በኢትዮጵያ ያለው ስርዓት በኢኮኖሚው ዘርፍ ሀገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ እየወሰዳት እንደሚገኝ ተጠቆመ

በኢትዮጵያ የሚገኘው ስርዓት ሀገሪቱን ወደ አደገኛ አቅጣጫ እየወሰዳት እንደሚገኝ ተነገረ፡፡ ስርዓቱ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊም ሆነ በሌሎች ዘርፎች እየተከተለ የሚገኘው መንገድ ሀገሪቱን ዋጋ እንዳስከፈላት ይታወቃል፡፡ በተለይ በአሁን ሰዓት ያለው የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጉዞ ግን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡ ባለሙያዎቹ፣ ስርዓቱ እየተከተለ ያለውን የኢኮኖሚ ጉዞ ቆም ብሎ እንዲመለከት ማስጠንቀቂያ እና ምክር አዘል ሀሳባቸውን በማጋራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጀምሮ፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ በየወሩ በገበያ ውስጥ እየተፈጠረ ያለው የዋጋ ንረት እና መሰል ጉዳዮች፣ ስርዓቱ በፕሮፓጋንዳው ዘርፍ ሲመካበት የኖረውን ‹‹የኢኮኖሚ እድገት›› በቅርብ ጊዜ ውስጥ ገደል እንደሚከተውም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ፡፡ በተለይ በውጭ ምንዛሬው በኩል የተፈጠረው አስደንጋጭ ችግር፣ ዕቃዎች ከወደብ ወደ መሐል ሀገር እንዳይገቡ እያደረገ እንደሆነ የሚገልጹት ባለሙያዎቹ፣ ችግሩ በዚህ ሳይወሰን በሀገር ውስጥ እየተካሔዱ ያሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችንም እያስቆመ እንደሚገኝም ባለሙያዎቹ ያክላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ስርዓቱ ወደ ኢንዱስትሪ መር እያሸጋገርኩት ነው ለሚለው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ መርዶ መሆኑም መረሳት እንደሌለበት ነው የባለሙያዎቹ ገለጻ የሚያስረዳው፡፡

በሆቴል፣ በጨርቃ ጨርቅ እና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶች፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በስራቸው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ እንደሚገኝ በምሬት እየገለጹ ናቸው፡፡ ሌሎች ባለሀብቶች ደግሞ በተፈጠረው የምንዛሪ እጥረት የተነሳ፣ ስራቸውን በከፊል ከመስራት ጀምሮ፣ ሙሉ ለሙሉ ስራውን ወደማቆሙ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ በመናገር ላይ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የግል ባለሀብቶች በፈጠሩት የስራ ዕድል ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች፣ መንግስት በፈጠረው የስራ ዕድል ተቀጥረው ከሚሰሩ ዜጎች ያልተናነሰ ቁጥር እንዳላቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የግሉ ዘርፍ በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ስራውን ሲያቆም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለስራ አጥነት ችግር እንደሚጋለጡ ይታወቃል፡፡ ይህ ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥነት ቀውስ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑ አይቀርም የሚሉ ታዛቢዎች፣ ስርዓቱ እየሔደበት ያለውን አደገኛ መንገድ መርምሮ ለተማሩ ሰዎች ዕድል እንዲሰጥ ታዛቢዎቹ ምክራቸውን ይለግሳሉ፡፡

እባካችሁን ተውንንንንንንን – ሥርጉተ – ሥላሴ

 

ከሥርጉተ – ሥላሴ 28.11.2017 /ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ/

ጎንደርን መሰል መከራን ልቻልህ ብለው ለተሸከሙ የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል …

„ሥጋቸውን መከራ ያስቻሉ፣ በፈጣሪያቸውም አምነው መከራ የተቀበሉ፣ በክፉ ሰዎችም የተነሣ የጎሰቆሉ ፈጣሪያቸውንም የወደዱ ሰዎች ብርና ወርቅን አይወዱም“ (መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 42 ቀጥር 9)

መነሻ

 

ልጆቻችን ታሪክ የሌለው ሞት እንዲሞቱ አንፈልግም” – „ከመቐለ ተወክለው ጎንደር በነበረው መድረክ የተሳተፉ እናት

ምን አለ ከምወደው ዝምታ ጋር ተርቲሜን ባስነካ። ስለምን ይሆን እምትቆሰቁሱን? … „ይገርማል ይደንቃል የእናትሽ ደም መቅረት“ይላል ጎንደሬ ሲተርት …. ምን አለ ብትተውን? ተውን እባካችሁ? ምን አለ ዘመን እንደረሳን እርስት ብታደርጉን? ምን አለ ከዕንባችን ጋር ሱባኤችን ብናደርግ?

አቶ ጸሐፊ እኔም አዳምጨዋለሁ። ህቅታ እዬተናነቀኝ። ሊያስታውከኝ እያቅለሸለሸኝ። „እናቱ የሞተችበትና ወንዝ የወረደችብት እኩል ያለቀሳል“ እንዲሉ …  ነው። ትናንት ደግሞ አቶ አሰገድ ገ/ ሥላሴ ይህውሃቱ አማራን – ኢትዮጵያን – ተዋህዶ ገዳይ ማንፌስቶ ዝክረ ማህበርተኛ „የትግራይ ህዝብ ምንም ፋይዳ አላገኝም“ ብለው የኮለሙትን ደግሞ አነበብኩ። ጉድ ሳይሰማ ነው … ምን ትሁንላችሁ ነው?  ኢትዮጵያ፤ አደግድጎ ኢትዮጵያዊው ሁሉ እኮ ሰጊድ ለከ እያለላችሁ ነው። ምነው ኢትዮጵያ እንደ ብራና ጥቅልል ብላ እነ ባሮም፤ አነ አዋሽም፤ እነ አባይም፤ እነ ነጋሌም፤ እነ ጣናም፤ እነ ላንጋኖም እነ አዲስ አበባም አነ ጋንቤላም አነ አዋሳም፤ አነ ወለጋም በቃ ጥቅልል ብለው እንደ ቦንዳ ጨርቅ ትግራይ ሄደው ይከትሙን? ያው በዛ ካርታ ውስጥ ይሸብለሉን? አንጡራቸው እኮ ከትሟል ያ አይበቃንም? ሌላው ቀርቶ ይህም ማዕረግ፤ ይህም የበላይነት፤ ይህም ሥልጣኔ ሆኖ „“ኑ ወደ ትግራይ በወጣት ቆነጃጅት ተዝናኑ፤ በዚህም ዘርፍ ጥሩ የቱሪዝም ሙቀት አለና ፈታ በሉ እኮም አለ“  … ማፈሪያ። የልጅ ንግድ፤ የባህል ንግድ፤ የወግ ንግድ፤ የትውፊት ንግድ። የነውር ውርርድ … የገመና ፉክክር እንዴት ሴት ወጣት ልጅን እንዲህ ለገብያ ለዛውም ለጸያፍ ሸቀጥ… አበስኩ ገበርኩ። እሰተዚህ ድረስ ነው ሁሉም አይቅርብን … ሂደቱ … እና እነ አቶ አሰገድ የቀራችሁ ነገር የለም። ገመና ሳይቀር ሽሚያ ላይ ነው ተጋሩ ጠረኑ … ፉክክር የተያዘው የተረዘዘው ሁሉ።

ምን እማይሰማ ነገር አለ … ካህኑ ሳይቀር ሥልጣነ ክርስቶስን አሽቀንጥሮ ካድሬነትን ተመስገን ብሎ እዬሰበከ ነው እኮ፤ ተነበርከኩ በኤሉሄ፤ የአሁኑ መንበርከክ አልበቃም መጎንበስንም በሰጊድ ለከ እከሉበት፤ ጆራችሁን ይዛችሁ ቁጭ ብድግ በሉለት ለተጋሩ ለፋሽስቱ እያለ ወጣት የአማራ የተዋህዶ አማንያን መንፈስ ስልብ ለማድረግ ታጥቆ ተነስቷል፤ ካድሬነት ምንም እንደሚል እያጣጣመ ነው እኮ … ዲያቆኑ … በሉት ካህኑ። የሰሞኑ የአማራ ብሄርተነት ምንትሶ ቅብጥርሶ በሚባለው የጉድ መድረክ … ጋብቻም ከፖለቲካ ጥገኝነት ሊመልጥ አልቻለም፤ ያው ነው ልምምጥ ዘመንተኛን።

እትት ይበርዳል …

… ምን አለ አማራ አብሮ ቢዋጋ ቢሞት ተጋሩ አይሙት እንጂ፤ አማራ አብሮ ምን አለ ጉና ላይ ፤ ባድመ ላይ ቢቀበር ለጌቶቹ ለነፈርኦን እስከ ደላቸው፤ በፍቅረ ንዋይ ቁንጣን አስከ አሳያዛቸው ድረስ፤ ምን አለ አማራ ቢዋደቅ በትግራይ ባርነት ተንብርክኮ ኤሉሄ ይበል እንጂ፤ ምን አለ አማራ ቢሰዋ ደሙ የውሻ ነው የንጉሦቹ አይሁን እንጂ .. ይሄ ልግጫ መቼ ነው የሚቆመው …?

አማራ ዛሬም ፍግም ይበል እንደ ለመደበት፤ ህም! ከጓሮው ወገኑን እያስቀበረ፤ ምን አለ አማራ ሁሉንም ይገብር ለሌላ ሲሳይነት ለሌላው ፍሰሃነት – ለሌላው ሰናይነት እስከ እስክስታነት እስከ ዘለለ ድረስ። እም! ለእሱ ኢትዮጵያዊነት ክብሬ – ኩራቴ ማለቱ ብቻ ይበቃዋል። በቃ! ሌላው ጵጵስና – አርበኝነት – የተጋድሎ ታሪክ እሱ ሰማዕት ይሁን በሰማይ ደጅ ያገኘዋል … የቀልዱ ብዛት አታከተ … በረደ እትትትት … ትትትት የ ዕውነት ትነት … ብነት …

እንጃ እኔ እንጃ ይህ ትንታግ እሳት የላሰ የአማራ ወጣት ግን ከእንግዲህ በጅ የሚል አይሆንም። የሚታሰርበት የሃይማኖት ገመድ እንኳን የለም። ሃይማኖት ቤተ እግዚአብሄር ሆነ መስጊዱ ማዕከሉ „ሰው“ ነው። ሰው ከሌለ ሁሉም የለም። እሱ ከሌለ አምልኮተ ዶግማው ወና ነው። የእኔ ጀግናዎች በተለይም የጎጃም አንበሶች የአሻምን ክብር ከለበሱት ቆዩ እኮ። ለአማራነታቸው ተግተው፤ በመንፈሳቸው ጎልብተው እዬሞቱ፤ እየተገበሩ ይገኛሉ የዘመን አውራዎች የበላይ ጌጦች … ባለጥንድ መክሊቶች። አራባራቱ የእኛ እያሉ ነው፤ ወልቃይት የእኛ እያሉ ነው፤ ራዕያ የእኛ እያሉ ነው። አንድም ነገር ቢያክሉ ደስ ይለኛል መተከል የእኛ ቢሉ …  … „ጣና ኬኛም“ ፋሲል የእኛ ፋሲል ኬኛ ብለዋል … ዘመን ጥሩ ነው። ሁሉንም ቢያንስ በመንፈስ መልክ አስያዘው። „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው። በቀለ ገርባ መሪዬ ነው“ ዘመን፤ ትውልድ አሻጋሪ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ገድለኛ የትንግርት ዋርካ ነው። ክስተት። አናባቢ ተነባቢም ተደሞ።ሚስጢር ለግዑፋን እንሆ ሆነ። ተመስገን!

ምን ነበር ያሉት ሥም የለሹ ጸሐፊ የሚያኮሩ ብልህ እናት።“ ወይ መዳህኒተአለም አባቴ? ስንቱን መስቃ እንቻል ይሆን ዘንድሮ? ስንቱንስ ጡር እንሸከም ይሆን ትናንትና ዛሬ? አሁን ከሙታን መንደር በከተመች ከተማ ይህን ያህል ሲደለቅ ሐሤት ሆኖ ሲመስጥ ትእቢት – ሲመሰገን፤ ጉድ በል ጎንደርስ አሁን ነው። ያ የፋቲክ ስብሰባ ስሜት የሚሰጥ፤ ለዛ ያለው ሆኖ ነው ወይንስ ለጨዋታ ማሟያ?  ወይስ ማተበ- ቢስነት? ለነገሩ ከመጤፍ ስላልቆጥርነው፤ ብጣቂም የክብር ቅርጥምጣሚ ስላልሰጠነው አጀንዳ እንዲሆን ለመስጮኽ ታስቦ ነው … በትርጉም መቃናት ከተቻለ …

እንዲህ ዓይኑን በጥሬጨው አሽቶ ከተመጣ ግን … መባል ያለበት ይባላል? ለነገሩ የተገለበጠ ነው ከአንዲት እናት ባህርዳር ላይ „ብሄር አልቦሽ“ ናቸው ልጆቼ ሲሉ አዳምጫለሁ። ትንሽም የተጋሩ ደም ያለባቸውም ይመስላል ገጻቸውን ሳስተውለው፤ የሆነ ሆኖ ተደማጭነት ነበረው። የትውልዱን ዕጣ ያነሱ ስለሆነ የተገባ ነበር፤ አምክንዮውም አቅም ነበረው። ብልህ ሊባሉ፤ አኮሩን ሊባሉ የሚገባቸውስ ይቺ ድንቅ ዬይልማና እና ዴንሳ ነዋሪ ናቸው። የነተጋሩ ችግር በፈለገው ዓይነት መሥፈርት ይሁን ከተበለጡ ቁንጣን- በቁንጣን ነው የሚሆኑት። እኛም አለን ዓይነት ነው … ታስታውሳላችሁ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዲቅሳ የመጀመሪያዋ የአንድ ብሄራዊ ፓርቲ መሪ ስትሆን አረና ደግሞ ወ/ሮ አረጋሽን ይዞ ብቅ ብሎ ነበር። ለምደነዋል። ሥም የለሹ ጸሐፊ …  ምን አለበት ይህነን ለባለቤቶች፤ ለመከረኞች፤ ለመስቃ ለባሾች ዳኝነቱን ቢተውት … ተዚያ ማዶ ተሁኖ ቁስል አይታከምም …  ብቻ እውነትም ጎንደር ተቆርቋሪ ልጅ ባታወጣም፤ ሌላ ታምረኛ ልጅ ፈጣሪ ስለሰጣት እምለስበታለሁ። ጉዳዩ እጅግ በሚመስጥ ሁኔታ የፋሲል መንፈስ ያረፈበት ቅድስና ስለሆነ። ሰፊ ጊዜ ሰጥቼ ወደ ውስጡም እዘልቃለሁ – ከሰሞናቱ። ያው ቅናት መለያው የሆነ ደግሞ ይብተክትክ።

በሌላ በኩል ቀድሞ ነገር የትኛውም ጸሐፊ ነው ከተጋሩ ውጭ „መቀሌን“  „መቐለ“ ብሎ የሚያወቀው። ስለዚህ ጸሐፊው አድማጭ ያልነበረውን የተጋሩ የገዳይ ብርአንባር – ግጥግጦሽ በጎንደር ማስጮኽ አሰኝቷቸው ስለሆነ ያው ቤተ ተጋሩ እሱ – በእሱ ነው፤ የሚደንቅ፤ የሚገርም የእኛ የሚባል ጠረኑ ልም ነው ከነተጋሩ .. ሠፈር … ሰውነት የለም። ተፈጥሯዊነት ድርቅ የመታው ነው።

„ልጀቻችን ታሪክ የሌለው ሞት እንዲሞቱ አንፈልግም።“ ወዘተ ወዘተ …. አዬ እናቴ ልጆቾዎት ከሞቱ እኮ ቆዩ። ሲፈጠሩ በሙት መንፈስ ነበር። ሙሶሎኒ በተፈጠረባት ምድሩ የድንጋይ ሐውልቱ ፍርሷል። ያን የድንጋይ ሐውልት የተሸከሙት የርስዎ የማህጸን ፍሬዎች ናቸው። እናትዬ ልጆቸዎት ጣሊያን ቀብሮት የሄደውን ቦንብ አፈንድተው ኢትዮጵያን ባለቤት አልቦሽ አድርገው፤ ፈረካክሰው፤ ሽንሽነው፤ በጎሳ አናውፀው መሳቂያ መሳለቂያ አድርገዋታል። የአፍሪካን ቁንጮ የነበረች ልዕለ ሐገር ከሞሪሺዬስም ከጋናም ያነሰች ናት። ሥነ – ልቦናዋን መጥምጠው አጋድመው እዬጋጡ፤ ከድሆች ተርታ ብቻ ሳይሆን ከፈራሽ ሀገሮች ተርታ እኮ ያሰልፏት የእርስዎ ማህጸን ያፈራቸው ርጉሞች ናቸው። ዛሬ … ዛሬማ ነጮች ሳይቀሩ ኢትዮጵያ ስለ አፈራቻቸው እሾኾች እና ጃርቶች ጉድ እያሉ እኮ ነው። …

