በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ባዶ እየሆኑ ነው ተባለ

BBN news November 29, 2017

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በተለይ በሃሮማያ እና በመቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች እስከ ትላንት ድረስ ትምህርታቸውን ጥለው እየወጡ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ሆኖም ካቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ አንድም ጥያቄ ባለመመለሱ ግቢውን ጥለው ለመውጣት እንደወሰኑ ተነግሯል፡፡
የሶማሌ ክልል ልዩ ጦር ወደ ኦሮሚያ ክልል እየገባ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በተለያዩ አካላት ተቃውሞ ሲቀርብበት እንደነበር ይታወቃል፡፡ ተቃውሞ ሲያቀርቡ ከነበሩ ወገኖች መካከል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ተማሪዎቹ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በኦሮሚያ ክልል እየፈጸመ የሚገኘው ጥቃት እንዲቆም ካለመለከቱ በኋላ፣ ጥያቄአቸው ምላሽ እንደሚያገኝ ተነግሯቸው ነበር ተብሏል፡፡ ሆኖም ልዩ ኃይሉ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ከሰላሳ በላይ ሰዎችን መግደሉ ሌላ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡
ይህ ጉዳይ ያስቆጣቸው ተማሪዎች ከሃሮማያ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመውጣት ላይ እንደሚገኙ ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተለይ ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የወጡ ተማሪዎች ቁጥር አስደንጋጭ መሆኑም ነው የተሰማው፡፡ በዚህም የተነሳ በግቢው መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት መስተጓጎሉም ታውቋል፡፡ በግቢው ውስጥ የቀሩት ተማሪዎች አነሰተኛ መሆናቸውን የጠቆሙት መረጃዎች፣ ግቢው አለወትሮው ጭር ማለቱንም አክለዋል-መረጃዎቹ፡፡

ህወሀት ውሳኔዎቹን ለምን ሸሸገን? ለምሳሌ ስለኤርትራ!

ዋዜማ ራዲዮ-በህወሀት ዝግና ምስጢራዊ የማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባዔ የደህንነት ሀላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋና ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አሸናፊ ሆነው ወጥተዋል። ትዕግስትና የመግባባት ችሎታ ለሚያንሳቸው ዶ/ር ደብረፅዮን ዝቅተኛ የካድሬነት ልምዳቸው ተደምሮበት በፓርቲው ውስጥ “ምንም አዲስ ነገር ሊያመጡ አይችሉም” ሲሉ ከወዲሁ ትችት የሚያቀርቡ አሉ። ለመሆኑ አዲሱ የህወሀት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ማን ናቸው? ከመጋረጃ ጀርባ ህወሀት ሰለተነጋገራቸውና ውሳኔ ስላሳለፈባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ለምን ሸሸገን? ቻላቸው ታደሰ የሚከተለውን ፅፏል ተጨማሪ የድምፅ ዘገባ ከግርጌ ያገኛሉ

ኢሕአዴግ መራሹ መንግስት በህዝባዊ አመጽ እና እያደገ በመጣ ብሄር ግጭት በተጠመደበት ሰዓት ካንድ ወር ለበለጠ ጊዜ መቀሌ ላይ ስብሰባ ተቀምጦ የከረመው የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን ዶክተር ደብረ ፂዮን ገብረ ሚካዔልን በሊቀመንበርነት፣ ወይዘሮ ፈትለ ወርቅ ገብረ እግዚያብሄርን ደሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መምረጡን  አስታውቋል፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ዶክተር ደብረጺዮንን ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠው እንግዲህ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የሕወሃት ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አባይ ወልዱን በግምገማ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ካሰናበተ በኋላ ነው፡፡
በርግጥም አቶ አባይ ወልዱ የአስኳሉ የሕወሃት ሊቀመንበር በሆኑበት ወቅት ከፌደራሉ መንግስት እና ዋና መቀመጫውን አራት ኪሎ ላይ ካደረገው ኢሕአዴግ የተነጠሉ ስለነበሩ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ፖለቲካ ተጽዕኖ የነበራቸው ሰው እንዳልነበሩ ግልጽ ነው፡፡ ዶክተር ደብረጺዮን ግን የፌደራሉን መንግስትም ሆነ የገዥውን ግንባር ውስጣዊ ፖለቲካ አጣምረው ሁነኛ ሚና ለመጫወት እድል ያገኛሉ፡፡

ህወሀት በሀገራዊ አጀንዳ ላይ ለምን ለብቻው ይነጋገራል?
ማዕከላዊ ኮሚቴው በሀገሪቱ ስለሚታየው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ ከኤርትራ ስለሚኖረው ግንኙነት እና ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአመራር ብቃት ጭምር አንስቶ ሲመክር እንደከረመ የዋዜማ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመው ሳለ ድርጅቱ ግን በመግለጫው በአመራር ሽግሽጉ ላይ ብቻ ያተኮረው፡፡ ይህም ሚስጢራዊ ከሆነው የሕወሃት ተፈጥሮ የሚመነጭ እና ራሱ ሕወሃትም የሚያምነው ባህሉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዋናነት ግን ሕወሃት ዛሬም ከተቸከለበት ኋላ ቀር አስተሳሰብ ሳይላቀቅ በዋናነት ቡድናዊነት ባጠላባቸው ውስጣዊ ድርጅታዊ ጉዳዮች ብቻ ተጠምዶ መክረሙን የሰሞኑ ግምገማ ውጤት ፍንጭ ይሰጣል፡፡
በርግጥም ርዕዮተ ዐለማዊ ጥራት በሚጎድላቸው የተወናበዱ የገዥው ግንባር ፖሊሲዎች እና ሀገራዊ ራዕይ ባነገበ አመራር እጥረት ሳቢያ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ የገባቸው ኢትዮጵያ አሁንም በዋነኛት የተራማጅነት እንጥፍጣፊ በሌለው ነጻ አውጭው ሕወሃት እየተመራች መቀጠሏ ለብዙ የውጭ ታዛቢዎች እንቆቅልሽ ነው የሚሆንባቸው፡፡
የሰሞኑ ግምገማ እና የአመራር ለውጥ የሚያሳየው እንግዲህ አቶ መለስ በሕይወት እያሉ በአምስት ዐመታት ውስጥ በየምዕራፉ እንደሚተገበር ይናገሩለት የነበረው የአመራር መተካካት ጉዳይ በሕወሃት ዘንድ ውሃ በልቶት እንደቀረ እና የተከተለው መንገድ ቡድናዊነት ባጠላበት ግምገማ ነባር አመራሮቹን ከሃላፊነት ማንሳት መሆኑን ነው፡፡
የሰሞኑ ሁኔታዎች የሚሳዩት ነባሩ አመራር ሁኔታዎችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ለመዝለቅ ያለውን ዝግጁነት የሚጠቁም ነው፡፡ በመጭው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔም በወጣት ወይም ለውጥ ፈላጊ አባላቱ እና በነባሩ አመራር መካከል ሁነኛ ፖለቲካዊ ፍጭት ተደርጎ ለውጥ ናፋቂው አዲሱ ሃይል አሸናፊ ሆኖ ካልወጣ አሮጌው ነባር አመራር ሁነኛ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ለመውሰድ የሚኖረው ቁርጠኝነት እምብዛም ነው የሚሆነው፡፡ እናም ሕወሃት ባሁኑ ወቅት በመንግስትም ሆነ በገዥው ግንባር ውስጥ መዋቅራዊ ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችለው ቁርጠኝነት በእጅጉ አጠራጣሪ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ ወደፊትም ቢሆን ጊዜውን የሚመጥኑ ማሻሻያዎችን ያፈልቃል ብሎ መጠበቅ አስቸጋሪ እየሆነ ነው፡፡

ሕወሃት ለመንግስት አዳዲስ ፖሊሲዎች እና ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ይዞ የመምጣቱ ዕድል አነስተኛ ቢሆንም ላለፉት ሦስት ዐመታት ያሳየውን ድርጅታዊ መዳከም ግን በመጭው መጋቢት በሚካደው የኢሕአዴግ ጠቅላላ ጉባዔ አሻሽሎ ለመቅረብ ሲዶልት እንደከረመ መገመት አያስቸግርም፡፡ በርግጥም የዋዜማ ምንጮች እንዳሉት ሥራ አስፈጻሚው በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም የአመራር ብቃት ላይ ተወያይቶ ሁነኛ ውሳኔ ላይ ደርሶ ከሆነ በቀጣዩ መጋቢት በሚካሄደው የኢሕአዴግ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርነቱን እና የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን መልሶ ለመያዝ የማሰቡ ነገር ጨርሶ ዝግ አይደለም፡፡

እናም ከመጋቢቱ የኢሕአዴግ ጉባዔ በፊት ወይ በጉባዔው ወቅት ኦሕዴድ እና ብአዴን በጋራ ወይም በተናጥል በፖለቲካ ስልጣን እና ሃብት ክፍፍል ረገድ ሁነኛ አቋም ይዘው ብቅ ካላሉ እና የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታም ባለበት ከቀጠለ ሕወሃት በቀጣዩ ምርጫ በትምህርት የላቁትን ዶክተር ደብረጺዮንን ለጠቅላይ ሚንስትርነት ይዞ ሊቀርብ ይችላል፡፡
በርግጥ ካፉት ሁለት ዐመታት ወዲህ ኢሕዴድ እና ብአዴን በኢሕአዴግ ውስጥ ሕወሃትን ሙሉ በሙሉ ባይገዳደሩም እንኳ የወሰኑ ጥቅሞቻቸውን ማስጠበቅ የሚችሉበት አንጻራዊ መልካም አጋጣሚ እንደተፈጠረላቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ አሁን ባላቸው ቁመና ግን በቅርቡ የሃይል ሚዛኑን የማስተካከል እድላቸው አናሳ ይመስላል፡፡ እናም ከመጋቢት በኋላም በዶክተር ደብረጺዮን የሚመራው ሕወሃት የበላይነቱን አስጠብቆ የመቀጠል እድሉ ሰፊ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡

የዶክተር ደብረፂዮን ስውር መሰላል
የሰሞኑ ግምገማ ዶክተር ደብረፂዮን እና የደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው አሠፋ አሸናፊ ሆነው የወጡበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በተለይ አቶ ጌታቸው አሠፋ ለአቶ መለስ እና ባለቤታቸው ወይዘሮ አዜብ ቀኝ እጅ የነበሩትን ምክትላቸውን አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስን ከዐመት በፊት ከመስሪያ ቤቱ ማሰናበት ችለው ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፖለቲካ ሳይንስ እና ከሰላም እና ደህንነት ጥናት ተቋም ያገኟቸውን ሁለት የድህረ ምረቃ ዲግሪዎች በመጥቀስ የአቶ ጌታቸው ቦታ እንዲሰጣቸው በግልጽ ስብሰባ ጭምር ይወተውቱ የነበሩት ሌላኛው የደህንነት ሹም እና የአድዋ ተዋላጁን አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካዔልን ደሞ ከስራ አንሳፍፈው ካቆዩ በኋላ በሙስና አስወንጅለው ከሦስት ዐመታት በፊት ዘብጥያ አስወርደዋቸዋል፡፡ በርግጥም አቶ ጌታቸው አቶ ኢሳያስን ሲያሰናብቱ እና ወልደ ሥላሴን ወደ ወህኒ ቤት ሲልኩ የወይዘሮ አዜብ መስፍንን ደጃፍ ለማንኳኳት የመጨረሻውን እንቅፋት እንዳስወገዱ ግልፅ ነበር፡፡ በርግጥም ወይዘሮ አዜብ ሰሞኑን ከሕወሃት አስፈጻሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ መታገዳቸው የዚሁ ሂደት መቋጫ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

በድርጅቱ ከያዙት ሃላፊነት አንጻር ዶክተር ደብረፂዮን ሊቀመንበር መሆናቸው ባይደንቅም ሰውዬው ግን ለፖለቲካ የሚመጥን ልምድም ሆነ ተፈጥሯዊ ጠባይ ስለሌላቸው በብዙ ወገኖች ዘንድ ግርምት መፍጠሩ አልቀረም፡፡

