡ አለነገር እነዚህ ሰዎች በዚህች ታሪካዊ ሀገር አልሰለጠኑም፡፡ የምናካክሰው ያለፈ በደልና ክፉ ሥራ ቢኖር ነው ለነዚህ የመርገምት ውሉዳን አሳልፎ የሰጠን፡፡ ራሳችንንና ታሪክን እንመርምር፡፡

በቅርብ የሰማሁትን አንድ ቀልድ መሰል እውነት ጣል ላድርግና ወደ ዋናው ጭብጥ ገብቼ ልሰናበት፡፡ ትግሬ ፌዴራሎች አንድን  ወጣት ይዘው ይቀጠቅጡታል አሉ፡፡  እየቀጠቀጡት ሳለ በኪሱ ያለው የሞባይል ስልክ ይጮሃል፡፡ ቀጥቃጩ ፌዴራልም አውጥቶ እንዲያናግር ቀጭን ትዛዝ ያስተላልፍለታል፡፡  በስልኩ ጩኸት ከድብደባው እፎይታ ያገኘው ወጣት ስልኩን እያወጣ ሳለ ፌዴራሉ ስልኩን “ላውድ ላይ ግበሮ” ይለዋል፡፡ ልጁም በታዘዘው መሠረት “ላውድ” ላይ አድርጎ መቀበያ ቁልፉን ይጫናል፡፡ በወዲኛው ጫፍ ያለው ደዋይ “ቧይ ስለምንድንው እንዴ ቶሎ እማታነሳው – ገብረ እግዚአብሔር አይደለህም እንዴ?” ሲል ያምቧርቃል፡፡ ይሄኔ ያ ወጣት “እሱን ብሆንማ በማን ዕድሌ!” ብሎ በቁጭት ይናገራል፡፡ ይታያችሁ – ኢትዮጵያን ማን ወደ እንጦርጦስ እያወረዳት እንደሆነ ልብ በሉ፡፡ ያስጠይቃል፡፡ በእግረ መንገድ – ትዝ ስላለኝ ነውና ይቺን ደግሞ ላልሰማችሁ ልመርቃችሁ፤ “አንዱ ኑሮ እንዴት ነው?” ብሎ ይጠይቀዋል አሉ፡፡ ሲመልስ “ከላይ እግዚአብሔር፤ ከታች ገብረ እግዚአብሔር ሳሉ ምን እሆን ብለህ” በማለት በውስጠ ወይራ  እንደዋዛ ቅኔ አዘል ብሶቱን ጣል ያደርግለታል፡፡ ብዙ ነገር አለ፤ ብዙ ጉድ ይወጣል፡፡

 

እኛ የገዛ ነፃነታችንን ለማምጣት የታደልን አንመስልም፡፡ አንድ ነን ስንል ከሁለት በላይ እንሆናለን፡፡ ዕንቆቅልሽ ፖለቲካ ውስጥ ገብተን እየዳከርን ነን፡፡ የተጣለብን አንደርብ እንዲህ በቀላሉ የሚለቀን አልሆነም፡፡ የተቃውሞው ጎራም እርስ በርሱ ለመራኮት የሚያውለው አጠቃላይ በጀት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሣ አሁን ወያኔ ቢወድቅ እንኳን ለሀገር የሚያውለው አቅም የሚኖረው አይመስልም፡፡ የኢትዮጵያውያን ባሕርይ በዚህ ዘመን ክፉኛ ተለዋውጧል፡፡ መጨረሻችንን ያሳምርልን እንጂ የገባንበት አዘቅት ቀላል አይደለም፡፡ አያ ሞትም፣ አያ ዕድሜም የየበኩላቸውን ድርሻ እየሞጨለፉ ደህና ደህና ሰዎችን እያሳጡን ነው፡፡ ይህ ሞት የሚሉት ወያኔን የሚጠየፍ ጉድ የኪነ ጥበብ መንደራችንንም በየሰዓቱ እየጎበኘ ያም መንደር ባድማ ሊሆን ነው፡፡ ጉዳችን ፈላ!!

 

ኑሯችን ከቀን ቀን እየዘቀጠ በተለይ በዚህን ሰሞን የወያኔው ብር የመግዛት አቅም ወደ ዚምባብዌና ሶማሊያ ደረጃ እየወረደ ነው፡፡ አንድ ኩንታል ጤፍ 3 ሽህ ብርን እየረገጠ ነው – “እየረገጠ ነው” በምልባት በዚህች ቅጽበት ራሱ ከመርገጥም አልፎ ወደ ላይ ሊሽቀነጠር ይችላል፡፡ መንግሥትም ህግም በሌለበት ሁኔታ ነፍሳችን ውሎ የሚያድረው በኪነ ጥበቡና በተዓምር እንጂ በማኅረሰብኣዊ የኑባሬ ቀመር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንደኛውና ዋናው  መንግሥትና ህግ በሌለበትና ሙስና የደም ዝውውር ዋና ሞተር በሆነበት በዚህ አደገኛ ዘመን በተለይ እኛ ጭቁን ደሞዝተኞች ውለን ማደራችን ነው፡፡ የኢኮኖሚው መላሸቅ፣ የህግና የሥርዓት መጥፋት፣ የሞራልና የባልህ መበረዝ … የዘመናችን መታወቂያ እንደመሆናው ዜጎች ከቤት ወጥተው ቢያንስ ብዙዎቹ ወደ ቤታቸው – ቤት ያላቸው ማለቴ ነው – መግባታቸው አንዳች መለኮታዊ ጥበቃ ያለን መሆኑን ብናምን ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አልተሳሳትንም፡፡ በተረፈ አያድርግብህ እንጂ መሀል አዲስ አበባ ላይ አንድ ጥጋበኛ በጥይትም ይሁን በእርግጫ ደፍቶህ ቢሄድ ጠያቂ የለውም –  ጠያቂ ኖሮ የደፋህ ሰው ቢታሰር ገንዘብ ወይም ሰው ካለው በሰዓታት ውስጥ ተፈትቶ እንደልቡ ሲፏልል ልታየው ትችላለህ፡፡ ቤትህን ወይ ንብረትህን ካስፈለገም ሚስትህንና ሴት ልጅህን ወያኔ ከፈለገ ዐዋጅ ማርቀቅና በነጋሪት ጋዜጣ ማውጣት ሳያሻው በፌዴራል ተብዬውና በአጋዚ ወታደር ገቢ ሊያደርግህ ሕወሓታዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንንም ታሪክ መዝግቦ ይዞታል፡፡ እነዚህ ቅሌታም ወያኔዎች ያላስመዘገቡት የገማ ታሪክ የለም፡፡ ያድርሰን፡፡

 

ወደ ዋናው መልእክቴ ገባሁ፡፡ በውጭም በሀገርም ውስጥ ያላችሁ ክርስቲያኖችም ሆናችሁ ሙስሊሞች ከልባችሁ ሆናችሁ ወደየምታመልኩበት አምላካችሁ ጸልዩ፡፡ በላ እየመጣብን ነው፡፡ ይህን በላ ሊመክትልን የሚችለው፣ ይህን መቅሰፍት ሊያበርድልን  ሥልጣን ያለው ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ እንደሰው ምኖትና መፍጨርጨር ቢሆን ኖሮ ብዙዎች ለዚህች ሀገር ደማቸውን አፍስሰውና ምትክ የሌለውን ቤተሰባቸውን የትም በትነው ትልቁን መስዋዕትነት በመክፈል ዘብጥያ ወርደው ነበር፡፡ ግን ያለ ፈጣሪ ፈቃድ የሚሆን ነገር የለምና ነገራችን ሁሉ የእምቧይ ካብ እየሆነ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተሸጋገርን እንገኛለን – በብርሃን ፍጥነት፡፡

 

