በእነ ንግስት ይርጋ ብይን ላይ ከተነሱት መካከል አንዳንድ ነጥቦች – “የኮለኔል ደመቀ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት በ120 ብር ገዝታለች”

ከጌታቸው ሽፈራው

1ኛ ተከሳሽ: ንግስት ይርጋ

#የቆሰሉትን (በጎንደሩ ሰልፍ) ለማሳከም የለበሰችውን ልብስ አውልቃ ከ5ሺህ ብር በላይ አሰባስባለች

#የኮለኔል ደመቀ ዘውዱን ፎቶ ባነር አሰርታለች

#የኮለኔል ደመቀ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት በ120 ብር ገዝታለች

#ሰልፉ በሰላም በመጠናቀቁና በወጣቱ ተስፋ ስላለው እትዬ ጣይቱ ብሎ እንደጠራት……………

4ኛ ተከሳሽ አወቀ አባተ

የሽብር ቡድኑ አባል ፎርም እንዲሞላ አድርጎት ፎርሙን በመሙላት በግልፅ የሽብር ቡድኑ አባል በመሆን

(ግንቦት ሰባት ምርጫ ቦርድ እውቅና እንደየሰጣቸው ፓርቲዎች አባሌ ሁን እያለ ፎርም ካስሞላ የዘመኑ ቀልድ ነው የሚሆነው)

5ኛ ተከሳሽ በላይነህ አለምነህ

#ቀይ ካርድ ይዛችሁ አደባባይ በመውጣት መንግስትን በኃይል ታገሉ እንዳለ… …

(ቀይ ካርድ አፈሙዝ እለው እንዴ? ቀይ ካርድ ከኃይል ትግል ጋር ከተያያዘ በየ ሳምንቱ ጎንደር አደባባይ ላይ ብቻ ሳይሆን መስቀል አደባባይ አጠገብ፣ ስቴዲየም ቀይ ካርድ ሲመዙ የሚውሉ ዳኞችም እንደነ አወቀ አባተ የግንቦት 7ትን ፎርም ሞልተዋል ተብለው የአቃቤ ህግ ክስ እንዳይቀርብባቸው ያሰጋል!)

በሌላ በኩል!

ዐ/ሕግ ባቀረበው የሰነድ ማስረጃ እነ ንግስት ይርጋ በ01/11/2009 ዓ.ም የተጻፈው የሰነድ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ መቃወሚያ አስገብተው ነበር። ከአሁን ቀደም ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተመሳሳይ መቃወሚያ አስገብተው የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብይን ሰጥቶላቸዋል። የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን ያደረገው ኮ/ል ደመቀ ይከላከሉ አይከላከሉ የሚለውን ከመበየኑ በፊት ነው።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት እነ ንግስት ያስገቡት የሰነድ ማስረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ሳይሰጥ ወደ ዋናው ብይን ገብቷል። የንግስት ጠበቃ ከብይኑ በኋላ ፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን የሰነድ መቃወሚያ ሊያይላቸው ይገባ እንደነበር ቅሬታቸውን አሰምተዋል። የሰነድ ማስረጃ መቃወሚያው ከዋናው ብይን ቀድሞ እንዲታይ የሚጠየቀው አግባብ አይደሉም የተባሉ የሰነድ ማድረጃዎችን መሰረት ተደርጎ ይከላከሉ ወይንስ አይከላከሉ የሚባል ብይን ሊሰጥ አይገባም በሚል ነው።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ነጋ የኔነው የክስ መቃወሚያ ብይን ላይ የፌደራል ፍርድ ቤት ስልጣን የለውም ያለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሆነውን የ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ጉዳይ ላይ የደህንነት መስርያ ቤቱ የፃፈው ሪፖርት በድምፅ ካልታገዘ በስተቀር በሰነድ ማስረጃነት ሊቀርብብኝ አይገባም ብለው ያቀረቡት የሰነድ መቀወሚያ ከብይኑ በፊት ተቀባይነት ማግኘቱ የሚታወስ ነው።

የንግስት ጠበቃ እንደገለፁልኝ በህጉ በ146 ላይ እንደተደነገገው መቃወሚያ የቀረበ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በማስረጃው ላይ ለቀረበው ክርክር ወዲያውኑ ይወስናል። ፍርድ ቤቱ የእነ ንግስትን የሰነድ ማስረጃ መቃወሚያ በዝምታ ማለፉ የስነ ስርዓት እና መብት ጥሰት ነው ብለዋል!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s