ደብረ ፂዮን በበረሃ ትግል ወቅትም በሕወሃት ሬዲዮ ጣቢያ በቴክኒኩ ዘርፍ እንጂ በካድሬነቱም ሆነ በድርጅት ፖለቲካዊ አመራር ልምድ ያላቸው ሰው አይደሉም፡፡ ከ1983 ጀምሮ ደሞ ለረዥም ዐመታት በደኅንነቱ መስሪያ ቤት ውስጥ ከአቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ በተጨማሪ የሟቹ ክንፈ ገብረ መድኅን ምክትል ሆነው ሲሰሩ ስለኖሩ አብዛኛው ልምዳቸው ከደኅንነት ሙያ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በደኅንቱ መስሪያ ቤት ውስጥም የመሠረታዊ ደኅንነት ኪነ ሙያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በማቋቋም በሃላፊነት መርተዋል፡፡ ማሰልጠኛው ነባሮቹን የደህንነቱ ባልደረቦች እና አዳዲስ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችን ተቀብሎ ለጥቂት ዐመታት ማሰልጠን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን ተቀዛቅዟል፡፡
ከ1993 የሕወሃት ክፍፍል በኋላ ግን አቶ መለስ ደብረ ፂዮንን ከደህንነቱ አንስተው ወዳንድ የትግራይ ክልል ዞን መድበው ልከዋቸው ነበር፡፡ በኋላም የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ሆነው ከቆዩ በኋላ ነው የሀገሪቱ ቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ መስፋፋቱን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው የቴሌኮሚኒኬሽን ሚንስትር የሆኑት፡፡ ይህን ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ደሞ የኢንፎርሜሽን ኔትወርክ ኤጀንሲን ከማቋቋም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በመምራት ላይ ስለሆኑ ዞሮ ዞሮ ከደኅንነት እና መረጃ ስራ ሳይርቁ ነው የቆዩት፡፡
ዶክተር ደብረጺዮን የማሳመን ችሎታ፣ ፖለቲካዊ ብልጠት እና የመደራደር ችሎታ እንዲሁም ሀገራዊ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ሁኔታዎችን ሰፋ አድርጎ ለማየት ትዕግስት ያጥራቸዋል ሲሉ በቅርብ የሚውቋቸው ይገልጧቸዋል፡፡ ከጥቂት ዐመታት በፊት ሚንስትር ሳሉ አንዴ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራንን ሰብስበው ሲያናግሩ መምህራኑ መንግስት ደመወዝ እንዲጨመርላቸው ጠይቀዋቸው ነበር፡፡ ደብረፂዮን ፈጣን ግን ደሞ አስደንጋጭ ምላሽ ነበር የሰጡት፡፡ “ደመወዝ አንጨምርም፤ ከፈለጋችሁ በትርፍ ጊዚያችሁ ከዩኒቨርስቲው ውጭ የማማከር ስራ እየሰራችሁ ራሳችሁን መደጎም ትችላላችሁ” ነበር ያሉት፡፡ ከህዝብ በሚሰበሰብ ቀረጥ ደመወዝ የሚከፈላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመህራን ትርፍ ጊዚያቸውን ለዩኒቨርስቲያቸው እና ለሀገሪቱ እድገት በሚጠቅሙ የምርምር ስራዎች እንዲያውሉ መምከር ሲገባቸው እውቀታቸውን ለዐለም ዐቀፍ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንዲሸጡ መገፋፋታቸው ካንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ያልተጠበቀ ነበር፡፡

አባይ ወልዱ በክልል ፕሬዝዳንትነት ይቀጥላል?
አቶ አባይ ወልዱ ከህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስለተነሱ ምናልባት በቅርቡ ድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔውን ሲያካሂድ የትግራይ ክልል ርዕስ መስተዳድርነቱን ጭምር እንደሚለቁ መጠበቅ ይቻላል፡፡ ምክንያቱ ደሞ በድርጅቱ ህገ ደንብ መሠረት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል ያልሆነ ሰው የክልሉን መንግስት ሊመራ የማይችል መሆኑ ነው፡፡ ያም ሆኖ ዶክተር ደብረጺዮን የፌደራሉ መንግስት ባለስልጣን በመሆናቸው የሕወሃት ሊቀመንበር ቢሆኑም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመሆን እድላቸው ግን ላሁኑ ዝግ ነው፡፡ ምናልባት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር አዲስ ዐለም ባሌማ ቦታውን ይይዛሉ ተብሎ እንዳይጠበቅ ደሞ በሰሞኑ ስብሰባ በማስጠንቀቂያ የታለፉ መሆናቸው መሰማቱ እድሉን ዝቅተኛ ሊያደርገው ይችላል፡፡
ሕወሃት እስካሁን ሊቀመንበሩ አዲሳባ ተቀማጭ ከሆነ ምክትሉ መቀሌ ላይ መቀመጥ አለበት የሚል ደንብ ባይኖረውም በውስጣዊ አሰራሩ ግን ይህንኑ ሊከተል እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡

አሽናፊው አንጃ
ይህ በእንዲህ እንዳለ እንግዲህ ባሁኑ ግምገማ አሸናፊ ሆኖ የወጣ የሚመስለው የአንጋፋው ፖለቲከኛ የአቶ ስብሃት ነጋ ቡድን በተለይ ከኤርትራ ጋር እርቅ እንዲፈጸም የመፈለግ አዝማሚያ እንዳለው ነው የሚገመተው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ሕወሃት በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ያሉ መምራንን እና ሌሎች ያገባኛል ባይ የትግራይ ተወላጆችን በመጠቀም ሰላምም ሆነ ጦርነት የሌለበትን እና ውሉ ያልለየለትን ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት በተለይ ትግራይ ክልልን በልማት ተጎጅ እንዳደረጋት በመግልጽ መፍትሄ እንዲበጅለት ጥሪ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ተደጋግመው መሰማት መጀመራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በርግጥም ሕወሃት ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል ከኤርትራ በኩል የሚመጡበትን አደጋዎች መዝጋትን እንደ ሁነኛ አማራጭ ማየቱ አይቀሬ ይመስላል፡፡
አሁን ዋናው ጥያቄ ዶክተር ደብረጺዮን ሕወሃትን እና ከቀውስ መውጫ ያጣውን ገዥውን ኢሕአዴግ ወዴት አቅጣጫ ይወስዱት ይሆን? የሚለው በቀጣይ ወራት የሚታይ ነው የሚሆነው፡፡

‘ የህወሃት ዝክረ ንግሥና እና የአድዋ ወያኔ ድል’ (በሃያሬ ተንለሱ)

አልበርት ኤንስታይን እንዲህ ይላል “ጥቂት ሠዎች ክሚኖሩበት ማህበራዊ አካባቢ ተፅእኖ ውጪ በተለየ መልኩ አስተያየታቸውን መግለፅ ይችላሉ። አብዛኛው ሠዎች ግን ይህን አስትያየት ማመንጨትም ሆነ መግለፅ አይችሉም።”

“Few people are capable of expressing with equanimity opinions which differs from the prejudice of their social environments. Most people are even incapable of forming such opinions.’’

የመቀሌውን የህወሃት ግምገማ አስመልክቶ የተለያዩ ግምቶችንንና መላ ምቶችን ሠማን። ህወሃት በተለያዩ አንጃዎች ስለመሠንጠቁና አደጋም እንዳንጃበበት አዳመጥን። ቅናትን ያስቆጠረው ግምገማ “ፖለቲካዊ ለውጦችን” ሊያመጣ ይችላል በሚል ቀቢፀ-ተስፋ የአንጃውን ብዛትና የእያንዳንዱን አንጃ መሪ በሥም ዘከርን። እነ እከሌ የለውጥ ሃዋሪያቶች እነ እከሌ ደግሞ አክራሪ ፀረ-ለውጥ ናቸው ስንል ፈረጅን። በሃሣብና በምኞት ታንኳ ወራጅ ወንዝ ላይ እየቀዘፍንና ከአንዱ ድብ ወደ ሌላው እየተላተምን ከረምን። በአዜብና በአባይ ወልዱ መታገድና መውረድ ሣቢያ “የመለስ ራዕይ” ተብዬው ገደል ገባ ብለን ፈነጠዝን። አንዱም ግምት ልክ አልነበረም። የባለ ብሩህ ህሊና መላ ምትም /Inteligent Hypothesis/ አልሆነም።
ይልቁንም የህወሃት ግምገማ የተሠኘው ድራማ ባለ ሁለት ስለት ጩቤ ነበር።

1. ፖለቲካዊና የወንጀል ሤራ /Political & Criminal Conspiracy/

በየአቅጣጫው እየተቀጣጠለ፣ በዓይነቱ፣ በመጠኑና በስፋቱ እየገዘፈ የመጣው ህዝባዊ ተቃውሞ እያየልና መቀልበስ ወደማይችልበት ደረጃ እያደገ በመምጣቱ፤ ይህም ነውጥ ለህወሃት የበላይነት በቻ ሣይሆን ለህልውናውም ፈተና እየሆነ መከሠቱ ነው። ይህን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ብሎም ለመደምሠስ የሚቻልበትን መንገድና ዘዴ የስብሠባው ዋነኛ አካል ነበር። ህዝባዊ ተቃውሞውን የመቀልበሱ ሃሣብ ላይ ሳይሆን መቀልበሻው ዘዴ ላይ ልዩነትን ማስተዋል ይቻላል። ይህ ተፈጥሯዊ ነው። ተቃውሞውን በመጨፍለቁ ላይ የአተገባበር ልዩነት ቢኖርም በመሠረተ ሃሣቡ ላይ ግን ህወሃት ፍፁም አንድነት እንዳለው መሳቱ ግን ፖለቲካዊ የዋህነትም ነው። ከወጤቱ መረዳት እንደተቻለው፤ በግምገማ ስም ህወሃት የተጠራው ስብሰባ ያተኮረው ባለ ሁለት ፈርጅ ስሌት ይህን ይመስላል።
ሀ). ህወሃት “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” የሚላቸው ሃይሎች ህዝባዊ መሠረታቸው እየሰፋ በመምጣቱ ሳቢያ የነርስን ጨኸት በመቀማት በተለይ “እህት ድርጅቶች” የሚላቸውን አኦህዴድና ብአዴንን የአኢትዮጵያዊነት አርማን በጊዜያዊነት በማሸከም ህዝቡን ከነዚህ “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” ተፀዕኖ ማላቀቅ፤ ወይንም እነዚሁን የማደጎ ልጆቹን ከደህንነት መዋቅሩ ጋር በማቀናጀት የጎሣንስ የእርስ በእርስ ግጭት/ Inter-tribal conflicts/ በማቀጣጠል፤ ህዝቡ የማዕከላዊ ወይም የፌደራል መንግስትን ጣልቃ ገብነት እንዲጠይቅ በማድረግ ህዝባዊ ድጋፍን ማሠባሰብ የመጀመሪያው ስልት ሲሆን፤ ይህ ካልተሣካ ግን ወደ ሁለተኛው ስሌት ይሻገራል።

ለ). የህወሃት ትርክት እንደወትሮው የህዝባዊው እምቢተኝነት መንሰዔ “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” ሤራ እንጂ ሕዝቡ የስርዐት ለውጥ ፈላጊነት አይደለም ብሎ እራሱንና አጃቢዎቹን ማሳመን ነው። ለዚህም ህወሃት ሊተገብር የተዘጋጀው የነዚህ “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” ድርጅታዊ ሰንሠለትን መበጠስ፣ በነርሱም ሰበብ በህብረሰቡ ውስጥ ተራማጅና ከገዢው ህወሃት “አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ቅዠትና ዴሞክራሲያዊ ብሄረተኝነት” አመለካከት ውጪ ያሉን የሃገሪቱን ዜጎች በጅምላ የሃይል እርምጃ በመውሰድ ማሰር፣ ማሳደድና መግደልንና ተቃውሞውን በሃይል መጨፍለቅ ነው።