“የጨው ተራራ ሲናድ፣ ሞኝ ይስቅ ብልኅ ያለቅስ” ይባላል፡፡ እየታዘብነው የምንገኘው ጉዳይ ይህን ይመስላል፡፡ ሀገር በጠራራ ፀሐይ እየፈረሰች ሳለ ዜጎች በፀጥታ ማለፍን መርጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን በሕይወት ያለች የሚመስላቸው የዋሃንም በርካታ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ሕይወት ውትር ውትር ስላለች ሀገር ሰላም የሚመስላቸው ገራገሮች ሞልተዋል፡፡ ግን ግን ሁኔታውን በጥሞና ላጤነ “የፋሲካው በግ በገናው በግ ይስቃል” እንዲሉ ነው፡፡ ሩዋንዳና ሦርያ፣ ሊቢያና ኢራቅ ወደ ኢትዮጵያ እምብርት ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ ላይ እያሉ በሰላም ተኝቶ እንቅልፉን የሚደቃ ካለ ጅል ነው፡፡ “እኔም በአንድ ቀን አልተቆረጥኩም” ብላታለች አሉ እጇን ማሳከክ እንደጀመራት ሕጻን ልጇ የነገረቻት አንዲት የሌፕረሲ አካል ጉዳተኛ፡፡ የኛም ነገር እንደዚሁ ነው፡፡ የወያኔዎችና ጌቶቻቸው ፍላጎት ይሄውና ይሄው ብቻ ቢሆንም ፈጣሪ ግን የእስካሁኑን ቆጥሮልን እንዲምረን መጸለይ አለብን፡፡ ብርቱ ጸሎት እናድርግ፡፡ ሰይጣኑ ሙሉ በሙሉ ከጠርሙሱ ከወጣ አንችለውም፡፡ የወያኔው ጌቶች በሰዓታት ውስጥ ዜጎቻቸውን ከኢትዮጵያ በተለይም ከመናገሻዋ ከሸገር ሊያወጡ ይችላሉ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞችና የንግድ እንዲሁም የፖለቲካ ተቋማትን በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር የተቆጣጠሩት የወያኔ ጭፍሮች ግን ማንም ወደየትም አይሰዳቸውም፡፡ ቀኑ ሲደርስና ፊሽካው ሲነፋ  እዚሁ መተላለቅ ነው፡፡ ክፉን በሩቅ ያድርግልን እንጂ ጥቂቶቻችን በሦስተኛው ዐይናችን እያየን ያለው  የመከራ ዶፍ ብዙ የመኸር ወቅት እንደሚጠይቅና ብዙዎችን እንደሚያረትም ግልጽ ነው፡፡ ወያኔዎች ከመነሻቸው ጀምሮ በተለይ በአማራና ለአማራ ራሮት ባለው ወገን ላይ ሁሉ – በለዘብተኛ ትግሬም ላይ ሳይቀር – የፈጸሙትን ግፍና በደል ላስተዋለ መጪው ዘመን ለወያኔ ምን ይዞ እንደሚመጣ ለመተንበይ ሁሴን ጅብሪልን ወይም ኖስትራዳመስን መሆን አይጠይቅም – ጡት የሚጠባ ሕጻንም በግልጽ ይታየዋል፡፡ (መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማይ ቀርባለችና ንስሃ ግቡ!” ይል ነበር፡፡ ጤናማ ትግሬዎች ወንድሞቻችንን ምከሩ – ጊዜ ካላቸው!)

 

ስለዚህ እባካችሁ ሌት ከቀን እንጸልይ፡፡ እዚህ በሀገር ቤት ቤተ ክህነቱም ቤተ እስልምናውም በወያኔ ስለተያዘ ከዘወትር ጸሎት ውጭ የተለዬ ምህላና እግዚኦታ መያዝ አይፈቀድም፡፡ ቤተ ክህነቱን በተለይ ከአቡነ ዘበሰማያት ያለፈ ዕውቀት የሌላቸው ወያኔ  ጳጳሣትና ቀሳውስት እንደተምችና አንበጣ ወርረው ይዘውታል፤ ደህና ካህናት ቢኖሩ እንኳን የሚናገሩትንና የሚሰብኩትን ከእግር እግር እየተከታተሉ የሰላምና የዕርቅ ነገር እንዳያነሱ በጥብቅ ያስጠነቅቋቸዋል፤ ሲፈልጉ ከሥራ አባርረው ለማኝ ያደርጓቸዋል፤ ከዚህም ባለፈ ለእስርና ለግድያም ይዳርጓቸዋል – ሰይጣን በአካል ተከስቶ ቤተ ክርስቲያንን እያስተዳደረ እንደሆነ ማመን ይቻላል፡፡ የፊጥኝ ነው የታሰርነው ወገኖች፡፡ የዛሬ ወመኔ ቄስና ጳጳስ እንኳንስ አለባበሳቸውን ከማሳመር ባለፈ  “ግብረ ድንግል”ንና “የዐቢ ክብራን” “በስማም”ንና “ነአኩተከ”ን እንኳን በቅጡ አይዘልቁም፡፡ ወያኔ ከጅማሮው ኦርቶዶክስንና ያንን የፈረደበትን ሕዝብ  ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እንደመነሳቱ ምኞትና ህልሙ ተሳክቶለት ዛሬ ኦርቶዶክስም ሞታለች፤ አማራውም አብዛኛው የተሰናዳለትን የጥፋት ድግስ ባለመረዳቱ አልነቃም – እያንጎላጀ እንደተኛ አለ፤ ዐውቆ የተኛን መቀስቀስ ደግሞ  አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን አድካሚም ነው፡፡ ከነቃና ለመብቱ ከተነሳ ግን ጉንዳንም ሱሪን ታስወልቃለችና እነዚህ ወያኔዎች መግቢያ የሚኖራቸው አይመስለኝም –  የማይቀርን ነገር ማስታወሴ እንጂ ወያን ለማስፈራራት መሞከሬ አይደለም፤ ግዑዝ አይፈራም፤ ኅሊናው በጥጋብ ሞራ የተጋረደበትም እንዲሁ፡፡ የትግራይ ሕዝብ ግን ከወንድሞቹ ከአማሮች ጋር ያለውን ታሪካዊ ትስስር ማጥበቅና  ነግ በኔን መገንዘብ ይኖርበታል – ዛሬ ትናንትን እንዳልሆነ ሁሉ ነገንም በዛሬነት መጠበቅ የዋህነት ነው – ሁሌ ፋሲካ የለም ጋሽዬ፡፡ አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ይህ የሎሚ ተራ ተራ ነገር ሰው ሰራሽ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ነውና ዛሬን ከትናንትናና ከነገ ጋር በማነጻጸር ሁሉም ቀልብ መግዛት ያለበት መሆኑን ነው፡፡ ትምክህትም እንበለው ትዕቢትና ዕብሪት ማንንም ለዘለቄታው አይጠቅምም፡፡ ከልብ መሆንና ማስተዋል ግን ዘላለማዊ የሆነ የማያስወቅ ስብዕናን ያላብሳል፡፡ የተገኘን ዕድል በጥበብ መጠቀም በታሪክ ያስወድሳል፤ በተቃራኒው ደግሞ የተገኘን ዕድል አልባሌ ማባከን በታሪክ ማኅደር ሊለቅ የማይችል ጥላሸትን ይቀባል፡፡ ለዛሬ ጥቅምና ፍላጎት ብለን ነገን መግደል የራስን ትውልድም እንደመግደል ይቆጠራል፡፡ ልጆቻችን አንገታቸውን ደፍተው እንዲሄዱ ሳይሆን ኮራ ብለው እንዲራመዱ የማያሣፍር ታሪክ ልንተውላቸው ይገባናል፡፡ ምርጫውን ለልባሞች ልስጥና በ“ቻው” ልሰናበት፡፡ ቸር ያሰማን፤ መልካም ክራሞት፡፡ የትናንቱን የአምቦን ጨምሮ በየቦታው ወያኔ የሚጨፈጭፋቸውን ልጆቻችንን ነፍስ ይማር፡፡     mz23602@gmail.com

