በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ባዶ እየሆኑ ነው ተባለ

BBN news November 29, 2017

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በተለይ በሃሮማያ እና በመቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች እስከ ትላንት ድረስ ትምህርታቸውን ጥለው እየወጡ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ሆኖም ካቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ አንድም ጥያቄ ባለመመለሱ ግቢውን ጥለው ለመውጣት እንደወሰኑ ተነግሯል፡፡
የሶማሌ ክልል ልዩ ጦር ወደ ኦሮሚያ ክልል እየገባ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በተለያዩ አካላት ተቃውሞ ሲቀርብበት እንደነበር ይታወቃል፡፡ ተቃውሞ ሲያቀርቡ ከነበሩ ወገኖች መካከል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ተማሪዎቹ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በኦሮሚያ ክልል እየፈጸመ የሚገኘው ጥቃት እንዲቆም ካለመለከቱ በኋላ፣ ጥያቄአቸው ምላሽ እንደሚያገኝ ተነግሯቸው ነበር ተብሏል፡፡ ሆኖም ልዩ ኃይሉ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ከሰላሳ በላይ ሰዎችን መግደሉ ሌላ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡
ይህ ጉዳይ ያስቆጣቸው ተማሪዎች ከሃሮማያ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመውጣት ላይ እንደሚገኙ ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተለይ ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የወጡ ተማሪዎች ቁጥር አስደንጋጭ መሆኑም ነው የተሰማው፡፡ በዚህም የተነሳ በግቢው መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት መስተጓጎሉም ታውቋል፡፡ በግቢው ውስጥ የቀሩት ተማሪዎች አነሰተኛ መሆናቸውን የጠቆሙት መረጃዎች፣ ግቢው አለወትሮው ጭር ማለቱንም አክለዋል-መረጃዎቹ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s