2. በእምብርትነት የሤራው ጠንሳሾችና ተቀፅላዎቻቸው /Hub-and-Spok Conspiracy/

የህወሃት “ግምገማና ተሃድሶ” የማደናገሪያ ስያሜ የተሰጠው የህወሃት የሤራ መከሸኛ ስብሰባ ከላይ በቁጥር 1 ላይ የተገለፀውን ህዝባዊ ተቃውሞን የማምከኛ መርሃግብር ያሣየው የህወሃትን መሠንጠቅ ሣይሆን፤ መርሃግብሩን ተግባራዊ በማድረግ ላይ የተከሰቱን አናሣ ልዩነቶች ለማጋባትና ለዚህም አገልግሎት በሚወል አዲስ ድርጅታዊ አወቃቀርን መከለሱ ነበር። ለዚህም የተደረሰበት የመግባቢያ ሠነድ/memorandum of understanding/ የህወሃትን ድርጅታዊ ጥንካሬ ለመጠበቅና ጠላቶቹን “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” ለመምታት ምስጢራዊ እርምጃዎችንና ሤራዎችን ለማቀነባበር፤ ህወሃትን የሚመሩትን ግለሰቦች ቤተሰባዊና ጎጣዊ ማድረጉን ያካትታል። ከቤተሰብና ጎጣዊ መረቡ ውጭ የሆኑትን የአዜብም\ና የአባይ ወልዱ መታገድና መወገድ አንዱ ነው። የጦስም ዶሮ ሆነዋል። የአሁኑ የህወሃት ቤተሰባዊና ጎጣዊ መረብ ፍፁም አድዋዊ (በአድዋ ተወላጆች የተሞላ) አድርጎታል። ለዚህም ማስረጃው ከዘጠኙ የህወሃት ፖሊት ቢሮ አባላት መካከል ስድስቱ ማለትም ደብረፅዮን፣ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር፣ ጌታቸው አሰፋ(ደህንነት አለቃ)፣ አባይ ነብሶ፣ አብርሃም ተከስተና አዲሳዓለም ባሌማ ፪/፫ ድምፅ ያላችው የአድዋ ተወላጆች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሦስቱ ውስጥ ኬሪያ መሃመድ(ባሏ ከአድዋ)፣ ዓለም ገ/ዋህድ (ሚስቱ ከአድዋ የሆነች)ና ጌታቸው ረዳ(ዱርዬው ወያኔ) ተቆጣጥረውታል። ህወሃት በአድዋዎች መዳፍ እጅ ሙሉ በሙሉ ወድቋል። ከእንግዲህ የሚመሩትና የሚያሽከረክሩት አድዋዎች ሆነዋል። ህወሃት ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ፤ አድዋዎች በትግራይ ህዝብ ላይ የበላይ ሆነዋል። ዛሬ ህወሃት የአድዋ – ህወሃት ነው። የአድዋም የበላይነት ማለት ፀረ- ኢትዮጵያና አኢትዮጵያዊ የሆኑ የባንዳ ቤተሰቦቻቸውን አርማ ያነገቡ ሹምባሾች ፈላጭ ቆራጭነት ማለትም ነው።

3. የነቢያቸው “የመለስ ራዕይ” ዕጣ ፈንታ

አንዳንድ ወገኖች የአዜብና የአባይ ወልዱ መወገድ “የመለስ ራዕይ” ግበዐተ-መሬት ነው ብለው ያምናሉ። “የመለስ ራዕይ” ማለት የኢትዮጵያ ህዝብን “በብሔር፡ጭቆና” ትርክት በማደንዘዝ ወደ ዘመነ መሣፍንት ጊዜ አስተሳሰብ በመመለስ ህዝቡን በማያባራ የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ//Inter-tribal conflicts/ በመክተት በሚፈጠረው የህዝብ በህዝብ መቃቃር፣ ቂም፣በቀልና መጠራጠር መካከል የትግራይን የበላይነት ማስጠበቅ ነው። ግዙፍ ስህተተ ነው። “የመለስ ራዕይ” ማለት የትግራይን የኢኮኖሚ፣የወታደራዊና የፖለቲካ የበላይነት በጅምላ፤ የአድዋ የበላይነት በነጠላ በኢትዮጵያዊያን ላይ መጫንና የባንዳ አባቶቻቸውን ያልተሳካ ህልም የመተግበር “ደደቢት ወለድ የሽፍታ ራዕይ”ነው። “የመለስ ራዕይ” የአፓርታይዳዊው የወያኔ ዘረኛ ስርዓት አርማና መሠረት ነው። መንግስት ያለ ፖለቲካዊ አይዲዮሎጂ ስለማይኖር ይህን “ራዕይ” በተሻለና ከጊዜው እሣቤ ጋር በሚጣጣም መልኩ መቅረፅ የሚችሉ በቁ ግለሰቦችን ህወሃት በሎሌዎች መሃል ባለመኖሩ ይህን “ራዕይ” እንደ እምነት መፅሃፍት ከመደጋገም ውጭ ምርጫም አይኖራቸውም።
ሞት ለህወሃት አፓርታይዳዊው የወያኔ ባንዳዎች ሥርዐት!

የማለዳ ወግ … ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ክብር ይገባሃል !( ነቢዩ ሲራክ)

* ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ክብር ይገባሃል

ብርቱው የቀድሞ ስራ ባልደረባዬ አንጋፋው የራዲዮ ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ በሀገራችን ” አሉ ” ከሚባሉት የራዲዮ ጋዜጠኞች መካከል አንዱና ቀዳሚው ይመስለኛል። ባልሳሳት ጋዜጠኛ ነጋሽና ጋዜጠኛ አለምነህ ጎልተው የወጡትና የታወቁበት ወቅት በገልፍ ጦርነት ጊዜ ይመስለኛል። በባህረ ሰላጤው ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ሬዲዮን ትኩስ መረጃዎች በጉጉት ይከታተል የነበረ ፣ የአረቦችን አንበሳ ምሳሌ የኢራቁ የቀድሞ ፕሬዚደ ንት ሳዳም ሁሴንን አስታውሶ ጋዜጠኛ አለምነህንና ጋዜጠኛ ነጋሽን ፣ ንግስት ሰልፉን አለማስታዎስ እንዴት ይቻላል ? ድምጸ መረዋዎች ባለተስገምጋሚ ድምጾች አይዘነጉም ፣ አይረሱም …

ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ በኢህአዴግ አዲስ የግዛት አመታት ድንበር ተሻግሮ የጀርመን ራዲዮ ባልደረባ ከሆነ በኋላም ይታወቃል። በተለይም በሳምንት አንድ ቀን በሚያዘ ጋጀው የማህደረ ዜና ዝግጅት ተወዳጅነቱ ከፍ ያለ ነው ። ነጋሽ በማህደረ ዜና ጥልቀት በተሞለበት መንገድ ዜና ትንታኔውን ከሽኖና አጣፍጦ ስለሚያቀርበው ጀርመን ራዲዮ የሚያደምጥ የነጋሽን ማህደረ ዜና ሊያመልጠው የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም። እናም ብቃትና ጥራት ያለው ስራና አቀራረቡ ነጋሽን ከብዙው ጋር አስተዋውቆታል ማለት እችላለሁ። እኔ እስከማውቀው ጀርመን ራዲዮ የሚያውቅ ሰው ጋዜጠኛ ነጋሽን የማያውቅ አላጋጠመኝም ።

ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ተግባቢ ፣ ተጫዋችና ሳቂታ ነው ። ማድመጥ ይወዳል ። አድምጦ ከገባው በላይ የመግ ለጽ ክህሎት አለው ። ነጋሽ የዋዛ መልካም ሰው አይምሰላችሁ:) ነጋሽ ከሙያው ውጭ ያለው ህይዎቱ ከቤተሰቡ ጋር የተቆራኘ መሆኑን አውቃለሁ ! ነጋሽ ጥሩ ሰብንዕና ያለው ፣ ሚስት ፣ ልጆቹንና ቤቱን ፣ ወዳጅ ዘመዶቹን አክባሪ አመለ ሸጋ ስለመሆኑ እመሰክራለሁ ! ነጋሽ ጸሐፊ ፣ ዜና አጠናቃሪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም ። ባለ ተስገም ጋሚ ድምጽ ብቻም አይደለም ። ጋዜጠኛ ነጋሽን ልክ የዛሬ 7 ዓመት ቦን ጀርመን ላይ ባለችው ጎጆው ተገኝቸ ስንጨዋወት ከተመለከትኩት ፣ ከታዘብኩት እውነት በላይ ስለ ጋዜጠኛ ነጋሽ መልካም ሰብዕናና መልካምነት በቅርበት የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክራሉ !

ሰሞኑን የጀርመን ራዲዮ የጉምቱውን ጋዜጠኛ የትዝታ ምስክርነት ተንቀሳቃሽ ምስል ይዞ ባሰራጨው መረጃ እንዲህ ይላል ” ነጋሽ መሐመድ በኢትዮጵያ ራዲዮ ሰዎችን በየዕለቱ አመሻሽ ላይ ያሰባስብ እንደነበር አጫውቶናል። በእርሶ አካባቢ ምን ይመስላል? #whereicomefrom ” ሲል የጋዜጠኛ ነጋሽን ትዝታ ያጋራናል ፣ ማድመጥ መልካም ነገር ነው ! ትዝታውን አድምጨ ለወዳጄ ምስጋናና ክብር ልሰጠው ወደድኩ ! እስኪ ብዙዎቻችሁ ስለወዳጃችን ስለ ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ የሚሰማችሁንና የምታውቁትን አጋሩኝ ?

አድናቆትና ክብር ይገባሃል ወዳጄ ጋዜጠኛ ነጋሽ … !

ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 20 ቀን 2010 ዓም

መጽሃፍ ቅዱስም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የኦነግ ማኒፌስቶ ሆነ!

አገሬ አዲስ

ህዳር 20 ቀን 2010 ዓም /29-11-2017

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጠላቶቿ የማይሰብቁት ጦር፣የማይሸርቡት ተንኮል የለም።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብዙሃን የዜና መስመሮች  ለማወቅ እንደቻልነው የጀርመን ሉተራን የእምነት ተቋም በጥናትና ምርምር ስም የተከበረውን ቅዱስ መጽሃፍ የፖለቲካ መሳሪያ በማድረግ ኢትዮጵያ የምትባለው ለዘመናት የታሪክና የእምነት ባለቤት የሆነችው አገር ቀጣዩ ትውልዷ እንኳንስ ታሪኳን ስሟንም እንዳያቅና እንዲረሳ ብሎም ፈራርሳ እንዳልነበረች እንድትሆን የማድረግ ሴራ በሚያራምደው በአገር በቀሉ የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጪ(ኦነግ) ነኝ በሚለው  ቅጥረኛው ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት አባል በንቲ ኦጁሉ በተባለው ፓስተር በኩል መጽሃፍ ቅዱስን በመከለስ የጥፋት ዘመቻውን ይፋ አድርጓል።

የፈረንጆቹ የካቶሊክና የሉተራኑ የእምነት ተቋማት ኢትዮጵያን የማፈራረሱ ስራ ዛሬ ወይም ትናንትና የጀመሩት ሳይሆን ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል።ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ፖርቱጋሎች የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እምነት አጥፍተው በራሳቸው የካቶሊክ እምነት ለመተካትና አገሪቱን በመዳፋቸው ስር ለማስገባት ያደረጉት ሙከራ በብሩህ መሪዎቿና የቤተክስርስቲያኗ ካህናት ትግል ሊከሽፍ ችሏል።ከዚያም በዃላ በተከታታይ አገሪቱን ለመያዝ በሃይማኖት ዙሪያ አያሌ ሙከራዎች ብሎም ደም ያፋሰሱ ጦርነቶች ተካሂደዋል።የጣልያንን ወራሪ ጦር ታንኩን ጠበል እረጭቶ ባርኮ የላከው የካቶሊኩ ጳጳስ ነበር።ከዚሁ ኢትዮጵያን ከማፈራረሱ ጋር አንዷ ዒላማ የሆነችው  ከአገር ወዳድ ጎን ለጎን  እንደ አንድ ወታደራዊ ተቋም ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የቆመችውና በጦር ሜዳ ላይ የዋለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ነበረች፤ አሁንም ነች።ቤተክርስቲያኗን ማፈራረስ አገሪቱን ለማፈራረስ የሚደረገውን ሙከራ ሁሉ ውጤታማ ያድርገዋል ብለው ስለሚገምቱ የግንባር ጦራቸውን የሚያሰልፉት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ነው።