ሌላው ደግሞ ምንድን ነበር እትጌ ያሉት „ጠላታችን ድህነት ነው“ እም! ወይንስ ህም! ይባል ይሆን። እኛ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እስከነ ማንፌስቶው ነው ጠላታችን። ይህ የመላ ኢትዮጵያውን ድምጽ ነው። ወያኔ ልቀቀን! በቃህን! ብሄራዊ እድምታ ነው። ከእነ ቅል ቋንቁራህ ብን በልልን ነው የትግሉ እንብርት። ለነገሩ እናንተማ ከድህነት አረንቋ ብቻችሁን ወጥታችሁ ከዓለም ደረጃ ጋር በብልጽግና ስትፎካካሩ ከብራዚል/ ከቻይና ጋር ሆነ እኮ መደባችሁ፤ የዓለሙ የንውይ መ/ቤትም ጨላማ የከተመባትን ያቺን የጥንት የጥዋቷን የትውፊት ከተማን፤ አጉራሻችሁን ጎንደርን ድጣችሁ እናንተኑ በምሽት፤ ብርሃንን እንደ አጋይስተ ዐለሙ አርአም ቦግ ብላችሁ በጨለማ የተከደነችውን ጎንደርን ደግሞ እንደሆነችው አድርጎ የሳትላይት ምስል ዕድሜ ለቴክኖሎጂ እንጂ አያችሁት አይደል። ስንት በእወቀት የበለጸጉ አንቱዎች አፈራችሁ በ26 ዐመታት? ቁጥር ሥፍር አለውን? አሁን ያአለው የትግራይ ሙሁር/ሊቃናት መበራከት ጣሪያ ላይ እኮ ነው። ጥበቃው፤ የህግ ከለላው ቀዳሚው ለትግራይ ዜግነት ለወርቁ ባለደም ነው። እኛ ደግሞ የባርነት ቀንብር ይውረድልን እግዚኦ የነፃነት ያልህ እያልን ነው። ኧረ ከእግዚኦታም በላይ ነው፤ ጠላታችን የማህበረ ፈርኦን፤ የማህበረ – ደራጎን፤ የማህበረ – ሳዖል አገዛዝ እንጂ ድህነት አይደለም። ከርሱ የፈርኦን ማህበር ሲተነፍስ ድህነቱም ደረጃ በደረጃ ይቃለላል። በቅድሚያ መኖሪያ ብኛኝ አፈር ይኑረን፤ አማራ ሀገር – ባዕት አልባ ነው። አማራ ተቆርቋሪ ባለቤት፤ የህግ ጥበቃ የለውም፤ አማራ ከማደጎ ልጅነትም በታች የተንዘገዘገ ነው። ተገንዞ – ተወግዞ – በግዞት የሚገኝ መከረኛ።

ከእናንተ ከሲኦሎች ስንላቀቅ እኛ ስለድህነት እንመክራለን – ነገ። እናንተ ሰለመብራት፤ ስለመንገድ ተጨነቁ የደላችሁ ናችሁ – ዛሬ ። የ26 ዓመት ሙሽሮች። ግን የጫጉላ ጊዜያችሁ መቼ ይሆን የሚጠናቀቀው? ሁልጊዜ ሠርግ ነው የእናንተ ነገር፤ ሁልጊዜ ሽርሽር ነው …  እኛ ግን  … „ጽድቁ ቀርቶብን በወጉ በኮነን“ ነው። ቢያንስ ለባርነቱን ሰላሙን ስጡት … „እዬም ሲደላ ነው“ እመቴዋ እማ የእኛ ዘመናይ። የእናንተ አልበቃ ብሎ በመላ ኢትዮጵያ አማራ እንዲሳደድ ነው የተደረገው … እንደ ቤተ – እስራኤላውያን … 2.5 ሚሊዮን ህዝብ ያመናችሁት ነው … ሌላውንም መሬት የቁጥር ተማሪ ከሆነች እሷው ትከውነው …. ምጽዕተ አማራ …

ጥሞና።

እኒህ የተጋሩ እናት ደፋር ከሆኑ¡ የእውነት አርበኛም ከሆኑ¡ ማባጨል ጌጣቸው ካልሆነ¡ መስቃ ድሪያቸው ካልሆነ¡ ካድሬነቱን ትትው ያወቃሉ ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠገዴ፣ ማይጸምሪ፣ አዳርቃይ፣ አዲረመጽ፤ ራያ፣ አሁን ደግሞ ግጨው ነገ ደግሞ ጎንደር ከተማ፤ የእነሱ እንዳልሆነ። ልጆቻቸው ለጉልበት ሥራ ነበር ወደ እኛ ይመጡ የነበሩት ወይንም ተፈጥሮ ጥሪኝኑ ስትሸሽግባቸው ቀን ለማሳለፍ። ስለምን ስለዛ አልተነፈሱም? የክፉ ቀናችን አጉራሻችን ጎንደር አስከፋነሽ በደልንሽ ይቅር በይን ስለምን – እኮ ስለምን አላሉም? ጎንደር የእነሱ ትዕቢት አልናፈቀውም እኮ። ጎንደር የእነሱን ከጫካ ገንባሌ ወደ ገበርዲን እና ፖርሳ ያደረጉትን ሽግግር ማዬትን አላሰኘውም? አይናፈቀውም የተጋሩ ትንፋሽ። ስለምን ሰለሚከረፋው ወራራ አልተሟገቱም „አኩሪዋ¡“ እናት? ስለምን ስለዛ የመሬት፤ የተራራ፤ የቅርስ፤ የተፈጥሮ ሃብት ስርቆት ግብግብ አላደረጋቸውም? መቼም ሌባ ልጅ አንገት የሚደፉበት እንጂ በአደባባይ ላይ ተወጥቶ የሚፎክሩበት፤ የሚያቅራሩበት፤ እንዲህ ቡራ ከረዩ፤ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚያሰኝ አይደለም። ለነገሩ በእንቁላሉ ያልተቀጣ … ልጅ ህይወቱ ስርቆት ናት። ነፍሱ እምነት ማጉደል ናት።

 

ግን ስለምን የሰው አንጡራ ሃብት ዘረፋ አልጠዘጠዛቸውም እኒህ እናት? ቀድሞ ነገር ፍቅር – ሰላም እኮ ጠበንጃ ደግኖ አይደለም። ጉባኤው ላይ እኮ ታዳሚው ጠበንጃ እና ትዕቢት ነበሩ። አይታያቸውም። የኦሮሞ ወገኖቹን አማራ እንዴት እንደተቀበለ አያስተውሉም? የኦሮሞ አባቶች አባ ገዳዎች እኮ ሲመጡ ብትራቸውን ይዘው ነበር የመጡት። በጠመንጃ በሠራዊት ታጅብው አልነበረም የመጡት። ጥጌ አንተ ነህ አምኘህ መጥቻለሁ፤ ያሻህ አድርገኝ ብለው እኮ ባዶ እጃቸውን ነበር የመጡት። ፋቲክን ተከተልኝ አላሉም። ምነው እነኛ የኦሮሞ አዛውንታት የታማኝነት አድባሮች ወደ ርሰተ ጉልታቸው መሠረት ወደ ሆነው ጎንደር ተመው በነበረ ታዩት ነበር ሐሤቱን። ፍቅር ልብስ አይደለም። ፍቅር ደም ነው። ፍቅር ውጪያዊ በኮስሞቲክ የሚሸበብ አይደለም የውስጥ ማንነት ነው።

የጎንደሩ ጉባውኤው አኮ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የጡንቻ ሙሉ ፓኬት ነበር። ትንፋሽ ተወጥሮ፣ መንፈስ ተንጠልጥሎ፣ የስጋት ግጥግጦሽ ፍርሃት ማጫ የተማታበት። ህዝቡን ማማን አልቻሉም እነ ተጋሩ ያመኑት ጠበንጃቸውን ብቻ ነበር። ለነገሩ ታማኝነትን የማያውቅ እንዴት ሌላውን ሊያምን ይችላል? ጎንደርን ሳያምኑት ነበር ወደ ጎንደር የሄዱት። ያደረጓትን ስለሚያውቁ። ይልቅ ቀደም ብዬም እንደ ተናገርኩት ጎንደር ከሚገኙት ተጋሩዎች ጋር ጥሩ ሃርሞኒ አድርጋችኋዋል። ሁለመናውን የሚቆጣጠሩት እነሱው አይደሉ … „እሚሉሽን ባልሰማሽ“ ነው … ንገሩን ባይ …

 

እናቴ እባከዎትን ጡር ይፍሩ። ቢያንስ ፈጣሪን?

 

ምን ጎንደር በዘመነ የትግሬ መሳፍንት ያልሆነው፤ ያልተዋረደው፤ ያለጣው ነገር አለና። ሥጋውስ አልቋል ለአጥነቱ ሰላም በሰጣችሁት። 40 አመታት ሙሉ ያለማቋረጥ የዋይታ ቤተኛ ነው – ጎንደር። የክርስቶስን ስቃይ – ህማማት የተቀበለ። የታቦር ተራራ። እናትዬ አሁንስ ተሸክሟችሁ ያለው እኮ ቻዩ፤ ሆደ ሰፊው፤ ታጋሹ፤ ሰብዕዊው ጎንደር አይደለምን? እህልና እውሃው ማን ሆነ እና?

 

ስንት ጊዜ ሰው ይገረማል? 

ስንት ወገን የወልቃይት የጠገዴ አባወራ እና እማ ወራ፤ ወጣትና ጉብል የአፈር ስንቅ የሆኑት፤ የካቴና እራት የሆኑት፤ የባዶ ስድስት ቤተኞች፤ በጢስ ታፍነው፤ በሳት ተንገብግበው ስንት ወገኖቻችን ነው ያለቁት? 40 ዓመት ሙሉ ጎንደር በትግራይ ምክንያት ጥቁር እንደለበሰች ነው። ጎንደር ከነተጋሩ ሥርዓት ውጪ ጠላት የላትም። ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሆነባት በሞቷ ይደነሳል፤ ይጨፈራል፤ የጎንደር ህዝብ እያበላ – እያጠጣ፤ ተጎነብሶ ያገለግላል ለጌቶቹ¡ …. ለጎንደር እርቁ ቀርቶበት ባርነቱ ፈቅዳችሁለት ሰላሙን በሰጣችሁት። ህጻናትን በባሩድ ባልቀቀላችሁ። ልጆቹን ልቅም አድርጋችሁ ወስዳችሁ ማዕከላዊ አሳሩን የክርስቶስን ስቃይ ታሳዩትአላችሁ፤ የቀሩትን በምግብ ብክልት በዬተገኙበት ቦታ ሁሉ ታድነው ለአፈር ስንቅ ሆነዋል፤ ሌሎቹ ደግሞ በቢላዋ ጫካ ገድላችሁ ትጥላላችሁ? ኧረ የእናትውስ የጉድ ነው! ከሰው ተፈጠራችሁ ለማለት ይከብዳል። ብናኝ ፈርሃ-እግዚአብሄር የነሳችሁ የጉድ ቁንጮዎች፤ አያድርግብኝ እንጅ እኔ እናንተን ብሆን እግሬን ከመቀሌ አላነሳትም ነበር። በፍጹም በህልሜ እንኳን አላስበውም። በምን የእውነት አቅም።  በዬትኛው የስብዕዊነት አቅም?… በዬትኛው የሃይማኖት ጥንካሬ? እንዴት ይሆናል? ቀራንዮ ጎለጎታ ያደረጋችሁትን መሬት ላይ እርቅ …. አቤት ያንት ያለህ ነው … እፍረተ ቢሶች … አሁን ሽም ሽር እየሰማን ነው። ለእኛ ያው ነው። ከዝንጀሮ ቆንጆ ነው። አንዱ ፈርዖን ቢነቀል ሌላዋን ፈርዖኒት ተክቶ ነው። ሄሮድስ ሲሞቱ አባይ የሄሮድስነቱን ቦታ ተኩ … ለእናንተ ይመቻችሁ። ለእኛ ግን የጨለማ ሽግሽጎሽ ነው። የመከራ ጥርኝ ነው። ከጭራቅ ጭራቅ ማማረጥ አይቻልም። አዲሱ ቶን ቀለማሙን ኢትዮጵያዊነት የሙጥኝ ማለት እንደሚሆን እንውቃለን፤ ሥማችሁንም እሰከመቀዬር ልትሄዱ ትችላላችሁ፤ መርዝ መርዝነቱን አይለቅም በፈለገው ውሃ ውስጥ ቢከዘን። ኢትዮጵያዊነት በውስጣችሁ አልነበረም የለምም።

 

ግፍና እግዚኦታው።

 

በትግራይ ዘመንተኞች የተወረሩት የጎንደር እና የወሎ ግዛቶች አስተዳደሩ ተከድኖ ይብሰል፤ እዬዳሁ ለመኖርም ፈቃድ የለም። አማርኛ ቋንቋ ተናጋራችሁ/ አማርኛ ዘፍን ሰማችሁ ተብለው ምን ፍዳ ላይ እንዳሉ አያውቁም „እኔ ኮራሁባቸው የተባሉት እናት?“ሎቱ ስባሃት ለጸሐፊው። የመንፈስ እከክ ይሉታል ይህን መሰል ግብዝ ግንዛቤ። ለመሆኑ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ የሚወለዱ የወልቃይት እና ጠገዴ እናት ልጆቻቸው አባት አልቦሽ ሆነው ሴቶች ተገደው እዬተደፈሩ፤ የሥነ – ልቦና ጥቃት እዬተፈጸመባቸው፤ በጉስቁል በእናቱ ሥም የሚጠራ ስንት ልጅ ነው ጎንደር  ያላት? ይህ በፋሽስት ጣሊያንስ ሆኗልን? „አማረ ነኝ“ ስላለ ብቻ እኮ ነው፤ ለዚህ ቨትረ ሥልጣን ደሙን ገብሮ ያበቃን ወንድም ኮ/ደመቀ ዘውዴ አስራችሁ እያንገላታችሁት ያለው? ልጆቹን ስንቅ አልባ አድርጋችሁ በጭንቀት ማጥ ውስጥ በስጋት የከተታችሁት። የእናንተዎች ደግሞ በኮንፒተር ተደግፈው ይማራሉ – ሰላምን እየጨለጡ። ለመሆኑ ማተብ አላችሁን? ለመሆኑ ሃይማኖት አላችሁን? ለመሆኑ ይሉንታ አላችሁን? ለመሆኑ በዚህ ባልደረቀ የደም ጉዞ ስለነገ ስላልተወለዱት የትግራይ ህጻናት አስባችሁ ታውቃላችሁ? በሰላም ጥያቄ ያቀረቡትን፤ እነ አቶ አታላይ ዛፌ፤ እነ ንግሥት ይርጋ፤ እነ  መብራቱ ጌታሁን፤ እነ አቶ ጌታሁን አደመ ሰረጸ፤ እነ አቶ አለነ ሻማ በላይ፤ እነ አቶ ነጋ ባንተይሁን ምንድን ናቸው ሰዎች አይደሉንም? ማነው አሁን ወንዶችን እስር ቤት እዬሰለበ/ እያንኮላሸ ልክ እንደ እንሰሳ፤ ሴቶችን እዬደፈረ ያም አልበቃ ብሎ ጥፍር ሴት እስረኛ የሚነቅል የእርስዎ የማህጸን ፍሬ አይደሉምን? ንግሥት ይርጋ የእርስዎ ልጅ አይደለችምን? ቀን ያሳለፈለዎት የልጅ ልጅ ናት ንግሥት ይርጋ ማለት  ስለምን ስለ እሷ አይሟገቱም? ወንዶችስ ወንድሞቾዎት አይደሉንም? …

ሐምሌ አቦዬ የ12ኛ ክፍል ፈተና ይሰጥ በነበረበት ወቅት ምንም የማያውቁ ህጻናት ተዘግቶባቸው በቦንብ ሲቃጣሉ እኒህ አናት የት እንዲያው የት ነበሩ? ባለሐሤቱ ጸሐፊ ለዚህ መልስ አለዎትን? ይህ ስለሆነ ነው ጸሐፊው ፍንክክን ብለው ጉሮ ወሸባዬ የሚሉት። አበሰኩ ገበርኩ …. አድነኝ ከእንዲህ ዓይነት ማተበ ቢስነት … ሆነ ኢ-ሰብአዊነት …. ከሰደበኝ የነገረኝ … ከገደለን የነማህበረ ሳዖል ዘመን የርስዎ ዕይታ ይሸታል – ይከረፋልም።

አዬ እናትነት አንጀቴ ስንት አዬን እቴ¡  

መቼስ ባህርዳር ላይ አንድ የጠገበ ተጋሩ 50 ወጣቶችን በደቂቃ ሲመትራቸው በባሩድ የት ነበሩ?። ጎንደር የተዘረፈው – ተዘርፎ፤ የተጋፈፈው – ተጋፎ፤ የተሸነሸነው – ተሸንሽኖ ሥን – ልቦናን ለመተርተር መቀሌ ላይ የተከፈተው የቅማንት ቢሮስ ስለሱስ ምነው አንድ አላሉም እኒህ የተጋሩ ቅምጥልጥል?

የአንባ ጊዮርጊስ እናት የሳቸው ዘሮች ጭፍጨፋ አልበቃ ብሎ፤ ከሱዳን በመጣ ወታደር እንደዛ ፍጹም በሚዘገነን አኳኋዋን እነዛ ታዳጊ ህጻናት ሲጨፈጨፉ፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ የተሰደደችበትን የመከራ ጊዜ ያሳስባል። እነዛ ከእድፍ፤ የተጣፈ ልብስ ያልተላቀቁት የአንባ ጊዮርጊስ እናቶች ወንድ ህጻናት ልጆቻቸውን ይዘው ጫካ ሲሰደዱ፤ ሬቻ ላይ በቀን 600 ወገን ሲረግፍ? ኧረ ጉድ ነው ለመሆኑ እኒህ „የሚኮሩ እናት¡“ ተብለው መወድሱ የተነበበላቸው የተጋሩ እናት ዓይናቸውስ መንፈሳቸውስ የት ላይ ነበር?  ወለጋ ላይ ወ/ሮ ታደሉ ልጃቸው ተገድሎ በሬሳው ላይ ተቀመጥው ሲደበደቡ ከቶ እኒህ እናት የትኛው ፕላኔት ላይ ነበሩ? ያን ጊዜ እኮ ሴት ነኝ የሚል ሁሉ መድፉን ጥሶ አደባባይ መውጣት ነበረበት፤ ሌላ ቦታ አይቻልም የትግራይ እናቶች ግን ቢያንስ ቤተ እግዚአብሄር ላይ ተገናኝተው ከአምላካቸው ጋር በአደባባይ በመከሩ? ማይ ጣይቱ ለይስሙላ ነበርን? ግን አልሆነም።

ከታላቋ ትግራይ ከልዕልት ቀዬ በስተቀር ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቀፍድዳ ሴት ልጆች ሲደፈሩ፤ የህዝብ አንጡራ ሃብት በዘመቻ ሲጋዝ፤ የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች የበቀል የጽዋ ማወራራጃ ሲሆኑ ግን እነኝህ ሴቶች/እናቶች ለማለት አቅም ይኖራል? በደል ይረሳል ወይንስ በዕጥፍ ያርሳል? አዎን የጎንደሩ ጉባኤ በእጥፍ በግፍ ያረሰን ነበር ።

እነኛ 20 ሺህ  የአማራ ወጣት በአንድ ወር ውስጥ ካለ በቂ መጠለያ – ህክምና – ምግብ አሳሩን ሲከፍል፤ ት/ቤቱ ሁሉ እስር ቤት ሲሆን፤ ማታ ማታ በዱላ ብዛት ያ ቀንበጥ እዬሞተ የትሜና ሲቀበር፤ የጎንደር ቅዳሜ ገብያን ያህል የህዝብ ሃብት፤ ጉሮሮ፤ የሀገር ቅርስ ከትግራይ ተነስተው ቤንዚንና ክብሬት ይዘው ሲቃጠል – ሲነድ፤ ሺዎች መጠጊያ አልባ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በግፍ ድርብ ሲታሰሩ – ሲማገዱ፤ እስር ቤቱን የሞላው እኮ የስሜን ጎንደር ወጣት – ጎልማሳ – አዛውንታት እኮ ናቸው። አሳዳጁ – ዳኛው – ፈራጁ – ህጉ –  ገዳዩ – ደብዳቢው – ጥፍር አፍላቂው – ደፋሪው – መስቃ ተናጋሪው – አንኮላሺው ደግሞ ትግሬ ነው።ምነው ፈጣሪ በሠራው ፍጡር መከራ ባንጨፍር? ኧ ትግራይ ላይ ያለኸው ማተብ የት ይሆን ያለኸው? ኧረ ትግራይ ላይ ያለኸው ሽበት ተጠዬቅ? ኧረ ትግራይ ላይ ያለኸው ገዳመ ደብረ ዳሞ ተጠዬቅ?