በዓቃቤ ህግ ማስረጃ ላይ የቀረበ የኮ/ል ደመቀ መቃወሚያ

ከጌታቸው ሽፈራው

“እኔ የተከሰስኩት ለምን አማራ ማንነት አቀረብክ ተብዬ ነው……………እኔ እንድከሰስ ምክንያት የሆነው በህገ ወጥ መንገድ በግዴታ የተነጠቀው የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለመንግስት ለማቅረብ በህዝብ ተመርጨ የማንነት ጥያቄውን በህጋዊ መንገድ በህገ መንግስቱ መሰረት ይመለከተዋል ለተባለ የመንግስት አካል ሁሉ ሳቀርብ ጥያቄውን ለማፈን ሲባል ከመኖርያ ቤቴ በሌሊት ተከብቤ ጥቃት ሊፈፀምብኝ ሲል ራሴን በመከላከሌ ነው” ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ

ለአማራ ብሔራዊ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት

ጎንደር

(ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ከጎንደር ማረሚያ ቤት)

ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች በሶስት ዘርፍ የሚከፈሉ ናቸው። እነሱም 1) ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ስልክ በመጥለፍ ተገኘ የተባለ ሪፖርት፣ 2) በአማራ ክልል ወደሙ የተባሉ ንብረቶች ዝርዝር እና ግምታቸውን የሚገልፅ ሪፖርት፣ 3) ምስክሮች በፖሊስ ሰጡት የተባለ ምስክርነት ሲሆን ምስክሮቹ በመሞታቸው የሰው ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ በማስረጃነት የቀረበ ሰነድ ነው። እነዚህን ሰነዶች እንደቅደም ተከተላቸው በሚመለከተው ዝርዝር የህግ መስፈርት ተቃውሞዬን አቀርባለሁ።

1) ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተገኘ የተባለ ሰነድ:_ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከስልክ ምልልስ ያገኘሁት ነው በሚል በእኔ እና በዚህ ክስ ውስጥ በሌሉ ሰዎች ላይ ሰፋ ያለ ሪፖርት አቅርቧል። ይሁን እንጅ ከእኔ በተቃራኒ ወገን የስልክ ንግግር አደረጉ የተባሉ ሰዎች ስልክ ቁጥር አለመጠቀሱና የድምፅ ማስረጃ አለመቅረቡ ሪፖርቱ ከስልክ ግንኙነት ያልተገኘ መሆኑን የሚያስረዳ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የማንም ሰው የግል ሕይወት በማንኛውም መልኩ በ3ኛ ወገን ጣልቃ ሊገባበት እንደማይችል በህገ መንግስቱ አንቀፅ 26 ከመደንገጉም በተጨማሪ በዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀፅ 17(1) እና (2) ስምምነት ተደርጎበታል።

የማንኛውም ሰው የግል ማንነት ወይም የቤተሰቡ ወይም የመኖርያ ቤቱ ወይንም በማንኛውም መልኩ የሚያስተላልፈው መልዕክት ( የሚያደርገው ግንኙነት) በዘፈቀደ ወይንም በህገ ወጥ መንገድ ጣልቃ አይገባበትም። ግላዊ ክብሩ አይደፈርም በሚል ተደንግጓል። ይህም የስልክ፣ የፖስታ እና ሌሎች ጠለፋዎችን የሚከለክል መሆኑን በግልፅ ያስረዳል። በተከታዩ ንዑስ ቁጥር ደግሞ መንግስት የተጣለበትን ግዴታ ይገልፃል።

ማንኛውም ሰው ከላይ የተጠቀሰው ጣልቃገብነት እንዳይፈፀምበት የህግ ጥበቃ ይደረግለታል። በማለት የመንግስትን ግዴታ የሚገልፅ ሲሆን በእኔ ላይ የተፈፀመው ግን ተቀራኒው ነው። ምክንያቱ ደግሞ መንግስት በግለሰቦች የግል ሚስጥር ውስጥ ገብቶ የቤተሰብ ሚስጥር ሲበረብር የነበር ስለመሆኑ ማስረጃውን ራሱ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተፈፃሚ እንዲሆኑ ይልቁንም ህገ መንግስቱ ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር ተጣጥሞ መተርጎም እንደሚገባው በአንቀፅ 13(2) ላይ አረጋግጣለች። በዚህም መሰረት በብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ተገኘ የተባለው ሪፖርት በራሱ እውነት ባይኖረውም እውነት ቢሆን ኖሮ እንኳን የግል ነፃነታችንን በመድፈር የተገኘ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።

2) በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 26(1) እና (2) የማንኛውም ሰው የግል ህይወት ማለትም ህይወቱ፣ ንብረቱ እና በማንኛውም የመገናኛ ዘዴ የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሊደፈሩ የማይገባ መሆኑን በአስገዳጅነት ከአረጋገጠ በኋላ በንዑስ ቁጥር 3 ላይ ደግሞ ለህዝብ ደህንነት ሲባል አገልግሎቱ ሊገደብ እንደሚችል ብቻ ይደነግጋል። ዐቃቤ ህግ በዚህ ክስ ያቀረበው ማስረጃ ግን ይህን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ የግል ህይወቴን የደህንነት ባለስልጣኖች ሲበረብሩት እንደነበር በመግለፅ ነው።

የስልክ፣ የፋክስ ወይንም ሌላው የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት በህዝብ ሰላምና ደህንነት ላይ አደጋ የሚያደርስ መስሎ በሚታይ ጊዜ አገልግሎቱን ማቋረጥ ወይንም መገደብ እንጅ የሰውን የግል ህይወት ገብቶ የግል ሚስጥራቸውን እንዲከታተል በህገ መንግስቱ አልተፈቀደም።
ይልቁንም የመንግስት ባለስልጣናት የማንኛውም የግል ህይወት እንዳይደፈር የመጠበቅ ግዴታ የተጣለባቸው መሆኑን በአስገዳጅነት ያረጋግጣል። በሌላ በኩል እኔ የተከሰስኩት ለምን የአማራ ማንነት አቀረብክ በሚል ብቻ ስለሆነ ከአሸባሪ ጋር ይገናኛል ተብሎ አስቀድሞ የተደረገ ክትትል አለመኖሩን ተገናኘህ የተባልኳቸው ስልክ ቁጥሮች አለመገለፃቸው ብቻ ሰነዱ በቅንብር እኔ ከታሰርኩ በኋላ የተዘጋጀ መሆኑን ከማስረዳቱ በተጨማሪ በስልክ ተገናኝታችኋል የተባሉት ሰዎች የግንቦት 7 አባል ስለመሆናቸው ሆነ አሸባሪ ስለመሆናቸው የቀረበ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ከአሸባሪ ጋር ተገናኝተሃል አያሰኝም።

በተደጋጋሚ የሚጠቀሱት እነ ሰረበ ጥሩነህ እና ደጀኔ ማሩ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ከመሰረቱ ስለመፈጠራቸውም አላውቃቸውም። እንደዚህ የሚባሉ ሰዎች ካሉም በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ወይም የአሸባሪ ቡድን አባል ይሁኑ አይሁኑ የማላውቅ ከመሆኑም በተጨማሪ በሪፖርቱ የተጠቀሱትን ስዎች ስለመሆናቸው ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ እኔን ከአሸባሪ ቡድን ጋር ተገናኝቷል ለማሰኘት የሚያስችል ብቃት የለውም።

3) በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁቁጥር 652/2001 አንቀፅ 14 ህገ መንግስቱን በግልፅ በሚቃረን ሁኔታ የተደነገገ ቢሆንም ቢያንስ የግለሰቦችን የግል ሚስጥር የመበርበሩ ስራ ሊከናወን የሚችለው ግን ፍርድ ቤት በውሳኔ ሲፈቅድ ነው። ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ከስልክ ጠለፋ ተገኘ የተባለው ማስረጃ ህገ መንግስቱንም ሆነ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን የሚቃረን ስለሆነ ከህግ ውጭ የተገኘ ማስረጃ የወንጀል ተግባር ማስረጃ መሆን እንደማይችል በህገ መንግስቱ በግልፅ ተመልክቷል። በዚህም መሰረት የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት መ/ ቤት ተገኘ የተባለው የሪፖርት ማስረጃ ህገ መንግስቱንም ሆነ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን በመጣስ በሌለ ነገር ላይ የተዘጋጀ በመሆኑ ተቀባይነት የሌውም እንዲባል እጠይቃለሁ።

4) ከብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት የቀረበ ሪፖርት ታማኝነቱን በተመለከተ:_ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 23 ላይ የብሔራዊ መረጃ እና ደህነት አገልግሎት ፅ/ ቤት የሚያቀርበው ሪፖርት ታማኝ ማስረጃ ነው ተብሎ ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለው ነፃ ዳኝነት ተቋም ተቋቁሟል ተብሎ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 78 የተደነገገውን እና በአንቀፅ 79 ደግሞ ዳኞች ከማንኛውም አካል ትዕዛዝ ነፃ ሆነው ይሰራሉ ተብሎ የተደነገገውን በግልፅ የሚጥስ ነው። ከነፃ ዳኝነት አንዱ እና የመጀመሪያው ዳኞች በችሎት ጠይቀው የተረዱትን እና የማስረጃ ምንጮችን ከስር መሰረቱ አይተው የተከራካሪ ወገኖችን ማስረጃዎች በእኩልነት መዝነው መወሰን ከቻሉ ብቻ ነው። በተጠቀሰው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀፅ 23 መግቢያ ላይ ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዳኞች ታማኝ ናቸው ብለው እንዲቀበሉ የሚያስገድድ (ልዩ ተፅዕኖ) የሚፈጥር ህግ ሲሆን በንዑስ አንቀፅ (1) ላይ “የመረጃ ምንጭ ወይንም ወረጃው እንዴት እንደተገኘ ባይገለፅም በሽብርተኝነት ወንጀል የተዘጋጀ ሪፖርት ታማኝ ነው” በሚል የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በየትኛውም መንገድ ያዘጋጀው (የራሱ አቋምም ቢሆን) ሪፖርቱ ታማኝ ማስረጃ ነው ተብሎ ተደንግጓል። ይህ ማለት ደግሞ ዳኞች በራሳቸው ስልጣን ማስረጃን እንዳይመዝኑ የተመዘነ ማስረጃ አለላችሁ ተብለው የተገደዱበት ህግ ነው።

ይህ ድንጋጌ ህገ መንግስቱን ስለሚቃረን ተፈፃሚ የማይሆን ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የፍርድ ቤቶች በነፃነት፣ በህሊናቸው እና በህግ መሰረት የተከራካሪ ወገኖችን ማስረጃ አይተው እና ሰምተው የመመዘን ስልጣን እያላቸው ሌላ ተቋም “ማስረጃህን እኔ አዘጋጅቸልሃለሁ። ያዘጋጀሁልህን ሪፖርት ብቻ አምነህ ተቀበል።” የሚለውን ለህገ መንግስቱ ተቃራኒ የሆነ ድንጋጌ መሰረት አድርጎ በማስረጃነት የቀረበው ሪፖርት የዳኝነት ነፃነትን በግልፅ የሚቃረን እና የተከራካሪ ወገን መብትንም ፈፅሞ የሚጥስ በመሆኑ በህገ መንግስት የተሰጡ መብቶችን የሚጥስ ህግ ባጋጠመ ጊዜ ደግሞ ፍርድ ቤቶች በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9(2) መሰረት ተፈፃሚ እንዳይሆን የማድረግ ህገ መንግስታዊ ስልጣን ስላላቸው በህግ አግባብ ያልተገኘውና ምንጩ ያልታወቀው የአንድ ተቋም ሪፖርት ፍርድ ቤቶች እንዲቀበሉ አይገደዱም።

ከሁሉም በፊት መከበር እና መፈፀም የሚገባው ህገ መንግስቱ ስለሆነ ፍርድ ቤቶች ” እኔ ያቀረብኩልህን ማስረጃ ብቻ አምነህ ተቀበል” በሚል ስሜት የተደነገገውን ህግ ተፈፃሚ እንዳይሆን ለማድረግ ግልፅ እና በቂ የህገ መንግስት ድጋፍ አላቸው። ይልቁንም ማንኛውም የመንግስት አካል ወይም ግለሰብ ህገ መንግስቱን የማስከበር ግዴታውን መወጣት ከሚችልባቸው አንዱና ዋነኛው ለህገ መንግስቱ ተቃራኒ የሆኑ ህጎችን ዋጋ እንዳይኖራቸው ወይም እንዳይፈፀሙ የማድረጉ ሀላፊነት እና ግዴታ የተጣለው በፍርድ ቤቶች ላይ ስለሆነ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተገኘ የተባለው ሪፖርት ከላይ በተጠቀሰው የህገ መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት ውድቅ እንዲደረግ እጠይቃለሁ።

5) በአማራ ክልል ስለወደሙ ንብረቶች የቀረበውን ማስረጃ በተመለከተ:_ በአማራ ክልል ህዝብ እየደረሰበት የነበረውን ግፍ እና በደል በሰላማዊ መንገድ ለመግለፅ አደባባይ በወጣበት ወቅት የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ የተበሳጨ ህዝብ በደም ፍላት በሰጠው አፀፋ በንብረት ካይ ጉዳት መድረሱን እስር ቤት ውስጥ ሆኜ ሰምቻለሁ። ይህ ግን ማንም ከማን ሳይሆን በህዝብ ቁጣ የተፈፀመ ተግባር ከመሆኑ በላይ ይልቁንም በክሱ እንደተገለፀው በአማራ ክልል ንብረት ወደመ የተባለው ከሀምሌ 11/2008 በኋላ ስለሆነ እኔ በህግ ጥላ ስር ሆኜ ንብረት ለማውደም እንደማልችል ማንም የሚረዳው ሆኖ ሳለ በእኔ ክሰ ላይ ማስረጃ ሆኖ መቅረቡ ህጋዊነት የለውም። ንብረት ስለመውደሙ ብቻ የቀረበው የሰነድ ማስረጃ እኔ ተከሳሽ መፈፀሜን የሚያስረዳ ባለመሆኑ እንዲሁም ይህ ድርጊት በበደል ምክንያት በተነሳ ግጭት የተፈፀመ እንጅ በሽብርተኝነት ተግባር የተፈፀመ አለመሆኑን የክሱ አቀራረብም ሆነ ከስልክ ጠለፋ ተገኘ የተባለው ሪፖርት በራሱ በግልፅ የሚያሳይ በመሆኑ በእኔ ላይ ማስረጃ ሆኖ መቅረቡ አግባብነት ስለሌለው የዐቃቤ ህግን ማስረጃ መሰረት አድርጎ ለሚሰጠው ብይን ከሽብር ወንጀል ጋር የሚያያይዘው ነገር ስለሌለ በማስረጃ ሚዛን ውስጥ ሊገባ አይገባውም ተብሎ ውድቅ እንዲደረግ እጠይቃለሁ።