የኢትዮጵያ አንድነትና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ መሆናቸውን  አይክዱም።የሁሉንም ጎሳ ተወላጅ  በእምነት ሃረግ አስተሳስራና  ሰብስባ፣ በዛፍ፣በወንዝ፣በቋጥኝና ተራራ.. ያምን የነበረውን ከጣኦት እምልኮ አላቃ፣በአንድ አምላክ ስም አጥምቃ፣የአንድ አገር  ብሔራዊ ስሜትን  ያጎናጸፈች፣ የሚግባባበትን ቋንቋ አዳብራ ያሰራጨች፣ያስተማረች፣ከትንሽነት ትልቅነትን የዘከረች፣ ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነች የሃይማኖት ተቋም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ነች።

ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ በፊት የአምላክን መኖር የተቀበለች፣በሕገ-ልቦና፣በብሉይ ኪዳን ሕገ-ኦሪትና በአዲስ ኪዳን የወንጌል ሕገ-ክርስቲያን እምነት ከፈጣሪ ጋር ተሳስራ የኖረች አገር ናት።ለኦሪታውያን የተሰጠውን ያምላክ ቃልኪዳንና ሕግጋት ለሰፈረበት ጽላት(ታቦት) (arc of the convenants)ማረፊያ፣ከክርስቶስም እልፈት በዃላ ግማደ መስቀሉ የተገለጠበትና ያረፈበት አገር በመሆኗ ልዩ ያደርጋታል።ቅናት ያደረባቸው ነጮች  ያንኑ ያምላክ ስጦታ ለመንጠቅ ያላሰለሰ ሙከራ እንዳደረጉ አይካድም።ይህ ትልቅ የእምነት ትርጉምና በገንዘብ የማይተመን ዋጋ ያለው ቅርስ በአክሱም ገዳም ውስጥ መኖሩ ይወራል  እንጂ በጣልያኖች ወይም በእንግሊዞች ተሰርቆ ላለመውጣቱ ወይም አሁን በስልጣን ላይ ያለው ያገሪቱን ቅርስና የታሪክ ንብረት መዝረፍና መሸጥ ልማዱ ያደረገው የወያኔ ቡድን ላለመሸጡ ማስረጃ የለም።  አልፎ አልፎ ጽላቱ እንግሊዝ አገር ፣ሰኮትላንድ ውስጥ እንደሚገኝ የሚናፈሰው ወሬ ካለምንም ፍንጭ የሚነገር አይደለም። በአክሱም  መኖሩንም በዓይኑ አይቶ ያረጋገጠ  የለም።እንኳንስ በቅርበት የዘረፋ ቀጠና ውስጥ ባሉት የአክሱም፣የላሊበላ፣የግሸን ማርያም፣የሓይቅ እስጢፋኖስ፣የዋልድባ ገዳማት ቀርቶ በርቀት ባሉት የደብረሊባኖስ፣የተልባበ ማርያም፣የተንታ ሚካኤል ደብርና ገዳማት ውስጥ ያሉትም ቅርሶች ከወያኔ ዘረፋ አልዳኑም። በወያኔ ጊዜ አይደረግም አይባልም፤እንኳንስ ቅርስ አገርም የሚሸጥ ሸቀጥ ሆኗል።

ቅኝ አገዛዝ በተከታታይ ደረጃ እንዲሁም መልክ እያደገ የመጣ ሂደት ነው፤በመጀመሪያ አገር በማሰስና በፍለጋ ስም(Expedition/Exploration) ሰላይ ቀሳውስቱን በማሰማራትና በማስፈር እንዲሁም በንግድ ልውውጥ ለወረራ ማደላደል፣

ቀጣዩ  በወታደር ሃይል በመውረር አገርን በቅኝ ግዛትነት መያዝ(Anexetion/colonization)ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ሃብቱን መዝረፍ ብቻ ሳይሆን ያገሩን ሕዝብ እንደ ዕቃ እየቀጠቀጡ እንደ እንስሳ ለጉመውና በሰንሰለት አስረው፣ ባርያ አድርጎ መሸጥ መለወጥ።

አሁን ባለንበት ዘመን ደግሞ ኔዎ ሊበራል የፖለቲካ ፍልስፍና ግሎባላይዜሽን(Globilization) በሚል ፈሊጥ ነጋዴዎችን በማዝመት የአገርን የተፈጥሮ ሃብት መመዝበር፣ ለም መሬት እየያዙ ለአገሩ ሕዝብ ገበያ የምግብ ፍጆታ የማይውሉ  ለውጭ አገር ገበያ የሚሆኑ የቅንጦት ምርቶችን አበባና ትምባሆ የመሳሰሉትን በማምረት መሬትና ጅረቶችን በኬሚካል መበከል።በአገሪቱ ሃብትና የሕዝብ ጉልበት የተቋቋሙ የምርት ተቋማትን በርካሽ ዋጋና በአገር ውስጥ የባንክ ብድር እየገዙ ኢንቨስትመንት (investment)በሚል ጭንብል በመቆጣጠር  የምርት ውጤቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ገቢው እንደኮበለለ እንዲቀር ማድረግ። የአገር ነጻ ኤኮኖሚ እንዳያድግና ጥገኛ እንዲሆን መሰናክል መፍጠር፤ ለዚያም አገር በቀል ተባባሪዎችን ስልጣን ላይ በማስቀመጥ የእጅ ዙር አገዛዝ (Neo-colonialism) ሕጋዊነት እንዲኖረው ማድረግ የዘመኑ ስልት ሆኗል።ከዱሮው የሚለየው ወታደር ሳያዘምቱ፣ጥይት ሳይተኩሱ በባንዳዎች ፊርማ የጸደቀ ስምምነት መሆኑ ብቻ ነው። የሚመረቱ ጥቂት ምርቶች ቢኖሩ ገቢያቸው ለልማት ሳይሆን በሚቀሰቅሱት የጎሳ ግጭት ምክንያት እነሱ በሚያመርቱት የጦር መሳሪያ ግዥ ላይ እንዲውልና ይበልጥ ድህነትና ቀውስ እንዲከሰት ማድረግ ከመሰረታዊው የቅኝ ግዛት ወረራ ዓላማ የተለዬ  አይደለም።

ሰላማዊና ረዳት መስለው በመግባት ውስጥ ውስጡን እየቦረቦሩ በእምነት የተሳሰረውን ሕዝብ ማለያየቱ ከጣልያኖች ወረራ በዃላ በተለይም ላለፉት ሃምሳ ዓመታት እያደገ የመጣ መሆኑን ታዝበናል። በአሜሪካኖች፣በጀርመኖች፣በስዊድኖች፣በእንግሊዞች የካቶሊክ፣የፕሮቴስታንት ልዩ ልዩ ሴክቶች እምነት ለበስ የስለላ ድርጅቶች ያደረሱት መከፋፈል ውጤቱ አሁን የምናዬው ሃቅ ነው።ድሃውን ሕዝብ በድህነቱ፣የከፋውን በብሶቱ፣ባለው ደካማ ጎን እየገቡ አገሪቱን ለማፈራረስ ካላቸው ዓላማ ጎን እንዲሰለፍ በመጀመሪያ የራሱ አገርና የማንነቱ መግለጫ የሆነውን፣አያት ቅድመ አያቶቹ  አክብረው የያዙትን ሃይማኖት፣ባህልና ታሪክ እንዲጠላና እንዲርቅ ብሎም ለጥፋት ተባባሪ እንዲሆን አድርገውታል።የአንድ አገር ሕዝብ የሚተሳሰርባቸውን እሴቶቹን እየናዱና እየበጣጠሱ ማራራቅ ብሎም እርስ በርሱ እየተጋጬ  ሃይሉ መንምኖ ለወረራ አመቺ ሆኖ የሚገኝበትን ስልት የመቀየሱ ተግባር በታሪክ  የታዬ ተደጋጋሚ ድርጊት ነው።ሊግባባ የሚችልበትን ቋንቋ እንዳይናገር፣የጋራ ምልክትና የማንነቱ መግለጫ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ እንዳያውለበልብ፣የስነምርምርና ስነጽሁፍ ባለቤት የሚያደርገውን የራሱን ፊደል አጥፍቶ በባእዳኑ ፊደል እንዲተካና ጥገኛ እንዲሆን፣ በአጠቃላይ ታሪክ አልባ ማድረጉ አገር የማጥፋቱ ሂደት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው።

ለዚህ ደባ የማይመቸውንና አገሪቱን አሳልፎ ያልሰጠውን ሕዝብ በተለይም አማራውን ለማዳከም ሲሉ ከሃይማኖቱ ጋር ያለውን ትስስር በቅድሚያ መበጠስ እንዳለባቸው በማመን የእምነቱን ተከታይ ዃላቀርና አውሬ አስመስለው በመሳል ሌላው ወገኑ እንዲፈራውና እንዲጠላው ብሎም እንዲርቀው ያላቋረጠ ቅስቀሳና የተሳሳተ ስብከት ሲነዙ ኖረዋል።በአሁኑ ስርዓት የነጮቹ ሃይማኖት በተለይም የፕሮቴስታንቶቹ ካለምንም ቁጥጥር በፈለጉበት ቦታ የመስፋፋት እድልና ነጻነቱ የተጠበቀ  ሆኗል።በቅርቡ በዚሁ በፈረንጆቹ ሃይማኖት ተኮትኩቶ ያደገው   ጠ/ሚኒስትር ነኝ ባዩ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለአሜሪካ ሚሲዮናውያን ከስድስት ሽህ በላይ የሚሆኑ የፕሮቴስታንት ተቋማት/የጸሎት ቤቶች እንዲመሰረቱ ፈቃድና ተስፋ ሰጥቷቸዋል።ይህ ትልቅ የወረራ ውል  በቅድሚያ  ተፈጻሚ የሚሆነው በፈረደበት የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲሆን ወደ ሌሎቹም ያገሪቱ ክፍሎች እንደ እባብ እየተሳበ የማይደርስበት ሁኔታ የለም።የደቡብም ሆነ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለፈጣሪው እንግዳና ባዳ አይደለም፤በሚያምንበት መንገድ አምላኬ ነው ከሚለው ጋር ሲገናኝ የኖረ ሕዝብ ነው። አሁን የሚፈልገው ቢኖር የኑሮ ሸክሙን የሚያቃልልለት፣ሰብአዊና የዜግነት መብቱን የሚያስከብርለት፣ልጆቹ ለቁም ነገር የሚበቁበት፣ህክምናና ትምህርት የሚያገኝበት ፣ከእርሃብ የሚገላገልበት ዘመናዊ እርሻና  የሚሰማራበት ልዩ ልዩ የስራ መስኮች  እንዲፈጠሩለት፣ሌሎች አገሮች ከደረሱበት የዕድገት ደረጃ ለመድረስ የሚያበቃው  ስርዓት እንዲሰፍን እንጂ ፈረንጆች ሰብስበው የሚያደነቁሩበት የጸሎት ቤት እንዲስፋፋበት አይደለም።