ጎንደር እኮ ከቀበሌ ገበሬ ማህበር በታች ናት። የሪጅን አቅም ለሆን እንኳን የተሳናት።

https://www.youtube.com/watch?v=iyEjZ0bGM94

ኢትዮ-ቴሌኮም በጎንደር ከተማ ሪጅን ባለማቋቋሙ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም፡-ደንበኞች“

 

ባለጊዜዋ እመቤት ….

አያወቁም የጋይንት ገበሬ እናንተን ቁሞ እንደሚያበላ። አያውቅም የሰቲት ሁመራ ካሽ ክሮፕ መዋለ ንዋይ ለትግራይ ልማት እንደሚውል። ዛሬ እኮ የአዲግራት አጠቃላይ ሆስፒታል ለህሙማን በነፃ ነው ህክምና የሚያደርገው። ጠበቃ ለሌላቸው ደግሞ ከዬትኛውም የትግራይ ቦታ ይሁን ጠበቃ ቀጥሮ ይከራከርላቸዋል። አዲግራት የኢትዮጵያዊቷ ሲዊዝ ናት። „#EBC የአዲግራት ዩንቨርስቲ በሚሰጠው ነፃ የህግና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን 25.11.2017“ ዘግቦት አዳምጫለሁ። በማን አንጡራ ሐብት ነው ይህን ያህል መንጠባረሩ? ጋንቤላ ላይ መሬት ላይ ነጠላቸውን አንጥፈው ህሙማን ባሊህ ባይ የላቸውም። የሆስፒታሉ ግንባታውም ቁሞ ቀር ሆኗል። ሃብቱ የጋንቤላ ተዝርፎ ግን ትግራይ ላይ ለዛውም አዲግራት ነፃ የህክምና አገልግሎት ለሁሉም በሽተኞች ይሰጣል። ይህም ብቻ ሳይሆን ሆስፒታሉ ጠበቃ አቁሞ ለባለጉዳዮች ይከራከርላቸዋል። ጠበቃ ማቆም ለማይችሉ የታላቋ ትግራይ ዜጎቹ። ያው ያለው ዜግነት ትግራዊነት አይደል።

አባቶችን የሃይማኖት እንኳን አያዩም የሚደርስባቸው ፍዳን አይሰሙም? እንደዚህ ዘመን የሃይማኖት አባቶቻችን የእስልምናም ሆነ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተሰደው ያውቃሉን? አሁን እስር ቤት የሚደርሰው የደናግሉ ስቃይ – ምን አደረጉ እነኝህ የዋልድባ ቅዱሳን። ምን ሠሩ? በጸለዩ – ግርማ ሌሊቱንና የቀን ሐሩሩን ታግሰው በሰገዱ፤ በፆሙ ስለእኛ ስለምን ይሆን የሚሰቃዩት? ስለምን እኮ ስለምን? ኧረ እግዜሩን ፍሩ ዕምነቱ ካለ? ኧረ አላህን ፍሩ ሃይማኖቱ ካለ ወጣቱን አታንገላቱት – ለህክምና አብቁት? ሊሆን የሚገባው እኮ አካኪ ሳይሆን ጥጋባችሁን ተግ አድርጋችሁ፤ ስለግፈኛች ልጆቻችሁ ሱባኤ ነበር ልትይዙ የሚገባው። እግዚአብሄርን ለምኑት በጽናት የሰው ልብ፤ የእናትነት አንጀት እንዲሰጣችሁ። ስለ ሰብዐዊነት ግድ እንዲሰጣችሁ። ስለ ተፈጥራዊነት እንድታስቡበት። ለምኑት የሁሉን ፈጣሪ … እናትነት ጸጋችሁ እኮ በኗል ወርቅና ጨርቅ ላይ ነው ነግሦ ያለው …

እርግጥ ነው የአዲግራት ዩንቨርስቲ በሚሰጠው ነፃ የህግና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን ሰብዕዊነቱን ወድጀዋለሁ፤ ይህ ሰብዕዊነት ሌሎች ኢትዮጵያ መሬቶች ላይ ቤተ ተጋሩ ይህን ያደርጋሉ ወይ ስለሚለው ግን … ዳሽ ነው። መሃንነቱ በቀረላቸው? የተሳሰተ መዳህኒት መሰጠቱ በቀረላቸው፤ መግደሉ ብቻ ሳይሆን ግድያው ከወቀሳ፤ ከዘለፋ፤ ከማንቋሸሽ ጋር መሆኑ በታገሰላቸው አብሶ አማራን …

የአማራ እናት ዛሬ ከብት የሚያቆም ጉብል ከብት ጠባቂ የላትም – መክናለች፤ ወንዱም ተንኮላሽታል፤ ለመታጨት የደረሰች፤ ማጫ የሚማታላት ባለ ጋሜና ታሪ የላትም። አልሰሙም አማራ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄደው ጥናት በዓይን ህመም/በትራኮማ/፤ በትምህርት፤ በጤና አጠባበቅ በሁሉም ዘርፍ የመጨረሻው ስለመሆኑ። እስር ቤቱን እኮ በአማራ እና በኦሮሞ የተሞላ ነው።

አዎን ሞት ለአማራ ድህንት ለትግራይ። አዎን መከራ ለአማራ ብሥራት ለትግራይ። ስቃይ ለአማራ – ትፍስህት ለትግራይ። መሰደድ ለአማራ ፋሲካ ለትግራይ። ቆላማው የአማረ ቦታ በወባ በሽታ እንዲያልቅ ተፈርዶበት የወባ ማጥፊያ ድርጅት ተዘግቶ ወደ ትግራይ ተዛውሯል። ኧረ ስንቱ … ሰማይና መሬት ቢቀጣጣል የነገረ ትግራይን ናዚዝም ተጽፎ … ተጽፎ… ተነግሮ… ተነግሮ አያልቅም  ….

የዛሬ ዓመት 20 ዓመት ዕድሜ ያሰቆጠረ የወያኔ ተፎካካሪ የተጋሩ አንድ ድርጅት ለፊርማ መጀመሪያ በ6 ቁጥር ተጀምሮ 50 እንኳን ፊርማ ውጪ ሐገር ማሰባሰበብ አልቻለም። 30 ላይ ነበር የቆመው። ሰሞኑን በታዬው የመቀሌ የአረና ሰላማዊ ሰልፍም 6 ነበሩ።  የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል „ሐገርን እግዚአብሄር ካልጠበቀ ወታደሮች /ሠራዊቱ በከንቱ ይደክማሉ“ ። ዛሬም እንደ ትናንቱ ማላገጥ፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ ማባጫል፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ መሳላቅ፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ ማዳዳጥ የነገን እንጃ ነው ….

አቤት! የተከሳሾቹ ብዛት ….

ሌላው የገረመኝ በዚህ ተከሳሾቹ ኢሳት እና አርቲስት ታማኝ በዬነ መሆናቸው ነው። ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ። ቀድሞ ነገር አቶ ታማኝ ብሄር ወይንስ ጎሳ አለውን? የለውም። እሱ እኮ ብሄርአልቦሽ ነው። እንዲያውም በአማራ ተጋድሎ ሰሞናት አንድ የሥጋ ዘመዱ ነኝ፤ ላልኖር ወይንም ልታሰር እችላለሁ አልገባውም ታማኝ እያለ የሚጽፍ ወንድም ነበር። አቶ ታማኝ አይደለም አማራነቱን ጎንደሬነቱ እራሱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ የሚያወቀው ፈጣሪ ነው። ሁለት ጊዜ እዚህ ሲዊዝ መጥቶ አይቸዋለሁ። እኔ ያዬሁት ጎንደሬዎች ወደ እሱ ሄደው ግንባራቸውን ሲያስመቱ እንጂ እሱ ጎንደሬያዊ ስሜቱ ሆነ ፍላጎቱ ኖሮት ቀርቦ ችግራችሁ ምንድን ነው? እንዴት ናችሁ? ሲል አላዬሁትም። ሌላው ቀርቶ አርቲስት ታማኝ በዬነ ሌሎች የአካባቢያቸውን ሰው ደግፈው፤ እረድተውና ከብክብክብ የማውጣት አቅማቸው አንቱ ነው። እሱ ደግሞ ከዚህ ውጪ ነው። ለዚህም ነው ከእሱ ውጪ ሌላ ዓዬነ – ገብ ጎንደሬ  ከእሱ ከእራሱ ውጪ ልናይ የማንችለው። አርቲስት ታማኝ በዬነ ልዩ የሆነ የጎንደር ጌጥ አይደለም። ይልቁንም አርቲስት ታማኝ የኢትዮጵያና የኢሳት ጌጥ ነው ቢባል የተሻለ ይመስለኛል። ብቻውን ነው ሲሮጥ የነበረው። የመንፈስ ተተኪዎችን በዙሪያው በተጠና እና በታቀደ ሁኔታ የማሰባሰብ አቅም የለውም። አጥር አልሠራም። የተጨነቀበትም አይመስልም። ይህ በእሱ ብቻ ሳይሆን በዛች ባልታደለችው ጎንደር የተፈጠሩ እትብተኞች ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የአማራ ሊቃናትም ችግርም ነው። አቦ አባ ዱላ ገመዳ ደግሞ መሠረታቸውን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ የማይቻለውን ችለው ሲያደርጉ እንደ ነበረ የፖለቲካ ተንታኙና ጋዜጠኛው አቶ ኤርምያስ ለገሰ በዝርዝር አስረድቶናል። ልብ ያላቸው ይህን ይሠራሉ። ሁሉንም ሳይጎዱ – ሁሉንም ሳያስከፉ።

የሆነ ሆኖ አርቲስት ታማኝ በዬነ አማራነቱንም ቢሆን የሚያውቀው እሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በተጨማሪም አማራ ነኝ ማለትም ሆነ አማራ ነኝ አለማለትም መብት ነው። ምንድ ነው ያለው ጋዜጠኛ በፈቃዱ ማንነቴ „ድህነት“ ነው አይደለም ያለው። ሐገሬም የተወልድኩባት „አዲስ አበባ“ ናት ነበር ያለው ከብራና ራዲዮ ጋር በተለዬ ሁኔታ ከዬኔታ ሙሉቀን ጋር በነበረው የውይይት ቆይታ። መብት ነው ሆንኩኝ አይደለሁም ለማለት። ወለጋ መወለድ ኦሮሞ እንደማያደርግ ሁሉ ጎንደር መወለድ በራሱ አማራ ሊያደርግ አይችልም። ይህ ሁሉም አካባቢ ያለ አምክንዮ ነው። አርቲስት ታማኝ በዬነ „አማራ ነኝ“ ብሎም አያውቅም። አማራ ነኝ ሳይል የአማራ ተጋድሎ አነሳሽ፤ አነቃቂ፤ አቀንቃኝ ሆነ ቤተኛም ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ሎጅኩ አያስኬድም። አልደከመበትም። በአማራ ተጋድሎ የነበረውን ዝንባሌ ቅርበትም በትጋት ስንከታተለው ነበር። እጅግ አሳሳቢ እና ውጋት የበዛበት ተጋድሎ ስለነበረ። በሚዲያ አቅም እንኳን አንድም ቀን „የአማራ ተጋድሎ“ በሥሙ ተጠርቶ ሲዘገብ አልተደመጠም – ልጅ ታማኝ በደከመለት፤ በተንከራተተለት ሚዲያ። „ባለቤቱን ካልፈሩ አጥሩን አይነቀንቁም“ እንደሚባለው ሆኖ። ይልቅ „መሬት /እስራኤል/፤ SBS /አውስትርልያ/ ፤ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ /አሜሪካ/፤ በሚገርም ሁኔታ በትጋትና በባለቤትነት፤ በተቆርቋሪነት ፍጹም በሆነ ስሜት ህብር ራዲዮ /አሜሪካ/ የድምጻችን ይሰማ BBN ኢትዮ ዩቱብም በሚገባ የእኔ ብለው ታታሪዎችን፤ ይመለከታቸዋል ያሉትን ሁሉ አወያይተዋል። አመክንዮውንም አብሰለውታል። ለአማራ ተጋድሎም በቂ ዕውቅና ከአክብሮት ጋር ሰጥተውታል። እነኝህ ሚደያዎች አመክንዮውን አልይህ ብለው አልገፈተሩትም። ወቅቱን አድምጠዋል። ከወቅት ጋር አልተላፉም። ከድህረ ገጽም ሳተናው እና ዘሃበሻ ብቻ ነበሩ የአማራ ተጋድሎ ደጋፊዎቹ፤ በቁርጥ ቀኑ እና በፈተናው የተገኙት፤ ለተጋድሎውም ዕወቅና በመስጠት አረገድ ሆነ ለዛች መከረኛ ማገዶዋ ጎንደር በመንፈስ የአይዞሽን ስንቅ የቀለቡት። ይመስገኑ – ይከበሩ። ታሪክ የማይረሳው ረቂቅ የተግባር ሰናይ ከዋኞች ናቸው እና። ጸሐፊዎችንም አላገለሉንም።

በዛን ጊዜ እልሁ፤ ጥቃቱ አይደለም ሰውን ቁሞ የሚሄደውን የሞተ ሬሳ የሚቀሰቅስ ነበር የግለቱ ክርፋት። እኔ እራሴ እልሁ እና ቁጭቱ ነበር ድብቅ ብዬ ከተቀመጥኩበት ገዳሜ ወጥቼ የምለውን ያልኩት። ዘገርድያን ሳይቀር ጎንደርን ሚዲያ የሌላት ከተማ ሲል ነበር የዘገበው። ይህ አይቆጠቁጥም? ይህ አያንገበግብም? ከዚህም በተጨማሪ ጎንደር ላይ በነበረው ገድል ዙሪያ የነበረው ሙግትም ቀላል አልነበረም። ሰበር ዜናዎች እና ዕድምታውም አስጨናቂ ነበር። በአውሮፕላን የሚያስጨፈጭፍ ነበር። ስለሆነም በጽኑ እንከታተለው ነበር። ለመሆኑ እኛ የገፋነውን መከራ ማን ጥቁር ቀሚሱን ሊለብስልን ኖሯል? ጎንደር የነበራት አንድ ዓይነ እሱ ብቻ ስለነበረ ሁሉንም በተደሞ አዳምጠናል። ነገር ግን የአርቲስት ታማኝ በዬነ መንፈሱ ከአማራ ተጋድሎ ጋር የተቆራኘ አልነበረም „ከነፃነት ሃይል“ ጋር እንጂ። ተጋድሎው በግራ ቀኝ በወጀብ ሲናጥ ሁነኛ አልነበረውም። ተቆርቋሪ አልነበረውም። ታታሪ ወጣቶች የነበረባቸው ፍረጃም ይህ ነው አይባልም። እንኳንስ አማራና ትግሬ እያለ ፕሮፖጋንዳ ሊነዛ ቀርቶ። እሱ በደከመበት ኢሳት እኮ ነው „የትግራይ ድምጽ“ ያለው ትግርኛ ተናጋሪዎች የሥራ ዕድል እና የታወቂነት ማክዳም እንደ ተጠበቀ ሆኖ። „ለተራበ ትቼ ለጠገበ አዝናለሁ“ እንዲሉ … እንጂ የአማራ ድምጽ አይደለም ኢሳት ያለው። አርቲስት ታማኝ በዬነ መረጃ የማሰበሳብ ጥሩ ተስጥዖ ስላለው እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊ አጀንዳዎች ወይንም ዘውገዎች ነገረ የአማራ ጉዳይ በእሱ ህሊና ያላው ቦታ በ1/80 ደረጃ ያያቸው ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እንደተጠበቁ ሆነው። ሲሰራማ እንደሌሎቹ እሞገትላቸው እንደ ነበሩት ወገኖቼ ጉዲት እስክባል ድረስ ተማግጄለታለሁ … እሱ ከቁጥር ባያስገባውም ከመጤፍ ባይቆጥረውም።

ብቻ በምን ሂሳብ ተዘዋውሮ በጥናት በተመሠረተ፣ ዳታዊ መረጃን በከወነ፤ እጅግ በሚመስጥ ቅንነትና ፖለቲካዊ ጨዋነት አማራዊ ጉዳትን ውስጡ ካደረገ፤ ከቦታው እዬተገኘ ፍዳውን የእኔ ካለ ከዬኔታ ሙሉቀን ጋር „አማራ ነኝ“ ያለለው አርቲስት ታማኝን ለአማራ ተጋድሎ ቅርበት ተመዛዝኖ እንደታዬ አላውቅም። በፍጹም ሁኔታ የተሳሳተ መረጃ ነው። የተሳሰተ ግንዘቤም ነው። ድፍን የጎንደር  ህዝብ እኮ ያውቀዋል ውጪም ያለው ሀገር ውስጥም አለው። በሚገባ በተደሞ ታዝበነዋል። ከዚህ በላይ መሄድ አልፈልግም።