6) ስለ ጦር መሳርያ የተሰጠው ማስረጃ በመከላከያ ማስረጃ የሚስተባበል ቢሆንም ያለኝን ህጋዊ ማስረጃ በማስታባበል መልኩ የቀረበው ማስረጃ ሌላ በህገ ወጥ መሳርያ እንደያዝኩ ተደርጎ የተፃፈው ማስረጃ ፍትህ ለማሳሳት የተሰጠ መሆኑን ሰነዱ በራሱ ያረጋግጣል። ሌሎች ከተለያዩ መ/ ቤቶች የተሰጡ ናቸው የተባሉ ማስረጃዎች እኔ የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነቱን ለማስመለስ የሚያቀርበውን የመብት ጥያቄ በህጋዊ መንገድ ለማስፈፀም በሀላፊነት መቀበሌን እንጅ የሽብር ወንጀል መፈፀሜን የሚያሳይ አንድም ነገር ስለሌለው ሁሉም የሰነድ ማስረጃዎች እኔን ጥፋተኛ ሊያሰኙ የሚችሉ ባለመሆናቸው በሰነድ ማድረጃዎቹ ሚዛን እንድከላከል ብይን ሊያሰጡ አይችሉም። ከዚህ በተጨማሪ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 23 ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፍርድ ቤቶች እንዲቀበሉ የተደነገገው በህገ መንግስቱ አንቀፅ 79 የተሰጠውን የዳኝነት ነፃነት የሚፃረር በመሆኑ እና ህገ መንግስቱን የሚቃረኑ ህጎች፣ የአሰራር ልምዶች ወይም የባለስልጣናት ውሳኔዎች በተገኙ ጊዜ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9(2) መሰረት ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ለማድረግ ዳኞች ግዴታ የተጣለባቸው ስለሆነ የአዋጁ አንቀፅ 23 ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ እንዳይሆን በማድረግ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ተገኘ የተባለውን ያለ ደጋፊ ማስረጃ በአንድ ተቋም ፍላጎት ብቻ ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሪፖርት ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንዲደረግ እጠይቃለሁ።

 

7) የሞቱ ሰዎች ምስክርነትን በተመለከተ:_ ረዳት ኢንስፔክተር ፈንታየ አበበ እና ም/ኮ/ር ገ/ እግዚያብሄር ገ/ መድህን የተባሉ ሰዎች በፖሊስ ቀርበው የምስክርነት ቃል ከሰጡ በኋላ በሞት በመለየታቸው አስቀድመው የሰጡት የምስክርነት ቃል በማስረጃነት እንዲያዝለት ዐቃቤ ህግ አቅርቧል። ነገር ግን ይህ ማስረጃ በሚከተሉት ምክንያቶች ተቀባይነት የለውም።

 

7•1 በማስረጃነት የቀረበው ሰነድ ሞቱ በተባሉ ሰዎች የተሰጠ ቃል ስለመሆኑ ምንም አይነት ማስረጃ አልቀረበም። በተለይ ም/ኮ/ር ገ/ እግዚያብሄር ገ/ መድህን መስከረም 21 ቀን 2009 ዓም ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የምስክርነት ቃሉን እንደሰጠ የሚገልፅ ሲሆን ከ19 ቀናት በኋላ ጥቅምት 9 ቀን 2009 ረዳት ኢ/ር ፈንታየ አበበ ለአማራ ክልል ፖሊስ ሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የምስክርነት ቃል ሰጠ መባሉ የሚታመን አይደለም። በአንድ ወንጀል ሁለት የተለያየ ስልጣን ያላቸው ተቋማት ምርመራ ማጣራት አይችሉም። በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራውን ከጀመረ በኋላ የአማራ ክልል ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ምርመራ ያደርጋል ተብሎ አይታሰብም። ም/ኮ/ር ገ/እግዚያብሄር ገ/ መድህን የተባሉት ምስክርነት ሰጡ ከተባለበት ቀን በኋላ ስለመሞታቸው፣ የት እና መቼ እንደሞቱ የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልቀረበም።

 

ከዚህ መረዳት የሚቻለው ለፖሊስ ሰጡት የተባለው የምስክርነት ቃል እውነትነት የሌለው መሆኑን ነው። ምስክርነቱ የም/ኮ/ር ገ/ እግዚያብሄር ገ/መድህን ነው ተብሎ የሚታመን ቢሆን ምስክሩ ያረጋገጡት ሰላማዊ ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ለማፈን በሌሊት ተዘጋጅተው መሄዳቸውን ብቻ ነው። በትክክል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢኖር ኖሮ በህዝብ መሃል ህጋዊ ቢሮ ከፍተው ህጋዊ የማንነት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት እና ለትግራይ ክልል መንግስት በማቅረብ ላይ ያሉ ሰላማዊ ሰዎችን በሌሊት ለመያዝ የጦርነት በሚመስል ሁኔታ ዝግጅት የሚያስደርግ ምክንያት አልነበረም። የምስክሩ ቃል ነው የተባለው እንደሚያስረዳው በከፍተኛ ሁኔታ የተደራጁ እና የታጠቁ ሀይሎች ለሀምሌ 5/2008 ሌሊት 10 ሰዓት ላይ መመርያ ተቀብለው እንዲያዙ በተዘረዘሩ 6 ሰዎች ቤት ሌሊት 11ሰዓት ላይ ደርሰው የተከሳሽን ቤት ከበው መያዛቸውን እና ህግ ለማስከበር ሳይሆን ለጦርነት ተዘጋጅተው መሄዳቸውን የሚያሳይ ሲሆን በሌሊት ጦር የዘመተበት ሰው ደግሞ ራሱን ለመከላከል የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ የግድ ስለሆነ ባልታሰበ ሁኔታ በሌሊት ከተከሳሽ መኖሪያ ቤት በመሄድ ተከሳሽን እንድሸበር አደረጉ እንጅ ተከሳሽን በአሸባሪነት የሚያሳይ ምስክርነት አይደለም።

 

የምስክሮችን ቃል ለመግለፅ አሁን ጊዜው ባይሆንም በጠቅላላ የቀረበው የሰው ሆነ የሰነድ ማስረጃ የፀጥታ ሀይሎች ከህግ ውጭ በሌሊት ከተከሳሽ መኖርያ ቤት በመሄዳቸው ምክንያት የተፈጠረ ግጭት መኖሩን እንጅ ተከሳሽ በአሸባሪነት ተግባር መሰማራታቸውን አንድም የሚያሳይ ማስረጃ የለም። ግጭት እና አሸባሪነት ደግሞ ፈፅሞ የሚያገናኛቸው ባህሪ የለም። አሸባሪነት የፖለቲካ ፣ የሀይማኖት ወይም የአይዲኦሎጂ ዓላማ ይዞ ህይወትን ለማጥፋት፣ ንብረትን ለማውደም የሚደረግ ዝግጅትና ተግባር ሲሆን ግጭት ደግሞ አሁን እየታየ ባለው ክስ በግልፅ እንደታየው አንደኛው ወገን ከህግ ውጭ ሲንቀሳቀስ ሌላኛው ወገን መብቱን ለማስጠበቅ በሚያደርገው መልስ የሚፈጠር ድንገተኛ ሁኔታ ነው። አሁንም በእኔ ላይ በተደረገው ሴራ ግጭት መፈጠሩን እንጅ አሸባሪነትን አያሳይም።

7•2 የሞቱ ሰዎች የሰጡት ቃል በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችለው ወደ ሞት እየተቃረቡ ባሉበት ወቅት እውነት ይናገራሉ ተብሎ ስለሚታመን ብቻ ነው። አሁን በማስረጃነት የቀረበው ሰነድ ግን በህጉ አላማ መሰረት እውነት ለመናገር ታስቦ በኑዛዜ መልክ የተሰጠ ሳይሆን ሞቱ የተባሉት ሰዎች በሙሉ ጤንነት ወይንም ለሞት የሚያሰጋ ምክንያት በሌለበት ጊዜ ለመርማሪ ፖሊስ ሰጥተዋል የተባለ ቃል ነው። እውነታው ይህ ከሆነ ሟቾች ተከሳሽን ለመወንጀል ሆን ብለው እና አስበው የሰጡት ቃል ስለመሆኑ የድርጊቱ አፈፃፀም በራሱ ያረጋግጣል።