የፈረንጆቹ ዓላማ ደሃውን ሕዝብ ስትሞት  የገነት ቤት ባለቤት ትሆናለህ በሚል ፈሊጥ በህይወት የያዘውን የመሬትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት እንዲያጣ የማድረግ ብልሃት ነው።ይህንን ብልሃት ከደረሰባቸው በዃላ የተገነዘቡት አንዱ የነጻነት ታጋይ የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ቄስ ዲስሞንት ቱቱ እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል”ነጮቹ እኛን ከመከራ ለማዳንና ለመርዳት የመጡ መስለው ሰበኩን፤እኛም በቀና መንፈስ ተቀበልናቸው።ውስጥ ለውስጥ አለያይተው እርስ በርሳችን እንድንጋጭ፣በአንድነት እንዳንቆም አደረጉን። መጽሃፍ ቅዱስ ሰጥተውን ዓይናችንን ጨፍነንና ወደላይ አንጋጠን  አምላክ! አምላክ! ስንል ከስር መሬታችንን ወሰዱት፤ የተፈጥሮ ሃብታችንን፣ማዕድናችንን መዝብረው ወደ አገራቸው አስኮበለሉት፤ ዓይናችንን ገልጠን ወደታች ስንመለከት የተረፈ ነገር የለም፤ከመጽሃፉ ቅዱሱ በቀር  የያዝነው ነገር የለም፤ባዶአችንን  አስቀሩን፤በአገራችን የበታችና ሁለተኛ ዜጋ፣የበይ ተመልካች  አደረጉን።”በማለት የነጮቹን መሰሪ ስራ አጋልጠውታል።

ኢትዮጵያም  በዘመነ ወያኔ የውጭ ባለሃብቶች መፈንጫ ሆናለች።የፈረንጆቹ የካቶሊክና የፕሮቴስታንቱ ሃይማኖት እንዲስፋፋ ሲደረግ  አገር በቀሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ግን እንዲከስም ፣ ተቋሙ ሃይማኖቱን በማያስከብሩ በካድሬ ጳጳሳት ተይዞ እድገቱ እንዲገታና አቅመቢስ እንዲሆን ተደርጓል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከላይ እስከታች ቆብ በጫኑ የወያኔ ሹሞች ታግታለች።ምዕመናን የሚሰበሰቡባት ሳትሆን ገንዘብ የሚሰበሰብባት የንግድ ተቋም ሆናለች።ለሃይማኖታቸው የሚቆሙት አባቶች ፣ቀሳውስትና ዲያቆናት የጥቃት ሰለባዎች ሆነዋል። በጥቅምና በፍርሃት ታውረው ለወያኔ ስርዓት ቡራኬ ከሚሰጡት በስተቀር ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው በቤተክህነቷ አስተዳደር ቀርቶ በደጀ-ሰላም ዙሪያ እንዲውሉ አይፈቀድላቸውም።እጣ ፈንታቸው እስራትና ስደት ሆኗል።

ከኢትዮጵያ ባህልና ታሪክ ጋር ተሳስሮ የኖረውም የእስልምና ሃይማኖት ከዚሁ ደባ አላመለጠም።ለእምነት መብታቸው የተነሱትን አትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ስርዓቱ በአክራሪነትና በሽብርተኛነት ፈርጆ፣ ሲገል፣ሲያቆስል ፣ሲያሳድድ፣የቀሩትንም በየእስር ቤቱ አጉሮ ሲያሰቃይ ኖሯል።አሁንም እያሰቃዬ ነው። በመረጧቸው መሪዎቻቸው ምትክ የራሱን ስልጣን አስከባሪ አድር ባዮች ተክቶ እርስ በርሳቸው እንዲጋጩ ሆነዋል።በአገር ወዳዶቹ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጀርባ በስማቸው የሚነግዱና የሚንቀሳቀሱ የኦነግ አክራሪ ሙስሊሞችም እንደ ፕሮቴስታንቱ ፓስተር ኦጀሎ ተነስተው ከክርስቲያኑ ወገኖቻቸው ጋር አብረው እንዳይሰለፉ የሚያደርጉት ጥረት አገር ከማፈራረሱ ሴራ ጋር የተያያዘ ነው።

ኢትዮጵያ እራሷን ጠብቃ ሌሎቹም ያፍሪካ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ መዳፍ እንዲወጡ ባደረገችው ያላሰለሰ ትግል የነጮቹ ወራሪ መንግሥታት ዋናዋ ጠላታቸው አድርገዋታል።ጥርሳቸውን ከነከሱባትና የበቀል ክንዳቸውንም ካነሱባት ውለው አድረዋል።

በቀጥታ ወረራ ሊሳካላቸው ያልቻለውን በተዘዋዋሪ አገር በቀል ባንዳዎችን ስልጣን ላይ በማውጣትና በማጠናከር ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሁለገብ ዘመቻ ከፍተዋል፤ ከሚሰሩት የመበታተን ስራ አንዱ ይህ ሰሞኑን በኦነግ ቄስ ነኝ ባይ ግለሰብና በአለቆቹ በጀርመን ሉተራን ቄሶች ትእዛዝ ተከልሶ የወጣው መጽሓፍ ቅዱስ ነው።በዚህ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ለዘመናት በሁሉም ሲሰበክና ተቀባይነት ኖሮት የዘለቀው የኢትዮጵያንና የፈጣሪን ግንኙነት የሚያወሳውን የተደጋገመ ታሪክ አውጥቶ በሌላ ኩሽ በሚል ስም  እንዲተካ ተደርጎ ቀርቧል።ከአርባ ስምንት ጊዜ በላይ የተጠቀሰው ስሟ በሌላ ተተክቶ እንዲጠራ ተደርጓል።ዘመቻው እንኳንስ በአገር ደረጃ በስምም ደረጃ እንዳትታወቅ የማድረግ የስነልቦና ጦርነት ነው።ኢትዮጵያን እንደ አገርና ለፈጣሪ ቅርበት ያለው ሕዝብ የሚኖርባት አገር እንደሆነች የክርስትና እምነት ብቻ ሳይሆን የሙስሊሙም፣የአይሁዱም፣የቡድሃውም እምነት ተከታዮች ከቅዱስ መጽሃፍቶቻቸው ውስጥ  የሰፈረ ሃቅ መሆኑን የሚመሰክሩት  ነው።የእነዚህ የተለያዩ እምነት ተከታዮች እምነታቸውንም በነጻነት የሚከተሉባት አገር ናት።ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በኩሽ መለወጥ ማለት ኢትዮጵያ የሚለውን ስም የተቀበሉትን  የእያንዳንዱን እምነት ከጥያቄ ውስጥ ማስገባትና ሁሉንም  ቅዱስ መጽሃፍትን መከለስ ማለት ነው።

ኢትዮጵያ የክርስቲያን አገር ብቻም ሳትሆን የአይሁድ በተለይም  የእስልምና  እምነት ተከታዮች እምነታቸውን ያዳኑባት፣ ያስፋፉባትና ያሰራጩባት ብሎም በነብዩ ሞሃመድ የተመሰከረላት የክርስቲያን አገር በመሆኗ አትዮጵያዊው ሙስሊም የሚኮራባትና የሚጠብቃት አገሩ ናት።ከዚያም አልፎ ተርፎ በመጀመሪያው ሰዓት የነብዩ ሞሃመድ ተከታይ፣ቃል አቀባይና የሶላቱ አብሳሪ የነበረው የቢላል አገር ነች። እስላምና ክርስቲያኑ አገሩ በጠላት ስትወረር  ሃይማኖትና ቋንቋ ሳይለየው እጅ ለእጅ ተያይዞ፣ትከሻ ለትከሻ ገጥሞ አብሮ እንደተዋጋውና ህይወቱን በጦር ሜዳ አሳልፎ እንደሰጠው ሁሉ በሰላም ጊዜ ሃይማኖቱ ሳያግደው ተጋብቶ ፣ወልዶ ከብዶ የኖረ ሕዝብ ነው። የክርስትና እምነት ሲጠቃ ፣የእምነቱ መጽሃፍ ሲበረዝ ፣ሙስሊሙ ለምን ብሎ ከሚጠቃው ወገኑ ጎን ይሰለፋል እንጂ አያገባኝም አይልም።።ነገም የራሱ የእምነት መጽሃፉ፣ቅዱስ ቁርአን ስለኢትዮጵያ በሚገልጸው የነብዩ ሙሃመድ የአደራ መልእክት የተነሳ  ሊበረዝበትና ሊከለስበት የማይችልበት ዋስትና የለውም።በዚህ መልክ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተመዘዘው ሳንጃ በራሱም ላይ የተመዘዘ ነው።ኢትዮጵያ ከሌለች ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን እስላሙም፣ይሁዳውም፣ካቶሊኩም፣ፕሮቴስታንቱም፣አማኙም ፣አላማኙም አገረቢስ ይሆናል።ዛሬ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኑና በእምነቱ ላይ የተመዘዘው የጥፋት አዋጅ ነገ በተራው የሌላው እምነት ተከታይ እጣ ፈንታ ይሆናል።ስልቱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊ የሆኑትን ሁሉ በየተራ የማጥፋት ስልት እንደሆነ መረዳት ይገባል።ኦነግ ከፍላጎቱ ውጭ የሆነውን የኦሮሞ ተወላጅ በተለይም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን በጠላትነት ፈርጆ እንደሚያጠፋው ጥርጥር የለውም።ኦሮሞ ነው ብሎ አይምረውም።ምናልባት እምነቱን ክዶ ወደ ኦነግ የጥፋት ፖለቲካ ከቀየረ ይተርፍ ይሆናል።ያም መትረፍ ከተባለ ነው።

ከዚሁ ከኦነግ የጥፋት ዘመቻ ጋር የተያያዘው ሌላው በስልጣን ላይ ያለው አገር አጥፊው ቡድን የሚነዛው ዘመቻ ነው።ወያኔም አገር ለማፈራረሱ ዓላማው የመጀመሪያ የክተት አዋጅ ያወጀበት በዚሁ  ኦነግ በተነሳበት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ላይ ነው።ይህ እምነት ፍጹም ኢትዮጵያዊ ፣በኢትዮጵያውያን የእምነት አባቶች  ፍልስፍናና ስርዓት የዳበረ፣ ከሕዝቡ ታሪክ፣ባህልና ስነልቦና ጋር በማይላቀቅ ድርና ማግ የተወሳሰበ በመሆኑ የኢትዮጵያ ደጀን ሆኖ ስለሚቆጠር የጥፋቱ እርምጃ ያተኮረው በእምነቱ ላይ መሆኑን የወያኔ መሪዎች ሳይደብቁ በይፋ ገልጸውታል።ለአገሪቱ አንድነት የጀርባ አጥንት ነው ብለው የሚቆጥሩትንና የሚፈሩትን “የአማራውን ማህበረሰብና የኦርቶዶክሱን እምነት አከርካሪውን ሰብረነዋል” ሲሉ በአደባባይ ተመጻድቀዋል። የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ አማራም መኖሩን ዘንግተውታል።በአማራው ክርስቲያን ላይ ጦር ሲመዘዝ አማራ የሆነው ሙስሊም ወይም ፕሮቴስታንት ወይም ካቶሊክ በሰላም ይኖራል ማለት አይደለም።ባማራነቱ የጥቃቱ ሰለባ ይሆናል። የዘነጉት ነገር ቢኖር እንወክለዋለን የሚሉት አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ መሆኑን ነው።እሱንስ አክርካሪቱን ሰብረውታል ?ወይስ ሊሰብሩት የቀን ቀጠሮ ይዘውለታል? የትግራይ ተወላጆችስ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሃይማኖታቸው ሲነካ ለምን ዝም አሉ?ዘር ከእምነት ይልቃል ሆኖባቸው ይሆን?

