የማለዳ ወግ … ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ክብር ይገባሃል !( ነቢዩ ሲራክ)

* ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ክብር ይገባሃል

ብርቱው የቀድሞ ስራ ባልደረባዬ አንጋፋው የራዲዮ ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ በሀገራችን ” አሉ ” ከሚባሉት የራዲዮ ጋዜጠኞች መካከል አንዱና ቀዳሚው ይመስለኛል። ባልሳሳት ጋዜጠኛ ነጋሽና ጋዜጠኛ አለምነህ ጎልተው የወጡትና የታወቁበት ወቅት በገልፍ ጦርነት ጊዜ ይመስለኛል። በባህረ ሰላጤው ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ሬዲዮን ትኩስ መረጃዎች በጉጉት ይከታተል የነበረ ፣ የአረቦችን አንበሳ ምሳሌ የኢራቁ የቀድሞ ፕሬዚደ ንት ሳዳም ሁሴንን አስታውሶ ጋዜጠኛ አለምነህንና ጋዜጠኛ ነጋሽን ፣ ንግስት ሰልፉን አለማስታዎስ እንዴት ይቻላል ? ድምጸ መረዋዎች ባለተስገምጋሚ ድምጾች አይዘነጉም ፣ አይረሱም …

ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ በኢህአዴግ አዲስ የግዛት አመታት ድንበር ተሻግሮ የጀርመን ራዲዮ ባልደረባ ከሆነ በኋላም ይታወቃል። በተለይም በሳምንት አንድ ቀን በሚያዘ ጋጀው የማህደረ ዜና ዝግጅት ተወዳጅነቱ ከፍ ያለ ነው ። ነጋሽ በማህደረ ዜና ጥልቀት በተሞለበት መንገድ ዜና ትንታኔውን ከሽኖና አጣፍጦ ስለሚያቀርበው ጀርመን ራዲዮ የሚያደምጥ የነጋሽን ማህደረ ዜና ሊያመልጠው የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም። እናም ብቃትና ጥራት ያለው ስራና አቀራረቡ ነጋሽን ከብዙው ጋር አስተዋውቆታል ማለት እችላለሁ። እኔ እስከማውቀው ጀርመን ራዲዮ የሚያውቅ ሰው ጋዜጠኛ ነጋሽን የማያውቅ አላጋጠመኝም ።

ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ተግባቢ ፣ ተጫዋችና ሳቂታ ነው ። ማድመጥ ይወዳል ። አድምጦ ከገባው በላይ የመግ ለጽ ክህሎት አለው ። ነጋሽ የዋዛ መልካም ሰው አይምሰላችሁ:) ነጋሽ ከሙያው ውጭ ያለው ህይዎቱ ከቤተሰቡ ጋር የተቆራኘ መሆኑን አውቃለሁ ! ነጋሽ ጥሩ ሰብንዕና ያለው ፣ ሚስት ፣ ልጆቹንና ቤቱን ፣ ወዳጅ ዘመዶቹን አክባሪ አመለ ሸጋ ስለመሆኑ እመሰክራለሁ ! ነጋሽ ጸሐፊ ፣ ዜና አጠናቃሪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም ። ባለ ተስገም ጋሚ ድምጽ ብቻም አይደለም ። ጋዜጠኛ ነጋሽን ልክ የዛሬ 7 ዓመት ቦን ጀርመን ላይ ባለችው ጎጆው ተገኝቸ ስንጨዋወት ከተመለከትኩት ፣ ከታዘብኩት እውነት በላይ ስለ ጋዜጠኛ ነጋሽ መልካም ሰብዕናና መልካምነት በቅርበት የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክራሉ !

ሰሞኑን የጀርመን ራዲዮ የጉምቱውን ጋዜጠኛ የትዝታ ምስክርነት ተንቀሳቃሽ ምስል ይዞ ባሰራጨው መረጃ እንዲህ ይላል ” ነጋሽ መሐመድ በኢትዮጵያ ራዲዮ ሰዎችን በየዕለቱ አመሻሽ ላይ ያሰባስብ እንደነበር አጫውቶናል። በእርሶ አካባቢ ምን ይመስላል? #whereicomefrom ” ሲል የጋዜጠኛ ነጋሽን ትዝታ ያጋራናል ፣ ማድመጥ መልካም ነገር ነው ! ትዝታውን አድምጨ ለወዳጄ ምስጋናና ክብር ልሰጠው ወደድኩ ! እስኪ ብዙዎቻችሁ ስለወዳጃችን ስለ ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ የሚሰማችሁንና የምታውቁትን አጋሩኝ ?

አድናቆትና ክብር ይገባሃል ወዳጄ ጋዜጠኛ ነጋሽ … !

ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 20 ቀን 2010 ዓም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s