ሟቾች የተባሉት ሰዎች የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ ተከሳሽ በቦታው አልነበሩም። ወይም የተከሳሽ ጠበቆች እየሰሙ የተሰጠ ቃል አይደለም። ማንኛውም ሰው ክርክሩን በግልፅ የመስማት ህገ መንግስታዊ መብት ያለው ሲሆን ተከሳሽ ወይንም ጠበቃው በሌሉበት ተሰጠ የተባለ ምስክርነት በመስቀለኛ ጥያቄ ወይም በተለያዩ የማብራሪያ ጥያቄዎች ነጥሮ ያልወጣ በመሆኑ ማስረጃው ተቀባይነት የለውም።

ከላይ በዝርዝር እንደተገለፀው እኔ እንድከሰስ ምክንያት የሆነው በህገ ወጥ መንገድ በግዴታ የተነጠቀው የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለመንግስት ለማቅረብ በህዝብ ተመርጨ የማንነት ጥያቄውን በህጋዊ መንገድ በህገ መንግስቱ መሰረት ይመለከተዋል ለተባለ የመንግስት አካል ሁሉ ሳቀርብ ጥያቄውን ለማፈን ሲባል ከመኖርያ ቤቴ በሌሊት ተከብቤ ጥቃት ሊገፀምብኝ ሲል ራሴን በመከላከል እና የመንግስት ባለስልጣናት በሚፈፅሙት አስተዳደራዊ በደል ከህዝብ በቀረበ ተቃውሞ ግጭት መፈጠሩን ሰነዱ ከሚያሳይ በቀር እኔም ግጭት ከመፈጠሩ ውጭ አሸባሪ ከተባለ ቡድንም ሆነ ግለሰብ ጋር ተገናኝቼ ስለማላውቅ በተለይ የአሸባሪ ቡድን አባል እየተባሉ የተጠቀሱት እነ ደጀኔ ማሩ፣ እነ ሰረበ ጥሩነህ የሚባሉ ሰዎች ስለመኖራቸው ወይንም የአሸባሪ ቡድን አባል ስለመሆናቸው ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ በጊዜያዊ ግጭት ወንጀል ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈፅሞ ከሆነም በመደበኛው የወንጀለኛ ህግ ከሚያስከስስ በስተቀር አሸባሪነት ሊሆን አይችልም።

ስለዚህ በህጋዊ መንገድ የመረጠኝን ህዝብ ማንነት ለማረጋገጥ ሳደርግ የነበረውን ጥረት ክሱም ሆነ ማስረጃው በግልፅ የሚያሳይ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎቹ በተከሳሽ ላይ መቅረባቸው ፍፁም ከእኔ ተግባር ጋር የሚገናኙ ስላልሆኑ በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተገኘ የተባለው ሪፖርትም ከላይ በሰፊው እንደተገለፀው የሀገሪቱን ህገ መንግስት፣ የዓለም አቀፍ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶችን ቃል ኪዳን ስምምነት እንዲሁም የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ራሱን በመጣስ የዜጎችን የግል ሚስጥር ለመበርበር ህገ መንግስቱን በመጣስ የተደነገገውን (የአዋጁን አንቀፅ 14) በመጣስ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ በመሆኑ ይህም በሪፖርት መልክ ከመቅረቡ ውጭ ሪፖርቱ የተዘጋጀበት የድምፅ ቅጅ ከሌለ ሪፖርቱን ያዘጋጀው የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት ፅ/ቤት አቋም ስለሆነ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ ስርዓት ቁጥር 146 መሰረት ስለምቃወማቸው በብይኑ ላይ በማንኛውም መለኪያ በማስረጃነት ተቆጥረው ለአሸባሪነት ወንጀል ሚዛን ውስጥ እንዳይገቡ በትህትና አመለክታለሁ!

ግራ ገባን እኮ ….የመከላከያ ሰራዊት ተብዬው ደግሞ ወደ ጠላት ሀገር የተላከ ይመስል የራሱን ህዝብ በጥይት ይጨፈጭፋል

አፈንዲ ሙተኪ
—-


ማዕከላዊ መንግሥቱ ለተቃውሞ ብተና ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ኃይል መላኩን ትቶ እስከ አፍንጫው የታጠቀ የመከላከያ ሰራዊት ይልካል።

የመከላከያ ሰራዊት ተብዬው ደግሞ ወደ ጠላት ሀገር የተላከ ይመስል የራሱን ህዝብ በጥይት ይጨፈጭፋል።

በመንግስት አካላት ዘንድ ያልታጠቀ ሰልፈኛን በጭስና በውሃ መበተን አልለመድ ብሏል።

አክቲቪስት ተብዬው ሶስት አይነት መረጃ እያሰራጨ ወጣቱን ውዥንብር ውስጥ ይከተዋል። ወጣቱ ለተቃውሞ ሲወጣ ደግሞ በሁለት ቡድን ይከፈልና አንደኛው ቡድን ከአቶ ለማ መገርሳ ካቢኔ ጋር ወግኖ ሰልፍ እንዳይደረግ ይለማምናል። ሌላኛው ቡድን “ትግሉ ተፋፍሞ መቀጠል አለበት” እያለ ሶሻል ሚዲያውን በትኩሳት ይንጠዋል። ሁሉም እንዳልነበረ ሆኖ ሲጠናቀቅ ግን ለሟች ሙሾ እያወረደ የአቶ ለማ ካቢኔንም ሆነ ገዳዮቹን ያወግዛል። “ኦፒዲኦ ድሮውንስ ተላላኪ” ወደሚለው የቀድሞ ሙዚቃው ይመለሳል።
—–
በዚህ መሀል ህዝብ አለቀ! በተለይም የደሀው ልጅ ተጨፈጨፈ።
—–
መከላከያ ነኝ ብሎ ሰው መጨፍጨፍም ሆነ አክቲቪስት ነኝ እያሉ ህዝብን ማስጨረስ መወገዝ አለባቸው። ኦፒዲኦም ራሱን ሳያጠናክር በጥቂት ወራት ውስጥ ያከማቸውን ትንሽዬ ጡንቻ እያሳየ ወጣቶች በርሱ ተማምነው ከመከላከያው ጋር ግብግብ እንዲገጥሙ ሰበብ መሆን የለበትም።
—–
በድጋሚ ፈጣሪ የወጣቶቻችንን ነፍስ ይማርልን።

ትናንት በአምቦ የተገደሉት ሰዎች ቀብራቸው ዛሬ ይፈጸማል። ከሟቾቹ መካከል የ13 ዓመት ልጅ ይገኝበታል ተብሏል።

ትናንት በአምቦ የተገደሉት ሰዎች ቀብራቸው ዛሬ ይፈጸማል። ከሟቾቹ መካከል የ13 ዓመት ልጅ ይገኝበታል ተብሏል። BBC Amharic

አምቦ ውስጥ ስኳር የጫኑ መኪናዎች እንዳያልፉ ተዝግቶ የነበረውን መንገድ ለማስከፈት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሰዎች ሞተዋል።

ዛሬ ከአምቦ ሆሰፒታል የሜዲካል ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ቶኩማ ክፍሌ እንደነገሩን፤ ትላንት በነበረው ግጭት ስድስት ሰዎች ህይወታቸው አልፎ ሆሰፒታል እንደደረሱ እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ከመጡ በኋላ ህይወታቸው እንዳለፈ አረጋግጠዋል።

ዶ/ር ቶኩማ እንዳሉት ህይወታቸው አልፎ ከመጡት እና በሆስፒታሉ ከሞቱት መካከል ሁለቱ ሴቶች ናቸው።

”የሁሉንም ሟቾች አስክሬን ማየት ባልችልም፤ ከተመለከትኳቸው አስክሬኖች እና ከባልደረቦቼ እንደሰማሁት ሁሉም የሞቱት በጥይት ተመትተው ነው። ከሟቾቹ መካከል ጭንቅላታቸውን የተመቱ ሲኖሩ፤ ሆዱን የተመታና ኦፕሬሽን ክፍል ደርሶ ብዙ ደም በመፍሰሱ የሞተም አለ” ብለዋል።