መጽሃፍ ቅዱሱን በመከለስ ስም የተደረገውን ይህንን የነጮችና የተባባሪዎቻቸውን  የጥፋት ዘመቻ ሁላችንም ልንቃወምና ልናወግዝ ይገባል።ይህ የፖለቲካ ድርጅት የፖሊሲ ጥያቄ ሳይሆን፣ የአገርና የሕዝብ ታሪክና ህልውና ጥያቄ ነው።ስለዚህ ለእውነትና ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመ የፖለቲካ ድርጅት ሁሉ ሊያወግዘውና ሊቃወመው ይገባል።አገር ከሌለች ስለለውጥ የሚናገሩበትና  ለስልጣን የሚታገሉበት ቦታ አይኖርም።

ለአገራቸው አንድነት ለእውነትና ለፍትሕ የቆሙ የሁሉም እምነት ተከታይ፣በተለይም የፕሮቴስታንት ተከታይ የሆነ ሊያወግዘውና ከዚህ አይነቱ መርዛማ ትምህርት እራሱን ሊያርቅ ይገባዋል። ይህ የኦነግ ቄስ ያቀረበው የክህደትና ክለሳ ስራ የፕሮቴስታንት ተከታዮችና በተለይም የኦሮሞ ልጆች ሊኮሩበትና ሊያከብሩት የሚገባ ሳይንሳዊ ግኝት አይደለም፤የአዋቂነት ውጤት ሳይሆን  ስውር የነጮችን  ገመድ በአንገት ላይ ጠምጥሞ መጓዝና እራስን ለባርነት አሳልፎ መስጠት ማለት ነው።ስለሆነም በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ የኦሮሞ ተወላጆች  በስማቸው የሚደረገውን አገርና እምነት የማጥፋት ሙከራ ሊታገሉት ይገባል።

ምንም እንኳን ኩሽ የሚለው ቃል ከእብራይስጥ ቋንቋ የጥቁር ሕዝብን ነገድ የሚያመለክት  ቢሆንም ፣ያ ስያሜ ደግሞ ከሁሉም በፊት በስነልቦና፣በኦሪትና(ብሉይ ኪዳን) በአዲስ ኪዳን እምነት ከፈጣሪ ጋር የቆዬ ግንኙነት የነበረውን አገርና ሕዝብ አመላካች ነው።ለዚያ ደግሞ የስርዓትና የእምነት ባለቤት የሆነችው  የጥቁር አገር ኢትዮጵያ ናት።መጽሃፍ ቅዱስ(ብሉይ ኪዳን) ከሂብሩ ወደ ግሪክ የተተረጎመው  ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3-1ኛው  ምአተ ዓመት(BC)ሲሆን ሴፕቷጊንት(Septuagint) በሚል ሲሰየም የተጻፈውም በኮይን(Koine) በተባለው የግሪክ ቋንቋ ነው።መጽሐፍ ቅዱስ በተከታታይ በተለያዩ ጊዜያት በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ በተለያዩ ተርጓሚዎች ተርጉሟል።አዲስ ኪዳን በመጀመሪያው ክፍለ-ዘመን ላይ ወደ ግሪክ የተተረጎመ ሲሆን ከዚያ በፊት ብሉይ ኪዳንን  ግሪኮች ሲተረጉሙት ኩሽ የሚለውን የጥቁር የነገድ አጠራርና ስያሜ  ለመግለጽ ኢትዮጵያ (የተቃጠለ ፊት ያለው ሕዝብ)ብለው ተርጉመውታል።ይህ የጥቁር ሕዝብ የሚኖበትም አገር በነገዱ ስም ኢትዮጵያ ተብሎ ለመጠራት በቃ።ይህም ስያሜ ላለፉት ብዙ ዘመናት ጸንቶ ለእኛ ትውልድ ተረፈ።ለወደፊቱ ትውልድ እንዲተርፍ ማድረግ የአሁኑ ትውልድ ድርሻ ነው።ይህንን አጠራር ፈረንጆቹም ተቀብለውት ኖረዋል።አሁን ኩሽ የሚለው ስያሜ ከቀረ ከሁለት ሽህ ዓመት በዃላ ተመልሶ ማምጣቱና መጽሐፍ ቅዱሱን መከለሱ ለእምነቱ ጥራት ታስቦ ሳይሆን በሚጠሏትና ለማፈራረስ በሚፈልጓት አገር ኢትዮጵያ በሚለው ስም ስለተተካ ብቻ ነው።ኩሽ የሚለው ቃል ኢትዮጵያ በሚለው ፈንታ በጀርመን ወይም በእንግሊዞች በሚለው ቢተካ ኖሮ ስህተት ነው ብለው ለማረም አይነሱም ነበር።

የሰሞኑ የካቶሊኮች ውጣ ውረድ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የካቶሊክ ቀሳውስቶች ኢትዮጵያን በማፈራረሱ የተረባረቡትን ወያኔንና ሻእብያን ለማስታረቅ ከላይ እታች እያሉ ነው።በወያኔ ጥያቄ፣በቫቲካን ትዕዛዝ የምስራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ማህበር የተባለው ድርጅት በሰላምና እርቅ ሰበብ በመካከላቸው ያለውን የጥቅም ቅራኔ አሶግደው ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉበት፣ በአንድ ግንባር እንዲሰለፉ ለማድረግ በአሜሪካና እንግሊዞች የተደገፈውን  ስልት ተግባራዊ ለማድረግ የሚስማሙበትን የእርቅ ሃሳብ ይዘው አሥመራና መቀሌ ገባ ወጣ በማለት ላይ ናቸው። እነዚህ ጳጳሳት ላለፉት ዓመታት ሁለቱም አምባገነንና ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች በሚቆጣጠሩት መሬት የሚኖሩ በሽህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ደም ሲፈስ፣በሚሊዬን የሚቆጠሩ ሲፈናቀሉና ሲሰደዱ፣በሽዎች የሚቆጠሩ በየእስር ቤቱ ሲሰቃዩና ሰብአዊ መብታቸው ሲደፈር፣ በአምላክ ምስል የተፈጠረው የሰው ልጅ በነዚሁ ጸረ ሃይማኖት በሆኑት ቡድኖች  ለመከራ ሲጋለጥ ምንም ያልተሰማቸውና ለምን ይሆናል ብለው ያልጠየቁ የካቶሊክ ቀሳውስት ክብደት የሰጡትና የተጨነቁበት ጉዳይ ቢኖር የሁለቱ አምባ ገነን ቡድኖች መራራቅ ነው። ብዙ አትዮጵያውያን ደማቸውን ያፈሰሱበትና መስዋእት የሆኑበት የባድሜ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት ያደረጉት የሰላም ጥረት አልነበረም።ይባስ ብለው የግጭቱ ሽፋን የሆነውን የባድሜን መሬት ለሻእብያ የእርቁ ገጸ-በረከት እንዲሆን ቀሳውስቱ ያቀረቡት አንዱ ሃሳብ መሆኑ ይፋ ሆኗል።አሁን ለዚህ እሩጫ ያነሳሳቸው ነገር በሁለቱም አምባ ገነኖች ላይ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከቀጠለ ሁለቱ የነጮቹ ተወካይ ቡድኖች ከስልጣናቸው ሊወገዱ ስለሚችሉና በሕዝቡ መካከል የተከሉት  የጥላቻና የልዩነት ግምብ ተደርምሶ ሕዝቡ የተቀማውን አንድነት አስመልሶ ኢትዮጵያ ሳትፈራርስ በአዲስ ስርዓት ፈረንጆቹ እንደልባቸው የማይፈነጩባት ጠንካራ አገር ሆና ትቀጥላለች፤ሌላውም የአፍሪካ አገር እንደ ቀድሞው የሷን ፈለግ ይከተላል የሚለው ስጋት ነው።

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ስርዓት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቀውስ ውስጥ ተነክሮ ይገኛል። መሪዎቹ ቡድን ለይተው እርስ በራሳቸው እየተወነጃጀሉ የስልጣን ሽኩቻ ገጥመዋል።በዚህ ሽኩቻ አንዱ የበላይ ቢሆን ሌላው እንደማይተኛና ሁሉም የስርዓቱ ወንጀለኞች በመሆናቸው ንጹህ ሆኖ የሚተርፍ እንደማይኖር የታወቀ ነው።የቅደም ተከተል ጉዳይ እንደሆነ የሚያመላክቱ ፍንጮች እየታዩ ነው። ድርጅቱ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ የነበሩና እስከ አሁን ድረስ በድርጅቱ ውስጥ ያሉት ሁሉም  በሙስና የተጨማለቁ፣የግድያ ወንጀል የፈጸሙ፣በሕዝብ ላይ እልቂት (ጀኖሳይድ)ያከናወኑ፣የአገር ዳር ድንበር አሳልፈው የሰጡ፣ብሔራዊ ክህደት የፈጸሙ ናቸው።በየጊዜው መናቆራቸው በስልጣን ውጣ ውረድ ምክንያት እንጂ በዓላማ ልዩነት አይደለም።  ከውስጣቸው ደፍሮ እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚል አይገኝም።ለዚህ ቀውስ የዳረጋቸው የሕዝቡ አልገዛም ባይነት ነው።የሕዝቡ ጥያቄ እከሌ ወርዶ እከሌ ይሾም አይደለም፤የእነሱ መስማማት ወይም  መጣላት የሕዝቡን ጥያቄ አይመልስም።የሚፈልገው  ለውጥ እስካልመጣ ድረስ የሕዝቡ ትግል ይቀጥላል።

የነጮቹ መንግሥታት በሚፈልጉት መንገድ የወያኔ ስርዓት ማንሰራራት ካቃተው ሌላ አማራጭ መፍጠራቸው አይቀርም።ወያኔ ጠፍጥፎ በተቃዋሚ ስም በግምጃ ቤቱ ካስቀመጣቸው ውስጥ አንዳንዶቹን ወደ መድረኩ እንዲወጡ በማድረግ፣ከውጭም በተቃዋሚ ስም የነጮቹን ጥቅም የሚያስጠብቁ “ነጭ አምላኩ” የሆኑትን ቡድኖችና ምሁራን በማካተት የፓርላማ ወንበር እንዲያገኙ በማድረግ በስም የተለዬ  መንግስት ለመመስረት ይፈልጉ ይሆናል።ለዚያም ከአንዳንዶቹ የድርጅት መሪዎች ጋር በድብቅ ውይይት ማካሄዳቸው ታውቋል።ያ ከሆነ ደግሞ በአዲስ ጉልበት አገራችን ስትታሽ ትኖራለች ማለት ነው።      ይህም ካልሰራላቸው ትግራይንና ኤርትራን በማቀላቀል ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ቀድሞ ያሰቡት የትግራይ ትግርኛ መንግሥት ማቋቋም ይሆናል። የሚፈልጉትም ሌላው በየፊናው ተበታትኖ በደካማ አቅሙ ሊቋቋም የማይችለው የእጅዙር አገዛዝ መረብ ውስጥ እንዲወድቅ ስለሆነ በዚህ መልኩ እንዲጠናቀቅ እንደሚያደርጉ ማሰቡና መዘጋጀቱ ብልህነት ነው።

ከዚህ ሁሉ ቀውስ ለመውጣት ያለው ብቸኛ አማራጭ አገር ወዳድ የሆነው ሃይል በየጎሳው መሰለፉን ትቶ፣ የፖለቲካ መስመር ልዩነቱን ወደ ጎን አስቀምጦ አገር በማዳኑ ላይ ሃይሉን በማስተባበር መታገል ብቻ ነው።የየጎሳው እኩልነት የሚረጋገጠውና  የፖለቲካ ጥያቄው መልስ የሚያገኘው በራሱና በሕዝቡ ብቻ የሚተማመን በፍልስፍና እና በእውቀት ላይ የተመሰረተ መርሃ ግብር ያለው፣በሁለመናው የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስቀድም የፖለቲካ ድርጅት በሕዝቡ ምርጫ ስልጣኑን ሲረከብ ብቻ ነው።ለዚያ ደግሞ አንድ ብቻ ሳይሆን ከሶስት ያልበለጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖር አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ የምርጫ ምህዳሩን ያሰፋዋል።እነዚህ ፓርቲዎች በመስመር ቢለያዩም በአገር ጥቅምና አንድነት ላይ ግን በአንድነት የሚቆሙ መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር በርቀት ሳይሆን በአገር ውስጥ ሆነው  የተበታተኑትን ሕዝባዊ ትግሎች ማያያዝና መምራት ይጠበቅባቸዋል።የፖለቲካ ድርጅቶቹም ሆኑ ለውጥ ናፋቂው ኢትዮጵያዊ  አደገኛውን የጎሳ ፖለቲካ መዋጋት ለስርዓት ለውጡ መሰረት መሆኑን ተረድተው የሚገባውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። አሁን በቡድን ተከፋፍሎ በተበታተነ የጭፍራ መልኩ የሚደረገው ትግል ለውድቀት እንጂ ለድል እንደማያበቃ ሊገነዘቡት ይገባል።

ኢትዮጵያን ከተከፈተባት ዘርፈ ብዙ ጥቃት እንከላከል!