ኢሳትም እንደ አቶ ታማኝ ብሄር አልቦሽ ነው። እንዲያውም ድምጽ አልቦሽ ናችሁ ተብሎ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በኢሳት የተጋሩ ድምጽ አለ፤ የፕ/ኢሳያስ አፈወርቂ ካቢኔ ልዩ ሃይል ወይንም የኮማንድ ፖስት ብቸኛው አለኝታ ቲፒዴኤም እንዲሁ ድምጽ ነበረው፤ እንጃ አሁን ይቀጠል አይቀጥል አላውቅም። ስለዚህ ሁለቱም አርቲስት ታማኝ በዬነ ይሁን ኢሳት ሊወቀሱ፤ ሊነቀሱ ከቶውንም አይገባም በነገረ አማራ የተጋድሎ አመክንዮ። ሥማቸውም በአማራ ዙሪያ ሊነሳ በፍጹም አይገባም። በሌላ በኩልም ለአማራ ተጋድሎ በእነሱ የጥረት ውጤት ነው ሊባል አይችልም። በአዎንታዊም ሆነ በአልታዊ ጎኑ ሁለቱንም ማንሳት አግባብነት በፍጹም ሁኔታ የለውም። „ላም ባልወለበት ኩበት ለቀማ ነው“  የሚሆነው። ለነገሩ  የአማራ ተጋድሎ ታታሪዎች ሲታሠሩ ክሳቸው በግንቦት ሰባቶች/ ሻብያዎች አይደል የሚባሉት። ግን ጭብጡ አይገናኝም። ግንቦት7 ሆነ ሻብያ ለአማራ ስሜት ቅርብ አይደሉም። በፍጹም። ጅማ ላይ፣ ባሌ ላይ፣ ሐረር ላይ፣ አርሲ ላይ፣ አፋር ላይ፣ የሚታሠሩ ወገኖች ግንቦት / ሻብያ አይባሉም፤ በእነዛ አካባቢዎችም ግንቦት 7ም አለሁኝ – ተከሰትኩ ብሎ አያውቅም። ስለምን ግንቦት ሰባት የአማራ ድርጅት ተደርጎ እንደሚወስድ ግራ ያጋባል። ግንቦት 7 የትኛውንም ብሄረስብ አይወክልም፤ ከንባታውን ይሁን አፋሩን … እኔ እንደሚሰማኝ ብሄር አልባ ነው … ለጉራጌውም ግድ አይሰጠውም፤ እንደ ሌሎች ብሄረሰቦች ነው የሚያው “ለዴሞክራሲ“ ነው አጀንዳው።

የሆነ ሆኖ ያለው ዕውነት አማራ በዞጉ እንዲደራጅም አይሹም። የአማራ ሊቃናትም ቢሆኑ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ናቸው። አይፈልጉትም „አማራ ነኝ“ ብሎ መውጣቱንም ሆነ መደራጀቱን። የአማራ ሊቃናት አማራ ነኝ ብሎ መውጣት የሚያሳፍራቸው እና በእጅጉም የሚጸዬፉት አመክንዮ ነው። ያፍሩበታል። ይሸሹታል። ቁሞ የሚጠብቅ አምክንዮ እንደሌለ እንኳን ሊገነዘቡት አልቻሉም። ሥጋ ተሸሽቶ የሚቻል ከሆነ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። ጥግም ከተገኘ። አሁን የምንአዬው የወ/ሮ ሄሮዳዳይ አዜብ መስፍን ችግርም ይሄው ነው። አሁን ንጥሯን የትግራይ ልጅ አምጥተው ቁብ ያደርጓታል እነ ተጋሩ። ምን አልባትም አዲስ የሴት ጠ/ሚር። እስከ አሁነም ትክን እያሉ ነበር ወ/ሮ አዜብን ተሸክመው የኖሩት። ወ/ሮ አዜብ ደግሞ የትግራይ አለቅላቂ ነበሩ። እነ ተጋሩ አለቅላቂነታቸውን ቢቀበሉትም የእነሱ ደም እንዳልሆኑ ያወቃሉ – ጠንቅቀው። የተውሶ ልብስ ተመልሶ እንደሚሄድም አላስተዋሉትም የመሪነት ባልህልሟ ድሃዋ¡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን። እንቦጩስ በሳቸው ህልም ላይ ነው የተመመው … እንቦጭ አሉ።

ቤተሰባዊ ተወልጅነትን መተላለፍ ጦሱ ለልጅ ነው የሚተርፈው። ሌላው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከሚታወቀው ዞጉ በላይ በህዝብ አደባባይ ተጨማሪ የዚህም ዘር አባል ነኝ በማለት አቅም ማከማቸት ወይንም ጥግ ሲሻ አማራ ግን ዞጉን አንደ አባ ጨጓሬ ይፈራዋል። እራስን ማግለል፤ አራስን መጸዬፍ የት ሊያደርስ እንደሚችል ባይታወቅም፤ ራስን ሳያከብሩ ሌላውን አከብራለሁ ወይንም አቀርባለሁ ማለትም የሚቻል አይሆንም። ራስን በሰብዕዊነት መንፈስ ውስጥ ባለቤት ሳያድርጉ የሰብዕዊ መብት አቀንቃኝ መሆንም አይቻልም። ይሄ የሃቅ እንክብል ነው። የሆነ ሆኖ በአማራው አማራዊ ተጋድሎ ውስጥ ያሉት ጎርበጥባጣ ጉዳዮች የተጋሩ ብቸኛው አውራ ህልም ነው። ሄሮድስ መለስ ዜናዊ እኮ „አማራ ሳይሆን ሃሳቡ ብቻ ነው መወከል ያለበት“ ያሉት ይህም ማለት የአማራ ሥጋና – ደም ውህደት ሳይሆን አማራ በስማ በለው ነው ድርጅቱ መዋቀር ያለበት ነበር ያሉት። አድርገውታልም። ይህን መሰል እጅግ ሽንክና ማሽንክ የሆነ ቲወሪ ነው የነበራቸው ሄሮድሱ። ሁሉም ክተት ያለው በዚህ መንፈስ ውስጥ ነው ከሊቅ እሰከ ደቂቅ። የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የሴራ ፖለቲካ ሰለባ victim ነው የተሆነው። ስለሆነም አማራ ባሊህ አልባ፤ ተቆርቋሪ አልባ ዛሬ ካለው የመከራ ዳጥ ውስጥ ይገኛል። የሁሉም ሕልም ከሊቅ እስከ ደቂቅ አማራ በሥጋና – በደሙ ነፍሱ እረፍት እንድታገኝ አይፈልግም። ባልተወለዱት የምህረት ብጣቂ ለማኝ እንዲሆን ነው የሚታሰበው። እሱም ከተሳካ ጆሮ በብድር ከተገኘ።

አማራው ጀርመን ከዓለም የመዳህኒት ፈላስፋነት ጉብ ያደረጋት ሚስጢር አልገባውም። የአውሮፓ ሊቃናትም ሆነ ሥልጣኔያቸው መሠረታቸው ከአማራ የቀደመ ፍልስፍና የተነሳ ስለመሆኑም አልተረጎሙትም። አማራነት በሥጋ ሲአልፉ እንኳን ሳይፈርሱ ለዘመናት ለመቀጠል የፈጣሪና የመሬት ቃልኪዳን የተፈጸመበት ስለመሆኑም አላስተዋሉትም። በውነቱ አማራነት አንገት የሚደፉበት፤ ወይንም ቅስም እንኩት የሚልበት ተዋራጅነት አይደለም። አማራነት ሙሉ ሰብዕና ከብቁ አቅም ጋር የተላበሰ ማንነት ነው። ሊወደድ ሊከበር የእኔ ሊባል የሚገባ ንጡር ማንነት ነው አማራነት። የቤተሰቤ የደም ንጥረን ነገር ስለምን እክደዋለሁ – እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ቆሜ እዬሄድኩኝ? አማራ ነኝ በማለቴ ከቶ ምን ሊቀርብኝ? የክብር – የሹመት – የሽልማት – የመወድስ ልቅምቃሚ እና ልቅላቂ … ቀልድ።

ይልቅ የሚፈራውም ይሄው አቅም ሃሳቡ ሳይሆን እኔ አለሁ ብሎ ሥጋና ደሙ ከነክህሎቱ አማራው ከወጣ፤ ጥገኛ ሆኖ ወይንም ተሽብልሎ ሳይሆን እራሱን ችሎ ቢወጣ ገጣሚውን የፖለቲካ መመጣጠን ምስሉን ስለሚቀይረው ነው። ቅኔው ተዚህ ላይ ነው። ስለሆነም አማራው እራሱን ሆኖ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ሽፋን ውስጥ ተደቁሶ፤ ወይንም ተጨፍልቆ ወይንም ተፈጭቶ ወይንም ደቆ እሱ ቀልጦ ሌላውን እንዲያበራ ነው የሚፈለገው … „በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበት“ እንዲሉ … የሰሞናቱ አቶ አለምነህ የሚባሉት ሆነ የነዲያቆን ዳንኤል ስብከተ ካቴናም ይሄው ነበር፤ የዶር ተስፋዬ ደመላሽ አዝለኝ ቅኖናም እንደተጠበቀ ሆኖ … ምስለ ግዕባዕቱ ሄሮድስ መለስን የእርቃን ደጀሰላም የሚሳለም  እንዲሆን የታሰበ ነው። እርቃኑን የቆመ ፖለቲካ ….

ቀመሩ መከራን ወደ ውጪ መላክ እና ማስመጣት Export and Import የማይችል ከመሆኑ ላይ ነው።

ስለ እኔ እራህብ እኔው እንጂ ሌላው ሰው ሊያውቅልኝ በፍጹም አይችልም። ራህብ በስማ በለው አይሆንም። ፍጥረተ ነገሩ የመከራ ምንጩ፤ አነሳሹ ከውስጥ ከቁስል/ ከመግል ነው የሚነሳው። ችግር – መከራ – ስቃይ – ፍዳ – ጭቆና ቀመሩ መከራን ወደ ውጪ በመላክ እና በማስመጣት Export and Import አይቻልም። ከውስጥ ነው የሚመነጨው። በሌላ በኩል ከሞት ጋር፤ ከስቃይ ጋር፤ ከመገለል ጋር፤ ከፍዳ ጋር፤ የሚኖረው ህዝብ ለሰቃዩ – ለሃዘኑ – ለመካራው ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ልክም – ደንበርም – መጠንም መስፈሪያም – ያልተሰራለት የናዚዊ የፋሽስታዊ የተጋሩ አገዛዝ አይደለም የአማራን ተጋድሎ ከዚያም ያለፈ ሌላ ዕድምታ ቢኖረው በፍጹም ሁኔታ የሚገርም አይደለም። እዛ የተፈጠሩ ሴቶች እንደ ተጋሩ በደል እና ልክ ማጣት እንደ ዩዲት ቢሆኑ አይደንቅም። እስከ ደንበር መጨረሻው ድረስ ቢሄዱ ሊገርምም አይገባም። በደሉ ልክ የለውም። ጎንደርን እኮ ሶርያ ነው እነ ተጋሩ ያአደረጓት። ይህን ጉድ ተሸክመው ከነባይረሳቸው ነው እርቀ ሰላም የሚሉት እንፋቲክ ከሙት ጋር እርቅ ማደረግ የሚቻል ከሆነ …

የሰማይ ጦሮ …

ሁለመናን ይህን ያህል መግረፍ በውነቱ የሰማይ ጦር/ጦሮም ያሳዝዛል። አባይ ለግብጽ ጎንደር ለትግራይ አንድ ነው ዕድምታው። እነ ተጋሩ ምን አላችው እና ነው ቁልቋል፤ አሞሌ እና አሸዋ ብቻ ነው ያላቸው። አሞሌም ለከብት ነው። ከብቱ ይኑር አይኑር እሚውቁት እነሱው ናቸው፤ ለዛውም ካለ ግጦሽ መሬት አልባ ከብት ከረባ። አሽዋም ለመሬት ነው፤ ቢበዛ ለሸንበቆ። መቼስ ቁልቋል ተብልቶ አይዋል አይታዳር … „በማን ላይ ቁመሽ እግዜርን ታሚያለሽ“ አይሆንም፤ አብረን „ተቀበርን ሲባል¡“  ለእንሱ ተንስዑ ጎንደር ጠፋች። በበቀል ፋስ ጎንደር ተፈለጠች። በትዕቢት ገጀሞ ጎንደር ተከተፈች። እመቤቲቱ …. ግፍ ፍሩ! ልዕልቲቱ ጥሩ ይፍሩ!

ደግሞ ገራሚው ስብከተ ኢትዮጵያዊነት ነው። ሙሽራዋ ትግራይ ተሸልማ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እዬታረደ፤ እንዲህ እዬተሰቀለ፤ እንዲህ እዬተደበደበ፤ እንዲህ እዬተዘረፈ፤ እንዲህ እዬተቀጠቀጣ … ኢትዮጵያዊነት የለም። ትውልድ በጭካኔ እዬተራደ፤ አያምርም እነ ተጋሩ ስለ ኢትዮጵያዊነት ባለሟል ለመሆን። አቅም የላቸውም። ከእነሱስ አፋር ጋንቤላ ቢል ያምርባቸዋል። ተፈታተሽን አኮ። የትግራይ ነፃ አውጪ ብሎ መሥርቶ ኢትዮጵያዊነት? ኢትዮጵያ ካለወደብ መቅረቷ ብቻ ሳይሆን ለሱዳን የተሰጠው የመሬት ጸጋ በታሪክ ዬትኛውም ሐገርና ህዝብ መንግሥት አድርጎት አያውቅም። ይህ የ21ኛው ክ/ዘመን አሳፈሪ ክስተት ነው። እኒህ እናት ስለምን ለሱዳን ሽልማት በቀረበው መሬት ላይ እንዲህ ግብግብ አይሉም – ስለ አንድነት ከሆነ፤ ስለ ልዑላዊነት ከሆነ ተቆርቋሪንቱ … ግርንቢጦች። እዛ ደንበር ላይ ያሉት ህፃናት በአጋዚና በሱዳን ወታደሮች እንደሚመነጠሩ አልሰሙም? ጆሮ ሊገዛ ቢችል ገዝቼ ብልክላቸው እንዴት ደስ ባለኝ ነበር …. ለ እኒህ ዘመናይት …

አንድነት በኣዋጅ አይመጣም፤ ፍቅር በፕሮፖጋንዳ አይመጣም፤ ደም በመስቃ ንግግር፤ በመታበይ አይድርቅም። በፍጹም። አማራ ዘሩን እንዲፈልስ፤ አማራ የተሰረዘ ማህበረሰብ እንዲሆን ተግቶ ተጋሩ እዬሠራ ነው። ደግሞም ሆኖለታል። „የትግራይ ተራሮች የአማራ መቃብር“  አይደል ዘፈኑስ ትንቢቱስ።  … ትግራይ አኮ ዛሬ የሚወዳደራት አንድም ከተማ የለም። ቆሻሻ የማይጣልባት፤ ሲጋራ የማይጤስባት፤ የፖለቲካ እሰረኛ የሌለባት፤ እስረኛ የወንጀሉም ቢሆን ቀን በነፃ ተለቀው ካሻቸው ሄደው ማታ ለአዳር ብቻ እስር ቤቱ የተሻለ ኑሮ ስላለው በፈቃዳቸው ይመለሳሉ። ትግራይ ከቻይና ከብራዚል ተርታ ተሰልፋለች፤ ዓለምዐቀፍ ተሸላሚም ናት። … ምርጥ ዜጎች በዬትኛውም ቦታ ዳኛ፣ መሪ፣ ፈራጅ፣ የኢኮኖሚ ሊቅ፤ የወታደራዊ ሊቅ፤ የውጭ ግንኙነት ኤክስፐርት፤ የድህነነት ልሂቅ፤ የማህበራዊ ኑሮ አንበል፤ የጥበብ ዓይኖች ምን የቀረ ነገር አለና። በሁሉም ዘርፍ ጥላ ከለላ ተሠርቷል። ትግርይ ላይ የመንፈስ ልቅና ከሙሉ አገልግሎት ጋር፤ በመላ ኢትዮጵያ የሚጋዘው ንበረት ደግሞ ሌላው የዲታነት መሰላል …

እናቱ ወ/ሮዋ  ምንም ማንም ሳይደርስባችሁ የተረገጋውን የ26 ዓመት የጫጉላ ጊዜ እዬኮመኮማችሁ ነው። ልጆቻችሁን በሰላም እያስተማራችሁ፤ ውጪ እየላካችሁ፤ እዬዳራችሁ – እዬኳላችሁ የልጅ ልጅ እያያችሁ … ውብ የመዝናኛ ወቅት ላይ ናችሁ። በሁሉም የሙያ ዘርፍ ብቁ ልጆችን ትግራይ አፍርታለች። በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ከመጨረሳው የሃብት ጣሪያ የእናንተ ዘሮች ናቸው። ነጭ ለባሾች። ዘማናዮች፤ ስልጡኖች … ይደክማል …

የዕዳ ቋት

ለታላቋ ትግራይ ህልም የኢትዮጵያ ልጅ ሱማሌ ሄዶ ይሰዋል። በሌላ በኩል ያልተገባ ቅራኔ ለትውልድ በዕዳ ተቀማጭ ሆኗል። ይህ ደግሞ ዘለግ ያለው የዕዳ ቋት ነው። በማናቸውም አህጉራዊ ዓለምአቀፋዊ የሥራ ዕድሎች ሁሉ ቤተ – ተጋሩ ተኮፍሶበታል። ኢትዮጵያማ ምን አጥንቷ ቀርቶ ለአንድ ሳምንት የሚሆን እንኳን ጥሪት አልቦሽ ናት። እናማ እነ ናዚ ፋሽቶች … እፈሩ …. ልጅ አያወጣም። ቁሞ፤ ደረት ነፍቶ የሚያናግር አንድም የሰብዕ ተፈጥሮ የለም። ይህ ደግሞ ዘር አይበቅልም። መሬቱስ ያው  ጠፍ ነው፤ ደግሞ የአሁኑ ግፍ መንታ ወላዱን ማህጸኑን ጠፍ እንዳያደርገው፤ ወደ ራሳችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁን ውቀሱ … ድንጋይ ተሸክማችሁ ጎንደርን ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያን ይቅርታ ብትለምኑ እንኳን እግዜሩ የሚፈቅድላችሁ ከሆነ …