ዶክትር ቶኩማ ጨምረውም አብዛኛዎቹ ሟቾች እድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው። ሆስፒታል ደርሰው ከሞቱት መካከል አንደኛዋ ሴት ስትሆን እድሜዋ በግምት 16 ወይም 17 ሊሆን እነደሚችል ተናግረዋል።

ከትላንት ጀምሮ ህክምና ተደርጎላቸው እየተመለሱ ያሉ ሰዎች እንዳሉ የሚናገሩት ዶ/ር ቶኩማ አሁን በሆስፒታሉ ከአስር ያላነሱ ሰዎች የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

ከእነዚህም መካከል በጽኑ የተጎዱ እንዲሁም ለህይወት የማያሰጋ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም እንዳሉ ዶክተር ቶኩማ ተናግረዋል።

በአምቦ ከተማ በተከሰተ ግጭት ሰዎች ተገደሉ

የአምቦ ከተማ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ በከተማዋ ብዙ እንቅስቃሴ ባይታይም ከትላንቱ አንፃር ከተማዋ ስላም እንደሆነች ገልፀዋል።

ትናንት የተገደሉት የአብዛኞቹ ሰዎች ቀብር ዛሬ ስለሚፈፀም፤ ከቀብር ጋር ተያይዞ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር የሃገር ሽማግሌዎች ከቀብር በኋላ ወጣቱ ወደ ቤቱ እንዲመለስ እያሳሰቡ ናቸው ብለዋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው ኩምሳ ደግሞ፤ ”የሟቾችን ማንነት፣ በማን እና በምን አይነት ሁኔታ እንደተገደሉ እየተጣራ ነው። እሰካሁን ባለን መረጃ ግን ከሟቾቹ መካከል ሦስት ሴቶች እና የ13 ዓመት ልጅ ይገኙበታል” ብለዋል።

አቶ ጌታቸው እንደሚሉት በአምቦ ስኳር ከጫኑ መኪኖች ጋር ተያይዞ የነበረው ግጭት ከሦስት እና ከአራት ቀናት በላይ አስቆጥሯል።

”ይህን ችግር ለመፍታት የክልሉ ፖሊስ እና የሃገር ሽማግሌዎች ወጣቶችን ለማወያያት ጥረት እያደረጉ ነበር። በዚህም መልካም ለውጦችን እየተመለከትን ነበር። ትናንት ተጨማሪ ኃይል ወደዚህ ከመጣ በኋላ ግን ይህ ሁሉ ችግር ተፈጠረ” ሲሉ ያስረዳሉ።

የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊው አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ እንዳሉት እስካሁን ባላቸው የተጣራ መረጃ ስምንት ሰዎች በትናንቱ ግጭት ሞተዋል ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ሮበርት ሙጋቤን የሾሙበት ድርጊት እንዲመረመርና ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠየቁ።

የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዚምባቡዌውን ሮበርት ሙጋቤን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርገው የሾሙበት ድርጊት እንዲመረመርና ጉዳዩ ሙስና ሆኖ ከተገኘ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠየቁ።
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 16/2010)

ቻይና ስፍራውን እንዲያገኙ ለተጫወተችው ሚና የተሰጠ ምላሽ ይሆን ወይ የሚሉ መላምቶች መንጸባረቃቸውንም በዋሽንግተን ፖስት ላይ ጥቅምት 25/2017 የቀረበው ጽሁፍ አመልክቷል። ለ18 አመታት የሲ ኤን ኤን ዘጋቢና ተንታኝ የነበረችውና በአሁኑ ወቅትም በዋሽንግተን ፖስት፣በቺካጎ ትሪቡንና መሰል ታዋቂ ጋዜጦች ላይ ትንታኔዎችን በመጻፍ ትታወቃለች ፍሪዳ ጊቲስ። እናም ዘጋቢዋ ጥቅምት 25/2017 በታተመው ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ ባቀረበችው ጽሁፍ የዶክተር ቴድሮስን ርምጃ ባለጸጋይቱን ሀገር ዚምባብዌን ኢኮኖሚ ላደቀቀ አምባገነን አዛውንት የቀረበ ሽልማት በማለት አውግዛለች።

በጤናውም ዘርፍ ሙጋቤ ለሀገራቸው ያደረጉት አስተዋጽኦ የለም ስትልም ተችታለች። አሜሪካ የዶክተር ቴድሮስ ርምጃን ማውገዟ፣የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር የሚያሳዝን ቀልድ መስሏቸው እንደነበር የተነገሩትን በጽሁፏ ያካተተችው ፍሪዳ ጊትስ፣የአየር ላንድ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ድርጊቱን ትንኮሳና አስደንጋጭ ሲሉ መናገራቸውንም በዚሁ በዋሽንግተን ፖስት ዘገባዋ ላይ አስፍራለች። የአለም ጤና ድርጅት ሰራተኛ ዶክተር ቴድሮስ በተቋሙ ተአማኒነትና የገንዘብ ምንጭ ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ሊታያቸው ይገባ ነበር ሲሉም መተቸታቸውም ተጠቅሷል። የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የፈጸሙት ድርጊት አለም አቀፉን ተቋም ጥያቄ ውስጥ ማስገባቱን ፍሪዳ ጊቲስ ገልጻለች።

ከዚህ ድርጊት በስተጀርባ ምን እንዳለ ግን ሊመረመር እንደሚገባ አስገንዝባለች። ይህ ርምጃ ከሙስና ጋር የተያያዘ ሆኖ ከተገኘም ዶክተር ቴድሮስ በአስቸኳይ ስልጣናቸውን መልቀቅ ይገባቸዋል ስትል ጥሪ አቅርባለች። የተባበሩት መንግስታት ጉዳዮችን የሚመረምረው ዩኤን ዋች ዳይሬክተር ሂለር ኒውር ይህ ሹመት ለሆነ ነገር የተሰጠ ማካካሻ ካልሆነ በእርግጥ ሽልማት ነው በማለት ከሹመቱ በስተጀርባ አንዳች ነገር ሊኖር ይችላል የሚል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።
ቴድሮስ ለአለም ጤና ድርጅት እንዲታጩ በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ሮበርት ሙጋቤ ድጋፍ ስላደረጉላቸው በምላሹ የተሰጠ ሽልማት ይሆን ሲሉም ጠይቀዋል። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ በጤና ጥበቃ ሚኒስትርነታቸው ወቅት ውጤታማ ቢሆኑም በማሰቃየት፣በጭቆናና በምርጫ ማጭበርበር የታወቀ አምባገነን መንግስት ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራቸው እንደነበሩም ጽሁፉ በዝርዝር አስቀምጧል።

ሙጋቤን የአለም ጤና ድርጅት አምባሳደር አድርገው ሲሾሙ እንዲመረጡ ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገችላቸው ቻይና ውለታ እየመለሱ ይሆን የሚል ጥርጣሬ መከተሉንም በጽሁፉ ተመልክቷል። ቻይና ተጽእኖዋን ወደ አለም አቀፍ መድረክ የማስፋት ፍላጎት እንዳላት ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውንም ጽሁፉ ያስታውሳል። ከምዕራቡ አለም የተገለሉትን የዚምባቡዌውን ሮበርት ሙጋቤን በከፍተኛ ደረጃ የምትደግፈውም እሷ በመሆኗ ጉዳዩ ከዚህ ጋር የተያያዘ ይሆን ወይ የሚለውም ጥርጣሬ ተያይዞ ተነስቷል።

በጥብቅ ጥበቃ ስር ኬንያ ምርጫ እያካሄደች ነው

 

የኬንያ ምርጫ

ለሁለተኛ ጊዜ ለመመረጥ የሚወዳደሩት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዜጎች ድምፅ እንዲሰጡ እና ስላም እንዲጠበቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ ድጋፊዎቻቸው በምርጫው እንዳይሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ቢያሽንፉም ራይላ ኦዲንጋ ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ የምርጫው አካሄድ ‘መዛባት’ ታይቶበታል በሚል ውጤቱ መሰረዙ ይታወሳል።