አገሬ አዲስ

እንዲህና እንዲያ ሆነ። አሞራው በረረረ ቅሉም ተሰበረ

ከሥርጉተ ሥላሴ 29.11.2017 ዙሪክ ሲዊዘርላንድ

„እንዳገኘ የሚናገር ሰው ራሱን ያስጠላል፤ ለቃሉም መወደድ የለውም። መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ 20 ቁጥር 19“

ዶር ደብረጽዮን ገብረ ሚኬኤል የህውሃት ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ታወቀ። የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ ህልመኛዋ ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንዲሁም የቆዳ መልሱ ህልመኛ የአቦይ ስብሃትም የወንድም ልጅ ህልም እንዲህና እንዲህ ሆነ። አሞራው በረረ ቅሉ ተሠበረ።

ምን እንጠብቅ?

ህጻናትን ገድሎ የሚፎከር አዲስ ተዋናይ? የወጣቶች የእርድ ሊኳንዳ ቤት የሚከፍት አዲስ ቢላዋ? ትውናው የኢትዮጵያ ሞት ወይንስ? ሰዎች ስለምን ወያኔ ሃርነት ትግራይ አጀንዳችን ሆነ ይላሉ። ስለምን አይሁን? አይሲሲ እኮ ሊቢያ ሳይሆን ኢትዮጵያ ላይ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ዘንድ ነው ያለው። እና እናማ የሥልጣን ዘመኑ በጎልቻ ልዋጭ በዚህ መልክ መጠናቀቁ ተሰማ።

ዜናው – ከእስረኛዋ ኢትዮጵያ …..

አቤቱ አምላካችን ሆይ መከራውን የምትሸከምበት ወይንም የምትፈነቅልበት አቅም ለእናታችን ለቅድስት ኢትዮጵያ ይስጥልኝ። አሜን፤

በሊቢያ ጉዳይ ማን ነዉ ተጠያቂ. – ልዑል አለሜ


አሁን የአፍሪካዊያን ስቃይ እጅግ ዘግናኝ ወደ ተባለ ደረጃ ላይ ደርሷል……. አለም ግን ከማዉራት የዘለለ አንዳችም ነገር እየፈየደ አይደለም…
ማን ነዉ ተጠያቂዉ

በሊቢያ በስደት የሚንከራተቱ አፍሪካዊያን ችግር ሊቢያ ብቻ ላይ የሚያነጣጠር አይደለም ይልቁንም አለማቀፋዊ ተደማጭነት ያላቸዉ ሐገሮች አለማቀፋዊ የስደተኞች መብት ላይ ያላቸዉ አቋም በራሱ ሌላ ችግር ነዉ ለዚህ ትልቁን ሚና የሚወስዱት በተለይ ፈረንሳይና ጣሊያን ሲሆኑ እጅግ ብዙ አፍሪካዊያን ወደ ሐገራቸዉ ለመግባት ሲሉ በሳሃራ በረሃዋ መቃብር ሊቢያ ዉስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እነደሚሰቃዩ ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ ይህን ማወቅ እና ዝም ማለት በራሱ እንደ ሐገር ከአለም አቀፍ ህግ ጋር ትልቅ ወንጀል ነዉ ከሁለቱ ሐገሮች መናሕሪያ የሆነርችዉ አዉሮፓ በራሷ ለዚህ መልስ እራሷን የምትዘጋጅበት መድረክ እንዲጠር አለም አቀፋዊ ጫና በአፍሪካዊያን መጀመር አለበት። 

ፈረንሳይ ይህንን ተጠያቂነት ቀድማ የተረዳችዉ ይመስላላ በአሁኑ ወቅት የተመድ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጉዳይ በሊቢያ ላይ ለመነጋገር የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም / ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እየጠየቀች ነው የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን-ኢፍስ ሌድሪን ፈረንሳይ የፍትህ ስርዓቱ በአግባቡና በፍጥነት በሊቢያ በኩል ካልተካሄደ በሊቢያ ላይ ማእቀብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርባለች።

የፈረንሳዩ ሚኒስቴር አንድ ነገር ማብራራት አልቻሉም ለየትኛዉ የሊቢያ መንገስት ነዉ ማስጠንቀቂያ ወይም ማእቀብ እንዲደረግበት ጥሪ ያቀረቡት የትኛዉን እዉቅና የተሰጠዉን መንግስት ነዉ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠዉ የሚሞግቱት በትሪፖሊ ያለዉን ነዉ ወይስ በምስራቅ በኩል ሃፍታርን የተቆጣጠረዉን አንጃ የቱን ነዉ መንግስት ብለዉ ማእቀብ እንደሚደረግበት ያስፈራሩት ምን በወደቀች ሐገር (failed state? ) ላይ እንደምን ያለ ማእቀብ ነዉ ዉጤታማ የሚሆነዉ የሚለዉ መጠይቅ ፈረንሳይን አላጋጭ አስብሏታል።

ለምሳሌ ጣልያንን ልንወስድ እንችላለን በሊቢያ ለሚንቀሳቀሱ የሰዉ አዘዋዋሪ ወይም አሻጋሪዎች እላፊ ገንዘብ በመክፈል በመጡበት ጀልባ እንዲመለሱ ታደርጋለች ይህ ለአሻጋሪዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሆነላቸዉ ሲሆን አሻጋሪዎቹ አፍሪካዊያን ስደተኞችን በማመላለስ ገቢያቸዉን እንዲያዳብሩ ሲያደርጋቸዉ በሌላ አንጻር እንዲህ አይነት እጅግ አደገኛ ስህተት የምትሰራዋ ጣሊያን በሊቢያ ለሚካሄደዉ ግፍ ሐላፊነት መዉሰድ ግዴታዋ እንዲሆን ያደርጋታል።

ባለፈው ሚያዝያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ዓለምአቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በሰሜን አፍሪካ ስደተኞችን ሊገድሉ የሚችሉበትን ምክንያት እና “የባሪያ ገበያ”ን በተመለከተ ሪፖርት አውጥቷል. ሪፖርቱ በአይ.ኦ.ኤም ተይዞ ወደ ትውልድ ሀገራቸዉ የተመለሱትን ስደተኞችን አስመልክቶ ነበር በሪፖርቱም መሰረታዊ ይዘት ከዚህ ሁሉ ደባ ጀርባ እነ ማን ሊኖሩ እንደሚችሉ ይሰነፍጣል።

ሐላፊነት በአንድ አካል ጫንቃ ላይ ለማስቀመጥ የተመቸችዉ ሊቢያ ዉስጥ የሚንቀሳቀስሱ የተለያዩ አማጺያንም ሆኑ ሌሎች ድርጅቶች ከዚህ ሁሉ ግፍ ጀርባ ከተጠያቂነት እንዳያመልጡ የግፉና የሰቀቀኑ መሪዎች ናቸዉ ለምሳሌ በሊቢያ በተለይም ባለፉት ሶስት የእርስ በርስ ጦርነቶች ወቅት የሐገሪቷን ብሄራዊ ደህንነት መፈራረስን በመንተራስ, በመቶዎች የሚቆጠሩ የሊቢያ ዜጎች ተጠልፈዉ ተሽጠዋል ለህገወጥ የጉልበት ብዝበዛ ለአካል ክፍል መበለት እና ልፍትወት ስጋ እንዲሁም ለከፍተኛ ስቃይም ተዳርገዋል።
እንደ አይ.ኦ.ኤም ሪፖርት ስደተኞችን በኒጀር በኩል ወደ ሊቢያ የሚያስገቡ አሻጋሪዎች ምንም ገንዘብ ከስደተኞቹ የማይቀበሉ ሲሆን ሊቢያ ከደረሱ ወዲህ ሐብታም የሊቢያ ገበሬዎች ለአንድ አፍሪካዊ 400 ዶላር እንደሚከፍላቸዉ ስደተኞቹም በዚያ በባርነት እንደሚቀሩ አጋልቷል ይህን ተገን ባድረገ መልኩ የሊቢያ ገበሬዎችም በዚህ የባሪያ ንግድ ዉስጥ ቀጥተኛ ተጠያቂዎች መሆናቸዉን አረጋግጧል

ሊቢያ መንግስት ተብሎ የተሰየመዉ አካል ደካማና እና ዝቅተኛ ማዕከላዊ ግዛት ሲሆን እንኳን ለስደተኞች ለራሱ ዜጎችም ደህንነትን ወይም መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ አልቻለም. የአፍሪካ ስደተኞች ቁጥር መጨመር በሊቢያ የሚገኙ የማቆያ ማእከሎች ማነስ እና ደረጃቸዉን አለመጠበቅእንዲሁም ኢሰብአዊነት እየጨመረ በመምጣቱ እንዲሁም በአብዛኛው በቋሚነት በተሰናከለ እና በተጠና የአውሮፓ ፖሊሲ ምክንያት ችግሮቹን መጋፈጥ የሚቻል አይደለም።

የምእራባዊያን ሚዲያ አገልግሎቶች በተለይም ዋሽንግተን ፖስት ነገሮችን በማፍረጥረጥ ጣሊያን ስድፈተኞችን ለማስመለስ ከፍተኛ ወጪ እንደምታደርግ ዘግቧል።
በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አዛዥ ዘይድ ራአድ አል-ሁሴን << ኢሰብአዊነት >> በማለት ያወገዙት አፍሪካዊያን ስደተኞችን ወደ ሊቢያ የመመለስ ፖሊሲ ከፍተኛ ፍጥጫ ይጠብቀዋል. 

የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮሜ ደግሞ በአውሮፓ ፖሊሲ ላይ የሰጡት ትችት አለም ወደ አዉሮፓ ሐገሮች እንዲጠቁም ሐሳብ ጭረዋል አልፋ ኮሜ << ስደተኞች እጅግ በጣም መጥፎ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እየኖሩ ነው. >> የአዉሮፓ ሐገሮች በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳች እንዲፈይዱ ጥሪ አቅርበዋል።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ስጦታ አበረከቱ

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ስጦታ አበረከቱ

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአቶ ገዛኸኝ ነብሮ እና በአቶ ቴዎድሮስ ተ/ሚካኤል አመካኝነት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የገንዘብ ስጦታ በተወካያቸው በኩል በዛሬው ዕለት አበረከቱ ።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በመወከል የተገኘው አቶ ነብዩ ባዘዘው፤ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚደረገው ስጦታ ቀጣይነት እንደሚኖረው በመግለጽ የ61,600 ብር ስጦታውን አበርክቷል ።

ጊንጥ አና ጊንጠኞች! – ዳንኤል ክብረት

ሙኃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት – ብዙ ጊዜ ጊንጥ የሚለውን ቃል ስሰማ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም ነበር ዛሬ ግን ጊንጥ አሪፍ ነገር አስተማረኝ፡፡ ይህንን እንድል ያስገደደኝ የዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አጭር ታሪክ ነው ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡

አንድ ሽማግሌ ውሃ ውስጥ ሊሰምጥ ያለ ጊንጥ ያዩና ሊያድኑት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም ጊንጡን ከውሃው ለማውጣት እጃቸውን ዘርግተው አነሱት በዚህ ጊዜ ጊንጡ ነደፋቸው:: እሳቸውም ደንግጠው ለቀቁት ጊንጡም ተመልሶ ወደውሃው ገባ፡፡

ሽማግሌው አሁንም የጊንጡን ውሃ ውስጥ መስመጥ ተመልክተው ድጋሚ እጃቸውን ለእርዳታ ዘረጉለት አሁንም በድጋሚ ጊንጡ ነደፋቸው ሲለቁት አሁንም ውሃ ውስጥ ገባ፡፡

ይህንን የሽማግሌውን ትእይንት የሚመለከት አንድ ሰው ወደ ሽማግሌው ጠጋ ይልና ‹‹ይህ እኮ ክፉ ፍጥረት ነው! ጊንጥ እሱን ለማዳን ሲሉ እርሶ እየተጎዱ እኮ ነው›› አላቸው።

ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የጊንጡ ተፈጥሮ መናደፍ ነው፡ የኔ ተፈጥሮ ደግሞ መርዳትና ማገዝ ነው፡ ስለዚህ ተፈጥሮዬ ክፉ አደለምና ጊንጡን ከመርዳት አላቋርጥም አረዳዴን ግን አስተካክላለሁ›› አሉና ጥቂት አሰብ አድርገው ተነስተው ከዛፉ ላይ አንድ ቅጠል ቀንጥሰው በቅጠሉ ጊንጡን ይዘው አወጡትና ህይወቱን አተረፉለት፡፡

እኛም እንዲህ ነን ሰውን ለመርዳት ስንሄድ ብዙ ጊንጦች ይነድፉናል፡ ደግ ልናደርግ ስንጓዝ ብዙ እንቅፋቶች ይመቱናል፡፡ ነገር ግን ጊንጡ እንዳይነድፈን እናደርጋለን እንጂ እንቅፋቱ እንዳይመታን እንጠነቀቃለን እንጂ እንዴት ደግ ማድረግ እናቆማለን ?