ይከወን መሰል ስለ እኒህ የተጋሩ ወ/ሮ መቼስ ሲሄዱ ማደር ነው … የግፉ ሸክም … የመስቃው ራዲዮ … ሲደመጥ …

… እናንተ በልዩ ጥበቃ ሥር ሆናችሁ 26 ዓመት ሙሉ የልባችሁን አድርሳችኋል። ሰርጉ – ልደቱ – የትምህርት ዕድሉ – ግንባታው – ታዋቂው ሰው/ ተፈላጊው ፍጡር መሆኑን – ሹመቱን  – የዓመቱ ምርጥነት ሽልማቱን – ጥሪቱ ምን የስለት/ ብርቅዬ ልጆችአይደላችሁ። ሌላው ደግሞ እዬሞተም – እዬተገደለም በጉልበቱ ተንበርክኮ ስለ እናንተ ብልጽግና ፍሰሃና ሐሤት ይደክማል። ይማስናል። ዛሬ ጋብቻው፤ አበልጅነቱ እኮ ጡፏል ከእናንተው ጋር። ልብሱ … ቁንዳላው ያው የእናንተ ጠረን መሆኑ እራሱ ይለፍ ያሰጣል። እዬን እኮ ነው ዲያቆናት ሥልጣነ ክህነትን አንዘግዝገው ጥለው ካድሬ ለዛውም የፋሽስት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሲሆኑ … ተዋህዶን አጠፋለሁ ብሎ ከተነሳ አራዊት ጋር በሃሳብ አብረው መጪ ሲሉ …

እስቲ አማራ በተባለው ክልል ማን እንደሚመራው ከልባችሁ ሆናችሁ አስተውሉት፤ ከንባታው፤ ሃድያው፤ ትግሬው፤ ኤርትራዊው ጉራጌው፤ ወላይታው ነው … በትግራይስ? መልስ አላችሁን? ትግሬ ያልሆነ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የጎሳ ፓርቲ  አባል ይሆናል? ኢትዮጵያ ላይስ መከላከያው፤ ደህነነቱ፤ ፖሊሱ፤ አዬር ሃይሉ፤ አዬር መንገዱ፤ ኢኮኖሚው፤ ኢፈርቱ ምን ያልተወረረ ነገር አለ? ቄራ ሳይቀር እስቲ …. እፈሩ …. ለነገሩ ይሉኝታ የሚባል አልሠራላችሁም …

  • ዶር. ተክለብርሃናን አብርሃ በአዲግራት ዩንቨርስቲ መምህር ናቸው። እንደ ዶሩ. ገለጻ በአዲግራት ዩንቨርስቲ 31 ሃኪሞች እና 6 የስፔሻሊስት እንዲሁም ተጨማሪ ባለሙያዎችን አክሎ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት በነጻ እንደሚሰጥ ገልጠዋል። በዩቨርስቲዎች የሚሰጠው ክህምና በምርጥ ሃኪሞች የተደገፈ ሲሆን፤ በሽተኞችም በአገልግሎቱ እንደረኩ ገልጸዋል። ዩንቨርሲቲው ከዚህ በተጨማሪ ምርጥ ጠበቃ አቁሞ የህግ አገልግሎት ለማያገኘው ወገኑ የህግ ድጋፍ በነጻ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልፆልል። ዶር ዘይድ ነጋሽ የዩንቨርስቲው አስተዳዳሪ አንደገለጹትም ዩንቨርስቲው በማናቸው ሴክተሮች የተሟላ እግዛና ድጋፍ በማደረግ ላይ እንደሆኑም አክለው አብራርተዋል። ዜናው በ25.11.2017 በነበረው የኢቢኤስ የቴሌቪዥን ስርጭት። /#EBC የአዲግራት ዩንቨርስቲ በሚሰጠው ነፃ የህግና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን …. 2.ደቂቃ ከ2. ሰከንድ /

 

ግፍ የማይፈራ „ሰው“ ህሊና አልተሠራለትም!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

 

ህወሓት ከ4ቱ “ማፍያዎች” በኋላ:- ሰጋትና ዕድል (በአስፋው ገዳሙ)

​ህወሓት ከ4ቱ “ማፍያዎች” በኋላ:- ሰጋትና ዕድል (በአስፋው ገዳሙ)

መግቢያ
ህወሓትና የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ከሊቃነ መናብርቶቻቸው ሞት በኋላ፡ የኮሚኒስትዋ ቻይና ታሪክ በሃገራችን ይደገም ይሆን? 

የሊቀ መንበር ማኦ ዜዶንግ ሶስተኛዋ ባለቤት ጂያንግ ኲንግ (Jiang Qing) ከ1965 አ.ም.ፈ በፊት ከመካከለኛ እርከን የዘለለ ታዋቂነት አልነበራትም፡፡ የኋላ ኋላ ግን፣ ነብሰበላው የቻይና አብዮት (Cultural Revolution 1966-1976) ከመሩትና ‹‹አራቱ ማፍያዎች (Gang of Four)›› በመባል ከሚታወቁት ወግ አጥባቂ ኮምኒስቶች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡ ዋና ግባቸው የሊቀ መንበር ማኦ ‹‹ራዕዮችን›› ማስቀጠልና እንዳለ መተግበር ነበር፡፡

እመቤት ጂያንግ ከ Wang Hongwen፣ Zhang Chunqiao፣ Yao Wenyuan ጋራ በመሆን እና በሊቀ መንበር ማኦ ድጋፋ ለዘብተኛ በሚባሉትና በ”Liu Shaoqi” እና Deng Xiaoping የሚመሩትን ቁም ስቅላቸውን ያሳዩዋቸው ነበር፡፡ ቀዮቹ ጥበቃዎች (Red Guards) የሚባሉት የወጣቶች ቡድን፣ የሚድያ፣ የኮምኒስት ፓርቲ ረቂቅ ሐሳብና ትምህርት የሚሳሰሉትን ትካላት በመቆጣጠርም ኮምኒስት ፓርቲውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውት ነበር ማለት ይቻላል፡፡

‹‹አራቱ ማፍያዎች›› ሊቀ-መንበር ማኦ ከሞተ በኋላ በመስከረም 9፣ 1976 ዓ.ም ያልተሳካ መፈንቅለ መንግስት በማካሄዳቸው የባላንጣዎቻቸው ሰለባ መሆን ጀመሩ፡፡ Hua Guofeng ‹‹አራቱን ማፍያዎች›› በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ለአራት ዓመታት በቁጥጥር ስር ውለው ከቆዩ በኋላም ከ1980 – 1981 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እመቤት ጂያንግና ዣንግ በሞት ፍርድ ሲቀጡ (በኋላ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ተቀይሮላቸዋል)፣ ዋንግ በእድሜ ልክ፣ ያኦ ደግሞ በ20 ዓመት እስራት ተቀጥቷል፡፡

እመቤት ጂያንግ በፍርድ ሂደቱ ወቅት በተናገረችውና ‹‹የሊቀ መንበር ማኦ ውሻ ነበርኩ፤ እንድነክስለት የሚፈልገኝን ሁሉ ነክሸለታለሁ (I was Chairman Mao’s dog – I bit who he wanted me to bite.)›› በሚለው ኑዛዜዋን ትታወቃለች፡፡ ‹‹አራቱ ማፍያዎች›› ከታሰሩ በኋላ፣ ኋ ኩፈንግ ለደንግ ዢያኦፒንግ ወደ ፖለቲካዊ አመራር መልሶታል፡፡ በመሆኑም ደንግ፣ ሊቀ መንበር ማኦ ከመሞቱ በፊት ጀምሮ ሲያቀነቅናቸው የነበሩት ለውጦችን ለመተግበር እድል አገኘ፡፡ ደንግ የእርሻና የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችን አሻሽሏል፤ የሕዝብ ብዛት ለመቀነስም ለአንድ ቤተሰብ አንድ ልጅ ፖሊሲ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ ‹‹ድመት አይጦችን እስከ ያዘች ድረስ ጥቁር ትሁን ነጭ አይገደኝም›› በሚለው አባባሉ የሚታወቀው ደንግ ወገ-አጥባቂ ኮሚኒስቶችን ቀስበቀስ በማስወገድ የቻይና የልማት ግስጋሴ ማንቀሳቀስ የቻለ የተግባር ሰው ነበር፡፡

ወደ ሃገራችን ስንመለስ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር በ2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ወሬው ሁሉ ‹‹ራእይ መለስ›› ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳይቀር ዓላማዬ ‹‹የመለስ ሌጋሲ ማስቀጠል ነው›› ብለው እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እጅግ ወግ-አጥባቂዎቹ ግን ከአራት የማይበልጡ የህወሓት ባለስልጣናት ናቸው፡፡ የአቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ሶስቱ በህወሓት ውስጥ እየተካሄደ በሚገኘው መራራ ሂስና ግለ ሂስ ሰለባ የሆኑት የትግራይ ክልል ፕረዚደንት አቶ አባይ ወልዱና  ምክትላቸው አቶ በየነ በክሩ ናቸው፡፡

ኣይተ አባይ ወልዱ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ በየነ በክሩ
ወይዘሮ አዜብ፣ ሂሱን መቋቋም አቅቷቸው መድርክ ረግጠው መውጣታቸውን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ይቅርታ ጠይቀው ወደ ግምገማው ቢመለሱም ከስራ አስፈፃሚና ከማእከላይ ኮምቴ አባልነታቸው ታግደዋል፡፡ የአራተኛው እጣ ፈንታ ግን እስካሁን ድረስ በውል አልታወቀም፡፡ ነገር ግን፣ የመከላከያ የበላይ ሃላፊው ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ አንዳንዶቹ ድግሞ ከሶስት ዓመታት በፊት ክፉኛ ተገምግመው ከማእከላይ ኮምቴ አባልነታቸው የተባረሩት አቶ ቴድሮስ ሐጎስም ‹‹የመለስ ራእይ›› አቀንቃኝና የወይዘሮ አዜብ ደጋፊ እንደነበሩ ይናገራሉ፡፡

ለመሆኑ ‹‹ከአራቱ ማፍያዎች›› ከስልጣን ከተወገዱ (ዝቅ እንዲሉ ከተደረጉ) በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉት ስጋቶችና መልካም ዕድሎች ምንድን ናቸው? 

ስጋት ፦ የተለመደው አዙሪት ይቀጥል ይሆን? 

በህወሓት ታሪክ የስልጣን ሽኩቻ እንጂ የአስተሳሰብ ለውጥ ተከስቶ አያውቅም፡፡ አንዱ ቡድን ሌላኛውን በማሸነፍና ከስልጣን በማባረር ነው የሚጠናቀቀው፡፡ ለዚህም የ1967፣ የ1969፣ የ1977 ና የ1993 ዓ.ም የድርጅቱ ህውከቶች (ሕንፍሽፍሽ) በዋቢነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሁሉም ህውከቶች የተፈቱት በሃይልና አሸናፊው ተሸናፊውን በመቅጣት ወይም ከድርጅቱ በማባረር ነበር፡፡ በመሆኑም የአሁኑም እንደቀድሞዎቹ በተመሳሳይ መልኩ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡

የአሁኑ ችግር አንዱ ቡድን ሌላኛውን በማባረሩ ብቻ የሚፈታ አይደለም፡፡ የችግሮቹ ምንጭ አጥንቶ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያሻል፡፡ ይህ ከሆነም ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ላይመለሱ ይችላሉ፡፡ ካልተመለሱ የህዝቡ ጥያቄ ይቀጥላል፡፡ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እየተቀጣጠለ የመጣው የሀገራችን ቀውስም እንዲሁ ይቀጥላል፡፡

መልካም ዕድል፦ የትግራዩ ደንግ ዢያኦፒንግ ማን ይሆን? ዶክተር ደብረፅዮን ወይስ ጌታቸው አሰፋ? 

አሁን ከስልጣን የተወገዱት ሰዎች በሁሉም መለክያዎች የውድቀት ተምሳሌት ናቸው፡፡ ብዙዎች ‘የሚናገሩትም ሆነ የሚሰሩት አያውቁም’ ይሏቸዋል፡፡ ‹‹የመለስ ራእይ›› ማስቀጠል ከሚለው በስተቀር ሌላ ወሬ አልነበራቸውም፡፡ አቶ አባይ ወልዱ በቀድሞ ጀነራሎች (አበበ ተክለሃይማኖትና ፃድቃን ገብረተንሳይ) ላይ የሰነዘሩት ‹‹መለስ የሌለ መሆኑን አይተው የተዳከምን መስሏቸው ሊያጠቁን ያስባሉ›› የሚለው ወቀሳቸው መራራ ትችት ቀርቦበታል፡፡

ዶክተር ደብረፅዮን በበኩላቸው “እንኳን እነዚህ ታጋዮች ማንም ኢትዮጵያዊ በሀገሩ የመናገርና የመፃፍ መብት አለው” የሚል አስተያየት ነበር የሰጡት፡፡ በሀገር ደረጃ የተከሰተው ቀውስ መንስኤም የተሻለ ግንዛቤ አላቸው፡፡ በባህሪያቸው የተለየ ሓሳብና ምክኒያታዊ የሆነ ትችት የመቀበል ችግርም የለባቸውም፡፡ በመሆኑም ከሌሎቹን ሁሉ በተሻለ አዲሱን ትውልድ የማቀፍ አዝማምያ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ አሁን እያሸነፈ ያለው ቡድን ከሳቸው ጋራ ተመሳሳይ አቋም ያለው ስለሆነ በተነፃፃሪ የተሻለ መፍትሔ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም በድርጅቱ ውስጥ የአስተሳሰብ (የእይታ) እና የፖሊሲ ለውጥ ሊያስተዋውቁም ይችላሉ፡፡

ማጠቃለያ
በአሁኑ ወቅት ሃገራችን በአደገኛ አጣብቅኝ ውስጥ ትገኛለች፡፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነን! የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ቀውሶች ይቀረፋሉ ሲባል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ ነው፡፡ በመሆኑም የተለየ እይታና አፈፃፀም ያለው አመራር ያስፈልጋል፡፡ አመራሩ የለውጥ እንቅፋት የሆኑትን ገሸሽ በማድረግ ለውጡን ተቀብሎ ለሃገራችን በሚጠቅም መልኩ ማስኬድ የሚችል መሆን አለበት፡፡ ከልሆነ ግን፣ በሃገራችን የእርሰ-በእርስ ጦርነት ጭምር ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም የሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ቀውሶች ይበልጥ ስር እንዲሰዱ ሊያደርግ ይችላል፡፡

***

By Asfaw  Gedamu 

ሩዋንዳ ስደተኞችን ከእስራኤል እንዳትቀበል ጥሪ ቀረበላት

እአአ 2014 በእስራኤል የሚኖሩ ስደተኞች በሀገሪቱ ውስጥ የጥገኝነት መብት እንዲሰጣቸው የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅትImage copyrightJACK GUEZ
አጭር የምስል መግለጫእአአ 2014 በእስራኤል የሚኖሩ ስደተኞች በሀገሪቱ ውስጥ የጥገኝነት መብት እንዲሰጣቸው የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት

መቀመጫቸውን እስራኤል ያደረጉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ሩዋንዳ ከእስራኤል የሚባረሩ ስደተኞችን እንዳትቀበል ለፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ግልጽ ደብዳቤ ጻፉ።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በእስራኤል የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማዘዋወር የጀመሩትን ድርድር ከፍፃሜ ለማድረስ በነገው ዕለት ተገናኝተው ይመክራሉ።

እስራኤል ከ35 ሺ በላይ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ልታዘዋውር ነው

የእስራኤል ባለስልጣናት ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ከ35ሺ በላይ የሚሆኑ ተቀማጭነታቸውን እስራኤል ያደረጉ የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንደሚዘዋወሩ ፍቃደኛ ካልሆኑ ደግሞ እሥራት እንደሚጠብቃቸው ገልጸው ነበር።

በሌላ በኩል የሩዋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሉዊስ ሙሺኪዋቦ ከኒው ታይምስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሩዋንዳ የምትቀበላቸው ስደተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ወደ ሩዋንዳ መምጣት የሚፈልጉትን ብቻ ነው ብለዋል።

መቀመጫቸውን እስራኤል ያደረጉ ሰባት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ይህን የእስራኤል አካሄድ ክፉኛ ኮንነዋል። ተቋማቱ ለሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ማብራሪያ እንዲሰጡዋቸው በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ጠይቀዋል።

“የተከበሩ የሩዋንዳ ሪፓበሊክ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ፤ ከእርሶና ከሩዋንዳ ህዝብ አስቸኳይ ትብብር እንሻለን። እስራእል እና ሩዋንዳ መልካም ግንኙነት ቢኖራቸውም፤ ግንኙነታቸው የአፍሪካ ስደተኞችን ሕይወት ለሸቀጥ ማቅረብን ሊጨምር አይገባም” ብለዋል የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማቱ ለካጋሜ በጻፉት ደብዳቤ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ ”ሩዋንዳ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከእስራኤል ለመቀበል ተስማምታለች። ስደተኞቹ ተገደው ይወጣሉ። ወደ ሩዋንዳ ለመሄድ ካልተስማሙ ደግሞ የሚጠብቃቸው እሥር ብቻ ነው” ብለዋል።

“እንዲህ ያለ የሰዎችን ነፃነት የሚጋፋ ስምምነት እንደማያጸድቁ ከፍተኛ እምነት አለን። አፍሪካውያን ስደተኞች በዚህ መልክ እንዲሸጡ እንደማይስማሙም ተስፋ አለን። ከፍቃዳቸው ውጪ የሚባረሩትን ስደተኞች እንደማትቀበሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ያሳውቁልን” ይላል ደብዳቤው።

“ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያለዎትን መልካም ግንኙነት ተጠቅመው እስራኤል የስደተኞት አገር መሆኗን እንዲያሳውቁልንና የኤርትራ እና የሱዳን ስደተኞችን ተቀብላ ማስተናገድ እንዳለባት ይንገሩልን” ሲሉ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች በደብዳቤያቸው ጠይቀዋል።

እአአ 2014 በእስራኤል የሚኖሩ ስደተኞች በሀገሪቱ ውስጥ የጥገኝነት መብት እንዲሰጣቸው የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅትImage copyrightGALI TIBBON
አጭር የምስል መግለጫእአአ 2014 በእስራኤል የሚኖሩ ስደተኞች በሀገሪቱ ውስጥ የጥገኝነት መብት እንዲሰጣቸው የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት

የጋራ ደብዳቤ የፃፉት የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የሚከተሉት ናቸው፦

  • በእስራኤል የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እርዳታ ሰጪ ተቋም (ኤ.ኤስ.ኤስ.ኤፍ)
  • በእስራኤል የሰብዓዊ መብት ተሟጓች የሕክምና ባለሙያዎች
  • መረጃ ለስደተኞች እና ተፈናቃዮች
  • በእስራኤል የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ቢሮ
  • በእስራኤል የዜጎች ሰብዓዊ መብት ማህበር
  • ካቭ ላኦ ኦቭ – ሰራተኞች መረጃና መስመር
  • በእስራኤል የኤ.ች.አይ.ኤስ ቢሮ

የእስራኤል መዲና በሆነችው ቴልአቪቭ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ የህዝብ መረጃና ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሻሮን ሐሬል ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ ሃገር የማዛወሩ ጉዳይ ለኮሚሽኑ አሳሳቢ ሆኖዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ሻሮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ “ከስደተኞቹ መካከል ብዙ ሴቶች እና ህጻናት መኖራቸው ችግሩን የተወሳሰበ ያደርገዋል። ከዚህ ቀደም በነበረን ልምድ ወደ ሶስተኛ ሀገር የሚዘዋወሩ ስደተኞች የሥራ ፍቃድ ማግኘት አይችሉም፤ የደህንንት ስሜት ስለማይሰማቸው ሜደትራንያን ባህርን አቋርጠው ለሌላ ስደት ይነሳሉ” ሲሉ ያስረዳሉ።

ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ?

ጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎችImage copyrightABEBAW AYALEW
አጭር የምስል መግለጫጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎች

ኢትዮጵያ ከሶስት ሺ አመታት የሚሻገር የስነ ጥበብ ታሪክ እንዳላት አጥኝዎች ያወሳሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና ከፍ ያለ ሚና እንደተጫወተ የሚመሰክሩ በየአብያተ ክርስትያናቱና በየገዳማቱ ግድግዳዎች ላይ ፤ በኃይማኖታዊ ድርሳናት ውስጥ እንዲሁም በእንጨት ላይ የተሰሩ በርካታ ስዕሎች ለዘመን መደራረብ እጅ ሳይሰጡ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ትምህርትቤት የስነ ጥበብ ታሪክ መምህርና ተመራማሪው አበባው አያሌው ‘ኧ ግሊምስ ኦፍ ኧ ስሪ ሚሊኒያ ኦፍ ኢትዮፒያን አርት’ በተሰኘ ፅሁፋቸው እንደሚያስረዱት በሶስተኛው እና በአራተኛው ክፍለ ዘመን መባቻ አካባቢ የቅድመ ክርስትና ስነ ጥበባዊ ስኬት ተመዝግቦ ነበር።

በወቅቱ የአክሱም ስርወ መንግስት በአገር ውስጥና ከሌሎች የውጭ አገራትም ጋር የሚደረጉ የንግድ እንቅስቃሴዎች እጅጉን ስኬታማ መሆኑ በተለይም ለኪነ ሕንፃና ለቅርፃ ቅርፅ ባለሞያዎች ከፍተኛ ድጋፍ ችሮታል።

በ4ኛው ምዕተዘመን ክርስትና የአክሱም መንግስታዊ ኃይማኖት ሊሆን ከበቃ በኋላ ግን ለሙታን መታሰቢያ የሚሆኑ ምስለ-ቅርፆችን እና ግዙፍ ሃውልቶችን ማቆም አንድም ከእምነቱ አስተምህሮ ጋር የሚፃረር ሆኖ በመታየቱ፤ በተጨማሪም የአረማዊ ዘመን ልማድ ተደርጎ በመቆጠሩ የቅርፃ ቅርፅ ጥበብ እየከሰመ ሲመጣ በፋንታው ክርስቲያናዊ ስነ-ስዕል አብቧል።

ነገር ግን በአክሱም ዘመን ከተሰሩት ክርስትያናዊ ስዕሎች ብዙዎቹ በተደጋጋሚ የአብያተ ክርስትያናትና የገዳማት እድሳት ምክንያት ጠፍተዋል።

ከቅድመ ክርስትያናዊ የጥበብ ስራዎች መካከል እስካሁን ያለው ትክክለኛነቱ የተረጋገጠው ብቸኛ ስዕል የአቡነ ገሪማ የወንጌሎች የድርሳን ውስጥ ምስል ነው።

ጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎችImage copyrightABEBAW AYALEW
አጭር የምስል መግለጫጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎች

(እ.ኤ.አ ከ1150 እስከ 1270)የነበረው የዛግዌ ስርወ መንግስት በስነ ጥበብ፣ በኪነ ሕንፃ እንዲሁም በስነ ፅሑፍ የላቀ ደረጃ ላይ መድረሱን የታሪክ ሊቃውንት እንዲሁም የተለያዩ ድርሳናት የሚመሰክሩ ሲሆን፤ ክርስትያናዊ ስዕል አብሮ በልፅጎ እንደነበርም ከመውደም የተራረፉ የግድግዳ ላይ ስዕሎች እንደሚመሰክሩ የአበባው ፅሁፍ ያሳያል።

በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ይበልጡኑ እየተስፋፋ በመጣበት ከ14ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ የቁም ጽሕፈት፣ ክርስትያናዊ ስነ ጽሑፍ እንዲሁም ስነ ስዕል አብረው ዳብረዋል።

የኢትዮጵያ ስነ ጥበባዊ ትውፊት ባልተቋረጠ ቅብብሎሽ ከዘመን ዘመን ለመቀጠሉ አንደኛው ምክንያት በየጊዜው የሚነሱትን ፈተናዎች ተቋቁማ ኢትዮጵያ እንደአገር መቀጠል መቻሏ ነው ሲሉ ፖላንዳዊው የስነ ጥበብ ታሪክ እና የስነ ስብ ተመራማሪ ስታኒስላቭ ኮይናትስኪ ‘ኢትዮፒያን አይከንስ’ በተባለው መጽሐፋቸው ያትታሉ።

ምንም እንኳ ከቀረው ዓለም ክርስትያናዊ ስነ ስዕል ጋር የይዘትና የቅርፅ ተመሳሳይነትን መያዙ ባይቀርም፤ የኢትዮጵያ ክርስትያናዊ ስነ ስዕል የራሱ ልዩ መገለጫዎችም አሉት።

ኮይናትስኪ በየጊዜው ከምዕራባዊውም ከምስራቃዊውም ዓለም ጋር ያዳበረቻቸው የቻለ ግንኙነት አሻራውን የቤተ ክርስቲያን ስነ ስዕል ላይ ማሳረፉን ይጠቅሳሉ።

ለዚህም በምሳሌነት የግሪክ፣ የኮፕት (የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን)፣ የኑቢያ እንዲሁም የአርመን ዱካዎች መስተዋላቸውን በአስረጅነት ይጠቅሳሉ።

ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ እውነታ እና በከፊልም በእርሱ ላይ ተመስርቶ ለምዕተ ዓመታት ያህል ከቅርብ የአፍሪካ አገራት እንኳ ተነጥላ መቆየቷ በመሰረታዊነት የራሷ የሆነ ልዩ ቤተ ክርስቲያናዊ የአሳሳል ጥበብን ታዳብር ዘንድ አስችሏታል።

ለምሳሌም በምዕራብ፣በመካከለኛውና በደቡባዊ አፍሪካ የስነ ቅርጽ ጥበብ በዋናነት ተመራጭ የስነ ጥበብ ዘርፍ ሲሆን የኢትዮጵያ ክርስትያናዊ ስነ ጥበብ ግን ዐብይ መገለጫው ስነ ስዕል ነው።

ጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎችImage copyrightABEBAW AYALEW
አጭር የምስል መግለጫጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎች

ቅዱስ ቀለማት

ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስነ ስዕል ልዩ መልኮች አንደኛው አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቀለማት ግልጋሎት ላይ መዋላቸው ነው።

ከጥቁርና ነጭ ቀለማት በተጨማሪ ሰማያዊ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ብቻ ለስዕል ስራ ይውላሉ።

የአበባው ጽሑፍ እንደሚያስረዳው እነዚህ ቀለማት እንደቅዱስና መለኮታዊ ቀለማት ይቆጠራሉ።

እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ቀለማት በየአካባቢው ከሚገኙ ዕፆች ተጨምቀው ይሰሩ የነበረ ሲሆን ሰማያዊ ደግሞ ከውጭ አገራት እንዲመጣ ይደረግ ነበር።

ጥልቀት አልባነት እና የጀርባ ከባቢ ያለመኖር

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስነ ስዕል ውስጥ ጥልቀት፣ ርቀትና ቅርበት እንዲሁም የጀርባ ከባቢን የሚያሳይ ገጽታ ማየት ያልተለመደ ሲሆን ስዕሎቹም ባለ ሁለት አውታር ብቻ ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን “ቅርጽን ሳይሆን ኃሳብን” ነው የሚስሉት ሲሉ በሌላኛው ‘ሜጀር ቲምስ ኢን ኢትዮፒያን ፔይንቲንግ ‘ መጽሐፋቸው የሚያስረዱት ኮይናትስኪ እንዲህ የሆነበትን ምክንያት ሲተነትኑ ለግለሰባዊ ስብዕና በአውሮፓዊያን የሚቸረውን ያህል አፅንዖት ስለማይሰጥ ነው ይላሉ።

ደብረማርቆስ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎችImage copyrightABEBAW AYALEW
አጭር የምስል መግለጫደብረማርቆስ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎች

የእይታ ቅብብሎሽ

በኦርቶዶክሳዊው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የስዕል ጥበብ ተመልካቹ ስዕሉን የሚያየውን ያህል ስዕሉም ተመልካቹን ያያል ተብሎ ይታመናል።

ይህም ሁኔታ ስዕሎች ኃይል እንዳላቸው እንዲታሰብ አስችሎታል።

የሌሎች ምስራቃዊ አብያተ ክርስትያናትን ያህል የቅዱሳን ምስሎች አምልኮ ባይኖርም በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ምስሎች ለጸሎት እንደሚያገለግሉ ኮይናትስኪ ይገልፃሉ።

ለቅዱሳን ስዕል የሚሰጥ የገዘፈ ክብር ከሚስተዋልባቸው መንገዶች አንዱ ምስሎቹ የሚቀመጡበት ሁኔታ ነው፤ እንደአብነት ከቅድስት ማርያም ወይንም ከስቅለት ስዕሎችን ጨርቅ የሚደረግ መሆኑን ልብ ማለት ይቻላል።

ደብረማርቆስ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎችImage copyrightABEBAW AYALEW
አጭር የምስል መግለጫደብረማርቆስ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎች

የሰው ፊት አቀማመጥ

የቤተ ክርስቲያን ምስሎች ባለሶስት አውታር ካለመሆናቸውም በላይ እንቅስቃሴ አይኖራቸውም። ብዙ ጊዜ ሰዎች፣ ቅዱሳን እና የመሳሰሉት ሲሳሉ እንቅስቃሴ አልባ ሆነው ነው።

አልፎ አልፎ ብቻ ፈረስ ጋላቢ ቅዱሳን በተወሰነ ድርጊት ውስጥ ሆነው ይታያሉ።

እንቅስቃሴንና አቅጣጫ በዓይን ውርወራ ወይንም የምልከታ አቅጣጫ ብቻ ይመላከታሉ።

የሰው ልጅ ፊት ሶስት ዓይነት ብቻ አቀማመጦች ይኖሩታል።

ቅዱሳን እና ፃድቃን ሙሉ በሙሉ ፊት ለፊት ሆነው ወይንም ሁለት ሶስተኛው ፊታቸው እየታየ ይሳላሉ።

ይህ የሚሆንበት ምክንያት ምስሉ በተመልካቹ ላይ ኃይሉን እንዲፈነጥቅ ከማሰብም በመነሳት ነው።

ኃጥኣን እና እርኩሳን ደግሞ ፊታቸው የጎንዮሽ ወይም አንድ አይናችው ብቻ እንዲታይ ይደረጋል።

ደብረሲና ጎርጎራ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎችImage copyrightABEBAW AYALEW
አጭር የምስል መግለጫደብረሲና ጎርጎራ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎች

ያልታወቁ ሰዓሊያን

በድርሳናት ውስጥ የሚሳሉ ስዕሎች ላይ የሰዓሊያን ስም ሰፍሮ የሚገኝባቸው አጋጣሚዎች አሉ።

ይሁንና ኃይማኖታዊ ስዕሎችን መስራት እንደኃይማኖታዊ ተግባር ስለሚቆጠር የሰዓሊያን ስም እምብዛም አይገኝም።

ብዙ ጊዜም ሰዓሊያን የአብያተ ክርስትያናትን ግድግዳዎች በኃይማኖታዊ ስዕሎች እንዲያስውቡ ስራ ሲሰጣቸው ተግባራቸውን ከመጀመራቸው አስቀድሞ ሱባዔ ገብተው መንፈሳዊ አመራርን ይሽታሉ።

ሕወሓት የቀድሞዋን የአባይ ጸሐዬ ሚስት (ሞንጆሪኖ) ሊቀመንበሩ ሊያደርግ ነው እየተባለ ነው


(ዘ-ሐበሻ) ትናንት የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ አባይ ወልዱን ከስልጣኑ ማስወገዱን የገለጸው ሕወሓት በ እርሳቸው ቦታ የቀድሞዋን የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ)ን ሊቀመንበር ሊያደርግ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች እየገለጹ ነው::

ለመሆኑ ሞንጆሪኖ ማናት? ለምትሉ:

ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ትርፉቶች በሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ጽፏት ነበር:: ተጨማሪ መረጃዎች እስኪመጡ መልካም ንባብ::

የሞንጆሪኖ ለቅሶ…

በሰፈሩት ቁና ሆነና ነገሩ የሕወሓት መሰንጠቅ የሞንጆሪኖን ፍጹማዊ አገዛዝ እንዲያከትም አደረገው:: በ እርግጥ የተስፈማሪያምን ያህል ውግዝ ከማርዮስ አልደረሰባትም:: ከአቶ መለስ ተግሳጽ ውጭ::

አቶ መለስ እንዲህ አላት:-

“ሞንጆሪኖ አዲስ አበባን የለውጥ ማዕበል ውስጥ አስገብተሽ ታስተካክያለሽ ብለን ነበር የላክንሽ:: አንቺ ግን የድርጅቱን አደራ በልተሽ ከጀርባ ስታደራጂ ከረምሽ:: ኸረ ለመሆኑ ምን ጎድሎብሽ ነው? እነስዬን ስታውቂያቸው ቀርተሽ ነው; አብረሽ ድርጅቱ ላይ ገመድ ልታጠልቂ የነበረው?”

ሞንጆሪኖ ተንሰቅስቃ አለቀሰች:: ስጋ ስው አትን ጠርታ ሁለተኛ እንደማይለመዳት ቃል ገባች:: እግሩ ላይ ተደፍታ ይቅርታ ጠየቀች:: ከነተወልደ ጋር እንዲኤት እንደተመሳጠረች ዘከዘከች:: የህቡዕ እንስቃሴው ከስድስት ወር በፊት በአዲሳባ መጀመሩን አስረዳች:: በአዲስ አበባ ያሉት የዞን ሊቀመናብርት ትልቁ ሥራቸው መሆኑን ገለጸች:: ካድሬዎቹ አባዝተው ስለበተኑት ወረቀት ዘከዘከች:: አመናት::

ፊቱን ወደ እሷ አነሳ… ራራላት::

እንደቀድሞ ባሏ አባይ ጸሐዬ የምህረቱ ተቋዳሽ አደረጋት:: የዘመናዊ ዕውቀት ማነስ የፈጠረው ችግር ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ የቀለም ትምህርት እንድትማር ፈረንጅ ሃገር ሰደዳት:: ትምህርቷን አጠናቃ እንደመጣች ጓዟን ጠቅልላ መቀሌ ገባች:: የትግራይን ካቤኔ ተቀላቀለች:: ለአቶ መለስ ያላትን ታማኝነቷን በተግባር አሳየች:: እሱም ካሳውን በቁሙ ተቀበለ:: በዚህ ሳይወሰን በሕወሓት ሁለተኛ ትውልድ ውስጥ እንድትታቀፍ የመጀመሪያው ምርጫ አደረጋት::

(ሞንጆሪኖ ፈትለወርቅ ሆናለች:: የአዲሷ ፈትለ ወጣትነት የድሮዋ ሞንጆሪኖ ነው:: አፍታም ሳይቆይ የሕወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በመቀሌ ተካሄደ:: ፈትለወርቅ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነች::

(የመለስ ትርፉቶች መጽሐፍ ገጽ 56 – 57)

ሕወሃት ሲስቅ ሆነ ሲጣላ አያስብም ከራሱ ሌላ! – ስዩም ተሾመ

ሕወሃት ሲስቅ ሆነ ሲጣላ አያስብም ከራሱ ሌላ! – ስዩም ተሾመ

ሕወሃት እንኳን ተለውጦ ሞቶም ከራሱ የበላይነት ሌላ አያሰብም፣ አያሳስበውም፡፡ #አባይ_ወልዱንከሊቀመንበርነት አወረደ፣ #አዜብ_መስፍንን ከድርጅቱ አገደ፣ #አርከበ ዕቁባይ ወጣ፣ ዶ/ር #ደብረፂዮን መጣ፣ … የአቦይ ስብሃት ቤተሰብ ሰባ፣ አባይ ፀሐዬ ገባ፣ … ወዘተ፣ ማንም ወጣ፥ ማንም መጣ፣ “#የሕወሃት_የበላይነት_ይብቃ!” የሚል አመራር ሊመጣ አይችልም፡፡ ሰሞኑን በሕወሃት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት፣ ዛሬ ደርሶ “እከሌ ተቀጣ፣ እከሌ ደግሞ ወጣ!” የሚሉት ከትጥቅ ትግል ጀምሮ የተለመደ፣ የማይቀየር የሕወሃት ድርጅታዊ ባህላቸው (Organizational Culture) እኮ ነው፡፡ ሕወሃት በውጫዊ ሃይል አስገዳጅነት ካልሆነ በስተቀር በራሱ ተነሳሽነት ለውጥና መሻሻል አምጥቶ አያውቅም፡፡ የተለወጠ መስሎ ቢቀርብ እንኳን የቀድሞውን ዓላማና ግብ ለማሳካት እንጂ አዲስ ራዕይና ተልዕኮ ሰንቆ ሊሆን አይችልም፡፡

ልብ አድርጉ…ሕወሃት ከዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው #በኦሮማራ ጫናና ግፊት ነው፡፡ አባይ እና አዜብ የተመቱት ትምክህተኛና ጠባብ ሃይሎችን ለመምታት በሚደረገው ጥረት አጋዥ ሆነው ባለመገኘታቸው እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ አስሬ ቢቀየር፣ ቢቀያየር “#የሕወሃት_የበላይነት_ይብቃ!” የሚል አመራር ሊመጣ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ የተፈጠረው የኦሮሞና አማራ ህዝብን በመለያየትና በማጋጨት የራሱን የበላይነትን በማስቀጠል ላይ ነው፡፡ ስለዚህ አይደለም በአመራርና በአሰራር ለውጥ፣ ሕወሃት #ሞቶ_ቢነሳ እንኳን ለኦሮሞና አማራ ህዝብ መብትና ተጠቃሚነት መስራት ሆነ ማሠራት አይችልም፡፡ አንዳንዶች ሕወሃት ውስጥ የሚስተዋለው “ለውጥና ሽግሽግ የፖለቲካ ለውጥ ያመጣል” የሚል ተስፋ አላቸው፡፡ ነገር ግን፣ ሕወሃት በህይወት እያለ ሞቶና ተቀብሮ እንኳን የራሱን የበላይነት ከማስቀጠል ያለፈ ሌላ ነገር አያስብም፣ አይሰራም፣ አያሰራም!! #ሕወሃት ሲስቅ ሆነ ሲጠላ #አያስብም ከራሱ ሌላ!!!