ዛሬ እየተካሄደ ባለው ዳግም ምርጫ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ሆነው መራጮችን እያስተናገዱ ነው። ነገር ግን የድምፅ ሰጪዎች ቁጥር ቀደም ሲል ከተደረገው ምርጫ አንፃር ዝቅተኛ እንደሆነ እየተነገረ ነው።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፀጥታ ጥበቃ ኃይሎች የመራጮችን እና የምርጫ ጣቢያዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በመላው ሃገሪቱ ተሰማርተዋል ተብሏል።

የኬንያ ምርጫImage copyrightANDREW RENNEISEN
አጭር የምስል መግለጫነሃሴ 2 የተካሄደው ምርጫ

በምርጫው ዋዜማ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ባስተላለፉት መልዕክት ‘አባቶቻችን የመምረጥ እድል እንደናገኝ መስዋትነት ከፍለዋል፤ ይህን እድል በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል’ ሲሉ ዜጎች ድምፅ እንዲሰጡ አሳሰበዋል።

የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ አሸንፈዋል ብሎ አውጆ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምርጫውን ውጤት ውድቅ ካደረገ በኋላ በኮሚሽኑ ላይ ከፍተኛ ወቀሳዎች እና ጥቃቶች ሲፈፀሙ ቆይቷል።

ባሳለፈነው ሳምንት የምርጫ ኮሚሽኑ ከፍተኛ ሃላፊ የግድያ ማስፈራሪያ ከደረሳቸው በኋላ ወደ አሜሪካ ሸሽተዋል።

ከመጀመሪያው ምርጫ እሰካሁን ድረስ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ ከምርጫ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች ከሰባ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ፖሊስ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ ሲተኩስ።

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ የድጋሚ ምርጫው ወደፊት እንዲካሄድ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ቢጠይቁም ዳኞች ሳይሟሉ በመቅረታቸው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀርቷል።

ከነሐሴው ምርጫ በኋላ ውዝግቡ ወደፍርድ ቤት ሄዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ዴቪድ ማራጋ ‘ምርጫው በህገ-መንግሥቱ መሰረት አልተካሄደም’ ስለዚህም የምርጫው ውጤት ‘ልክ ያልሆነ እና ወጋ ቢስ’ ነው በማለት ውድቅ አድረገዋል።

ዋና ዳኛው እንዳሉት ከስድስቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አራቱ የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤቱን ሲያስተላልፍ መዛባት ተፈፅሟል ብለዋል ።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ የምርጫው ውጤት ‘ግልፅ አልነበረም ሊረጋገጥም አይችልም’ ብሎ ነበር።

ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት የፈፀመውን አይነት ስህተት እንዳይደገም ምንም አይነት ማሻሻያ አላደረገም ቢለው ቢከሱም ኮሚሽኑ ይህን ክስ ውድቅ ያደርጋል።

ጥምር የፖለቲካ ፓርቲያቸው ምርጫው ላይ የሚሳተፈው የምርጫ ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ማሻሻያ ሲያደርግ እንደሆነ ቀድመው አሳውቀው ነበር።

ኦዲንጋ ዛሬ እየተካሄደ ያለውን ምርጫ ለማጨናገፍ ‘ግዙፍ’ ህዝባዊ ሰልፍ እደሚጠሩ አሳውቀው፤ አስከፊ ግጭት እንዳይከሰት ደጋፊዎቻቸው በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ እንዳይገኙ ጠይቀዋል።

በአማራነታቸው ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን እስረኞች ተናገሩ

በአማራነታቸው ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን እስረኞች ተናገሩ

” አማራ አህያ ነው። ግማሹ ደግሞ ጅብ ነው። አህያውን በጅብ እናስበላዋለን እያሉ ይደበድቡኝ ነበር።” ዘመነ ጌቴ

” እኔ የታሰርኩት አማራ ስለሆንኩ ነው። ማዕከላዊ አንተ ሆዳም አማራ እየተባልኩ ነበር የምመረመረው” ሰይድ ኑርሁሴን ሰይድ

(በጌታቸው ሺፈራው)

በአማራነታቸው ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ እስረኞች ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ገለፀዋል። ዛሬ ጥቅምት 16/2010 በዋለው ችሎት በርካታ ተከሳሾች አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን አብዛኞቹ በአማራነታቸው ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል። በእነ ክንዱ ዱቤ መዝገብ 2ኛ ተከሳሽ የሆነው ዘመነ ጌቴ ” አማራ አህያ ነው። ግማሹ ጅብ ነው። አህያውን በጅብ እያስበላን ፀጥ እያደርገዋለን። እንኳን አማራን ሶማሊንም ፀጥ አድርገነዋል” እያሉ ይደበድቡት እንደነበር ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

“እኛ አማራ ወይንም ኦሮሞ መሆን ፈልገን አልተወለድንም። ግን በዘራችን ምክንያት በደል እየደረሰብን ነው” ያለው ዘመነ ማዕከላዊ በተፈፀመበት ድብደባ ጆሮ እና አይኑ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ገልፆአል። ” ማዕከላዊ የተሰበረው አጥንቴ፣ የተጎዳው አይንና ጆሮዬ ሳይድን አሁንም ቂሊንጦ እየተደበደብኩ ነው። የመኖር ዋስትና የለኝም” ብሏል። አቶ ዘመነ በአማራነቱ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን ሲገልፅ ዳኞች ሊያስቆሙት ሲሞክሮ ችሎት ውስጥ የነበሩት በኦነግና በግንቦት ሰባት የተከሰሱ እስረኞች “የተፈፀመውን ነው የሚናገረው። ይናገር!” እያሉ በማጉረምረም በአንድ ላይ በፍርድ ቤቱ ላይ ጫና ሲያሳድሩ ለመታዘብ ተችሏል።

ከአቶ ዘመነ ጌቴ በተጨማሪ በእነ ተሻገር ወልደሚካኤል ክስ መዘገብ 3ኛ ተከሳሽ የሆነው ተስፋሁን ማንዴ ” አማራ ደደብ ነው!” እየተባለ በማንነቱ እንዲሸማቀቅ መደረጉን ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚሁ መዝገብ 6ኛ ተከሳሽ ሰኢድ ኑርሁሴን በበኩሉ ” እኔ የታሰርኩት በአማራነቴ ነው። ማዕከላዊ ሆዳም አማራ እየተባልኩ ተመርምሬያለሁ” ብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሾቹ በደል ያደርሱባቸው የነበሩት የማዕከላዊ መርማሪዎች ችሎት ውስጥ እንዳሉ ገልፀው ሲያሸማቅቋቸው የነበሩ አካላት ችሎት ውስጥ መገኘት እንደሌለባቸው አመልክተዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ” እነሱን ችሎት ገብታችሁ አትከታተሉ የምንልበት ስልጣን የለንም” ሲል የእስረኞችን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል።

በሌላ በኩል የወልቃይት ማንነት ጉዳይ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት እነ መብራቱ ጌታሁን አቃቤ ህግ ያቀረበው ማስረጃ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበር ቢሆንም ብይኑ አልተሰራም በሚል ለህዳር 11/2010 ተለወጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። 1ኛ ተከሳሽ መብራቱ ጌታሁን “እኛ በመታሰራችን ቤተሰቦቻችን ችግር ውስጥ ወድቀዋል” ብለዋል። በተጨማሪም ሀምሌ 5/2008 ጎንደር በተያዙበት ወቅት ፖሊስ የያዘባቸው ገንዘብ እንዳልተመለሰላቸውና ደረሰኝም እንዳልተሰጣቸው ገልፀዋል።

እነ ክንዱ ዱቤ ለህዳር 11 እንዲሁም እነ ተሻገር ወልደሚካኤል ለህዳር 15 / 2010 ተቀጥሮባቸዋል።