አንተም አንቺም ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ ያለን ሰዎች በሙሉ ስንፈጠር ደግና መልካም ነን፡፡ ግን ሰውን ክፉ የሚያደርገው ተፈጥሮው ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡

ለዛ እኮ ነው በነዚህ ጊንጦች ስለተነደፍን መልካም ለማድረግ ቅስቀሳ በጎ ለመስራት ማጣራት መጠራጠር በሌላ አይን መመልከት ጀመርን፡፡

እስኪ የዛሬዋን አዲስ ቀናችንን እንዲህ ብንውላትስ ሰው ስንረዳ እንደጊንጥ በሚሆኑ ሰዎች ተሸንፈን መልካም ከማድረግ ከምንቆጠብ የምንረዳበትን መንገድ ለይተን ብናውቅስ፡፡

በነገራችን ላይ ለሰው በጎ ማድረግ ሲባል በገንዘብ ብቻ ይመስለናል አይደለም:: በየቤቱ ገንዘብ ኖሮት ሰው የናፈቀው ህሊና አለ:: ስለዚህ አንዳንዶች ፈገግታችንን አንዳንዶች እኛነታችንን አንዳንዶች መሰማትን ይፈልጋሉና በየደረስንበት ለመልካም ነገር ጊንጥ ፈርተን እምቢ እንዳንል፡፡

መልካም የምታደርጉ ሁሉ ግን ጊንጡንም ቢሆን ከማዳን አትቦዝኑ።

ዳኛ ዘርዐይ ወልደሰንበት ዛሬ ማሕሌት ፋንታሁንን በችሎት መሐል በወቀሳ አስጠነቀቋት | ጌታቸው ሽፈራውም….

ጌታቸው ሽፈራው

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን “አክላቸው ወንድወሰን” በተባለ የፌስቡክ አድራሻ የዳኛ ስም ተጠቅሶ የተፃፈ የፍርድ ቤቱን ክብር የሚነካ ፅሁፍ አጋርተሻል በሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

አሚር በፌስቡክ የተፃፈ ፅሁፍ ስር አስተያየት እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም እኔ (ጌታቸው ሺፈራው) የምፈልገውን የፍርድ ቤት ውሎ ብቻ ቆርጬ እንደምዘግብ ይህም ምን “ሸንቆጥ” ለማድረግ እንደተፈለገ ፍርድ ቤቱ እንደሚረዳው፣ ለሌላ ሰውም መረጃ እንደምልክ ፍርድ ቤቱ ገልፆአል። ፍርድ ቤቱ ለሌላ ሰው መረጃ ትልካለህ ሲል የጠቀሰው ማስረጃም ሆነ የሰው ስም የለም።

ናትናኤል (የአባቱ ስም ያልተጠቀሰ)፣ አንገቱ ላይ “ሻርፕ” ያደርጋል የተባለና በችሎት ያልነበረ ግለሰብም ስሙ በችሎት ተጠቅሷል።

ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን በችሎት ቀርባ አጋርተሽዋል ስለተባለው ፅሁፍ የተጠየቀችው በጠዋቱ የፍርድ ቤት ጊዜ ሲሆን ለከሰዓት ተቀጥሮ ከአሁን ቀደም የምትፅፋቸው ፅሁፎች አጋራችው የተባለውን አይነት ይዘት እንደሌለው በመጥቀስ በተግሳፅ እንደታለፈች ፍርድ ቤቱ ገልፆአል።

ፌስቡክ ላይ የተፃፉ ፅሑፎችን ዳኞች እንደሚያነቡ የገለፀው ፍርድ ቤቱ ይህን የምናደርገው የፍርድ ቤቱን ክብር ለማስጠበቅ ነው ብሏል። ፍርድ ቤቱ “እንዲህ የምናደርገው እናንተን ሃራስ ለማደረግ አይደለም” ቢልም ለሌላ ሰው መረጃ መላክና መሰል ጉዳዮች ላይ ተላከለት የተባለ ሰው ስም፣ ምን እንደተላከ እና እንዴት እንደተላከ ሳይጠቅስ ማስጠንቀቂያ መሰል ምክር ሰጥቶ አልፏል።

በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊስ አክላቸው ወንድ ወሰን የሚል የፌስቡክ አድራሻን አጣርቶ ለፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተላልፏል።

ከአሁን ቀደም በዚሁ ችሎት መሃል ዳኛው “የተቀረፀ በሚመስል መልኩ ቃል በቃል እየተዘገበ ነው” እንዲሁም የግራ ዳኛው የተዛቡ ዜናዎች በፌስቡክ እየተላለፉ ነው በሚል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

______________
ዳኛ ዘርዐይ ወልደሰንበት ዛሬ ማሕሌት ፋንታሁንን በችሎት መሐል በወቀሳ አስጠነቀቋት

በፍቃዱ ዘ-ኃይሉ እንደጻፈው

ዳኛ ዘርዐይ ወትሮም ትዝብት የማያጣው የፌ/ከፍ/ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ዳኛ ሆነው ከመጡ ጀምሮ ሌላ የውዝግብ መንስዔ ሆነዋል። ታዳሚውን በጥርጣሬ ይሁን በጥላቻ በማያስታውቅ ሁኔታ የሚገረምሙት እኚህ ዳኛ ከመጡ ወዲህ ችሎቱ ቁጡ እና ለተከሳሽ ቀርቶ ለታዳሚ አስፈሪ ሆኗል። በሚገርም ሁኔታ እሳቸው ገጽታ ላይ የሚነበበው ቁጣ ሌሎቹ ዳኞች ላይ አይነበብም። የችሎቱ ዳኞች ባለፈው ግዜ (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራውን ጨምሮ የአውሮጳ ኅብረትን ወክለው ችሎቱን የሚታዘቡ) ታዳሚዎችን በማስነሳት “እነማን ናችሁ? ለምንድን ነው የመጣችሁት?” ብለው ጠይቀዋል። ይህ በሕግ አግባብ ተገቢ ይሁን አይሁን የሕግ ባለሙያዎች አስተያየት የሚሰጡበት ነው። ችሎቱን ለሚታደሙት እና በራሳቸው ከደረሰባቸው ኢፍትሐዊነት በመነሳት የሰብኣዊ መብት ጥሰት አቤቱታዎችን አድምጦ ለሕዝብ ለማጋለጥ እና የፍርድ ቤት ውሎዎችን በመዘገብ፣ ችሎቱን አክብረው፣ የሕግ የበላይነት እና የችሎቱ ነጻነት ላይ ያላቸውን ሁሉ ጥርጣሬ ቀብረው፣ ለፍትሕ ስርዓቱ የግልጽነት ድባብ ለማላበስ የለት እንጀራ ሳያምራቸው በብዙ መስዋዕትነት ለሚከፍሉት ወዳጆቼ ምን ያህል አስደንጋጭ እና የማስፈራራት ስሜት እንዳለው አውቃለሁ። በመሆኑም በጣም አዝኛለሁ!

ችሎቱ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት የተለያየ ሰበብ ተለጥፎባቸው የተከሰሱ ሰዎች የሚበዙበት እንደመሆኑ ብዙ ቅሬታዎች ይቀቡበታል። ለዚህ ደግሞ ችሎቱ ማድረግ የሚችለው ዝቅተኛው ነገር ቅሬታዎቹን ማድመጥ ነው። ከዚህ በፊት የነበሩት ዳኞች ቢያንስ ይህንን ሞክረው ነበር። ነገር ግን እኚህን ዳኛ ጨምሮ አዲሶቹ ከመጡ ጀምሮ ችሎቱ የተከሳሾችን ቅሬታ ማቅረብ እንደጠብ ማጫር ነው የሚመለከተው። ተከሳሾቹ በችሎቱ ላይ ጭላንጭል እምነት እንኳ እንዳይቀራቸው በተለይ ዳኛ ዘርዐይ በተግሳፅ እና ቁጣ ያሸማቅቋቸዋል። እኚህ ዳኛ በወልቃይት ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም በጦማር ላይ የጻፉ በመሆኑ ብዙ ተከሳሾች በገለልተኝነት ጉዳያችንን ያያሉ ብለን አናምንም ብለው እንዲነሱ ጠይቀዋል። አቶ ዘርዐይ ግን ይበልጥ እልህ የተጋቡ ይመስላሉ።

ዛሬም የችሎት ታዳሚውን ማስደንገጣቸውን ቀጥለውበታል። ማሕሌትን አስነስተው አንድ ራሷ በጻፈችው እና ሌላ ደግሞ የሰው ‘ሼር’ ባደረገችው ጽሑፍ ሳቢያ ወቅሰዋታል። ነገሩን “የችሎቱን ክብር ከመጠበቅ” ጋር አያይዘው፣ “harass ለማድረግ አይደለም” ብለው ቢያቃልሉትም፤ የሚሰጠው ስሜት ግን የማሸማቀቅ ነው። ማሕሌት ‘ሼር’ ያደረገችው ጽሑፍ ላይ “ፍርድ ቤቱን የበቀል ቤት” በሚል የሚገልጸውን ሳታስተውል ማጋራቷን ገልጻለች። ነገር ግን ለብዙ ሰዎች የፍርድ ቤቱ ነጻነት እና ለሕግ የበላይነት ተገዢነት ሁሌም አጠራጣሪ ነው። ይህንን በሐሳብ መግለጽ ለምን የፍርድ ቤቱን ክብር መንካት እንደሚሆን አሁንም ለሕግ ባለሙያዎች አስተያየት እተወዋለሁ። በተጨማሪም፣ ዳኛ ዘርዐይ እነ ጋዜጠኛ ጌታቸውንም አስነስተው “የምትጽፉትን ነገር እናያለን” ብለዋቸዋል። አሚር የተባለ የመብት ተቆርቋሪንም እንዲሁ “የምትጽፋቸውን ‘ኮሜንቶች’ እናያለን” ብለውታል።

ከአንድ ዓመት በፊት፣ ብሌን መስፍን አስቸኳይ ግዜ አዋጁን አስታክኮ የታሰረች ግዜ፣ የጉለሌ አንደኛ ደረጃ ችሎት የፈቀደላትን በዋስ የመፈታት መብት፣ በዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ባይነት፣ የከለከሏት ዳኛ ዘርዐይ ነበሩ። የዛን ዕለት ይህን ሁሉ ዓመት ሳውቃት የማላውቀውን፣ ማሒ ስታለቅስ አይቻታለሁ። የዳኛ ዘርዐይ ውሳኔ ነበር ያኔም ያስለቀሳት። አሁንም ተግሳፃቸው ተከትሏት ልደታ መጥቷል።