ኢት-ኢኮኖሚ: ወያኔ 25 ሽህ ህፃናትን ለጉዲፈቻ ሽጦል!!! የደም ገንዘብ!!! – ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም


እናት አበበች ጎበና፣ ደግሞ ነጋ….ሰው ፍለጋ….ህፃን እንቦቀቅላ!…ህፃን ለጋ….የጉዲፈቻ ቱጃር የደም ዋጋ!!!

(ለቀ.ኃ.ሥ ህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት፣ ለትንሣኤ ብርሃን ህፃናት ማሳደጊያ፣ ለህፃናት አንባና ‹አልወለድም› ደራሲ አቤ ጎበኛ መታሰቤያ ትሁን፡፡) የቀ.ኃ.ሥ ዘመነ መንግሥት የቀኃሥ ህፃናት ማሳደጊያ ድርጅትና የትንሣኤ ብርሃን ህፃናት ማሳደጊያ ድርጅቶች፣የደርግ ህጻናት አምባ ተቆማት ወላጆቻቸው በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያት የተለዮቸውን ህጻናቶችን ተቀብለው በሃገር ውስጥ በማሳደግና በማስተማር ለትልቅ ደረጃ ማድረሳቸው ታሪክ ምስክር ነው፡፡ የዶክተር አበበች ጎበና የህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት በሃገር ውስጥ ብቻ ህፃናት እንዲያድጉ በማድረግ በጥሩ ስነ-ምግባርና መልካም ግብረገብነት አንፀው፣ አስተምረው ለትልቅ ደረጃ በማድረሳቸው ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት በኢትዮጵያ ከ2003/7 እኤአ ለ22 የጉዲፈቻ ንግድ ኤጀንሲዎች ፍቃድ መሰጠቱ በተለይ አሜሪካ ላሉ የህፃናት ንግድ መጦጦፉ ማስረጃ ነው፡፡

‹‹ጉዲፈቻ በኢትዩጵያ የቆየና በህብረተሰቡ ውስጥ የጎለበተ በመልካም እሴት የሚጠቀስ የማህበራዊ ትስስር ማጠናከሪ እንደሆነ ታወቃል፡፡ ከሃገር ውጪም ህጋዊ በሆነ መንገድ ህፃናት በጉዲፈቻ ሲሰጡ ቆይቶል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ ከአፍሪካ ወደ 35 ሽህ ልጆች በጉዲፈቻ መሰጠታቸውንና ከእነዚህም መካከል 25 ሺዎቹ ከኢትጵያ መሆናቸው በህዝብ ተወካች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቆሚ ኮሚቴ የቤተሰብ ህግ እንደገና ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ውይይት ላይ ተጠቁሞል፡፡›› ኅዳር 1/2010ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

• 25,000 ህጻናት ልጆች በአማካኝ ከአንድ ሕፃን 20 ሽህ ዶላር ሽያጭ ቢሆን 500,000,000 ዶላር በ20 ብር ምንዛሪ ተመን በ10,000,000,000 ቢሊዮን ብር ህፃናት ተሸጠዋል፡፡
• 25,000 ህጻናት ልጆች በአማካኝ ከአንድ ሕፃን 30 ሽህ ዶላር ሽያጭ ቢሆን 750,000,000 ዶላር በ25 ብር ምንዛሪ ተመን በ18,750,000,000 ቢሊዮን ብር ህፃናት ተሸጠዋል፡፡
የጉዲፈቻ/ማደጎ ህፃናት ሽያጪ፤የጦር አበጋዞች ከማደጎ ህፃናት ሽያጪ የሚያግበሰብሱት የነፍስ ሽያጪ በተመለከተ ጥናቶች ያካተቱት መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 70 የውጪ ሃገር የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች በሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር Ministry of Women’s Affairs ፍቃድ ሰጪነት ተመዝግበው በመስራት ላይ ናቸው፡፡ በሃገራቶች መኃል የሚከናወነውን የጉዲፈቻ ሥነ-ስርዓት ከሚያቀላጥፉ ድርጅቶች/ ተቆማት መሃክል የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች፣ የግልና የመንግሥት ህፃናት ማሳደጊያ ድርጅቶች፣ ፍርድ ቤት፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የሚመለከታቸው ኢንባሲዎች፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ኢሚግሬሽን አውቶሪቲ፣ የፍትህ ሚኒስትር፣ የፖሊስ ኮሚሽን፣ እና የሃገር ውስጥ የመንግስት ባለስልጣናት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ በሃገራት መኃል የሚከወነውን የጉዲፈቻ ሥነ-ስርዓት ያመቻቻሉ፡፡ በዚህ ጥናት መጥፎ የሰሩ እንዳሉ ሁሉ መልካም የሰሩም እንዳሉ ማወቁ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለምን ህፃናት በማደጎነት ባህር ማዶ እማያውቁበት ሃገር፣ባህል፣ስነልባና ቀውስ ተዳረጉ፣ የማደጎ ድርጅቶች በእውን ንፁህ ሥራ ይሰራሉ የሚለው በጥናት የተረጋገጠ ብዙ መረጃ ስላለ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዳይመስለን፡፡ ለጥናት መረጃ መስጠት ግልፅ አሰራርና ፈሪሃ እግዚአብሄር ያላቸው የጉዲፈቻ ድርጅቶች ትመሰገናላችሁ፡፡ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ መሠረት በሃገሪቱ 150,000 ህፃናቶች የጎዳና ተዳዳሪዎች እንደሆኑና ከዚህም ውስጥ 60,000 የጎዳና ተዳዳሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ጎዳናዎች ላይ እንደሚኖሩ ገልፀዋል፡፡ According to a Ministry of Labor and Social Affairs (MOLSA) report, approximately 150,000 children lived on the streets, and 60,000 of these children lived in the capital
የማእከላዊ ስታቲስቲክስ መረጃ መሠረትም 5.4 ሚሊዩን ህፃናቶች እናትና አባታቸውን በሞት የተለዬቸው እንደሆነና በተለያዩ ምክንያቶች ህፃናቶች በህክምና እጦት በሞት እንደሚቀጠፉና በሆስፒታሎች ውስጥ ተጥለው እንደሚገኙ ተገልጾል፡፡ There were an estimated 5.4 million orphans in the country, according to the report of Central Statistics Authority. Government-run orphanages were overcrowded, and conditions were often unsanitary. Due to severe resource constraints, hospitals and orphanages often overlooked or neglected abandoned infants. Children did not receive adequate health care, and several infants died due to lack of adequate medical attention. There were multiple international press reports that parents received payment from some adoption agencies to relinquish their children for international adoption, and that some agencies concealed the age or health history of children from their adoptive parents. The government was slow to investigate these allegations.
በኢትዩጵያ በጉዲፈቻ የሚሸጡ ልጆች ቁጥር መጨመሩን የአንድሪው ጂኦጊጋን፣ ጥናቶች ያረጋግጣሉ በ2002 እኤአ 262 የነበረ ሲሆን በአምስት አመታት ግዜ ውስጥ አስር እጥፍ ጨምሮ በ2007 እኤአ 2520 ብዛታቸው ደርሶል፡፡ የኢትጵያ የጦር አበጋዞች መንግስት በአማካኝ ከአንድ ሕፃን 20 ሽህ ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን በ2007 እኤአ 50 ሚሊዩን ዶላር ከሽያጩ ገቢ ስብስቦል፡፡ 1990እኤአ 3500 ኢትዮጵያዊያን ህፃናቶች በአሜሪካ አሳዳጊዎች ቤተሰብ ውስጥ በጉዲፈቻነት ተሰጥተው ነበር፣ በ2007 እኤአ ብቻ 1250 ህፃናቶች በአሜሪካ ጉዲፈቻ ሆነዋል፣የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማዕከል ዴሬክተር በዋሽንግተን ሄርሜላ ከበደ አስታውቃለች፡፡ በ2008እኤአ 4,000 ህጻናት ማደጎ እንደሚያገኙ የመንግስት ሹሞች ገምተው ነበር፡፡ የአንድሪው ጂኦጊጋን ጥናት ከድረ-ገፅ ያንቡ፡፡
• በአሜሪካ ዓለም ዓቀፍ የጉዲፈቻ ማደጎ ህጻናት ተቆማት ትልቅ ቢዝነስ ወይም ንግድ ናቸው፣ ብዙዎቹ ዓለም ዓቀፍ የግል ጉዲፈቻ ኤጀንሲ ድርጅቶች በአማካይ 30,000 ዶላር በመክፈል የማደጎ ህፃን ለማግኘትና ተስፋ የሚጣልበት ወላጅ ለመሆን ወረፋ ይጠብቃል፡፡
• አንድሪው ጂኦጊጋን፣ ርሃብ፣ በሽታና ጦርነት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ህፃናት ያለወላጅ አስቀርቶቸዋል፡፡ አስገራሚ አይደለም የዓለም ዓቀፍ የጉዲፈቻ ቢዝነስ እዚህና አሜሪካ ውስጥ ሊዳብርና ሊያብብ የቻለው በተለይ በአሜሪካ ውስጥ የጉዲፈቻ ለማግኘት ወረፋ ሰልፍ አለ፡፡
• አንድሪው ጂኦጊጋን፣ በትንሹ 70 የማደጎ ኤጀንሲዎች የቢዝነስ ማዕከላቸውን በኢትዮጵያ መሥርተዋል፡፡ ግማሾቹ የጉዲፈቻ ድርጅቶች በህግ ያልተመዘገቡ ሲሆኑ ነገር ግን ትንሽ ህግና ደንብ ብቻ ያላቸው ሲሆን ማጭበርበርና ማታለል የተለመደ ድርጊት ነው፡፡ አንዳንድ የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች በንቃት ህፃናትን በመመልመል ሲሳተፉ፣ ሂደቱን ህፃናትን እንደ አዝመራ መሰብሰብ፣ማምረት ይሉታል፡፡
• አንድሪው ጂኦጊጋን፣ በየሣምንቱ 30 ህፃናቶች በጉዲፈቻነት አገራቸውን ለቀው ይሄዳሉ፣ በአዲስ ቤት ‹‹ቤት ለእንቦሳ›› ይባላሉ፣ አዲስ ወላጆችና እርግጠኛ ያልሆነ የወደፊት ህይወት ይጠብቃቸዋል፡፡

“In the United States international adoptions are a big business, where a large number of private international adoption agencies are paid on average $30,000 a time to find a child for hopeful parents.ANDREW GEOGHEGAN: Famine, disease and war have orphaned around five million Ethiopian children. It’s not surprising then that the business of international adoptions is thriving here and Americans in particular are queuing up to adopt a child…ANDREW GEOGHEGAN: At least 70 adoption agencies have set up business in Ethiopia. Almost half are unregistered, but there’s scant regulation anyway and fraud and deception are rife. Some agencies actively recruit children in a process known as harvesting…ANDREW GEOGHEGAN: About 30 Ethiopian children are leaving the country every week, bound for a new home, new parents and an uncertain future.”
• የኃይለማርያም ደሣለኝ ልጆች የኪራይ ቤት ተሠጣቸው፣ቱጃሮች ቤት ገዙላት፣6ት የመንግስት መኪና ተመደበላቸው፣ የደሃ ወላይታ ልጆች በቀን ሥራና በሌሊት ሥራ አካላቸውን እንዲሸጡ ተዳረጉ፡፡
• በኢትዮጵያ በወጣት ፈጅ የአግአዚ ሠራዊት የተገደሉ ህፃናት የፍርድ ቀን መቼ ይሆናል!!!
• ጉዲት ገነት ዘውዴ 9 ሚሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለማሳያዣ ተበድራ ለልጆ ቪላ ቤት ገዛች፡፡
• አዲሱ ለገሠ መንግሥት የሠጠውን መኖሪያ ቤት ወደ ግል አዘዋወረ፣ የግል ሃብቱ አደረገው!!! የስብሃት ነጋ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ብዙ የመንግሥት ቤቶችን ወደ ግል ንብረትነት አዘዋውረዋል፡፡
• የስብሃት ነጋ ልጅ የብዙ ሚሊዩን ብር ጨረታ አሸነፈ!!! ደሃ የትግራዋይ ኮረዶች ቺቺኒያ ሠፈር ሠፈሩ!!
• ህወኃት/ኢህአዴግ ሹማምንት ልጆቻቸውን ከባህር ማዶ ያስተምራሉ፣የደሃ ልጆች ለስደት ተዳርገዋል!!!
• ህወኃት/ኢህአዴግ ጀነራል መኮንኖች፣ ሚንስትሮች፣ አምባሳደሮች ወዘተ በህፃናት ሽያጪ ፎቅ ገነቡ!!!
• አንዳርጋቸው ፅጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ወዘተ አባታቸውን የተነጠቁ ህፃናቶች ህይወት አያሳዝንም!!!
• ከበረሃ ጀምራችሁ ‹‹ማንጁስ›› የህፃናት ጦር ከመለመለ ድርጅት ምን ይጠበቃል!!!
• በወያኔ ዘመን ታዳጊ ህፃናት ሴትና ወንዶች የፆታ ጥቃት ይፈፀምባቸዋል!!! ፍትህ የለም!!!
• የሃገራችንን የእምነትና ባህል እሴት ያዋረዱት ሸህ አል-አሙዲ በሴት እህቶቻችን ላይ ያደረሱት መረን የለቀቀ ሽርሙጥና በፈጣሪ ፍርድ አግኝቶል! ልዑሉ ምስጋና ይገባሃል!!! ለወያኔም የፍርድ ቀን ደርሶል!!!
በኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች የክርስትና፣ የእስልምና፣ የፕሮቴስታንት ወዘተ ተቆማት ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናት ማሳደግና ማስተማር ከተቆማቸው ቢጠበቅም አስተዋፅኦቸው ኢምንት ነው፡፡ የሃይማኖት ተቆማት የበጎ አድራጎት ሥራን መሥራት አልታደሉም፣የራሳቸውን የተንደላቀቀ ኑሮና ንግድ ከመምራት ሌላ አያውቁም፡፡
በቀ.ኃ.ሥና ደርግ ዘመን የነበረን አኩሪ የህጻናት ማሳደጊያ ተቆም አፍርሶ ወያኔ የፈለፈላቸው የግል የጉዲፈቻ የንግድ ድርጅቶች በአዲስ አበባ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ አዳማ፣ ደቡብ ክልል ሶዶ ዙሪያ፣ አፋር አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ወዘተ እንደ አሸን በፈሉ የቢዝነስ/ የንግድ ጉዲፈቻ ድርጅቶች ከ2003/7 ተቆቁመው ከህጻናት ንግድ ሽያጭ ፎቅ ሲገነቡ ይሰተዋላሉ፡፡ የጉዲፈቻ ኤጀንሲ ሰራተኞች፣ጋዜጠኞች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ድርጊቱን ማጋለጥ ከህሊና ፀፀት ያድናችኃል፡፡ የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች ድረ-ገፆች ሁሉም ዝግ መሆናቸው ለምን!!! በአሜሪካ ስላሉ የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች ቱጃር ዶክተሮች፣አዲስ አበባ ውስጥ ፎቅ ገነቡ፡፡ ዲያስፖራው ያለማጋለጥ ዝምታ እስከመቼ ይሆን!!!
በኢትዮጵያ የጉዲፈቻ/ማደጎ ህፃናት ኤጀንሲ የተመዘገቡ-በፊብሪዋሪ 2008እኤአ

