በአፄ ምንሊክ ዘመን ሰአት እላፊ የሚቆጣጠሩት ወታደሮች የኢትዮጵያ ሶማሌዎች ነበሩ ።

ሰዓት እላፊ (እዮብ ዘለቀ )

አዲስ አበባ ከተቆረቆረች በኋላ መጠጥ ቤቶች እየበረከቱ በመሄዳቸው ለሊቱን በሙሉ ተኩስ ሳያባራ ያድር ጀመር፡፤ በዚያን ጊዜም ምኒሊክ የማይታወቅ የሰዐት እላፊ አዋጅ አወጁ፡፡
በመላ ኢትዮጵያም እንዲሰራበት ተደርጎ ተደነገገ የአዋጁንም ቃል በግል ደብዳቤያቸው መሸኛ እያደረጉ ለየመኳንንቱ ሁሉ በያገሩ ላኩለት፡፤ “…ለሊት ለሊት ተኩስ የማይተኮስበት ከተማ ከሆነ ሕዝቡ ሰላማዊ ነውና እላፊ አታድርግበት፡፤ ተኩስ እየተተኮሰ ፀጥታውን የሚነሳ ከሆነ ግን እላፊውን ትከልበት…” እያሉ ላኩ
ብላት መርስኤ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ በልጅነታቸው ማለት በ1896 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ስላዩት ሁኔታ በመጸሃፋቸው ሲገልጹ የሰዓት እላፊንም ነገር ገልጠዋል፡፡


” … ሌሊት ከተማዋን የሚጠብቁት ዘበኞች ከሐረርጌ የመጡ ሲሆን ሱማሌዎች ነበሩ፡፡ ሕዝቡ ደወርያ ይላቸዋል፡፡ ማታ ሶስት ሰዓት ሲሆን ለህዝቡ የሚያሰሙት አንድ የጩኸት ድምጽ አላቸው፡፡ ሕዝቡም ያን ድምጽ ሲሰማ በቤቱና በግቢው መከተት አለበት፡፡ ሱማሌ ከጮኸ በኋላ ከአጥሩ ውጭ በመንገዱም ሆነ በሜዳ ላይ የተገኘውን ሰው እየያዙ ይወስዱና አስረው ያሳድሩታል፡፡ በማግስቱም መቀጫ አስከፍለው ይለቁታል፡፤ መቀጫውም አንድ ሩብ እንደነበር አስታውሳለው፡፤ በዚያን ጊዜ የነዚህ ዘበኞች ሥልጣን የቱን ያህል እንደሚፈራና እንደሚከበር በጣም ትዝ ይለኛል፡፡…”
ከሄን አብኩነርሮሲን ሞታንዶን እና መረብ የታሪክ ፀሃፊዎች እንደጻፉት ደግሞ ከመሸ በኋላ መዘዋወር ቀርቶ ቤቱን ከፍቶ በበራፉ ላይ ቆሞ የተገኘ ሁሉ ታስሮ አድሮ በማግስቱ መቀቻውን ይከፍል ነበር፡፡
የምኒልክ አዋጅና ማስገንዘቢያ ደብዳቤ ከደረሳቸው መኳንንት መሀል በቅድሚያ የሰዓት እላፊን በተግባር ያዋሉት የጎጃሙ ራስ ኃይሉ ናቸው፡፡

ምንጭ፡ ጳውሎስ ኞኞ አጤ ምንሊክ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s