No. Name of the Adoption Agencyየማደጎው የድርጅት ስም፣ RegistrationNo. Date ofRegistration Name of theRepresentative Address Countryof Origin
1. ዋይድ ሆሪዞንስ ፎር ቺልድረን ኢንክWide Horizones For Children Inc. 1041 26/03/2003 ዶክተር ጸጋዬ በርሄDr. Tsegaye Berhe 52-89-8909 204181 አሜሪካAmerica
2. አሜሪካ ፎር አፍሪካ አዶፕሽን ኢንክ Americans For African Adoption, Inc. 1106 3/07/2003 ወ/ት ትግስት ከበደW/t Tigist Kebede 09 233007 አሜሪካAmerica
3. አዶፕሽን አድቮኬትስ ኢንተርናሽናልAdoption Advocates International 1104 30/06/2003 አቶ ሳምሶን ተስፋዬAto Samson Tesfaye 09 203390 አሜሪካAmerica
4. ቺልድረንስ ሆም ሶሳይቲ ኦፍ ሜኔሶታChildren’s Home Society of Minnesota 1255 30/10/2003 አቶ አስናቀ አማኑኤልAto Asenake Amanuel 45991302 228770 አሜሪካAmerica
5. ዶቭ አዶፕሽን ኢንተርናሽናል ኢንክDove Adoption International Inc. 1363 27/11/2003 አቶ ስንታየሁ ጌታቸውAto Sentayehu Getachew 09 61933 አሜሪካAmerica
6. ክርስቲን ወርልድ አዶፕሽንChristian World Adoption 2277 16/09/2005 አቶ ዳኜ ገዛህኝAto Dagne Gezahegne 09 86816812-29-99 አሜሪካAmerica
7. ዘ ግላድኔይ ሴንተር ፎር አዶፕሽንThe Gladney Center for Adoption 2439 6/12/2005 አቶ በላይነህ ታፈሰAto Belayneh Tafesse 09 211764 አሜሪካAmerica
8. ኢሊን አዶፕሽን ኢንተርናሽናል ኢንክIllien Adoptions International, Inc. 2538 30/1/2006 አቶ ተመስገን ገብረስላሴAto Temesgen G/Selassie 09 208085 አሜሪካAmerica
9. አዶፕሽን አሶስያሽን ኢንክAdoption Association Inc. 2560 7/2/2006 አቶ ጌታቸው ወረደአብተውAto Getachew Werede Abitew 09 411158 አሜሪካAmerica
10. ዌስት ሳንድ አዶፕሽን ኤንድ ካውንስሊንግWest Sands Adoptions and Counseling 2512 13/01/2006 ዶክተር አለማየሁ ተሰማDr. Alemayehu Tessema 09 40582409 234088 አሜሪካAmerica
11. ቺልድረን ኦፍ አፍሪካ ኢንተርፕራይዝ ዲቢኤሆፕ አዶፕሽን ኤጀንሲChildren of African Enterprises dba Hope Adoption Agency 2630 23/03/2006 አቶ ሽመልስ ደምሴAto Shimeliss Demissie 09 860448 አሜሪካAmerica
12. አሜሪካ ወርልድ አዶፕሽን አሶስያሽንAmerica World Adoption Association 2685 25/05/2006 ሚስተር ራቫን ሃንሎንMr.Ryan hanlon   አሜሪካAmerica
13. ቺልድረንስ ሀውስ ኢንተርናሽናልChildren’s House International 2686 26/05/2006 ወ/ሮ ሃና ኪዳኔ ወ/ማርያምMs. Hanna Kidane W/mariam   አሜሪካAmerica
14. አዶፕሽን አቬኒውስAdoption Avenues 2749 20/06/2006 አቶ አበበ ጉታAto abebe Guta 09 607166 አሜሪካAmerica
15. ኢንተርናሽናል አዶፕሽን ጋይድስ ኢንክInternational Adoption guides Inc.(IAG) 3140 1/07/2006 አቶ ሃይሌ አያልነህAto Haile Ayalneh አሜሪካAmerica
16. ኦል ጎድስ ኢንተርናሽናል ኢንክAll god’s International Inc. 2959 18/12/2006 ወ/ሮ አልማዝ አስረሳህንw/ro Almaz Asresahin 09 397594 አሜሪካAmerica
17. ቤታንያ ክርስቲያን ሰርቪስስBethany Christian Services 3047 28/03/2007 አቶ ሚልኪያስ ካራቶAto Milkiyas Karato አሜሪካAmerica
18. ቺልድረንስ ሃውስ ኢንተርናሽናልChildren’s House International 3055 03/04/2007 አቶ ጸጋዬ ፍስሃAto Tsegaye Fesseha 0911 303338 አሜሪካAmerica
19. ቡንክነር አዶፕሽን ኤንድ ማተርኒቲ ሰርቪስBunckner Adoption & Maternity service Inc. 3193 4/2007 ሚስተር ጆቢር አማኑኤልMr. Jobir Amanuel 0116621051 አሜሪካAmerica
20. ቤተር ፊውቸር አዶፕሽን ስርቪስBetter future Adoption service 3136 4/06/2007 ሚስተር ጆቢር አማኑኤልMr. Jobir Amanuel 0911 427630 አሜሪካAmerica
21. ኢንተርናሽናል አዶፕሽን ኔትInternational Adoption Net 3147 08/06/2007 አቶ አበበ ባዩAto Abebe Bayou 0911 427630 አሜሪካAmerica
22. ሴለብሬት ቺልድረን ኢንተርናሽናል ኢንክCelebrate children International Inc. 3345 Dec. 10/2007 አቶ ደረጀ የሺድንበርAto dereje Yeshidinber   አሜሪካAmerica

Source: http://www.ethiopianembassy.org/PDF/ListofAdoptionAgenciesRegisteredinEthiopia.pdf
Some of orphanages operate in Ethiopia particularly in Sodo Zuria area are -1) Children Cross Connection,2) Moses Children’s Home,3) Kingdom Vision international,4) Foundation for Children‘s Hope,5) HlDOTA for Children’s Hope, 6) BETHZATA Children’s Home Association,7) Special Mission Community Based Development. In the Oromia Regional Government 1) World Vision 2) Matti Orphanage 3) Kid’s Care 4) Hunde 5) Vision 6) Segeda 7) Faya Orphanage. In Adama City Administration 1) Selaam Orphanage 2) KVI (Kingdom Vision International) 3) Kid’s Care 4) Betazata Women’s Association 5) Joseph Children’s Home 6) Orphan, Vulnerable People and Old Women’s Association.’’ source:- http://etd.aau.edu.et/bitstream/TenaganeAlemu.pdf.

ወያኔ በዓመት በአማካይ 1000 ሽህ ህፃናት የሸጠባት አገር!!! በወያኔ ዘመን አልወለድም!…አልወለድም!!…አልወለድም!!!

ህወሀት ጉልቻ እየቀያየረ ነው። (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

የፊት ለውጥ ይዞ ሊመጣ መሆኑ ታውቋል። አዜብ መስፍን ባፋንጉሎ ተብላለች። የኢትዮጵያን ህዝብ ደም የመጠጠው ኢፈርት የተሰኘው ድርጅት የንትርኩ ማጠንጠኛ ይመስላል። እነአዜብና በየነ ምክሩ ከዚሁ ድርጅት ጋር በተያያዘ አይናቸው ደም በለበሰባቸው በእነስብሃት ነጋ ብጫና ቀይ ካርድ ተሰጥቷቸዋል። እነስብሃት ለጊዜው በለስ ቀንቷቸዋል። የመለስ ሌጋሲን ከመለስ ጋር እንዲቀበር የፈለጉት እነስብሃት የሌጋሲውን አቀንቃኞች በጠረባ እያሏቸው ነው። ስብሰባ ሳይጠናቀቅ መግለጫው መቅደሙ ግን ገና ጦርነቱ ያላበቃ መሆኑን ያሳያል።
እነኣዜብ ኢፈርትን ለነስብሃት አስረክበው ቤታቸው ይገባሉ? የመለስ ዜናዊ አምላኪ የሆነው ሳሞራ የኑስ ምን ብሎ ይሆን? ኢፈርትን የተቆጣጠረ ሻምፒዮን ይሆናል። የኢኮኖሚ ጡንቻ የሚሰጠው ኢፈርት ለፖለቲካው የበላይነት የጀርባ አጥንት መሆኑን አቦይ ስብሃት ልቅም አድርገው ያውቁታል። እናም የመለስን ሌጋሲ ከነአስጠባቂዎቹ መንግሎ ለመጣል መንገዱን በኢፈርት ጀምረውታል። በፖለቲካው ቀጥለዋል። እነአዜብ እጃቸውን አጨብጭበው ኢፈርትን ካስረከቡ የመልስን ሌጋሲ ብቻ ታቅፈው ይቀራሉ።
ፈረንጆቹ the bottom line ይላሉ። ዋናው ጉዳይ እንደማለት ነው። እናም ዋናው ጉዳይ የአዜብ መወገድና የስብሃት ማንሰራራት አይደለም። ጉልቻ ቢቀያየር ትርጉም የለውም። ወጥ አያጣፍጥም። ኢትዮጵያን አይቀይርም። ሌሎችንም ቱባ ባለስጣናት በማባረርና በእስር የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በመፍታት ይህቺን የምጥ ጊዜ ለመሻገር ህወሀት ተዘጋጅቷል። ፊት በመቀየር፡ ጉልቻ በመለወጥ ህወሀት የሚድን ከመሰለው ተሳስቷል። ህወሀት ከነግሳንግሱ፡ ከነኮተቱ፡ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ፡ አንድም ትራፊ ሳያስቀር ካልተወገደ በቀር ለውጥ አይኖርም። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚናፍቀው ያንን ነው።Image may contain: 1 person

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ: የሚያስተክዝ ወግ – (በእውቀቱ ስዩም )

ከየረር በር እስከ ቦሌ የሚሄድ ምኒባስ የመሳፈር እድል ያልገጠመው ሰው ስለ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ልተንትን ቢል ማን ይሰማዋል?
እና ትናንት የተሳፈርኩበት ምኒባስ ካፍ እስከ ሰደፍ ሞልቶ ነበር፤ የምኒባሱ ነባር ወንበር የተሳፋሪውን ብዛት ባገናዘበ መልኩ ሽግሽግ ተደርግጎበታል፤
ወደ ሁዋለኛው ወንበር በሚወስደው ቀጭን መተላለፊያ ላይ የሚብረከረክ እግር ያለው አግዳሚ ወንበር ተዘርግቱዋል፤ወያላው ካግዳሚው ወንበርና በበሩ መካከል የተረፈችውን ክፍተት እንኩዋን ለግራችን መዘርጊያ ብሎ አልማራትም፤ ላንድ ሰው መቀመጫ የምትሆን ሙዳየ ምፅዋት የምትመስል ሳጥን አኑሮባታል::

እኔ በበኩሌ ታክሲ ውስጥ የሰው ኪስ ያወለቀ በስርቆት ሊከሰስ አይገባውም ባይ ነኝ፤ ምክንያቱም ፤ እጅህን ከደረትህ ላይ ባነሳህ ቁጥር ሌላ ሰው ኪስ ውስጥ የመግባት እድልህ ሰፊ ነው፤
ባገራችን የወሲብ ትንኮሳ ዋናው መነሻ የስነምግባር እጥረት ሳይሆን የትራንስፖርት እጥረት መሆኑ የገባኝ የዚያን ቀን ነው፤ አልፎ አልፎ በሴት ተሳፋሪዎችና በወንድ ተሳፋሪዎች ማህል ፤የግብረስጋ እንኩዋ ባይሆን የግብረ ወንበር ግንኝነት ያጋጥማል፤ ሳትፈልግ፤ከፊትለፊትህ ካለው ወንበር ሞልቶ የፈሰሰ የሴት ልጅ ገላ ጉልበትህ ላይ Assቀምጠህ ረጅም ምንገድ ልትጉዋዝ ትችላለህ፤
የታክሲው መደበኛ ወንበሮች እንደ ማሽላ ቂጣ ተበጣጥሰዋል ፤ወንበር አገኘሁ ብለህ፤ ተንደርድረህ፤ ባንደኛው የወንበር ቅሪት ላይ ፊጥ ብትልበት አፈንግጦ የወጣ ሚስማር፤ ቂጥህ ላይ ማንም የማያደንቀው ዲምፕል ሊበጅልህ ይችላል፤ እኔ የተቀመጥሁበት የሁዋለኛው ወንበርማ የትየ አዛለችን ታጣፊ አልጋ አስታወሰኝ፤

የዛሬ ምናምን አመት እኔና ጋዜጠኛ ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ፤አስኒ ጋለሪ ግርጌ ፤በዘጠና ብር ቤት ተከራይተን ነበር፤አይ ጊዜ! ዛሬ በዘጠና ብር ቤት ይቅርና የእዝን ኩባያ መከራየት አትችልም፤ በርግጥ ቤቱ መለስተኛ ኮንቴይነር የሚያክል ሆኖ ባለ አንድ ክፍል ነው፤ እኔና ፍቅር “ሳሎኑን አንተ ውሰደው ምኝታ ቤቱን እኔ ልውሰደው ብለን” የምንከፋፈልበት እድል ስላልነበረን ግድግዳ ተከፋፈልን፤ እኔ በምስራቅ በኩል ባለው ግድግዳ ወስጄ የምርቃቴ ቀን የለበስኩትን ሱፍ ሰቀልሁበት፤

ፍቅር ይልቃል ድርሻውን የምራቡን ግድግዳ ወስዶ ”

“የወፍ ስጋ በላሁ ቢጥመኝ መረቁ..” ብሎ የሚጀምር ፤በዳንቴል የተጣፈ የግጥም ጥቅስ ሰቀለ፤(ጥቅሱን ካገር ቤት ይዞት ነው የመጣ)

ቤቲቱን ያከራየን ደላላ “ቤቱ ፈርኒሽድ ነው ” ሲል ምን ለማለት እንደፈልፍገ የገባኝ ቆይቶ ነው፤በቤቱ የምስራቅ ማእዘን ላይ ፤ እግር ያለው ያሸዋ ማጣርያ ወንፊት የሚመስል የረገበ አሮጌ የሽቦ አልጋ ተተክሉዋል፤ ያልጋው እግር በወለሉ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተቀብሮ ከመኖሩ የተነሳ ቅጠል ማቆጥቆጥ ሁሉ ጅምሩዋል፤ እዛ ላይ መተኛት ማለት በቃ ራስን ወፌ ይላ እንደመስቀል ነው ፤ እንዲያውም ፍቅር ይልቃል “ ተኝተህ ሳይህ፤ መቀስ ምት እየመታ ባየር ላይ ባስማት ተንሳፎ የቀረ ተጫዋች ትመስላለህ” ይለኝ ነበር፤አልጋው ላይ አንድ ሳምንት እንደተኛሁበት ቅዠት ይጫወትብኝ ጀመር፤
ሲብስብኝ አንድ ቀን አከራያችንን እትየ አዛለችን ጠርቼ ፤

“እትየ አዙ ! ይቅርታ አርጉልኝና ይሄ አልጋ…”ብየ ሳልጨርስ
“ አልጋ አልከው? አላወቅኸውም እንጂ ቅርስ ላይ ነው ተኝተህ የምታድር ! አያቴም አባቴም ለረጂም ጊዜ ታመው የሞቱት እዚህ አልጋ ላይ ነው”፤አሉኝ
በማግስቱ እኔና ደባሌ ቤቱን ጥለን ጠፋን፤

ወደ ምኒባሱ እንመለስ፤ አንድ ሰው ምኒባስ ውስጥ ካልገባ በቀር የውሃ እጥረት የሚያስከትለውን ያካባቢ ውድመት እንዴት ሊረዳ ይችላል፤
አጠገቤ፤ ሚጢጢ ራስና የትየለለሌ ትከሻ ያለው፤ የተገለበጠ ሚዶ የመሰለ ጎረምሳ ቁጭ ብሎ ነበር፤አጠገቡ ቁጭ ብሎ በከስክስ ጫማው ህዳርን የሚያጥነውን ተሳፋሪ ምን አለው መስላችሁ?
“ጀለሴ! ጫማህን ለፈደራል ፖሊስ ለምን አታከራየውም? ጠረኑኮ ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ይበትናል”

ቦሌ ድልድይ ጋ ስንደርስ፤ እጄን ወደ ሱሪየ የግራ ኪስ ሰድድሁ! የተልባ ማሻው ሚካየል ድረስልኝ! ሁለት መቶ ብር አጭቆ የያዘ ቦርሳየ በነበረበት የለም፤ መጀመርያ ደነገጥሁ፤ አጥብቄም አዘንሁ፤ ወድያው ግን ተፅናናሁ፤ በዚህ ግፍያ ማሃል፤ ግራ ኩላሊቴ በነበረበት ቦታ መገኜቱም ተመስጌን ነው፡
የደረሰብኝን ለወያላውና ተናግሬ የምከፍለው ሁለት ብር እንደሌለኝ ለማስረዳት ሞከርኩ፤ፍንክች አላሉም፡ ከግራ ቀኝ ጠምደው ያዋክቡኝ ጀመር፤ ቢጨንቀኝ ሹፌሩን “የስልክ ቁጥርህን ስጠኝና የሁለት ብር ካርድ ትራንስፈር ላድርግልህ”አልሁት፤
በጭቅጭቃችን ማሃል ሹፌሩ አተኩሮ ፊቴን ሾፈውና፤
“አንተ ገጣሚው ሰውየ ነህ አይደል?”
አለኝ፤
እየተሽኮረመምሁ መሆኔን ገለጥሁ፤’ አንተ ደህና! ከፈለግህ ለዛሬ መዋያ የሚሆን አንድ ሁለት መቶ ብር አበድርሃለሁ” ይለኛል ብየ ስጠብቅ፤
‘ ያን ሁሉ መፃፍ እየቸበቸብህ እንዴት ሁለት ብር መክፈል ያቅትሃል?”ብሎ ጮኸብኝ
“እንደ ነገርሁህ ቦርሳየን ዘርፈውኝ ነው”
“በቃ ለጥቅስ የሚሆን ሁለት መስመር ግጥም ገጥምሀ ስጠንና ሂድ”አለኝ ወያላው፤
ትንሽ አሰብሁና የዛሬ ምናምን አመት ፍቅር ይልቃል ግድግዳ ላይ ያየሁዋትን ጥቅስ በወረቄት ገልብጨ አቀበልሁት፤
የወፍ ስጋ በላሁ ቢጥመኝ መረቁ
መታማት አይቀርም ምን ቢጠነቀቁ፤